የይመስል ውል (simulated contract) እና ሽሽግ ውል (counter-deed or back-letter) ተቋቁመዋል የሚያሰኙ ሕጋዊ መሰረቶችና ሕጋዊ ውጤታቸው፡አንድ ባለእዲ ለባለገንዘቦች የገባውን ግዳታ ላለመወጣት ካለው ወ/ሮ ፍሬህይወት ጋሜ እና እነ ወ/ሮ ኤልሳቤት ኪ/ማሪያም በመነሳት ብቻ ሳይከስር በእጁ ያለው ሀብት ለባለገንዘቡ የመብት ጥያቄ ማስፈፀሚያ እንዲይውል በተለያዩ መንገድች በተንኮል ንብረቱን በግዥ ወይም በስጦታ አገኘሁ ከሚል ሶስተኛ ወገን ጋር በመመሳጠር ባለገንዘቡን የሚጎዲ የአጭበርባሪነት ተግባር በመፈፀም ንብረቱን ቢያስተላለፍ ከሶስተኛ ወገን ጋር የተደረገው ውል ሕጋዊ ውጤት የማይኖረው ስለመሆኑ (2 ሰዎች)
No summary available.
መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሮ ፍሬህይወት ጋሜ ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ወ/ሮ ኤልሳቤት ኪ/ማሪያም 2ኛ. ኤስኤን ቢ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ቤት ገንብቶ የማስረከብ ዉል አፈጻጸም መነሻ ያደረገ ክርክር የሚመለከት ነዉ።ክርክሩ የተጀመረዉ 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ መነሻ ሲሆን የአሁን አመልካች ደግሞ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተሰጠ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 መሰረት በመቃወም የተከራከሩ ናቸዉ። የክሱም ይዘት በአጭሩ፡ከተጠሪ ጋር በቀን 19/11/2003 ዓ/ም በተደረገ ውል ስምምነት 2ኛ ተጠሪ G+1 የሆነ የቤተሰብ መኖሪያ ቤት በ9 ወራት ውስጥ ገንብቶ ስመ-ንብረቱን በ1ኛ ተጠሪ ስም ለማስረከብ ግዳታ የገባ ሲሆን፤ 1ኛ ተጠሪ ደግሞ ብር 4,478,000.00 ለመክፈል ስምምነት አድርገናል።በዚህ መሰረት 1ኛ ተጠሪ በውለ አንቀፅ 3/6 ስር በተቀመጠው የአከፊፈል መንገድ በአጠቃላይ ብር 3,950,000 የከፈልኩ ቢሆንም ተከሳሽ በውለ መሰረት በ9 ወራት ውስጥ ቤቱን ገንብቶ ስመ ንብረቱን በ1ኛ ተጠሪ ስም አስመዝግቦ የማጠቃለያ ሥራ አከናውኖ በውል በገባው ግዳታ መሰረት ሉያስረክበኝ አልቻለም። በመሆኑም 2ኛ ተጠሪ በውለ መሰረት በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16 ከተሰሩት 28 ነጠላ የቤተሰብ ቤቶች ቪላ ውስጥ በስሜ ሲከፈልበት የነበረውን ብልክ ሲ6 የካርታ ቁጥር 4/9/9/22/521/00 የሆነውን ቤት ገንብቶ አጠናቆ ስመ ንብረቱን በ1ኛ ተጠሪ ስም አስመዝግቦ ከሉዝ ክፍያ ነፃ የሆነ ቤት በውለ ግዳታ መሰረት እንዱያስረክበኝ፤ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ገንብቶ ሉያስረክበኝ ከሚገባው ጊዜ በእጅጉ የዘገየ በመሆኑ ማስረከብ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ የሚታሰብ በወር ብር 5,000.00 እና ለደረሰብኝ መጉላላት ኪሳራ በውለ መሰረት ተሰልቶ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
2ኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጠዉ መልስ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በሐምል 19 ቀን 2003 ዓ/ም ላይ ቤት ገንብቶ ለማስረከብ የውል ስምምነት እንዲደረገ አምኖ ነገር ግን ከመንግስት በተሰጠ ትዕዛዝ በተያዘው መሬት ላይ ማንኛውም የቤት ግንባታ እንዲይደረግ እገዲ ተጥልበት ከቆየ በኋላ እግደ የተነሳው በቀን 15/12/2006 ዓ/ም ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ለሁለት ዓመታት ያህል ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት 2ኛ ተጠሪ የቤት ግንባታውን ማከናወን አልቻለም። 1ኛ ተጠሪ በተለያየ ጊዜ ለ2ኛ ተጠሪ የከፈለት በክሱ ላይ እንደገለፁት ሳይሆን ብር 3,450.000 ብቻ ነው። በውለ መሰረት ቀሪ ክፍያቸውን ብር 1,028,000.00 ከፍለው እንዱረከቡ 2ኛ ተጠሪ በተደጋጋሚ በቃልና በፅሁፍ የጠየቀ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ግን ብር የለኝም በማለት ሉከፍለ አልቻለም። 2ኛ ተጠሪ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው ከ9 ወራት በኋላ በቀን 09/09/2009 ዓ/ም በተፃፈ ደብዲቤ 1ኛ ተጠሪ እንደ ውለ ሉፈፅሙ ባለመቻላቸው በውል ስምምነታችን መሰረት ከከፈለት ገንዘብ ላይ 3 ፏርሰንት ተቀንሶ የከፈለት ገንዘብ ከሚመለስላቸዉ በቀር ቤት ለመረከብ ክስ ማቅረብ አይችለም። በመሆኑም 1ኛ ተጠሪ በውል ስምምነታችን መሰረት ክፍያ ባለመፈፀማቸው 2ኛ ተጠሪ 1ኛ ተጠሪ የጠየቁትን ክፍያ በርትዕ የሚከፍልበት ምክንያት የለም።ዉለ የፈረሰዉ 1ኛ ተጠሪ ግዳታቸዉን ባለመወጣታቸዉ ምክንያት በመሆኑ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ለማስረከብ አይገደድም ተብል ክሱ ዉድቅ እንዱደረግለት በመጠየቅ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 03/05/2010 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪዎች በቀን 19/11/2003 ዓ/ም ባደረጉት ውል መሰረት 1ኛ ተጠሪ ያለባቸዉን ቀሪ ክፍያ ባለመክፈላቸዉ የበኩላቸዉን ግዳታ ሳይወጡ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ለማስረከብ አይገደድም ሲል ክሱን ውድቅ በማድረግ ወስኗል።1ኛ ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 06/09/2010 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን በጊዜዉ ገንብቼ ማስረከብ ያልቻልኩበት ምክንያት ግንባታ እንዲይካሄድ በመንግስት እግድ በመሰጠቱ ነዉ በማለት የተከራከረዉን በተመለከተ 2ኛ ተጠሪ እግደ ሳይሰጥ በፉት 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ገንብቶ ለማስረከብ የሚያስችል በቂ ጊዜ ነበረዉ፤2ኛ ተጠሪ ቤቱን ገንብቶ አስረክቦ በዉለ መሰረት መሰብሰብ ሲገባዉ ዉለን በተናጠል ማቋረጡ ተገቢ አይደለም።የስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ግዳታቸዉን ሳይወጡ 2ኛ ተጠሪ ግዳታቸዉን እንዱወጡ መጠየቅ አይችለም ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ የግራ ቀኙን ዉል ይዘት ያገናዘበ አይደለም በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር በክሱ የተጠቀሰዉን ቤት ግንባታ አጠናቆ ስመ ሀብቱን ወደ 1ኛ ተጠሪ እንዱያዛዉሩ፤2ኛ ተጠሪም ቀሪ ክፍያ የመጠየቅ መብት አለዉ ሲል ወስኗል።
በመቀጠል 2ኛ ተጠሪ በፋደራል ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ በመ/ ላይ አቅርቦ ችልቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 24/03/2011 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ የይግባኝ ሰሚዉን ውሳኔ በማሻሻል 2ኛ ተጠሪ ቤቱን አጠናቆ ለ1ኛ ተጠሪ እንዱያስረክብ እና ስመ ሀብቱን እንዱያዛውር ሲል የሰጠውን የውሳኔ ክፍል በማፅናት ቀሪ ክፍያውን በተመለከተ 2ኛ ተጠሪን ክስ አቅርቦ የመጠየቅ መብት በመጠበቅ የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል በመሻር ክርክሩ በዚያው መዝገብ ቀጥል ክፍያውን በተመለከተ ውሳኔ ላሰጥበት ይገባል ሲል ጉዲዩን በዚህ ረገድ ለፈዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መልሷል።
ጉዲዩ ከላይ በተመለከተዉ መሰረት ከተወሰነ በኋላ እንደገና የተንቀሳቀስዉ አመልካች በይግባኝ ሰሚዉ ችልት በተሰጠ ዉሳኔ መብታቸዉ እንደተነካ በመግለጽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 መሰረት ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ሲሆን የአቤቱታቸዉም ይዘት በአጭሩ፡- የመቃወም አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ በቀን 10/01/2010 ዓ/ም ድርድር ተደርጎ በቀን 27/01/2010 ዓ/ም በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት በተደረገ ዉል 2ኛ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት ለአመልካች በብር 4,500,000.00 ሽጧል።አመልካች ቤቱን የገዛሁት ቤቱ ከዕዲና እገዲ ነጻ መሆኑን በማረጋገጥ ነዉ።በዚህ አግባብ አመልካች የቤቱ ባለሀብት ከሆንኩ በኋላ ቤቱን ተረክቤ ብር 873,120.00 ተጨማሪ ወጪ በማዉጣት ቤቱን በአመልካች ፍላጎት መሰረት ምቹ ለማድረግ ተጨማሪ ማስተካከያ/ግንባታ አድርጌያለሁ። 2ኛ ተጠሪም ከአመልካች ጋር ግብይት ባደረገ ጊዜ በቤቱ ላይ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ክርክር እንዲለው አላሳወቀኝም። አመልካች ቤቱን ከ2ኛ ተጠሪ ስለተረከብኩ 1ኛ ተጠሪ ከግንባታ ዉለ ጋር የተያያዘ ግንኙነት ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ከሚኖረዉ በስተቀር በቤቱ ላይ መብት የላቸዉም ተብል ዉሳኔዉ እንዱሻርላቸዉ አቤታቸዉን አቅርበዋል።
ይግባኝ ሰሚዉ ችልት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎችን መርምሮና መዝኖ በቀን 15/06/2011 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች የ2ኛ ተጠሪ ማኅበር 50 ከመቶ ባለአክሲዮ/ባለድርሻ የሆኑት የአቶ ዲዊት ዘሪሁን ባለቤት በመሆናቸዉ ሽያጩ እዉነት አይደለም እንጂ እዉነት ነዉ ቢባል እንኳን ሽያጩ ከባለቤታቸዉ ጋር የተደረገ በመሆኑ አስቀድሞ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ያደረገዉ ፀንቶ ባለበትና ክርክርም በፍርድ ቤት መኖሩን ባለአክሲዮኖች እያወቁ አመልካች የትዲር አጋራቸዉ በመሆናቸዉ ጉዲዩ በፍርድ ቤት ተይዞ ያለ በመሆኑ በድጋሚ መሸጥ ያልተገባ ድርጊት ነዉ።በመሆኑም አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር አደረጉት የተባለዉ ዉል በእዉነት ላይ የተመሰረተ ግብይት ሳይሆን ሆነ ተብል ቤቱ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲይተላለፍና ፍርድ እንዲይፈጸም ለማድረግ የቀረበ አቤቱታ ነዉ በማለት የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ አስቀድሞ የሰጠዉን ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 360/2 በመሰረት በማጽናት ወስኗል።
በመቀጠል አመልካች ለዚሁ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበዉ ችልቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 28/05/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ በግልጽ የቀረበን ክርክር እና የተቆጠረን ማስረጃ መሰረት በማድረግ ተገቢዉን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን አጣርቶ ዉሳኔ አለመስጠት መሰረታዊ የክርክር አመራር ጉድለት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 246 እና ተከታዮቹን መሰረት በማድረግ በሰ/መ/፣39144 እና በተለያዩ የሰበር መዝገቦች ላይ አስገዲጅነት ያለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።አመልካች አስቀድሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 41 መሰረት ወደ ክርክሩ መግባት ይችለ ነበር የሚለዉ የ1ኛ ተጠሪ መከራከሪያ ተገቢነትና ዉጤቱ፣ በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ የቤት ሽያጭ ዉል የማስመሰል ዉል ነዉ በማለት 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መከራከሪያ እና ማስረጃዎች ተገቢነትና ዉጤቱ፣ዉለ እዉነተኛ ዉል ነዉ ቢባል እንኳን ዉለ የተደረገዉ በአመልካች እና የአመልካች የትዲር አጋር ባለአክሲዮን በሆኑበት 2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገ ዉል መሆኑ ከሦስተኛ ወገን መብት አንጻር የሚኖረዉ ዉጤት ከሕግ አንጻር የሚያስከትለዉ ዉጤት፣ በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ የቤት ሽያጭ ዉል ከ1ኛ ተጠሪ መብት አንጻር ተፈጻሚነት ሉኖረዉ አይገባም ቢባል አመልካች በቤቱ ላይ ተጨማሪ የማስተካከያ ግንባታ አድርገዋልን?አድርገዋል ከተባለ የወጪ መጠንና ዉጤቱስ ምን ላሆን ይገባል? አመልካች ቤቱን ከገዙ በኋላ ቤቱ አሁን በሚገኝበት ሁኔታ የደረሰዉ በአመልካች ገንዘብ ነዉ ከተባለ እና በልላ በኩል ሻጭ ለማስረከብ የሚገደደዉ በ1ኛ ተጠሪ ገንዘብ የተገነባዉን ነዉ የሚለዉንና ቤቱ በሶስተኛ ወገን እጅ መኖሩ የሚፈጥረዉ ሕጋዊ ዉጤት ምን ላሆን ይገባል የሚለትንና ተያያዥ ጭብጦች በማስረጃ አጣርቶ ሕግን መሰረት ያደረገ ዉሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343/1 መሰረት ለይግባኝ ሰሚዉ ችልት መልሶለታል።
ይግባኝ ሰሚዉ ችልት መዝገቡን አንቀሳቅሶ ከፍ ሲል በተገለጸዉ መሰረት የተያዙትን ጭብጦች ከግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃዎች አንጻር መርምሮ በቀን 26/08/2013ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ አከራካሪዉን ቤት በተመለከተ ክስ መቅረቡንና ክርክር መኖሩን አስቀድሞ አመልካች ያዉቁ የነበረ መሆኑን ለማስረዲት 1ኛ ተጠሪ አቅርበዉ ያሰሟቸዉ ምሰክሮች በክርክራቸዉ መሰረት አላስረደም። የ2ኛ ተጠሪ ባለድርሻ የሆኑት አቶ ዲዊት ዘሪሁን የአመልካች የትዲር አጋር በመሆናቸዉና አቶ ዲዊት ዘሪሁን ደግሞ የክርክሩን መኖር ያዉቁ ስለነበር በተዘዋዋሪ መንገድ አመልካች የክርክሩን መኖር ያዉቁ እንደነበር ግምት ይወሰድልኝ ሲለ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት ክርክር በግምት ላይ የተመሰረት ከሚሆን በስተቀር በማስረጃ የተረጋገጠ አይደለም።ስለሆነም 1ኛ ተጠሪ አመልካች የክርክሩን መኖር አስቀድመዉ ያዉቁ ነበር በማለት ያቀረቡትን ክርክር በማስረጃ አላስረደም በማለት ወስኗል።
አንዱሁም በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ ዉል እዉነተኛ ዉል ነዉ ወይስ የማስመሰል ዉል ነዉ የሚለዉን ጭብጥ በተመለከተም የ2ኛ ተጠሪ ባለድርሻዎች አቶ ቴዎድሮስ ዘሪሁን ላቀዉ እና አቶ ዲዊት ዘሪሁን ላቀዉ መሆናቸዉ እና አቶ ዲዊት ዘሪሁን ከአመልካች ጋር በጋብቻ ተሳስረዉ የሚኖሩ መሆናቸዉ ግራ ቀኙ የማይካካደትና በማስረጃም የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ናቸዉ።አመልካች የቤት ሽያጭ ዉለን ባለቤታቸዉ አባል ከሆኑበት ኃላፉነቱ ከተወሰነ የግል ማኅበር ጋር መዋዋላቸዉ በራሱ ዉለን የማስመሰል ዉል የሚያደርገዉ አይደለም።ሆኖም 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ ክስ የመሰረቱት በቀን 24/02/2010ዓ/ም ሲሆን ክስ ከማቅረባቸዉ በፉት ከ2ኛ የመቃወም ተጠሪ ጋር በቤቱ ጉዲይ አለመግባባት ዉስጥ ገብተዉ የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል።አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ዉል በአዋዋይ ፉት ያደረጉትም 1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ስላደረጉት ዉል አፈጻጸም ጉዲይ አለመግባባት ላይ በነበሩበት ጊዜ በቀን 27/01/2010ዓ/ም ነዉ።የአመልካች ባለቤት የ2ኛ ተጠሪ ማኅበር ሥራ አስኪያጅ መሆናቸዉ ባይረጋገጥ እንኳን ከላላኛዉ የማኅበሩ ባለድርሻ ጋር ባላቸዉ ቤተሰባዊ ትስስር ምክንያት በማኅበሩና በ1ኛ ተጠሪ መካከል በዉለ አፈጻጸም ጉዲይ አለመግባባት መከሰቱን አያዉቁም ነበር ማለቱ የማኅበራዊ ኑሮን ገሀዲዊ እዉነታ መሰረት ያደረገ ላሆን አይችልም።ቤቱ የተገዛዉ ጋብቻዉ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ነዉ።ቤቱ የአመልካች የግል ንብረት እንጂ የባለቤታቸዉ ድርሻ ያለበት አይደለም በሚል በአመልካች በኩል የቀረበ ክርክር የለም።በመሆኑም የማኅበሩ ባለድርሻ የአከራካሪዉም ቤት የጋራ ባለሀብት ይሆናለ።እንዱህ አይነት ግብይት በመሰረቱ የሦስተኛ ወገኖችን መብት የሚነካ እስካልሆነ ድረስ በንግድ ሕጉም ሆነ ለጉዲዩ አግባብነት ባላቸዉ ላልች ሕጎች ክልከላ ያለበት አይደለም።ይሁን እንጂ የማኅበሩ አንደኛ ባለድርሻ ባለቤት የሆኑት አመልካች ወደግዥዉ የገቡት በተለመደዉ የክንዉኖች ፍሰት ተመርተዉ ሳይሆን በማኅበሩ አንደኛዉ ባለድርሻ ባለቤት/አመልካች/ አማካኝነት የ1ኛ ተጠሪን መብትና ጥቅም ለመጉዲት እና 1ኛ ተጠሪ ተከራክረዉ ሉያሰጡ የሚችለትን ፍርድ ከወዱሁ ለማጨናገፍ በማሰብ 2ኛ ተጠሪ በወሰደዉ እርምጃ መነሻ መሆኑን ክርክሩ ያሳያል።በመሆኑም በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ የሽያጭ ዉል ከ1ኛ ተጠሪ መብት አንጻር የማስመሰል ዉል ነዉ ከሚባል በስተቀር አዉነተኛ ዉል ነዉ ለማለት የሚቻል አይደለም።ዉለ በአዋዋይ ፉት መደረጉም የማስመሰል መሆኑን የሚያስቀር አይደለም።ዉለ ከአመልካች አንጻር እዉነተኛ ነዉ ቢባል እንኳን አመልካች የደረሰባቸዉን ጉዲት ከ2ኛ ተጠሪ መጠየቅ የሚችለ ከሚሆን በቀር 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የገባዉን በፍርድ ጭምር የተረጋገጠዉን የዉል ግዳታ እንዲይፈጽም እንደመከላከያ ሉያገለግል የሚችል አይደለም።ለእንዱህ አይነት የዉል ማሰናከያ መንገድች መፍቀድ ዜጎች በዉልች ላይ እምነት እንዱያጡ የሚያደርግ ነዉ።ስለሆነም በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል በቀን 27/01/2010ዓ/ም የተደረገዉ የ1ኛ ተጠሪን መብትና ጥቅም ለመጉዲት በማሰብ የተደረገ የማስመሰል ዉል ነዉ የሚል ድምዲሜ ላይ ተደርሷል።
በተጨማሪም አመልካች ባቀረቡት ማስረጃዎች ቤቱን ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ ዉል ገዝተዉ ከያዙ በኋላ አንዲንድ የማጠናቀቂያ ሥራዎችን መስራታቸዉን ያስረደትን 1ኛ ተጠሪ ሥራዉ አለመሰራቱን በማስረዲት አላስተባበለም።በልላ በኩል በ1ኛ ተጠሪና በ2ኛ ተጠሪ መካከል በተደረገዉ ዉል መሰረት 2ኛ ተጠሪ የተጠናቀቀ ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ግዳታ ገብቷል።አመልካች ብር 873,120.00 ለቤቱ ተጨማሪ ወጪ ያወጡት የዱዛይን ለዉጥ በማድረግ የተወሰኑ ግንባታዎችን በማፍረስ እንደሆነ አቤቱታቸዉ የሚያሳይ ሲሆን ያቋረቧቸዉ ምስክሮችም የግድግዲ ቁምሳጥን፣የኪችን ሥራ፣የደረጃ መወጣጫ፣የጂብሰም ሥራ እና ላልችንም ተመሳሳይ ሥራዎችን መስራታቸዉን መስክረዋል።ከዚህ ዉጭ የዱዛይን ለዉጥ በማድረግ እና የተወሰኑ ግንባታዎችን በማፍረስ የለዉጥ ሥራዎችን የሰሩ ስለመሆኑ ግን ምስክሮቹ የሰጡት ምስክርነት አያሳይም።በአመልካች በተሰሩ ሥራዎች መካከል አንዲንድቹ የቤቱ ግንባታ አካል ሆነዉ በ2ኛ ተጠሪ ሉሰሩ የሚችለ ቢሆኑም ያወጡትን ወጪ ከ2ኛ ተጠሪ መጠየቅ ከሚችለ በስተቀር የተሰሩ ሥራዎች የዋጋ ግምት ከአጠቃላይ ቤቱ እና ከቤቱ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር ቤቱን ይዘዉ እንዱቀሩ ለመወሰን የሚያስችል ዉጤት የሚያስከትለ አይደለም።ስለሆነም ይህ ችልት አስቀድሞ በቀን 06/09/ 2010ዓ/ም እና በቀን 15/06/2011ዓ/ም የተሰጠዉን ዉሳኔ የሚያስለዉጥ ምክንያት አልተገኘም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 360/2 መሰረት በማጽናት ወስኗል።
አመልካች በቀን 11/09/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ፡- የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ያደረጉት ውል ሆነ ብለው 1ኛ ተጠሪን ለመጉዲት አስበው ነው ሲል በማስረጃ ያልተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችን በመውሰድ በሕግ ግምት እንዱወሰድባቸው ያልተደነገጉ ፍሬ ነገሮች ላይ ግምትን መሰረት በማድረግ የሰጠዉ ውሳኔ ነዉ።አመልካች ቤቱን የገዙት 1ኛ ተጠሪ የዉል ግዳታቸዉን መወጣት ባለመቻላቸዉ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ያለዉን ዉል ከሰረዘ በኋላ ነዉ። ይግባኝ ሰሚዉ ችልት የአመልካች ባለቤት አቶ ዲዊት ዘሪሁን የ2ኛ ተጠሪ ባለአክሲዮን ከሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ዘሪሁን ጋር ባላቸው ቤተሰባዊ ትስስር ምክንያት በ2ኛ እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል ያለውን አለመግባባት አቶ ዲዊት ዘሪሁን አያውቁም ብል መገመት አይቻልም ያለበት አግባብ እና ግብይቱ 1ኛ ተጠሪን መብትና ጥቅም ለመጉዲት የተደረገ ነዉ ሲል በማስረጃ ባልተረጋገጠ ፍሬ ነገር ላይ ግምት በመዉሰድ የደረሰበት ድምዲሜ በሰ/መ/፣37105 እና በላልችም ላይ የተሰጠ አስገዲጅ ትርጉም የሚቃረን በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። አንድ ባለአክሲዮን ባለአክሲዮን የሆነበትን ኩባንያ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እንዱያዉቅ አይጠበቅም ወይም ያዉቃል ተብል የሕግ ግምት አልተሰጠበትም።2ኛ ተጠሪ ሲሰራ የነበረዉ 45 ቪላ ቤቶችን እና ላልች አፓርታማ ቤቶችን ስለሆነ ስለዚህ ቤቶች ሁለ ሽያጭ ሥራ አስኪያጅ ያልሆኑትና በ2ኛ ተጠሪ የሥራ እንቅስቃሴ ዉስጥ ተሳትፍ የላላቸዉ ባለአክሲዮን ያዉቃለ ተብል ሉገመት አይችልም።አመልካች ዉለን በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ከመፈራረማቸዉም በተጨማሪ የቤቱን ሽያጭ ዋጋ ስለመክፈላቸዉ የተጨማሪ እሴት ታክስ(ተ.እ.ታ) ደረሰኝ በማቅረብ አረጋግጠዋል።ተ.እ.ታ ለመንግስት ተከፍልበት ክፍያ የተፈጸመበት ሽያጭ የማስመሰል ዉል አለመሆኑ አንደ አመላካች ነገር ነዉ።
በተጨማሪም ይግባኝ ሰሚዉ ችልት ግን በዚህ መከራከሪያ ነጥብ ላይ ምንም ሳይል አልፎል።ዉለ የማስመሰል ቢሆን ኖሮ አመልካች ብር 873,120.00 የሚያህል ከፍተኛ ወጪ በማዉጣት ቤቱ ላይ ከፍተኛ ግንባታ አያካሂደም ነበር።ይግባኝ ሰሚዉ ችልት ከዚህም አንጻር ለቀረበዉ ክርክር ምንም ሳይል አልፍታል።የማስመሰል ዉል የሚባለዉ በተዋዋይ ወገኖች መካከል እዉነተኛ ዉል ሳይኖር፣ለሶስተኛ ወገን ግን ዉል ያለ እንዱመስል ተደርጎ የሚገባ ዉል ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም ጉዲዩን ለይግባኝ ሰሚ ችልት ሲመልስ ከዚህ አንጻር እንዱጣራ ሆኖ እያለ ችልቱ ግን የተዋዋይ ወገኖችን ሀሳብ በመመርመር ቅን ልቦናን መሰረት አድርጎ የተፈጸመ ዉል ነዉ ወይስ አይደለም ከሚል አንጻር አይቶ ግምትን መሰረት አድርጎ ድምዲሜ ላይ እንዱደርስ ባለመሆኑ የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እንደሆነ ያሳያል።እንዱሁም አመልካች በገዙት ቤት ላይ ከፍተኛ ግንባታ በማከናወን እንደሰሩ ስለተረጋገጠ ዉለን አፍርሶ ወደ ነበሩበት ለመመለስ የማይቻል ስለሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1817 መሰረት የአመልካች የቤት ባለቤትነት እንደ ረጋ እንዱቀር በአንጻሩ 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ተመሳሳይ ቤት የመተካትን እና መሰል አማራጭ የካሳ አከፊፈል መንገድች በመከተል አለመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ አመልካች በቤቱ ላይ ሕጋዊ ባለቤት ስለሆኑ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ለ1ኛ ተጠሪ ያስረክቡ ተብል የተሰጠዉ ዉሳኔ ይሻርልኝ በማለት በመጠየቅ አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
ሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ ለክርክር ምክንያት በሆነዉ ቤት ላይ እገዲና እዲ ያለመኖሩን አረጋግጦና ግዥ ፈጽመዉ ስመ ሀብቱ በስማቸዉ ዞሮ በሚመለከተዉ አካል ተመዝግቦ እና በአመልካች ተጨማሪ ግንባታ አካሂደዉ ባለበት የስር ፍርድ ቤት በተጨባጭ ያልተረጋገጡ ግምቶችን በራሱ ጊዜ በመዉሰድ አመልካች ቤቱን እንዱለቁ የወሰነበትን አግባብ ከፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 1817፣ 2330፣ 2090፣2119 እና ከሰ/መ/፣43845፣39336 እና ተያያዥ ትርጉሞች ጋር ተገናዝቦ እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በሚከተለዉ መሰረት መልሳቸዉን አቅርበዋል።
1ኛ ተጠሪ በቀን 22/11/2013 ዓ/ም ጽፈዉ ባቀረቡት መልስ፡- አመልካች ለክርክር መነሻ የሆነው ቤት ስመ ሀብት በአመልካች ስም የዞረ ነው በሚል የተከራከሩ ቢሆንም የቀረበ ማስረጃ የለም። የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠዉ የቀረቡለትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መሰረት አድርጎ እንጂ በግምት ላይ ተመስርቶ አይደለም። የአመልካች ባለቤት እና የ2ኛ ተጠሪ ባለድርሻ መካከል ያለው ቤተሰባዊ ትስስር፣ 2ኛ ተጠሪ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በመሆኑ ቤተሰባዊ ትስስር ባላቸዉ ሰዎች የተቋቋመ መሆኑ አመልካች እንዲለት ትርጉም የማይሰጥ ተራ ነገር ተደርጎ የሚታለፍ አይደለም። የስር ፍርድ ቤት እነዚህንና በአመልካች እና የ2ኛ ተጠሪ በባለአክሲዮኖቹ መካከል ያለዉ ግንኙነት ሆነ ተብል የ1ኛ ተጠሪን መብት ለመጉዲት የተደረገ ዉል እንደሆነ ያሳያል ሲል የደረሰበት ድምዲሜ በቀረቡት የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች የተረጋገጡትንና በክርክሩ ሂድት ያልተካደ ፍሬ ነገሮችን መሰረት ያደረገ ነዉ።በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል በተደረገ ዉል ላይ ገንዘቡ በዉለ ደረሰኝነት እንደተከፈለ መገለጹ፣ነገር ግን አመልካች በማስረጃነት ያቀረቡት ደረሰኝ ቁጥር 001 አዱስ ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የደቤ ሽያጭ እንደተፈጸመ የሚያሳይ መሆኑ አመልካች ከተ.እ.ታ ጋር ክፍያ ፈጽመናል ያለት እንደከፈለና ሽያጩ እዉነት እንደሆነ ለማስመሰል ያቀረቡት እንደሆነ ያሳያል።የሽያጭ ዉለ ገንዘብ ሳይከፈል እንደተከፈለ ተደርጎ ዉል መፈጸሙ በእርግጥ ንብረቱን በሽያጭ ስም ከ1ኛ ተጠሪ በማዉጣት በባለቤታቸዉ አቶ ዲዊት ዘሪሁን በኩል የድርጅቱ ባለድርሻ ለሆኑት ንብረት የማሸሽ መንገድ እንጂ በቅን ልቦና የዉልን መሰረተ ሃሳቦች ባከበረ መልኩ የተደረገ ዉል አለመሆኑን የሚያሳይ ነዉ።
እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ሰርቶ እንዱያስረክበኝ 1ኛ ተጠሪ በ2003ዓ/ም ሲዋዋል የቤቱ ዋጋ ብር 4,478,000.00 የነበረ ሲሆን ከ7 ዓመት በኋላ አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር አደረኩኝ ባለት ዉል ላይ ቤቱ በብር 4,500,00.00 ለወደፉት ሰርቶ ሲያስረክቡ አንድ ቤት ያለዉ ዋጋ እና ምንም አይነት ክፍያ ሳይፈጽም ያለቀ ቤት የሚሸጥበት ዋጋ በማንኛዉም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት አንድ ወይም ተቀራራቢ ላሆን ስለማይችል ማስረጃን እንደሚመዝን ፣ፍሬ ነገሮችን ትርጉም ባለዉ እና ምክንያታዊ በሆነ አግባብ ለሚተነትን ፍርድ ቤት በእርግጥ ሽያጩ የ1ኛ ተጠሪን መብት በመጉዲት ንብረቱን በቤተሰብ ደረጃ የማስቀረት ስልት መሆኑ አከራካሪ አይደለም።የአመልካች እና የ2ኛ ተጠሪ ባለድርሻ አቶ ዲዊት ዘሪሁን ሚስት መሆናቸዉ ላላኛዉ ባለድርሻ አቶ ቴዎድሮስ ዘሪሁን ደግሞ የአቶ ዲዊት ወንድም መሆናቸዉ ያለዉ እንድምታ 2ኛ ተጠሪ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በመሆኑ ከሚኖረዉ ባህርይ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ ሚስት በሚሉዮን ብር ቤት ሲገዙ ባል አያዉቅም ተብል ሰለማይገመት፣በ2ኛ ተጠሪ ዉስጥ ያለዉ ግማሽ የአክሲዮን ዋጋ የአመልካች ባለቤት ብቻ ሳይሆን የአመልካች የጋራ ሀብት ጭምር መሆኑ፣ ሚስት ቤቱን እየገዙ ያለት የጋራ ንብረታቸዉ ከሆነዉ 2ኛ ተጠሪ ላይ መሆኑ የሚያሳየዉ በቤተሰባዊ ትስስር የ1ኛ ተጠሪን መብት ለመጉዲትና አለአግባብ ለመበልጸግ እንደሆነ የሚያሳይ ነዉ።አመልካች በቤቱ ላይ ተጨማሪ ግንባታ ማካሄዲቸዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1817 እና 2330 መሰረት ቤቱን የእሳቸዉ የሚያደርግ አይደለም።አመልካች በቤቱ ላይ የፉኒሽንግ ሥራ ከመስራት ባለፈ በቤቱ ላይ መሰረታዊ ለዉጥ የሚያመጣ አፍርሶ የመስራት ሥራ አልሰሩም።የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1817 ተፈጻሚነትም በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንጂ በ1ኛ ተጠሪ ላይ አይደለም።የቤቱ ዋጋ በአሁኑ ጊዜ ከብር 15,000,000.00 በላይ ስለሚያወጣ አመልካች አወጣሁኝ ያለት ወጪ እጅግ አነስተኛ ነዉ።የቤቱን 20 በመቶ የማያክል ሥራ ወደነበርንበት ለመመለስ አስቸጋሪ ነዉ በማለት የቀረበዉም ክርክር የሕግ ድጋፍ ያለዉ አይደለም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠዉ ፍሬ ነገሮችን በሚገባ አረጋግጦ በመሆኑ ጉድለት ስለላለበት ይጽናልኝ በማለት ተከራክረዋል።
2ኛ ተጠሪ በቀን 30/10/2013ዓ/ም በሰጠዉ መልስ 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች ቤቱን ሸጠዉ ዕዲና እገዲ ያለመኖሩ ተጣርቶ፣በሁለተኛ ተጠሪና በ1ኛ ተጠሪ መካከል የነበረዉ ዉል ተቋርጦ በነበረበት ጊዜ በመሆኑ፣አመልካች ቤቱን የገዙት በቅን ልቦና በመሆኑ፣ይግባኝ ሰሚዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ ከፍሬ ነገር ይልቅ በግምት ላይ የተመሰረተ በመሆኑና ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በተለያዩ ጊዜያት የሰጠዉን የሕግ ትርጉም የሚቃረን በመሆኑ፣በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ ዉል የማስመሰል ዉል ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ ሳይኖር ይግባኝ ሰሚዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ ነዉ በማለት መልሱን ሰጥቷል።አመልካችም የመልስ መልስ በማቅረብ አቤቱታቸዉን በማጠናከር ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ በአጭሩ የተመለከተዉ የግራ ቀኙን ክርክርና በተለያየ ጊዜ ከጉዲዩ ጋር በተያያዘ በየደረጃዉ ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ቤቱን ስለገዛሁና ተጨማሪ ግንባታም ስለፈጸምኩበት 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች ሉያስረክብ ይገባል ተብል የተሰጠዉ ዉሳኔ መብቴን ስለሚነካ ይሻርልኝ በማለት ያቀረቡት የተቃዉሞ አቤቱታ ዉድቅ በመደረጉ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደተመረመረዉም በ1ኛ ተጠሪ እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል በቀን 19/11/2003 ዓ/ም በተደረገ ውል መሰረት 2ኛ ተጠሪ በክሱ የተጠቀሰዉን ቤት ግንባታዉን አጠናቆና ስመ ሀብቱን በ1ኛ ተጠሪ ስም አድርጎ ለ1ኛ ተጠሪ እንዱያስረክብ ይግባኝ ሰሚዉ ችልት ጉዲዩን በመ/ ላይ በይግባኝ ተመልክቶ በቀን 06/09/2010 ዓ/ም ዉሳኔ ሰጥቷል። ይህ የዉሳኔ ክፍል በዚሁ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በቀን 24/03/2011ዓ/ም በተሰጠዉ ዉሳኔ ፀንቷል።አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 መሰረት በመቃወም አቤቱታ ያቀረቡት 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ እንዱያስረክብ ዉሳኔ የተሰጠበትን ቤት በተጠሪዎች መካከል የተደረገዉ ዉል ተቋርጦ በነበረበት ጊዜ ከዕዲና እገዲ ነጻ መሆኑን በማረጋገጥ በዉል አዋዋይ ፉት በቀን 27/01/2010 ዓ/ም በተደረገ ዉል ገዝቼ በመረከብ ተጨማሪ የማሻሻያ ግንባታ ያደረኩበት በመሆኑ ባለቤት የሆንኩበትን ቤት 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ እንዱያስረክብ የተሰጠዉ ዉሳኔ መብቴን የሚነካ ስለሆነ ሉሻር ይገባል በማለት ነዉ።1ኛ ተጠሪ በዚህ የተቃዉሞ አቤቱታ ላይ ያቀረቡት ክርክር ከላይ በዝርዝር የተመለከተ ሲሆን በዋናነት ክርክራቸዉ አመልካችና የ2ኛ ተጠሪ ግማሽ ባለድርሻ ባለትዲሮች በመሆናቸዉ የማኅበሩ 2ኛ ባለድርሻም የአመልካች ባል ወንድም በመሆናቸዉ፣ በማኅበሩ ዉስጥ የአመልካች ባል ባላቸዉ ድርሻ ላይ አመልካችም የጋራ ባለሀብት በመሆናቸዉ፣ቤቱም የተገዛዉ ከዚሁ የጋራ ባለሀብት ከሆኑበት 2ኛ ተጠሪ ላይ በመሆኑ እና አመልካች በሚሉዮኖች ብር ቤት ሲገዙ ባለቤታቸዉ አያዉቁም ተብል ስለማይገመት ከቤት ርክክብ ጋር በተያያዘ በተጠሪዎች መካከል የነበረዉን አለመግባባት እያወቁ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን እንዲይረከቡ በማድረግ የ1ኛ ተጠሪን መብትና ጥቅም በመጉዲት ቤቱን 2ኛ ተጠሪ በሽያጭ እንዲስተላለፈ በማስመሰል ለማሸሽ የተደረገ ዉል ነዉ።እንዱሁም የቤቱ ዋጋ ከ7 ዓመት ባላይ ቆይቶ በተቀራራቢ ዋጋ እንደተሸጠ መገለጹና አመልካች የቤቱን ዋጋ ሳይከፍለ እንደከፈለ ተድርጎ በዉለ ላይ መጻፈ ዉለ የይስሙላ መሆኑን ስለሚያሳይ የአመልካች አቤቱታ ዉደቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል። 2ኛ ተጠሪም ለአመልካች ቤቱ የተሸጠዉ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የተደረገዉ ዉል ተቋርጦ ባለበት ጊዜ በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ተገቢ ነዉ ሲል ተከራክሯል።
ከዚህ ከግራ ቀኙ ክርክር በመነሳት ከላይ ለያዝነዉ ዋና ጭብጥ ተገቢዉን ዉሳኔ ለመስጠት ይረዲ ዘንድ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ የቤት ሽያጭ ዉል ለይምሰል የተደረገ ዉል (simulated contract) ነዉ ወይስ በ1ኛ ተጠሪና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ ዉል እንዲይፈጸም ለማድረግ (2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ያለበትን ግዳታ ላለመወጣት) ብል በተንኮል የተፈጸመ ዉል ነዉ? ዉለ ለይምሰል የተደረገ መሆኑ በምን አግባብ ሉረጋገጥ ይችላል? ለይምሰል የተደረገ ዉል በሦስተኛ ወገን መብት ላይ የሚያስከትለዉ ሕጋዊ ዉጤት ምንድን ነዉ? በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የቤት ሽያጭ ዉል የተደረገዉ 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ያለበትን ግዳታ ላለመወጣት ብል በተንኮል የፈጸመዉ ዉል ነዉ የሚባል ከሆነ የተንኮል ተግባር መኖሩስ በምን አግባብ ሉረጋገጥ ይገባል?
የሚለ ተጓዲኝ ጭብጦች አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር ተገናዝቦ ዉሳኔ ማግኘት ያለባቸዉ ናቸዉ። በዚህ ረገድ ይግባኝ ሰሚዉ ችልት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎች መርምሮና መዝኖ በሰጠዉ ዉሳኔ በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ ዉል በእርግጥም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገ ሳይሆን ቤቱን 1ኛ ተጠሪ እንዲይረከቡ በማድረግ የ1ኛ ተጠሪን መብትና ጥቅም ለመጉዲት ታስቦ የተደረገ የማስመሰል ዉል በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ተቀባይነት የለዉም የሚል የፍሬ ነገር ድምዲሜ ላይ ደርሷል።
በቀዲሚነት በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ የቤት ሽያጭ ዉል ለይምሰል የተደረገ ዉል (simulated contract) ነዉ ወይ? በሚል የያዝነዉን ጭብጥ መርምረናል።የይምሰል ዉል (simulated contract) በታዋቂዉ ብላክስ ልዉ መዝገበ ቃላት(በ9ኛ እትም ገጽ 373) ላይ የሚከተለዉ ትርጓሜ ተሰጥቶታል፡- simulated contract … A contract that, by mutual agreement, does not express the true intent of the parties.- A simulated contract is absolute when the parties intend that the contract will impose no obligations; no obligations are enforceable on the parties by such a contract. A simulated contract is relative if the parties intend it to impose obligations different from those recited in the contract; the intended obligations are enforceable if all relevant conditions are met. A simulated contract may affect the rights of third parties.ይህም በግርድፈ የይምሰል ዉል ማለት የተዋዋዮችን እዉነተኛ ሀሳብ(ፍላጎት) የማያሳይ ስምምነት ነዉ።የይምሰል ዉል ፍጹማዊ እና አንጻራዊ ተብል የሚታወቅ ሲሆን የመጀመሪያዉ አይነት የይምሰል ዉል በተዋዋዮች ላይ ምንም ግዳታ የማይፈጥር እና የሚፈጸም ምንም ግዳታ የላለበት ነዉ።ሁለተኛዉ አንጻራዊ የይስሙላ ዉል የሚባለዉ ደግሞ ተዋዋዮች በዉል ከተስማሙት በተለየ ሁኔታ ግዳታ ለማቋቋም አስበዉ ያደረጉት ከሆነ በዚህ መልኩ ያቋቋሙት ግዳታ ላልች አስፈላጊ ሁኔታዎች ሲሟለ እንዱፈጸም የሚደረግ ነዉ።የይምሰል ዉል የሦስተኛ ወገኖችን መብት ሉነካ የሚችል ነዉ የሚል ሀሳብ የያዘ ነዉ።
የይስሙላ ዉል በተመለከተ የሕግ ትንታኔ የጻፈ አንድ አድሪያን ጋብሪኤል ዱነስኩ(Adrian-Gabriel Dinescu) የተባለ የሕግ ምሁር “simulated contract is nothing else than to lie about something,to present a distorted truth and which is presented to the outsider world as true …whilest between the parties ,a secret agreement is drawn, the true expression of their will, and which is adversely different than the apparent contract.” በሚል ይገልጸዋል።ይህም በግርድፈ የይምሰል ዉል ስለአንድ ተግባር ከመዋሸትና እዉነታዉን ከማዛባት የዘለለ ካለመሆኑም በተጨማሪ በምስጢር የተደረገዉ ላላ እዉነተኛ ስምምነት እያለ ከተዋዋዮቹ ዉጭ ለሆኑ ሰዎች እዉነተኛዉ ዉል ይህ ለይምሰል የተደረገዉ ዉል እንደሆነ አስመስል ለማቅረብ የሚፈጸም ተግባር ነዉ በሚል ሉገለጽ የሚችል ነዉ።
ይህንን ትርጓሜ ይዘን ከዚህ ጉዲይ ጋር በተያያዘ በፍትሐ ብሓር ሕጋችን የተደነገገዉን የተመለከትን እንደሆነ በመርህ ደረጃ አንድ ሰዉ የላላ ሰዉ ባለዕዲ በመሆኑ ብቻ ከንብረቱ ጋር በተያያዘ ዉል ከመዋዋል አይታገድም።እንዱህ አይነት ክልከላ ማስቀመጥ የመዋዋል ነጻነቱን እና የንብረት ባለሀብትነት መብቱን ዋጋ ቢስ ማድረግ ይሆናል።አንድ ሰዉ ሀብቱ ላይ በዚህ አግባብ ዉል የፈጸመ እንደሆነ ዉለ ከእርሱ ላይ ገንዘብ ያላቸዉን ሰዎች መመለሻ እንደሚሆን እና ዉለ ከተረጋገጠበት ቀን (the date of authentication) ጀምሮ ወይም እንዱህ አይነት ዉል ለሕዝብ ይፊ እንዱደረግ ሕግ የሚያዝ ከሆነ ይሄዉ ሥርዓት ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ ከዚህ ሰዉ ንብረት ላይ ልዩ መብት በሚያገኙት ሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ እንደሚሆን በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1989 ስር የተደነገገዉ ያሳያል።በዚህ መልኩ በተለይም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1989/1 ስር የተደነገገዉን ፕሮፋሰር ጥላሁን ተሾመ የኢትዮጵያ የዉል ሕግ መሰረተ ሀሳቦች በሚል ባሳተሙት መጽሐፊቸዉ ገጽ 333 ላይ ‛አንድ ሰዉ የላላ ሰዉ ዕዲ እያለበት ንብረቱን ቢሸጠዉ፣ቢለዉጠዉ ወይም በስጦታ ቢያስተላልፈዉ የእርሱ ባለገንዘብ የሆነዉ ሰዉ ንብረቱ የተላለፈለትን ሰዉ 'የገዛኸዉ ንብረት፣ የለወጥከዉ ዕቃ፣ወይም የተቀበልከዉ ስጦታ የእኔ ባለእዲ የሆነ ሰዉ ሀብት ነዉ፤እርሱ የእኔን ዕዲ ሳይከፍል ሀብቱን ለአንተ ሉያስተላልፍ አይችልም' ብል አዱሱን ተረካቢ ሉከለክለዉ መብት የለዉም።“ በማለት አብራርተዉ ጽፈዋል። ይህም የሚያስገነዝበዉ የባለዕዲዉ የመዋዋል ነጻነት እና ባለዕዲ ቢሆንም በንብረቱ ላይ ያለዉን የባለቤትነት መብቱን የመጠቀም መብት ሉረጋገጥለት እንደሚገባ ነዉ።
ከላይ በተመለከተዉ መልኩ በመርህ ደረጃ ለላላ ሰዉ ባለዕዲ የሆነዉ ሰዉ ስላለዉ መብት የተደነገገዉ ሁለት ልዩ ሁኔታዎች አለት።አንደኛዉ ልዩ ሁኔታ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1990 ስር የተደነገገዉ ልዩ መብት ስላላቸዉ ገንዘብ ጠያቂዎች(Preferred/Secured Creditors) የተደነገገዉ ሲሆን ይሓዉም በሕግ አግባብ በንብረቱ ላይ የመያዣ መብት ያቋቋሙ ሰዎች ወይም በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 168 ላይ ሥለሰራተኞች የቅድሚያ መብት የተደነገገዉን ዓይነት መብቶች በተመለከተ ሲሆን ሁለተኛዉ ልዩ ሁኔታ ደግሞ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1991/1 ስር እንደተደነገገዉ ባለዕዲዉ ንብረቱን በተመለከተ ያደረገዉ ዉል የይምሰል ዉል ሲሆን ነዉ።በእነዚህ ልዩ ሁኔታዎች መሰረት አንድ ለላላ ሰዉ ባለዕዲ የሆነ ሰዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1989 ስር በተደነገገዉ መሰረት ንብረቱን በተመለከተ ዉል የመዋዋል ነጻነት ስላለዉ ብቻ ወይም ንብረቱ ላይ የባለሀብትነት መብት ስላለዉ ብቻ ከላላ ሰዉ ጋር በሚያደርገዉ እዉነተኛ ዉል ወይም በይምሰል ዉል ልዩ መብት ያላቸዉን ገንዘብ ጠያቂዎቹን መብት እና ከእሱ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎችን መብት መጉዲት አይችልም።
የይምሰል ዉል (simulated contract)ም ሆነ ላላ ሽሽግ ዉል (counter-deed or back-letter) በተመሳሳይ ተዋዋይ ወገኖች መካከል የሚደረግ ነዉ። ለይምሰል የተደረገ ዉል ካለ ላላ ይህንን የሚቃረን ሁለተኛ ዉል እንዲለ ያስገነዝባል። ሁለቱም ዉልች እርስ በእርስ የሚጣረሱ ዉልች ስለሚሆኑ ለሁለቱም ዉልች ዉጤት መስጠት አዲጋች ይሆናል።በዚህን ጊዜ ከሁለቱ ዉልች አንደን ማስፈጸም የግድ ይላል።የይምሰል ዉለን የሚዋዋለት ዉለ ዉጤት እንዱኖረዉ አስበዉ እንዲልሆነ (lack of the intention obligandi) ይቆጠራል። በዚህ መሰረት የይምሰል ዉል የተዋዋለበት ዓላማ ይህ ለይምሰል የተደረገ ዉል ዉጤት እንዱኖረዉ በማሰብ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1991/2 ስር እንደተደነገገዉ ለመደበቅ የፈለጉት ዉል ወይም ድብቅ የሆነዉ ዉል (counter-deed or back-letter) በተዋዋዮች መካከል ብቻ ተፈጻሚ እንዱሆን ይደረጋል ማለት ነዉ። በመሆኑም አንድ ከንብረቱ ጋር በተያያዘ ወይም በልላ ምክንያት ለላላ ሰዉ ባለዕዲ የሆነ ሰዉ ንብረቱን በተመለከተ የይምሰል ዉል ተዋዉል የተገኘ እንደሆነ ከዚህ ሰዉ ገንዘብ የሚጠይቀዉ ሰዉ ለይምሰል ከተደረገዉ ዉል ዉጭ ላላ ሽሽግ ዉል እንዲለ በማስረዲት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1991 እና በቁጥር 1994 ስር የተደነገገዉን መሰረት በማድረግ ባለዕዲዉ ያደረገዉ ዉል የማስመሰል እንጂ ተፈጻሚ እንዱሆን የተደረገ እዉነተኛ ዉል አለመሆኑን በመግለጽ በሽሽግ ዉለ መሰረት መብቱ በፍርድ እንዱከበርለት ለመከራከር ወይም ዲኝነት ለመጠየቅ ይችላል።
ይህንንም ከያዝነዉ ጉዲይ ጋር አያይዘን ያየን እንደሆነ ሁለተኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በገባዉ ዉል መሰረት ያለበትን ግዳታ ላለመወጣት(ግንባታዉን አጠናቆ ለ1ኛ ተጠሪ ላለማስረከብ) ብል አመልካች ቤቱን እየጠበቁ ያለዋጋ እንዱገለገለበት የሚፈቅድ እዉነተኛ ዉል ወይም ሽሽግ ዉል (counter-deed or back-letter) ካደረገ በኋላ 1ኛ ተጠሪና ላላዉ ሰዉ ቤቱን ለአመልካች እንደሸጠ እንዱቆጥሩለት በማሰብ ብቻ ከአመልካች ጋር በዉል አዋዋይ ፉት በተደረገ ዉል ቤቱን እንደሸጠ በማስመሰል ቢዋዋል የሽያጭ ዉለ ለይምሰል እንደተደረገ ዉል ይቆጠራል።በዚህን ጊዜ 1ኛ ተጠሪ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1991/2 እና 1994 መሰረት የሽያጭ ዉለ የይምሰል ዉል በመሆኑ እዉነተኛዉና ሉፈጸም የሚገባዉ አመልካች ቤቱን ያለ ዋጋ በጠባቂነት እንዱገለገለበት የተደረገዉ ዉል ነዉ በማለት ይህ አዉነተኛ ዉል ቀሪ ሆኖ ቤቱን 2ኛ ተጠሪ አንዱያስረክባቸዉ የመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል ።
ሆኖም ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በያዝነዉ ጉዲይ በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል በዉል አዋዋይ ፉት በቀን 27/01/2010 ዓ/ም ከተደረገዉ ከአከራካሪዉ የቤት ሽያጭ ዉል ዉጭ ይሄኛዉን ዉል የይምሰል ዉል እንዱሆን የሚያደርግ ሽሽግ ዉል (counter-deed or back-letter) ስለመኖሩ በተጨባጭ በማስረጃ ተረጋግጦ በ1ኛ ተጠሪ የቀረበ ግልጽ ክርክር የለም።በመሆኑም በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ ዉል የይምሰል(የማስመሰል/simulated) ዉል ነዉ ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም። በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ የቤት ሽያጭ ዉል የይምሰል ዉል አይደለም የሚል ድምዲሜ ላይ ስለደረስን ከዚህ ጋር በተያያዘ ዉለ ለይምሰል የተደረገ መሆኑ በምን አግባብ ሉረጋገጥ ይችላል? ለይምሰል የተደረገ ዉል በሦስተኛ ወገን መብት ላይ የሚያስከትለዉ ሕጋዊ ዉጤት ምንድን ነዉ?በሚል የያዝናቸዉን ጭብጦች መመርመር አስፈላጊ ባለመሆኑ አልፈናቸዋል።
በልላ በኩል በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የቤት ሽያጭ ዉል የተደረገዉ በ1ኛ ተጠሪና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ ዉል እንዲይፈጸም ለማድረግ ወይም 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ያለበትን ግዳታ ላለመወጣት ብል በተንኮል የተፈጸመ ነዉ ወይስ አይደለም? የተንኮል ተግባር መኖሩስ በምን አግባብ ሉረጋገጥ ይገባል? በሚል የያዝናቸዉን ጭብጦች ቀጥለን መርምረናል። እንደመረመርነዉም ተንኮለኛ ባለዕዲ ለቅን ልቦና ተቃራኒ በሆነ ተግባር ሀብቱ ለባለገንዘቡ የመብት ጥያቄ ማስፈጸሚያ እንዲይዉል በተለያዩ መንገድች በሦስተኛ ሰዎች ስም የማዛወር ወይም የመሰወር ተግባር ሉፈጽም ይችላል።
ፕሮፋሰር ጥላሁን ተሾመ ከላይ በተጠቀሰዉ መጽሐፊቸዉ ገጽ 341-342 እዉቁን ፈረንሳዊ የሕግ ሉቅ ፕላንዮልን ጠቅሰዉ እንዲሰፈሩት ‛…ንብረቱ ለባለገንዘቦቹ የመብት ጥያቄ መመለሻ እንደሚዉል የተረዲዉ ባለዕዲ ሀብቱን ከእነዚህ ባለገንዘቦች ለመሸሸግ… ንብረቱን በግዥ ወይም በስጦታ አግኝቻለሁ ከሚል ሦስተኛ ወገን ጋር በመመሳጠር ባለገንዘቡን የሚጎዲ ሸር ሉያዉጠነጥን ይችላል።…ለራሱ ምንም ባይጠቀም እንኳን ክፊት በማሰብ ብቻ ሀብቱን ለጓደኞቹና ለዘመድቹ በማከፊፈል ባለገንዘቡን የሚጎዲ ተግባር ሉፈጽም ይችላል።…እንዱህ በዋዛ ሉታወቁና ሉረጋገጡ በማይችለ እጅግ በርካታ መንገድች የባለገንዘቡን መብት ለመጉዲት የሚችለ አጋጣሚዎችን ባለዕዲዉ ሉጠቀም ይችላል።“ሕግ ደግሞ ምን ጊዜም ለቅን ልቦና አሰራር የማያወላዲ አቋም ስላለዉ የባለዕዲዉን የተንኮል ሥራ የሚገታበትን መንገድ ለባለገንዘቡ ይዘረጋል በሚል ስለተንኮለኛ ባለዕዲ ባህርይ ገልጸዋል። ይህንን አባባላቸዉን በሚደግፍ አኳኋን በፍትሐ ብሓር ሕጋችን ከቁጥር 1995 እስከ 2000 ድረስ ባለ ድንጋጌዎች ባለገንዘቦች መብታቸዉን የሚያስከብሩበት አግባብ ተደንግጓል። የእነዚህ ድንጋጌዎች ዓላማ ማንኛዉም ሰዉ በልላዉ ኪሳራ ለመበልጸግ ብል የሰራዉ ሥራ ባለገንዘቡን በሚጎዲ አኳኋን በሕግ ፉት ዉጤት ሉሰጠዉ አይገባም የሚለዉን ርትዓዊ አተያይን መሰረት ያደረገ ነዉ።በዚህ መሰረት በተለይ ከባለዕዲዉ መክሰር ዉጭ ያለ የባለዕዲዉን ድርጊቶች በተመለከተ ባለገንዘቡ እንዱያረጋግጥ የሚጠበቅበት ባለዕዲዉ ንብረቱን ወይም ያለዉን መብት ሆነ ብል እየለቀቀ ወይም እያስተላለፈ መሆኑንና ይህንንም እያደረገ ያለዉ ባለገንዘቡ የመብት ጥያቄዉን የሚያስፈጽምበትን ንብረት እንዱያጣ ለማድረግ ተንኮል አስቦ እንደሆነ፤ባለዕዲዉ ሆነ ብል እየለቀቀ ወይም እያስተላለፈ ያለዉ ይህ መብት(ንብረት) ለባለገንዘቡ መብት አፈጻጸም መድን በመሆኑ የዚህ ሀብት መጥፊት ወይም ላላ ሰዉ መተላለፍ የባለገንዘቡ ጥያቄ መፍትሓ እንዲያገኝና ጉዲት እንዱደርስበት በማሰብ መሆኑን እና ይህ መብት(ንብረት) ባለገንዘቡ በራሱ ስም በሚጠይቀዉ ጥያቄ ልክ መሆኑን ማስረዲት እንደሚጠበቅባቸዉ በዘርፈ የተጻፈ ድርሳናትና በፍ/ብ/ሕግ ከቁጥር 1995 - 1999 የተደነገጉ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት ያስገነዝባለ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የባለዕዲዉ የማጭበርበር ተግባር ከባለዕዲዉ መክሰር ጋር ሉያያዝና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2000 እና በንግድ ሕጉ ስለመክሰር በተደነገገዉ አግባብ ባለዕዲዉ ከስሯል ተብል ተወስኖ በንግድ ሕጉና በልላ ሕግ በተደነገገዉ አግባብ የባለገንዘቦቹ መብት ጥበቃ እንዱያገኝ የሚደረገዉ መቼ ነዉ የሚለዉን ማየት ጠቃሚ ይሆናል። በእኛ እምነት የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2000 ተፈጻሚ የሚሆነዉ ባለእዲዉ ለባለገንዘቦች የገባዉን ግዳታ ላለመወጣት ካለዉ ዓላማ በመነሳት ብቻ ሳይከስር በተንኮል በእጁ ያለዉ ሀብት ለባለገንዘቡ የመብት ጥያቄ ማስፈጸሚያ እንዲይዉል በተለያዩ መንገድች ንብረቱን በግዥ ወይም በስጦታ አገኘሁኝ ከሚል ሦስተኛ ወገን ጋር በመመሳጠር ባለገንዘቡን የሚጎዲ የአጭበርባሪነት ተግባር በመፈጸም ንብረቱን ባስተላለፈበት በማንኛዉም ጊዜ ሁለ ሳይሆን ባለዕዲዉ ተቃዉሞ የቀረበባቸዉን ሥራዎች የሰራዉ ራሱን ለማክሰር የፈጸመዉ ተግባር ሲሆንና መክሰሩም ሲረጋገጥ ብቻ ላሆን ይገባል።
በያዝነዉ ጉዲይ ከላይ በዝርዝር እንደተመለከተዉ አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 መሰረት በ1ኛ እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የነበረዉ ክርክር ተሰምቶ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ያደረገዉን ዉል በተናጠል መሰረዙ ተገቢ አይደለም ተብል 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ በክሱ የተጠቀሰዉን ቤት ገንብቶ ለማስረከብ በገባዉ የዉል ግዳታ መሰረት የቤቱን ግንባታ አጠናቆ ለ1ኛ ተጠሪ እንዱያስረክብ ተወስኗል።በዚህ መልኩ ዉሳኔ ከመሰጠቱ በፉት እና 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የፈጸመዉን ዉል በተናጠል ሰርዣለሁ ከማለቱ በፉት በተጠሪዎች መካከል ከቤት ርክክብና ከቀሪ ክፍያ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ለረጅም ጊዜ የቆየ አለመግባባት እንደነበር የግራ ቀኙ ክርክር ያሳያል።
ከንግድ ሕጋችን ከተለያዩ ድንጋጌዎች እና በአገራችን በልማድ ከዲበረዉ አሰራር መረዲት እንደሚቻለዉ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ምንም እንኳን የራሱ የሆነ ሕጋዊ ሰዉነት ያለዉ የንግድ ማኅበር ቢሆንም ለሕዝብ ግልጽ በሆነ አኳኋን አክሲዮኑ ለማንኛዉም ሰዉ ለሽያጭ ቀርቦ በባለአክሲዮኖች የሚቋቋም ሳይሆን ዘመዲሞች የሆኑ ወይም በጓደኝነት ወይም በሙያ እርስ በእርሳቸዉ በደንብ የሚተዋወቁ ሰዎች ካፒታል በማዋጣት የሚቋቋሙት ነዉ።እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሆኖ የተቋቋመ መሆኑ አከራካሪ ካለመሆኑም በተጨማሪ 2ኛ ተጠሪ የተቋቋመዉ ካለዉ ካፒታል ግማሹን የአመልካች ባለቤት ባለድርሻ በመሆንና ቀሪዉን ግማሽ ድርሻ ደግሞ የአመልካች ባል ወንድም ድርሻ በመሆን ያቋቋሙት እንደሆነ በይግባኝ ሰሚዉ ችልት በማስረጃ የተረጋገጠና በአመልካችም ያልተካደ ፍሬ ነገር ነዉ።2ኛ ተጠሪ በዚህ መልኩ ዘመዲሞች በሆኑ ሁለት ሰዎች የተቋቋመ በመሆኑ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት ርክክብና ከቀሪ ክፍያ አከፊፈል ጋር በተያያዘ በተጠሪዎች መካከል የነበረዉን አለመግባባት ክርክሩ ወደ ፍርድ ቤት ከመምጣቱ በፉት 2ኛ ተጠሪን ያቋቋሙ ማኅበረተኞችም ሆኑ አመልካችም ማኅበረተኛ ከሆኑት ባለቤታቸዉ በኩል አያዉቁም ተብል አይገመትም።
በተጨማሪም አመልካች አከራካሪዉን ቤት በቀን 27/01/2010 ዓ/ም በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ አጅንሲ በተደረገ ዉል ከ2ኛ ተጠሪ ላይ በብር 4,500,000.00 ገዝቻለሁ ያለትን በሚሉዮኖች ብር የተደረገ ግብይት ባለቤታቸዉ (የ2ኛ ተጠሪ ግማሽ ባለድርሻ) አመልካች ቤቱን ከማንና በምን ያህል ገንዘብ ለመግዛት ዉል እንደተዋዋለና በቤቱ ላይ አስቀድሞ መብት ያቋቋመ ሰዉ መኖር አለመኖሩን በተመለከተ ከአመልካች ጋር መረጃ የመለዋወጥ እድል እንዲላቸዉ ይግባኝ ሰሚዉ ችልት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎችን መሰረት አድርጎ ያረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ነዉ። እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት በየጊዜዉ ተከፍል በሚጠናቀቅ የአከፊፈል ሥርዓት ገንብቶ ለ1ኛ ተጠሪ ለማስረከብ በ2003ዓ/ም ስምምነት ያደረዉ በብር 4,478,000.00 ሆኖ ግንባታዉ በመጠናቀቅ ደረጃ ያለዉን ይህንኑ ቤት ከ7 ዓመት በኋላ ለአመልካች በአንጻራዊነት ዝቅተኛ እንደሆነ በሚገመት ዋጋ በብር 4,500,000.00 በሽያጭ ማስተላለፈና (በዉለ ላይ ቤቱ የተሸጠበት ገንዘብ በዉለ ደረሰኝነት እንደተከፈለ የሚገልጽ ቢሆንም የይግባኝ ሰሚዉ ችልት መዝገብ እንደሚያሳየዉ የሽያጩ ዋጋ በዉለ ደረሰኝነት የተከፈለ ሳይሆን በተ.እ.ታ. ደረሰኝ ቁጥር 001 በደቤ ሽያጭ የተፈጸመ ግብይት እንደሆነ) የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።
ሲጠቃለል ከዚህ በላይ በተመለከተዉ አግባብ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች መገንዘብ የተቻለዉ 2ኛ ተጠሪ የማኅበሩ አንደኛዉ ባለድርሻ ሚስት ለሆኑት አመልካች በአንጻራዊነት ዝቅተኛ እንደሆነ ግንዛቤ በሚወሰድ ዋጋ በሽያጭ ያስተላለፈዉ ቤት ለ1ኛ ተጠሪ በገባዉ የዉል ግዳታ መሰረት 1ኛ ተጠሪ ያስገነበቱ ቤት መሆኑ ከግራ ቀኙ ክርክር፣ ከቀረቡት ማስረጃዎችና ከአጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ የተረጋገጠ ነዉ።በዚህ መልኩ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት ለአመልካች በሽያጭ ያስተላለፈዉ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ባደረገዉ ዉል ላይ የተመለከተዉን ቤት በመሆኑ ይህንን ያደረገዉ 1ኛ ተጠሪ በክርክሩ የሚረቱና 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ያስረክብ የሚባል ከሆነ 2ኛ ተጠሪ የማስረክበዉ ቤት በይዞታዬ ስር አይገኝም ለማለት እና 1ኛ ተጠሪ የሚረከቡትን ቤት እንዱያጡና በዚህም ምክንያት በመብትና ጥቅማቸዉ ላይ ጉዲት እንዱደርስባቸዉ ለማድረግ በማሰብ የፈጸመዉ የተንኮል ተግባር እንደሆነ ያሳያል።ይግባኝ ሰሚዉ ችልት በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ ዉል በእርግጥም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገ ሳይሆን ቤቱን 1ኛ ተጠሪ እንዲይረከቡ በማድረግ የ1ኛ ተጠሪን መብትና ጥቅም ለመጉዲት ታስቦ የተደረገ ዉል ነዉ በሚል ያረጋገጠዉ የፍሬ ነገር ድምዲሜም ይህንኑ የሚያስገነዘብ ነዉ።የተንኮል ተግባር ድርጊቱን ተመካክረዉ ከሚፈጽሙ ሰዎች ዉጭ ለማንኛዉም ሰዉ በግልጽ በሚታይና በሚሰማ አኳኋን የሚሰራ ባለመሆኑ የተንኮል ተግባር መኖሩን ለማረጋገጥ የሚቀርብ ማስረጃም ይህንኑ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችና ከነባራዊ ሁኔታዎች በመነሳት ግንዛቤ( factual inferences) ሉወሰድበት የሚችል ነዉ።ይግባኝ ሰሚዉ ችልትም በተጠቀሰዉ አግባብ አስቀድሞ ሰበር ሰሚ ችልት ይዞ የመለሰለትን ጭብጦች በግራ ቀኙ የታመኑትንና በማስረጃ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች መነሻ በማድረግ ድምዲሜ ላይ ደርሷል ከሚባል በስተቀር አከራካሪ ጭብጦችን በሙለ በግምት ላይ ተመስርቶ ወስኗል የሚያስብል ባለመሆኑ በዚህ ረገድ በአመልካች የቀረበዉን ክርክር አልተቀበልንም።
እንዱሁም በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ ዉል እንዱፈርስ የተሰጠ ዉሳኔ ባይኖርም አመልካች ለ2ኛ ተጠሪ የከፈለት ገንዘብ ካለ እና 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በገባዉ የዉል ግዳታ ላይ ከተመለከተዉ የግንባታ ሥራ ዉጭ የፈጸሙት ግንባታ ካለ ከ2ኛ ተጠሪ ላይ ለተጨማሪ ግንባታ ያወጡት ወጪ እንዱተካላቸዉ መጠየቅ እንዱችለ በይግባኝ ሰሚዉ ችልት ተወስኖላቸዋል።እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ መስራት ይገባዉ ከነበረዉ ግንባታ በላይ በቤቱ ላይ አመልካች በራሳቸዉ ገንዘብ የሰሩት ተጨማሪ የማሻሻያ/የግንባታ ሥራ ካለ 1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ አመልካች ጋር በፈጸሙት ዉል ላይ ከተመለከተዉ በላይ የሆነ ወይም የተሻለ የግንባታ ማሻሻያ የተደረገለትን ቤት ተረክበዉ አለአግባብ እንዲይበለጽጉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2162 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት አላግባብ ስለመበልጸግ በተመለከተው የሕግ ክፍል አግባብ አመልካች ክስ በማቅረብ መጠየቅ ይችላለ። ከዚህ ዉጭ የሕጉ ድንጋጌዎች የ2ኛ ተጠሪን የተንኮል ተግባር የመቅጣትና የ1ኛ ተጠሪን(የገንዘብ ጠያቂን) መብት የማስከበር ዓላማ ያለዉ በመሆኑ አመልካች ተጨማሪ ግንባታ/ማሻሻያ በቤቱ ላይ አድርጌያለሁ በማለታቸዉ ብቻ በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ የቤት ሽያጭ ዉል ጸንቶ እንዱቀጥል የሚደረግበት አግባብ የለም።ይህ ይሆን የነበረዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1997 መሰረት ቤቱን የገዙት በቅን ልቦና መሆኑ ሲረጋገጥ ነዉ።ነገር ግን በዚህ ድንጋጌ ተቃራኒ ንባብ መሰረት ከላይ እንደተመለከተዉ አመልካች ቤቱን የገዙት ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ባላቸዉ ግንኙነት ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር በተንኮል 1ኛ ተጠሪ እንዱጎደ ለማድረግ መሆኑ ስለተረጋገጠ ከዚህ አንጻር ያነሱት ክርክር የሕግ ድጋፍ ያለዉ አይደለም።በመሆኑም ይግባኝ ሰሚዉ ችልት አስቀድሞ በመዝገቡ ላይ የወሰነዉን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 360/2 መሰረት በማጽናት የሰጠዉ ዉሳኔ ከፍ ሲል በዝርዝር በተመለከተዉ አግባብ በተወሰነ ደረጃ ምክንያቱ ከመለወጡ በስተቀር ከዉጤት አንጻር ሲታይ ጉድለት ያለበት ባለመሆኑ ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 26/08/2013ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንቷል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስቀድሞ በሰ/መ/ ላይ በቀን 24/03/2011ዓ/ም በተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት በቀሪዉ ጉዲይ ላይ ተገቢዉን እንዱወስን የዉሳኔዉ ግልባጭ ይተላለፍለት። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል።ይጻፍ። መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.