የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ለማስተላለፍ የተደረገ ውል በውል አዋዋይ ፉት ተረጋግጦ የተመዘገበ ከሆነ በስጦታ ውለ ላይ ውለ በስጦታ ሰጪና በምስክሮች ፉት የመነበብ ስርዓት የተፈፀመበት ነው ተብል እነ መሰረት ወ/አማኑኤል (2 ሰዎች) እና የመነበብ ስርዓት በሰነድ አረጋጋጩ እንደተፈፀመ ተቆጥሮ የስጦታ ውለ ህጋዊ ውጤት እንዱኖረው ላደረግ የሚገባ ስለመሆኑ (የፋ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት በፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በሰ/መ/፣70057፣147331፣17429 ላይ እና በላልች መዝገቦች ላይ ከኑዛዜ እና ከስጦታ ውል ፍርምና ከመነበብ ስርዓት ጋር በተያያዘ የተሰጠ የሕግ ትርጉም ተለውጧል።) እነ ጌታቸው ይልማ (3 ሰዎች)
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 30 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- መአዛ አሸናፉ ሰለሞን አረዲ ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል መከተል የሚገባዉን ፍርማሉቲና ሕጋዊ ዉጤቱን የሚመለከት ነዉ። ተጠሪዎች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአመልካቾች ላይ በመሰረቱት ክስ አመልካቾች ከሟች እናታችን ወ/ሮ ስንቅነሽ ወልደአማኑኤል በዉርስ የሚተላለፍልንን ቤት ይዘዉ በቀን 06/07/2009ዓ/ም በተደረገ የስጦታ ዉል ሟች አስተላልፈዉልናል በማለት የዉርስ ሀብት አካል ሆኖ ሉጣራና ክፍፍል ሉፈጸምበት አይገባም በማለት ተቃዉመዋል።ሆኖም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 እና 881/2 በተደነገገዉ መሰረት በስጦታ ዉለ ላይ ለስጦታ አድራጊዋ መነበብ እንዲለበት የተመለከተዉ ሥርዓት የተፈጸመ ስለመሆኑ ዉለ አያሳይም።የስጦታ ዉለ ተጠሪዎችን ከዉርስ የሚነቅል ነዉ። እንዱሁም የስጦታ ዉለ ተደረገ በተባለበት ጊዜ የሟች እድሜ ከ90 አመት በላይ ስለሆነ በስጦታ ዉለ ላይ ያለዉ ፊርማ አና ስም በሟች እናታችን የተጸፈ አይደለም።ስለሆነም የስጦታ ዉለ ፈራሽ ነዉ ተብል ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካቾች ለክሱ በሰጡት መልስ የስጦታ ዉለን ሟች በምስክሮች ፉት ተነቦላቸዉ ፈርመዋል።የስጦታ ዉለ በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተደረገ በመሆኑ የዉለን ይዘትና ፊርማዉን ማስተባበል አይቻልም።ሟች ከመሞታቸዉ በፉት ባላቸዉ በንብረታቸዉ ላይ የመወሰን መብት ተጠቅመዉ በስጦታ ባስተላለፈልን መሰረት የቤቱ ስመ ሀብት በቀን 17/09/2009 ዓ/ም በአመልካቾች ስም ተመዝግቦ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጥቶናል።ሟች የስጦታ ዉለን ሲያደርጉ እድሜያቸዉ ከ80 ዓመት በላይ የማይሆን ቢሆንም እድሜያቸዉ 80 ወይም 90 ዓመት በመሆኑ የስጦታ ዉለን ተገንዝበዉ ሉፈርሙ አይችለም ልባል አይችልም።ሰነድችን ለማፈራረምና ለመመዝገብ ሥልጣን የተሰጠዉ የመንግስት አካል ሟች በስጦታ ዉለ ቤቱን ለማስተላለፍ ሙለ ፍላጎት እንዲላቸዉ አረጋግጦ ዉለን ስለመዘገበ ከዚህ አኳያ የቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም።ሟች በህይወት እያለ ለአመልካቾች በስጦታ ስላስተላለፈና ሟች ኑዛዜ ትተዋል የሚያሰኝ ነገር ባለመኖሩ ሟች በስጦታ ባስተላለፈት ንብረት ላይ የዉርስ ጥያቄ ሉነሳ ስለማይችል ተጠሪዎች ከዉርስ ተነቅለናል በሚል የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የለዉም የሚለ መከራከሪያዎችን በማንሳት ክሱ ዉድቅ እንዱሆን በመጠየቅ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ እና የስጦታ ዉለን ከሕግ ጋር አገናዝቦ በመመርመር በቀን 19/02/2011ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የስጦታ ዉለ የመጨረሻዉ ክፍል ‛ስጦታ አድራጊ ለስጦታ ተቀባይ ወደዉና ፈቅደዉ ተስማምተዉ በዉለ የተጠቀሰዉን መኖሪያ ቤት በስጦታ ሉያስተላልፈና በዉለም ላይ ሲፈራረሙ ማየታችንን በፊርማችን እናረጋግጣለን።“ በማለት ምስክሮች ማረጋገጣቸዉንና መፈረማቸዉን የሚያሳይ ቢሆንም በዉለ ላይ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 እና 881/2 ስር በአስገዲጅነት በተደነገገዉ መሰረት የስጦታ ዉለ ስለመነበቡ በግልጽ የሰፈረ ነገር የለም።ሕጉ ኑዛዜዉ መነበብ አለበት የሚል ብቻ ሳይሆን የተነበበ ስለመሆኑም ተገልጾ መጻፍ አለበት የሚል በመሆኑ በሕጉ አግባብ በዉለ ላይ የመነበብ ስርዓት መፈጸሙን በሚያመላክት መልኩ አልተገለጸም።ዉለ በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተመዘገበ ቢሆንም ይህ አካል በሕጉ በጥብቅ የተደነገገዉን መስፈርት ማስቀረት አይችልም።ዉለ በዉል አዋዋይ ፉት መደረጉ ዉለ በሕጉ የተመለከተዉን መስፈርት ማሟላት አለማሟላቱን ከመመርመር የሚያግድ አይደለም።በመሆኑም ሟች ወ/ሮ ስንቅነሽ ወ/አማኑኤል በቀን 06/07/2009 ዓ/ም በተደረገ የስጦታ ዉል በአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ ወረዲ 06 ክልል ዉስጥ የሚገኘዉን የቤት ቁጥር 338 የሆነ መኖሪያ ቤት ለአመልካቾች በስጦታ ለማስተላለፍ ያደረጉት ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 እና 881/2 ስር በተደነገገዉ እና በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ አስገዲጅ ትርጉም መሰረት የመነበብ ሥርዓት የተፈጸመበት ስለመሆኑ የተገለጸበት ስላልሆነ ፈርሷል በማለት ወስኗል።
አመልካቾች ከፍ ሲል በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በመ/ አከራክሮ በቀን 28/09/2011 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ በዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ ኑዛዜ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 882 መሰረት ዋጋ እንዱኖረዉ በ2 ምስክሮች ፉት መደረጉ ብቻ በቂ ነዉ።በዚህ ድንጋጌ መሰረት ኑዛዜዉ ለምስክሮች መነበብ እንዲለበት እንደቅድመ ሁኔታ አልተደነገገም። በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ 17(1/ሀ እና ሐ) ስር ተረጋግጦ የሚመዘገብ የስጦታ ዉል በምስክሮች ፉት መነበብ እንዲለበት አላስቀመጠም።ይህም የሆነዉ ገለልተኛ የሆነዉ አካል በግልጽ የተደረገ ኑዛዜን ሲያረጋግጥ የኑዛዜዉን ፍሬ ነገር ለምስክሮችም ሆነ ለተናዛዡ በመግለጽ(በማንበብ) ያረጋግጣል ተብል ስለሚጠበቅ ሕግ አዉጪዉ በዚህ አግባብ የሚረጋገጠዉን ሰነድ ለምስክሮች ማንበብ ይገባዋል ብል መደንገግ አላስፈለገዉም።ስለዚህ ኑዛዜዉ በምስክሮች ፉት አልተነበበም ተብል ክርክር ላቀርብበት የሚገባ አይደለም።ከዚህ አኳያ በአዋጅ ቁጥር 922/2008 ላይ የተደነገገዉ ግልጽ ነዉ። ይህ አዋጅ ከፍትሐ ብሓር ሕግ በኋላ የወጣ ሕግ በመሆኑ በሁለቱ ሕጎች መካከል ተቃርኖ ካለ የፍትሐ ብሓር ሕጉ ተፈጻሚነት አይኖረዉም።ስለሆነም የስጦታ ዉለ በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተደረገ ስለሆነና ስለኑዛዜ ከተደነገገዉ አንጻር የሚታይበት ምክንያት ስለላለ የስር ፍርድ ቤት ዉለ የፍትሐ ብሓር ሕግ ያስቀመጠዉን ፍርማሉቲ አላሟላም በማለት እንዱፈርስ መወሰኑ ተገቢ አይደለም ሲል የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ ሽሯል።
በመቀጠል ተጠሪዎች ይግባኝ ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዉ ችልቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 29/07/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ በአከራካሪዉ ዉል ላይ ስጦታ አድራጊዋ ተነቦላቸዉ የፈረሙ ስለመሆኑ በግልጽ የሚያሳይ ሀረግ የለም።ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 ስር ኑዛዜዉ በተናዛዡ ፉት መነበብ አለበት ተብል የተደነገገዉ ሥርዓት የተፈጸመበት አይደለም።ዉለ በዉል አዋዋይ ፉት መደረጉ በሕግ በአስገዲጅነት የተደነገገዉን ይህንን ሥርዓት የሚያስቀር ካለመሆኑም በተጨማሪ ለስጦታ ሰጭዋ የተነበበ ስለመሆኑ በሰነደ ላይ አልተገለጸም የሚል ክርክር ከማቅረብ የሚከለክል አይደለም።እንዱሁም የስጦታ ዉለ ስጦታ ሰጭ በህይወት እያለ የሚፈጸም መሆኑም የሕጉን መስፈርት እንዲያሟላ የሚያደርግ አይደለም።ስለሆነም የስጦታ ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 ስር በተደነገገዉና በሰ/መ/፣147331 ላይ በተሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት በስጦታ ሰጪዋ ፉት ስለመነበቡ ስለማያሳይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዉለ እንዱፈርስ መወሰኑ ተገቢ ነዉ በማለት የከፍተኛ ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል።አመልካቾች ለዚህ ችልት በቀን 15/11/2012 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ይግባኝ ሰሚዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ አጭር ይዘት የሚከተለዉ ነዉ።
ስጦታ ሰጭዋ በህይወት እያለ ስመ ሀብቱ ወደ አመልካቾች ስም ዞሮ ተመዝግቧል። ስጦታ ሰጭዋ በሞቱበት ጊዜ ቤቱ በእጃቸዉ ስላልነበረ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881 እና 2443 ተፈጻሚነት የለዉም።እነዚህ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት የሚኖራቸዉ ስጦታ ሰጭዋ የስጦታ ዉለ የሚፈጸመዉ እኔ ከሞትኩ በኋላ ነዉ በሚል ያደረጉት ስጦታ ቢሆን ነበር።ስጦታ አድራጊ በህይወት እያለ የሚፈጸም የስጦታ ዉል ከሆነና የንብረቱ ስመ ሀብት ወደ ስጦታ ተቀባይ የዞረ ከሆነ ስለኑዛዜ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881 የተደነገገዉ ተፈጻሚነት የለዉም በማለት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/(ቅጽ 10) የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።በዚህ መሰረት አከራካሪዉ ዉል በዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 882 መሰረት በሁለት ምስክሮች ፉት የተደረገ ዉል ከሆነ በቂ ነዉ።በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 ስር የተደነገገዉ ተፈጻሚነቱ በዉል አዋዋይ ፉት ላልተደረገ(በተለምድ የመንደር ዉል በሚባለዉ አኳኋን ለተደረገ የስጦታ(ኑዛዜ)) ብቻ ነዉ።የስጦታ ዉለ በተደረገበት ጊዜ ስጦታ ሰጭ በንብረታቸዉ ላይ የመወሰን መብታቸዉን ተጠቅመዉ ለአመልካቾች ሲያስተላልፈ በምስክሮች ፉት ፈቃዲቸዉ ተጠይቆና ተረጋግጦ የተመዘገበ ዉል ሆኖ እያለ ስለመነበቡ የሚገልጽ ሀረግ በዉለ ላይ ባለመገለጹ ብቻ ኑዛዜዉ ፈራሽ ላሆን እንደማይችል በሰ/መ/(ቅጽ 2) ላይ አስገዲጅ ትርጉም ተሰጥቶበታል።በአዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ 17/ሀ መሰረት የተደረገ የስጦታ ዉል ሕጋዊነቱ ተረጋግጦ የተመዘገበ ስለሆነ ወይም ይዘቱና ፊርማዉ እምነት የሚጣልበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 መሰረት የመነበብ ስርዓት አያሟላም ተብል ይዘቱ ሉስተባበልና ሉፈርስ የሚገባ አይደለም ተብል ይግባኝ ሰሚዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ የተፈጸመዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ታርሞ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ይፅናልን በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ ሟች ለአሁን አመልካቾች ያደረጉት የስጦታ ዉል በዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ መሆኑ ባልተካደበት ሁኔታ ሟች በህይወት እያለ ስመ ሀብቱ የተዛወረን ቤት የስር ፍርድ ቤት ፍርማሉቲ አያሟላም በማለት ዉለ ፈራሽ ላሆን ይገባል ሲል የወሰነበት የሕግ አግባብ ተጠሪዎች ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በቀን 17/02/2013 ዓ/ም የተፃፈ በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ አቅርበዋል።
አመልካቾች ሟች በህይወት እያለ በስጦታ ንብረታቸዉን አስተላልፈዉልናል በማለት ያነሱት ክርክር ተጠሪዎች የማናዉቀዉና አዱስ ክርክር በመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 329 ላይ የተደነገገዉን የሚቃረን በመሆኑ ተቀባይነት ሉኖረዉ አይገባም።ተጠሪዎች የስጦታ ዉል መኖሩን ያወቅነዉ ዉርስ በተጣራበት ጊዜ ነዉ።የስጦታ ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443፣881/2 እና 882 ስር የተደነገገዉን ፍርማሉቲ የማያሟላ በመሆኑ ፈራሽ ነዉ ተብል መወሰኑ ሕግን መሰረት ያደረገ ስለሆነ የተፈጸመ ስህተት የለም።እናታችን በህይወት እያለ የቤቱ ስመ ሀብት ወደ አመልካቾች ስም ዞሮ የተመዘገበዉ የስጦታ ዉለ ሕጉ ያስቀመጠዉን ፍርማሉቲ ባላሟላበት ሁኔታ በመሆኑና ተጠሪዎችም የዉርስ ሀብቱን እንዲንካፈል በማሰብ ከቅን ልቦና ዉጭ ያደረጉት በመሆኑ ስመ ሀብቱ በአመልካቾች ስም ዞሮ መመዝገቡ የሕጉን ፍርማሉቲ የማያሟላ ዉል እንዲይፈርስ የሚከለክል አይደለም።ስለሆነም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 መሰረት የስጦታ ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881-883 ስር የተደነገገዉን ፍርማሉቲዎች ማሟላት እንዲለበት በአስገዲጅነት የተደነገገዉን ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የስጦታ ዉል እንደማያሟላ ተረጋግጦ የተወሰነ በመሆኑ የተፈጸመ ስህተት የለም ተብል የሰበር አቤቱታዉ ዉድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል። አመልካቾችም በቀን 14/03/2013 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም ሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ከግራ ቀኝ ክርክር፣ከዚህ ቀደም ከጉዲዩ ጋር በተያያዘ በሰበር ሰሚ ችልት ከተሰጠ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም እና አግባብነት ካለዉ ሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም ሟች ወ/ሮ ስንቅነሽ ወ/አማኑኤል በአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ ወረዲ 06 ክልል ዉስጥ የሚገኘዉን የቤት ቁጥር 338 የሆነ መኖሪያ ቤታቸዉን በቀን 06/07/2009ዓ/ም በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ፉት ተረጋግጦ በተመዘገበ የስጦታ ዉል ለአመልካቾች በስጦታ ለማስተላለፍ ዉል መዋዋላቸዉን ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን የተሰጣቸዉ የስር ፍርድ ቤቶች ከግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃዎች የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።አንዱሁም ሟች ወ/ሮ ስንቅነሽ ወ/አማኑኤል ከዚህ አለም በሞት የተለዩት በቀን 05/06/2010ዓ/ም መሆኑን፣ተጠሪዎች የሟች ወራሾች መሆናቸዉን ያረጋገጡት በቀን 17/07/2010ዓ/ም እንደሆነና የስጦታ ዉለን ተከትል በሟች ስም የነበረዉ ቤት ወደ አመልካቾች ስም ዞሮ ተመዝግቦ ለአመልካቾች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጣቸዉ በቀን 17/09/2009ዓ/ም እንደሆነ ከስር የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገብ ተመልክተናል።ግራ ቀኙን ያከራከረዉና የዚህን ችልት የሕግ ትርጉም የሚሻዉ ጭብጥ ሟች ወ/ሮ ስንቅነሽ ወ/አማኑኤል መኖሪያ ቤታቸዉን ለማስተላለፍ ያደረጉት የስጦታ ዉል በስጦታ ሰጭዋና በምስክሮች ፉት ካልተነበበና በዉለ ላይ የማንበብ ሥርዓት ስለመፈጸሙ ያልተመለከተ ከሆነ ሕጋዊ ዉጤቱ ምን ላሆን ይገባል?
ከዚህ ጋር በተያያዘ ተፈጻሚነት ያላቸዉ ሕጎች ትክክለኛ ትርጉም ምን ላሆን ይገባል? የሚለ ናቸዉ።
ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ የስጦታ ዉል ላይ የዉለ ጉዲይ የሆነዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ማስተላለፍ በመሆኑ በፍትሐ ብሓር ሕጉ ቁጥር 2443 ስር በተደነገገዉ የስጦታ ዉል ፍርም ሥርዓት መሰረት መፈጸም ይኖርበታል።በዚህ ድንጋጌ ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ ዉል የሚፈጸምበት ፍርም በሚከተለዉ መሰረት ተደንግጓል።
ቁ.፪ሺ፬፻፵፫ የስጦታ ሥርዓት ፍርም(፩) የማይንቀሳቀስ ንብረቶች ‛በማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ መብትን የሚሰጥ ስጦታ በግልጽ በሚደረግ ኑዛዜ አሰራር ዐይነት ካልተደረገ ፈራሽ ነዉ።“ የሕጉ የእንግሉዝኛዉ ቅጅ Art. 2443 - Form – 1. Immovabes ‛A donation relating to an immovable or a right on an immovable shall be of no effect unless it is made in the form governing the making of a public will (Art. 881-883).” ከላይ ይዘቱ የተመለከተዉን ድንጋጌ አፈጻጸምና ትርጓሜ ከመመልከታችን በፉት ስለስጦታ ምንነት መመርመሩ ተጠቃሹ ድንጋጌ ሉኖረዉ የሚገባዉን ትክክለኛ አፈጻጸምና ትርጉም(Application and interpretation) ላይ ለመድረስ ጠቃሚ ይሆናል።ከስጦታ ዉል ሕግ(Law of Contracts of Donation) ጽንሰ ሀሳብና በዘርፈ ከተጻፈ ድርሳናት እንደምንገነዘበዉ ስጦታ ሁለት ገጽታዎች አለቱ።ይሄዉም ስጦታ ሰጪዉ በህይወት እያለ ስጦታ ተቀባዩ የተሰጠዉን ንብረት የግል አድርጎ እንዱጠቀም መብት የሚሰጥ ስጦታ ዐይነት በላቲን donation inter vivos (የቁም ኑዛዜ) ተብል የሚታወቀዉ አንደኛዉ ነዉ። ይህም ስጦታ ሰጭ በህይወት እያለ በንብረቱ ላይ ያለዉን የመወሰን ወይም ከሁለ የሰፊ የባለቤትነት መብት በመጠቀም ለፈለገዉ ሰዉ ንብረቱን የሚያስተላልፍብትን ሥርዓት የሚመለከት ነዉ።ሁለተኛዉ ዐይነት ደግሞ ስጦታ ሰጪዉ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ ተፈጻሚ የሚሆን [የ]ስጦታ [ዉል] በላቲን donation mortis causa በሚል የሚታወቀዉ ነዉ። ይህም አንድ ሰዉ ሲሞት ንብረቱን የሚወስደዉን ወይም የሚወርሰዉን ሰዉ ከወዱሁ በስጦታ ዉል የሚወስንበት ሥርዓት ሲሆን ስጦታ ተቀባዩ ስጦታ በተደረገለት ንብረት ተጠቃሚ መሆን የሚጀምረዉ ስጦታ ሰጪዉ መሞቱን ተከትል በመሆኑ እንደ ኑዛዜ ስጦታ የሚቆጠር ነዉ።እንዱሁም ይህ ሁለተኛዉ ዐይነት የስጦታ ዉል የሟቹን ሀሳብ በአግባቡ ተግባራዊ ከማድረግ (executing the will of the deceased) አንጻር እና ስጦታ ያልተደረገላቸዉ የሟቹ ወራሾች ሉኖራቸዉ የሚችለዉ የዉርስ መብት ከግምት እየገባ በዉርስ ሕጉ መሰረት ሟቹ ያደረገዉ የስጦታ ዉል አፈጻጸም ሉመረመር ስለሚችል በእንዱህ አይነት ስጦታ የስጦታ ሰጭዉ መብት በአንጻራዊነት በሕግ በተመለከተዉ ምክንያት ሉገደብ የሚችል ነዉ።
ይህንን አጠቃላይ የስጦታ ጽንሰ ሀሳብ ይዘን ከላይ ይዘቱ የተመለከተዉን ድንጋጌ እንመልከት።በአገራችን ስጦታንና ኑዛዜን የሚገዙ ድንጋጌዎች በፍትሐ ብሓር ሕጉ በሁለት የተለያዩ ዘርፍች ተደንግገዋል። በፍትሐ ብሓር ሕጉ ከቁጥር 2427 እስከ 2470 ስለ ስጦታ በጠቅላላዉ የተደነገገ ሲሆን በፍትሐ ብሓር ሕጉ አንቀጽ (Title) አምስት ስር ስለወርስ በጠቅላላዉ እና በተለይ ደግሞ በክፍል 3 ከቁጥር 857 ጀምሮ ባለ ድንጋጌዎች ስለኑዛዜ ተደንግጓል።ከላይ ይዘቱ የተመዘገበዉ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 ከርዕሱ ጀምሮ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ሲተላለፍ ዉለ መደረግ ስላለበት ፍርም በጠቅላላዉ የሚመለከት መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነዉ።በድንጋጌዉ ላይ የተመለከተዉን ፍርም መከተል ያለበት የትኛዉ ዐይነት የስጦታ ዉል ነዉ የሚለዉን ድንጋጌዉ ልዩነት አለማስቀመጡንም የድንጋጌዉ ይዘት ያሳያል። ይህም ስጦታ ሰጭ በህይወት እያለ ተፈጻሚ የሚሆነዉን የስጦታ አይነት (donation inter vivos) በተመለከተ የሚደረግ ዉልም ሆነ ስጦታ ሰጭ ከሞተ በኋላ ተፈጻሚ የሚሆነዉን ስጦታ (donation mortis causa) በተመለከተ የሚደረግ ዉል በድንጋጌዉ ላይ በተመለከተዉ መሰረት በግልጽ ለሚደረግ ኑዛዜ በፍ/ብ/ሕግ ከቁጥር 881 እስከ 883 የተደነገገዉን ተከትል መደረግ እንዲለበት በአስገዲጅነት መደንገጉን የሚያሳይ ነዉ። በዚህ መልኩ ጥብቅ የሆነ የዉል አደራረግ ሥርዓት የተደነገገበት ምክንያት ስጦታ ሰጭ ያለዋጋ ስጦታ ወይም ችሮታ በማድረግ ሀሳብ(without consideration) ንብረቶቹን (ከንብረቶቹ አንደን) ለመስጠት ግዳታ የሚገባበት በመሆኑ ዉለ የስጦታ ሰጭዉን ፈቃድ (ፍላጎት) በማያሻማ መልኩ የሚገልጽ መሆኑን ለማረጋገጥ እንዱያስችል ለማድረግ ካለዉ ዓላማ ነዉ።
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 የተደነገገዉ ሁለቱም ዐይነት የስጦታ ዉል መከተል ስላለበት ፍርም የተደነገገ መሆኑን ተመልክተናል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ለሁለቱም ዐይነት ስጦታ ዉል በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጻሚ የሚሆኑት በፍትሐ ብሓር ሕግ ስለኑዛዜ በሚመለከተዉ ክፍል ዉስጥ ካለ ድንጋጌዎች መካከል በግልጽ ስለሚደረግ ኑዛዜ ፍርም ከቁጥር 881 እስከ 883 ድረስ የተመለከቱት ሲሆኑ ከእነዚህ ድንጋጌዎች በስተቀር ኑዛዜን የሚገዙ ላልች ድንጋጌዎች ስጦታ ሰጭ በህይወት እያለ ተፈጻሚ የሚሆነዉን የስጦታ ዐይነት (donation inter vivos) በተመለከተ ተግባራዊ የሚሆኑ አይደለም።ይህንን ድምዲሜ የሚያጠናክረዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2428 ላይ በሞት ምክንያት የሚደረጉ ስጦታዎች (donation mortis causa) በሚል ርዕስ ስር ‛ሰጪዉ ሲሞት ይፈጸማለ ተብለዉ በተወሰኑት ስጦታዎች ላይ ስለኑዛዜ የተነገሩት ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ይሆናለ።“በሚል መደንገጉ ነዉ።በመሆኑም ስጦታ ሰጭ በህይወት እያለ ተፈጻሚ የሚሆነዉን የስጦታ ዉል ፍርም (forms of donation inter vivos) በተመለከተ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881-883 ድረስ የተደነገጉ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ሲሆኑ በላልች ይሄኛዉን የስጦታ ዉል በሚመለከቱ ጉዲዮች ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ድንጋጌዎች በፍ/ብ/ሕግ በቁጥር 2427 እና ተከታዮቹ ስለስጦታ የተደነገጉት ናቸዉ።
ቀጥለን በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር ከቁጥር 881 እስከ 883 ስር በግልጽ ለሚደረግ ኑዛዜ (ከዚህ በኋላ ኑዛዜ ተብል የተገለጸዉ እንደነገሩ ሁኔታ የስጦታ ዉልንም የሚመለከት ነዉ) ከተቀመጡ የፍርም ሥርዓቶች መካከል ከተያዘዉ ጉዲይ ጋር በተያያዘ ትርጉም ለሚሹ ድንጋጌዎች አጽንኦት ሰጥተን እንመረምራለን።
በፍ/ብ/ሕግ ከቁጥር 881 እስከ 883 ድረስ ባለ ድንጋጌዎች በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ ማሟላት ያለባቸዉ ናቸዉ ተብለዉ የተጠቀሱ መስፈርቶች፡- 1)ኑዛዜዉ በጽሁፍ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ(የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/1 ይመለከተዋል)፣2) ስለምስክሮች ብዛት፣ችልታ እና ስለተናዛዡና ስለምስክሮች ፊርማ(የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881(1 እና 3)፣882 እና 883 ይመለከቷል)፣ 3) ኑዛዜዉ በተናዛዡና በአራት ምስክሮች ፉት መነበብና ይኸዉ ሥርዓት መፈጸሙንና የተፈጸመበትን የሚያመላክት መሆን ያለበት ስለመሆኑ(በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 ይመለከቷል) እንዱሁም 4) እነዚህን መስፈርቶች አለማሟላት ስለሚያስከትለዉ ዉጤት ተደንግጓል።ምንም እንኳን በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ በዉል አዋዋይ ፉት እንዱደረግና እንዱመዘገብ (Authentication) ሕግ ባያስገድድም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 882 ስር እንደተመለከተዉ በግልጽ የተደረገዉ ኑዛዜ በዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ እንደሆነ ኑዛዜዉ በሁለት ምስክሮች ፉት የተደረገና የተፈረመ ከሆነ በቂ ሲሆን ከዚህ ዉጭ በሆነ አኳኋን በተለምድ የመንደር ዉል በሚል በሚገለጸዉ አኳኋን የተደረገ ከሆነ ግን ኑዛዜዉ(የስጦታ ዉለ) በአራት ምስክሮች ፉት ተደረጎ በአራቱም ምስክሮች የተፈረመ መሆን አለበት።
ላላዉ ትርጉም የሚሻዉ ነጥብ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 ስር ኑዛዜዉ በተናዛዡና በአራት ምስክሮች ፉት መነበብና ይኸዉ ሥርዓት መፈጸሙንና የተፈጸመበትን የሚያመላክት መሆን አለበት የሚለዉ መስፈርት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 882 መሰረት በዉል አዋዋይ ፉት ለተደረገ ግልጽ ኑዛዜ ጭምር ሉፈጸም የሚገባ ሥርዓት ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉ ነዉ። አንድን ሕግ ተግባራዊ ለማድረግ ወይም ለመተርጎም ጥቅም ላይ የሚዉለ የተለያዩ መርሆዎች፣ድክትሪኖችና ቴክኒኮች ያለ ሲሆን የሕጉን ቃላት በቀጥታ ተግባራዊ ማድረግ (Texutualism ) ተብል የሚታወቀዉን የአተረጓገም አካሄድ የሚከተለ ዳኞች (ፍርድ ቤቶች) ሕግ አዉጪዉ አካል ያወጣቸዉን ሕግጋት ሕጎቹ በወጡበት ጊዜ ያላቸዉን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸዉ እንጂ ሕግ አዉጪዉ በቃላቶቹ ለማስተላለፍ የፈለገዉን ዓላማ መፈለግ የለባቸዉም የሚል አስተሳሰብ የሚከተለ ናቸዉ። ላላዉ የሕግ አተረጓጎም አካሄድ ዓላማዊነት (Purposeivism) ተብል የሚታወቀዉ ሲሆን ይህንን ዘዳ ተከትለዉ ሕግ የሚተረጉሙ ዳኞች(ፍርድ ቤቶች) ትርጉም የሚያስፈልጋቸዉን ሕግጋት ሲተርጉሙ ሕግ አዉጪዉ ሕጉን ሲያወጣ የነበረዉ ሀሳብና ሉያሳካ የፈለገዉ ዓላማ ምን እንደሆነ አዉቀዉ መተርጎም አለባቸዉ የሚለዉን ኃላፉነት መወጣት አለባቸዉ የሚለዉን ታሳቢ ያደርጋለ።ይህንንም ኃላፉነት ለመወጣት ማንኛዉም ሕግ የራሱ የሆነ ዓላማ ይዞ የሚወጣ በመሆኑ ዳኞች የሚተረጎመዉን ሕግ ቃላቶች፣አዉድ፣የጉዲዩን ምንነት፣ዉጤት እና የሕጉን መንፈስ ተከትለዉ ወደ ሕግ አዉጪዉ ዓላማ የሚያደርስ ትርጉም መስጠት አለባቸዉ ይላለ።በዋናነት የሚጠቀሱ የሕግ አተረጓጎም እነዚህ ቢሆኑም ከዓላማዊነት አተረጓጎም ጋር ተቀራራቢ ዉጤት ያለዉ ቴሉ'ልጅካል የሕግ አተረጓጎም(teleological interpretation of law) እና ላልች የሕግ አተረጓጎም ሥርዓቶች መኖራቸዉም የሚታወቅ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 79/1 ስር እንደተደነገገዉ በአገራችን የዲኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች በመሆኑ ዲኝነት በተጠየቀበት ጉዲይ ላይ አግባብነት ያለዉን ተፈጻሚ ሕግ ለይቶ በቀጥታ ተግባራዊ ማድረግም ሆነ ለሕጉ ትርጉም መስጠት ባስፈለገ ጊዜ ሕጎችን በመተርጎም ዲኝነት መስጠት የፍርድ ቤቶች ሥራ ነዉ። ሕግ መተርጎም ማለት ለአንድ ሕግ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ፍቺ መስጠት ማለት ነው።በአገራችን ዳኞች ሕግን ሲተረጉሙ መከተል ስላለባቸዉ መርሆዎችና ዘዳዎች ወጥ በሆነ መልኩ የወጣ ሕግ ባይኖርም በተለያዩ ሕጎች ላይ በተበታተነ መልኩ የተደነገገዉንና(ለአብነት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1733-1737) በዲኝነት ሥራ በተግባር የዲበረዉን (Judicial jurisprudence) መሰረት በማድረግ ትርጉም የማያሻቸዉ ሕጎች ሲሆኑ በቀጥታ ተግባራዊ በማድረግ ትርጉም የሚፈልጉትን ደግሞ ሕግ ፉደል ብቻ ሳይሆን ፉደልና መንፈስ (letter and sprit) መሆኑን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ፉደለን ብቻ ሳይሆን መንፈሱንም የተከተለ እንዱሆን በማድረግ የሕግ አተረጓጎም ዘዳዎችን በየሚዛናቸዉ በማየት ሲተረጎም ይስተዋላል።ይህ ሰበር ሰሚ ችልት እስከአሁን በሰጠዉ የሕግ ትርጉሞች ላይ በአብዛኛዉ በዚህ መልኩ ትርጉም ለሚፈልጉ ሕግጋት ትርጉም ሲሰጥ ቆይቷል፤እየተሰጠም ይገኛል።የተያዘዉም ጉዲይ በዚሁ አግባብ ተመርምሯል።
በያዝነዉ ጉዲይ ላይ ትርጉም ከሚሹ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በተያያዘ አስቀድሞ በሰበር ሰሚ ችልት የተሰጡ ትርጉሞችን የተመለከትን እንደሆነ በሰ/መ/(ቅጽ 13 ላይ እንደታተመዉ) ላይ በተሰጠ የሕግ ትርጉም የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 882 የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/1 ተከታይ ሆኖ የተደነገገ በመሆኑና በዉል አዋዋይ ፉት ለሚደረግ ግልጽ ኑዛዜ ስለመነበብ ሥርዓት የተደነገገዉ በኋለኛዉ ድንጋጌ አስፈላጊ አይሆንም ተብል ስላልተደነገገ በዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ ኑዛዜ ቢሆን እንኳን በተናዛዡና በምስክሮች ፉት ኑዛዜዉ ስለመነበቡ በሰነደ ላይ ካልተመለከተ ኑዛዜዉ ፈራሽ ነዉ በማለት ወስኗል። በሰ/መ/ ላይም ተመሳሳይ ትርጉም ተሰጥቷል።በልላ በኩል ደግሞ በላልች በሰ/መ/(ቅጽ 2 ላይ እንደታተመዉ) እና በሰ/መ/(ቅጽ 4 ላይ እንደታተመዉ) ሕጉ ኑዛዜ መነበብ አለበት ብል ያስቀመጠበት ዓላማ ኑዛዜዉ በሚነበብት ወቅት የተናዣዡ ፈቃድ መሟላቱን ማረጋገጥ እንዱቻል በመሆኑ በኑዛዜዉ ላይ ስለመነበቡ ባይገለጽም በኑዛዜዉ ላይ ‛ሲናዘዙ ሰምተናል፤አይተናል“ በሚል የተገለጸዉ አገላለጽ ምስክሮች ያዩትና የሰሙት ኑዛዜዉ ሲደረግና የተጻፈዉ ሲነበብ ነዉ ተብል ሉገመትና ለኑዛዜዉ ዉጤት ሉሰጠዉ ይገባል የሚል ትርጉም ተሰጥቷል።
እንዱሁም ከቁም ኑዛዜ (ከስጦታ ዉል )ጋር በተያያዘ በሰ/መ/(ቅጽ 5 ላይ እንደታተመዉ) ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቁም ኑዛዜ (donation inter vivos) በዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 መሰረት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 882 ስር የተደነገገዉን ፍርማሉቲ የሚያሟላ ነዉ በሚል ትርጉም ተሰጥቷል።
ስለአንድ ጉዲይ ለተደነገገ ድንጋጌ ትርጉም ሲሰጥ የሚሰጠው ትርጉም የተለያየ ሳይሆን ካለት የተለያዩ ትርጉሞች ውስጥ ለድንጋጌዉ ህይወት ለሰጡት ቃላትም ተገቢዉን ዋጋ በመስጠት ሕጋዊ ተቀባይነት ያለውንና ወደ ግቡ የሚያደርስ ትርጉም መስጠት ይገባል። የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 መስፈርት የተደነገገዉ በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ ወይም ደግሞ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 ላይ በተደነገገዉ መሰረት ሁለቱም ዐይነት ስጦታ ሲደረግ የስጦታ ዉለ ሉከተል የሚገባዉ ፍርም አካል ሆኖ የተደነገገ ነዉ።በዚህ መልኩ ስለፍርም ለተደነገገዉ ድንጋጌ ትርጉም ሲሰጥ ቃላቱን ብቻ ሳይሆን በድንጋጌዉ በተካተቱ ቃላት ለማሳካት የተፈለገዉን ዓላማ ከግብ በሚያደርስ መልኩ ወጥ የሆነና በአግባቡ ጥቅም ላይ ሉዉል የሚችል ትርጉም ላሰጥ ይገባል።በተጨማሪም ከዚህ ድንጋጌ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ በተለይም ኑዛዜ ወይም የስጦታ ዉል በሕግ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ወይም ዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ በሆነ ጊዜ ከዚህ ድንጋጌ ጋር ግንኙነት ያለዉ በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 922/2008 እና ይህንን አዋጅ ተግባራዊ ሲያደርግ የሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የሚከተለዉ አሰራር ከግምት ገብቶ ሉመረመር ይገባል።
እንደሚታወቀዉ ኑዛዜ እና የስጦታ ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር በተደነገገዉ መሰረት የግድ በዉል አዋዋይ ፉት እንዱደረጉ የማይጠበቅባቸዉ የዉል አይነቶች ናቸዉ። ስለኑዛዜና ስለስጦታ ዉል ሕጉ ባስቀመጠዉ ፍርም ላይ በተለይም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 ስር ‛ኑዛዜዉ መነበብ እንዲለበትና ይኸዉ ስለመፈጸሙ በኑዛዜዉ ሰነድ ላይ መመልከት አለበት‛ የሚለዉ መስፈርት የተቀመጠበት ዓላማ በኑዛዜዉ ወይም በስጦታ ዉለ ላይ የሰፈረዉ ቃል የተናዛዡ ወይም የስጦታ ሰጭዉ መሆኑን በመቆጣጠር ፈቃደን ያለእንከን መስጠቱን ማረጋገጥ ይቻላል በሚል ዓላማ ነዉ። ይህንን ዓላማ ለማሳካት የተቀመጠዉ መስፈርት በዉል አዋዋይ ፉት ያልተደረገ ኑዛዜ ወይም የስጦታ ዉል ሲሆን ኑዛዜዉ ወይም የስጦታ ዉለ በተናዛዡ (በስጦታ ሰጭ) እና በአራት ምስክሮች ፉት ካልተነበበና ይኸዉ ሥርዓት መፈጸሙ በኑዛዜ ሰነደ ወይም በስጦታ ዉለ ላይ ካልተመለከተ በሰነደ ላይ የሰፈረዉ ቃል የተናዛዡ(የስጦታ ሰጪዉ)መሆኑ ሉረጋገጥ የሚችልበት መንገድ ስለማይኖር በጥብቅ ተግባራዊ ላደረግና ይኸዉ ሥርዓት ካልተፈጸመም ኑዛዜዉ ወይም የስጦታ ዉለ ፈራሽ ላሆን ይገባል።
በልላ በኩል ኑዛዜ ወይም የስጦታ ዉል በዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ እንደሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 ስር የተደነገገዉ የፍርም አካል የሆነዉ መስፈርት ሲሆን በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 922/2008 (በቀድሞዉ የሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 334/1995/በአዋጅ ቁጥር 467/1997 እንደተሻሻለዉ በተመሳሳይ እንደተመለከተዉ) ዓላማና በአዋጁ ዝርዝር ድንጋጌዎች አንድን ሰነድ ለማረጋገጥ ከተዘረጋዉ ሥርዓት ጋር ተገናዝቦ መታየት አለበት።በዚህ አዋጅ መግቢያ ላይ እንደተመለከተዉ…በሰዎች መካከል የሚደረጉ ማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ላልች መስተጋብሮችን በሚመለከት የሚፈጸሙ የዉል እና ላልች ግንኙነቶችን በሕግ አግባብ በማረጋገጥ እምነት የሚጣልበት ሰነድ ማመንጨት በአዋጁ በተዘረጋዉ ሥርዓት ለማሳካት የታለመ ዓላማ ነዉ።
በተጨማሪም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 7/3 ስር እንደተመለከተዉ ማንኛዉም ሰነድ የማረጋገጥና የመመዝገብ ተግባር እንዱፈጽም በአዋጁ ሥልጣን የተሰጠዉ አካል የዜጎችን የግል ንብረት የማፍራት፣የመጠቀም እና በሕጋዊ መንገድ የማስተላለፍ መብቶችን በማስከበር የፍትሕ ሥርዓቱን በማገዝ የሕግ የበላይነትን የማስጠበቅ ዓላማ ከግብ የማድረስ ኃላፉነት አለበት።በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 2(2 እና 5) ፣8/5 እና 10/2 ስር ሰነድ አረጋጋጩ አዱስ ሰነድ በአዘጋጁ ወይም ጉዲዩ በሚመለከተዉ ሲፈረም ማየትና ይኸዉ መፈጸሙን ማረጋገጥ ወይም በትክክል መስፈሩን በማረጋገጥ እንዱፈረም ማድረግ ፣ለመረጋገጥ የሚቀርቡ ሰነድችን ሕጋዊነት ማረጋገጥ እንዱሁም በአዋጁ አንቀጽ 17 ስር የተደነገገዉ እንደተጠበቀ ሆኖ አግባብ ባላቸዉ ሕጎች የተደነገገዉን ሥርዓት መከተል የሰነድ አረጋጋጩ ተግባርና ኃላፉነት እንደሆነ ተደንግጓል። በተጨማሪም ሰነድ አረጋጋጩ ሰነድ ከማረጋገጡና ከመመዝገቡ በፉት የሰነደን ይዘት የመለወጥ ወይም የማስለወጥ ሥልጣን ባይኖረዉም የሰነደን ይዘት ትክክለኛነት የማረጋገጥና የሰነደ ይዘት ሕግንና ሞራልን የማይቃረን መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፉነት እንዲለበት በአዋጁ አንቀጽ 13 ላይ የተደነገገዉ ያሳያል።
ሰነድ አረጋጋጩ ከላይ በተጠቀሰዉ መሰረት የማረጋገጥ ኃላፉነቱን በአግባቡ ይወጣል በሚል እምነት ሕግ አዉጪዉ በአዋጁ አንቀጽ 17 ስር የስጦታ ዉል ወይም ኑዛዜ የማረጋገጥና የመመዝገብ ተግባር በሚፈጸምበት ጊዜ ሁለት ምስክሮች እንዱፈርሙ ማድረግ እንደሚገባ ከመደንገጉ በስተቀር በዚህ በአዋጁ አንቀጽ 17 ላይ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 በተደነገገዉ መሰረት ሰነድ አረጋጋጭ ‛ኑዛዜ መነበብ እንዲለበትና ይኸዉ ስለመፈጸሙ በኑዛዜዉ ሰነድ ላይ መመልከት አለበት‛ የሚለዉ በኑዛዜ ሰነደ ወይም በስጦታ ዉለ ላይ መመልከቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል በሚል አልደነገገም።ሕግ አዉጭዉ ይህንን መስፈርት በዝምታ ያለፈበት ምክንያት የስርዓቱ መፈጸም አስፈላጊ አይደለም በሚል ሳይሆን ሰነድ አረጋጋጭ ኑዛዜ ወይም የስጦታ ዉል ከማረጋገጡና ከመመዝገቡ በፉት(before authenticating and registering) የሰነደን ይዘት ትክክለኛነት የማረጋገጥና ይዘቱ ሕግንና ሞራልን የማይቃረን መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፉነት በአግባቡ ይወጣል በሚል እምነት ሰነደ ላይ በቃላት ባይገለጽም አረጋጋጩ የማረጋገጥ ተግባሩን ሲወጣ የታለመዉ ዓላማ ከግብ ይደርሳል በሚል ነዉ።
በመሆኑም በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ(ሥልጣን በተሰጠዉ ዉል አዋዋይ ፉት) ተረጋግጦ በተመዘገበ የኑዛዜ ሰነድ ወይም የስጦታ ዉል ላይ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 በተደነገገዉ መሰረት ‛ኑዛዜ መነበብ እንዲለበትና ይኸዉ ስለመፈጸሙ በኑዛዜዉ ሰነድ ላይ መመልከት አለበት‛ የሚለዉ ሥርዓት ስለመፈጸሙ በግልጽ ያልተገለጸ ቢሆንም እንኳን ይህ ተግባር ኑዛዜ ወይም የስጦታ ዉል ከመረጋገጡና ከመመዝገቡ በፉት በሰነድ አረጋጋጩ እንደተፈጸመ ሉቆጠር ይገባል እንጂ ይህ ሥርዓት ስለመፈጸሙ የሚያመላክቱ ቃላት ወይም ሐረጋት በኑዛዜ ሰነደ ወይም በስጦታ ዉለ ላይ አልተመለከተም በሚል ኑዛዜዉ ወይም የስጦታ ዉለ ፈራሽ ላሆን አይገባም።
ከላይ ከተመለከተዉ የሕጎቹ አቋምና ትርጉም አንጻር የያዝነዉን ጉዲይ ስንመለከት ሟች ወ/ሮ ስንቅነሽ ወ/አማኑኤል በአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ ወረዲ 6 ክልል ዉስጥ በካርታ /1 የተመዘገበ በቤት ቁጥር 338 የሚታወቀዉን መኖሪያ ቤታቸዉን በቀን 06/07/2009ዓ/ም በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ተረጋግጦ በተመዘገበ ዉል ለአመልካቾች በስጦታ ማስተላለፊቸዉ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።በዉለ ላይ ስጦታ ሰጭና ሁለት ምስክሮች መፈረማቸዉ ተመልክቷል። እንዱሁም የስጦታ ዉለ ላይ አመልካቾች ሟች በህይወት እያለ መኖሪያ ቤቱን በስማቸዉ እንዱጠቀሙበት ሟች መስማማታቸዉ ተመልክቷል። በዚህ መሰረት ሟች በህይወት እያለ የመኖሪያ ቤቱ ስመ ሀብት ከሟች ስም ወደ አመልካቾች ስም ዞሮ መመዝገቡ ስለተረጋገጠ ስጦታዉ ስጦታ ሰጭ በህይወት እያለ ተፈጻሚ የሚሆን የስጦታ ዐይነት (donation inter vivos) ነዉ። ለእንዱህ ዐይነት ስጦታ ከዉለ ፍርም ዉጭ ላለ ጉዲዮች ተፈጻሚ የሚሆኑ ድንጋጌዎች በፍትሐ ብሓር ሕጉ ስለስጦታ የተደነገጉ ድንጋጌዎች በመሆናቸዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2463 መሰረት ስጦታ ተቀባዮች ስጦታዉን መቀበላቸዉን ዉለ ያሳያል።በስጦታ ዉለ ላይ ከፍርም አንጻር ስለመፈጸሙ በቃላት ወይም በሐረጋት ያልተመለከተዉ ሥርዓት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2 ስር የተደነገገዉ ‛ኑዛዜ(የስጦታ ዉለ) መነበብ እንዲለበትና ይኸዉ ስለመፈጸሙ በኑዛዜዉ ሰነድ(በስጦታ ዉለ) ላይ መመልከት አለበት‛ የሚለዉ ነዉ።ይህ በስጦታ ዉለ ላይ ስለመፈጸሙ ያልተመላከተዉ የፍርም መስፈርት ከላይ እንደተገለጸዉ የስጦታ ዉለ በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ተረጋግጦ የተመዘገበ በመሆኑ በሰነድ አረጋጋጩ ዉለ ተረጋግጦ በተመዘገበበት ጊዜ እንደተፈጸመ የሚቆጠር በመሆኑ ሥርዓቱ ስለመፈጸሙ በዉለ ላይ በቃላትና በሐረጋት ባለመገለጹ ብቻ እንዲልተፈጸመ ተቆጥሮ ዉለ ፈራሽ የሚሆንበት ምክንያት የለም።
ሲጠቃለል የስጦታ ዉል ስጦታ ሰጪዉ በህይወት እያለ የሚፈጸምም ሆነ ስጦታ ሰጭዉ ከሞተ በኋላ የሚፈጸም ቢሆንም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 ስር በተደነገገዉ መሰረት በፍ/ብ/ሕግ ከቁጥር 881 እስከ 883 ድረስ በግልጽ ለሚደረግ ኑዛዜ የተደነገገዉን ፍርም ተከትል መፈጸም አለበት።ሆኖም የስጦታ ዉል በዉል አዋዋይ ፉት ተረጋግጦ የተመዘገበ ከሆነ ግን በስጦታ ዉለ ላይ ዉለ በስጦታ ሰጭና በምስክሮች ፉት የመነበብ ሥርዓት የተፈጸመበት እንደሆነ የሚያመላክት አገላለጽ ያልተመለከተ ቢሆንም የመነበብ ሥርዓት በሰነድ አረጋጋጩ እንደተፈጸመ ተቆጥሮ ዉለ ዉጤት ሉኖረዉ ይገባል።በዚህ መሰረት በሰ/መ/(ቅጽ 13 ላይ እንደታተመዉ)፣በሰ/መ/፣በሰ/መ/(ቅጽ 2 ላይ እንደታተመዉ) እና በሰ/መ/(ቅጽ 4 ላይ እንደታተመዉ) እና በላልች መዝገቦች ላይ ከኑዛዜና ከስጦታ ዉል ፍርም ጋር በተያያዘ የተሰጠ የሕግ ትርጉም ተፈጻሚነታቸዉ በዉል አዋዋይ ፉት ተረጋግጠዉ ባልተመዘገቡ ኑዛዜዎችና የስጦታ ዉልች ላይ ብቻ ነዉ በሚል በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26 መሰረት ተሻሽለዋል።እንዱሁም በሰ/መ/(ቅጽ 5 ላይ እንደታተመዉ) በተሰጠ የሕግ ትርጉም ላይ የቁም ኑዛዜ(ስጦታ ሰጭ በህይወት እያለ የሚፈጸም የስጦታ ዉል/donation inter vivos) በዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ ከሆነ በፍ/ብ//ሕግ ቁጥር 2443 መሰረት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 882 ስር የተደነገገዉን ፍርማሉቲ ካሟላ በቂ እንደሆነ በሚያመላክት መልኩ መተርጎሙ- በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 ላይ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881 እስከ 883 ድረስ የተደነገጉ የፍርም አካል የሆኑ ላልች መስፈርቶችን ያላገናዘበና ሰነድ አራጋጋጭ የሰነደን ይዘት ትክክለኛነትና የስጦታ ሰጭዉን ፈቃድ ከማረጋገጥ ጋር ያለበትን ኃላፉነት ቀሪ እንደሆነ በሚያመላክት መልኩ የተሰጠ ትርጉም በመሆኑ በመዝገቡ ላይ ከፍርም ጋር በተያያዘ የተሰጠዉ የሕግ ትርጉም ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ትርጉም እንዱተካ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26 መሰረት ተለዉጧል።ስለሆነም የስር የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከላይ እንደተመለከተዉ የስጦታ ዉለ ፈራሽ ነዉ ብል መወሰኑ እንዱሁም ጉዲዩን በይግባኝ ያየዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ከላይ በዝርዝር በተመለከተዉ መሰረት በማየት የስጦታ ዉለ ዉጤት እንዱኖረዉ በማድረግ መወሰን ሲገባዉ አዋጅ ቁጥር 922/2008ን መሰረት በማድረግ የስጦታ ዉለ ሉፈርስ አይገባም ሲል የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሰነዉን በመሻር የሰጠዉ ዉሳኔ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881/2ን ዓላማ እና የአዋጅ ቁጥር 922/2008ን ዓላማና በአዋጁ የተዘረጋዉን ሰነድ የሚረጋገጥበትን ሥርዓት ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 19/02/2011ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 29/07/2012ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 28/09/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ ከላይ በፍርደ ሀተታ ላይ በተመለከተዉ አግባብ በተወሰነ ደረጃ ምክንያቱ ተሻሽል በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንቷል።
በሰ/መ/፣ በሰ/መ/፣በሰ/መ/ እና በሰ/መ/ ላይ እና በላልች መዝገቦች ላይ በተመሳሳይ ከኑዛዜ እና ከስጦታ ዉል ፍርም ጋር በተያያዘ የተሰጠ የሕግ ትርጉም ከፍ ሲል በፍርደ ላይ በተመለከተዉ ልክ ተሻሽለዋል።እንዱሁም በሰ/መ/ ላይ እና በተመሳሳይ በላልች መዝገቦች ላይ የተሰጠ የሕግ ትርጉም ከቁም ኑዛዜ(ከስጦታ ዉል) ፍርም ጋር በተያያዘ የተሰጠዉ የሕግ ትርጉም በዚህ ፍርድ ማጠቃለያ ላይ በተመለከተዉ አግባብ ተለዉጧል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
ግራ ቀኙ ሲጠይቁ ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ ዕግድ ካለ ተነስቷል ፤ይጻፍ።
የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ይመለስ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.