ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈልበትን እቃ ወይም አገልግልት የሚሸጥ ማንኛውም የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ ለተጠቃሚው የሚሸጠውን እቃ ወይም አገልግልት ዋጋ ሲገልፅ በዋጋው ላይ 15 በመቶ ተ.እ.ታ አካቶ መግለፅ ወይም ዋጋው ተ.እ.ታ ያላካተተ ከሆነም ይህንኑ ለገዥ በማያሻማ አኳኋን ማሳወቅና ተ.እ.ታ በደረሰኝ የመሰብሰብ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ የእቃው ወይም የአገልግልት ዋጋ ላይ ተ.እ.ታ መካተቱ ሳይገለጽ ወይም ዋጋው ላይ ተ.እ.ታ አልተካተተም ብል በግልጽ ለተጠቃሚው ሳይገለጽ ግብይት የተፈፀመ እንደሆነ የእቃው ወይም የአገልግልቱ ዋጋ ነው ተብል በውለ የተጠቀሰው ገንዘብ ተ.እ.ታ እንዲካተተ የሚቆጠር ዲይናሚክ ልጅስቲክ አቅርቦት የድጋፍ አገልግልት እና አቶ ፈሬሳ ኢድ
No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ዲይናሚክ ልጅስቲክ አቅርቦት የድጋፍ አገልግልት ተጠሪ፡- አቶ ፈሬሳ ኢድ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ከሽያጭ ዋጋ ጋር ተጨማሪ እሴት ታክስ(ተ.እ.ታ) በግልጽ ተለይቶ መገለጽ አለመገለጹ የሚያስከትለዉን ሕጋዊ ዉጤት የሚመለከት ነዉ። አመልካች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረተዉ ክስ አመልካች የሰላዲ ቁጥር 03-853387 ኢት የሆነ አውቶብስ መኪና በቀን 15/11/2009 ዓ/ም በተደረገ የሽያጭ ውል በብር 310‚000.00 ለተጠሪ ሽጦለት ተጠሪ ብር 250‚000.00 በመክፈል መኪናውንና ሉበሬውን ተረክበዋል። ቀሪውን ብር 60‚000.00 እና የተ.አ.ታ ብር 45‚000.00 በድምሩ ብር 106‚500.00 የሚከፍለት እስከ ቀን 25/11/2009 ዓ/ም ድረስ ተጠሪ ያላገባ የሚል ማስረጃ አሟልተዉ አቅርበዉ በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ቀርበው የመኪናው ስመ ሀብት በተጠሪ ስም ሲዞር ነው በሚል ስምምነት የተደረገ ቢሆንም ተጠሪ የበኩላቸዉን ግዳታ አልተወጡም። ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም እንደውለ ለመፈፀም ፈቃደኛ አልሆኑም። ስለሆነም ተጠሪ የከፈለትን ቃብድ ለቀውና ተ.እ.ታ ከፍለው መኪናውንና ሉበሬውን ለአመልካች እንዱያስረክቡ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ በውላችን መሰረት የመኪናውን ባለቤትነት እንዱያዛውርልኝ፤ ከግብር ነፃ ነው የሚል ማስረጃ እንዱያቀርብ ወይም ውክልና ሰጥቶኝ ቀሪውን ክፍያ እንድሰጠው በተደጋጋሚ ብጠይቅም ፍቃደኛ አልሆነም ። በውለ ላይ ተጠሪ ተ.እ.ታ ለመክፈል አልተስማማሁም። ብር 250‚000.00 ስከፍል ተ.እ.ታ አልጠየቀኝም። የውለ አብዛኛው ክፍል የተፈፀመ ስለሆነና ዉለን የሚያስፈርስ ሕጋዊ ምክንያት ስለላለ ውለ ሉፈርስ አይገባም ተብል ክሱ ውድቅ እንዱደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል።
እንዱሁም ተጠሪ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በማቅረብ አመልካች በውለ መሰረት ግዳታውን ለመወጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ በውለ መሰረት ከግብር እዲ ነፃ ማስረጃ እና ያላገባ የሚል ማስረጃ ይዞ በመቅረብ የሸጠዉን መኪና በሚመለከተው አካል ፉት ቀርቦ ስመ ሀብቱን በተጠሪ ስም እንዱያዛወር ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች ለተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ በሰጠዉ መልስ ከውለ ቀነ ገደብ በፉት መንገድና ትራንስፖርት ቀርበን የውል ፍርም ሞልተን እኔ ፈርሜ ተጠሪ በፍርሙ ላይ ሳይፈርሙ ስለቀረ ውለ ሳይፈፀም ቀርቷል። አመልካች እንደ ውለ ለመፈፀም ፈቃደኛ ሆኖ ለተጠሪ ማስጠንቀቂያ ጭምር ሰጥቶ ተጠሪ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ክሳቸው ውድቅ ይደረግልኝ በማለት መልስ ሰጥተዋል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮች ሰምቶ በቀን 25/08/2011 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ግራ ቀኝ በመካከላቸው በቀን 15/11/2009 ዓ/ም የመኪና ሽያጭ ውል ማድረጋቸው አልተካካደም። በአመልካች ክስ ላይ እንደተመለከተው በውለ ላይ ተጠሪ ተ.እ.ታ.ብር 46‚500.00 ለአመልካች ለመክፈል አልተስማሙም። በውለ ላይ ተጠሪ የተስማሙት ቀሪ ብር 60‚000.00 የመኪናው ስመ ሀብት ሲዞርላቸው ለመክፈል ነው። አመልካች ተጠሪ ተ.እ.ታ ጨምሮ ብር 106‚500.00 ሉከፍለ ይገባል በማለት የገለፀው መከራከሪያ ከውለ ውጪ ነው። ስለሆነም በውለ ያልተመለከተዉን ተ.እ.ታ ተጠሪ እንዱከፍለ በመጠየቁ ምክንያት ውለ ሉፈርስ አይገባም። እንዱሁም በወለ ላይ አመልካች ተሽከርካሪው ከእዲና እገዲ ነፃ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ እንዲለበት ስላልተመለከተና የመኪናውም ስመ ሀብት ወደ ተጠሪ ያልተዛወረው በዚህ ምክንያት መሆኑ ስላልተረጋገጠ አመልካች ከግብር እዲ ነፃ ማስረጃ እንዱያቀርቡ የተጠየቀው ተቀባይነት የለውም።
በመሆኑም በሽያጭ ውለ መሰረት አመልካች ያላገባ ማስረጃ አቅርቦ ተጠሪም ቀሪውን ብር 60‚000.00 ከፍለው ግራ ቀኝ ውለን ያስመዝግቡ በማለት ወስኗል።
በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 14/05/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አፅንቷል። አመልካች በቀን 16/11/2012 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጡ ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በቀን 15/12/2009 ዓ/ም በተደረገ የመኪና ሽያጭ ውል ላይ ዋጋዉ ብር 310,000.00 ተብል የተጠቀሰዉ የመኪና መሸጫ ዋጋ (Selling value) ነዉ።ተጠሪ ተ.እ.ታ የመከፈል ግዳታ እንዲለባቸዉ ቀድሞ ተነግሯቸዋል፤እንዱሁም ተጠሪ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ ስለሆኑና ባላቸዉ ሰፉ የንግድ ልምድ ተ.እ.ታ እንደሚከፍለ ያዉቃለ።እንዱሁም ተ.እ.ታ በባህሪው ሸማች ላይ የተጣለ ኃላፉነት በመሆኑ ተጠሪ ከአመልካች ድርጅት ግብይት ሲፈፅም ይህንኑ ታሳቢ ማድረግና ተ.እ.ታ የመክፈል ሕጋዊ ግዳታቸዉን ሉወጡ ይገባል። ዋናው ውል የሚደረገው በመንገድና ትራንስፖርት ባለሥልጣን ፉት በመሆኑ የመኪና ሽያጭ ውል ሲደረግ በመንደር ውል የመኪናው ዋጋ ብቻ ተጠቅሶ ቅድሚያ ክፍያ ይከፈላል።በዚህ መሰረት የሽጭ ዋጋው ታይቶ የተ.እ.ታ ክፍያ መጠኑ ለተጠሪ ሲገለፅ በመንገድ ትራንስፖርት ባለሙያ የተዘጋጀውን ውል ግዳታዬ አይደለም ብለዉ ትተዉ መሄዲቸዉ በስር ፍርድ ቤት በምስክሮች ተረጋግጧል። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ተ.እ.ታ ሉከፍለ አይገባም በማለት መወሰናቸዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታ አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ በተደረገው የመኪና ሽያጭ ዉል ላይ ተ.እ.ታ የመክፈል ኃላፉነት የሻጭ ነው ተብል የመወሰኑ አግባብነት ከተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ አንጻር እንዱመረመር ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 18/03/2013 ዓ/ም የተፃፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ፡አመልካች በውል ስምምነት ላይ የላለን የተ.እ.ታ ክፍያ በተጨማሪነት ሉከፈለኝ ይገባል በማለት ያቀረበዉ ጥያቄ ከስምምነታችን ውጪ አለአግባብ ለመበልጸግ ነዉ። በአዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀፅ 23 መሰረት ተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ ነጋዳ ሽያጭ ፈፅሞ ገንዘብ ከተቀበለ ለተቀበለው ገንዘብ የተ.እ.ታ ደረሰኝ ሉቆርጥ እንደሚገባ ፤ የተቀበለውን ገንዘብ ሰብስቦ ለሚመለከተው የታክስ ባለስልጣን ታክሱን በወቅቱ ገቢ ማድረግና ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባዉ የደነገገ ቢሆንም አመልካች በቼክ ቅድመ ክፍያ ብር 250,000.00 ሲቀበል የተ.እ.ታ ደረሰኝ ለተጠሪ አልሰጠም። አመልካች ሽያጭ መፈጸሙንም ለገቢዎች መስሪያ ቤት አለማሳወቁን አረጋግጫለሁ።በዚህ ምክንያት ጉዲዩ በወንጀል እየታየ ይገኛል።
በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት የመኪናው ስመ ሀብት ዝውውር የተፈፀመ በመሆኑ አመልካች የተ.እ.ታ ክፍያ ጥያቄ ለማንሳት ከውልም ከሕግም የመነጨ መብት ስለላለዉ በስር ፍርድ ቤቶች የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም በቀን 21/05/2013 ዓ/ም የተፃፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም በግራ ቀኙ መካከል በቀን 15/11/2009 ዓ/ም በተደረገ የሽያጭ ውል አመልካች የሰላዲ ቁጥር 03-853387 ኢት የሆነ አውቶብስ መኪና በብር 310‚000.00 ለተጠሪ ሽጦለት ተጠሪ ብር 250‚000.00 በመክፈል መኪናውንና ሉበሬውን እንደተረከቡና ለአመልካች ሉከፍለ የሚገባ ቀሪ ብር 60‚000.00 እንደሆነ በዉለ ላይ ከተመለከተዉ የስር ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ፍሬ ነገር ነዉ።ግራ ቀኙም በዉለ ላይ የተገለጸዉ ይሄዉ እንደሆነ ይተማመናለ። በዉለ ላይ ስለተ.እ.ታ በግልጽ የተባለ ነገር አለመኖሩንም ግራ ቀኙ የሚካካደት አይደለም። ግራ ቀኙን ያከራከረዉና የዚህን ችልት ምላሽ የሚሻዉ ጭብጥ በዉለ ላይ የመኪናዉ ሽያጭ ዋጋ ነዉ ተብል የተገለጸዉ ብር 310,000.00 ተ.እ.ታ ያካተተ ነዉ ወይስ አይደለም?ዋጋዉ ተ.እ.ታ አላካተተም የሚባል ከሆነ ዉጤቱ ምን ላሆን ይገባል?
የሚለ ናቸዉ።ከዚህ ጋር በተያያዘ አመልካች በዋጋዉ ላይ ተ.እ.ታ ስላልተካተተ ተጠሪ በዋጋዉ ላይ የተ.እ.ታ ብር 46‚500.00 ተ.እ.ታ ጨምረዉ ሉከፍለ ይገባል በማለት ሲከራከሩ ተጠሪ ደግሞ አመልካች የመጀመሪያዉን ክፍያ ሲቀበለ የተ.እ.ታ ደረሰኝ ሳይሰጡኝ ክፍያዉን ከመቀበላቸዉም በተጨማሪ አመልካች በተ.እ.ታ ስም ሉከፈለኝ ይገባል ብለዉ የጠየቁትን ገንዘብ መክፈል እንደሚገባኝ ግልጽ ስምምነት ባለማድረግና በዉለም ላይ ስላልተመለከተ ልከፍል አይገባም በማለት ተከራክረዋል።የስር ፍርድ ቤቶችም የተጠሪን ክርክር በመቀበል ወስነዋል።
እንደሚታወቀዉ የተ.እ.ታ በፍጆታ ዕቃ ወይም በተጠቃሚው ወጪ ላይ የተመሰረተ ታክስ ሲሆን የሚሰበሰበውም ምርት ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ ሲገባ ወይም ማንኛውም ታክስ የሚከፈልበት የዕቃና የአገልግልት ግብይት ሲካሄድ ከተጠቃሚዉ ላይ በመሆኑ ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስ አይነት ነው። ይህንን ታክስ ልዩ ከሚያደርጉት ባህሪያት አንደ በደረሰኝ ላይ ተመስርቶ መከናወን መቻለና በዚህ ምክንያት በቀላለ ሳይከፈል ሉታለፍ ወይም ሉጭበረበር አለመቻለ ነዉ። በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 7(1 እና 3) ላይ በተመለከተዉ መሰረት የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ ከተ.እ.ታ ነጻ ከተደረጉ እቃዎች ወይም አገልግልቶች በስተቀር እቃዎች ፣ አገልግልቶች ፣ የግብአት አቅርቦቶች ሽያጭ ሲያከናዉን 15 በመቶ ተ.እ.ታ በእቃዉ ዋጋ ላይ ጨምሮ ከገዥ ወይም ከተጠቃሚዉ ላይ መሰብሰብ ይጠበቅበታል። ከላይ እንደተመለከተዉ የእቃዉ ወይም የአገልግልቱ ዋጋ የሚባለዉ በእቃዉ/በአገልግልቱ ላይ በተጨመረዉ እሴት ላይ ተ.እ.ታ ተጨምሮ በተጠቃሚዉ የሚከፈል ገንዘብ ነዉ።ስለሆነም ተ.እ.ታ የሚከፈልበትን እቃ ወይም አገልግልት የሚሸጥ ማንኛዉም የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ ለተጠቃሚዉ የሚሸጠዉን እቃ ወይም አገልግልት ዋጋ ሲገልጽ በዋጋዉ ላይ 15 በመቶ ተ.እ.ታ አካቶ መግለጽ ወይም ዋጋዉ ተ.እ.ታ ያላካተተ ከሆነም ይህንኑ ለገዥ በማያሻማ አኳኋን ማሳወቅና በደረሰኝ መሰብሰብ ይኖርበታል።(አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 7 እና የንግድ ዉድድርና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 15/2 ይመለከቷል።) በመሆኑም ተ.እ.ታ መክፈል የተጠቃሚዉ ግዳታ ቢሆንም የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ ሰዉ ተ.እ.ታ የሚከፈልበትን እቃ/አገልግልት ሽያጭ ሲያከናዉን ተ.እ.ታ የመሰብሰብ ግዳታ ስላለበት በእቃዉ ወይም በአገልግልት ዋጋ ላይ ተ.እ.ታ ማካተቱን ሳይገለጽ ወይም ዋጋዉ ላይ ተ.እ.ታ አልተካተተም ብል በግልጽ ለተጠቃሚዉ ሳይገለጽ ግብይት የፈጸመ እንደሆነ የእቃዉ ወይም የአገልግልቱ ዋጋ ነዉ ተብል በዉለ የተጠቀሰዉ ገንዘብ ተ.እ.ታ ያካተተ እንደሆነ ይቆጠራል።ይህም ሻጭ ግብይቱን የፈጸመዉ ተ.እ.ታ በመሰብሰብ እንደሆነ ይቆጠራል እንደማለት ነዉ።
እንዱሁም በአንድ የሽያጭ ዉል ስለዋጋ የሚደረገዉ ስምምነት ከዉለ ጉዲዮች አንደ በመሆኑ ስለሚሸጠዉ እቃ ዋጋ በተዋዋዮች ግልጽ ስምምነት ተደርጎ በማያሻማ አኳኋን በዉለ ላይ መገለጽ እንዲለበት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1680/1፣1711፣ 1714 እና 2266 ስር ከተደነገገዉ መገንዘብ ይቻላል።ለሽያጭ ዉል ዋጋ የዉለ አይነተኛ ጉዲይ እንደመሆኑ በዉለ ከተመለከተዉ በላይ የእቃዉን ዋጋ መጨመር የገዥን ግዳታ ማክበድ ስለሚሆን ገዥ በዚህ አግባብ ዋጋዉ ከፍ እንደሚል ቢያዉቅ ኖሮ ዉለን ላይዋዋል ይችል ስለነበር በዉለ ላይ ተቃራኒ ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር ዉለ መፈጸም ያለበት ገዥ በዉለ በግልጽ የተመለከተዉን ዋጋ ብቻ እንዱከፍል በማድረግ ላሆን ይገባል።በተያዘዉም ጉዲይ በመኪና ሽያጭ ዉለ ላይ በግልጽ የመኪናዉ ዋጋ ነዉ ተብል የተገለጸዉ ብር 310,000.00 ስለሆነና በዉለ ከተመለከተዉ ዋጋ ወጪ ብር 46‚500.00 ተ.እ.ታ ተጠሪ እንደሚከፍለ በዉለ ያልተመለከተ በመሆኑ ተጠሪ ለመክፈል የሚገደደት ይህንን ያህል ገንዘብ ብቻ ነዉ።
ሲጠቃለል የመኪናዉ ዋጋ ነዉ ተብል በዉለ አንቀጽ 310,000.00 ተ.እ.ታ ያካተተ እንደሆነ ይቆጠራል። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች እንደዉለ እንዱፈጸም ሲወስኑ አመልካች በዉለ ላይ ያልተመለከተዉን የተ.እ.ታ ብር 46‚500.00 ተጠሪ በመኪናዉ ዋጋ ላይ ጨምረዉ እንዱከፍለ ያቀረበዉን ዲኝነት ጥያቄ ዉድቅ በማድረግ መወሰናቸዉ ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ ከሚባል በስተቀር የተፈጸመ ስህተት የለም።በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 25/08/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 14/05/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል።ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።