ማንኛውም አካል ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ባስገባቸው እቃዎች በአንደም ሆነ በላልቹ ወይም በልላ ምክንያት የሚፈለግበት መክፈያ ጊዜው የደረሰ የታክስ እዲ መኖሩን የኢትየጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ያረጋገጠ እንደሆነ እዲው ተከፍል እስኪያልቅ በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ የቀዲሚነት መብት ስላለው በታክስ አስተዲደደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41(4) (ለ) መሰረት በማናቸውም የፍርድ ሂደት ዕገዲ በተደረገበት ወይም የአፈፃፀም ትዕዛዝ የተሰጠበት ንብረትን ባለስልጣኑ የመያዝ ስልጣን የላለው መሆኑ የተመላከተ ቢሆንም ድንጋጌው ንብረትን የመያዝ ሁኔታን ብቻ የሚከለክል እንጂ ባለስልጣኑ የግብር እዲውን ለማስከፈል የሚኖረውን የቀደምትነት መብት የሚያሳጣ ስላለመሆኑ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀፅ 73(3)፣ እና 130፣122(1)፣ 6 እና የታክስ አስተደዲደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀፅ 39(1 እና 2) ከቀረጥ ነጻ የገባ ንብረት ተመልሶ እስካልወጣ ድረስ ተገቢው የግብር እዲ ተከፍልበት ሀገር ውስጥ የሚቀር በመሆኑ ለግብር እዲ በዋስትና ሉያዝ የሚችል መሐመድ አብደላሂ የማሽነሪ ኪራይ እና በጉምሩክ ኮሚሽን የአዱስ አበባ ቃሉቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት
No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- መሐመድ አብደላሂ የማሽነሪ ኪራይ፡- ጠበቃ በፍቃደ ስዩም ቀረቡ ተጠሪ፡- በጉምሩክ ኮሚሽን የአዱስ አበባ ቃሉቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት፡- ነ/ፈጅ፡- አሸናፉ ማሞ ቀረበ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ክርክሩ አፈፃፀምን መሰረት ያደረገ ሲሆን ጉዲዩ በተጀመረበት የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች የፍ/ባለመብት ዩኢቲ አልሳሜክስ ኢኮ አስፊልት ኢትዮጵያ 35 የፍርድ ባለእዲ የአሁን ተጠሪም ተጠሪ በመሆን ተከራክረዋል።
በስር ፍ/ቤቶች ከተደረገው ክርክር መገንዘብ የሚቻለው አመልካች የስር የፍ/ባለእዲው ብር 1,778,477.29 (አንድ ሚሉዮን ሰባት መቶ ሰባ ስምንት ሺ አራት መቶ ሰባ ሰባት ከ29/100) እንዱከፍለው ባቀረበው የአፈፃፀም ክስ መነሻነት የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ንብረትነቱ የፍ/ባለእዲው የሆነ የአስፊልት ፓቺንግ ፕላንት ማሽን በሐራጅ ተሽጦ ለፍ/ባለመብቱ ክፍያ እንዱፈፀምለት ለፋደራል ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዲይሬክቶሬት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ዲይሬክቶሬቱም ሐራጁን እያከናወነ ባለበት የክፍለ ፖሉስ ንብረቱ በጉምሩክ ፅ/ቤት ታግዶል በማለቱ አፈፃፀሙ ሉቀጥል አለመቻለን ገልፆ ሰኔ 12 ቀን 2011 ዓ.ም ፍ/ቤቱ መመሪያ እንዱሰጥበት ጠይቋል። የአፈፃፀም ችልቱም ተጠሪ በጉዲዩ ላይ ምላሽ እንዱሰጥበት ያደረገ ሲሆን ተጠሪ በሰጠው ምላሽ በፍ/ባለእዲው ስም ያልተከፈለ የጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስ ብር 98,474,858.17 (ዘጠና ስምንት ሚሉዮን አራት መቶ ሰባ አራት ሺ ስምንት መቶ ሀምሳ ስምንት ከ17/100) የሚፈለግበት በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 983/2008 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ማገደን ገልፆ ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ ከፍ/ባለእዲው የሚፈልገው ገንዘብ የፍ/ባለእዲው ያለ ቀረጥና ታክስ ወደ ሀገር ውስጥ ላስገባቸው የተለያዩ እቃዎች(ማሽኖች) ለእያንዲንደ ሉከፍል የሚገባውን ጠቅላላ ገንዘብ የሚመለከት ነው። በመሆኑም የፍ/ባለእዲው ንብረት በሆነው የአስፊልት ፓንቺንግ ፕላንት ማሽን ላይ የፍርድ አፈጻፀም ዲይሬክቶሬቱ ሐራጁን እንዱቀጥል እና በዚህ ንብረት ላይ በተጠሪ የሚፈለገውን ቀረጥና ታክስ ከሽያጭ ገንዘቡ ላይ ተቀናሽ ሆኖ ተራፉው ለአመልካች እንዱከፈል ብይን ሰጥቷል።
ተጠሪ ይህን ብይን በመቃወም ለፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታውን አቅርቧል። የይግባኝ አቤቱታው ይዘት ባጭሩ ጉዲዩን በመጀመሪያ በተመለከተው የከፍተኛ ፍ/ቤት ከፍ/ባለእዲው የሚፈለገው ጠቅላላ የቀረጥ እና ታክስ እዲ ብር 98,474,858.17 መሆኑን እና ማሽኑን ቀድመን ለአጠቃላይ እዲው መያዣ የያዝን መሆኑን በመግለፅ ማስረጃዎችንም ጭምር በማቅረብ ተከራክረናል። ተጠሪ ባለው የቀደምትነት መብት መሰረት ማሽኑን እና ላልች ንብረቶችን ይዞ በግልፅ ጨረታ በመሸጥ ለእዲው ማካካሻነት ማዋል እንደሚችል በፋደራል ታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41/8 እና አንቀፅ 41/9 ላይ ተደንግጓል። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት በማሽኑ ላይ ብቻ የሚፈለግ እዲ ተቀናሽ ሁኖ ተራፉው ለአመልካች እንዱከፈል መወሰኑ የታክስ አስተዲደደር አዋጁ አንቀፅ 41(8)(9)፣ 122(6)፣ የጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 122(6) እና 148(2)ን ስለሚቃረን ሉታረም ይገባል በማለት ነው። አመልካች ለይግባኝ አቤቱታው በሰጠው መልስ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት አቤቱታውን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ወይም 418 አግባብ አላቀረበም። በታክስ አስተዲደር አዋጅ አንቀፅ 41(4)(ሀ) መሰረት በክርክር ታግድ በአፈፃፀም ተይዞ ትዕዛዝ የወጣበትን ንብረት መያዝ ስለማይቻል እና ተጠሪው የፍ/ባለእዲው ያለበትን የግብር እዲ እንዱከፍል ጠይቆት እንቢተኛ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ማሽኑ ለጠቅላላ እዲ ክፍያው ሉውል ይገባል በማለት ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል። ይግባኙን የተመለከተው ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ በሕግ አግባብ የተቋቋመ የመያዣ መብት በሕግ ጥበቃ የሚደረግለት ስለመሆኑ በፍ/ሕ/ቁጥር 2828፣ 2857(1) እና 3059 ተመላክቷል። ይህ መብት ያለው ሰው ከላላው ሰው የቅድሚያ መብት አለው። ተጠሪ የግብር ሰብሳቢ ተቋም በመሆኑ በአዋጁ ቁጥር 983/08 አንቀፅ 39(1) መሰረት የመክፈያ ጊዜው የደረሰ ታክስ በሙለ ተከፍል እስኪያልቅ ድረስ በባለእዲው ማንኛውም ንብረት ላይ የቀደምትነት መብት ያለው በመሆኑ በዚህ አግባብ እዲው ተከፍል ሳያልቅ የአስፊልት ፓንቺንግ ፕላንት ማሽኑ ላይ ብቻ የሚፈለገው እዲ ተቀናሽ ተደርጎ ቀሪው ለአመልካች እንዱመለስ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ችልት ግንቦት 6 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታውን ያቀረበው የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሳኔውን በመቃወም ነው። የአቤቱታው ይዘት ባጭሩ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀፅ 73 መሰረት ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ለግንባታ ስራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ማሽነኖች ስራቸውን ከጨረሱ በኋላ ተመልሰው ከሀገር ውስጥ የሚወጡ በመሆኑ ለተጠሪ የቅድሚያ መብት አይፈጥሩም።
ተጠሪ የስነ ስርዓት ሕጉ በሚፈቅደው አግባብ አቤቱታ አቅርቦ አልተከራከረም። የፍ/ባለእዲውንም ጠይቆ እዲውን አልከፍልም ባላለበት ሁኔታ የከፍተኛ ፍ/ቤቱ የሰጠው ውሳኔ መሻሩ አግባብ አይደለም።
በተጠሪ አና በፍ/ባለእዲው መካከል በውል የተቋቋመ የመያዣ መብት መኖሩ ሳይረጋገጥ እንዱሁም ማሽኑ ልዩ ተንቀሳቃሽ እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ስላልሆነ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የፍ/ሕ/ቁጥር 2828፣2857(1) እና 3059ን ጠቅሶ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚል ነው።
ጉዲዩ በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ጨረታ የወጣበት ንብረት ለግንባታ ስራ ከቀረጥ ነፃ የገባ ሁኖ የቀረጥ እዲ አለብህ ክፈል ተብል ማስታወቂያ ባልወጣበት አመልካች በስር ፍ/ቤት የጠቅላላ እዲ ተጠያቂ የሆነበት አግባብነት ከጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 እና ከፋደራል ታክስ አስተዲደደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀፅ 41(8)(9) እንዱሁም ጉዲዩን በይግባኝ ያየው ጠ/ፍ/ቤት ንብረቱ በመያዣ ውል እንደተያዘ እና እንደማይንቀሳቀስ ንብረት በመውሰድ በፍ/ሕ/ቁጥር 2828፣ 2857(1) እና 3059 አንፃር ጉዲዩን ያየበትን አግባብ ለማጣራት ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልሱን እንዱያቀርብ ታዟል።
ተጠሪ ሐምል 10 ቀን 2012 ዓ.ም የተፃፈ መልሱን አቅርቧል። የመልሱ ይዘት ባጭሩ አመልካች የጉምሩክ አዋጅ 859/06 አንቀፅ 73ን መሰረት አድርጎ ያቀረበው አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ያልተነሳ በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 329 መሰረት ተቀባይነት የለውም። ተቀባይነት አለው ቢባል እንኳ ተጠሪ ባለእዲው መክፈል የነበረበትን የቀረጥ እና ታክስ እዲ ብር 98,474,858.17 በድህረ እቃ አወጣጥ ኦዱት አረጋግጦ በቁጥር 4.3/አ52/1025 መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ለድርጅቱ ወጪ ተደርጓል። ድርጅቱም በ15 ቀናት ውስጥ ባለመክፈለ በአዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀፅ 122(6) እና 983/08 አንቀፅ 41(8) እና 41(9) መሰረት የድርጅቱ ንብረት ለቀረጥ እና ታክስ እዲው ዋስትና በመሆናቸው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተጠሪ የቀደምትነት መብት አለው በማለት መወሰኑ አግባብ ነው። ተጠሪ በክርክሩ ተሳታፉ የሆነው ፍ/ቤቱ በጉዲዩ ላይ ጣልቃ ገብቶ መልስ እንዱሰጥ ባዘዘው መሰረት ነው። የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ የፍ/ሕ/ቁጥር 2828፣2857(1)ን የጠቀሰው ተጠሪ ከላይ በተጠቀሱት አዋጆች የተሰጠውን የቀደምትነት መብት ለማጠናከር ሲሆን በፍ/ሕ/ቁ 1127 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ማሽን ልዩ ተንቀሳቃሽ በመሆኑ እንደማይንቀሳቀስ ንብረት የሚቆጠር በመሆኑ የፍ/ሕ/ቁጥር 3059 መጠቀሱም ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል።
አመልካች ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልቱ ያስቀርባል ሲባል የተያዘውን ጭብጥ በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች ከተደረጉ ክርክሮች፣ በማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
እንደመረመርነውም አመልካች በዋናነት የሚከራከረው በፍርድ አፈፃጸም የተያዘው ንብረት ከቀረጥ ነፃ የገባ እና ተመልሶ ከሀገር ውስጥ የሚወጣ ስለሆነ ለተጠሪ የቅድሚያ መብት የሚሰጥ አይደለም።
ተጠሪም የፍርድ ባለእዲው የግብር እዲውን እንዱከፍለው ሳይጠይቅ እና የስነ ስርዓት ሕጉን ተከትል አቤቱታውን ሳያቀርብ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ለጉዲዩ ተገቢነት የላላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች በመጥቀስ በፍርድ አፈጻጸም የተያዘውን ንብረት ለጠቅላላ የግብር እዲ ክፍያው ሉውል ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ ሉታረም ይገባል በማለት ነው። በአንፃሩ ተጠሪ የሚከራከረው የፍርድ ባለእዲው ጠቅላላ የሚፈለግበትን የግብር እዲ ብር 98,474,858.17 ባለመክፈለ በማንኛውም የፍርድ ባለእዲው ንብረት ላይ ተጠሪ የቀደምትነት መብት ስላለው የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሳኔ ተገቢ መሆኑን በመጥቀስ ነው።
በመጀመሪያ አመልካች የአፈፃፀም ትዕዛዝ የተሰጠበት ማሽን ከቀረጥ ነፃ የገባ እና ተመልሶ ከሀገር የሚወጣ ስለሆነ ለተጠሪ የቅድሚያ መብት አይፈጥርም በማለት የሚያቀርበውን መከራከሪያ መመልከቱ ተገቢ ነው። በአመልካች እና በፍ/ባለእዲው መካከል በፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤቱ በነበረው የአፈፃፀም ክርክር መነሻነት ችልቱ ንብረትነቱ የፍ/ባለእዲው የሆነ የአስፊልት ፓቺንግ ፕላንት ማሽን ተሽጦ ለአመልካች እንዱከፈል ለፋደራል ፍ/ቤቶች የአፈፃፀም ዲይሬክቶሬት በሰጠው ትዕዛዝ መነሻነት ዲይሬክቶሬቱ ንብረቱን በሐራጅ ለመሸጥ እንቅስቃሴ ላይ ባለበት ተጠሪ አፈፃፀሙ እንዲይቀጥል አድርጓል በማለት ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ እንዱሰጥበት ጠይቋል። በዚህ መነሻነት ችልቱ ተጠሪ በጉዲዩ ላይ ምላሽ እንዱሰጥ እና በክርክሩ ተሳታፉ እንዱሆን አድርጎ ግራ ቀኙን ሲያከራክር አመልካች ማሽኑ ከቀረጥ ነፃ የገባ በመሆኑ ተጠሪው የቀደምትነት መብት የለውም በማለት ያቀረበው ክርክር የለም።
በመሆኑም በስር ፍ/ቤቶች ያላነሳውን አዱስ መከራከሪያ በዚህ ችልት ሉያነሳ የሚችልበት አግባብ ስለላለ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 329 መሰረት ተቀባይት የለውም። በተጨማሪም ከቀረጥ ነጻ የገባ ንብረት ተመልሶ እስካልወጣ ድረስ ተገቢው የግብር እዲ ተከፍልበት ሀገር ውስጥ የሚቀር በመሆኑ ለግብር እዲ በዋስትና የማይያዝበት የህግ አግባብ የለም።
በቀጣይ መታየት ያለበት ጉዲይ በስር ፍ/ቤቶች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 እና 418 መሰረት ተጠሪ አቤቱታ አቅርቦ አልተከራከረም በማለት አመልካች የሚያነሳው ክርክር ነው። በመሰረቱ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 በክርክሩ ተሳታፉ ያልሆነ አካል በላልች ተከራካሪዎች መካከል በተደረገ ክርክር መብቱን የሚነካ ፍርድ የተሰጠ እደሆነ በድንጋጌው የተጠቀሱ መመዘኛዎችን በማሟላት ፍርደን በመቃወም ለማስለወጥ አቤቱታ የሚያቀርብበትን አግባብ የሚመለከት ሲሆን በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ዋናውን ፍርድ በመቃወም የሚያቀርበው መከራከሪያ በላለበት በዚህ ድንጋጌ መሰረት አቤቱታውን ማቅረብ ነበረበት ልባል አይችልም። በተጨማሪም የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 በፍርድ አፈጻፀም ምክንያት የተከበረ ወይም የተያዘ ንብረት ላይ መብት ወይም ጥቅም አለኝ የሚል አካል የሚያነሳው መከራከሪያ የሚስተናገድበትን አግባብ የሚመለከት ነው። ይህም ድንጋጌ መብት ወይም ጥቅም አለኝ የሚለው ተከራካሪ በክርክሩ ተሳታፉ የሚሆነው የግድ ግለሰቡ ወይም ተከራካሪው በቅድሚያ በራሱ አነሳሽነት በፍርድ ቤት በሚያቀርበው አቤቱታ መነሻነት ብቻ ስለመሆኑ በአስገዲጅነት የሚያስቀምጠው መመዘኛ የለም። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪው በጨረታ እንዱሸጥ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የወጣበት የፍ/ባለእዲው የሆነውን ንብረት በግብር እዲ ዋስትናነት ይዤዋለው በሚል እንዲይሸጥ በማድረጉ ፍ/ቤቱ ጥሪ አድርጎ በጉዲዩ ላይ የግራ ቀኙን ማስረጃ እና ክርክር ሰምቶ ተገቢ ነው የሚለውን ትዕዛዝ ሰጥቷል። በመሆኑም ተጠሪ በዚህ ረገድ የሚያነሳው መከራከሪያ የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
በሶስተኛ ደረጃ ምላሽ ማግኘት ያለበት የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የፍ/ሕ/ቁጥር 2828፣2857 እና 3059 ድንጋጌን የመጥቀሱ አግባብነት ነው። በመሰረቱ ማንኛውም ፍ/ቤት በተከራካሪዎች የሚቀርቡ ክርክሮችን መርምሮ እና የክርክሩን ጉዲይ በመለየት አግባብነት ያለውን የሕግ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ውሳኔ መስጠት ያለበት ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 182 መገንዘብ ይቻላል። በተያዘው ጉዲይ አከራካሪው ነገር በአፈፃፀም በተያዘው የአስፊልት ፓቺንግ ፕላንት ማሽን ላይ ግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የሆነው ተጠሪ የቀደምትነት መብት አለው? ወይስ የለውም? የሚለው ነው። ተጠሪም በንብረቱ ላይ የቀደምትነት መብት አለኝ በማለት የሚያነሳው ክርክር የግብር እዲን መነሻ ያደረገ ስለሆነ ለጉዲዩ በቀጥታ ተፈፃሚነት ያለው የጉምሩክ አዋጁ እና ላልች ግብርን የሚመለከቱ ልዩ ሕጎች ናቸው። ይሁን እንጂ ጉዲዩን ከሚገዙ ልዩ ሕጎች በተጨማሪ እንደ አስፈላጊነቱ ፍ/ቤቱ ለጉዲዩ ተገቢነት ያላቸውን ድንጋጌዎች በማመሳሰል እንዲይጠቀም የሚከለክለው ነገር የለም። በተያዘው ጉዲይ የአስፊልት ፓንቺንግ ፕላንት ማሽኑ ተንቀሳቃሽ ንብረት በመሆኑ እና የቀደምትነት መብት የሚኖረውን ውጤት ለማሳየት የፍ/ሕ/ቁጥር 2828 እና 2857ን መጥቀሱ የሚያስነቅፍ ባይሆንም የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት የፍ/ሕ/ቁጥር 3059 ድንጋጌን በውሳኔው ላይ መጠቀሱ አግባብነት የለውም።
በመጨረሻ አከራካሪ በሆነው የአስፊልት ፓቺንግ ፕላንት ማሽን ላይ ተጠሪ የቀደምትነት መብት አለው ተብል የመወሰኑን አግባብነት መመልከቱ አስፈላጊ ነው። የግንባታ ስራን ለማከናወን ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ተደርገው በጊዜያዊነት ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ እቃዎች ስራው በተጠናቀቀ የ3 ወር ጊዜ ውስጥ ከሀገር ውስጥ ተመልሰው መውጣት ያለባቸው ስለመሆኑ እና ከሀገር ውስጥ በሕግ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ተመልሰው ካልወጡ ወይም በልላ መንገድ ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ አስመጪው አካል ተገቢውን ቀረጥና ታክስ የመክፈል ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ ከጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀፅ 73(3) እና 130 መገንዘብ ይቻላል። የፍርድ ባለእዲው የተጠቀሰውን ማሽን ለግንባታ ስራ ከቀረጥ ነፃ ያስገባው እና ከሀገር ውስጥ ተመልሶ ያልወጣ መሆኑ ግራ ቀኙን አላከራከረም። በተጨማሪም ታክስ በማንኛውም ሁኔታ ያልተከፈለ ወይም ሉከፈል ከሚገባው በታች የተከፈለ መሆኑ በድህረ ኦዱት ምርመራ የተደረሰበት እንደሆነ ባለስልጣኑ ዱክላራሲዮን አቅራቢውን ሉያስከፍለው የሚችል ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 122(1) ላይ ተመላክቷል። በድንጋጌው ንዐስ አንቀፅ 6 መሰረትም ባለእዲው የቀረጥ እና ታክስ እዲውን ያልከፈለ እንደሆነ ባለስልጣኑ በገቢ ግብር አዋጁ የተመለከተውን ንብረት ይዞ የማስፈፀም ስርዓት ተፈፃሚ የሚያደርግ ስለመሆኑ ተመላክቷል። ከዚህም ላላ የታክስ አስተደዲደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀፅ 39(1 እና 2) በሚመለከተው አካል የተመዘገበ ማንኛውም ቀዲሚ ዋስትና የተሰጠበት መብት (ባንኮች ዋስትና የተቀበለባቸው የገንዘብ ጥያቄዎች እና የተቀጣሪዎች የደመወዝ ቅድሚያ መብት) እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በታክስ ሕግ መሰረት ታክስ ከፊዩ መክፈል የሚገባው የመክፈያ ጊዜው የደረሰ ታክስ በሙለ ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ ባለሥልጣኑ በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ የቀደምትነት መብት የሚኖረው ስለመሆኑ ተመላክቷል። ይህም ማንኛውም አካል ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ባስገባቸው እቃዎች በአንደም ሆነ በላልቹ ወይም በልላ ምክንያት የሚፈለግበት መክፈያ ጊዜው የደረሰ የታክስ እዲ መኖሩን ባለስልጣኑ ያረጋገጠ እንደሆነ እዲው ተከፍል እስኪያልቅ በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ የቀዲሚነት መብት ያለው ስለመሆኑ ያረጋግጣል። ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍ/ቤቶች የፍርድ ባለእዲው በጠቅላላው ብር 98,474,858.17 ያልተከፈለ (የበሰለ) የግብር እዲ ያለበት ስለመሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን አመልካችም የገንዘብ መጠኑን ወይም የመክፈያ ጊዜው የደረሰ አለመሆኑን አስመልክቶ በመቃወም ክርክር ቢያቀርብም ክርክሩን የሚደግፍ ማስረጃ አላቀረበም። በታክስ አስተዲደደር አዋጁ አንቀፅ 41(4) (ለ) መሰረት በማናቸውም የፍርድ ሂደት ዕገዲ በተደረገበት ወይም የአፈፃፀም ትዕዛዝ በተሰጠበት ንብረትን ባለስልጣኑ የመያዝ ስልጣን የላለው መሆኑ የተመላከተ ቢሆንም ድንጋጌው ንብረቱን የመያዝ ሁኔታን ብቻ የሚከለክል እንጂ ባለስልጣኑ የግብር እዲውን ለማስከፈል የሚኖረውን የቀደምትነት መብት የሚያሳጣ አይደለም።
በመሆኑም የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የፍርድ ባለእዲው ላለበት ጠቅላላ የግብር እዲ ተጠሪ በባለእዲው ንብረት ላይ የቀዲሚነት መብት አለው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈፀመበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በፍ/ይ/መ/ መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችልት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ ነሐሴ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠውን ብይን ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ትእዛዝ በዚህ መዝገብ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል። ይጻፍ።
No topics extracted.