በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1195 (1) መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብትነት ምስክር ወረቀት በማወቅ በአስተዲደር ክፍል የተሰጠው ሰው ባለሃብት እንደሆነ የተወሰደውን የህግ ግምት ማስተባበል የሚቻለው ማስረጃው የተገኘው ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ ሁኔታ መሆኑን በማስረዲት እንደሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1196 በተደነገገበት ሁኔታ የሰው ምስክር በመስማትና ቦታው ድረስ በመሄድ የችልት ምልክታ በማድረግ የሚሰጥ ውሳኔ የምስክር ወረቀት በተሰጠበት ንብረት ላይ ባለሃብትነትን የማይለውጥ አቶ ነጋ ኃይለ እና ወ/ሮ ሀና ኃይለ
No summary available.
ቀን፡-ታህሳስ 22/2013 ዓ.ም ዳኞች፡- መዓዛ አሸናፉ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ አመልካች፡- አቶ ነጋ ኃይለ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሀና ኃይለ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ጭብጥም ቦታ እና አዋሳኙ በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰውን በ287.88 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈን ጠቅላላ ንብረት ጥር 09/2002 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል ወንድማቸው በሆኑት በአሁን አመልካች ስም በብር 35,000(ሰላሳ አምስት ሺህ) ገዝተው አመልካች ቤቱን እንዱያስተዲድሩላቸው ሰጥተው ወደ ውጭ ሀገር የሄደ መሆኑን፤ ውጭ ሀገር ሆነውም ለቤቱ ማስጨረሻ የሚሆን ብር በአመልካች ስም እየላኩ ቤቱን ያሰሩ መሆኑን፤ ከውጭ ሀገር ከተመለሱ በኋላ አመልካች በእማኞች ፉት ቤቱ የእርሳቸው መሆኑን አምነው ቤቱን የሚመለከቱ ሰነድችን በሙለ ያስረከባቸው ቢሆንም በቤቱ ውስጥ የነበሩትን ተከራዮች አስወጥተው እንዱያስረክቧቸው ሲጠይቁ ለመፈፀም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ጠቅሰው በፍርድ ኃይል ተገደው ቤቱን እንዱያስረክቧቸው ዲኝነት የሚጠይቅ ነው።
አመልካች ለዚሁ ክስ በሰጡት መልስ ቤቱን ለራሳቸው እንጂ ለአሁን ተጠሪ እንዲልገዙ፤ በሽያጭ ውለ ላይም ተጠሪ በ4ኛ ምስክርነት ከመፈረም በቀር በቤቱ ላይ መብት የላለቸው መሆኑን፤ ውጭ ሀገር ሆኜ ገንዘብ ልኬ አሰርቻለሁ ያለትም ሀሰት መሆኑን፤ ቤቱን ለማሰራት ከብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ) በላይ ወጪ ያደረጉ ሲሆን ተጠሪ ይህንን ገንዘብ ለመላክ አቅም ያልነበራቸው መሆኑን፤
ተጠሪ ከውጭ ሀገር የላኩትም 320(ሶስት መቶ ሃያ) የኩዌት ገንዘብ ብቻ ሲሆን ይህም በእለቱ የምንዛሪ ተመን 1,000(አንድ ሺህ) የኢትዮጵያ ብር ብቻ መሆኑን፤ ቤቱን የሚመለከቱ ሰነድችን ለተጠሪ የሰጡት የነበረባቸውን እዲ እንዱከፍሎቸው ተጠሪ ይጨቀጭቋቸው የነበረ በመሆኑ ለእዲ መያዥያነት በሚል እንጂ ቤቱ የሚመለከታቸው ሆኖ እንዲልሆነ፤ የቤት ባለቤትነት የሚረጋገጠው ህጋዊ ሰነድ በማቅረብ እንጂ በሰው ምስክር ባለመሆኑ እና ከዚህ አኳያ ተጠሪ ቤቱ የራሳቸው ለመሆኑ ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ ባለመኖሩ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ሰምቶ እንዱሁም ቦታው ድረስ ሄድ የችልት ምልክታ ካደረገ በኋላ በሰጠው ውሳኔ የአሁን ተጠሪ ያቀረቧቸው ምስክሮች ክስ የቀረበበት ቤት የተጠሪ ለመሆኑ ሲያስረደ በአሁን አመልካች በኩል የቀረቡት ደግሞ አመልካች ቤቱን ሲያስተዲድሩ የነበረ ከመሆኑ ውጭ ቤቱ የራሳቸው ለመሆኑ አላረጋገጡም በሚል ምክንያት አመልካች ቤቱን ለተጠሪ ሉለቁ ይገባል ብሎል። ይኸው ውሳኔ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ፀድቋል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ነሓሴ 24/2011 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት በመጥቀስ በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። የአቤቱታው መሰረታዊ ይዘትም ለክርክር ምክንያት የሆነውን ቤት በስማቸው ሲገዙም ሆነ ውል ሲዋዋለ የአሁን ተጠሪ በአካል ተገኝተው በ4ኛ ምስክርነት ስለመፈረማቸው እና የቀረቡት ላልች የሰነድ ማስረጃዎችም የንብረቱ ህጋዊ ባለቤት አመልካች መሆናቸውን በማያሻማ ሁኔታ የሚያረጋግጡ ሆነው እያለ የስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃውን በማድበስበስ አልፈው የሰጡት ውሳኔ ከህግ አግባብ ውጭ ነው፤ ቤቱን የሸጡ ግለሰብ በምስክርነት ቀርበው ቤቱን የገዛሁትም ሆነ ገንዘብ የከፈልኩት አመልካች ሰለመሆኔ አስረድተው እያለ እንዱሁም ቤቱ ላይ ህጋዊ የባለቤትነት መብት ያቋቋምኩ ለመሆኔ ተገቢነት ባላቸው እና በማናቸውም መልኩ ሉስተባበለ በማይችለ እጅግ በርካታ የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎች አረጋግጬ ባለበት የስር ፍርድ ቤቶች እነዚህን ማስረጃዎች ወደ ጎን በማለት ውሳኔ መስጠታቸው ስህተት ነው፤ በአንፃሩ የአሁን ተጠሪ ክስ የቀረበበት ቤት ላይ መብት ያላቸው ለመሆኑ የሚያስረዲ ማስረጃ አልቀረበም፤ ቤቱ ተሰርቶ ያለቀው ተጠሪ ውጭ ሀገር በነበሩበት ወቅት ሲሆን ለአመልካች የላኩት 320 የኩዌት ገንዝብ ብቻ ነው፤ ከዚህ በላይ ገንዘብ የተላከ ለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ የለም፤ የስር ፍርድ ቤቶች እነዚህን አልፈው ቤቱን ለተጠሪ እንድለቅ መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ክስ የቀረበበትን ይዞታና ቤት በተመለከተ የይዞታ ማረጋገጫው በአመልካች ስም የሚገኝ ለመሆኑ ከመረጋገጡ አንፃር የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1195 ድንጋጌን ያገናዘበ መሆን ያለመሆኑ ለዚህ ችልት ቀርቦ እንዱመረመር በመታዘዙ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
በዚሁ አግባብ ተጠሪ የካቲት 26/2012 ዓ.ም የተፃፈ መልስ ሰጥተዋል። የቀረበው መልስ ፍሬ ቃልም ቤቱ በተገዛበት ወቅት አመልካች ምንም ገንዘብ ያልነበረ ሲሆን ተጠሪ ቤቱን የገዛሁት ከባለቤቴ ጋር ተፊትቼ በንብረት ክፍፍል ከደረሰኝ ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ) ውስጥ ነው፤ ቤቱም ሲገዛ ይዞታው የገጠር ይዞታ የነበረ በመሆኑ እና በእንደዚህ ዓይነት ቦታ ላይ ውክልና መስጠት አይቻልም በመባለ ምክንያት እና አመልካች ወንድሜ በመሆኑ በመተማመን በስሙ እንዱገዛ አድርጌ ወደ ውጪ ሀገር ሄጃለሁ፤ ውጭ ሀገር ሆኜም በአመልካች ስም ገንዝብ እየላኩ ቤቱን ማሰራቴን፤ ከውጭ ሀገር ከ6 ዓመት ቆይታ በኋላ ስመጣም አመልካች በሽማግላዎች ፉት ቤቱን የሚመለከቱ ሰነድችን አስረክቦኛል፤ አለመግባባቱም የመጣው በቤቱ መኖር ስለምፈልግ ውስጥ የነበሩ ተከራዮችን እንዱያስለቅቅልኝ በመጠየቄ ነው፤ የቤቱ ስመ ሀብት በአመልካች ስም መሆኑ ባለሀብት እንደሆነ ግምት የሚያስወስድ ቢሆንም ባቀረብኳቸው ማስረጃዎች ቤቱ የራሴ መሆኑን በማስረዲት አስተባብያለሁ፤ የስር ፍርድ ቤቶችም ያቀረብኳቸውን ማስረጃዎች ብቻ ሳይሆን በቦየታው ድረስ ሄደው በችልት ምልከታ የተገነዘቡትን መሰረት አድርገው የወሰኑ በመሆኑ ውሳኔ የሚነቀፍበት ነጥብ የለውም የሚል ነው። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ በማቅረብ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሉሻር ይገባል በማለት ሞግተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም የግራ ቀኙ ክርክር ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንደተመረመረውም ግራ ቀኙ የሚከራከሩት በቤት ይገባኛል ጉዲይ በመሆኑ ክርክሩ የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት ነው። በዚህ ንብረት ላይ የባለሃብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የተሰጠው ለአሁን አመልካች ስለመሆኑ ግራ ቀኙ የተካካደት ጉዲይ አይደለም። የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብትነትን በማወቅ በአስተዲደር ክፍል የባለሃብትነት ምስክር ወረቀት የተሰጠው ሰው የዚሁ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት እንደሆነ የሚያስቆጥረው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1195(1) ይደነግጋል። በእርግጥ በዚህ መልኩ የተሰጠ ምስክር ወረቀት በራሱ ፍፁም ሳይሆን ሉስተባበል የሚችል ማስረጃ ነው። ሉስተባበል የሚችልውም የባለሀብትነት ምስክር ወረቀቱ የተሰጠው ከደንብ ውጭ በሆነ አሰራር ወይም ማስረጃውን ለመስጠት ሥልጣን በላለው አስተዲዲር ክፍል መሆኑን፤ ወይም ማስረጃው የተሰጠው በማይረጋ ፅሁፍ መሰረት ወይም ለከሳሹ መቃወሚያ ላሆን በማይችል ፅሁፍ መሰረት መሆኑን፤ ወይም ማስረጃው የተሰጠበት ንብረት የተገኘው የምስክር ወረቀቱ ከተሰጠ በኋላ ስለመሆኑ በማስረዲት እንደሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1196 ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል። የዚህ ድንጋጌ አጠቃላይ መንፈስ የሚያስገነዝበው በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1195(1) የባለሃብትነት ማስረጃን በመያዝ ብቻ የተወሰደውን የህግ ግምት ማስተባባል የሚቻለው ማስረጃው የተገኘው ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ ሁኔታ መሆኑን በማስረዲት እንደሆነ ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች ክስ በቀረበበት ንብረት ላይ በአስተዲደር ክፍል የተሰጠ የባለሀብትነት ማረጋጋጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው ለመሆኑ ተጠሪ በራሳቸው አልካደም። ከዚህ ጋር በተያያዘ በዚህ ሰበር ችልት ክርክር ያቀረቡት መከራከሪያ የንብረቱ ስመ ሀብት በአመልካች ስም የሚገኝ ቢሆንም ንብረቱ የራሴ ለመሆኑ ባቀረብኳቸው ማስረጃዎች በማረጋገጥ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1195 መሰረት የተወሰደውን የህግ ግምት አስተባብያለሁ የሚል ነው። እንግዱህ አስተዲደር ክፍል በአንድ ንብረት ላይ የባለሀብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትን የሚሰጠው ማስረጃው የተጠየቀበት ንብረት በእርግጥም የጠያቂው ስለመሆኑ በራሱ በኩል ተገቢን ማጣራት አድርጎ ነው የሚል ግምት ይወሰዲል። እናም በዚህ መልኩ የተሰጠ ማስረጃን ማስተባበል የሚቻለው ንብረቱ የእኔ ነው የሚለውን ፍሬ ነገር በማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ማስረጃውም ከህግ እና የአሰራር ደንብ ውጭ የተሰጠ መሆኑን በማረጋገጥ ነው። ከዚህ አኳያ ተጠሪ ቤቱ የራሴ ነው በማለት ይህንኑ የሚያረጋግጡላቸውን የሰው ምስክር ከማቅረብ ባለፈ ቤቱ ላይ ለአመልካች የተሰጠው የባለሃብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1196 ስር በተመለከተው አግባብ ከህግ እና አሰራር ደንብ ውጭ የተሰጠ ስለመሆኑ ያቀረቡት መከራከሪያም ሆነ ያረጋገጡት ነገር የለም። ይህ ባልተረጋገጠበት ተጠሪ ማስረጃውን አስተባብለዋል የሚያስብል ነገር ባለመኖሩ ተጠሪ አረጋገጫለሁ የሚለት ፍሬ ነገር ለአመልካች የተሰጠውን ማስረጃ ዋጋ የሚያሳጣው አይሆንም።
ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ በየደረጃው ያለት የክልለ ፍርድ ቤቶች በህግ አግባብ የተሰጠ እና ባለው የህግ ስርዓት ያልተስተባበለ የባለሀብትነት ማረጋገጫ ማስረጃን ወደ ጎን በማለት አመልካች ቤቱን እንዱለቁ መወሰናቸው ግልፅ የህግ ድንጋጌን የተላለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ በእርግጥም የሚነቀፍ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/26077 ላይ መጋቢት 18/2011 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እንዱሁም የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/03140 ላይ ታህሳስ 28/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
የዚህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.