በጽሁፍ የተደረገ ውል በይዘቱ ውለ ለጥቅሙ የተደረገለትን ሶስተኛ ወገን የማይገልጽ ከሆነ በውለ ላይ በግልጽ ከተመለከቱት ከተዋዋዮች ሀሳብ ውጪ በመውጣት ተዋዋዩ ውለን በስሙ የተዋዋለው ለራሱ ጥቅም ሳይሆን ለላላ ሶስተኛ ወገን ጥቅም ነው በማለት በውለ በግልጽ ከተመለከተው ተዋዋይ ውጪ ላላ ሰው ተጠቃሚ እንዱሆን በማድረግ ፍርድ ቤቶች ውልን አንዱተረጉሙ ህግ ስለማይፈቅድ በእኔ ገንዘብ የተገዛ ቤት ነው በሚል በልላ ሰው ስም የተገዛና የተመዘገበ ቤት ለማስለቀቅ የሚቀርብ ክስ ተቀባይነት የላለው አቶ መልካምአየሁ መንገሻ እና እነ ወ/ሮ አለም በርሄ (2 ሰዎች)
No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 26 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ መልካምአየሁ መንገሻ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ አመልካች በእኔ ገንዘብ ለእኔ ጥቅም የተገዛ ቤት ነዉ በማለት በተጠሪዎች ስም የተመዘገበ ቤት አስለቅቀዉ ለመረከብ ያቀረቡት ክስ ዉድቅ ተደርጎ በመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል የቀረበ የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ።አመልካች በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ የ1ኛ ተጠሪ ባለቤት እና የ2ኛ ተጠሪ አባት እንዱሁም የአመልካች ወንድም በሆኑት አቶ ታደለ መስፍን ስም ቤት ለመግዛት ፈልጌ በቀድሞ ወረዲ 22 በአሁኑ በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበላ 02 ወይም ወረዲ 02 የካርታ ቁጥር 02/35/8608/1237/01 የተመዘገበ የቦታዉ ስፊት 263 ካሬ ሜትር የወ/ሮ ቀነኔ ዲርጌ ንብረት የሆነዉን ቤት ቅድመ ክፍያ ብር 385,000.00 በባንክ ሂሳባቸዉ በወንድሜ ስም ገቢ አድርጌያለሁ።ብር 578,600.00 ለሻጭ ወኪል በመክፈል በተለምድ የመንደር ዉል በሚባለዉ በሟች ወንድሜ ታደለ መስፍን ስም የቤት ግዥ ፈጽሜያለሁ።ለስም ማዛወሪያና ለተያያዥ ወጪዎች ብር 100,000.00 ከፍያለሁ።አመልካች በዜግነት ካናዲዊ ስለሆንኩ የመቆያ ጊዜዬ ስለተጠናቀቀ ቀሪዉን ሟች ወንድሜ እንዱጨርሱ ዉክልና በመስጠት ተከራይቶ የሚኖርበትን ቤት ለቆ በዚህ ቤት ዉስጥ በጠባቂነት እንዱቀመጥበትም አድርጌያለሁ።ከዚህ በኋላ ሟች ቤቱን በብር 200,000.00 እንደተገዛ በማስመሰል በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት እንዱመዘገብ በማድረግ ህይወታቸዉ እስካለፈበት መስከረም 2003 ዓ/ም ድረስ በመኖሪያነት ቀሪዎቹን ክፍልች ጨምረዉ ሲገለገለበት ነበር። ተጠሪዎች ቤቱን በአደራ መልክ የተቀመጡበት መሆኑን እያወቁ የቤቱን ስመ ሀብት በስማቸዉ አዛዉረዉ አስመዝግበዋል።ስለሆነም ተጠሪዎች ምንም ገንዘብ ያላወጡበትንና ያላፈሩትን ከሕግ ዉጪ አለአግባብ ለመበልጸግ ይዘዉ አለቅም ስላለ ቤቱን ለቀዉ እንዱያስረክቡኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መልስ የ1ኛ ተጠሪ ባለቤትና የ2ኛ ተጠሪ አባት ሟች አቶ ታደለ መስፍን ከቤቱ ሕጋዊ ባለቤት በቀን 13/04/2003 ዓ/ም በሕጋዊ መንገድ ግዥ ፈጽመዉ ያገኙትና ስመ ሀብቱም በስማቸዉ ተዛዉሮ ይገኝ የነበረ ነዉ።አቶ ታደለ መስፍን ከሞቱ በኋላም ዉርሱ ተጣርቶ ስመ ሀብቱ ወደ ተጠሪዎች ስም ዞሯል።አመልካች ሟች በአደራ የቤቱ ጠባቂ ነበሩ በማለት የገለጹት የሕግ መሰረት የለዉም።ሟች የወሰደት ገንዘብ ካለ የብድር ግንኙነት መኖሩን መሰረት በማድረግ ከሚጠይቁ በስተቀር ለተያዘዉ ጉዲይ አግባብነት ስለላለዉ ክሱ ዉደቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎች መርምሮ በቀን 23/07/2013 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች በክሳቸዉ ላይ ቤቱን በአደራ በጠባቂነት እንዱይዙ ሰጥቻቸዋለሁ በማለት የገለጹ ቢሆንም ይህ ላሆን የሚችለዉ በቤቱ ላይ ተጠሪዎች መብት እንደላላቸዉ ሲያረጋግጡ ነዉ።ቤቱን በሰነድች ማረጋገጫና ምዘገባ ጽ/ቤት በቀን 13/04/2003ዓ/ም በተደረገ ዉል ገዥ በመሆን ከሻጮች ጋር የተዋዋለት ሟች አቶ ታደለ መስፍን ናቸዉ። አመልካች ለቤቱ መግዣ የተከፈለዉ ገንዘብ የእኔ ነዉ ቢለም ይህንን የሚገልጽ ፍሬ ነገር በዉለ ዉስጥ አልተመለከተም።አቶ ታደለ መስፍን ዉለን ያደረጉት በራሳቸዉ መብት እንጂ በዉክልና አይደለም።በዚሁ እለት አቶ ታደለ መስፍን ከሻጩ ጋር የመንደር ዉል ያደረጉት በራሳቸዉ ስም ነዉ።ይህ ባይሆን እንኳ የመንደር ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1720/1 መሰረት እንደረቂቅ የሚቆጠር ነዉ።በዉል አዋዋይ ፉት የተደረገዉ ዉል መሰረት ሆኖ የቤቱ ስመ ሀብት ወደ አቶ ታደለ ስም ዞሮ ተመዝግቧል።አቶ ታደለ ከሞቱ በኋላ ወደ ተጠሪዎች ስም ተላልፍአል።በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1195 መሰረት በቤቱ ላይ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ያላቸዉ ተጠሪዎች ሲሆኑ አመጣጡም በሕጋዊ ዉል ላይ የተመሰረተና ዉለም እስካሁን ስላልፈረሰ ባለቤት ስለመሆናቸዉ የሚወሰደዉ ግምት አልተስተባበለም። በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1731/1 እና 1952/1 መሰረት የሽያጭ ዉለ መብትና ግዳታ የሚፈጥረዉ በተዋዋዮች መካከል ስለሆነ ተዋዋይ ያልሆኑት አመልካች በዉለ ላይ ለእሳቸዉ ጥቅም የተደረገ ስለመሆኑ የተገለጸ ነገር ባለመኖሩ ዉለ የሚሰጣቸዉ መብት የለም።አመልካች ይህንን ዉል አላስፈረሱም።አመልካች ለቤቱ መግዣ ወይም ለእኔ ግዛልኝ ብለዉ ገንዘብ ሰጥተዉ ከሆነ ገንዘቡን ከሚጠይቁ በስተቀር በዉለ ሕጋዊነት ላይ የሚያመጣዉ ለዉጥ የለም።ተጠሪዎችም ቤቱን በሕጋዊ መንገድ መያዛቸዉን አያስቀረዉም።ተጠሪዎች ቤቱ በሕጋዊ መንገድ በቤተስብ እና በዉርስ ሕግጋት መሰረት ተላልፍላቸዉ ስለያዙት በአደራ ይዘዋል ወይም አለአግባብ በልጽገዋል ለማለት እንደማይቻል ከፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1162 እና 2779 ይዘት መገንዘብ ይቻላል።ስለሆነም ተጠሪዎች ክስ የቀረበበትን ቤት የያዙት የባለሀብትነት መብት በሕጋዊ መንገድ ተላልፍላቸዉ ስለሆነ ለአመልካች ለቀዉ ሉያስረክቡ እና በስማቸዉ የተመዘገበዉ ሉሰረዝ አይገባም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።እንዱሁም አመልካች ለሟች አቶ ታደለ መስፍን የሰጡት ገንዘብ ካለ የሚመለከተዉን ሰዉ ከሰዉ የመጠየቅ መብታቸዉ የተጠበቀ ነዉ ሲል ወስኗል።
አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ በቀን 18/06/2013ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞባቸዋል።
አመልካች በቀን 18/09/2013 ዓ/ም የተጻፈ አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ፡-በስር ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 246 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ጭብጥ ተይዟል በሚል በዉሳኔዉ የገለጸዉ ፍጹም ሀሰት እና የአመልካችን ፍትህ የማግኘት እና በእኩል የመደመጥ መብት ያላከበረ ስለሆነ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 25 እና 37 ስር የተደነገገዉን የሚቃረን ነዉ።የስር ፍርድ ቤት ክርክሩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 246 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት አልመራም።አመልካች ያቀረብኩትን 20 ገጽ የሰነድ ማስረጃዎች እና የኤላክትሮኒክስ ዱጂታል ማስረጃዎችን በአንድነት ሳይመረምርና ምስክሮች ቃላቸዉን ሳይሰጡ እንዱሁም ተገቢዉን ጭብጥ ሳይመረምር የሰጠዉ ዉሳኔ ነዉ።አመልካች ያቀረብኩት ክስ በቅን ልቦና ላይ የተመሰረተ ሆኖ ከሕግ አግባብ ዉጭ ያቀረብኩት ክስ ዉድቅ መደረጉ ሳያንስ ለተጠሪዎች ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብት ጠብቆ የሰጠዉ ዉሳኔ የሕጉን መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበ ነዉ።ስለሆነም የተፈጸመዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ታርሞና የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ተሽሮ ተገቢዉ ጭብጥ ተመስርቶ የአመልካች የመሰማት መብት ተጠብቆ፣ በአመልካች ማስረጃዎች ተጣርቶና ተመርምሮ እንዱወሰን ጉዲዩ ለስር ፍርድ ቤት ሉመለስ ይገባል በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃዎች ሳይሰማ የወሰነበትን አግባብ ከመሰረታዊ የክርክር አመራር መርሆዎች አንጻር ተጠሪዎች ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ በመሰጠቱ ተጠሪዎች በቀን 25/02/2014 ዓ/ም የተጻፈ መልስ አቅርበዋል።የመልሳቸዉም ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች ያቀረቡት ክስ የቤት ባለቤትነትን የመፊለም ነዉ።አመልካች በክሳቸዉ መሰረት እና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1206 መሰረት ቤቱን በእጃቸዉ ይዘዉ ሲያዙበት እንደነበር እና በቤቱ ላይ ከተጠሪዎች የበለጠ መብትና ጥቅም እንዲላቸዉ የሚያሳይ ማስረጃ በማቅረብ አላስደም። አመልካች ቤቱን በስሜ ግዛልኝ በማለት ከሟች ጋር ያደረጉት ዉል የለም፤ማስረጃ ሆኖም አልቀረበም።ቤቱን በሟች አቶ ታደለ መስፍን ስም የገዙ ስለመሆኑ የሚያሳይ አንድም የሰነድ ማስረጃ አላቀረቡም።ተጠሪዎች ቤቱ በስማችን ተመዝግቦ የሚገኝ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ አቅርበን አስረድተናል። የአመልካች ጠበቃ የኤላክትሮኒክስ እና የሰነድ ማስረጃ ስላለኝ አቀርባለሁ እያለ በችልት ሁልጊዜ በቃል ከመናገር ባለፈ ዉሳኔ እስከተሰጠበት እለት ድረስ ያቀረቡት ማስረጃ የለም።ማስረጃ አቅርበዉ ባላስረደበት ሁኔታ የስር ፍርድ ማስረጃ ካለ ለወደፉት ይቅረብ ብል ትእዛዝ ለመስጠት የሚችልበት የሕግ አግባብ ሳይኖር እንደተከለከለ አስመስለዉ ያቀረቡት ክርክር በሕግ ተቀባይነት የለዉም።የስር ፍርድ ቤት የክርክር አመራርም ሆነ የተሰጠዉ ዉሳኔ ከጭብጥ አመሰራረት አኳያም ሆነ ከማስረጃ ምዘና አንጻር የአመልካችን ፍትህ የማግኘት መብት ታልፍ የተሰጠ ነዉ ልባል የሚችል ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ እንዱሁም ምስክሮች ያልተሰማዉ የቀረበዉ ማስረጃ የመፊለም ክስ ላይ ዉሳኔ ለመስጠት በቂ ሆኖ ስለተገኘ በመሆኑ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ዉድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
በአመልካች በኩል የቀረበ የመልስ መልስ የለም።
ከዚህ በላይ አጠር ባለመልኩ የተገለጸዉ የግራ ቀኙን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም ሰበር አጣሪ ችልት የያዘዉን ጭብጥ ከግምት በማስገባት የስር ፍርድ ቤት አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት ተጠሪዎች እንዱለቁላቸዉ ለማስወሰን ያቀረቡትን ክስ ዉድቅ በማድረግ በሰጠዉ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም የአመልካች ክስ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት በሰጠኋቸዉ ገንዘብ የ1ኛ ተጠሪ ባለቤትና የ2ኛ ተጠሪ ወላጅ አባት ሟች አቶ ታደለ መስፍን በስሜ ለእኔ ጥቅም የገዙልኝ ሆኖ ሳለ በመጀመሪያ በሟች ስም በኋላም በተጠሪዎች ስም ያለአግባብ ስመ ሀብቱ ሉመዘገብ ችሎል በማለት የቤት ባለሃብት ስለሆንኩ ተጠሪዎች በአደራ በጠባቂነት የያዙትን ቤት ለቀዉ እንዱያስረክቡኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት የጠየቁበት ነዉ።ተጠሪዎች ደግሞ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት ሟች በስማቸዉ የገዙትና በስማቸዉ ተመዝግቦ የነበረና በኋላም ሲሞቱ በሕግ አግባብ ወደ ተጠሪዎች ስም ዞሮ የተመዘገበ እንጂ አመልካች በክሳቸዉ እንደገለጹት በአመልካች ገንዘብ የተገዛና በአደራ የያዝነዉ አይደለም በማለት ተከራክረዋል።የስር ፍርድ ቤት ክሱን ዉድቅ በማድረግ የወሰነዉ ቤቱ በአመልካች ገንዘብ ለአመልካች ጥቅም በሟች አቶ ታደለ መስፍን ስም የተገዛ ስለመሆኑ እና አመልካች ከተጠሪዎች የተሻለ በቤቱ ላይ የባለቤትነት መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ ከተጠሪዎች የተሻለ ማስረጃ በማቅረብ አላስረደም በማለት ነዉ።
እንደሚታወቀዉ በልዩ ሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር የፍትሐ ብሓር ክርክር መመራትና እና እልባት ማግኘት ያለበት በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ የተዘረጋዉን ሥነ ሥርዓት ተከትል ላሆን ይገባል።ይህም ያስፈለገበት ምክንያት ክርክሮች ፍትሐዊ በሆነ አግባብ እንዱታዩ ያደርጋል ተብል ታምኖበት በተዘረጋዉ ሥነ-ሥርዓት አግባብ ታይተዉ የጊዜ የገንዘብና የሰዉ ሀብት ብክነት በሚቀንስ አግባብ በቅልጥፍና ታይተዉ ፍትሐዊ እልባት እንዱያገኙ ሕጉ ያቀደዉ ዓላማ እንዱሳካ ለማድረግና የሥነ ሥርዓት ሕጉ መሰረታዊ ግብ የሆነዉን ከሥረ ነገር ሕጎች (Substantuve Laws) ወይም ከዉል የተገኙ መብትና ግዳታዎችን ማስፈጸም ይቻል ዘንድ ነዉ።በሥነ ሥርዓት ሕጉ ከተዘረጉ ሥነ ሥርዓቶች መካከል አንደ ስለ ጭብጥ አመሰራርት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 246-248 እና 251-252 የተደነገገዉ ነዉ።በዚህ አግባብ ጭብጥ መመስረት የሚያስፈልግበት ምክንያት ግራ ቀኙ በተከራከሩበት ነጥብ ላይ ብቻ ተመስርቶ አከራካሪዉን ጭብጥ ከተገቢዉ ማስረጃ ወይም ሕግ አንጻር መርምሮ የሥነ ሥርዓት ሕጉን ዓላማ እና ግብ በሚያሳካ መልኩ ፍትሐዊ ዉሳኔ መስጠት ይቻል ዘንድ ነዉ።በዚህ አግባብ ጭብጥ የሚመሰረተዉ ደግሞ ክሱን የሚሰማዉ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቀርቦ ከሆነ ዉሳኔ ከሰጠ በኋላ ክሱንና ቀርቦም ከሆነ መከላከያ መልሱን መሰረት በማድረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 241 መሰረት ተከራካሪዎችን ከመረመረ በኋላ የክሱን ይዘት፣መከላከያ መልሱን፣ በተከራካሪ ወገኖች የቀረበዉን የጽሁፍ ማስረጃ፣ ግራ ቀኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 241 ተመርምረዉ የሰጡትን መልስ እና ሕግን መሰረት በማድረግ እንደሆነ በሕጉ በቁጥር 248 ላይ የተደነገገዉ ያስገነዝባል።እንዱሁም ጭብጥ የሚመሰረተዉ በተከራካሪ ወገን የተካደዉን የሕግ ወይም የፍሬ ነገር ክርክር መሰረት በማድረግ ሲሆን ዋነኛ ዓላማዉም ለጉዲዩ ትክክለኛ ዉሳኔ መስጠት ይቻል ዘንድ ነዉ።(የሕጉ ቁጥር 246/1 እና 247 ይመለከቷል።) እንዱሁም አንድን ፍሬ ነገር ማስረጃ አቅርቦ የማስረዲት ሸክምን ከሚመለከተዉ መሰረታዊዉ መርህ (Basic Principle of Burden of Proof) መረዲት እንደሚቻለዉ አንድ አከራካሪ ፍሬ ነገር አለ ወይም የለም ብል የሚከራከር ሰዉ ፍሬ ነገሩ መኖሩን ወይም አለመኖሩን በማስረጃ የማስረዲት ሸክም(ግዳታ) አለበት። (የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 258-260 እና የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2001 ይመለከቷል)። በፍትሐ ብሓር ክርክር ማስረጃ የሚቀርበዉ ተከራካሪ ወገን በተመቸዉ ጊዜ ሁለ ሳይሆን በሥነ ሥርዓት ሕጉ በተዘረጋዉ ሥነ ሥርዓት አግባብ ነዉ።ይኸዉም ከሳሽም ሆነ ተከሳሽ የሆነ ወገን አለኝ የሚለዉንና በእጁ የሚገኘዉን ማስረጃ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 223/1 እና 234 መሰረት ዘርዝረዉና ምን እንደሚያስረዲላቸዉ ገልጸዉ እንዱሁም በእጃቸዉ የማይገኘዉንና በራሳቸዉ ማቅረብ የማይችለትን ማስረጃዎች የሚገኝበትን ቦታ ገለጸዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 145 መሰረት በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዱቀርብላቸዉ መጠየቅና ከክሱ እና ከመከላከያ መልሳቸዉ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።እንዱሁም በልዩ ሁኔታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 137 መሰረት አስቀድሞ ያልቀረበ ማስረጃ ክሱ ከመሰማቱ በፉት ክስ እስከሚሰማበት ቀን ድረስ ማቅረብ እንደሚቻል፤ እንዱሁም በከባድና በበቂ ምክንያት አስቀድሞ ማቅረብ ያልተቻለዉን ማስረጃ በፍርድ ቤቱ ፈቃደኝነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 256/1 ስር በተደነገገዉ አግባብ ማቅረብ እንደሚቻል ተደንግጓል።ከዚህ ዉጭ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 136፣249፣ 264(1 እና 2) እና 345 በደነገገዉ አግባብ ፍርድ ቤቱ አንጻራዊ እዉነታ የመፈለግ ኃላፉነቱን ለመወጣት ወይም ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት ያስችለዉ ዘንድ ፍርድ ከመስጠቱ በፉት በማንኛዉም ጊዜ ማስረጃ አስቀርቦ ወይም ምስክሮች ጠርቶ መስማት ከሚችል በስተቀር በተከራካሪ ወገኖች ማስረጃ በዘፈቀደ በማንኛዉም ጊዜ የሚቀርብበት ሥነ ሥርዓት የለም።
በያዝነዉ ጉዲይ አመልካች የስር ፍርድ ቤት ጭብጥ ሳይመሰርት ጭብጥ እንደመሰረተ አድርጎ የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት መብቴን በሚጎዲ አኳኋን ዉሳኔ ሰጥቷል በማለት አጥብቀዉ ተከራክረዋል። በመሰረቱ በፍትሐ ብሓር ፍትሕ አስተዲደር የተከራካሪ ወገኖች የመሰማት መብት የሚከበረዉ ክስ የቀረበበት ተከሳሽ መጥሪያ በአግባቡ ደርሶት አለኝ የሚለዉን መልስ በጽሁፍ በማስረጃ አስደግፍ እንዱያቀርብ በቂ ጊዜ በመስጠት ቀጥልም በሥነ ሥርዓት ሕጉ በተዘረጋዉ ሥርዓት አግባብ ክርክሩን በዲኛዉ መሪነት እንዱያሰማና ማስረጃዉ እንዱመረመርለት ወይም እንደየክርክሩ አይነት ምስክሮቹን አቅርቦ በማሰማት ክርክሩን የሚያስረዲበትን አግባብ በማመቻቸት ነዉ።ከላይ እንደተመለከተዉ አመልካች ክሱን የመሰረቱት የቤቱ ባለቤት መሆናቸዉን ገልጸዉ ተጠሪዎች በቤቱ እየኖሩበት የሚገኙት በጠባቂነት በአደራ በመያዝ እንደሆነና በመጀመሪያ ሟች አቶ ታደለ መስፍን አለአግባብ በስማቸዉ እንዲስመዘገቡት በኋላም አቶ ታደለ መስፍን ሲሞቱ የሟቹ ባለቤት በሆኑት በ1ኛ ተጠሪና በሟቹ ልጅ 2ኛ ተጠሪ ስም አለአግባብ አዛዉረዉ አስመዝግበዋልና ይልቀቁልኝ በማለት በመሆኑ ክሱ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1206 ስር የተደነገገዉን የመፊለም ክስ (petitory action) የሚመለከት ነዉ።ተጠሪዎች ደግሞ ቤቱን በዉል ገዝተዉ በስማቸዉ ያስመዘገቡት ሟች አቶ ታደለ መስፍን እንደሆኑና የእሳቸዉን ሞት ተከትል በሕግ አግባብ ተላልፍላቸዉ የቤቱ ስመ ሀብት በስማቸዉ ተመዝግቦ እንደሚገኝ እና በክሱ ላይ እንደተገለጸዉ በአደራ የያዙት እንዲልሆነ በመግለጽ ተከራክረዋል።
አመልካች በተጠሪዎች ላይ የመሰረቱት ክስ ባለቤትነትን መፊለምን የሚመለከት መሆኑን ተመልክተናል። የስር ፍርድ ቤት ይህንን የክሱን ሥረ ነገር እና የተጠሪዎችን ክርክር መሰረት በማድረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 241 በሚያዘዉ መሰረት ተከራካሪዎችን መመርመሩን ወይም የመጀመሪያዉን የክስ አሰማም ሥነ ሥርዓት ማከናወኑን እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 241 መሰረት ግራ ቀኙን መርምሮ የሰማዉንና የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክርና ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ በጉዲዩ ላይ ትክክለኛ ዉሳኔ ለመስጠት ያስችለኛል ያላቸዉን ጭብጦች መመሰርቱን ከዉሳኔዉ ግልባጭ ተገንዝበናል። የያዛቸዉ ጭብጦችም ‛ተጠሪዎች ክስ የቀረበበትን ቤት ለቀዉ ለአመልካች ለማስረከብ ይገደዲለ ወይስ አይገደደም? ይገደዲለ ከተባለ ስመ ሃብቱ በአመልካች ስም ዞሮ ሉመዘገብ ይገባል ወይስ አይገባም?“ የሚለ ናቸዉ። እነዚህ ጭብጦች የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎች መሰረት ያደረገ ከመሆኑም በተጨማሪ አመልካች ላቀረቡት የመፊለም ክስ እና በተጠሪዎች በቀረበ ክርክር ላይ ትክክለኛ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለ ስለሆኑ ጉድለት ያለባቸዉ እንዲልሆኑ ተገንዝበናል።ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤት ክስ በመስማት ለጉዲዩ ትክክለኛ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለትን ተገቢ ጭብጦች የመሰረተ በመሆኑ ከክስ አሰማምና ከጭብጥ አመሰራረት ጋር በተያያዘ የአመልካችን የእኩልነት ፣የመሰማትና ፍትህ የማግኘት መብት በሚነካ አኳኋን የተፈጸመ የክርክር አመራር ጉድለት ስለላለ አመልካች ከዚህ አኳያ ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልንም።
በተጨማሪም አመልካች ክሳቸዉን በሕግ ተቀባይነት ያለዉንና ተገቢዉን ማስረጃ በማቅረብ አላስረደም በሚል በስር ፍርድ ቤት በተደረሰበት ድምዲሜ የተፈጸመ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
አመልካች ንብረት የሚገኝበትን ሕጋዊ መንገድ ተከትለዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት ባለሀብት መሆናቸዉን ተገቢዉንና ተቀባይነት ያለዉን ማስረጃ በማቅረብ ማስረዲት ይኖርባቸዋል።በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1184 እና 1185 ስር እንደተመለከተዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት መሆን የሚቻለዉ በሕግ ወይም በዉል ወይም በኑዛዜ (በሕጋዉያን ተግባሮች/Juridical acts) መሰረት ነዉ። በዉል ወይም በኑዛዜ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነትን ለማስተላለፍ ወይም በዉል ወይም በኑዛዜ መሰረት ባለሀብት መሆን የሚቻለዉ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ላይ ማስመዝገብ ሲቻል መሆኑን በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1185 እና ከቁጥር 1553 እስከ 1646 ድረስ ከተደነገገዉ መገንዘብ ይቻላል።እንዱሁም የአንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት መሆኑን የሚያረጋግጥ የባለሃብትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በስሙ በአስተዲደር አካል የተሰጠዉ ሰዉ የዛ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት ነዉ ተብል እንደሚቆጠር በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1195/1 ስር ተደንግጓል።ይህ የሕግ ግምት ሉስተባበል የሚችል ግምት እንደሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1195/2 ላይ ተመልክቷል።
ከላይ ከተመለከተዉ አንጻር ስናይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት አስቀድሞ በሕግ ዉል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠዉ አዋዋይ ፉት ባልተደረገ(በተለምድ የመንደር ዉል በሚባለዉ) ሟች አቶ ታደለ መስፍን ስም የተገዛ በኋላም በቀን 13/04/2003ዓ/ም በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ዘንድ በተደረገ የቤት ሽያጭ ዉል ሟች አቶ ታደለ መስፍን በስማቸዉ የገዙት ቤት እንደሆነ የስር ፍርድ ቤት በማስረጃነት ከቀረቡ የዉል ሰነድች ያረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ነዉ።አመልካች ቤቱን በራሴ ገንዘብ የተገዛና በሟች ወንድሜ ስም መግዛት ስለፈለግሁ የሟቹ ስም በገዥነት በዉለ ላይ ሉጠቀስ ችሎል በማለት ተከራክረዋል።በመርህ ደረጃ ዉል መብት እና ግዳታ የሚፈጥረዉ ዉለን ባቋቋሙ ሰዎች መካከል ነዉ። በልዩ ሁኔታ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1953 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ በተመለከተዉ አግባብ አንድ ሰዉ በዉለ ላይ የተመለከተዉን መብት ላላ ሰዉ እንዱጠቀምበትና ከዉለ የሚመነጨዉንም ግዳታ እንዱወጣ ለላላ ሰዉ ጥቅም በሚል ዉል ሉዋዋል ይችላል።በዚህ አግባብ አንድን ዉል የተዋዋለ ሰዉ በዉለ የመጠቀሱ ጉዲይ የእንደራሴነት አይነት ይሆናል።ከእነዚህ ድንጋጌዎች መንፈስና ዓላማ መረዲት እንደሚቻለዉ አንድ ዉል ከተዋዋዮች ዉጭ ለሆነ ላላ ሰዉ ጥቅም የተደረገ ነዉ እንዱባል ዉለ ለጥቅሙ የተደረገለት ሰዉ ማን እንደሆነ በዉለ ላይ በግልጽ መገለጽ ይኖርበታል።ምክንያቱም በጽሁፍ የተደረገ ዉል በይዘቱ ዉለ ለጥቅሙ የተደረገለትን ሦስተኛ ወገን የማይገልጽ ከሆነ በዉለ ላይ በግልጽ ከተመለከቱት ከተዋዋዮች ሀሳብ ዉጭ በመዉጣት ተዋዋዩ ዉለን በስሙ የተዋዋለዉ ለራሱ ጥቅም ሳይሆን ለላላ ሦስተኛ ወገን ጥቅም ነዉ በማለት በዉለ በግልጽ ከተመለከተዉ ተዋዋይ ዉጭ ላላ ሰዉ ተጠቃሚ እንዱሆን በማድረግ ፍርድ ቤቶች ዉለን እንዱተረጉሙ ሕግ ስለማይፈቅድላቸዉ ነዉ።(የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1733 ይመለከቷል።)ከዚህ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ሟች አቶ ታደለ መስፍን አከራካሪዉን ቤት በገዙበት ዉል ይዘት ላይ ቤቱ የተገዛዉ ለአመልካች ጥቅም መሆኑ የሚያመላክት ነገር እንደላለ አረጋግጧል። የዉለ ይዘት አከራካሪዉ ቤት የተገዛዉ ለአመልካች ጥቅም መሆኑን የማያሳይ ከሆነ ዉለ የተደረገዉ ለአመልካች ጥቅም ነዉ የሚለዉን በምስክሮች የሚረጋገጥበት የሕግ አግባብ የለም።
ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት ሟችም ሆኑ ተጠሪዎች በጠባቂነት እየኖሩ እንደያዙ በክሳቸዉ ላይ በገለጹበት አግባብ በቤቱ ላይ ከሟች አቶ ታደለ መስፍን ወይም ከተጠሪዎች በተሻለ ሁኔታ ባለቤት ናቸዉ ተብል እንዱገመት የሚያያደርግ ማስረጃ በማቅረብ ማስረዲት ይኖርባቸዋል።አመልካች ይህንን ማድረግ የሚችለት ደግሞ ከላይ በተመለከተዉና በክሳቸዉ ላይ በገለጹት አግባብ ቤቱ የተገዛዉ ለእሳቸዉ ጥቅም መሆኑን በዉለ ማስረጃነት ማስረዲት ቢችለ ነበር።ሆኖም በዚህ አግባብ አላስረደም።ይልቁንም ዉለ የአመልካችን ክርክር የሚደግፍ ይዘት የላለዉ ከመሆኑም በተጨማሪ ሟች አቶ ታደለ መስፍን ቤቱን በዉል በስማቸዉ ገዝተዉ በፍ/ብ/ሕግ ከቁጥር 1553 እስከ 1646 ድረስ ስመ ሀብቱን በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ አስመዝግበዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1195 መሰረት የባለሃብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት በስማቸዉ ወስደዉ የያዙት እንደሆነና አቶ ታደለ መስፍን ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላም በቤተሰብ እና በዉርስ ሕጋግት መሰረት የቤቱ ስመ ሀብት ወደ ተጠሪዎች ስም ዞሮ እንደተመዘገበ የስር ፍርድ ቤት የቀረቡለትን ማስረጃዎች መርምሮና መዝኖ አረጋግጧል።ይህም ቤቱ በሟች አቶ ታደለ መስፍን ተይዞ የነበረዉም ሆነ ተጠሪዎች ቤቱን የያዙት በአመልካች ክስ ላይ እንደተገለጸዉ በጠባቂነት ሳይሆን የቤቱ ባለሀብት በመሆናቸዉ ምክንያት እንደሆነ የሚያስቆጥር ነዉ።በዚህ አግባብ ከክሱና ከመልሱ ጋር በግራ ቀኙ በቀረቡ ማስረጃዎች እነዚህ ፍሬ ነገሮች እስከተረጋገጡ ድረስ የሥር ፍርድ ቤት ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በያዛቸዉ ጭብጦች ላይ ትክክለኛ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉ በመሆኑና ከዚህ ዉጭ ምስክሮችን በመስማት ሉረጋገጥ የሚገባ የፍሬ ነገር ጭብጥ የላለ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ምስክሮችን ሳይሰማ በጉዲዩ ላይ ዉሳኔ መስጠቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 255 ስር የተደነገገዉን መሰረት ያደረገ የዉሳኔ አሰጣጥ ነዉ ከሚባል በስተቀር የክርክር አመራር ጉድለት ፈጽሟል የሚያስብል አይደለም።
ሲጠቃለል የስር ፍርድ ቤት በሥነ ሥርዓት ሕጉ አግባብ የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት በጉዲዩ ላይ ዉሳኔ ለመስጠት አስፈላጊ የሆኑ ጭብጦች በመመስረት ክርክሩን እንደመራ አረጋግጠናል። ግራ ቀኙን ያከራከሩትን ጭብጦች ከማስረጃ እና ከሕግ አንጻር አገናዝቦ ዉሳኔ ከመስጠት አንጻርም አመልካች ባቀረቡት ክስ መሰረት አከራካሪዉ ቤት ለእሳቸዉ ጥቅም የተገዛ እና የቤቱ ባለሃብት መሆናቸዉን እንዱሁም ተጠሪዎች ቤቱን የባለቤትነት መብት ሳይኖራቸዉ በጠባቂነት ይዘዉ አንለቅም ማለታቸዉን በማስረጃ አለማስረዲታቸዉን የቀረቡለትን ማስረጃዎች የመመርመርና የመመዘን ሥልጣኑን በአግባቡ ተጠቅሞና ተገቢዉን ሕግ መሰረት በማድረግ የሥር ፍርድ ቤት አረጋግጧል።እንዱሁም የአከራካሪዉ ቤት ባለሀብቶች ተጠሪዎች እንደሆኑ የሥር ፍርድ ቤት የቀረቡለትን ማስረጃዎች መርምሮና መዝኖ አረጋግጧል።ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት ተጠሪዎች ባለሀብት የሆኑበት እንደሆነ በማረጋገጥ ተጠሪዎች ቤቱን ሉለቁ አይገባም በማለት የአመልካችን ክስ ዉድቅ በማድረግ በሰጠዉ ዉሳኔና በዚህ ዉሳኔ ላይ የቀረበዉን ይግባኝ ይግባኝ ሰሚዉ ችልት በመሰረዙ ከክርክር አመራር ረገድም ሆነ ከሕግ አተገባበር አኳያ በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 23/02/2013ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር በመ/ ላይ በቀን 18/06/2013ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንተዋል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ብለናል።
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.