ተወላጅ መሆን ለወራሽነት ብቁ ከሚያደርጉ ህጋዊ መስፈርቶች ውስጥ አንደ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 842 እና 830 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ የሚቻል ቢሆንም ይህ ማለት ግን የሟችን ንብረት ለመውረስ ስለተወላጅነት በተመለከተው ሥርዓት መሰረት መወለድን ማረጋገጥ የግድ ማለት ሳይሆን በተለይ ውርሱ የሚመለከተው ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆችን በሆነ ጊዜ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ መያዝ በቂ ወ/ት ዮዱት ሰለሞን እና ወ/ሮ አይናለም ወርቁ
No summary available.
የሰ.መ.
ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ወ/ት ዮዱት ሰለሞን ተጠሪ፡- ወ/ሮ አይናለም ወርቁ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ችልት የቀረበው የምትክ ወራሾች የአውራሾቻቸውን ተወላጅነት ስላላረጋገጡ ሉወርሱ አይችለም በሚል የተሰጠን የመጨረሻ ውሳኔ ህጋዊ አግባብነት መርምሮ ለመወሰን ነው።
የክርክሩ ሥረ ነገር አመጣጥ እንዱህ ነው። የአሁን አመልካች የሴት አያታቸው የኑዛዜ ወራሽነት ባረጋገጡበት የወረዲ ፍርድ ቤት መዝገብ ላይ የአሁን ተጠሪ በመቃወም አመልካችነት ቀርበው በመከራከራቸው ኑዛዜው በህግ የተቀመጠውን ፍርማሉቲ አያሟላም በሚል ውድቅ ይደረጋል። ከዚህ በኋላ አመልካች የወላጅ አባታቸው ምትክ ወራሽነት በፍርድ ቤት በማረጋገጥ የአሁን ተጠሪ ይዘው የሚገኙትን የአያታቸውን የውርስ ሃብት እንዱያካፍሎቸው አዱስ ክስ ያቀርባለ። ይኸው ጉዲይ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ደርሶ የሰበር ሰሚ ችልቱ የአሁን አመልካች የኑዛዜ ወራሽነት ውድቅ መደረጉ ምትክ ወራሽነቷን የሚከለክል መሆኑ አለመሆኑ ተጣርቶ እንዱወሰን ለወረዲው ፍርድ ቤት በነጥብ ይመልሳል።
በዚህ መልኩ ጉዲዩ የተመለሰለት የወረዲው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ከሰማ በኋላ ግራ ቀኙ የአያታቸው ወ/ሮ ማሰሬ ወልደዓብ የምትክ ወራሽ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ በሚል ክርክር የተነሳበትን የሟች የውርስ ሃብት ተጠሪ ለአመልካች እንዱያካፍለ ይወስናል።
በአሁን ተጠሪ ይግባኝ ባይነት ይህንኑ ውሳኔ በይግባኝ የተመለከተው የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩ በነጥብ ከተመለሰ በኋላ የተሰሙት የግራ ቀኙ የሰው ምስክሮች ለየቀረቡላቸው ተከራካሪ ወገኖች እንደ ክሱ እና መከላከያ መልሱ ያረጋገጡ መሆኑን፤ የኑዛዜ ወራሽነት ክርክር በተደረገበት መዝገብ ላይ የተሰሙት ምስክሮች ደግሞ የሟች ብቸኛ ልጅ የተጠሪ ወላጅ እናት መሆናቸውን ያረጋገጡ መሆኑን፤
የተጠሪ እናት በሞቱ ጊዜም ሟች ወ/ሮ ማሰሬ ወልደዓብ የሞተችው ልጄ ነች በሚል ለቅሶ ተቀምጠው እድርም የበለ ስለመሆኑ መረጋጡን በምክንያትነት በመጥቀስ አመልካች ልትወርስ አይገባም በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማሻሻል ወስኗል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በበኩለ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር የወረዲ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅንቷል።
በዚሁ ጉዲይ ላይ የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/291900 ላይ የግራ ቀኙን የሰበር ክርክር ከሰማ በኋላ ሚያዝያ 08/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ ግራ ቀኙ የአያታችን ምትክ ወራሾች ነን ከማለት ባለፈ ወላጆቻቸው በእርግጥም የአያታቸው ተወላጅ ስለመሆናቸው በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 769 እና 770(1 እና 2) ወይም በክልለ የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 171፣ 172፣ እና 174 በተመለከተው አግባብ ባልተረጋገጠበት ምትክ ወራሽ ናቸው ተብል መወሰኑ አግባብ አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ሽሮ ግራ ቀኙ ሉወርሱ አይችለም ብሎል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔን በመቃወም ነው። አመልካች ሀምላ 02/2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ፍርድ መግቢያ ላይ የተጠቀሰውን ነጥብ ግራ ቀኙ በተገኙበት ለማጣራት ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም የቀረበውን ክርክር ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ፤ በስር ፍርድ ቤቶች ከተከናወነው ክርክር ይዘት እና አድማስ አንፃር ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በመሰረቱ መወለድ እና ወራሽነት ሁለቱም በቤተሰብ ህግ የሚገዙ ፅንሰ ሀሳቦች ቢሆኑም አንድ ዓይነት ዓላማ እና ግብ ያላቸው አይድለም። የመወለድ መሰረተ ሀሳብ ዋናው ዓላማ ወላጅን እና ቤተዘመድን ለይቶ ከማወቅ ጋር የተያያዘ የማንነት ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን የወራሽነት ፅንሰ ሀሳብ መሰረታዊ ዓላማ ደግሞ ከሞት በኋላ የሟቹ ንብረት የመውረስ መብት ላላቸው ሰዎች የሚተላለፍበትን ሥርዓት የሚመለከት ነው። በቤተሰብ ህግ ውስጥ ሁለቱ መሰረተ ሀሳቦች የሚረጋገጡበት መንገድም የተለያየ ነው። መወለድ የሚረጋገጠው በቀዲሚነት የልደት ምስክር ወረቀት በማቅረብ መሆኑን፤ በዚህ መልኩ የሚቀርብ የልደት ምስክር ወረቀት ከላለ ደግሞ ተወላጅነት በሁኔታ የማረጋገጥ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 769 እና 770(1) ድንጋጌዎች እንዱሁም ከኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/1995 እና 83/1996 አንቀፅ 171-174 ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
በአንፃሩ የወራሽነት መብት ከኑዛዜ አልያም ያለ ኑዛዜ የሚመነጭ መሆኑን ከማረጋገጥ ባለፈ በህግ ተለይቶ የተቀመጠ ማረጋገጫ መንገድ የለም። በእርግጥ የሟች ተወላጅ መሆን ለሟች ወራሽነት ብቁ ከሚያደርጉ ህጋዊ መስፈርቶች ውስጥ አንደ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 842 እና 830 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል። ይህ ማለት ግን የሟችን ንብረት ለመውረስ ስለተወላጅነት በተመለከተው ሥርዓት መሰረት መወለድን ማረጋገጥ የግድ ይላል ማለት እንዲልሆነ ሉጤን ይገባል።
በተለይ ውርሱ የሚመለከተው ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆችን በሆነ ጊዜ (የማስረጃውን ህጋዊነት የመቃወሙ ጉዲይ እንደተጠበቀ ሆኖ) ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ መያዝ በቂ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 996-998 ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች ወላጅ አባትዋ የሟች ወ/ሮ ማሰሬ ወልደዓብ ልጅ መሆናቸውን እና አባትዋ ሟችን ቀድመው የሞቱ ስለመሆኑ ተረጋግጦ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት የምትክ ወራሽነት ማስረጃ ተሰጥቷቸዋል። የዚህን ማስረጃ ህጋዊነት አስመልክቶ የቀረበ ተቃራኒ ክርክርም ሆነ የተረጋገጠ ነገር ባለመኖሩ አመልካች በወላጅ አባትዋ እግር ተተክተው የውርስ ሀብት የተባለውን ንብረት ለመጠየቅ በህግ የተቋቋመ መብት አላቸው ማለት ነው። እናም በዚህ መልኩ የተረጋገጠ መብት እያለ አመልካች የአባታቸውን ተወላጅነት እንዱያረጋግጡ የሚገደደበት ህጋዊ ምክንያት የለም።
ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በህግ ያልተቀመጠን መመዘኛ ጠቅሶ አመልካች የወላጅ አባታቸውን ተወላጅነት ስላላረጋገጡ ሉወርሱ አይችለም በሚል ከአመልካች አኳያ የሰጠው ውሳኔ የተወላጅነት እና የወራሽነት ፅንሰ ሃሳቦችን ባህሪ እና መሰረታዊ ልዩነት ያላገናዘበ መሰረታዊ የህግ አረዲድ እና አተረጓጎም ስህተት ሆኖ በመገኘቱ በእርግጥም የሚነቀፍ ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
1.የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/291900 ላይ ሚያዝያ 08/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የዚህን ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.