በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1179 ስር የተመለከተው በልላ ሰው ይዞታ ላይ የሚደረግ ግንባታን የመቃወም ጉዲይ አግባብ ባለው የአስተዲደር አካል በተሰጠ ይዞታ ላይ በሚደረግ ግንባታ ላይ ተፈፃሚነት የላለው እነ ወ/ሮ አለሚቱ ተክላ (2 ሰዎች) እና እነ ወ/ሮ እብስቴ ምስክር (2 ሰዎች)
No summary available.
ቀን፡-26/08/2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የከተማ ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/አቤ/መ/ቁ/03-76609 ላይ ህዲር 02/2012 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አንደኛ ተጠሪ የካቲት 10/2001 ዓ.ም ፅፈው በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት አዊ ዞን ብሕረሰብ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁን ሁለተኛ ተጠሪ እና አመልካቾች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። አንደኛ ተጠሪ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ክስ ቦታ እና አዋሳኙ በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰውን 1100 ካሬ ሜትር የከተማ ይዞታ አቶ ግርማ ጓልየ የተባለው ሟች ልጃቸው በ1989 ዓ.ም በህጋዊ መንግድ ለዲቦ ቤት ስራ በሚል ከመንግስት ተመርቶ ይህንኑ ይዞታ እላዩ ካለው ጅምር ግንባታ ጋር በመያዥያነት አስይዞ ከልማት ባንክ ብር ተበድሮ እዲውን ሳይከፍል የሞተ መሆኑን፤ እርሱ ከሞተ በኋላ በወራሽነት ሟች የተበደረውን እዲ ከፍለው በመጨረሳቸው ንብረቱ እንዱተላለፍላቸው ከልማት ባንክ ማረጋገጫ አፅፈው ወደ ሁለተኛ ተጠሪ ጽ/ቤት ሲሄደ ጽ/ቤቱ ከይዞታው ላይ በስሜን አቅጣጫ 20X8 ሜትር በአጠቃላይ 160 ካሬ ሜትር ይዞታ ለአሁን አመልካቾች አስተላልፍ አመልካቾቹም በይዞታው ላይ ቤት ሰርተው መያዛቸውን ያረጋገጡ መሆኑን፤ ይኸው ይዞታ እንዱለቀቅላቸው ቢጠይቁም ለመፈፀም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀው ተከሳሾቹ በፍርድ ኃይል ተገደው በይዞታው ላይ ያለውን ቤት በራሳቸው ወጪ አፍርሰው እንዱያስረክቧቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት ሁለተኛ ተጠሪ እና አመልካቾች አለን ያለትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የስረ ነገር ክርክር በማቅረብ ተከራክረዋል። በዚሁ አግባብ ጉዲዩ እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ ከታየ በኋላ ክስ በቀረበበት ይዞታ ላይ የአሁን አመልካቾች ቤቱን ሲሰሩ ከአሁን አንደኛ ተጠሪ የቀረበ ተቃውሞ መኖር ያለመኖሩ በግራ ቀኙ ምስክር እንዱጣራ እንዱሁም ክርክር የተነሳበት ይዞታ መጠን እና የአሁን አንደኛ ተጠሪ ተቀነሰብኝ የሚለት የይዞታ መጠን በባለሙያ ተጣርቶ እንዱወስን በነጥብ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተመለሰ መሆኑን፤ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም እንዱያጣራ በተባለው ነጥብ ላይ የግራ ቀኙን ምስክር በመስማት እና ስለይዞታው ከክፍለ አስተዲደር ተጣርቶ እንዱቀርብለት ካደረገ በኋላ በሰጠው ውሳኔ አመልካቾች ቤቱን ሲሰሩ የአሁን አንደኛ ተጠሪ ተቃውመው የነበረ ለመሆኑ አረጋገጫለሁ፤ አስተዲደር ክፍለም የላላውን ሰው ይዞታ ቀንሶ ለላላው መስጠት አይችልም፤
አመልካቾች በቦታው ላይ ስላወጡት ወጪ ከፈለጉ አስተዲደሩን ከሚጠይቁ በቀር የአሁን አንደኛ ተጠሪ በይዞታው ላይ ያላቸውን መብት የሚያጡበት ምክንያት ባለመኖሩ በይዞታው ላይ የሰሩትን ቤት አፍርሰው ሉያስረክቧቸው ይገባል በማለት ወስኗል።
ከዚህ በኋላ በነበረው ክርክር የከተማ አስተዲደሩ የክርክሩ አካል ያልነበረ በመሆኑ ጉዲዩ እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ታይቶ በሰ/መ/ቁ/119930 ላይ ሚያዝያ 24/2009 ዓ.ም በዋለው ችልት የአሁን ሁለተኛ ተጠሪ የክርክሩ አካል ተደርጎ እና የሚያቀርበው መከራከሪያ ተሰምቶ እንዱወሰን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በነጥብ ተመልሷል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም በታዘዘው መሰረት ለሁለተኛ ተጠሪ መጥሪያ ልኮለት ባለመቅረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ አዟል። ዋናውን የክርክር ጭብጥ በተመለከተ የአሁን አመልካቾች ቤት የሰሩበትን ይዞታ በህጋዊ መንገድ ከሚመለከተው አስተዲደር ክፍል የወሰደ ስለመሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ቤቱን አፍርሰው ይዞታውን ሉለቁ አይገባም፤ የአሁን ተጠሪ ይዞታቸው ለላላ አካል በመጠሰቱ ምክንያት ለደረሰባቸው ጉዲት ከፈለጉ አስተዲደሩን ይችላለ በማለት ቀድሞ የሰጠውን ውሳኔ በማጠናከር ወስኗል። በዚሁ ውሳኔ ላይ የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በበኩለ የይግባኝ ሰሚ ችልቱን ውሳኔ በመሻር የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔን አፅንቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔን በመቃወም ነው። አመልካቾች ታህሳስ 01/2012 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። ፍሬ ቃለም ይዞታው ስልጣን ባለው አስተዲደደር አካል በህጋዊ መንገድ የተሰጠን ሲሆን ግንባታውን ያከናወነውም ተገቢውን የግንባታ ፈቀድ በማውጣት ነው፤ በይዞታው ላይ ግንባታ ስናከናውንም የአሁን አንደኛ ተጠሪ በራሳቸው የግንባታ እቃ ሲሸጡልን የነበረ እና ግንባታውን የሚያውቁ ቢሆንም ቤቱ እንዲይሰራ ያቀረቡት ተቃውሞ አልነበረም፤ በዚህ መልኩ ቤቱ ከተሰራ ከአምስት ዓመት በኋላ አፍርሰው ይዞታውን ይልቀቁልኝ ተብል ክስ መቅረቡም ሆኖ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ይህንኑ ተቀበል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉሻር ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካቾች ለክርክር ምክንያት የሆነውን ቤት የሰሩት በህግ አግባብ ከሁለተኛ ተጠሪ ባገኙት 160 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ስለመሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ እና አንደኛ ተጠሪ በወቅቱ አንስቼ ነበር የሚለትን መቃወሚያ እንዲልገፈበት በተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካቾች ቤቱን አፍርሰው ይዞታውን ያስረክቡ ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለዚህ ችልት ቀርቦ እንዱመረመር በመታዘዙ ምክንያት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
በዚሁ መሰረት አንደኛ ተጠሪ ጥር 18/2012 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካቾች ቤቱን ሲሰሩ መቃወሜን በከፍተኛው ፍ/ቤት ቀርበው በተሰሙት ምስክሮች የተረጋገጠ በመሆኑ ግንባታውን አልተቃወምሽም ልባል አይገባም፤ በባንክ እዲ ምክንያት ይዞታው ታግድ ባለበት እና ስለመታገደም ማዘጋጃ ቤት በራሱ እያወቀ ለመኪና ማቆሚያ ተብል በተተው ቦታ ላይ ቅን ልቦና በጎደለው መልኩ በካርታ ላይ ካርታ ከመሰጠቱም በላይ ግንባታው በህገ ወጥ መንገድ የተገነባ በመሆኑ እንዱፈርስ መወሰኑ ተገቢ ነው በማለት ተከራክረዋል።
ሁለተኛ ተጠሪ በበኩለ ጥር 08/2012 ዓ.ም በተጻፈ መልስ ቦታው ለአሁን አመልካቾች ሲሰጥ ክፍት እና የሚቆጣጠር ሰው ያልነበረው ነው፤ በቦታው ላይ ግንባታ ሲከናወንም የአሁን አንደኛ ተጠሪ አሸዋ እና ጠጠር ለአመልካቾች ሲሸጡ የነበረ እና ስለግንባታውም የሚያውቁ ቢሆንም ያቀረቡት ተቃውሞ አልነበረም፤ አመልካቾች በቦታው ላይ የሰሩት ግንባታ ከሚፈርስ ይልቅ ለአሁን አንደኛ ተጠሪ ላላ ተመጣጣኝ ይዞታ ቢሰጣቸው የተሻለ ይሆናል በማለት ተከራክሯል።
አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ በማቅረብ ሞግተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆኑት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔዎች፤ በስር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ከክርክሩ አመጣጥ መረዲት እንደሚቻለው የአሁን አንደኛ ተጠሪ ክስ ያቀረቡበት ይዞታ ቀደም ብል ለአሁን አንደኛ ተጠሪ አውራሽ ልጅ የነበረ ሲሆን ከዚሁ ይዞታ ላይ 160 ካሬ ሜትር ተቀንሶ ለአሁን አመልካቾች የተሰጠ መሆኑ እና አመልካቾችም በዚሁ ይዞታ ላይ ቤት የሰሩ ስለመሆኑ አላከራከረም። የአንደኛ ተጠሪ ዋነኛ መከራከሪያ ይዞታው ከህግ አግባብ ውጭ ተቀነሶ ለአመልካቾች የተሰጠ በመሆኑ በይዞታው ላይ የተሰራው ቤት ፈርሶ ይዞታውን ልረከብ ይገባል የሚል ነው። አመልካቾች በበኩላቸው ቤቱን የሰራነው በህጋዊ መንገድ በተሰጠን ቦታ ላይ በተገቢ የግንባታ ፈቃድ በመሆኑ እና ግንባታውንም ስናከናውን የቀረበብን ተቃውሞ ባለመኖሩ አፍርሰን ልንለቅ አይገባም በማለት አጥብቀው ይሞግታለ።
እንግዱህ ከዚህ የክርክር አድማስ በዋናነት ሁለት አብይት ነጥቦች ምላሽ ማግኘት የሚጠበቅባቸው መሆኑን መረዲት ይቻላል። አንደኛው በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1179 ስር የተመለከተው በልላ ሰው ይዞታ ላይ የሚደረግን ግንባታ የመቃወም ጉዲይ ስልጣን ባለው አስተዲደር አካል በተሰጠ ይዞታ ላይ የሚደረግ ግንባታን ያጠቃልላል? ወይስ አያጠቃልልም? የሚል ነው። ሁለተኛው ደግሞ አግባብ ካለው የአስተዲደር ክፍል በህጋዊ መንገድ በተሰጠ ይዞታ ላይ ይዞታ ተቀባዩ ሀብትና ንብረቱን አፍስሶ ግንባታ ካከናወነ በኋላ ይዞታው የላላ ሰው መሆኑን ቢረጋገጥ ውጤቱ ምን ላሆን ይገባል?
የሚለው ነው። እነዚህ ሁለቱ ነጥቦች በሚከተለው መልኩ በተናጠል ታይተዋል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ ባለመሬቱ ሳይቃወም በልላ ሰው መሬት ላይ ህንፃ የሰራ ሰው የዚሁ ህንፃ ባለሃብት እንደሆነ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1179(1) ይደነግጋል። የዚህ ድንጋጌ መሰረታዊ ሀሳቡ የሚመነጨው ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1178 ነው። የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1179 ድንጋጌ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1178 ይዘት ጋር ተዲምሮ ሲታይ መገንዘብ የሚቻለው አንደ ቁምነገር ህንፃ የሚገነባው ሰው ህንፃውን የሚገነባው የራሱ ሳይሆን በልላ ሰው ይዞታ ላይ ስለመሆኑ የሚያውቅ እና የሚቀበል መሆኑን፤ ህንፃውን የሰራው ሰውም በገነባው ህንፃ ላይ የሚኖረው መብት ትክክለኛ ባለይዞታው ግንባታውን አስመልክቶ በሚኖረው እውቀት እንዱሁም ግንባታውን በመቃወም ወይም አለመቃወሙ ሁኔታ ላይ የሚመሰረት መሆኑን ነው። በልላ አገላለፅ የፍ/ብ/ህ ቁጥር 1179 ድንጋጌ የሚመለከተው በአንድ መሬት ትክክለኛ ባለይዞታ እና በዚሁ ይዞታ ላይ መብት ሳይኖረው ህንፃ በሰራ ሰው መካከል የሚኖረውን የመብት አድማስ ነው።
በአንፃሩ ስልጣን ባለው አስተዲደር አካል በተሰጠው ይዞታ ላይ ህንፃ የሚሰራ ሰው በይዞታው ላይ ግንባታ የሚያከናውነው በይዞታው ላይ ትክክለኛ ባለመብት ነኝ በሚል ስሜት እንጂ ይዞታው የላላ ሰው ቢሆንም ባለው የህግ አግባብ ወደፉት የህንፃው ባለሃብት እሆናለው በሚል እንዲልሆነ ግንዛቤ ሉወሰድበት የሚችል ጉዲይ በመሆኑ ግንኙነቱ በሁለት ግለሰቦች መካከል ሳይሆን በመንግስት እና በባለይዞታው መካከል ነው። እናም አግባብ ካለው አስተዲደር አካል በተሰጠ ይዞታ ላይ በባለይዞታው የሚከናወን ግንባታን አስመልክቶ ይዞታው ይገባናል የሚለ ላልች ሰዎች ግንባታውን መቃወም አለመቃወማቸው ህንፃውን በሰራው ሰው የባለሀብትነት መብት ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም። በመሆኑም በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1179 ስር የተመለከተው በልላ ሰው ይዞታ ላይ የሚደረግ ግንባታን የመቃወም ጉዲይ አግባብ ባለው አስተዲደር አካል በተሰጠ ይዞታ ላይ በሚደረግ ግንባታ ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ ውጤቱ ሀገሪቱ ከምትከተለው የመሬት ስሪት ባህሪ፣ ከዜጎች ህገ መንግስታዊ የንብረት ባለቤትነት መብት እና ኋላ ላይ ትክክለኛ ባለይዞታ መሆኑ የተረጋገጠው ሰው በልላ መንገድ ከመካስ አኳያ ከሚኖረው ተነፃፃሪ መብት ጋር ተገናዝቦ ላታይ የሚገባው ጉዲይ ነው። ከዚህ አንፃር የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት ከታወጀ በኋላ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሃብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ መሆኑን እና መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሕሮች፣ ብሕረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት በመሆኑ ዜጎች በባድ መሬት ላይ የሚኖራቸው የይዞታ መብት ብቻ ስለመሆኑ የህገ መንግስት አንቀፅ 40(3) ድንጋጌ ያስገነዝባል።
በልላ በኩል በመሬት ላይ ጉልበት እና ገንዘባቸውን አፍስሰው ሀብት ያፈሩ ዜጎች የዚያው ንብረት የባለሀብትነት መብታቸው በህገ መንግስት ጥበቃ የተደረገለት ስለመሆኑ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 40(7) ድንጋጌ ያስገነዝባል። ከዚህም የተነሳ በባድ መሬት ላይ መብት አለን ከሚለት ሰዎች ይልቅ ይዞታውን በእጁ አድርጎ እና ንብረት አፍርቶበት የያዘ ሰው የተሻለ መብት ያለው ስለመሆኑ ይኸው ችልት በሰ/መ/ቁ/105125 ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል። ከዚህ አንፃር ለክርክር ምክንያት የሆነው ይዞታ መሰረቱ የአሁን አንደኛ ተጠሪ አውራሽ የነበረ ቢሆንም አመልካቾች ይህንኑ ይዞታ ስልጣን ካለው አስተዲደር አካል አግኝተው ንብረት ያፈሩበት በመሆኑ ባድ ይዞታው ይገባኛል ከሚለት አንደኛ ተጠሪ ይልቅ የተሻለ መብት አቋቁመዉበታል። እናም ባድ ይዞታው የእኔ ነው በሚል መነሻ ምክንያት ብቻ አመልካቾች በይዞታው ላይ ያፈሩትን ንብረት አፍርሰው እንዱለቁ የሚገደደበት ህጋዊ ምክንያት የለም። በአንፃሩ የአሁን አንደኛ ተጠሪ ጥያቄ ባድ ይዞታን የሚመለከት በመሆኑ እና በተወሰደባቸው ይዞታ ምትክ ተመጣጣኝ ይዞታ ለማግኘት እድለ ያላቸው እና ሁለተኛ ተጠሪም በዚሁ መልኩ ለመፈፀም ፈቃደኛ ስለመሆኑ ካቀረበው መከራከሪያ መረዲት የሚቻል በመሆኑ በዚሁ መልኩ እንዱካሱ ማድረጉ ተገቢ ይሆናል።
ሲጠቃለል የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ከዚህ አኳያ ማየት ሲገባው አመልካቾች ቤት የሰሩበት ይዞታ የላላ ሰው ስለመሆኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት በመያዝ አመልካቾች ግንባታውን አፍርሰው ይዞታውን እንዱለቁ መወሰኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1179 ድንጋጌ የተፈፃሚነት ወሰን፤ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ህገ መንግስት የተመለከተውን የመሬት ስሪት ባህሪና የዜጎች የንብረት ባለቤትነት መብት እንዱሁም አንደኛ ተጠሪ በልላ መንገድ ከመካስ አኳያ የሚኖራቸውን ተነፃፃሪ መብት ያላገናዘበ መሰረታዊ የህግ አረዲድ እና አተረጓጎም ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ተሰጥቷል።
የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/አቤ/መ/ቁ/03-76609 ላይ ህዲር 02/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/36997 ላይ መጋቢት 07/2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ሁለተኛ ተጠሪ ከአሁን አንደኛ ተጠሪ ይዞታ ላይ ቀንሶ ለአመልካቾች በሰጠው 160 ካሬ ሜትር ይዞታ ምትክ ተመጣጣኝ መጠን እና ደረጃ ያለውን ይዞታ እንዱተካላቸው ተወስኗል።
የዚህን ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
በዚህ መዝገብ ላይ የተሰጠ የእግድ ትዕዛዝ ካለ ተነስቷል። ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.