No summary available.
መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዲ 10 ቤቶች አስተዲደር ጽ/ቤት ተጠሪ፡- ጂብሪል ሚስባህ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች መስከረም 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. በቀን 06/03/2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. በቀን 18/11/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች የመቃወም አመልካች፣ የአሁን ተጠሪ እና በዚህ የሰበር ክርክር የላለ ወ/ሮ አብረኸት አለማየሁ እና አቶ ንዲጋ ከማል ደግሞ የመቃወም ተጠሪዎች ሆነው ተከራክረዋል። የአሁን አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ያቀረበው የመቃወም አቤቱታ ይዘት በአጭሩ፡- ፍርድ ያረፈበት በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዲ 10 ቤ.ቁ 1223 የሆነው ቤት አካል የሆነው አንድ ክፍል ቤት ባለቤትነቱ የአመልካች መሆኑ እና የስር 2ኛ እና 3ኛ የመቃወም ተጠሪዎች ተከራይተው የሚኖሩበት ቤት መሆኑን፤ የተጠቀሰው ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሷል ወይስ አልተወረሰም የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የሚያስችል ስልጣን ሳይኖረው የወሰነ መሆኑን ይህንኑ ቤት አስመልክቶ የተሰጠው ውሳኔ ይሻርለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
የአሁን ተጠሪ በሰጡት መልስ ፍርድ ያረፈበት ቤት የግል ቤት መሆኑን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ ይህንኑ ቤት በሚመለከት አስቀድሞ የሰጠው ውሳኔ ሉጸና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የስር 2ኛ እና 3ኛ የመቃወም ተጠሪዎች እንደ አመልካች አቤቱታ አቀራረብ ፍርድ ያረፈበት የመንግስት ቤት ነው ተብል ይወሰንልን በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ከሚመለከተው አካል ስለጉዲዩ ተጣርቶ እንዱቀርብለት ካደረገ በኋላ በአመልካች የቀረቡት ሰነድች በሙለ የቤት ቀጥር 1224 ን የሚመለከቱ ናቸው፤ ፍርድ ያረፈበት በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዲ 10 ቁጥሩ 1223 የሆነው እና በካርታ ቁጥር 18/36/3523/00 የሚታወቀው ቤት የተጠሪ ቤት መሆኑ የክፍለ ከተማው የይዞታ አስተዲደር የሽግግር ጊዜ አገልግልት ፕሮጀክት ጽ/ቤት በሰጠው ማስረጃ ተረጋግጧል፤ ጽ/ቤት ከዚህ ቀደም በሰጠው ማስረጃም የስር 2ኛ እና 3ኛ የመቃወም ተጠሪዎች የሚኖሩበት ቤት ለተጠሪ በተሰጠው ካርታ ውስጥ የተካተተ መሆኑን አረጋግጧል፤ የአመልካች የመቃወም አቤቱታን መነሻ በማድረግ ፍርድ ቤቱ በድጋሚ በሰጠው ትዕዛዝም በተሰጠው የቤት ቁጥር 1223 የተጠሪ ቤት መሆኑ እና የቤት ቁጥር 1223 እና 1224 የተለያዩ ቤቶች ወይም አንድ ቤት መሆን አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል መረጃ እንደላለው ገልጾአል፤
በተመሳሳይ የንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የቤቶች አስተዲደር ጽ/ቤት በሰጠው ምላሽም ቁጥሩ 1223 የሆነው ቤት የግል ቤት መሆኑ እና ቁጥር 1224 ደግሞ የመንግስት ቤት መሆኑን ሁለቱም ቤቶች በአንድ ግቢ በአንድ ጣራ ተያይዘው የሚገኙ እና የያራሳቸው ክፍል ያላቸው ቤቶች መሆናቸውን አረጋግጧል፤ ለተጠሪ የተሰጠው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለጊዜው የታገደ መሆኑን የተገለጸ ቢሆንም ካርታው መታገደ ቤቱ የአመልካች መሆኑን አያረጋግጥም፤ ካርታው በሕጉ አግባብ አስካልመከነ ድረስ ተጠሪ ባለቤት እንደሚሆኑ ግምት ይወሰዲል፤ ስለሆነም ይህንኑ ቤት አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ አስቀድሞ የሰጠው ውሳኔ ሉሻር አይገባም በማለት ወስኗል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ መዝገቡን ለውሳኔ ከቀጠረ በኋላ አመልካች የአከራካሪው ቤት ካርታ ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ.ም የመከነ መሆኑን የሚያሳይ ተጨማሪ ማስረጃ እንዲለው ገልጾ ፍርድ ቤቱ ይህን ማስረጃ እንዱቀበለው አመልክቷል። ፍርድ ቤቱም አመልካች ተጨማሪ ማስረጃ እንዱያያዝለት ያቀረበውን አቤቱታ ክርክሩ ተጠናቆ መዝገቡ ለፍርድ ከተቀጠረ በኋላ የቀረበ ስለሆነ ጥያቄው ስነ ስርዓታዊ አይደለም በማለት ውድቅ አድርጎታል። በመቀጠልም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ተጠሪ የጠየቀው ዲኝነት በሕጋዊ ካርታ ግብር እየከፈልኩ የምጠቀምበት ቤት ይለቀቅልኝ የሚል በመሆኑ አመልካች አዋጅ ቁጥር 47/67ን በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የሚያስችል ስልጣን የለውም በማለት ያቀረበው መከራከሪያ አግብብነት የለውም፤ ተጠሪ አከራካሪውን ቤት አስመልክቶ የተሰጠው ካርታ ስለመምከኑ የቀረበ ማስረጃ ስለላለ ተጠሪ የቤቱ ሕጋዊ ባለቤት እንደሆነ ይገመታል በማለት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዘቱም፡- አከራካሪው ቤት ለረጅም ዓመታት በመንግስት እጅ የቆየ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የሚያስችል የስረ ነገር ስልጣን የለውም፤ አመልካች የተጠሪ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በቀን 20/08/2009 ዓ.ም ታግድ እንደነበረ እና በቀን 13/09/2010 ዓ.ም እንደ መከነ የሚያሳይ ተጨማሪ ማስረጃነት እንዱያያዝ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቧል፤ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ማስረጃው ሉያያዝ አይገባም በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገ ቢሆንም ይህንኑ በፍርደ ላይ ሳያስቀምጥ ካርታው ስለመምከኑ የቀረበ ማስረጃ የለም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ለክርከሩ ምክንያት የሆነውን ቤት አካቶ ለተጠሪ ተሰጥቶ የነበረው ካርታ እንዱመክን የተደረገ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ደብዲቤ በተጨማሪ ማስረጃነት እንዱታይለት ለስር ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 327(3) መሰረት አቤቱታ አቅርቦ በብይን ውድቅ በተደገረበት ሁኔታ ካርታው ስለመምከኑ የቀረበ ማስረጃ የለም በሚል የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የማጽናቱን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ለተጠሪ የተሰጠው ካርታ እንዱመክን ደብዲቤ ከተጻፈ በኋላ ለተጠሪ እንዱፃፍ እና እንዱያውቀው ሳያደርጉ ስሙን በቀድሞ ሻጭ በማድረግ ጉዲዩ ለብይን ከተቀጠረ ከ10 ወራት በኋላ ተጨማሪ ማስረጃ ይያያዝልን በማለት ያቀረቡት ጥያቄ አግባብነት የለውም፤ አመልካች ተወርሷል ተብለው በመንግስታዊ እና ህዝባዊ ተቋማት ቁጥጥር ስር ያለ ቤቶች በተያያዘ መርምሮ የመወሰን ስልጣን የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ እንጂ የፍርድ ቤቶች አይደለም በማለት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጣቸውን ውሳኔዎች በመጥቀስ ያቀረበው ክርክር ለጉዲዩ አግባብነት የለውም፤ ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ ሑደት መገንዘብ የቻልነው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአሁን ተጠሪ እና በስር 2ኛ እና 3ኛ የመቃወም ተጠሪዎች መካከል ሲደረግ በነበረው ክርክር መርምሮ ውሳኔ የሰጠው በቀን 26/11/2008 ዓ.ም መሆኑን፤ አመልካች ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት አቤቱታ ያቀረበ መሆኑን እና ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ ለተጠሪ የተሰጠው ካርታ እስካልመከነ ድረስ ተጠሪ የአከራካሪው ቤት ባለቤት እንደሆነ ይገመታል በማለት በቀን 06/03/2010 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ አስቀድሞ በመዝገቡ የሰጠውን ውሳኔ ያጸና መሆኑን፤ አመልካች ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ መሆኑን፤ በመቀጠልም በቀን 15/02/04 ዓ.ም በካርታ ቁጥር 18/36/3523/00 የተሰጠው ካርታ ከቀበላ ቤት ጋር ተቀላቅል የወጣ መሆኑ ስለተገለጸ የክፍለ ከተማው መሬት ልማት ማኔጅመንት በቀን 03/09/2010 ዓ.ም ባጸደቀው መሰረት መክኗል በማለት ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ.ም የጸፈውን ደብዲቤ በተጨማሪ ማስረጃነት እንዱቀበለው ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረበ መሆኑን፤ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤት ደግሞ አመልካች ያቀረበውን የተጨማሪ ማስረጃ ላያይዝ ጥያቄ መዝገቡ ለውሳኔ ከተቀጠረ በኋላ የቀረበ ነው በማለት ውድቅ አድርጎ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ያጸና መሆኑን ነው። ስለሆነም በዚህ ችልት ምላሽ ሉያገኝ የሚገባው የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ ፍርድ ቤቱ የአሁን ተጠሪን እና የስር ተከሳሾችን አከራክሮ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ እንዱሁም አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት ባቀረበው አቤቱታ መነሻነት ግራ ቀኙን አከራክሮ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ካርታዉ መምከኑ ፍርደን የሚያስለዉጥና ተጠሪ በፍርድ ያረጋገጠዉን መብት የሚያሳጣ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
የአሁን ተጠሪ መብት ያገኙበት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዱመክን የተደረገው ከፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላ ሲሆን ካርታውን ለማምከን አስተዲደሩ የሰጠው ምክንያት ከቀበላ ቤት ጋር ተቀላቅል የተሰጠ ነው በሚል ነው።
በመሰረቱ መንግስት የሕዝብና የመንግስትን ንብረት የመጠበቅና የማስጠበቅ ሃላፉነት እና ግዳታ እንዲለበት ሁለ የግለሰቦችን የንብረት መብት የማክበርና የማስከበር ሃላፉነት እንዲለበት ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 9(1)(2)፤ 12/1 እና 40/1 ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም እነዚህን ሁለት መሰረታዊ የመንግስት ሀላፉነቶች መነሻ በማድረግ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1195 የማይንቀሣቀስ ንብረት ባለሃብትነትን በማወቅ በአስተዲደር ክፍል የምስክር ወረቀት ሲሰጥ የምስክር ወረቀቱን ያገኘው ሰው የማይንቀሣቀሰው ንብረት ባለሀብት ሆኖ ሉገመት እንደሚገባ ይደነግጋል። ሆኖም ይህ የሕሉና ግምት ካርታው የተሰጠው ከደንብ ውጪ በሆነ አሰራር ወይም ይህን ለመስጠት ስልጣን በላለው የአስተዲደር ክፍል ወይም በማይረጋ የምስክር ወረቀት መሰረት ማስረጃ ተሰጥቶ ከሆነ ማፍረስ እንደሚቻል የዚሁ ሕግ ቁጥር 1196 ድንጋጌ በግልጽ ያሣያል። ስለሆነም አንድ የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሚሰረዝበት አካሄድ ሕጋዊ ስርዓት የተበጀለት ከሆነና በሕግ አግባብ የተገኘውን ማስረጃ መሰረት አድርጎ የመፊለም ክስ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት አቅርቦ ዲኝነት ያገኘ ሰው በዚሁ ፍርድ መሰረት መብቱ ከሚከበርለት በቀር ከፍርድ በኋላ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተሩ ተከራካሪ ሁኖ በተረታው አካል በመሰረዙ ምክንያት በፍርድ የተረጋገጠለትን መብት ሉያጣ አይገባም።
የአስተዲደር አካለ በፍርድ ቤት ክርክር መረታቱን ከተረዲ በኃላ በሕጉ የተሰጠውን ስልጣን መነሻ በማድረግ ለፍርደ መስጠት መሰረት የሆነውን ማስረጃ ዋጋ በማሣጣቱ ምክንያት ጉዲዩ እንደ አዱስ ላታይ ይገባዋል ከተባለ ውጤቱ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 37 ላይ ለዜጎች የተሰጠውን ፍትሕ የማግኘት መብት እንዲይረጋገጥ እና ከሁለም በላይ ደግሞ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 78/1 እና 79(1) እና (4) ስር የተረጋጠውንና የተከበረውን የነፃ ፍርድ ቤት መኖርንና የዲኝነት ስልጣን ትርጉም አልባ የማድረግ እና ክርክሮች መቋጫ እንዲይኖራቸው የማድረግ ውጤት አለው።
ስለሆነም አመልካች በክርክር ሂደት በፍርድ አደባባይ ከተረታ በኋላ ተጠሪ መብት ያገኘበትን ካርታ በማምከን አስቀድሞ የተሰጠው ውሳኔ እንዱለወጥለት ያቀረበዉ አቤቱታ አግባብነት የለውም።
በመሆኑም የስር ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በውጤት ደረጃ ተቀብለን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
No topics extracted.