የቅድሚያ ክፍያ ማገቻ ሰነድ (Advance Payment Guarantee/Bond) በሰነድ ሰጪውና በተጠቃሚው (ቅድሚያ ክፍያ በከፈለው አሰሪ) መካከል የዋስትና ውል የሚያቋቁም ሰነድ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1902 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎችና በአንቀጽ 3271 መሰረት የሚገዛ ስለመሆኑ ዋናውን ውል ለማከራከር ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት ተቀፅላውን ውል የሚመለከት ክርክር ተቀብል የመዲኘት ስልጣን ያለው ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ እና አዱስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት
No summary available.
ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ተጠሪ፡- አዱስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ፅ/ቤት መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የቅድመ ክፍያ ዋስትና አፈጻጸም መነሻ ያደረገ እና ከዚህ ጋር የተያያዘ ክርክር የመዲኘት ስልጣን የሚመለከት ነዉ። የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተወስኖ በየደረጃዉ በይግባኝና በሰበር ታይቶ በትእዛዝ በጸናዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ነዉ።ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአሁን አመልካች ላይ እና በስር 1ኛ ተከሳሽ ከበደ ካሳዬ የሕንጻ ሥራ ተቋራጭ ላይ እና በስር 3ኛ ተከሳሽ ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ላይ በመሰረተዉ ክስ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር በቀን 23/11/2007 ዓ/ም ባደረግነው በቦላ አራብሳ ሳይት የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ውል በጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ(ተ.እ.ታ) ጨምሮ በብር 26,801,738.00 ለመስራት ውል ተዋዉል ለግንባታው የዋናውን ውል 20% ቅድመ ክፍያ እንዱከፈለው ከአሁን አመልካች ለብር 5,360,347.60 ተ.እ.ታ ጨምሮ የቅድመ ክፍያ ጋራንቲ አቅርቧል።እንዱሁም ከስር 3ኛ ተከሳሽ ደግሞ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ቦንድ አቅርቧል።ተጠሪ የቅደመ ክፍያ ዋስትና በመቀበል ብር 5,360,347.60 ለስር 1ኛ ተከሳሽ ክፍያ ተፈፅሟል። ነገር ግን የስር 1ኛ ተከሳሽ በገባው ውል መሰረት ግንባታውን ባለመፈፀሙና በማጓተቱ በተለያዩ ጊዜያት ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ግንባታውን ሉያጠናቅቅ ባለመቻለ በቀን 04/13/2008 ዓ/ም ውለን አቋርጠናል። በመሆኑም አመልካች በሰጠው የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና መሰረት ግዳታውን ያልተወጣ በመሆኑ የስር 1ኛ ተከሳሽ ወስድ ሥራ ላይ ያላዋለውን ብር 422,500.66 (አራት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር ከስልሳ ስድስት ሳንቲም) ለባንኩ ካሳወቅንበት ከቀን 27/01/2009 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለን ይወሰንልኝ የሚል ዲኝነት በመጠየቅ ክስ መስርቷል።
አመልካች ለክሱ በሰጠዉ መልስ የግንባታ ዉል የአስተዲደር ዉል ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን የለዉም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም በአማራጭ በሰጠዉ መልስ አመልካች ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር የገባው የዋስትና ውል ግዳታ ውለ ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ተጠሪ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር ባለው ውል 1ኛ ተከሳሽ በውለ ውስጥ የተጣለበትን ግዳታ መወጣት እንዲልቻለ ገልፆ ብቻ የክፍያ ጥያቄ ሲያቀርብ ለመክፈል ነው። ተጠሪ በቀን 27/01/2009ዓ/ም በጻፈዉ ደብዲቤ ዋስትናዉ ታግድ እንዱቆይ የጠየቀዉ ከዋስትና ዉለ መንፈስ ዉጭ ነዉ። ክፍያዉን ማገድ ከአመልካች ሥልጣን ዉጭ እና ከዋስትና ውለ መንፈስ ውጪ በመሆኑ ትርጉም የማይሰጥና የክፍያ ጥያቄም እንዲልቀረበ የሚያሳይ ስለሆነ አመልካች ክፍያዉን ለመፈጸም አይገደድም።ተጠሪ በቀን 01/07/2010ዓ/ም በተጻፈ ደብዲቤ የዋስትና ገንዘቡን አመልካች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ እንዱደረግልን በማለት የጻፈዉ ደብዲቤ ለአመልካች አልደረሰዉም።ስለመድረሱም ማስረጃ አልቀረበም።
በዋስትና ሰነደ መሰረት የክፍያ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለዉ ከቀን 04/02/2008ዓ/ም እስከ ቀን 28/01/2009ዓ/ም ድረስ በመሆኑና ተጠሪ በተጠቀሰዉ ጊዜ ዉስጥ የክፍያ ጥያቄ ያልቀረበ ስለሆነ የመክፈል ግዳታ የለብንም በማለት ክሱ ዉድቅ እንዱደረግለት በመጠየቅ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ በሰጠዉ ብይን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ ካለፈ በኋላ ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ግራ ቀኙን አከራክሮና ማስረጃዎችን ከተገቢው ሕግ ጋር በማገናዘብ በቀን 20/01/2013 ዓ/ም ውሳኔ የሰጠ ሲሆን አመልካችን በተመለከተ በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች የቅድመ ክፍያ ዋስትና መስጠቱ የተረጋገጠ ነዉ። እንዱሁም የስር 1ኛ ተከሳሽ ከተቀበለዉ ቅድመ ክፍያ ላይ ብር 422,500.06 ሥራ ላይ አለማዋለም በማስረጃ ተረጋግጧል።በቁጥር ቢአይቢ/ኬ5ቢ/052/2015 እ.ኤ.አ በቀን 15/10/2015 ቅድመ ክፍያ ዋስትና መሰረት ተጠሪ ክፍያ ለመጠየቅ 1ኛ ተከሳሽ የዉል ግዳታዉን ለመወጣት ሳይችል ሲቀር ዉለ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ዉስጥ በደብዲቤ ገልጾ ሲያቀርብ የካሳ ክፍያ ይከፍላል የሚል ነዉ።ተጠሪ በቀን 27/01/2009 ዓ/ም በተፃፈ ደብዲቤ 1ኛ ተከሳሽ በዉለ መሰረት እየሰራ ባለመሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ዉለ ስለመቋረጡ ጠቅሶ ብሩ ይታገድልኝ የሚል በመሆኑ የክፍያ ጥያቄ አልደረሰንም የሚያስብል አይደለም። በተጠሪ በቀን 27/01/2009 ዓ/ም የተጻፈዉ ይህ ደብዲቤ በቀን 06/07/2010 ዓ/ም ለአመልካች እንደደረሰዉ ተረጋግጧል።የዚህ ደብዲቤ ይዘት ዉለ ጸንቶ በነበረበት ጊዜ የክፍያ ጥያቄ መቅረቡን አያሳይም በሚል አመልካች ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት ያለዉ አይደለም። በመሆኑም አመልካች ለተጠሪ በሰጠዉ የቅድመ ክፍያ ዋስትና መሰረት ብር 422,500.06 መመለስ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ከሚታሰብ 9% ሕጋዊ ወለድ ጋር ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት ለተጠሪ ይክፈል ሲል ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 18/09/2013 ዓ/ም በተሰጠው ውሳኔ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማጽናት ወስኗል። በመቀጠል አመልካች አቤቱታዉን ለከተማዉ ሰበር ሰሚ ችልት ቢቀርቡም ችልቱ በመ/ ላይ በቀን 12/11/2013 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ አቤቱታውን ሰርዞበታል።
አመልካች በቀን 19/11/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ፡-ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ዉል የግንባታ ዉል እንጂ የአስተዲደር ዉል አለመሆኑንና አመልካች በፋዳራል መንግስት የተመዘገበ የንግድ ድርጅት መሆኑን ምክንያት በማድረግ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን የለዉም ሲል አመልካች ያቀረበዉን መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ብይን ጉዲዩን በስረ ነገሩ ተመልክቶ በአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 41 እና በፋደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 5(1/ተ) ስር የተደነገገዉንና በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነዉ። በቅድመ ክፍያ ዋስትና ዉለ መሰረት አመልካች የክፍያ ጥያቄ ማቅረብ ያለበት ዉለ ጸንቶ ባለበት ጊዜ ሲሆን ተጠሪ በቀን 27/01/2009ዓ/ም የጻፈዉ የዋስትና ገንዘብ ይታገድልኝ የሚል እንጂ የክፍያ ጥያቄ አይደለም።የክፍያ ጥያቄ አይደለም እንጂ ነዉ ቢባል እንኳን ተጠሪ ክፍያዉ የሚፈጸምበትን አሰራር አለመግለጹም የሚያሳየዉ ጥያቄዉ የክፍያ ጥያቄ አለመሆኑን ነዉ።በአጠቃላይ ተጠሪ ለአመልካች የጻፈዉ ደብዲቤ የዋስትና ገንዘቡ ታግድ እንዱቆይለት ብቻ በመጠየቅ በሆነበት እንደ ክፍያ ጥያቄ ሉቆጠር የሚችል ነዉ ማለቱ ስህተት ነዉ።የቅድመ ክፍያ ዋስትና ጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ ተጠሪ የክፍያ ጥያቄ አቅቦ እያለ አመልካች ክፍያ እንዱፈጽም የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት የግንባታና ዋስትና ውልችን መነሻ ያደረገና ያልተከፈለ ገንዘብ ለማስመለስ የቀረበውን ክስ ተቀብል ለማየት የስረ ነገር ስልጣን ያለዉ መሆን ስላለመሆኑ ከአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 41(1/መ) እና በሰበር መ/ እና በላልች ተመሳሳይ መዝገቦች ከተሰጠዉ ትርጉም አንፃር እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 23/05/2014 ዓ/ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል።ይዘቱም በአጭሩ፡- ተጠሪ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረገዉ የግንባታ ዉል መሰረት የግንባታ ሥራዉን እና ሂደቱን ለማሳለጥ ለግንባታ የሚያስፈልጉ ማናቸዉንም ግብአቶች የማቅረብ ኃላፉነት እንዱሁም የግንባታ ሥራ አፈጻጸሙን ያለማቋረጥ ተከታትል የማሰራት እና ጉድለት ሲኖርም እርምጃ የመዉሰድ የአሰሪዉ መስሪያ ቤት እንደሆነ በዉለ የተመለከተ በመሆኑ ለክሱ መነሻ የሆነዉ ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3132/ለ እና በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት የአስተዲደር ዉል በመሆኑ ይህንን ዉል መነሻ ያደረገ ክስ የመዲኘት ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1/መ) መሰረት የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሥልጣን ሥላለዉ በዚህ ረገድ የተፈጸመ ስህተት የለም። የዋስትና ውል እራሱን ችል የሚቆም የውል ግንኙነት ሳይሆን ላላ ውልን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም የውል አይነት ሲሆን በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1923/1 መሰረት ዋናው የውል ግዳታ ከላለ የዋስትናው ውል ግዳታም እንደማይኖር ይደነግጋል። በግራ ቀኛችን ያለው ክርክር ዋናው ውል ጉድለት የላለበት ከመሆኑም በላይ አመልካች ውለ የአስተዲደር መስሪያ ቤት ውል መሆኑን እያወቀ ዋስትና የሰጠና ዋስትና ውለም የግንባታ ውለን የሚከተል በመሆኑ የስረ ነገር ስልጣንም በዚሁ መልክ የሚታይ ስለሆነ አመልካች ያነሳው መከራከሪያ ተቀባይነት የለውም።የዋስትና ሰነደ ያለቅደመ ሁኔታ የተደረገ ስለሆነ ተቋራጩ እንደዉለ አለመፈጸሙን ተከትል ተጠሪ በጠየቀዉ በማንኛዉም ሰዓት ለመክፈል ግዳታ አለበት።
ተቋራጩ እንደ ዉለ አለመፈጸሙን ተከትል ተጠሪ ጥያቄ ያቀረበ ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም።ተጠሪ ዋስትናዉ ታግድ እንዱቆይ የጠየቀዉ አመልካች ለቅድመ ክፍያ የሰጠዉን የዋሰትና ገንዘብ ብር 5,360,347.60 በሙለ ከመጠየቅ የተሰራዉን ስራ አጣርቶ እና ከክፍያዉ ላይ ቀናንሶ ፍትሐዊ በሆነ አኳኋን ተቋራጩ ሥራ ላይ ያላዋለዉን ለመጠየቅ በሚል በመሆኑ አመልካች ከሥራ ተቋራጩ ጋር በፍ/ብ/ሕጉ ስለዋስትና በተደነገገዉ መሰረት የአንድነትና የነጠላ ኃላፉነት ስላለበት የዋስትና ገንዘቡ እንዱታገድ መጠየቁ እንደ ክፍያ ጥያቄ ማስጠንቀቂያ ሉቆጠር ይገባል ተብል በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም።የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በሰጠዉ ዉሳኔ የቅድመ ክፍያ ዋስትና እንደብድር ዋስትና (financial guaranty bond) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለባለገንዘቡ መክፈል እንዲለበት አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቷል።በዚህ መሰረት የስራ ተቋራጩ ያልመለሰዉ የቅድመ ክፍያ መኖሩ ከታወቀ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1845 ስር የተደነገገዉ የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ዉስጥ መጠየቅ ይቻላል።የዋስትና ዉለ ላይ ያለ ኃይለ ቃላት መተርጎም ያለባቸዉ የግንባታ ዉለንና በግንባታ ዉል ተፈጻሚነት ያላቸዉን አጠቃላይ ድንጋጌዎች መሰረት አድርጎ ሉተረጎም ይገባል።እንዱሁም በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት በዋስትና ዉለ ላይ ያለ ቅድመ ሁኔታዎች የተጠሪን መብት በሚገድብና የአመልካችን የአንድነትና የነጠላ ኃላፉነት በሚያስቀር መልኩ ሉተረጎም ስለማይገባ የስር ፍርድ ቤቶች በሰጡት ዉሳኔ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት መልሱን በመስጠት ተከራክሯል። አመልካችም በቀን 15/06/2014 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለመልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኙ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት የያዘዉን ማስቀረቢያ ጭብጥ በተጨማሪ አመልካች በቅደመ ክፍያ ዋስትና ዉለ መሰረት ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ይክፈል ተብል በመወሰኑ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
በመጀመሪያም የስር የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመዲኘት የሚያስችል የዲኝነት ሥልጣን ያለዉ መሆን አለመሆኑን በተመለከተ መርምረናል።ተጠሪ በአመልካች እና አሁን በዚህ መዝገብ ተከራካሪ ባልሆኑት በስር 1ኛ ተከሳሽ (በሥራ ተቋራጭ) እና በስር 3ኛ ተከሳሽ(የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ስጭ) ላይ ክስ የመሰረተ ሲሆን የክሱም ይዘት የስር 1ኛ ተከሳሽ በግንባታ ዉለ ላይ በተመለከተዉ አግባብና ጊዜ ዉስጥ ባለመፈጸሙ በቀን 04/13/2008ዓ/ም ዉለ እንዱቋረጥ መደረጉን ገልጾ ቅድመ ክፍያ ተከፍልት ተመላሽ ያላደረገዉን ገንዘብ ብር 422,500.06፣ ከተጠሪ የግንባታ ግብአቶችን ተረክቦ በሥራ ላይ ያላዋለዉን ብር 11,890,574.81፣ የዉሃ ፍጆታ ክፍያ ብር 11,604.06፣ ሥራ በመጓተቱ ምክንያት በዉለ መሰረት የመዘግየት ክፍያ ብር 26,801.73፣ በመጓተቱ ምክንያት ኪሳራ ብር 750,448.66 1ኛ ተከሳሽ ከሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍል፤ የሥር 3ኛ ተከሳሽ ደግሞ በመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና መሰረት ብር 2,330,585.91 እንዱከፍል እና የአሁን አመልካች ደግሞ በቅድመ ክፍያ ዋስትና መሰረት የሥር 1ኛ ተከሳሽ ተመላሽ ያላደረገዉን ብር 422,500.66 ከቀን 27/01/2009 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍል ዲኝነት የጠየቀበት ነዉ። አመልካች ለስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በፋዳራል መንግስት አካል የተመዘገበ የንግድ ድርጅት በመሆኑና ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የግንባታ ዉል የአስተዲደር ዉል ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን የለዉም ሲል ተቃዉሞዉን ያቀረበ ቢሆንም የስር ፍርድ ቤት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የግንባታ ዉል የአስተዲደር ዉል ነዉ በሚል የዲኝነት ሥልጣን እንዲለዉ በመግለጽ የአመልካችን መከራከሪያ ዉድቅ አድርጓል።
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3131 እና 3132 ስር በተደነገገዉ መሰረት አንድ ዉል የአስተዲደር መሥሪያ ቤት ዉል ለመባል ከተዋዋዮቹ አንደኛዉ ወገን መንግስት ወይም ላላ የአስተዲደር መሥሪያ ቤት ሆኖ፡- (ሀ) ሕግ ወይም ተዋዋዮች ግልጽ በሆነ ቃል የአስተዲደር መሥሪያ ቤት ዉል ነዉ ብለዉ ለዉለ ስያሜ ሲሰጡት፤ (ለ) ዉለ ከሕዝብ አገልግልት ሥራ ጋር የተያያዘና ለሥራዉም አፈጻጸም የተዋዋዩን የአስተዲደር መሥሪያ ቤቱን ሥራ ተካፊይነት ሳይቋረጥ የሚጠይቅ ሲሆን፤ (ሐ) በዉለ ዉስጥ በአስቸኳይ ለጠቅላላ ጥቅም (urgent considerations of general interest) ብቻ የሚያስፈልጉና የግል ሰዎች በሚያደርጓቸዉ ዉልች ዉስጥ የማይገኙ አንድ ወይም ብዙ ዉለታዎች ያለበት ሲሆን ነዉ ከሚለ መመዘኛዎች አንደን አሟልቶ ሲገኝ ነዉ። በተሻሻለው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1/መ) የከተማው አስተዲደር አስፈጻሚ አካላት ወይም በከተማው አስተዲደር ባለቤትነት ሥር ያለ ተቋማት የሚገቧቸውን አስተዲደራዊ ውልች (administrative contracts) በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮችን የመዲኘት ሥልጣን በከተማው ፍርድ ቤት ሥር የሚወድቅ የዲኝነት ሥልጣን ነው።እንዱሁም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ውል የከተማው አስተዲደር አስፈጻሚ አካላት ወይም በከተማው አስተዲደር ባለቤትነት ሥር ያለ ተቋማት ያደረጉት የአስተዲደር ውል እስከሆነ ድረስ በየትኛውም ገንዘብ መጠን ላይ የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ሥልጣን ይኖረዋል።
ለክርክሩ መሰረት የሆነዉ ተጠሪ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር በቦላ አራብሳ ሳይትአራት ባለ ሰባት ፍቅ ወጪ ቆጣቢ የጋራ መኖሪያ ሕንጻዎች ለማስገንባት የተፈጸመዉ ዉል በግልጽ የአስተዲደር ውል የተባለ አለመሆኑ አከራካሪ አይደለም። የአዱስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር አስፈጻሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግልት አካላት እንደገና ለማቋቋም ባወጣዉ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 5/5 እና 24 ላይ እንደተመለከተዉ ተጠሪ ለከተማዋ ነዋሪዎች ግልጋልት የሚዉል ምቹና ተደራሽ መኖሪያ ቤቶች ለመገንባትና ለማስገንባት የከተማ አስተዲደሩ አስፈጻሚ አካል ሆኖ የተቋቋመ በመሆኑ ለግራ ቀኙ ክርክር መሰረት የሆነዉ ዉል የአስተዲደር አካል ከሆነዉ ተጠሪ ጋር የተፈጸመ መሆኑን ተረድተናል። አመልካች ሕንጻዎቹን ለመገንባት የሚያገለግለ የግንባታ እቃዎችን ለስር 1ኛ ተከሳሽ እያቀረበ 1ኛ ተከሳሽ እነዚህን የሚቀርቡለትን ግብዓቶች እየተጠቀመ ግንባታዉን የሚፈጽም መሆኑን የግራ ቀኙ ክርክር ያሳያል። ግብዓቶቹን የሚያቀርበዉ ተጠሪ ከሆነ ግብዓቶቹ ለሚገነቡት ሕንጻዎች ጥቅም ላይ መዋላቸዉን ለማረጋገጥ የተጠሪን ክትትል የሚጠይቅ ዉል መሆኑን መረዲት ይቻላል። አመልካችም በደፈናዉ የግንባታ ዉለ የአስተዲደር ዉል አይደለም ብል ከመግለጽ ባለፈ በዉለ አፈጻጸም ላይ ተጠሪ ስላለዉ ተሳትፍ ክድ አልተከራከረም። ተጠሪ የመኖሪያ ቤቶቹን የሚያስገነባዉ ለከተማዉ ነዋሪዎች መሆኑ፣የመሬትና የመሰረተ ልማት አቅርቦት መኖሩን የማረጋገጥ ኃላፉነት ያለበት መሆኑ፣ ለቤቶች ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችና የግንባታ እቃዎችን ገዝቶ የማቅረብ እና ከዱዛይን እስከ ኮንስትራክሽን ያለት የሥራ ሂደቶች ደረጃቸዉን እንዱጠብቁ በማድረግ የቤት ልማት ፕሮግራሙ በቅልጥፍና እንዱከናወን የማድረግ ተግባርና ኃላፉነት የተሰጠዉ የአስተዲደር መሥሪያ ቤት እንደሆነ በከተማ አስተዲደሩ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 24 ላይ የተመለከተዉ ያሳያል። ተጠሪ የከተማ አስተዲደሩ አስፈጻሚ አካል (የአስተዲደር መሥሪያ ቤት) ሆኖ የተቋቋመ መሆኑ፣ በተጠሪና በስር 1ኛ ተከሳሽ መካከል የተፈጸመዉ የግንባታ ዉልና ሕግ ተጠሪ ላይ ከጣለበት ተግባርና ኃላፉነት መገንዘብ የሚቻለዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ዋናዉ የግንባታ ዉል ከሕዝብ አገልግልት ሥራ ጋር በቀጥታ የተያያዘና የተጠሪን የግንባታ ግብዓት ከማቅረብ ጀምሮ በግንባታ ሥራዉ አፈጻጸም ላይ ያልተቋረጠ ተካፊይነት እንደነበረዉ የሚያሳይ ነዉ።
ስለሆነም ለክሱ መሰረት የሆነዉ ዋናዉ የግንባታ ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3132/ለ ስር በተመለከተዉ መመዘኛ መሰረት የአስተዲደር ዉል መሆኑን በግልጽ የሚያሣይ ነዉ። የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት በተሻሻለዉ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1/መ) ስር የከተማዉ አስተዲደር አስፈጻሚ አካላት ወይም በከተማዉ አስተዲደር ባለቤትነት ሥር ያለ ተቋማት የሚገቧቸዉን አስተዲደራዊ ዉልች በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮችን የመዲኘት ሥልጣን የተሰጠው በመሆኑና ተጠሪና የስር 1ኛ ተከሳሽ ያደረጉት የግንባታ ዉል የአስተዲደር ውል በመሆኑ የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመዲኘት ሥልጣን ያለው ሆኖ አግንኝተነዋል።
ላላው ከከተማው አስተዲደር ፍርድ ቤቶች የዲኝነት ስልጣን ጋር ተያይዞ ላታይ የሚገባው የፍደራል መንግስት አካል ተመዝጋቢ የሆነዉ የአሁን አመልካችና የስር 3ኛ ተከሳሽ የክርክሩ ተሳታፉ መሆናቸዉ በዲኝነት ስልጣን ላይ ለውጥ ያመጣል አያመጣም የሚለው ነው። ተጠሪ ከግንባታ ውል አንጻር አመልካች ላይ ክስ ሲያቀርብ በአመልካች ላይ ደግሞ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ውል አኳያ ክሱን አጣምሮ አቅርቧል።ክሱ በቀረበበት ጊዜ ሥራ ላይ በነበረዉ በፋደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5/6 ላይ በፋደራል መንግሥቱ አካል የተመዘገቡ የንግድ ድርጅቶችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮችን የመዲኘት ስልጣን የፍደራል ፍርድ ቤቶች እንደሆነ ተደንግጓል። አመልካች የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናዎች የሰጠው በተጠሪ እና በስር 1ኛ ተከሳሽ መካከል የተደረገውን የግንባታ ውል ውጤታማ ለማድረግ እንደመሆኑ ከአመልካች ጋር የተደረገው የዋስትና ውል የዋናው ውል ማለትም የግንባታ ውለ ተቀጽላ ተደርጎ የሚወሰድ ይሆናል። እንዱህ ዓይነት በአንድነት ተጣምረው መታየት የሚችለ ጉዲዮች በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ተነጥል ከታየ ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ሉያሳካው የፈለገውን ጉልበት፣ወጭና ጊዜ(ሀብት) ቆጣቢ በሆነ አግባብ ክርክርን የመምራት ዓላማ እንዲይሳካ ያደርጋል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 17/2 ላይ በአንድ ክስ ውስጥ የተለያዩ ዲኝነቶች ሲቀርቡ ዋናውን ወይም ከፍተኛውን ዲኝነት የሚመለከተው ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን እንዲለው ተመልክቷል። ተጠሪ ያቀረቡት ዋናው የክስ መሰረት ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር የተደረገው የአስተዲደር ውል የሆነው የግንባታ ውል ሲሆን በዚህ ውል ላይ ማን ግዳታውን አልተወጣም የሚለውን ተከትል የአመልካች ኃላፉነትም የሚወስን በመሆኑ አመልካች ላይ የተጠየቀው ዲኝነትም ተከታይና ተጨማሪ ዲኝነት በመሆኑ ዋናውን ዲኝነት ለመወሰን ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት አብሮ መወሰን ይኖርበታል። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ቅጽ 16 ላይም ተመሳሳይ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
አመልካች የሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ እንደተመለከተዉ የግንባታ ግብአቶች የማቅረብና ግብአቶቹ ለግንባታ ሥራዉ መዋላቸዉን የመከታተል ኃላፉነት የአስተዲደር መስሪያ ቤቱ ባልተሰጠ ዉል ላይ የተመሰረተ ክርክር መነሻ ተደርጎ የተሰጠ የሕግ ትርጉም በመሆኑ እና በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉም የሕግ ትርጉምም ከዲኝነት ሥልጣን ጋር የተያያዘ ቢሆንም የክሱ ስረ ነገር የነበረዉ የዉሃ ፍጆታ ዉል በመሆኑ አሁን ከተያዘው ጉዲይ ጋር የጭብጥ ልዩነት ያለበት በመሆኑ ለዚህ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያላቸዉ አይደለም።ይልቁንም ከተያዘዉ ጉዲይ ጋር በተያያዘ በሰ/መ/ በቀን 28/11/2012 ዓ/ም በተሰጠ ዉሳኔ(ያልታተመ) ላይ የተጠቀሰዉ አይነት የአስተዲደር አካል ተሳትፍ ያለባቸዉ የግንባታ ዉልች የአስተዲደር ዉል የሚያሰኝ መስፈርት እንደሚያሟለ እንዱሁም በሰ/መ/ በቀን 30/06/2013 ዓ/ም (ያልታተመ) በተሰጠዉ ዉሳኔ ላይ የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ዲኝነት ሥልጣን ከሚመለከተዉ የአስተዲደር ዉል ጋር ተያይዞ የቅድመ ክፍያ እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ዉልች በተመለከተም የከተማ አስተዲደሩ ፍርድ ቤቶች የመዲኘት ሥልጣን እንዲለቸዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ተሰጥቷል።
በመሆኑም ከላይ እንደተመለከተው ከዋናው የግንባታ ውል ጋር ተያይዞ የተነሳውን ክርክር የመዲኘት ስልጣን የከተማው ፍርድ ቤቶች በመሆኑ ከአመልካች አንጻር የተጠየቀውን ዲኝነትም የከተማው ፍርድ ቤቶች የመዲኘት ስልጣን አላቸው ብለናል። ስለሆነም የስር የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን እንዲለዉ ገልጾ የአመልካችን መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም ብለናል።
ላላዉ የዚህን ችልት ዉሳኔ የሚሻዉ ጭብጥ አመልካች በቅደመ ክፍያ ዋስትና ዉለ መሰረት ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለተጠሪ ይክፈል ተብል በመወሰኑ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን?የሚመለከት ነዉ።እንደመረመርነዉም አመልካች በስር 1ኛ ተከሳሽ ጠያቂነት ለተጠሪ የሰጠዉ በሰነደ ላይ Advance payment Guarantee ተብል የተገለጸ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና መሆኑ አከራካሪ አይደለም።አመልካች በዚህ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሰነድ መሰረት የስር 1ኛ ተከሳሽ ከተጠሪ ላይ በቅድመ ክፍያ መልክ የወሰደዉን ገንዘብ ከቀን 04/02/2008ዓ/ም እስከ ቀን 28/01/2009ዓ/ም ድረስ ባይመልስ በዚህ ጊዜ ዉስጥ በተጠሪ ጥያቄ ሲቀርብለት አመልካች እስከ ብር 5,360,347.60 ድረስ ለተጠሪ ለመክፈል ግዳታ መግባቱን የሥር ፍርድ ቤት ከሰነደ ያረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ነዉ።ግራ ቀኙን ያከራከረዉ ተጠሪ በሰነደ ላይ በተጠቀሰዉ ጊዜ የስር 1ኛ ተከሳሽ በቅድሚያ ክፍያ መልክ የወሰደዉን ገንዘብ ሥራ ላይ አለመዋለን ገልጾ አመልካች በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሰነደ መሰረት የክፍያ ጥያቄ አቅርቧል ወይስ አላቀረበም? በሰነደ ላይ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ ተጠሪ የክፍያ ጥያቄዉን ያላቀረበ ከሆነ ሕጋዊ ዉጤቱ ምን ላሆን ይችላል የሚለ ጭብጦች ናቸዉ።ከዚህ አኳያ ተጠሪ ያነሳዉ ክርክር በቀን 27/01/2009 ዓ/ም ለአመልካች በጻፈዉ ደብዲቤ የስር 1ኛ ተከሳሽ በዉለ መሰረት እየሰራ ስላልሆነ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ዉለ ስለተቋረጠ ብሩ ይታገድልኝ በሚል ስለጠየቅሁ የክፍያ ጥያቄ እንደቀረበ ይቆጠራል በሚል ሲሆን አመልካች ደግሞ ተጠሪ ከቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሰነደ ዉጭ ዋስትናዉ ታግድ እንዱቆይ መጠየቁ በቅድሚያ ዋስትና ዉለ መሰረት የክፍያ ጥያቄ እንዲቀረበ አያስቆጥርም በሚል ተከራክረዋል።የስር ፍርድ ቤት አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለተጠሪ እንዱከፍል የወሰነዉ ተጠሪ በቀን 27/01/2009 ዓ/ም የጻፈዉ ደብዲቤ የዋስትና ዉለ ጸንቶ ባለበት ጊዜ የተጻፈ በመሆኑና ይህ ደብዲቤ ተጠሪ በቀን 05/07/2010 ዓ/ም ክፍያ ይፈጸምልን ሲል ከጻፈዉ ጋር ተያይዞ ሲታይ ተጠሪ የክፍያ ጥያቄዉን ዉለ ጸንቶ ባለበት ጊዜ አልጠየቀም የሚያስብል አይደለም በማለት ነዉ።
ከላይ በተመለከተዉ አግባብ ለቀረበዉ የግራ ቀኙ ክርክር ተገቢዉን ዉሳኔ ለመስጠት ይረዲ ዘንድ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሰነድ (Advance Payment Guarantee/Bond) ምነትና ከላልች የዋስትና አይነቶች ያለዉ አንድነትና ልዩነት ምን እንደሆነ ማየቱ ጠቃሚ ይሆናል።በዚህ ረገድ መታየት ያለበት ይህ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ (ቅጽ 13 ላይ የታተሙ)የሕግ ትርጉም ነዉ።በእነዚህ መዛግብት ላይ በተሰጡ ዉሳኔዎች ላይ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ሰነድ (Performance Guarantee Bond) እና የገንዘብ ዋስትና ሰነድ (Financial Guarantee Bond) በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1920 እስከ 1951 ድረስ በተመለከቱ ድንጋጌዎች መሰረት የሚገዙ የዋስትና ዉልች ናቸዉ የሚል አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ተሰጥቶባቸዋል።በሰ/መ/ ላይ በተሰጠ ዉሳኔ ላይ እንደተመለከተዉ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ሰነድ (Performance Guarantee Bond) ማለት አንድ ሰዉ አንድን የተለየና የተወሰነ ሥራ ለላላ ሰዉ ለመስራት ግዳታ ከገባ ይኸዉ ሰዉ በዉለ መሰረት የገባዉን ግዳታ መፈጸም የሚችል መሆኑን ለማረጋገጥ ላላዉ ሰዉ የሚያቀርበዉ ዉል ነዉ። እንዱሁም ከኮንስትራክሽን ሥራ ጋር በተያያዘ የሚሰጥ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ለኮንስትራክሽን ሥራዉ በዉለ መሰረት መከናወን ዋስትና የሚሰጥ ሰነድ እንደሆነ ትርጉም ሰጥቷል።በልላ በኩል በሰ/መ/ ላይ በተሰጠ የሕግ ትርጉም ላይ እንደተመለከተዉ የገንዘብ ዋስትና ሰነድ (Financial Guarantee Bond) ላላ ሰዉ ያለበትን የገንዘብ እዲ በገባዉ ዉል መሰረት ባይከፍል ላላ ሰዉ ራሱ ለአበዲሪዉ እንደሚከፍል ገልጾ ራሱን ግዳታ ዉስጥ የሚያስገባበት የማገቻ ሰነድ እንደሆነ የተለያዩ ሕግጋትን በማጣቀስ ትርጉም ሰጥቷል።
ከላይ በተጠቀሱት የሰበር ሰሚ ችልት የሕግ ትርጓሜዎች ላይ ስለ ቅድሚያ ክፍያ ዋስትና (Advance Payment Guarantee/Bond) ምንነትና ከመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና እና ከገንዘብ ዋስትና ሰነድ ጋር ያለዉ አንድነትና ልዩነት ምን እንደሆነ የተመለከተ ነገር ባለመኖሩ ምንነቱን መመርመር ያስፈልጋል።
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፊይናንስ ደንብ ቁጥር 17/1989 አንቀጽ 2/1 ስር በተሰጠዉ ትርጓሜ መሰረት ‛የቅድሚያ ክፍያ“ ማለት የዋጋ ልዉዉጥ ያልተደረገበት እና ተቀባዩ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሚያወራርደዉ ክፍያ ሲሆን ዉልን መሰረት በማድረግ በዉለ የተመለከተዉ ግዳታ ከመጠናቀቁ በፉት በየደረጃዉ የሚደረግን ክፍያ አይጨምርም የሚል ትርጉም ተሰጥቶታል።በልላ በኩል ስለቴምብር ቀረጥ አከፊፈል በወጣ አዋጅ ቁጥር 110/1990 አንቀጽ 2/2 ላይ ‛ማገቻ(Bond) ማለት የተወሰነ ነገር በመፈጸሙ ወይም ባለመፈጸሙ ምክንያት የሚቀር ሆኖ አንድ ሰዉ ለላላዉ ገንዘብ ለመክፈል ግዳታ የሚገባበት ማናቸዉንም ሰነድ ወይም በምስክር የተረጋገጠ ሆኖ፣ ነገር ግን በትእዛዝም ሆነ ለአምጪዉ የማይከፈልበት አንድ ሰዉ ለላላዉ ገንዘብ ለመክፈል ግዳታ የሚገባበትን ማናቸዉንም ሰነድ ይጨምራል።“የሚል ትርጓሜ ሰጥቶታል።በተጨማሪም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3271 ስር ሥራ ተቋራጩ ከመስሪያ ቤቱ ጋራ ስለ ተዋዋለዉ ሥራ አስቀድሞ ገንዘብ ለመቀበል የሚችለዉ ለዚሁ አስቀድሞ ለሚከፈለዉ ገንዘብ እጅግ ቢያንስ ግማሹን መልሶ ለመክፈል የሚችል አንድ ዋስ ወይም ላላ ዋስትና ከሰጠ በኋላ ሆኖ በዚህ መልኩ አስቀድሞ የሚከፈለዉ ገንዘብ በሥራዉ ዉል ጊዜ በተወሰነዉ መሰረት ወደፉት ሥራ ተቋራጩ ከሚፈልጋቸዉ ቀሪ ገንዘቦች ላይ ተቀናሽ የሚሆን ገንዘብ እንደሆነ ተደንግጓል።ከተጠቃሾቹ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለዉ በተለይ ከግንባታ(ከኮንስትራክሽን) ዉል ጋር በተያያዘ ሥራ ተቋራጩ ከአሰሪዉ ጋር በገባዉ ዉል መሰረት ሥራ ከመጀመሩ በፉት ለወደፉት ሥራ ሰርቶ በየጊዜዉ ከሚከፈለዉ ክፍያ ላይ እየተቀነሰ ለአሰሪዉ ተመላሽ እንደሚያደርግ ወይም እንደሚከፍል በመስማማት አስቀድሞ የሚቀበለዉ ገንዘብ ቅድሚያ ክፍያ የሚባል ሲሆን፤ በዚህ መልኩ ሥራ ተቋራጩ ከአሰሪዉ በቅድሚያ የሚቀበለዉን ገንዘብ በዉለ በተወሰነዉ ጊዜ የግንባታ ሥራ ሰርቶ ከሚከፈለዉ ገንዘብ ላይ በየጊዜዉ እየቀነሰ ለአሰሪዉ(ለከፊዩ) ካልመለሰ ወይም መመለስ ካልቻለ ላላ ሶስተኛ ወገን በዚህ መልኩ በቅድሚያ ክፍያ መልክ ለሥራ ተቋራጩ የተሰጠዉን ገንዘብ ወይም ሥራ ተቋራጩ ሳይመለስ የቀረዉን ገንዘብ እከፍላለዉ ብል ራሱን ግዳታ ዉስጥ የሚያስገባበት ዉል ደግሞ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ዉል (Advance Payment Guarantee/Bond) እንደሚባል ነዉ።
ስለሆነም የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ዉል (Advance Payment Guarantee/Bond) የሚሰጥበት ምክንያት ከመለየቱ በስተቀር ዓላማዉ ቅድሚያ ክፍያ ለሥራ ተቋራጩ የከፈለዉ አሰሪ ሥራ ተቋራጩ በዉለ መሰረት የተቀበለዉን ገንዘብ በየጊዜዉ ከአሰሪ ከሚከፈለዉ ገንዘብ ላይ እየተቀነሰ ተመላሽ እንዱደረግ ማድረግ ባልቻለ ጊዜ ሦስተኛ ወገን ወይም በተግባር እንደሚሰራዉ ደግሞ ባንኮች ለሥራ ተቋራጩ ዋስ በመሆን የሚሰጡት የዋስትና ሰነድ በመሆኑ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ሰነድ (Performance Guarantee Bond) እና የገንዘብ ዋስትና ሰነድ (Financial Guarantee Bond) ከሚሰጥበት ዓላማ ጋር ተመሳሳይ ዓላማ ያለዉ ነዉ። በሰ/መ/ (ቅጽ 13 ላይ የታተሙ) በተሰጡ ዉሳኔዎች ላይ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ሰነድ (Performance Guarantee Bond) እና የገንዘብ ዋስትና ግዳታ ሰነድ (Financial Guarantee Bond) በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1920 እስከ 1951 ድረስ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት የሚገዙ የዋስትና ዉልች ናቸዉ ተብል አስገዲጅ የሕግ ትርጉም እንደተሰጠዉ ሁለ በሥራ ተቋራጩ በቅድሚያ ክፍያ መልክ የተወሰደዉ ገንዘብ ለአሰሪዉ የሚመለስ ስለመሆኑ ዋስትና እንዱሆን የሚሰጥ የቅድሚያ ክፍያ ማገቻ ሰነድም (Advance Payment Guarantee/Bond) በሰነድ ሰጪዉና በተጠቃሚዉ(ቅድሚያ ክፍያ በከፈለዉ አሰሪ) መካከል የዋስትና ዉል የሚያቋቁም ሰነድ በመሆኑ በእነዚሁ የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት የሚገዛ ነዉ።ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በያዝነዉ ጉዲይ ላይ እንደሆነዉ የግንባታ ዉለ የአስተዲደር ዉል በሆነ ጊዜ የአስተዲደር ዉል በሆነዉ የግንባታ ዉል መነሻ የተሰጠ ቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ተመላሽ የሚደረግ ስለመሆኑ ዋስትና እንዱሆን በልላ ሰዉ የሚሰጥ ሰነድ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3271 ስር እንደተደነገገዉ የዋስትና ዉል ተደርጎ የሚቆጠር ነዉ።ከዚህ ጋር በተያያዘ አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሰነደ እንደዋስትና ዉል የሚቆጠር ስላልሆነ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1920 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት የላቸዉም ሲል ያቀረበዉን ክርክር አልተቀበልንም።
በልላ በኩል ከላይ በተጠቀሱት በሰ/መ/ ላይ በተሰጡ ዉሳኔዎች ላይ መልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ሰነድ (Performance Guarantee Bond) እና የገንዘብ ዋስትና ግዳታ ሰነድ (Financial Guarantee Bond) መሰረት ያደረገ የክፍያ ጥያቄ የሚመለከት ክስ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1845 መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ጊዜ ዉስጥ ክሱ ካልቀረበ ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን አስገዲጅ ትርጉም ተሰጥቷል።በዚህ መልኩ የሕግ ትርጉም የተሰጠዉ ዉልቹ የዋስትና ዉል በመሆናቸዉ በዋሱ ላይ ተፈጻሚ የሚሆነዉ የይርጋ ጊዜ በዋናዉ ባለዕዲ ላይ ተፈጻሚነት ያለዉ የይርጋ ጊዜ ስለሆነ እና ግንኙነቱም የኢንሹራንስ ዉል ግንኙነት ስላልሆነ በንግድ ሕግ ቁጥር 674/1 ስር የተደነገገዉ የይርጋ ጊዜ ተፈጻሚነት የለዉም በሚል መነሻ ነዉ።የሕግ ትርጉሙ ላሰጥ የቻለዉም በግልጽ በመዝገቦቹ ላይ የይርጋ መቃወሚያ ተነስቶ ክርክር ተደርጎበት በበታች ፍርድ ቤቶች የይርጋ መቃወሚያ እና ተፈጻሚነት ስላለዉ ሕግ በተመለከተ ግልጽ ዉሳኔ ተሰጥቶ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ ስለነበር ነዉ።
በያዝነዉ ጉዲይ አመልካች በግልጽ ቅድሚያ ክፍያ መነሻ በማድረግ ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ታግዶል ሲል በግልጽ በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ላይ በተዘረጋዉ ሥርዓት መሰረት ያቀረበዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የለም። የቀረበዉ ክርክር ተጠሪ በዋስትና ሰነደ መሰረት የክፍያ ጥያቄዉን ከቀን 04/02/2008ዓ/ም እስከ ቀን 28/01/2009ዓ/ም ድረስ አላቀረበም የሚል ነዉ። ከላይ እንደተመለከትነዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሰነድ የዋስትና ዉል በመሆኑ ይህንን ዉል መነሻ ያደረገ ክስ ማቅረብ የሚቻለዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1845 ስር በተደነገገዉ መሰረት በ10 ዓመት ጊዜ ዉስጥ ነዉ። በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1855 ስር በተደነገገዉ መሰረት ክስ የማቅረብ መብት ቀሪ የሚሆንበት ጊዜ ገደብ ወይም ይርጋ የሚደነገገዉ በሕግ ሲሆን ሕግ የወሰነዉ የይርጋ ጊዜ እንዱቀር ወይም እንዱለወጥ አስቀድሞ ለመስማማት ወይም ለመዋዋል አይቻልም።በመሆኑም በግራ ቀኙ መካከል በተፈጸመዉ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ዉል ላይ ‛ከቀን 04/02/2008ዓ/ም እስከ ቀን 28/01/2009ዓ/ም ድረስ“ ተብል የተመለከተዉ ጊዜ ተጠሪ ለአመልካች የክፍያ ጥያቄ የሚያቀርብበት ጊዜ እንጂ ክስ የማቅረቢያ ጊዜ ገደብ ተደርጎ ሉወሰድ የሚችል አይደለም።
ሆኖም ተጠሪ በ10 ዓመት ጊዜ ዉስጥ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ዉል መሰረት ያደረገ ክስ ማቅረብ የሚችለዉ በዋስትና ዉለ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ ማለትም ከቀን 04/02/2008 ዓ/ም እስከ ቀን 28/01/2009ዓ/ም ድረስ“ ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ይከፈለኝ የሚል ጥያቄ ለአመልካች አቅርቦ አመልካች የክፍያ ጥያቄዉን ሳይቀበል ከቀረበት ቀን ጀምሮ ነዉ። ዉለ የዋስትና ዉል ቢሆንም ከላላዉ ዋስትና ልዩ የሚያደርገዉ ባህርይ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1920 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ የተመለከተዉ ዋስ የዋስትና ግዳታ ዉስጥ የሚገባዉ ለራሱ ጥቅም በማግኘት ባለመሆኑ፤በባንኮች ወይም በኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚሰጥ ቅድመ ክፍያ ዋስትና፣የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና …ወዘተ ግን ባንኮች ወይም የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የንግድ ድርጅቶች በመሆናቸዉ ዋስትናዎቹን ሲሰጡ ዋስትና እንዱሰጠዉ ከሚያመለክተዉ ሰዉ ላይ ባላቸዉ አሰራር መሰረት ክፍያ ወይም መያዣ በመቀበል በመሆኑ እና በዚህ መልኩ የሚቀበለት ክፍያ ወይም መያዣ በጊዜ የተገደበ ስለሚሆን በዋስትና ሰነደ ላይ ከተመለከተዉ ጊዜ ዉጭ የዋስትና ሰነደ ተጠቃሚ የክፍያ ጥያቄ ባቀረበበት በማንኛዉም ጊዜ ክፍያ መፈጸም አለባቸዉ የሚባል ከሆነ በባንኮች፣ በስተጀርባቸዉ ባለት ባለአክሲዮን፣ ገንዘብ አስቀማጮች ላይ ብልም በአገር ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ጉዲት ስለሚደርስ የዋስትና ሰነደ ተጠቃሚ የክፍያ ጥያቄዉን በዉለ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ ማቅረብ ይኖርበታል።
እንዱሁም በቅድሚያ ዋስትና ሰነደ ላይ ‛…በዚህ ዋስትና ስር የሚቀርብ ማንኛዉም የክፍያ ጥያቄ እስከ ቀን 28/01/2009ዓ/ም ድረስ መቅረብ የሚኖርበት ሲሆን በእኛ በኩል ጥያቄዎች ተቀባይነት የሚኖርባቸዉ ከመቀበያዉ ቀን በፉት ወይም በእለቱ ነዉ።…“ በሚል የተገለጸዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1865 ስር በስምምነቱ ወይም በልዩ ሁኔታዉ ለባለገንዘቡም እንዱጠቅም ተብል ካልተደረገ በቀር የጊዜዉ መሰጠት ሁልጊዜ ለባለዕዲዉ ጥቅም እንደተደረገ ይቆጠራል በሚል ከተደነገገዉ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሰነደ ላይ የተመለከተዉ ተጠቃሹ ጊዜ በዋናነት ለአመልካች ጥቅም የተቀመጠ እንደሆነ የሚያሳይ ነዉ።በመሆኑም የተጠሪ ክስ ተቀባይነት አግኝቶ አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ እንዱከፍል ሉወሰን የሚችለዉ ተጠሪ የክፍያ ጥያቄዉን እስከ ቀን 28/01/2009ዓ/ም ድረስ ማቅረቡ ሲረጋገጥ ብቻ ነዉ።
ነገር ግን የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የክፍያ ጥያቄዉን በቅድሚያ ክፍያ ዉለ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ አቅርቧል ሲል የደረሰበት ድምዲሜ የማስረጃ ምዘና ከሚመለከተዉ መሰረታዊ መርህ አተገባበር አኳያ መመርመር ያለበት እንደሆነ ተገንዝበናል።የስር ፍርድ ቤት ወደዚህ ድምዲሜ የደረሰዉ ተጠሪ በቀን 27/01/2009ዓ/ም በቁጥር ቢ/ግ/ቅ/13/24/246/09 ለአመልካች የጻፈዉን ደብዲቤ ይዘት ጠቅሶ የደብዲቤዉ ይዘት ‛የስር 1ኛ ተከሳሽ በዉለ መሰረት እየሰራ ባለመሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ዉለ ስለመቋረጡ ጠቅሶ ብሩ ይታገድልን ።“ የሚል በመሆኑ የዚህ የደብዲቤ ይዘት ተጠሪ በቀን 05/07/2010ዓ/ም ክፍያ ይፈጸምልኝ ብል ለአመልካች ከጻፈዉ ደብዲቤ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ ተጠሪ በቀን 27/01/2009 ዓ/ም በጻፈዉ ደብዲቤ የክፍያ ጥያቄ አላቀረበም የሚያስብል አይደለም በሚል ነዉ።ሆኖም ተጠሪ ተገቢዉን ማስረጃ አቅርቦ ማስረዲት የሚገባዉና የስር ፍርድ ቤትም ተጠሪ ማስረዲቱን ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ተጠሪ የክፍያ ጥያቄዉን እስከ ቀን 28/01/2009ዓ/ም ድረስ ለአመልካች ማቅረቡን ቢሆንም ተጠሪ በቀን 27/01/2009ዓ/ም ለአመልካች የጻፈዉ ደብዲቤ ይዘት በግልጽ የሚያሳየዉ በዚህ ደብዲቤ የጠየቀዉ የዋስትና ገንዘብ እንዱታገድ እንጂ በዋስትና ሰነደ ላይ የተመለከተዉ ገንዘብ እንዱከፈለዉ መጠየቁን የሚያሳይ አይደለም።እንዱሁም በዋስትና ዉለ ላይ የተመለከተዉ ጊዜ ካለፈ በኋላ 1 ዓመት ከ6 ወር በላይ ቆይቶ ክፍያ ይፈጸምልኝ በማለት ተጠሪ በቀን 05/07/2010 ዓ/ም ለአመልካች የጻፈዉ ደብዲቤም በቀን 27/01/2009ዓ/ም ከተጻፈዉ ደብዲቤ ጋር ተጣምሮ መታየቱም የሕግ መሰረት የላለዉና በዉለ የተመለከተዉ ጊዜ ለአመልካች ጥቅም መቀመጡን ዋጋ የሚያሳጣ በመሆኑ ተቀባይነት ያለዉ አይደለም።
ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ዉለ ላይ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ የክፍያ ጥያቄ አቅርቧል በማለት አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለተጠሪ ይክፈል ሲል የደረሰበት ድምዲሜ ተጠሪ በማስረጃነት ባቀረበዉና በቀን 27/01/2009ዓ/ም ከተጻፈዉ የሰነድ ማስረጃ ግልጽ ይዘት ዉጭ ከመሆኑም በተጨማሪ የዉለን የጊዜ ሁኔታና ዓላማ ያላገናዘበ ነዉ ብለናል። አንድን ክርክር ለማስረዲት የቀረበ ማስረጃ ይዘትን ያላገናዘበ ዉሳኔ መስጠት የማስረጃ ምዘና የሚመለከት መሰረታዊ መርህ የጣሰ ሰለሚሆን መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንደሆነ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ(በቅጽ 11 እንደታተመዉ) እና በሰ/መ/ ላይ እና በላልች መዛግብት ላይ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።በመሆኑም አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለአመልካች እንዱከፍል በአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተወሰኖ በየደረጃዉ በከተማዉ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እና በሰበር ሰሚ ችልት የጸናዉ ዉሳኔ የማስረጃ ምዘና መሰረታዊ መርህና የሕግ አተገባበር ጉድለት ያለበት በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተከታዩ ተወስኗል።
የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 20/01/2013 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 18/09/2013 ዓ/ም የሰጠው ዉሳኔ እና የከተማዉ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 12/11/2013ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሻሽለዋል።
አመልካች ቅድሚያ ክፍያ ዋስት ዉል መሰረት ተደርጎ የተጠየቀዉን ብር 422,500.00(አራት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ለተጠሪ ሉከፍል አይገባም ብለናል።ይህንን ገንዘብ የስር 1ኛ ተከሳሽ ለተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት አለበት የተባለዉ የዉሳኔ ክፍል እና ላላዉ የዉሳኔ ክፍል አልተነካም።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.