ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ መብቶች እና ግዳታዎች የሚመሩት በንብረት ህግ አጠቃላይ መርሆዎች በመሆኑ የከተማም ሆነ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀምን አስመልክቶ የሚወጡ ህጎች/አዋጆች በንብረት ህግ ማዕቀፍ ዉስጥ የሚመደቡ በመሆኑ ከንብረት ጋር በተገናኘ ያለ ጽንሰ ሃሳቦች፣ ህጎች እና መርሆዎች ከመሬት ጋር በተያያዘ ለሚቀርብ ክርክር እንደየአግባብነታቸዉ ተፈፃሚነት ያላቸው ስለመሆኑ አንድን ንብረት አስመልክቶ የሚቀርበዉን ክስ ተከትል ንብረትን የሚመለከት የህግ ክፍል ተፈፃሚ የሚሆነዉ ከሳሽ ክሱን ያቀረበዉ ንብረቱን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በእጁ ካደረገ በኋላ በንብረቱ ላይ ያለዉ መብት እንዱከበርለት የተረጋገጠ ሲሆን በመሆኑ የተጠየቀዉ ዲኝነት ንብረትን የሚመለከት መሆኑ ብቻዉን ጉዲዩን የንብረት ክርክር የማያደርገው ሰይድ ዐመር እና ወ/ሮ ሀዋ ሰይድ
No summary available.
መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ሰይድ ዐመር ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሀዋ ሰይድ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ጋብቻ በአንደኛዉ ተጋቢ ሞት ምክንያት መፍረሱን ተከትል የሟች ወራሽ የሆነ ሰዉ የገጠር መሬትን አስመልክቶ በሚያቀርበዉ የድርሻ ክፍፍል ጥያቄ ላይ ተፈፃሚነት ያለዉን የይርጋ ደንብ የሚመለከት ነዉ። ክርክሩ በተጀመረበት በደቡብ ወል ዞን ወረ ባቦ ወረዲ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ በመሆን በተጠሪ ላይ ባቀረበዉ ክስ ተጠሪና ወላጅ አባቴ በ1976 ዓ.ም በድልድል መሬት ያገኙ ሲሆን ተጠሪ የአባቴን ድርሻ መሬት እንድታካፍለኝ ብጠይቃትም ፍቃደኛ ስላልሆነች የአባቴን ድርሻ መሬት እንድትሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀዉን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ። ተጠሪ በበኩሎ በሰጠችዉ መልስ ክሱ በይርጋ ይታገዲል፣ አመልካች መብትና ጥቅም የለውም የሚለ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ያቀረበች ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም አመልካች አባቱ ሲሞት መሬቱን እኩል ተካፍለን በየግላችን የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አሰርተን አመልካች የአባቱን ድርሻ የያዘ በመሆኑ ሉጠይቀኝ አይገባም በማለት ተከራክራለች።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ የወረዲዉ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተጠሪ የአመልካች አባት ድርሻ የሆነውን መሬት የያዘች በመሆኑ ለአመልካች ታስረክብ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘችዉ ተጠሪ ይግባኟን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበች ሲሆን ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የወረዲው ፍርድ ቤት የተጠሪን የይርጋ መቃወሚያ ያለፈው በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ከመረመረ በኋላ የአመልካች አባት ከሞቱበት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ተጠሪ ይዞታውን በስሟ በደብተር ላይ አስመዝግባ ይዛ የምትጠቀምበት በመሆኑ፤
አመልካችም አባቱ በህይወት እያለ የጎጆ መውጫ መሬት ተሰጥቶት ሲጠቀም እንደቆየ በሰውና ማስረጃ በመረጋገጡ፤ የአመልካች አባት ከሞተ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት ድረስ ያለው ጊዜ ሲታይ 20 ዓመት ያለፈው መሆኑን ጠቅሶ ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት የወረዲ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሽሮታል። አመልካች በበኩለ በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ውድቅ ተደርጎበታል። በመቀጠል የሰበር አቤቱታውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበ ሲሆን ይህም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 22/03/2012 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ይዞታውን በህጋዊ መንገድ ይዛ ስትጠቀምበት ነበር በማለት በደፈናው ገልጾ ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት ቢወስንም በምን ዓይነት ህጋዊ መንገድ እንደተያዘ አልገለጸም፤ በይዞታው ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማውጣቷም ይዞታውን ህጋዊ አያደርገውም፤ በህገ-ወጥ መንገድ መሬትን የያዘ ማንኛውም ሰው የይርጋ መቃወሚያን ሉያነሳ እንደማይችል እየታወቀ ክሱ በይርጋ ይታገዲል ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል በማለት ዲኝነት ጠይቃለች።
የሰበር አቤቱታዉ ተመርምሮም የገጠር መሬት ውርስን በሚመለከት ተፈፃሚነት ያለው የይርጋ ደንብ የትኛው እንደሆነ ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ባቀረበዉ መልስ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው የይርጋ ደንብ በውርስ ህጉ ላይ ያለው የይርጋ ደንብ ሲሆን ይህንኑ መሰረት አድርጎ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሳኔ ትክክለኛ እና ተገቢ በመሆኑ ሉፀና ይገባዋል በማለት ተከራክራለች። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቶ ተከራክሯል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም መዝገቡን ለማስቀረብ በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ እንደሚቻለዉ አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረበዉ ክስ ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ያደረገዉ የአባቱ የነበረ እና በዉርስ የሚተላለፍለትን ይዞታ ተጠሪ ድርሻዉን ልታካፍለዉ ፍቃደኛ አለመሆኗን በመጥቀስ ሲሆን፣ተጠሪ በበኩሎ አባቱ መሞቱን ተከትል አመልካች ድርሻዉ የተሰጠዉ ከመሆኑም በላይ የአመልካች አባት በ1990 ዓ.ም በዚህ ዓመት በሞት የተለየ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ሉታገድ ይገባል በማለት መከራከሯን ነዉ።አባቱ በ1990 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ስለመሆኑ አመልካች ክድ አይከራከርም። የዉርስ ድርሻ ይገባኛል ጥያቄ ሳያቀርብ የቆየበት የተለየ ምክንያት ያለዉ ስለመሆኑም አመልካች የገለጸዉ ነገር የለም። ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካች ክስ በይርጋ ይታገዲል በሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰዉም ክሱ የቀረበዉ አዉራሽ ከሞተበት ከ 20 ዓመት በኋላ መሆኑን በመጥቀስ ቢሆንም ለዚህ ተፈፃሚነት ያለዉ ህግ (ድንጋጌ) ግን አልጠቀሰም። አመልካች በዚህ ችልት ባቀረበዉ ክርክር ክሱ በይርጋ አይታገድም በማለት አጥብቆ የሚከራከረዉ በአማራ ክልል የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 55 መሰረት በህገ ወጥ መንገድ የተያዘን መሬት ለማስለቀቅ የሚቀርብ ክስ በይርጋ አይታገድም በማለት ነዉ። ስለሆነም ይርጋን አስመልክቶ ከገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጁ ላይ የተመለከተዉ የይርጋ ድንጋጌ ለተያዘዉ ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉ መሆን ያለመሆኑ አመልካች ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ካደረገዉ የክስ ምክንያት ጋር በማገናዘብ ማየቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሰረቱ የፍትሐብሕር ጉዲይ የቀረበለት ፍርድ ቤት በቀዲሚነት እንዱያከናዉን ከሚጠበቁበት ተግባራት ዉስጥ አንድ እና መሰረታዊዉ ለቀረበለት ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉ የህግ ክፍል የመለየት ተግባር (identification of applicable law) ነዉ። አስቀድሞ ይህን ማድረግ የቀረበዉ ክስ የክስ ምክንያት ያለዉ መሆን አለመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ያለዉ መሆን አለመሆኑን እና ላልች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ካለ አስቀድሞ በመለየት መርምሮ ተገቢዉን ዉሳኔ ለመስጠት የሚያችለዉ ሲሆን፣ ጉዲዩ ወደ ሙለ የክርክር ሂደት (full scale trial) የሚገባ ከሆነም በጉዲዩ ላይ ትክክለኛ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉን ጭብጥ ይዞ ክርክሩን በመምራት ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉን ድንጋጌ በአግባቡ ለይቶ ፍትሐዊ ዉሳኔ ለመስጠት ያስችላል። በአጠቃላይ አስቀድሞ በጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉን የህግ ክፍል መለየት ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ከክርክር አመራር ሥርዓት ጋር በተያያዘ በሥ/ሥርዓት ህጉ የተመለከቱትን ደንቦች እና ድንጋጌዎች መሰረት ባደረገ መልኩ ክርክሩን ይመራ ዘንድ ያስችለዋል። የክርክር አመራርን አስመልክቶ በህጉ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ጉዲዩን መምራት፣ የክርክር አመራሩ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ እንዱሆን በማድረግ የተከራካሪ ወገኖችን ሥነ ሥርዓታዊ ፍትሕ እንዱረጋገጥ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ፤ ለጉዲዩ ትክክለኛ ጭብጥ በመያዝ፣ ተቀባይነት እና አግባብነት ያለዉን ማስረጃ ለይቶ በማስቀረብ እና በመመርመር ወሳኝ የሆኑ ፍሬ ነገሮች ነጥሮ እንዱወጡ በማድረግ ብልም ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉን የህግ ድንጋጌ ለይቶ ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ በጉዲዩ ላይ ፍትሐዊ ዉሳኔ እንዱሰጥ ያስችላል። በክስ አቤቱታ ላይ የሚገለጹ ነገሮችን አስመልክቶ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 222 ላይ ከሳሽ ለክሱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች እንዱሁም ተከሳሽ ለክሱ ምክንያት በሆነዉ ነገር ላይ በኃላፉነት የሚጠየቅበትን ሁኔታ ከሳሽ በግልጽ በክሱ ማካተት እንዲለበት፤ እንዱሁም የሚጠየቀዉ ዲኝነት በግልጽ መመልከት እንዲለበት በአንቀጽ 224 በአስገዲጅ መልክ ከደነገገባቸዉ ምክንያቶች ዉስጥ አንደ ክስ የቀረበለት ፍርድ ቤት ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉን የህግ ክፍል አስቀድሞ እንዱለይ ለማስቻል እንደሆነ ይታመናል።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ፣ ከላይ እንደተገለጸዉ፣ አመልካች ባቀረበዉ ክስ የጠየቀዉ ዲኝነት ተጠሪ በእጇ የሚገኘዉን የአባቱ ድርሻ የሆነዉን መሬት እንድታካፍለዉ ነዉ። ይህም ዲኝነቱ ከገጠር መሬት ጋር የተያያዘ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ። ምንም እንኳ አሁን በአገራችን በስራ ላይ ባለዉ የመሬት ስሪት መሰረት መሬት የህዝብ እና የመንግስት በመሆኑ እንዱሁም መሬት የእራሱ የሆነ የተለየ ባህርይ ያለዉ ቢሆንም፤ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ መብቶች እና ግዳታዎች፣ አጠቃላይ ግንኙነቶች የሚመሩት በንብረት ህግ አጠቃላይ መርሆዎች በመሆኑ የከተማም ሆነ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀምን አስመልክቶ የሚወጡ ህጎች/አዋጆች በንብረት ህግ ማዕቀፍ ዉስጥ የሚመደቡ መሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል። ስለሆነም ከንብረት ጋር በተገናኘ ያለ ጽንሰ ሃሳቦች፣ ህጎች እና መርሆዎች ከመሬት ጋር በተያያዘ ለሚቀርብ ክርክር እንደየአግባብነታቸዉ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል። በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ የንብረት ህግ ማለት ለአንድ ንብረት ባለመብት ወይም ባለይዞታ የሆነ ሰዉ ከላልች ሰዎች ጋር የሚኖረዉን ግንኙነት የሚገዛ ነዉ። የንብረት ህግ አንድ ሰዉ በአንድ ንብረት ላይ ባለቤትነት ወይም ባለይዞታ ላሆን የሚቻልበትን መንገድ፤ የመብቱ ዓይነት፣ ስፊት እና ማዕቀፍ፤ መብቱ ከአንደ ወደ ላላ ሉተላለፍ የሚችልበትን ሥርዓት የሚደነግግ የህግ ክፍል ነዉ። ንብረትን የመከታተል መብት፣ በመብቱ ማዕቀፍ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የመጠቀም መብት እንዱሁም ክስ አቅርቦ መብትን የማስከበር መብት የንብረት ባለ ሀብት ወይም ባለይዞታ መሆን ከሚሰጣቸዉ መብቶች ዉስጥ ዋነኞቹ ስለመሆናቸዉ መገንዘብ ያስፈልጋል።
አንድ ሰዉ የአንድ ንብረት ባለመብት ወይም ባለይዞታ መሆኑ የሚታወቀዉ እና የንብረት ባለ ሀብት ወይም ባለይዞታ መሆን በሚሰጣቸዉ መብቶች ተጠቃሚ ላሆን የሚችለዉ ንብረቱን በህግ አግባብ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በእጁ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑም ከአጠቃላይ የንብረት ህግ ጽንሰ ሃሳብ የምንገነዘበዉ ነዉ። ስለሆነም አንድን ንብረት አስመልክቶ የሚቀርበዉን ክስ ተከትል ንብረትን የሚመለከት የህግ ክፍል ተፈፃሚ የሚሆነዉ ከሳሽ ክሱን ያቀረበዉ ንብረቱን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በእጁ ካደረገ በኋላ በንብረቱ ላይ ያለዉ መብት እንዱከበርለት የቀረበ ክስ መሆኑ በክሱ የተረጋገጠ ሲሆን ነዉ። ይህም ማለት አንድ ከሳሽ ባቀረበዉ ክስ የጠየቀዉ ዲኝነት ንብረትን የሚመለከት መሆኑ ብቻዉን ጉዲዩን የንብረት ክርክር አያደርገዉም ማለት ነዉ። በአጠቃላይ ንብረትን የሚመለከት ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ዲኝነት ሁለት ገጽታዎች ያለት ሲሆን አንደኛዉ የንብረት ባለሀብትነት ወይም ባለይዞታነትን ወይም ከንብረቱ ጋር በተያያዘ ያለዉን ማንኛዉንም መብት ለማስከበር የሚቀርብ ዲኝነት ሲሆን፤ ሁለተኛዉ የንብረት ባለቤትነት ወይም ባለይዞታነት መብት በፍርድ ኃይል እንዱተላለፍለት በዚህም የንብረቱ ባለሀብት ወይም ባለይዞታ ለመሆን የሚቀርብ ዲኝነት ነዉ። የመጀመሪያዉ በንብረት ህግ ማዕቀፍ የሚመራ ሲሆን፣ ሁለተኛዉ ዓይነት ለቀረበዉ የመብት ይተላለፍልኝ ጥያቄ መሰረት የሆነዉን ምክንያት መሰረት በማድረግ የሚወሰን ሲሆን እንደየጉዲዩ ባህርይ በተለያዩ የህግ ማዕቀፍች መሰረት የሚዲኝ ነዉ፤ ይህም ማለት ለቀረበዉ የመብት ይተላለፍልኝ ዲኝነት መሰረቱ ዉል ከሆነ የዉል ህግ ድንጋጌዎች፣ ዉርስ ከሆነ የዉርስ ህግ ድንጋጌዎች፣ ጋብቻ መፍረሱን ተከትል የቀረበ ከሆነ የቤተሰብ ህግን መሰረት በማድረግ ላታይ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል ማለት ነዉ። ይህ፣ ከፍ ሲል በተመለከተዉ ምክንያት፣ ከመሬት ጋር የተያያዘ ለሚቀርቡ የመብት ጥያቄዎችም እንደየአግባብነታቸዉ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክስ ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ያደረገዉ የሟች አባቱ ባለቤት የነበሩት ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት ይዛ ስለምትገኝ የአባቱን ድርሻ እንድታካፍለዉ ነዉ። ይህም የሚያሳየዉ አመልካች የወራሽነት መብቱን ተጠቅሞ የአባቱን የባልነት ድርሻ መሬት ተጠሪ እንድታካፍለዉ መጠየቁን የሚያሳይ ነዉ። በአመልካች አባት እና በተጠሪ መካከል የነበረ ጋብቻ በሞት ምክንያት መፍረሱን ተከትል የቀረበ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ጥያቄን የሚመለከት በመሆኑም ጉዲዩ የሚመራዉ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል በተመለከተ በቤተሰብ ህጉ ላይ በተመለከቱት ደንቦች እና መርሆዎች መሰረት ነዉ። ይሁንና ጋብቻ መፍረሱን ተከትል የንብረት ክፍፍል ጥያቄ የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የቤተሰብ ህግ የተለየ ድንጋጌ የለዉም። የክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009ም ሆነ ከዚህ በፉት የነበረዉ አዋጅ ቁጥር 133/98 ይህን ጉዲይ የሚገዛ ድንጋጌ የላቸዉም። በአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 55 ላይ የተመለከተዉ የይርጋ ደንብም ቢሆን ያላግባብ የተያዘን የገጠር መሬት ለማስለቀቅ ለሚቀርብ የዲኝነት ጥያቄ እንጂ (ይህ የይርጋ ደንብ ይዞታዬ ያላግባብ ተይዟል በሚል ለሚቀርቡ ለሁለም ጉዲዮች ተፈፃሚነት አለዉ ወይ? የሚለዉ ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ) የባለ ይዞታነት መብት ይተላለፍልኝ በሚል ለሚቀርብ ክስ ተፈፃሚነት ያለዉ አይደለም። በልላ በኩል የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ (በቅጽ 4 ላይ እንደታተመዉ) ጋብቻ በአንደኛዉ ተጋቢ ሞት ምክንያት በፈረሰ ጊዜ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ በአስር ዓመት ጊዜ ዉስጥ ካልቀረበ ጥያቄዉ በይርጋ እንደሚታገድ የህግ ትርጉም ሰጥቷል። ይህ ዉሳኔ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 መሰረት በተያዘዉ ጉዲይ ላይ ተፈፃሚነት ያለዉ ነዉ።
በመሆኑም አመልካች አባቱ ከሞቱበት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ጥያቄ ሳያቀርብ ቆይቶ ከ20 ዓመት በኋላ ያቀረበዉ የድርሻ ይገባኛል ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ ነዉ። ስለሆነም፣ ምንም እንኳን ለቀረበዉ ክስ ምክንያት የሆነዉን ጉዲይ በአግባቡ በመመርመር ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉን የይርጋ ድንጋጌ መለየት ሲገባዉ ይህን ባለማድረግ በደፈናዉ ክሱ በይርጋ ይታገዲል ማለቱ ስህተት ቢሆንም፣ የደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካች ክስ በይርጋ ይታገዲል በሚል ክሱን ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ ከዉጤት አንፃር ሲታይ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ተከታዩ ተወስኗል።
የደቡብ ወል ዞን መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 02/05/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 01-07795 በቀን 09/07/2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት እንዱሁም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/8 በቀን 02/03/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።