የሁከት ይወገድልኝ ክስ የቀረበለት ፍርድ ቤት ሁከት የተፈጠረ መሆን ያለመሆኑን አጣርቶ በመወሰን ረገድ ሁከት ተፈጠረ በተባለበት ወቅት ንብረቱ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በከሳሽ ይዞታ ስር የነበረ መሆን አለመሆኑን እና ተከሳሽ በክሱ የተጠቀሰዉን ተግባር ለመፈጸም የሚያስችል መብት ያለዉ መሆን ያለመሆኑን እንጂ ከዚህ በላይ በመሄድ በዉርስ እና በይዞታ ባለቤትነት ላይ ተመስርቶ መወስን ተገቢነት የላለው ስለመሆኑ የፍትሐ ብሓር ህግ አንቀጽ 1140፣ 1149 (1) እና 1149 (3)
No summary available.
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሮ አሚና አደን ኡመር ተጠሪ፡- አቶ አብዱ ሙሀመድ ኡመር **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የገጠር መሬትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በሱማላ ክልል አውበሬ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረበው ክስ አደን ኡመር ከተባለ ግለሰብ ላይ ገዝቼው ይዞታነቱ የእኔ የሆነውና በቦድለይ ቀበላ የሚገኘው ስፊቱ 192 ሜትር፣ ርዝመቱ ደግሞ 226 ሜትር የሆነውና ለ24 ዓመታት ያክል ያለማንም ተቃውሞ ስጠቀምበት የቆየሁበት የእርሻ መሬት ላይ አመልካች ሁከት የፈጠረች በመሆኑ ሁከት እንዱወገድ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀዉን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ።
አመልካች በበኩሎ በሰጠችው መልስ አከራካሪውን መሬት ከአባቴ በውርስ ያገኘሁት ሲሆን ተጠሪ መሬቱን ከማንም ላይ የመግዛት መብት የለውም፤ ከተጠሪ ጋር የሚያገናኘን ምንም ነገር የላለ ሲሆን አመልካች በአካባቢው መሬት የለውም፤ በዚሁ መሬት ላይ በቀበላው አስተዲደር እና በወረዲው ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰጥቶኛል በማለት የተጠሪ ክስ ውድቅ እንዱደረግላት ተከራክራለች።
የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ የሰማው የወረዲዉ ፍርድ ቤት አከራካሪውን መሬት አመልካች በውርስ ከአባቷ ያገኘችው ነው በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጎታል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከቱት የፊፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በበኩለ የግራ ቀኙ ክርክር ጭብጥ የነበረው ሁከት ይወገድልኝ ሆኖ እያለ መሬቱ ለአመልካች ከዉርስ ጋር የተያያዘ ጭብጥ ተይዞ ውሳኔ መሰጠቱ ስህተት ነው፤መሬቱንም ተጠሪ ለ24 ዓመታት ያህል በእጁ ይዞ የቆየና አመልካችም በሀገር ውስጥ እንዲልነበረች በመረጋገጡ መሬቱ የተጠሪ ነው በማለት የስር ሁለቱ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ሽሯል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 22/03/2012 ዓ.ም በተፃፈ ሶስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተፈጽመዋል ያለቻቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረምላት ጠይቃለች። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም በአጭሩ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ክርክሩ የሁከት ይወገድልኝ ሆኖ ሳለ ይዞታው የማነው የሚለው ጭብጥ ተይዞ ውሳኔ መሰጠቱ አግባብ አይደለም በማለት የስር ሁለቱ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሲሽር ሁከት ተፈጥሯል ወይስ አልተፈጠረም የሚል ጭብጥ መስርቶ የስር ፍርድ ቤት የመሰለውን እንዱወስን ጉዲዩን መመለስ እየተገባው በህግ ከተሰጠው ስልጣን በመውጣት ማስረጃን መዝኖ መሬቱ የተጠሪ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በስር ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ ሁከት ይወገድልኝ ሆኖ እያለ ይዞታው የማነው የሚል ጭብጥ ተይዞ ውሳኔ መሰጠቱን ስህተት ነው በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ሽሮ እራሱ መልሶ ይዞታው የአመልካች ነው ሲል የሰጠዉን ዉሳኔ አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቧል። ተጠሪም በጉዲዩ ላይ መልስ አንዱሰጥበት ተደርጎ በቀን 02/07/2012 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ አከራካሪውን መሬት ከአቶ አደን ኡመር ላይ ገዝቼ አጥር አጥሬበት፣ ቤት ሰርቼ እና እያረስኩት ለ25 ዓመታት ያህል የተጠቀምኩበት ሲሆን ለ15 ዓመታት ያህል ደግሞ በስሜ ግብር ስከፍልበት ቆይቻለሁ። አመልካች ይህንን ይዞታዬን ልቀቅ በማለት አጥር ማፍረስ ስትጀምር ሁከት እንዱወገድልኝ የከሰስኳት ሲሆን የወረዲ ፍርድ ቤቱ ካቀረብኩት ዲኝነት ውጪ ይዞታው የማነው የሚል ጭብጥ በመያዝ ይዞታውን አመልካች በውርስ ያገኘችው ነው በማለት የሰጠውን ውሳኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመሻር መሬቱ የተጠሪ ይዞታ ነው ሲል የሰጠው ውሳኔ ስህተት የላለበት በመሆኑ ሉፀና ይገባዋል በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታዋን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥታለች።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ከተያዘው ጭብጥ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
እንደመረመረዉም ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክስ ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ያደረገዉ ለ24 ዓመታት በእጁ በነበረዉ ይዞታ ላይ አመልካች ሁከት የፈጠረችበት መሆኑን ሲሆን የጠየቀዉ ዲኝነትም ሁከት ይወገድልኝ የሚል ነዉ። እንደሚታወቀዉ ማንኛውም ዜጋ በንብረት መብቱ ላይ ከሚፈጸም የመብት ጥሰት በህግ ጥበቃ ይደረግለታል። ለዚህም መሰረታዊ ምክንያት ማንኛዉም ሰዉ ንብረቱን በሰላም እንዱጠቀምበት ወይም እንዱገለገልበት ለማስቻል ነዉ። በዚህም መሰረት የንብረት ባለመብት ወይም ባለይዞታ መሆን ከሚሰጣቸዉ መብቶች ዉስጥ አንደ የሁከት ይወገድልኝ ክስ አቅርቦ የባለይዞታነት መብትን ማስከበር ነው። በመሆኑም በህጋዊ ይዞታዉ ላይ ሁከት የተፈጠረበት ወይም ከህግ ዉጪ ንብረቱ የተወሰደበት ሰዉ ለፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ በይዞታዉ ላይ የተፈጠረዉ ሁከት እንዱወገድ ወይም የተነጠቀዉ ንብረቱ እንዱመለስ እንዱሁም እንደ ሁኔታዉ በሁከቱ ምክንያት የደረሰበት ጉዲት ካለ ካሳ እንዱከፈለዉ ለፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ይችላል (የፍትሐ ብሓር ሕጉ አንቀጽ 1149/1/ ይመለከቷል)። የሁከት ይወገድልኝ ክስ የቀረበለት ፍርድ ቤት ሁከት የተፈጠረ መሆን ያለመሆኑን አጣርቶ በመወሰን ረገድ ግምት ዉስጥ እንዱያስገባ የሚጠበቅበት ሁከት ተፈጠረ በተባለበት ወቅት ንብረቱ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በከሳሽ ይዞታ ስር የነበረ መሆን አለመሆኑን እና ድርጊቱን የፈጸመዉ ሰዉ ወይም ተከሳሽ በክሱ የተጠቀሰዉን ተግባር ለመፈጸም የሚያስችል መብት ያለዉ መሆን ያለመሆኑን ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1140፣ 1149(1) እና 1149(3) ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ይህም የሚያሳየዉ ሁከት መኖር አለመኖሩን በመወሰን ረገድ ከግራ ቀኝ የንብረቱ ህጋዊ ባለቤት ማን ነዉ? የሚለዉን ጭብጥ ይዞ መመርመር አግባብነት የላለዉ መሆኑን ነዉ። የፍትሐብሕር ጉዲይ የቀረበለት ፍርድ ቤት የግራ ቀኝን ክርክር መሰረታዊ ባህርይ ከግምት ዉስጥ ያስገባ ትክክለኛ የህግ እና የፍሬ ነገር ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን የመምራት ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 246(1)፣ 247 እና 248 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ይህን አለማድረግ ክርክሩ ከጊዜ እና ከወጪ አንፃር ዉጤታማ እንዲይሆን የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ በተሳሳተ ድምዲሜ ላይ ሉያደርስ የሚችል መሆኑንም ልብ ይሎል።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ይዞታ ለብዙ ዓመታት በተጠሪ እጅ የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች ተጠሪ በክሱ ላይ ያመለከተዉን ተግባር የፈጸመች ስለመሆኑ ክዲ አትከራከርም። የአመልካች ክርክር ይዞታዉ ከአባቴ በዉርስ የሚተላለፍልኝ ነዉ፤ እንዱሁም ተጠሪ ይዞታዉን ከማንም ለመግዛት መብት የለዉም፣ ሽያጩ ከመነሻዉም ዉጤት የላለዉ ነዉ የሚል ነዉ።
በእርግጥ የሽያጭ ዉለ ህገ-ወጥ ላሆን ይችላል፤ ይዞታዉም እንዱሁ በዉርስ የሚተላለፍላት ላሆን ይቸላል። ይሁንና አመልካች ይዞታዉ የሟች አዉራሼ ነዉ የምትል ከሆነ ይህንኑ በማረጋገጥ እና የሽያጭ ዉለም በህግ አግባብ እንዱፈርስ በማድረግ ተጠሪ በህግ አግባብ ይዞታዉን ለቆ እንዱያስረክባት መጠየቅ ከምትችል በስተቀር በተጠሪ እጅ የሚገኘዉን ይዞታ በኃይል ለመያዝ መብት የላትም።
ስለሆነም አመልካች በተጠሪ ይዞታ ላይ የፈጸመችዉ ድርጊት የሁከት ተግባር ነዉ የማይባልበት ምክንያት የለም። ከዚህ አንፃር ሲታይ ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ የወረዲዉ ፍርድ ቤት እንዱሁም ይግባኙ የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ጉዲይ መሰረታዊ ባህርይ ባላገናዘበ መልኩ ይዞታዉ ለአመልካች በዉርስ የሚተላለፍላት ነዉ በማለት የተጠሪን ክስ ዉድቅ ማድረጉ ስህተት በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ሁለቱ ፍርድ ቤቶች በዚህ አግባብ የሰጡት ዉሳኔ ከክርክሩ ጭብጥ ዉጪ ነዉ በማለት መተቸቱ በአግባቡ ነዉ። ነገር ግን ተጠሪ በአመልካች እጅ ያለዉን ይዞታ በኃይል መያዟን ብቻ መሰረት በማድረግ ሁከት እንዱወገድ መወሰን ሲገባዉ ከዚያ በላይ ሄድ ይዞታዉ የተጠሪ ነዉ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔም ከክርክሩ ጭብጥ ዉጪ በመሆኑ መታረም የሚገባዉ ነዉ።
በአጠቃላይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት ለረጅም ጊዜ በተጠሪ ይዞታ ስር የሚገኝ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች ከይዞታዉ መብት አለኝ የምትል ከሆነ በህግ አግባብ መብቷን ማስከበር እየቻለች ይዞታዉን በኃይል መያዟ በእርግጥም የሁከት ተግባር መፈጸሟን የሚያሳይ ሲሆን፣ በክልለ በየደረጃዉ ያለ ፍርድ ቤቶች የሁከት ተግባር ተፈጽሟል ለማለት የሚቻልበትን ሁኔታ አስመልክቶ ከላይ የተመለከቱትን የፍትሐብሕር ህግ ድንጋጌዎች መሰረት አጣርቶ የተፈጸመ የሁከት ድርጊት መኖር አለመኖሩን መወሰን ሲገባቸዉ ከዚህ በላይ በመሄድ በዉርስ እና በይዞታ ባለቤትነት ላይ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የአዉበረ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 106/09 በቀን 08/10/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፣ የፊፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 08/10/2011 በቀን 09/05/2011 ዓ.ም እንዱሁም የሶማላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 05-01-90/011 በቀን 26/02/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ይዞታ የተጠሪ ነዉ በሚል በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠዉ ዉሳኔ ተሽሮ በአንፃሩ ይዞታዉን አስመልክቶ የፈጸመችዉን ሁከት እንድታቆም ተወስኗል።
አመልካች በይዞታዉ ላይ መብት አለኝ የምትል ከሆነ መብቷን ለማስከበር ልታቀርብ የምትችለዉን ክስ ይህ ዉሳኔ አይከለክልም።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.