ጋብቻ በፍቺ ውሳኔ መፍረሱን ተከትል በንብረት ክርክር ወቅት የግል ዕዲ ነዉ ተብል ውሳኔ ያገኘ ዕዲ ፍ/ቤት ቀርቦ ባልተለወጠበት ሁኔታ በባለዕዲው ተጋቢ በኩል ለመጣው እዲ ላላኛው ተጋቢ ተጠያቂነት የላለበት ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 34 (1)፣ የፍደራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 57፣ 70፣ 71፣ 89 እና 93
No summary available.
ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካች፡ ……..ወ/ሮ ቱኒዝ ሙለጌታ- ጠበቃ ብርሃኑ ተሻገር ቀርበዋል ተጠሪዎች፡ ………1. አቶ አብርሃም ከለለዉ- ቀርበዋል 2. አቶ ዲንኤል ይስፈልኝ ጠበቃ ይልማ አቻሜ ቀርበዋል 3. ወ/ሮ እመቤት አድማሱ ይህ መዝገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የባልና ሚስት የጋራ ሀብትና የግል ዕዲን የሚመለከት ክርክር የተጀመረዉ በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር አመልካች፣ የአሁን 1ኛ ተጠሪ የሥር ተጠሪ፣ የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የሥር የመቃወም አመልካቾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.247544 በ20/5/2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ የአሁን አመልካች እና የአሁን 1ኛ ተጠሪ በመካከላቸዉ የነበረዉ ጋብቻ በፍቺ ዉሳኔ መፍረሱን ተከትል አመልካች ባቀረበችዉ የንብረት ዝርዝር በአዱስ አበባ ከተማ አዱስ ከ/ክ/ማ ወረዲ 8 የሱቅ ቁጥር 380 ሸራ ተራ አካባቢ በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉ ለተጠሪ የግል እዲ በሐራጅ የተሸጠ ስለሆነ ንብረቱ የጋራ ሀብታችን በመሆኑ የሽያጭ ገንዘቡ ግማሽ ድርሻዬ እንዱወሰንልኝ በማለት ያመለከተች ሲሆን፤ የአሁን 1ኛ ተጠሪ በበኩለ ባቀረበዉ ክርክር በፍርድ የተረጋገጠዉ ዕዲ የባልና ሚስት እዲ ስለሆነ እዲዉ ተከፍል የሚተርፍ ገንዘብ ካለ እኩል ልንካፈል ይገባል እንጂ እዲዉ ሳይከፈል ግማሽ ድርሻ እንዱወሰንልኝ በማለት ያቀረበችዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን በማጣራት በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን 1ኛ ተጠሪ የተባለዉ እዲ መጠንና ባለገንዘቦቹ እነማን እንደሆኑ፣ ከአመልካች ጋር የጋራ ዕዲቸዉ መሆኑን በማስረጃ ያስረዲዉ ነገር ስለላለ ከተያዘዉ ገንዘብ ላይ ግማሹ የአሁን አመልካች ድርሻ ነዉ በማለት ወስኗል።
ይህን ዉሳኔ ተክትል የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት የመቃወሚያ ማመልከቻ ያቀረቡ ሲሆን፣ የአሁን 2ኛ ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ለንግድ ሥራቸዉ ምክንያት ህዲር 15 ቀን 2005 ዓ.ም የሚመነዘር ቼክ ብር 350,000 ጽፈዉ ሰጥቶኝ በቂ ስንቅ ስለላለዉ ክስ አቅርቤ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.246856 በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ገንዘቡን ከተለያየ ወጪና ወለድ ጋር እንዱከፍለ የተወሰነባቸዉ ስለሆነ ከአመልካች ጋር የጋራ ዕዲቸዉ በመሆኑ የጋራ ንብረታቸዉ ተሽጦ ከተቀመጠዉ ገንዘብ ዉስጥ እዲዉ አስቀድሞ እንዱከፈልኝ፣ ዉሳኔዉ እንዱነሳልኝ በማለት አመልክቷል። የአሁን 3ኛ ተጠሪ በበኩለ ባቀረበዉ አቤቱታ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ለንግድ ሥራቸዉ ምክንያት ብር 300,000 መጋቢት 20 ቀን 2004 ዓ.ም የሚመነዘር ቼክ ጽፈዉ ሰጥተዉኝ በቂ ስንቅ ስለላለዉ ክስ አቅርቤ የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.246809 በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ይህን ገንዘብ ከወለድና ከተለያዩ ወጪዎች ጋር እንዱከፍለኝ ስለወሰነበት፣ እዲዉ ከአመልካች ጋር የጋራ እዲዉ ስለሆነ ይህን ገንዘብ እንዱከፍለኝ እንዱወሰንልኝ፣ ዉሳኔዉ እንዱሻሻልን በማለት አመልክቷል።
የአሁን አመልካች በዚህ የመቃወም ማመልከቻ ላይ በሰጠችዉ መልስ የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የጠቀሱት እዲ የተወሰነዉ በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ ነዉ፣ እዲዉ ከጋብቻዉ በፉት 1ኛ ተጠሪ የገባዉ ነዉ፣ እዲዉ እኔን የሚመለከት አይደለም በማለት ተከራክራለች። የአሁን 1ኛ ተጠሪ በበኩለ የተጠቀሰዉ እዲ በትዲር ዉስጥ የተፈጠረ ስለሆነ የጋራ እዲ ነዉ በማለት ተከራክሯል።
የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በዚህ ላይ በሰጡት መልስ ይህ እዲ የተፈጠረዉ የአሁን አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በጋብቻ ዉስጥ እያለ በመሆኑ በቤተሰብ ሕጉም ሆነ በንግድ ሕጉ የጋራ እዲቸዉ ነዉ በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች እዲን በተመለከተ በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ ዉሳኔ ያሰጡበትን መዛግብት በማየት የአሁን 1ኛ ተጠሪ ለአሁን 2ኛና 3ኛ ተጠሪዎች እንዱከፍል የተወሰነበት እዲ የግል እዲ ነዉ ወይስ ከአሁን አመልካች ጋር የጋራ እዲቸዉ ነዉ? የሚለዉን ጭብጥ በመያዝ በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.246856 በሆኑት መዝገቦች ለዉሳኔ መሰረት የሆኑት ሁለቱም ቼኮች የተጻፈባቸዉ ቀን የአሁን አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ጋብቻ ከፈጸሙ በኋላ ሲሆን፣ የአሁን አመልካች ይህን የሚያስተባብል ማስረጃ በማቅረብ ያስረዲችዉ ነገር የለም፤ በፋዳራለ የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 70 (1) መሰረት ከአሁን 1ኛ ተጠሪ የግል ሀብት የሚጠየቅ ቢሆንም ይህን ዕዲዉን ለመሸፈን በቂ ካልሆነ ከአሁን አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የጋራ ሀብት ላይ ከ1ኛ ተጠሪ ድርሻ እንዱከፈል፤ ይህም ዕዲዉን የማይሸፍን ከሆነ ከአሁን አመልካች ድርሻ እንዱከፈል በማለት ወስኗል። የአሁን አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበች ቢሆንም ፍ/ቤቱም ቅሬታዉን አያስቀርብም በማለት የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማሻር ነዉ።
የአሁን አመልካች በ28/5/2012 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የመቃወሚያ ማመልከቻ ያቀረቡበት ፍርድ መብታቸዉን የማይነካ ሆኖ ሳለ የሥር ፍ/ቤቶች አቤቱታቸዉን በመቀበል የሰጡት ዉሳኔ ሉታረም ይገባል። የሥር ፍ/ቤት በፍርደ እንዲረጋገጠዉ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በ1ኛ ተጠሪ ላይ ያስፈረደት እዲ የ1ኛ ተጠሪ የግል እዲ እንጂ አመልካችን የሚመለከት አይደለም። ዕዲዉ የአሁን 1ኛ ተጠሪ የግል እዲ ነዉ ተብል በፍርድ ተረጋግጦ እያለና እዲዉ ለትዲር ጥቅም መዋለ ፍርድ ባልተሰጠበት እዲዉ ከአመልካች የግል ሀብት እንዱከፈል መባለ ተገቢ አይደለም። የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.246856 ላይ የሰጠዉ ዉሳኔ 1ኛ ተጠሪ በሰጠዉ ቼኮች ስለሆነ አመልካችን አይመለከትም፤
በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል በነበረዉ ክርክር 1ኛ ተጠሪ እዲ መኖሩን ጠቅሶ የተከራከረ ቢሆንም በማስረጃ ማስረዲት ባለመቻለ ዉድቅ ተደርጎበታል። እነዚህ ቼኮች ለክፍያ ያቀረቡት ጋብቻችን ከፈረሰ እና ቼኮቹ ለክፍያ መቅረብ ከሚገባቸዉ ጊዜ የ2ኛ ተጠሪ 3 ዓመት ከ11 ወር በኋላ እና የ3ኛ ተጠሪ 4 ዓመት ከ7 ወር ካለፈ በኋላ የቀረቡና የክፍያ ጊዜያቸዉ ያለፈባቸዉ ሆኖ ሳለ፣ 1ኛ ተጠሪ በእነዚህ ቼኮች የቀረበዉን ክስ በተመለከተ በቂ መከላከያ እያለዉ ማስፈቀጃ ሳያቀርብና ሳይከራከር ዉሳኔ እንዱሰጥበት ሆኗል። 1ኛ ተጠሪ በእነዚህ ቼኮች በወንጀል ተከሶ የተቀጣ ሆኖ ሳለ፣ አሁን የቀረበዉ ክርክርና የተሰጠዉም ፍርድ የአመልካችን ጥቅም ለመጉዲት ሆን ተብል የተጻፈ ቼክ መሰረት ተደርጎ የተሰጠ ዉሳኔ ነዉ። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልኝ አመልካች እዲዉን ልትከፍል አይገባትም ተብል እንዱወሰንልኝ ወጪና ኪሳራም እንዱወሰንልኝ በማለት ተከራክራለች።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣በሥር ፍ/ቤት ክርክር ያስነሳዉ እዲ የግለ ነዉ ተብል ከተወሰነ በኋላ የባለእዲዉ ሀብት እዲዉን የማይሸፍን ከሆነ አመልካች ትክፈል የተባለበት እና ከጋብቻ ፍቺ በኋላ የቀረበ እዲም የግል ነዉ ተብል ከተወሰነ የጋራ የሚሆንበት አግባብነት፣ ለማጣራት ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ታዟል።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ ባቀረበዉ መልስ ለክርክር መነሻ የሆነዉ ሱቅ ከአመልካች ጋር ጋብቻ ዉስጥ ያፈራነዉ ንብረት በመሆኑ፣ ቼኩም ከአመልካች ጋር በጋብቻ ዉስጥ ለእያንዲንደ እቃዎች መግዣ በደቤ ስንጠቀምበት የነበረዉ ስለሆነ እዲዉ የአመልካችም ጭምር ነዉ በማለት ተከራክሯል።
የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪ ህዲር 3 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ ተጠሪዎች በ1ኛ ተጠሪ ላይ በቼክ ጉዲይ ክስ አቅርበን በመ.ቁ.246856 ላይ አስወስነንበታል። ይህ እዲ የአመልካችና የ1ኛ ተጠሪ የጋራ እዲቸዉ ስለሆነ የጋራ ሀብታቸዉ ከመከፊፈላቸዉ በፉት እዲዉ መከፈል አለበት። ይህ እዲ በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ በትዲር ዉስጥ እያለ የተፈጠረ እዲ በመሆኑ ከ1ኛ ተጠሪ የግል ሀብት፣ ይህ ካልሆነ ከጋራ ንብረታቸዉ ለ1ኛ ተጠሪ የሚደርሰዉ ድርሻ፣ ይህም እዲዉን ለመክፈል በቂ ካልሆነ ከአመልካች ድርሻ እንዱከፈል ተወስኗል። 1ኛ ተጠሪ ነጋዳ የነበሩ በመሆናቸዉ እና አመልካችና 1ኛ ተጠሪ በትዲር ዉስጥ እያለ የተገባ እዲ በመሆኑ፣ በቼክ ክርክር የተሰጠዉ ዉሳኔ አለመሻሩን በመገንዘብ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ የሚነቀፍበት የሕግ አግባብ ስለላለ፣ አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለዉም ተብል፣ የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ እንዱጸናልን በማለት ተከራክሯል። የአሁን አመልካች ተጠሪዎች ያቀረቡት መልስ ተቀባይነት የለዉም የምትልባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር የሰበር አቤቱታዋን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርባለች።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙ ክርክር፣ የሥር ፍ/ቤቶች የተሰጡት ዉሳኔ እና ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምሮታል። በዚህ መሰረት እንደመረመርነዉ፡
የአሁን አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በ5/5/2004 ዓ.ም ጋብቻ ፈጽመዉ ባልና ሚስት ሆነው አብረዉ ሲኖሩ ቆይተዉ፤ የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.53007 በ26/4/2008 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ የአመልካች እና የ1ኛ ተጠሪ ጋብቻ በፍቺ ዉሳኔ እንዱፈርስ መወሰኑን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የነበራቸዉ ጋብቻ በዉሳኔ ከፈረሰ በኋላ የፍቺ ዉጤትን በተመለከተ የጋራ ንብረት እንዱያካፍላት የጠየቀች ሲሆን፤ በዚህ መሰረት በአዱስ አበባ አዱስ ከ/ክ/ከተማ ወረዲ 8 ዉስጥ የሚገኘዉ የሱቅ ቁጥር 380 የአመልካች እና የ1ኛ ተጠሪ የጋራ ሀብታቸዉ መሆኑ ያላከራከረ ጉዲይ ነዉ። በመሆኑም የዚህ ሱቅ የሽያጭ ገንዘብ በፋደራለ የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 213/1992 አንቀጽ 62 (1) መሰረት የአመልካች እና የ1ኛ ተጠሪ የጋራ ሀብታቸዉ እስከሆነ ድረስ፣ ንብረቱ በዚህ ሕግ አንቀጽ 90 መሰረት ለሁለቱም እኩል የሚከፊፈል ይሆናል። ይህ መብት ሕግ ከዘረጋዉ አግባብ ዉጭ ሉሸራረፍ እና የአንደኛዉን ተጋቢ የጋራ ሀብት የመካፈል መብት የሚነፍግ ሁኔታ መኖር እንደላለበት መገንዘብ ያስፈልጋል።
አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ መካከል በነበረዉ የንብረት ክፍፍል ክርክር፣ የአሁን አመልካች የጋራ ንብረታችን እንድንካፈል በማለት ዲኝነት የጠየቀች ሲሆን፤ 1ኛ ተጠሪ በበኩለ የጋራ ንብረት መኖሩን በማመን ተከራክሮ፣ ባልና ሚስት በትዲር ዉስጥ በአንደ በፍርድ ዕዲ መኖሩ ከተረጋገጠ የባልና ሚስት ንብረት ከመከፊፈለ በፉት እዲዉ መከፈል አለበት በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤ የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.53007 በ23/5/2008 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ 1ኛ ተጠሪ የጋራ እዲ ስላለብን ቅድሚያ መከፈል አለበት ከማለት ዉጭ እዲዉ ምን ያህል እንደሆነ መጠኑን ጠቅሰዉ ባለገንዘቦቹ እነማን እንደሆኑ በጽሁፍም ሆነ በቃል ተብራርቶና ግልጽ ተደርጎ በማስረጃ ተደግፍ የቀረበ ነገር የላለ በመሆኑ፣ 1ኛ ተጠሪ የጋራ እዲ አለብን ስለሆነም እዲዉ በቅድሚያ እንዱከፈል ዉሳኔ እንዱሰጥልኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ የትኛዉ እዲ እንደሆነ ስለማይታወቅ የሕግና የማስረጃ ድጋፍ የላለዉ ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም በማለት ወስኗል። ከዚህ ዉሳኔ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለዉ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በትዲር ዉስጥ በነበረን ጊዜ የጋራ እዲ አለብን በማለት 1ኛ ተጠሪ ያቀረበዉ ክርክር በፍ/ቤት ተጣርቶ በተሰጠዉ ፍርድ ተቀባይነቱ የቀረ በመሆኑ፣ አመልካች በተጠሪዉ በኩል ለሚመጣዉ እዲ ተጠያቂ የምትሆንበት አግባብ አይኖርም። የአሁን 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በጋብቻ ዉስጥ በነበረን ጊዜ የጋራ እዲ አለብን በማለት ይህን ዉሳኔ የሚቃወም ከሆነ በሕግ ስልጣን ለተሰጣቸዉ በየደረጃዉ ላለት ፍ/ቤቶች ቅሬታዉን አቅርቦ ዉሳኔዉን ማስለወጡን የሚያሳይ ነገር የለም። የአሁን 1ኛ ተጠሪ በዚህ አግባብ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ስልጣን ላለዉ ፍ/ቤት ቅሬታዉን አቅርቦ ያስለወጠዉ ነገር በላለበት አሁን ለተነሳዉ ክርክር ከአመልካች ጋር በጋብቻ በነበርን ጊዜ የጋራ እዲ ስላለብን የጋራ ንብረታችን ከመከፊፈለ በፉት እዲዉ መከፈል ይገባዋል በማለት የሚያቀርበዉ ክርክር ተቀባይነት ሉኖረዉ የሚችልበት አግባብ የለም።
በልላ በኩል የአሁን 2ኛ ተጠሪ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.246856 ላይ በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ ከቼክ ጋር በተያያዘ ጥቅምት 24 ቀን 2009 ዓ.ም በተፊጠነ ሥነሥርዓት ባቀረበዉ ክስ 1ኛ ተጠሪ ህዲር 15 ቀን 2005 ዓ.ም የሚመነዘር ቁጥሩ BT 1873998 በሆነዉ ቼክ ብር 350,000 ጽፈዉ ለ2ኛ ተጠሪ የሰጠ ስለሆነ ባንክ ሲጠየቅ በቂ ገንዘብ የላለዉ መሆኑ ስለተረጋገጠ ገንዘቡን ከነወለድና ወጪ ጋር እንዱከፍለኝ እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱም 1ኛ ተጠሪ መጥሪያ ተቀብል ለመከላከል ስላልጠየቀ መልስ የማቅረብ መብቱን በማለፍ በ29/3/2009 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ 1ኛ ተጠሪ ብር 350,000 ቼኩ ለባንክ ለክፍያ ከቀረበበት ከ28/2/2009 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ለ2ኛ ተጠሪ እንዱከፍል በማለት ወስኗል። የአሁን 3ኛ ተጠሪ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.246809 ላይ በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ ከቼክ ጋር በተያያዘ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓ.ም በተፊጠነ ሥነሥርዓት ባቀረበችዉ ክስ 1ኛ ተጠሪ መጋቢት 20 ቀን 2004 ዓ.ም የሚመነዘር ቁጥሩ BT 1575795 በሆነዉ ቼክ ብር 300,000 ጽፈዉ ለ3ኛ ተጠሪ የሰጠ ስለሆነ ባንክ ሲጠየቅ በቂ ገንዘብ የላለዉ መሆኑ ስለተረጋገጠ ገንዘቡን ከነወለድና ወጪ ጋር እንዱከፍለኝ እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት የጠየቀች ሲሆን፤ ፍ/ቤቱም 1ኛ ተጠሪ መጥሪያ ተቀብል ለመከላከል ስላልጠየቀ መልስ የማቅረብ መብቱን በማለፍ የካቲት 24 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ 1ኛ ተጠሪ ብር 300,000 ቼኩ ለባንክ ለክፍያ ከቀረበበት ከ3/13/2008 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ እና ከወጪዎች ጋር ለ3ኛ ተጠሪ እንዱከፍል በማለት ወስኗል። እንደሚታወቀዉ ከንግድ ሕግ አንቀጽ 854 ድንጋጌ ማየት እንደሚቻለዉ ቼክ እንደቀረበ የሚከፈልበት ሲሆን በዚህ ሕግ አንቀጽ 855 መሰረት ቼክ የወጣበት ቀን ከግምት ዉስጥ ሳይገባ በቼኩ ላይ የተጻፈዉ ቀን አንስቶ በሚከተለት ስድስት ወራት ዉስጥ እንዱከፈልበት መቅረብ እንዲለበት ተደንግጓል። ከፍ ሲል በተጠቀሱት መዛግብት ላይ የተሰጠዉ ዉሳኔ ይዘት ሲታይ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ራሱ ቼኩን ፈርሞ ለተጠሪዎች የሰጠ ሲሆን ቼኩን መሰረት አድርጎ ለቀረበዉ ክስ ደግሞ በሕግ አግባብ ለመከላከል ማስፈቀጃ በማቅረብ የመከላከያ መልሱን አቅርቦ ሳይከላከልና ሳይከራከር ዉሳኔ የተሰጠ መሆኑን ያሳያል። እንዱሁም አሁን በግራ ቀኙ መካከል በተያዘዉ ክርክር የአሁን 1ኛ ተጠሪ ቼኩን ለምን ዓላማ ፈርሞ ለ2ኛ እና ለ3ኛ ተጠሪዎች ሉሰጣቸዉ እንደቻለ በሕግና በማስረጃ አስደግፍ ያረጋገጠዉ ነገር እንደላለ የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። ይልቁንም ፍ/ቤቶች በሰጡት ዉሳኔ 1ኛ ተጠሪ ለ2ኛ እና ለ3ኛ ተጠሪዎች ፈርሞ በሰጣቸዉ ቼኮች ምክንያት የመጣዉ እዲ የግል እዲዉ መሆኑን በማረጋገጥ ዉሳኔ ማሳለፊቸዉን ነዉ።
እንደሚታወቀዉ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 34 (1) ሥር እንደተደነገገዉ ጋብቻ ፈጽመዉ ቤተሰብ የሚመሰርቱ ወንድችና ሴቶች በጋብቻ አፈጻጸም፣ በጋብቻዉ ዘመንና በፍቺ ጊዜ እኩል መብት እንዲላቸዉ ያስገነዝባል። በመሆኑም ፍ/ቤትም ሆነ ማንኛዉም አካል ከተጋቢዎች ጋብቻ ጋር በተያያዘ ለሚወስደት እርምጃም ሆነ ለሚሰጡት ዉሳኔ ይህን የሕገ መንግስታዊ መርህን ባከበረና ባስጠበቀ መልኩ መፈጸም የሚገባዉ ጉዲይ ነዉ።
በዚህ መሰረት ባልና ሚስት በትዲራቸዉ ዘመን የጋራ ሀብታቸዉን በተመለከተ እና ከፍቺ ዉጤት ጋር በተያያዘ የጋራ ንብረት ክፍፍል አስመልከቶ መወሰን የሚገባዉ በሕገ መንግስቱ የተመለከተዉን የእኩልነት መርህ በጠበቀና ባከበረ አግባብ መሆን አለበት።
በፋዳራል መንግስት ደረጃ ጋብቻ በንብረት በኩል የሚያስከትለዉ ዉጤት በፋደራለ የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 57 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች አግባብ የሚመራ መሆኑ ተመልክቷል። በዚህ በፋደራለ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 70፣ 71፣ 89 እና 93 ድንጋጌዎች ሥር ደግሞ የባልና ሚስት እዲን የሚመለከቱ ጉዲዮች ተመልክቷል። በእነዚህ ድንጋጌዎች የባልና ሚስት የግል እዲ እና የጋራ እዲ በምን አግባብ መታየት እንደሚገባዉ ተደንግጎ እናገኛለን። በዚህ ሕግ አንቀጽ 70 (1) መሰረት ከባል ወይም ከሚስት በግል የሚጠየቅ ዕዲ፣ ከባለዕዲዉ ተጋቢ የግል ሀብት፣ የግል ሀብቱ ዕዲዉን ለመሸፈን በቂ በማይሆንበት ጊዜ ከጋራ ሀብታቸዉ ይከፈላል በማለት ተደንግጎ እናገኛለን።
በዚሁ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 89 ሥር እንደተመለከተዉ ከባልና ሚስት አንደኛዉ ወይም ሁለቱም በጋራ በፍርድ የተረጋገጠባቸዉ ወይም ሁለቱም ያመኑት ዕዲ መኖሩ የታወቀ እንደሆነ፣ ይኸዉ ዕዲ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ከመከፊፈለ በፉት ተቀንሶ የሚከፈል እንደሆነ ይደነግጋል። በዚህ ሕግ አንቀጽ 93 ሥር ደግሞ ጋብቻዉ ከፈረሰ በኋላ ከባልና ሚስት ስለሚጠየቅ ዕዲ ያመለክታል።
በመሆኑም የአሁን 1ኛ ተጠሪ የግል ዕዲዉ የሆነዉ ከፍ ሲል በተጠቀሱት ምክንያቶች ከአመልካች ጋር የጋራ ዕዲቸዉ የሚሆንበት አግባብ ባለመኖሩ በፋደራለ የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 70 (1) መሰረት ከጋራ ሀብታቸዉ ከአመልካች ድርሻ ላይ የሚከፈልበት ምክንያት አይኖርም። የሥር ፍ/ቤቶች በ1ኛ ተጠሪ ላይ የተወሰነዉ የግል ዕዲዉ ሆኖ እያለ እና አመልካች ለዕዲዉ ተጠያቂ የምትሆንበት አግባብ ሳይኖር፣ ከጋራ ንብረታቸዉ ከሆነ የሱቅ ቁጥር 380 የሽያጭ ገንዘብ የአመልካች ግማሽ ድርሻ የሚከፈልበት አግባብ ሳይኖር፣ ለዕዲዉ ክፍያ የ1ኛ ተጠሪ የግል ሀብትና ከጋራ ሀብቱ የእሱ ድርሻ ያልበቃ እንደሆነ፣ ከአመልካች ድርሻ መከፈል አለበት በማለት የሰጡት ዉሳኔ ከፍ ሲል የተጠቀሱት የሕግ ድንጋጌዎች የሚቃረን ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ የግል ዕዲ ከጋራ ንብረት ከግማሽ ድርሻዋ ለመክፈል ኃላፉነት ሳይኖርባት፣ ከጋራ ንብረት ከሆነዉ የሱቅ ቁጥር 380 የሽያጭ ገንዘብ ግማሹን ተካፍላ የመዉሰድ መብት እያለት፣ አመልካች ግማሽ ድርሻዋን ከመዉሰዶ በፉት አስቀድሞ ዕዲዉ መቀነስ አለበት በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.53007 በ2/4/2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.247544 በ20/5/2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት በአብላጫ ድምፅ ተሻሽሎል።
የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በ1ኛ ተጠሪ ላይ ክስ አቅርበዉ ያስወሰኑት ዕዲ የ1ኛ ተጠሪ የግል ዕዲ ሆኖ ሳለ ከአመልካች ጋር የጋራ ዕዲቸዉ ነዉ ተብል አመልካች ከሚደርሳት የንብረት ግማሽ ድርሻ ላይ አስቀድሞ ዕዲዉ መከፈል አለበት በማለት የሰጡት የዉሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን 1ኛ ተጠሪን በተመለከተ የሰጡት የዉሳኔ ክፍል አልተነካም ጸንቷል።
የአሁን አመልካች የ1ኛ ተጠሪን የግል ዕዲ ከጋራ ንብረት ግማሽ ድርሻዋ ለመክፈል ኃላፉነት የለበትም፣ ዕዲዉ አመልካች አይመለከታትም ብለናል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ይህ ችልት በ9/7/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.53007 የተጀመረዉ የአፈጻጸም ክርክር እንዱታገድ የሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
የመ.ቁ.246856 ለፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችልት ይመለሱ። የመ.ቁ.53007 ለፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ኮ/ቀራንዮ ምድብ ችልት ይመለስ።
No topics extracted.