በባለሀብትነት መብት አለመጠን መገልገል በተፈጠረ ጊዜ ይህንን አስመልክቶ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1149 እና 1225 መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ላቀርብ የሚችለው በተጨባጭ በይዞታ መብት ላይ የተፈጠረን የሁከት ተግባር ለማስወገድ እንጂ ሉሰራ የታሰበ ሰራ ሉያስከትል የሚችለውን ጫና በመገመት ባልተፈፀመና ወደፉት ሉፈጠር በሚችል ድርጊት ላይ የሁከት ክስ ላቀርብ የማይችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149 ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 9(1) (2)፤ 12/1 እና 40/1 ድንጋጌዎች እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1195 እና 1196 እና ጂብሪል ሚስባህ
No summary available.
ጥቅምት 26/2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ መኮንን ስሜነህ ተጠሪ፡
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዲዩ ለዚህ ችልት የቀረበው አመልካች በተጠሪ መኖሪያ ቤት አካባቢ የወፍጮ ቤት ስራ ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመራቸው የሁከት ተግባር በመሆኑ ሉቆም ይገባል በማለት የተወሰነበትን የህግ አግባብ መርምሮ ለመወሰን ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በደቡብ አቸፈር ወረዲ ፍርድ ቤት በአሁን አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። የቀረበው ክስ ይዘትም አመልካች ለሆቴል ስራ በሚገለገለበት G+2 ህንፃቸው ጎን የወፍጮ ስራ ለመስራት ቤት ገንብተው እና የመብራት ቆጣሪ አስገብተው በዝግጅት ላይ መሆናቸውን፤ በቦታው ላይ ወፍጮ ከተተከለ ለጤናም ሆነ ለማህበራዊ ኑሮ ችግር የሚያደርስባቸው መሆኑን በመግለፅ ድርጊቱ የሁከት ተግባር ነው ተብል እንዱወገድላቸው ዲኝነት የሚጠይቅ ነው።
የአሁን አመልካችም ለዚሁ ክስ በሰጡት መልስ ክሱ የቀረበው ወደፉት ሁከት ይፈጠርብኛል በሚል ሲሆን በተጠሪ እና በወፍጮ ቤቱ መካከል የ50 ሜትር ርቀት ያለ በመሆኑ እና የተጠቀሰው ህንፃም ለሆቴል ስራ ሳይሆን ለብረታ ብረት እና ላልች እቃዎች ንግድ እየዋለ ያለ በመሆኑ የሚፈጠር ሁከት የለም፤ ተጠሪ በራሳቸው በቦታው ላይ የወፍጮ ስራ ለመስራት በባለቤታቸው ስም ፈቃድ አውጥተው በሂደት ላይ ያለ በመሆኑ ሁከት ይፈጠርብኛል በሚል ክስ ሉያቀርቡ አይችለም በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆን ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት የወረዲው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን በመስማት እንዱሁም ስለ ጉዲዩ አግባብነት አለው ካለው የአስተዲደር ክፍል ተጣርቶ እንዱቀርብለት ካደረገ በኋላ የወፍጮ ስራው በቦታው ላይ መቀጠል በተጠሪ አኗኗር ላይ ሁከት የሚያስከትል ስለመሆኑ አረጋግጫለሁ በሚል ምክንያት ግንባታው እንዱቆም ወስኗል።
ይህንኑ ውሳኔ በይግባኝ የተመለከተው የባህር ዲር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የከተማው መሪ ፕላን የትኛው ስራ በየትኛው ሳይት ላይ መሰራት እንዲለበት ለይቶ ባላስቀመጠበት አመልካች በህጋዊ መንገድ በቦታው ላይ የወፍጮ ስራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ንግድ ፈቃድ አውጥተው ስራ መጀመራቸው የሁከት ተግባር ነው የሚባል አይደለም በሚል የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሽሯል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ይህንኑ ወሳኔን አፅንቷል።
የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በበኩለ በሰ/አ/መ/ቁጥር 03-76409 ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ሰኔ 05/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ እና ትዕዛዝ በመሻር የወረዲ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔን በመቃወም ነው። አመልካች ሐምል 25/2011 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። ፍሬ ቃለም የወፍጮ ስራው ባልተጀመረበት እና ሁከት ስለመፈፀሙም የተረጋገጠ ነገር በላለበት ሁከት ተፈጥሯል መባለ ከህግ አግባብ ውጪ ነው፤ ከተጠሪ ጋር የማንዋሰን እና በመካከላችንም የአራት ሰዎች ቤት እያለ እንዱሁም ተጠሪ በራሱ ተመሳሳይ ስራ ለመስራት በሂደት ላይ እያለ የወፍጮ ስራው መጀመር ሁከት ይፈጥራል በሚል መወሰኑ አግባብ አይደለም የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በመግቢያው ላይ የተገለፀውን ነጥብ ግራ ቀኙ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ጉዲዩ ለዚህ ችልት እንዱቀርብ በመታዘዙ ምክንያት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪ ህዲር 29/2012 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የሁከት ክስ በተፈጠረ ሁከት ላይ ብቻ ሳይሆን ወደፉት ሉፈጠር በሚችል ድርጊት ላይም ላቀርብ የሚችል በመሆኑ እና የስር ፍርድ ቤቶችም በዚሁ መልኩ የወፍጮ መተከል በተጠሪ ኑሮ እና ጤና ላይ እርግጠኛ የሆነ ጉዲት ሉያደርስ እንደሚችል አጣርተው የወሰኑ በመሆኑ ውሳኔው ሉነቀፍ አይገባም በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ በማቅረብ ሞግተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም የግራ ቀኙ ክርክር ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ፤ በስር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ከክርክሩ አጀማመር መረዲት እንደሚቻለው የአሁን ተጠሪ ለወረዲው ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ አመልካች በቤቴ አጎራባች ላይ ሉሰራ በሂደት ላይ ያለው የወፍጮ ስራ በኑሮ እና ጤናዬ ላይ ችግር የሚያስከትል በመሆኑ ድርጊቱ የሁከት ተግባር ነው ተብል ሁከቱ ይቁምልኝ የሚል ነው።
እንግዱህ የአንድ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው ንብረቱን በተመለከተ በህግ ከተረጋገጡለት መብቶች ውስጥ አንደ በሀብቱ ላይ የተፈጠረው ህገ ወጥ ሁከት እንዱወገድለት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ማቅረብ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149(1) ይደነግጋል። በመሰረቱ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149(1) የሁከት ተግባርን የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮችን ከመጥቀስ ባለፈ በራሱ “ሁከት” ለሚለው ቃል የሰጠው ግልፅ ትርጉም የለም። ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለውም የሁከት ተግባር የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮች ተብለው የተጠቀሱት ሁለት ድርጊቶች ናቸው። አንደኛው ባለይዞታው በሀብቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም መብቱ ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት አልያም የሚፈጠር እንቅፊት (Interferance) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በባለይዞታው እጅ የነበረን ንብረት/ይዞታ/ በሙለ ወይም በከፉል በመውሰድ ባለይዞታውን በዚያው መጠን ይዞታ አልባ ማድረግን (Dispossession) የሚመለከት ነው።
በልላ በኩል የሁከት ተግባሩ በሁለት መንገድ ሉፈፀም የሚችል ስለመሆኑ በዚሁ ዙሪያ ከተደረጉ የምርምር ፅሁፍች ይዘት መገንዘብ ይቻላል። አንደኛው ይዞታውን ከባለይዞታው እጅ በመውሰድ ወይም በይዞታው ሰላማዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም መብት ላይ በተጨባጭ/በተግባር/ የሚፈፀም ጣልቃ ገብነት/Disturbance in fact/ ነው። ላላኛው ደግሞ በባለይዞታው የይዞታ መብት ላይ በህግ ረገድ የሚፈጠር ሁከት/Disturbance in law/ የሚል ነው። ሁለተኛው የሁከት ዓይነት አብዛኛውን ጊዜ የሚፈፀመው አስተዲደር ክፍል ይዞታውን በተመለከተ በራሱ ተነሳሽነትም ሆነ በልላ ወገን ጠያቂነት በተለያየ መንገድ የባለይዞታውን የይዞታ መብት በሚነካ መልኩ በሚወሰደው አስተዲደራዊ እርምጃ ነው። ይህ አስተዲደራዊ እርምጃ እንደየሁኔታው ባለይዞታው ይዞታውን በተመለከተ አንድን ድርጊት እንዱፈፅም ወይም እንዲይፈፅም በማድረግ አልያም የባለሃብትነት መብቱን የሚያሳጣ ወይም የሚገድብ ተግባር በመፈፀም ላሆን ይችላል።
በእነዚህ ሁኔታዎች በይዞታው ላይ ሁከት የተፈጠረበት ባለይዞታ የተወሰደበት ነገር እንዱመለስለት ወይም የተነሳው ሁከት እንዱወገድለት እና በድርጊቱ ስለደረሰው ጉዲት ኪሳራ እንዱሰጠው በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ እና ዳኞችም ይኸው ስለመፈፀሙ ሲያረጋግጡ የተፈጠረው ሁከት እንዱወገድ እና ተገቢ ሆኖ ሲገኝም ካሳ እንዱከፈል ሉወስኑ እንደሚችለ ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149 ድንጋጌ ጠቅላላ ይዘት መገንዘብ ይቻላል። ይህ ሲሆንም ፍርድ ቤቶች በሁከት ክስ አርዕስት የቀረበው ጉዲይ በልላ የህግ ማዕቀፍ ከሚስተናገድ ክርክር ጋር እንዲይቀላቀል ተገቢውን ጥንቃቄ ሉያደርጉ እና ክርክሩንም ሆነ የቀረበውን ማስረጃ ከዚሁ አኳያ ብቻ ሉመለከቱ ይገባል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ ክስ ያቀረቡት በተጨባጭ በይዞታ መብታቸው ላይ የተፈጠረን የሁከት ተግባር ለማስወገድ ሳይሆን ሉሰራ የታሰበው የወፍጮ ቤት ስራ ሉያስከትል የሚችለውን ጫና በመገመት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ በተጨባጭ ባለተፈፀመ ድርጊት ላይ በይሆናል የሁከት ክስ የሚቀርብበት የህግ ማዕቀፍ የለም። ከተጠሪ ክስ ጭብጥ በግልፅ መረዲት የሚቻለውም ጉዲዩ በቀጥታ የሚመለከተው በፍትሐ ብሕር ህግ ቁጥር 1225 ስር የተመለከተውን በባለሀብትነት መብት አለመጠን ስለመገልገል ጉዲይን እንጂ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1149 ስር የተመለከተውን በይዞታ ላይ የሚፈጠር የሁከት ተግባርን አይደለም።
በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1225 መሰረት በባለሃብትነት መብት አለመጠን የመገልገል ተግባር መኖር አለመኖሩ የሚለየው የመብቱ አጠቃቃም በጉርብትና አኗኗር ሉታገሱት ከሚቻለው በላይ በአጎራባች ነዋሪዎች መብት ላይ ጉዲት የሚያደርስ መሆኑን በማረጋገጥ ነው። ይህን ለማረጋገጥ ደግሞ በዚህ መልኩ ክስ የቀረበበት ሰው በንብረት መብቱ ቢያንስ መጠቀም መጀመርን የሚጠይቅ ይሆናል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች የወፍጮ ስራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ሂደቶች ከመጀመር ባለፈ ስራው በተጨባጭ አልተጀመረም። ይህ ባልሆነበት የወፍጮ ስራው በተጠሪ አኗኗር እና ጤና ላይ ጉልህ የሆነ ጉዲት የሚያደርስ ስለመሆኑ በተጨባጭ የሚታወቅ ነገር የለም። እናም የስር ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን በዚህ መልኩ ሉያስተናግደ ሲገባ ለጉዲዩ አግባብነት የላውን የህግ ድንጋጌን ጠቅሰው ግማሹ ሁከት አለ ሲል ላላው ደግሞ ሁከት የለም በማለት መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ አረዲድ እና አተገባበር ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/አ/መ/ቁጥር 03-76409 ላይ ሰኔ 05/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በባህር ዲር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/0312523 ላይ ጥር 08/2010 ዓ.ም ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት በፍ/መ/ቁ/01.47520 ላይ ሚያዝያ 05/2010 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ ምክንያቱ ተለውጦ በውጤት ደረጃ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የዚህን ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.