በባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር ወቅት ድብቅ የጦር መሳሪያ መኖሩ እስከተረጋገጠ ድረስ በሕግ አግባብ ስልጣን ባለዉ አካል አለመመዝገቡ መሳሪያዉ የለም የሚያስብል ሳይሆን የኢኮኖሚ ጥቅም ያለዉ እና ባልና ሚስት በትዲር እያለ ያፈሩት እስከሆነ ድረስ ከሚመለከተዉ አካል ተመዝግቦ መሳሪያዉን ለመያዝ ፈቃድ አለመሰጠቱ፣ የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት እንዲይሆን የማያደርገዉ ስለመሆኑ የአማራ ክልል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 79/1995 አንቀጽ 73 (1) እና
No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- 1.ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2.ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካች፡- አቶ ካሳ በለጠ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሥራይቱ ነጋሽ ይህ መዝገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር የተጀመረዉ በባህርዲር ዙሪያ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ፍ/ቤት በመ.ቁ.83938 ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የአሁን ተጠሪ ከአሁን አመልካች ጋር በነበረን ጋብቻ ዉስጥ ያፈረናቸዉ ንብረቶች እንዱያካፍለኝ በማለት ዘርዝራ ካቀረበቻቸዉ መካከል አጭር ሚኒሽር መሳሪያ የጋራ ሀብታችን ስለሆነ የአሁን አመልካች እንዱያካፍለኝ በማለት ዲኝነት ጠይቃለች።
የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ላይ ባቀረበዉ ከአሁን ተጠሪ ጋር ያፈራነዉ አጭር ሚኒሽር መሳሪያ የለም ሐሰት ነዉ፣ ላልች ንብረቶችን በተመለከተ ክርክሩን አቅርበዋል።
ከዚህ በኋላ የሥር የወረዲዉ ፍ/ቤት ጉዲዩን በመመርመር የሚኒሻ ጽ/ቤት ስለመሳሪያዉ አጣርቶ እንዱልክ በታዘዘዉ መሰረት አጭር ሚኒሽር መሳሪያ በአሁን አመልካች ስም ተመዝግቦ እንደላለ የገለጸዉን እና የሰዉ ምስክሮች በመስማት በሰጠዉ ዉሳኔ አጭር ሚኒሽር የጦር መሳሪያ መኖሩ በማስረጃ ያልተረጋገጠ ስለሆነ የአሁን ተጠሪ ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም፣ በላልች ንብረቶች እና በልጆች ቀለብ ጋር በተያያዘ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ ሰጥቷል። የአሁን ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለባህርዲር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበች ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን በትዕዛዝ ዉድቅ በማድረግ የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን ተጠሪ አሁንም በዚህ ዉሳኔ እና ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበች ሲሆን ችልቱ ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበትን መሬት እና ባህርዛፍ በተመለከተ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት፤
አጭር ሚኒሽር የጦር መሳሪያ በተመለከተ ግን የአሁን ተጠሪዎች የሰዉ ምስክሮች በሰጡት የምስክርነት ቃል የአሁን አመልካች ድብቅ አጭር ሚኒሽር የጦር መሳሪያ ያለዉ መሆኑን ያስረደ ስለሆነ፣ ይህ መሳሪያ ድብቅ በመሆኑ አለመመዝገቡ መሳሪያዉ የለም የሚያሳኝ ስላልሆነ፣ የአሁን አመልካች ይህን መሳሪያ ለአሁን ተጠሪ ሉያካፍላት ይገባል፣ የሚኒሽር የጦር መሳሪያ ግምት ብር 10,000 ስለሆነ ይህን መሳሪያ እጣ በማጣጣል በእጣዉ አጭር ሚኒሽር መሳሪያዉ የደረሰዉ ለላለዉ ብር 5,000 እንዱከፍልና አጭር ሚኒሽር የጦር መሳሪያ እንዱወስድ በማለት በዚህ ረገድ የሥር ፍ/ቤቶችን ዉሳኔ በመሻሻል ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለመሻር ነዉ።
የአሁን አመልካች በ22/9/2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ ለክርክር መነሻ የሆነዉ አጭር ሚኒሽር መሳሪያ በስሜ ተመዝግቦ እንደማይገኝ የሚኒሻ ጽ/ቤት ገልጾ እያለ የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የአሁን ተጠሪ የሰዉ ምስክሮች ዘመድ አዝማድ ሆኖ በሀሰት በሰጡት የምስክርነት ቃል ድብቅ መሳሪያ አለ በሚል ተጠሪ እንድትካፈል በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ የህግ ግድፈት ያለበት ስለሆነ እንዱሻርልኝ በማለት አመልክቷል።
ይህ ችልት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንደትሰጥ ባዘዘዉ መሰረት በ15/6/2012 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ የሥር ፍ/ቤት አከራካሪዉን የጦር መሳሪያ እኩል እንካፈል የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ ስለሆነ እንዱጸናልኝ በማለት ተከራክራለች። የአሁን አመልካች የመልስ መልስ ስላላቀረበ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተጠቀሰዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በዚህ ጉዲይ ምላሽ ማግኘት ያለበት ፣የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ለክርክር ምክንያት የሆነዉ አጭር ሚኒሽር የጦር መሳሪያ የጋራ ሀብት ስለሆነ ግራ ቀኙ እንዱካፈለ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ መሆኑን ተገንዝበናል። የአሁን ተጠሪ ባቀረበችዉ ክስ አጭር ሚኒሽር የጦር መሳሪያ የጋራ ሀብታችን ስለሆነ እንዱያካፍለኝ በማለት የጠየቀች ሲሆን፣ አመልካች በበኩለ ይህ የጦር መሳሪያ የለም በማለት ተከራክሯል። የሚኒሻ ጽ/ቤት በጻፈዉ ደብዲቤ አጭር ሚኒሽር የጦር መሳሪያ በአሁን አመልካች ስም ተመዝግቦ እንደላለ ገልጾዋል። በልላ በኩል የአሁን ተጠሪ የሰዉ ምስክሮች በሰጡት የምስክርነት ቃል የአሁን አመልካች ድብቅ አጭር ሚነሽር የጦር መሳሪያ እንዲለዉ መመስከራቸዉን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። በመሆኑም የአሁን ተጠሪ ለክርክር ምክንያት የሆነዉ ድብቅ አጭር ሚኒሽር የጦር መሳሪያ ያለዉ በመሆኑ ባይመዘገብም መሳሪያዉ መኖሩን የሰዉ ምስክሮች የመሰከሩ ሲሆን፣ በአመልካች በኩል የቀረቡት የሰዉ ምስክሮች ስለዚህ መሳሪያ ያለት ነገር አለመኖሩን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። ይህ ማለት የአሁን አመልካች ድብቅ አጭር ሚኒሽር የጦር መሳሪያ ያለዉ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ መሳሪያዉ በሕጉ አግባብ ስልጣን ባለዉ የሚኒሻ ጽ/ቤት ዘንድ አለመመዝገቡ መሳሪያዉ የለም የሚያስብል አይደለም። ይህ ሚኒሽር የጦር መሳሪያ መኖሩ እስከተረጋገጠ ድረስ በሕጋዊ መንገድ ስለመያዙ ከሚመለከተዉ አካል ዘንድ ተመዝግቦ ፈቃድ አለመሰጠቱ መሳሪያዉ የለም እና የኢኮኖሚ ዋጋ የለዉም የሚያስብል ነገር አይሆንም። ይህ የጦር መሳሪያ የኢኮኖሚ ጥቅም ያለዉ መሆኑን በመገንዘብ የአማራ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት በ2007 ዓ.ም ባወጣዉ የጦር መሳሪያ ዋጋ ተመን ማሻሻያ መሰረት የሚኒሽር የጦር መሳሪያ ግምቱ ብር 10,000 መሆኑን አመልክቷል። ይህ የጦር መሳሪያ የኢኮኖሚ ጥቅም ያለዉ ንብረት እና ባልና ሚስት ይህን መሳሪያ በትዲር እያለ ያፈሩ እስከሆነ ድረስ፣ ከሚመለከተዉ አካል ዘንድ መሳሪያዉ ተመዝግቦና መሳሪያዉን ለመያዝ ፈቃድ አለመሰጠቱ፣ የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት እንዲይሆን የሚያደርገዉ እና ጋብቻቸዉ በፍቺ ሲፈርስ የሚካፈለት ንብረት አይሆንም የሚያስብል አይደለም። ይህም ከአማራ ክልል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 79/1995 አንቀጽ 73 [1] እና 101 አንጻር ማየት ይቻላል። ስለሆነም ለክርክር መነሻ የሆነዉ አጭር ሚኒሽር የጦር መሳሪያ መኖሩ በማስረጃ እስከተረጋገጠ ድረስ፣ ግራ ቀኙ ይህን ንብረት እንዱካፈለ መባለ ተገቢ ነዉ። ይህ ችልት በኢ.ፋ.ዳ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 80 [3፣ ሀ] እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ከተሰጠዉ ስልጣን አንጻር የአሁን አመልካች ያቀረበዉ ቅሬታ የሥር ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆኑን የሚያስገነዝብ ስላልሆነ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ለክርክር መነሻ የሆነዉ አጭር ሚኒሽር የጦር መሳሪያ የግራ ቀኙ የጋራ ሀብት ስለሆነ እኩል እንዱካፈለ በማለት የክፍፍል ሥርዓቱን በማመልከት የሰጠዉ ዉሳኔ በሕጉ አግባብ የተሰጠ እንጂ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ፍ/ቤት በመ.ቁ.83938 ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 [1] መሰረት ጸንቷል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.