አስቀድሞ ከዉርስ ንብረት የተቀበለ ወራሽ የዉርስ ክፍፍል ፊይል ሲከፈት የዉርስ ሀብቱን ለመዉረስ ካልጠየቀ አስቀድሞ የወሰደዉን ንብረት ወደ ዉርስ ሀብት መልሶ ለመዉረስ የሚገደድበት አግባብ የላለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1073 እና ተከታዮቹ እነ አቶ ምንዲዬ አስታጥቄ (2 ሰዎች) እና እነ ወ/ሮ በላይነሽ አስታጥቄ (5 ሰዎች)
No summary available.
ሚያዚያ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካቾች፡ ……..1. አቶ ምንዲዬ አስታጥቄ 2. አለሚቱ አስታጥቄ ቀርበዋል ተጠሪዎች፡ ……….1. ወ/ሮ በላይነሽ አስታጥቄ 2. ብርቱካን አስታጥቄ 3. ጌጤ አስታጥቄ ተወካይ ወ/ሮ አለሜ ነገሰ ቀርበዋል 4. ደነቀ አስታጠቄ 5. ናትናኤል አስታጥቄ ይህ መዝገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የዉርስ መሬት ክርክር የተጀመረዉ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በሄጦሳ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካቾች የሥር 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር ከሳሾች፣ በዚህ ችልት የክርክሩ ተካፊይ ያልሆኑ ባሻዉ አስታጥቄ እና ዲምጦ አስታጥቄ የሥር 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካቾች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.3095 በ19/5/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሾች (የአሁን ተጠሪዎች) በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ወላጅ አባታችን አቶ አስታጥቄ ረታ በ2008 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን የሟች የዉርስ ይዞታ የሆነዉን 8 ገመድ የእርሻ መሬት የተለያየ መጠን ተከሳሾች ይዘዉ ስለሚገኙ አንድ ላይ ተመልሶ ለወራሾች ክፍፍል እንዱደረግልን እንዱወሰን በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
የሥር 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች (የአሁን አመልካቾች) በዚህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ አባትና እናታችን በ1987 ዓ.ም አንድ አንድ ገመድ የእርሻ መሬት ሰጥተዉን እስካሁን እየተጠቀምንበት ያለን ስለሆነ ልንጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክሯል። የሥር 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾችም በሰጡት መልስ አባትና እናታችን በ1998 ዓ.ም አንድ አንድ ገመድ የእርሻ መሬት ሰጥተዉን ለአስራ ሶስት አመታት በየግላችን ስንጠቀምበት የነበረ ስለሆነ ክሱ በይርጋ ዉድቅ ነዉ፣ 3ኛ ተከሳሸ ከአባቴ 3 ገመድ መሬት በኪራይ የተቀበልኩኝ ስለሆነ የኪራይ ጊዜዉ ሲያልቅ መከፊፈል ይችላለ በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ የሥር የወረዲዉ ፍ/ቤት የሰዉ ምስክሮች በመስማት በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ ከ1ኛ- 3ኛ የተጠቀሱት ተከሳሾች አባታቸዉ በሕይወት እያለ አንድ አንድ ገመድ መሬት ሰጥቷቸዉ ሲጠቀሙበት የቆዩ ስለሆነ ይህ መሬት የዉርስ ይዞታ ስላልሆነ የከሳሾች ጥያቄ ዉድቅ ነዉ፤ 3ኛ ተከሳሽ 3 ገመድ መሬት በኪራይ ይዣለሁ እና 4ኛ ተከሳሽ አንድ ገመድ መሬት በስጦታ ተሰጥቶኛል የሚለትን በተመለከተ በማስረጃ ስላልተረጋገጠ የዉርስ መሬት በመሆኑ የሟች ልጆችና ወራሾች እንዱከፊፈለ በማለት ወስኗል። የሥር ከሳሾች ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን በትዕዛዝ ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የሥር ከሳሾች አሁንም በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡ ሲሆን ችልቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር ተከሳሾች ለክርክር መነሻ የሆነዉን መሬት በስጦታ አግኝተናል የሚለበት የስጦታ ዉል በሚመለከተዉ አካል ያልተመዘገበ ስለሆነ መሬቱ የዉርስ ሀብት ነዉ፤ መሬቱም ሟች ከሞተ በኋላ የተያዘ መሆኑ በሰዉ ማስረጃ እና ከመሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት የቀረበ ማስረጃ ያረጋገጠ ስለሆነ ሟች ከሞተ በኋላ ሶስት አመት ስላልሞላ የቀረበዉ ክስ በይርጋ የሚታገድ ባለመሆኑ፣ ለክርክር መነሻ የሆነዉ 8 ገመድ የእርሻ መሬት የዉርስ ሀብት በመሆኑ፣ የሟች ወራሾች 8 ቦታ እኩል እንዱከፊፈለ በማለት የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማሻሻል ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማሻር ነዉ።
የአሁን አመልካቾች በ30/6/2012 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በአመልካቾች እጅ የሚገኘዉን አንድ አንድ ገመድ የእርሻ መሬት አባትና እናታችን በ1987 ዓ.ም ሰጥተዉን ለ23 ዓመታት ያህል እየተጠቀምንበት ያለን መሆናችን በማስረጃ አረጋግጠን እያለ እና ይህ ደግሞ በተጠሪዎች ማስረጃ ባልተስተባበለበት፣ ተጠሪዎች ያቀረቡት ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ ሆኖ ሳለ፣ የሥር ፍ/ቤቶች በአመልካቾች እጅ የሚገኘዉን የእርሻ መሬት ወደ ዉርስ ሀብት ተቀላቅል እኩል እንካፈል የሚል ዲኝነት ባልተጠየቀበት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልን፤ የሥር የወረዲዉ ፍ/ቤት እና የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ እንዱጸናልን፣ ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልን በማለት በዝርዝር አመልክቷል።
ይህ ችልት የሰበር አቤቱታ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ባዘዘዉ መሰረት በ16/3/2013 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ አከራካሪዉ መሬት ከአመልካቾች ተሰጥቶ የግላቸዉ መሆኑን የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ የለም፤ መሬቱ የዉርስ ሀብት መሆኑ ስለተረጋገጠ የገቢ ምንጭ የላለን እኛ ተጠሪዎች በመሆናችን በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ መሰረት ቅድሚያ የማግኘት መብት አለን፣ አመልካቾች የዉርስ ሀብት እንካፈል የሚለ ከሆነ በእጃቸዉ ላይ ያለዉን የእርሻ መሬት ወደ ዉርስ ቀላቅለዉ እንዱካፈለ፣ ይህ ካልሆነ በእጃቸዉ ላይ ያለዉን ይዞታ ይዘዉ እንዱቀሩ እንዱወሰንልን በማለት ተከራክሯል። የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት የመልስ መልስ ለክርክር መነሻ የሆነዉና በእጃችን ላይ ያለዉ መሬት በስማችን ተመዝግቦና የባለይዞታነት ማረጋገጫ ደብተር የተሰጠን ሆኖ ሳለ፣ እኛ በእጃችን ያለዉ ሀብት ይበቃናል እንጂ የቀረዉን የዉርስ ሀብት ከላልች ወራሾች ጋር እንድንካፈል ያቀረብነዉ ጥያቄ ስለላለ ተጠሪዎች ያቀረቡት መልስ ተቀባይነት የለዉም በማለት የሰበር አቤቱታቸዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በዚህ ጉዲይ ምላሽ ማግኘት ያለበት የአሁን አመልካች የዉርስ ሀብት እንድካፈል የሚል ጥያቄ ባቀረቡበት ቀደም ሲል በወላጆቻቸዉ ተሰጥቷቸዉ ለረጅም አመታት ሲጠቀሙበት የቆዩትን አንድ አንድ ገመድ የእርሻ መሬት ወደ ዉርስ ሀብት መልሰዉ ከላልች ወራሾች ጋር እንዱካፈለ መባለ ተገቢ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ መሆኑን መገንዘብ ችለናል። በዚህ መሰረት የአሁን አመልካቾች ከሥር ጀምሮ ባቀረቡት ክርክር ወላጆቻችን በሕይወት እያለ የሰጡትን አንድ አንድ ገመድ የእርሻ መሬት የግላችን ስለሆነ ልንጠየቅ አይገባም ብል ከመከራከር ባለፈ የወላጆቻችን ቀሪ የዉርስ ሀብት ከላልች ወራሾች ጋር እንድንካፈል በማለት የጠየቁት ዲኝነት ያለመኖሩን መገንዘብ ተችሎል።
ተጠሪዎችም ባቀረቡት ክርክር አመልካቾች የዉርስ ሀብት እንካፈል የሚለ ከሆነ የእርሻ መሬቱን ወደ ዉርስ እንዱቀላቅለ፤ ይህ ካልሆነ የያዙትን መሬት ይዘዉ እንዱቀሩ፣ ቀሪ የዉርስ ሀብት እንዲይጠየቁ በማለት መከራከራቸዉ ሲታይ አመልካቾች በእጃቸዉ ያለዉ የእርሻ መሬት እንዲይጠየቁ እንጂ ቀሪ የዉርስት ሀብት መጠየቃቸዉን አስረግጠዉ ያቀረቡት ክርክር የለም።
በሥር ፍ/ቤት በማስረጃ የተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ሲታይ የአመልካቾች ወላጆች በሕይወት እያለ በ1987 ዓ.ም አንድ አንድ ገመድ የእርሻ መሬት ለአመልካቾች ሰጥቷቸዉ አመልካቾች ከዛን ጊዜ ጀምሮ በመሬቱ ሲጠቀሙበት መቆየታቸዉን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። በመሆኑም የአሁን አመልካቾች ቀደም ሲል በወላጆቻቸዉ ተሰጥቷቸዉ ለረጅም አመታት ሲጠቀሙበት የነበረዉ የእርሻ መሬት እንዲይጠይቁ እንጂ ቀሪ የዉርስ ሀብት ለመካፈል ያቀረቡት ጥያቄ አለመኖሩን ያስገነዝባል። ይህ ከሆነ ምላሽ ማግኘት ያለበት ጉዲይ አመልካቾች ቀሪ የዉርስ ሀብት ለመካፈል ጥያቄ ባላቀረቡት አስቀድመዉ በወላጆቻቸዉ ተሰጥቷቸዉ ሲጠቀሙበት የነበሩትን የእርሻ መሬት ወደ ዉርስ መመለስ አለባቸዉ ወይ? የሚለዉ መሆኑን መረዲት ይቻላል።
እንደሚታወቀዉ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1073 መሰረት ዉርሱን አልቀበልም ያለ ወራሽ ከሟቹ አስቀድሞ የወሰደዉን ነገር በዉርስ ዉስጥ መልሶ መግባት እንደላለበት ይደነግጋል። ይህ ማለት ወራሽ አስቀድሞ ከዉርስ የተቀበለዉ ንብረት/ነገር ካለ እና ዉርስ ሲከፈት የዉርስ ሀብቱን ለመዉረስ ካልጠየቀ ይህን አስቀድሞ የወሰደዉን ንብረት/ነገር ወደ ዉርስ መልሶ የዉርስ ሀብቱን ለመዉረስ የሚገደድበት አግባብ የለም፤ ወራሹ የዉርስ ሀብት ለመዉረስ ከፈለገ ግን አስቀድሞ የወሰደዉን ነገር ሳይመለስ የዉርስ ሀብት የሚዉርስበት አግባብ ስለላለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1074 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የሚፈጸም ይሆናል ማለት ነዉ።
በዚህ አግባብ አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካቾች ወላጆቻቸዉ አስቀድሞ የሰጧቸዉን አንድ አንድ ገመድ የእርሻ መሬት ልንጠየቅ አይገባም ብለው ከመከራከራቸዉ በስተቀር የዉርስ ሀብት ልንካፈል ይገባል ብል ያቀረቡት ጥያቄ አለመኖሩን ካቀረቡት ክርክርም ሆነ ከሥር ፍ/ቤቶች የዉሳኔ ግልባጭ የምንገነዘበዉ ጉዲይ ነዉ። ይህ ከሆነ ደግሞ አመልካቾች አስቀድሞ የተሰጣቸዉ የእርሻ መሬት ይዘዉ እንዱቀሩ ከመጠየቅ ባለፈ የሟች አባታቸዉን የዉርስ ሀብት ለመካፈል የጠየቁት ዲኝነት እስከላለ ድረስ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ የህግ ድንጋጌ አስቀድሞ የወሰደትን የእርሻ መሬት ወደ ዉርስ ሀብት ለመመለስና ዉርሱን ከላልች ወራሾች ጋር ለመካፈል የሚገደደበት የህግ አግባብ የለም ማለት ነዉ። ስለሆነም የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አመልካቾች አስቀድሞ የወሰደትን የእርሻ መሬት ልንጠየቅ አይገባም ከማለት ባለፈ የዉርስ ሀብት ለመካፈል ያቀረቡት ጥያቄ በላለበት አስቀድሞ የወሰደትን የእርሻ መሬት ወደ ዉርስ መልሰዉ ከላልች ወራሾች ጋር ሉከፊፈለት ይገባል በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ ከፍ ሲል የተጠቀሰዉን የህግ ድንጋጌ ዓላማና የግራ ቀኙን ክርክር ያላገናዘበ ስለሆነ የህግ ድጋፍ የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የአሁን አመልካቾች አስቀድሞ የወሰደትን አንድ አንድ ገመድ የእርሻ መሬት ወደ ዉርስ መልሰዉ የዉርስ ሀብቱን ከላልች ወራሾች ጋር ሉከፊፈለት ይገባል በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ አግባብ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል።
የሄጦሳ ወረዲ ፍ/ቤት በመ.ቁ.26761 በ9/4/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.83480 በ27/5/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.309550 በ19/5/2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሻሽለዋል።
የሥር የወረዲዉ ፍ/ቤት እና የሥር የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች አስቀድሞ የወሰደትን አንድ አንድ ገመድ የእርሻ መሬት ወደ ዉርስ መመለስ የለባቸዉም በማለት የሰጡት የዉሳኔ ክፍል አልተነካም ጸንቷል። ነገር ግን እነዚህ ፍ/ቤቶች የሥር 3ኛ ተከሳሽ አንድ ገመድ የእርሻ መሬት ወደ ዉርስ መመለስ የለበትም በማለት የሰጡት ዉሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የአሁን አመልካቾች አስቀድሞ የወሰደትን የእርሻ መሬት ወደ ዉርስ መልሰው የዉርስ ሀብቱን ከላልች ወራሾች ጋር እንዱከፊፈለ በማለት የሰጠዉ የዉሳኔ ክፍል ተሽሯል። ነገር ግን የሥር 3ኛ ተከሳሽ በተመለከተ እና ቀሪዉ የዉሳኔ ክፍል አልተነካም ጸንቷል።
የአሁን አመልካቾች አስቀድሞ የወሰደትን አንድ አንድ ገመድ የእርሻ መሬት ልንጠየቅ አይገባም ከማለት ባለፈ የዉርስ ሀብት ለመካፈል ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ ስለላለ፤
አመልካቾች ይህን አስቀድሞ የወሰደትን የእርሻ መሬት ወደ ዉርስ ለመመለስ አይገደደም ብለናል። አመልካቾች አስቀድሞ የወሰደትን የእርሻ መሬት ይዘዉ ከሚቀሩ በስተቀር ቀሪ የዉርስ የእርሻ መሬትን ከላልች ወራሾች ጋር ለመካፈል አይችለም ብለናል።
በአመልካቾች እጅ ካለዉ የእርሻ መሬት በስተቀር የሟች አባታቸዉ የዉርስ መሬት (ስድስት ገመድ የእርሻ መሬት) አመልካቾችን ሳይጨምር በላልች ወራሾች /ተጠሪዎች/ መካከል እኩል ሉከፊፈለት ይገባል ብለናል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ይህ ችልት በ2/7/2012 ዓ.ም በሄጦሳ ወረዲ ፍ/ቤት በአፈጻጸም መ.ቁ.30585 ላይ የተጀመረዉ የአፈጻጸም ክርክር ታግድ እንዱቆይ የሰጠዉ እግድ ትዕዛዝ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
No topics extracted.