ፍ/ቤቶች በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 155 (3) እና በፋደራል የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 57 (4) መሰረት ከግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የቀረበላቸዉን ጉዲይ የሕግ ስህተት ካልሆነ በቀር ፍሬ ነገር በማስረጃ አጣርቶ ድምዲሜ ላይ ለመድረስ ስልጣን የላላቸዉ ቲ.ኤም.ዜድ.ቢ ኃ/የተ/የግል ማህበር እና በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት
No summary available.
ሚያዚያ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. መዓዛ አሸናፉ 2. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 3. ቀነዓ ቂጣታ 4. ፈይሳ ወርቁ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካች፡- ቲ.ኤም.ዜድ.ቢ ኃ/የተ/የግል ማህበር - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት - የቀረበ የለም ይህ መዝገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ በዱክላራሲዮን ከተገለጸ ዕቃ ዉጭ ማስመጣትና በዚህ ላይ የሚወሰን ቀረጥ የሚመለከት ክርክር የተጠሪ ጽ/ቤት የወሰነዉን የመዉረስ ዉሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ክርክሩ የተጀመረ ሲሆን አመልካች ይግባኝ እና ተጠሪ ደግሞ መልስ ሰጭ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.162466 መስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የተጠሪ ጽ/ቤት አመልካች ከዉጭ ያስመጣዉ ጥሬ ዕቃ እንዱወረስ የሰጠዉን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ፣ ለፋዳራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ያቀረበ ሲሆን፤
የይግባኙ አጭር ይዘት፡ ይግባኝ ባይ በጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንደስትሪ የተሰማረ ሲሆን በከፉል ያለቁ (semi-finished) ጥሬ እቃዎችን ከውጪ በማስመጣት በግብአትነት የሚጠቀም በመሆኑ በመልስ ሰጭ በኩል በዱክላራሲዮን ቁጥር.C.23969/15 ዱክላር አድርገን ለልጆች ልብስ መስሪያ ጥሬ እቃ (track suit) የሚሆን በከፉል ያለቀለት (finished material recycled closed polyster fabric) ያስመጣንና መልስ ሰጭም ይህን ስያሜ መስጠት ሲገባው፣ ካስመጣነው ጥሬ እቃ ጋር በማይመሳሰል 100 % polyster knitted fabric ነው ሲል ስያሜ ሰጥቶት ያልጠበቅነውን ዋጋ በመስጠቱ ለመልስ ሰጪ በየደረጃው ቅሬታችንን ብናቀርብም ውድቅ በመደረጉ ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አመልክተን ክርክር ላይ ባለንበት ወቅት የእቃውን መወረስ የሰማን በመሆኑ ህጉ ለዚህ ዘርፍ የሰጠውን ማበረታቻን ከግምት ዉስጥ ያላስገባ ስለሆነ የመልስ ሰጭ የዉርስ ዉሳኔ ዉድቅ ሆኖ ለመንግስት ቀረጥና ታክስ ተፈላጊዉን ዋስትና አስይዘን ያስመጠናዉን ጥሬ ዕቃ ወደ ምርት እንድንለዉጥ እንዱወሰንልን በማለት አመልክቷል።
በዚህ ይግባኝ ላይ መልስ ሰጭ ባቀረበዉ መልስ ይግባኝ ባይ በዱክላራሲዮን ቁጥር C.23969/15 ለማስመጣት ዱክላር ያደረገው blanket material (semi-finished) ሲሆን፣ ግን ያስገባዉ በባለሙያ በተደረገዉ አካላዊ ፍተሻ እንደተረጋገጠዉ knitted/crouched fabric for the manufacturing of baby cloth ሆኖ በመገኘቱ በአስመጪዉ የቀረበው የግብይት ዋጋ ተቀባይነት እንደማያገኝና የእቃዉ ታሪፍ ምደባም የሚቀየር ሲሆን ፣ይግባኝ ባይ ያስገባዉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ 2.8 USD/Kg በመሆኑ፣ በዱክላራሲዮኑ ላይ ከተጠቀሰው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ 1.8 USD/Kg ስለሆነ፣ ከተጠየቀዉ ከ50% በላይ የዋጋ ልዩነት ስላለው መወረሱ ህጋዊ እንደሆነ በአዋጅ ቁ.859/2006 አንቀጽ 8፣ 13፣ 102 እና መመሪያ ቁ.111/2008 አንቀጽ 5 (2) (ሀ) ላይ ተደንግጓል፤ ይግባኝ ባይ ያስገባው እቃ በዱክላራሲዮን /14 ከዚህ ቀደም ከገባዉ እቃ ጋር ተመሳሳይና ከአንድ ላኪ ድርጅት ከመጡና ከጉምሩክ ዲታ ቤዝ በተገኘ መረጃ ነው፤ በዚህ ምክንያት ይግባኝ ባይ ያቀረበውን ስያሜ ውድቅ በማድረግ ጥሬ ዕቃዉን መውረሱ በህግ አግባብ ስለሆነ የጽ/ቤቱ ዉሳኔ እንዱጻናልን በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ የፋዳራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ ይግባኝ ባይ ከዉጭ ያስመጠዉ ጥሬ እቃ ላይ ከኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የቀረበዉ የባለሙያ አስተያየት ዕቃዉ ብርድ ልብሶችን ለማምረት የሚያገለግል መሆኑን አረጋግጠናል የሚል ሲሆን፤ ይግባኝ ባይ መንግስት የሀገር ውስጥ አምራችን ማበረታቻ እንዱያገኙ ለማድረግ እና ጉምሩክ ታሪፍ ማበረታቻ ተጠቃሚ ስለሆኑ ይህን እድል ለመጠቀምና በዱክላራሲዮኑ ላይ ያለው ትክክል አለመሆኑን በመረዲት semi-finished recycled polyster fabric for truck suit የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ከነመቀጫዉ መክፈል ያለበት ሲሆን መልስ ሰጭ በግብአቱ ላይ ያስተላለፈው የመውረስ ውሳኔ ከህግ ውጪ ነው በማለት በመሻር ወስኗል።
የሥር መልስ ሰጪ ጽ/ቤት (ይግባኝ ባይ) በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር ይግባኝ ባይ (መልስ ሰጭ ማህበር) ወደ ሀገር ውስጥ የገባዉ ጥሬ ዕቃ ላይ ለውጥ መደረጉ በግልጽ ተረጋግጦ ሲሆን በዚህ ለውጥ የዋጋ ልዩነት ከ50% በላይ ያሳያ መሆኑ እየታወቀና ይህም ባልተስተባበለበት ሁኔታ የመንግስትን ማበረታቻ እንዱያገኙ የሚል ምክንያት በመጥቀስ ይግባኝ ባይ እቃዉ እንዱወረስ የተላለፈውን ውሳኔ መሻሩ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (1) (ለ) እና መመሪያ ቁጥር 112/2006 አንቀጽ 15 (2) (ለ) ድንጋጌዎች ያላገናዘበ ነው በማለት የጉባኤዉን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል።
የሥር መልስ ሰጭ ማህበር በዚህ ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ20/4/2012 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ የፋዳራል ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አመልካች ወደ ሀገር ዉስጥ ያገባዉ ዕቃ ስያሜ ምን ላሆን ይገባል የሚለዉን ጭብጥ በመያዝ በማጣራት ተጠሪ semi-finished recycled polyster fabric for truck suit በመመደብ የሰጠዉ የዉርስ ዉሳኔ ተገቢ አለመሆኑን በመወሰን በመሻር ወስኗል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በግብር ይግባኝ ጉባኤ በሚደረጉ ክርክሮች ላይ በይግባኝ ለመዲኘት የተሰጣቸዉ የዲኝነት ስልጣን ከሕግ ጭብጥ ጋር የተያያዘ ብቻ መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 155 (2) (4) እና የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 112 (1) ላይ በግልጽ ተመልክቶ እያለ ፍ/ቤቶች ከዚህ ዉጭ የማስረጃ ምዘና ስልጣን ሳይኖራቸዉ፣ የጥሬ ዕቃዉ ስያሜና ዋጋዉን ተጠሪ ሳያስረዲ የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የጉባኤዉ ስያሜና ዉሳኔ እንዱጸናልን በማለት በዝርዝር አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣ያከራከረው የአሁን አመልካች ወደ አገር ውስጥ ያስገባው እቃ ለመወረስ እንደምክንያት የቀረበው ለማስመጣት የተጠየቀውና ያስመጣው ዋጋ ልዩነቱ ከ50% በላይ ሆኗል በሚል በመሆኑ አስመጣለው ያለው እቃና በኢንስቲትዩቱ የተረጋገጠው እቃ ዋጋ ከ50% በላይ መሆኑ ስለመረጋገጡ ለማጣራት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ታዟል።
የአሁን ተጠሪ በ25/6/2012 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ አመልካች በዱክላራሲዮን ቁጥር C.23969/15 ለማስገባት መግለጫ blanket material (semi-finished) ሆኖ ሳለ የተጠሪ መ/ቤት ባደረገዉ አካላዊ ፍተሻ ዕቃዉ knitted/crouched fabric for the manufacturing of baby cloth መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን በዚህ የአገላለጽ ልዩነት የቀረጥና ታክስ ልዩነት ከ50% በላይ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን አመልካች ይህን ያስተባበለበት ሁኔታ የለም፣ የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንስትቲዩት የላከዉ መግለጫ ዕቃዉ ባህር ከሚገልጽ በስተቀር የዕቃዉን ምንነት ያስቀመጠ ነገር የለም፣ ይህ መግለጫ የተጠሪ መ/ቤት በፍተሻ አገኘሁ የሚለዉን ዕቃ ይባልጥ የሚገልጽ አስተያየት ነዉ። ተጠሪ አመልካች ወደ አገር ያስገባዉ ዕቃ ለማስገባት ከገለጸዉ ዕቃ ልዩነት ስያሜ ምክንያት የዕቃዉ ዋጋ ልዩነት ከ50% በላይ መሆኑ በማስረጃ ነጥሮ ተረጋግጦ የዉርስ ዉሳኔ የተላለፈ ስለሆነ በዚህ ረገድ የቀረበ ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ ስለሆነ እንዱጸናልን ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልን በማለት በዝርዝር ተከራክሯል። አመልካች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ከተባለዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ የአሁን አመልካች ወደ አገር ለማስገባት በዱክላራሲዮን ቁጥር C.23969/15 መግለጫ በሰጠዉ እና በተጨባጭ ወደ አገር ያስገባዉ ጥሬ ዕቃ መካከል የስያሜ ልዩነት እንዲለ ከግራ ቀኙ ክርክርና ከሥር በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እና የሥር ፍ/ቤቶች የዉሳኔ ግልባጭ መረዲት የሚቻል ጉዲይ ነዉ። በግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤም ሆነ በሥር ፍ/ቤቶች እንደተመለከተዉ አመልካች ወደ አገር ለማስገባት መግለጫ የሰጠዉ ጥሬ ዕቃ blanket material (semi-finished) ሆኖ ሳለ፣ በተጨባጭ ወደ አገር ያስመጣዉ ግን ከዚህ ስያሜ ዉጭ መሆኑን እና የተጠሪ መ/ቤት በባለሙያዎቼ አድርጌአለሁ ባለዉ አካላዊ ፍተሻ ዕቃዉ knitted/crouched fabric for the manufacturing of baby cloth መሆኑን በመግለጽ፣ የዚህን ጥሬ ዕቃ ስያሜ መነሻ በማድረግ መከፈል ይገባል ያለዉ የቀረጥና ታክስ ዋጋ መተመኑን መገንዘብ ተችሎል። የሥር የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በበኩለ ወደ አገር የገባዉ ጥሬ ዕቃ እና ለማስገባት የተሰጠዉ መግለጫ ላይ የተጠቀሰዉ ጥሬ ዕቃ ልዩነት ያለዉ መሆኑን በመቀበል፣ የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ስለጉዲዩ ሙያዊ አስተያየት እንዱሰጥ በጠየቀዉ መሰረት ግንቦት 3 ቀን 2008 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ አስተያየቱን መስጠቱን ከጉባኤዉ የዉሳኔ ግልባጭ የምንረዲዉ ነዉ። አመልካች ወደ አገር ያስገባዉ ጥሬ ዕቃ ባህርና የዕቃዉ አገልግልት ከሚያብራራ በስተቀር የዕቃዉን ስያሜ እንደማይገልጽ እና የተጻፈዉን ደብዲቤ ይዘት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በዉሳኔዉ በዝርዝር ማስቀመጡን ማየት ይቻላል። ይህ ከሆነ አመልካች በዱክላራሲዮን ላይ ከገለጸዉ ጥሬ ዕቃ ዉጭ ወደ አገር ያስመጣ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ፣ ከፍ ሲል የተጠቀሰዉ ኢንስቲትዩት የጻፈዉ ሙያዊ አስተያየት የዕቃዉን ባህርና አገልግልት የሚገልጽ እንጂ ስያሜዉን የማያመለክት በሆነበት፣ የሥር የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የዕቃዉ ስያሜ semi-finished recycled polyster fabric for truck suit ተብል እንደተጻፈ በመዉሰድ፣ በዚህ አግባብ አመልካች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ከነመቀጫዉ በመክፈል የተጠሪ መ/ቤት በግብዓቱ ላይ ያስተላለፈው የመውረስ ዉሳኔ መሻሩን የዉሳኔዉ ግልባጭ ያሳያል። ይህ ጉዲይ በይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛና ጠቅላይ ፍ/ቤት የቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቶቹ ጉባኤዉ ለዕቃዉ የሰጠዉ ስያሜ ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ዉሳውኔን መሻራቸዉን ማየት ይቻላል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በዉሳኔዉ እንዲመለከተዉ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ለጥሬ ዕቃዉ ስያሜ ለመስጠት መነሻ ያደረገዉ ኢንስቲትዩቱ የጻፈዉ ደብዲቤ ቢሆንም የደብዲቤዉ ይዘት ሲታይ ጉባኤዉ ለዉሳኔዉ መሰረት ያደረገዉን ስያሜ እንዲማያመለከትና የተላከዉ ደብዲቤ ይዘት በዝርዝር በማስቀመጥ፤ የተጠሪ መ/ቤት ለዕቃዉ የሰጠዉ ስያሜ ተገቢ መሆኑን በማረጋገጥ መወሰኑን የዉሳኔዉ ግልባጭ ያመለክታል። የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤዉ ከኢንስቲትዩቱ ግንቦት 3 ቀን 2008 ዓ.ም ተጽፍ የተላከዉን ደብዲቤ ይዘት ያላስቀመጠ በመሆኑ፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ደግሞ በሰጠዉ ዉሳኔ የደብዲቤዉን ይዘት በግልጽ ያመለከተ በመሆኑ፣ ፍ/ቤቱ በዉሳኔዉ የገለጸዉ የደብዲቤዉ ይዘት ትክክለኛ መሆኑን ይህ ችልት ተገንዝቧል። ይህ ከሆነ ደግሞ የፋዳራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተላከዉ ደብዲቤ የዕቃዉን ስያሜ በማይገልጽበት ሁኔታና የደብዲቤዉ ይዘት የማይለዉን ትርጉም በመስጠት፣ ማስረጃዉ የማይለዉን መሰረት በማድረግ፣ አመልካች ወደ አገር ያስገባዉን ዕቃ ስያሜ በማስጠት፣ ይህን መሰረት አድርጎ የተጠሪ መ/ቤት ያስተላለፈዉ የዉርስ ዉሳኔ በመሻር አመልካች የዕቃዉን ቀረጥና ታክስ ከነመቀጫዉ በመክፈል እንዱወስደዉ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ የቀረበዉን ማስረጃ መሰረት ያደረገ ዉሳኔ ነዉ ለማለት አይቻልም። ፍ/ቤት ወይም በሕግ የዲኝነት ስልጣን የተሰጠዉ አካል የቀረበዉን ማስረጃ ይዘቱን በትክክል ካስቀመጠ በኋላ ማስረጃዉን መዝኖ ተገቢ ነዉ ያለዉ ድምዲሜ ላይ መድረስ የማስረጃ ምዘና መርህ የሚደግፈዉ አግባብ ቢሆንም ማስረጃዉ የማይለዉን እንደሚል በመግለጽና ይዘቱን በመለወጥና የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት ይህን መሰረት በማድረግ ዉሳኔ መስጠት የማስረጃ ምዘና መርህን የሚቃረን ነዉ። በዚህ አግባብ የሚሰጥም ዉሳኔ የቀረበዉን ማስረጃ መሰረት ያደረገ ወይም በማስረጃ የተደገፈ ነዉ ለማለት አይቻልም። በልላ በኩል አመልካች ባቀረበዉ ክርክር የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሰጠዉ የጥሬ ዕቃዉን ስያሜ የሚደግፍ ላላ ማስረጃ ማቅረቡን የሚያመለክት ነገር የለም። ይህ ከሆነ ደግሞ የሥር ፍ/ቤቶች የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አመልካች ወደ አገር ያስገባዉ ጥሬ ዕቃ በተመለከተ የሰጠዉ ዉሳኔ በማስረጃዉ የተደገፈ አይደለም በማለት ዉድቅ በማድረግ፣ የተጠሪ መ/ቤት የሰጠዉን ስያሜ ማለትም knitted/crouched fabric for the manufacturing of baby cloth ነዉ በማለት ድምዲሜ ላይ በመድረስ የሰጡት ዉሳኔ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 155 (3) እና የፋዳራል የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 57 (4) ሥር ከግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የቀረበዉን ዉሳኔ የህግ ጉዲይ ላይ ብቻ ዲኝነት አይቶ እንዱወስኑ ከተሰጣቸዉ ስልጣን ዉጭ ወጥቶ ፍሬ ነገር አይተዋል የሚያስብል አይሆንም። ስለሆነም አመልካች ወደ አገር ያስገባዉ ጥሬ ዕቃ knitted/crouched fabric for the manufacturing of baby cloth ነዉ ብለዉ የሥር ፍ/ቤቶች የደረሱበትን ድምዲሜ ይህ ችልት ፍሬ ነገር የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን በሕግ የተሰጠዉ ስልጣን ስለላለዉ ይህን የዕቃዉን ስያሜዉ የሚቀበለዉ ይሆናል፡ በዚህ ረገድ የአሁን አመልካች የሥር ፍ/ቤቶች ከስልጣናቸዉ ዉጭ ወጥተዉ ፍሬ ነገር አጣርቶ ዉሳኔ አሳልፎል በማለት ያቀረበዉ ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
በልላ በኩል በዚህ ጉዲይ መታየት ያለበት የአሁን ተጠሪ አመልካች ወደ አገር ያስገባዉን ጥሬ ዕቃ ለመዉረስ የሚያስችለዉ ሁኔታ ተሟልቷል ወይስ አልተሟላም? የሚለዉ ነጥብ መሆኑን ተገንዝበናል። በዚህ መሰረት አመልካች ባቀረበዉ ክርክር ወደ አገር ያስገባዉ ዕቃ ከተመዘገበዉ አጠቃላይ ዋጋ ከ50% በላይ መሆኑን ተጠሪ የማስረዲት ግዳታዉን ባልተወጣበት፣ የዋጋዉ ልዩነቱ ተጣርቶ ዕቃዉን የዉርስ ዉሳኔ ለማስተላለፍ የሚያበቃ መሆኑ ሳይረጋገጥ የተሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ አይደለም የሚል ነዉ። ተጠሪ በበኩለ ባቀረበዉ ክርክር አመልካች ወደ አገር ያስገባዉ ዕቃ በዱክላራሲዮን ላይ ከተመዘገበዉ ጠቅላላ ዋጋ ልዩነቱ ከ50% በላይ ማለትም 55.5% መሆኑን በተጠሪ መ/ቤት በተሰጡት ዉሳኔዎች ጋር ተያይዞ በተሰሩት ቀመር አስረድተናል፣ ስለሆነም በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (1) (ለ) እና በመመሪያ ቁጥር 112/2008 አንቀጽ 15 (2) መሰረት የዉርስ ዉሳኔ መሰጠቱ ተገቢ ነዉ በማለት ተከራክረዋል። ከዚህ አንጻር የሥር የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እና ፍ/ቤቶች አመልካች ወደ አገር ያስገባዉ ዕቃ ዋጋ በዱክላራሲዮን ላይ ከተመዘገበዉ አጠቃላይ ዋጋ ከ50% በላይ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉን ነጥብ ያዩበት አግባብ መታየት አለበት። የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤዉ ተጠሪ የዉርስ ዉሳኔ ያስተላለፈበትን የዕቃዉን ስያሜ ስለቀየረዉ፣ በዚህ ምክንያት የዋጋዉ ልዩነቱ ከ50% በላይ አለመሆኑን ስለተገነዘበ፣ ተጠሪ የዉርስ ዉሳኔ በሰጠበት የዕቃዉ ስያሜ መሰረት የዋጋዉ ልዩነት ከ50% በላይ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉን ፍሬ ነገር ለማጣራት የሄደበት መሆኑን የሚያሳይ ነገር የለም። የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩለ ለዕቃዉ ተጠሪ የሰጠዉን ስያሜ በመቀበል በዚህ ምክንያት የተፈጠረዉ ለዉጥ የዋጋ ልዩነት ከ50% በላይ ያሳዩ መሆኑ የሚታወቅና ያልተስተባበለ ነዉ ብል ዉሳኔ ከመስጠት በስተቀር የሥር ጉባኤዉ በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት የዋጋዉን ልዩነት በማስረጃ አንጥሮ ስለማዉጣቱ የገለጸዉ ነገር የለም። በዚህ ረገድ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የደረሰበት ድምዲሜ ሲታይ በዕቃዉ ስያሜ ልዩነት ምክንያት የተፈጠረዉ የዋጋ ልዩነት ከ50% በላይ እንደሆነ በጉባኤዉ እና በዚህ ፍ/ቤት ዘንድ ከተደረገዉ ክርክር የምንገነዘበዉ ነዉ በማለት ማለፈን እንጂ የዋጋዉን ልዩነት በተመለከተ በምን አግባብ እንደተጣራ የሚገልጽ ሆኖ አልተገኘም።
እንደሚታወቀዉ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (1) (ለ) መሰረት ተደብቆ የተገኘዉ ዕቃ ዋጋ በዱክላራሲዮን ከተመዘገበዉ አጠቃላይ ዋጋ ከ50% በላይ ሆኖ ሲገኝ ተደብቀዉ የተገኙት ዕቃዎች ዉርስ ሆነዉ ለመንግስት ገቢ እንደሚደረጉ ይደነጋግል። እንግዱህ አመልካች ያስገባዉ ዕቃ ዋጋ በዱክላራሲዮን ከተመዘገበዉ አጠቃላይ ዋጋ አንጻር ሲታይ የዋጋዉ ልዩነት ከ50% በላይ ከሆነ በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (1) (ለ) መሰረት ዕቃዉን የሚያስወርስ ሲሆን፣ የዋጋዉ ልዩነቱ ግን ከዚህ በታች ከሆነ ዕቃዉ ላይ የዉርስ ዉሳኔ ለማሳለፍ የሚያበቃ አይሆንም ማለት ነዉ። ስለዚህ አመልካች ባስገባዉ ዕቃ እና በዱክላራሲዮን ላይ ከተመዘገበዉ አጠቃላይ ዋጋ መካከል ያለዉ የዋጋ ልዩነት ከ50% በላይ መሆን አለመሆኑ ፍሬ ነገር የማጣራት ስልጣን ባለዉ የፋዳራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ተጣርቶ መረጋገጥ ያለበት ጉዲይ ነዉ።
የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 155 (1) ማየት ይቻላል። የሥር ፍ/ቤቶች በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 155 (3) እና በፋዳራል የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 57 (4) መሰረት ከግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የቀረበላቸዉን ጉዲይ የሕግ ስህተት ያለበት ከሆነ ብቻ ስለሚያዩ ፍሬ ነገር በማስረጃ አጣርቶ ድምዲሜ ላይ ለመድረስ ስልጣን የላቸዉም። ስለሆነም የፋዳራል ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አመልካች ወደ አገር ያስገባዉ ዕቃ በዱክላራሲዮን ላይ ከተመዘገበዉ አጠቃላይ ዋጋ መካከል የዋጋ ልዩነቱ ከ50% በላይ መሆን አለመሆኑን በማጣራት፣ አመልካች ያስገባዉን ዕቃ ለዉርስ የሚያበቃዉ ሁኔታ መሟላት አለመሟላቱ ላይ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ የመስጠት ስልጣን አለዉ። በመሆኑም የፋዳራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በዚህ አግባብ በማጣራት አመልካች ያስመጣዉ ዕቃ ላይ የዉርስ ዉሳኔ ለማስተላለፍ የሚያበቃ ምክንያት አለ ወይስ የለም? የሚለዉን ነጥብ በማጣራት ዉሳኔ መስጠት ሲገባዉ ይህን ሳያደርግ የሰጠዉን ዉሳኔ የሥር ፍ/ቤቶች ደግሞ በጉባኤዉ ዘንድ በግልጽ ተጣርቶ ዉሳኔ እንደተሰጠበት በማመልከት መወሰናቸዉ የህግ ድጋፍ የለዉም።
ሲጠቃለል የፋዳራል ግብር ይግባኝ ጉባኤ አመልካች ያስመጣዉን ጥሬ ዕቃ ለማስወረስ የሚያበቃ ነገር ከዋጋ ልዩነት አንጻር መኖር አለመኖሩን በአግባቡ ሳያጣራ የሰጠዉ ዉሳኔ እና የሥር ፍ/ቤቶች በዚህ ረገድ ጉባኤዉ ሳያጣራ የሰጠዉን ዉሳኔ በማረም አጣርቶ ዉሳኔ እንዱሰጥበት ማድረግ ሲገባቸዉ ይህን ሳያደርጉ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.205263 ሐምል 13 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.162466 መስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሻሽሎል።
የፋዳራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ መስከረም 30 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች ወደ አገር ያስገባዉ ጥሬ ዕቃ ስያሜ knitted/crouched fabric for the manufacturing of baby cloth ነዉ በማለት የሰጡት የዉሳኔ ክፍል አልተነካም ጸንቷል። የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች ያስገባዉ ዕቃ በዱክላራሲዮን ላይ ከተመዘገበዉ አጠቃላይ ዋጋ ልዩነት ምን ያህል እንደሆነ በጉባኤዉ ዘንድ መጣራቱን ሳያረጋግጡ የዋጋዉ ልዩነት ከ50% በላይ ነዉ በማለት በዕቃዉ ላይ ዉርስ ዉሳኔ በተጠሪ መሰጠቱ ተገቢ ነዉ በማለት የሰጡት የዉሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የፋዳራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተዘጋዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ ሐተታዉ በተመለከተዉ መሰረት አመልካች ወደ አገር ያስገባዉ ዕቃ knitted/crouched fabric for the manufacturing of baby cloth መሆኑን በመገንዘብ፤ ይህ የገባዉ ዕቃ በዱክላራሲዮን ላይ ከተመዘገበዉ አጠቃላይ ዋጋ ልዩነቱ ከ50% በላይ ነዉ ወይስ አይደለም? የዋጋ ልዩነት አለ ከተባለ ዕቃዉ ዉርስ ሆኖ ለመንግስት ገቢ የሚያስደርግ ነዉ ወይስ አይደለም?
የሚለትን ነጥቦች አግባብነት ባለዉ ማስረጃ በማጣራት ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.343 (1) መሰረት ተመልሶለታል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.