ያለፍርድ ቤት ፈቃድ የህፃን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ የሚደረግ ውል ህጋዊ ውጤት የላለው ፍቅሩ መገርሳ እና እነ ሚሉዮን ተካ (2 ሰዎች)
No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዚያ 28 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ፍቅሩ መገርሳ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቤት ሽያጭ ዉል ለማስፈረስ የተጠየቀ ዲኝነት የሚመለከት ነዉ። አመልካች በፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁን ተጠሪዎች ላይ በመሰረተዉ ክስ በቡራዩ ገፈርሳ ቀበላ በቀድሞ የቤት ቁጥር 665 በኢዱሱ የቤት ቁጥር 4765 የሚታወቅ በ100.8ካሬ ሜትር ስፊት ቦታ ላይ የተሰራ አራት ክፍል ያለዉን አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰዉን መኖሪያ ቤት ከአባቴ በዉርስ ተላልፍልኛል።ይህንን ቤት ተጠሪዎች አታለዉኝ በቀን 24/10/2007ዓ/ም እድሜዬ 14 ዓመት ሆኖ እያለ በዉክልና ሥልጣን ቁጥር ቅ2/6107/13/07 ለ2ኛ ተጠሪ እንዱሰጣት በማድረግ 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ በብር 40,000.00(አርባ ሺህ ብር) ሽጣለታለች። በዉለ ላይ ደግሞ በብር 300,000.00 እንደተሸጠ ተደርጎ ተጽፎል።በወቅቱ እድሜዬ 14 ዓመት ስለነበር ዉል ለማድረግ በምችለበት እድሜ ላይ ስላልነበርኩ በኦሮሚያ ክልል ቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 83/1996 አንቀጽ 233/3 እና 316 ዉለ ፈራሽ ነዉ።ቤቱ ተሽጦ የተገኘዉ ገንዘብም ለእኔ ጥቅም የዋለ አይደለም።ስለሆነም 2ኛ ተጠሪ የፍርድ ቤት ፈቃድ ሳታገኝ ንብረቴን መሸጧ መብቴን የጎዲ በመሆኑ ዉለ ፈርሶ ቤቴን እንዱያስረክቡኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
1ኛ ተጠሪ ለክሱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም በሰጠዉ መልስ ዉለ የተፈጸመዉ በቀን 24/10/2007ዓ/ም ነዉ።የቤቱ ሽያጭ ዉል ሲፈጸም ቤቱ አንድ ክፍል የነበረ ነዉ።በአሁኑ ወቅት ብር 250,000.00 ወጪ አዉጥቼ አራት ክፍልችን ሰርቻለሁ።አመልካች በ1989ዓ/ም ስለተወለደ በ2007 ዓ/ም የቤቱ ሽያጭ ዉል ሲፈጸም የአመልካች እድሜ 18 ዓመት ነበር።ይህንንም የቀበላ መታወቂያ እንዱሰጠዉ ከጠየቀበት፣ ቁጥር 4630/07 ከሆነዉ መታወቂያዉና ከመዝገቡ ዉስጥ ከሚገኘዉ ማስረጃ ማረጋገጥ ይቻላል።ይህንን መታወቂያዉን ይዞ የዉክልና ሥልጣን በፋዳራል ሰነድች ማረጋገጫ ጽ/ቤት ቀርቦ ለ2ኛዋ ተጠሪ ሰጥቷታል።2ኛ ተጠሪም በዚህ ዉክልና በመጠቀም ቤቱን ሽጣልኛለች።ስለዚህ አመልካች እድሜዬ 18 ዓመት ሳይሞላኝ ነዉ የሸጥኩት በማለት ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም።አመልካች ይህንን ክርክሩን በ2ኛ ተጠሪ ላይ እንጂ በ1ኛ ተጠሪ ላይ መከራከሪያ ሉያደርግ አይችልም።አመልካች ሆነ ብል ቤቱን መልሶ ለመዉሰድ እድሜዉ 18 ዓመት ሳይሞላ የተደረገ ለማስመሰል ሥልጣን በላለዉ አካል የተሰጠ ማስረጃ ስላቀረበ ተቀባይነት ሉሰጠዉ አይገባም።አመልካች ቤቱ የተሸጠዉ በብር 40,000.00 እንጂ በብር 300,000.00 አይደለም በማለት ያቀረበዉ ክርክር በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 መሰረት ተቀባይነት የለዉም።ቤቱን ከገዛሁ በኋላም ብር 250,000.00 ወጪ አዉጥቼ ተጨማሪ ግንባታ ስለፈጸምኩ ክሱ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።
2ኛ ተጠሪም ለክሱ በሰጠችዉ መልስ እኔ የአመልካች እናቱ ሆኜ አመልካች በዉርስ ያገኘዉን ቤት በማስተዲደር ላይ እያለሁ በገጠመኝ ችግር ምክንያት ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ተማክሬ አመልካች በሰጠኝ የዉክልና ሥልጣን ቤቱን በብር 40,000.00 ለ1ኛ ተጠሪ ሽጨለታለሁ።1ኛ ተጠሪ የአመልካች እድሜ 14 ዓመት እንደሆነ እያወቀ ያጋጠመኝን ማህበራዊ ችግር ተገን አድርጎ አመልካች ለእኔ ዉክልና እንዱሰጠኝ በማድረግ ዉለ እንዱፈጸም አድርጓል።1ኛ ተጠሪ የማይገባዉን ብልጽግና ለማግኘትና የአመልካችንና የ2ኛ ተጠሪን መብት ለመጣስ ብል ቤቱ በብር 40,000.00 ተሽጦ እያለ በብር 300,000.00 እንደተሸጠ አድርጎ አሳስቶ ጽፍ አስፈርሞኛል። ስለሆነም አመልካችን ለመጉዲት ብዬ የፈጸምኩት ዉል ባለመሆኑ ክሱ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክራለች።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮች በመስማት እንዱሁም የአመልካች እድሜ ተመርምሮ ማስረጃ እንዱቀርብ በማድረግ የቀረቡለትን ማስረጃዎች በመመርመር በቀን 18/02/2012 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ የዉክልና ሥልጣን በሰጠበትና የቤት ሽያጭ ዉል በተደረገበት ጊዜ የአመልካች እድሜ 16 ዓመት እንደነበር በማስረጃ ተረጋግጧል።በኦሮሚያ ክልል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 233/3 መሰረት እድሜዉ 18 ዓመት ያልሞላዉ ሰዉ የሚፈጽመዉ ማንኛዉም ዉል በሕግ ፉት የማይጸና ነዉ ሲል በመደንገጉ አመልካች እድሜዉ 16 ዓመት ላይ ሆኖ ለ2ኛ ተጠሪ የሰጠዉ የዉክልና ሥልጣን የሕግ ድጋፍ ያለዉ አይደለም።ነገር ግን 2ኛ ተጠሪ አመልካች በዉርስ ያገኘዉን ይህንን ቤት ስታስተዲድር እንደነበር ስለተረጋገጠ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 237/1 መሰረት አባት በህይወት በላለበት ሁኔታ እድሜያቸዉ ለአቅመ አዲም/ሄይዋን ላልደረሱ ልጆች አሳዲጊ ሞግዚት/አስተዲዲሪ እንደምትሆን በመደንገጉ 2ኛ ተጠሪ ለምታሳድገዉ አመልካች ጥቅም ለማዋል ማንኛዉንም ድርጊት መፈጸም ትችላለች።ቤቱ የተሸጠዉ የአመልካች እድሜ 18 ዓመት ሳይሆን 18 እንደሞላዉ በማድረግ መታወቂያ በማዉጣትና ለ2ኛ ተጠሪ ዉክልና እንዱሰጥ የተደረገዉ ሆን ተብል አመልካችን ለመጉዲት ተብል ሳይሆን ቤቱ ተሽጦ በተገኘዉ ገንዘብ ላይ ላላ ገንዘብ በመጨመር ለአመልካች ቤት የገዛችለት መሆኑ በምስክሮች ቃል ተረጋግጧል።የ1ኛ ተጠሪ ምስክሮችም 1ኛ ተጠሪ ዉለን አመልካችን ለመጉዲት ብል እንዲልፈጸመ መስክረዋል።እንዱሁም በ2ኛ ተጠሪ የቀረቡ ምስክሮች ያስረደት ቤቱ ሉሸጥ የቻለዉ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን የአካባቢዉ ሰዎች ስላስቸገሯት ቤቱ ወዲለበት አካባቢ ሄዲ በመቆጣጠር ለማስተዲደር ባለመቻሎ ምክንያት ነዉ። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የተቻለዉ ቤቱ የተሸጠዉ ለአመልካች ጥቅም ተብል እንደሆነ ነዉ።የኦሮሚያ ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 294 ላይ ሞግዚት የሚንቀሳቀስ ንብረት ሲሸጥ የፍርድ ቤት ፈቃድ ማግኘት እንዲለበት የደነገገ ቢሆንም ቋሚ ንብረት ሽያጭ በተመለከተ የደነገገዉ ነገር የለም።የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ ለሕጻኑ ጥቅም የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጥ እንደሚቻል ትርጉም ሰጥቷል።በሰ/መ/ ላይ በኦሮሚያ ሕግ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ባይደነገገም በፋዳራል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 306 እና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2207/1 ስር የተደነገገዉን የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጥ እንደሚቻል ትርጉም ሰጥቷል።2ኛ ተጠሪ ቤቱን ሉሸጡ የቻለት ለአመልካች ጥቅም በማለት በመሆኑ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉለ ሉፈርስ አይገባም በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮና በስር ፍርድ ቤት የቀረቡትን ማስረጃዎችን መዝኖ በቀን 14/05/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን የሸጠችዉ ባላት አመልካችን የማሳደግ ሥልጣን ቢሆንም 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች ጥቅም የዋለችዉ ነገር የለም።ዉለ ሲደረግ የአመልካች እድሜ 18 ዓመት ስላልሞላዉ በፍርድ ቤት ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ከልጁ ጋር ማንኛዉንም ዉል መፈጸም እንደማይቻል በኦሮሚያ ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 306/1 ስር በመደንገጉ አመልካች ለ2ኛ ተጠሪ ዉክልና በሰጠበት ጊዜ እድሜዉ ለአቅመ አዲም እንዲልደረሰ 1ኛ ተጠሪ እያወቀ አመልካችን በማታለል ቤቱን መግዛቱ ተረጋግጧል።ስለሆነም ተጠሪዎች የአመልካች እድሜ ለአቅመ አዲም አለመድረሱን እያወቁ በክፈ ልቦና አታለዉ ዉክልና እንዱሰጥ በማድረግ የፈጸሙት ዉል በመሆኑና ከሽያጩ የተገኘዉም ገንዘብ ለአመልካች ጥቅም ስላልዋለ ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1704/1 እና 1808/1 መሰረት እንዱፈርስ በመወሰን የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ ሽሯል።እንዱሁም 1ኛ ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች እንዱያስረክብና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1815/1 መሰረት አስቀድሞ ወደነበሩበት እንዱመለሱ ወስኗል።
በመቀጠል 1ኛ ተጠሪ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አቤቱታ አቅርቦ ችልቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 15/07/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የግራ ቀኙ ምስክሮች ቃል ሲመዘን 1ኛ ተጠሪ ቤቱን የገዛዉ ዉክልና ከወሰደችዉ 2ኛ ተጠሪ ላይ ነዉ እንጂ እድሜዉ ለአቅመ አዲም ያደረሰዉ ልጅ አሳዲጊና የንብረት አስተዲዲሪ ላይ ነዉ የሚል አይደለም።የተረጋገጠዉ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን የገዙት ዉክልና ካላት 2ኛ ተጠሪ ላይ ነዉ።በመሆኑም አመልካች እድሜዉ ለአቅመ አዲም ደርሷል ወይስ አልደረሰም እንዱሁም ዉክልና መስጠት ይችል ነበር ወይ በሚል የሚጣራበት ምክንያት የለም።ይህ ቢሆን እንኳን የተሸጠዉ ቤት ለአመልካች ጥቅም እንደዋለ ከግራ ቀኙ ምስክሮች ቃል መረዲት ስለተቻለና ቤቱ ከተሸጠ በኋላ በቤቱ ላይ መሰረታዊ ለዉጥ መደረጉን መገንዘብ ተችሎል።ከዚህ በተጨማሪ ቤቱ የተሸጠበት ዋጋ መረጋገጥ ያለበት በጽሁፍ ከተደረገዉ ዉል ላይ በመሆኑ በብር 300,000.00 እንደተሸጠ ተረጋግጧል።በአጠቃላይ ዉልን የሚያስፈርስ ምክንያት ሳይኖር ዉለ እንዱፈርስ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ አጽንቷል። አመልካች በቀን 26/12/2012 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ በዚህ መልኩ በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
አመልካች በዉርስ ያገኘሁት ቤት ለ1ኛ ተጠሪ በተሸጠበት ጊዜ እና አመልካች ለ2ኛ ተጠሪ የዉክልና ሥልጣን በሰጠሁበት በቀን 24/01/2007ዓ/ም እድሜዬ ለአቅመ አዲም እንዲልደረሰ ባቀረብኩት ማስረጃና የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍሬንሲክ እንዱመረመር አስደርጎ አረጋግጧል።ለአቅመ አዲም ያልደረሰ ህጻን ምንም አይነት ዉል ማድረግ እንደማይችልና ዉል አድርጎ ከሆነም ዉለ ፍርስ እንደሆነ በኦሮሚያ ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 233/1፣316 እና 321/1 ስር በግልጽ ተደንግጓል።ስለሆነም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት 1ኛ ተጠሪ ቤቱን የገዛዉ ልዩ ዉክልና ካላት 2ኛ ተጠሪ ላይ ስለሆነ ዉለ ሉፈርስ አይገባም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።1ኛ ተጠሪ ዉልን በቅን ልቦን የፈጸምኩት ነዉ የሚል ክርክር በግልጽ አላነሳም።ይልቁንም አመልካች ለስር ፍርድ ቤት ባቀረብኩት ማስረጃ ዉለ በቅን ልቦና እንዲልተፈጸመ አስረድቻለሁ።አመልካች ይህንን ቤት ለማግኘት በአቶ አየለ ባሻ ተወክዬ በምእራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስከራከር 1ኛ ተጠሪ እህቴን ቅድስት መገርሳን ወክል ሲከራከር ስለነበር ቤተሰብ ስለሆነ እድሜዬ ለአቅመ አዲም እንዲልደረሰ እንደሚያዉቅ ለስር ፍርድ ቤት በቀን 30/09/2000ዓ/ም የተጻፈ ቃለ ጉባኤ አቅርቤ አስረድቻለሁ።2ኛ ተጠሪ ቤቱን አከራይተሽ እንዲትጠቀሚ የአካባቢዉ ደርዬዎች ያስቸግሩሻልና ሽጭልኝ በማለት 1ኛ ተጠሪ 2ኛ ተጠሪን እንደጠየቃት እና አመልካች ለአቅመ አዲም ሳልደርስ እንደ ደረስኩ ተደርጎ መታወቂያ እንዱወጣልኝና ለ2ኛ ተጠሪ ዉክልና እንዱሰጥ 1ኛ ተጠሪ በራሱ መኪና አዱስ አበባ ኳስ ሜዲ አካባቢ ወደሚገኘዉ ዉልና ማስረጃ ወስደዉኝ አድሜዉ ለአቅመ አዲም አልደረሰም በሚል እንዲባረሯቸዉና መሳለሚያ አካባቢ ወደአለዉ ላላ ዉልና ማስረጃ መስሪያ ቤት ሄደን ትልቅ ጃኬት አልብሰዉኝ እንዱሁም ወደ ዉስጥ ገብቶ አነጋግሮ ወጥቶ እንዲስፈረመኝ በመግለጽ በመመስከራቸዉ 1ኛ ተጠሪ ቅን ልቦና እንዲልነበረዉ ተረጋግጧል።ዉለ ሲደረግ የአመልካች እድሜ ለአቅመ አዲም ደርሶ ቢሆን ኖሮ በቀጥታ ከእኔ ጋር በመዋዋል ዉለን መፈጸም ስለሚቻል እኔ ዉክልና እንዱሰጥ ማድረግ አይጠበቅበትም ነበር።ቤቱም የተሸጠዉ በብር 40,000.00 እንጂ በብር 300,000.00 እንዲልሆነ በማስረጃ ተረጋግጧል። ከሽያጩ የተገኘዉን ገንዘብ 2ኛ ተጠሪ ከማባከኗ በስተቀር ለእኔ ጥቅም አላዋለችም።ለእኔ ጥቅም ያዋለች ስለመሆኑም የቀረበ ማስረጃ የለም።በመሆኑም የአመልካች ፈቃድ የተገኘዉ እድሜዬ ለአቅመ አዲም ባልደረሰበት በመሆኑ ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1710 መሰረት ሉፈርስ ይገባል ተብል የተሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ ሆኖ እያለ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ይህንን ዉሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስተት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት የተሸጠዉ አመልካች አቅመ አዲም ሳይደርስ ለ2ኛ ተጠሪ በሰጠዉ ዉክልና ሥልጣን ሆኖ እያለ የቤት ሽያጭ ዉለ ሕጋዊ ነዉ ተብል የተወሰነበትን አግባብ ከኦሮሚያ ክልልና ከፋዳራል ቤተሰብ ሕግጋት ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በተናጠል የተጻፈ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
1ኛ ተጠሪ በቀን 21/05/2012ዓ/ም በተጻፈ መልሱ በቀን 24/10/2007ዓ/ም በተደረገ ዉል ንብረትነቱ የአሁን አመልካች የሆነን ቤት ሞግዚቱና አሳዲጊ እናቱ 2ኛ ተጠሪ በነበራት የዉክልና ሥልጣን ሶስት ምስክሮች ይዛ ቀርባ በብር 300,000.00 ሽጣልኛለች። ከሽያጩ በተገኘዉም ገንዘብ 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች በስሙ ወዱያዉኑ በሆለታ ከተማ ዉስጥ ሳዲሞ በሚባል ቀበላ ዉስጥ መኖሪያ ቤት ገዝታለት አመልካች እስካሁን በዚህ ቤት እየተጠቀመ ሲለሚገኝ በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት ገንዘቡ ለአመልካች ጥቅም ስለዋለ ዉለ ሉፈርስ አይገባም ተብል በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም። ለአመልካች ቤቱን በዉርስ ተከራክሮ ያገኘለት አቶ አየለ ባሳ ምስክር ሆኖ ቀርቦ ሽያጩ ያለምንም ማታለል እንደተፈጸመና ለአመልካች ቤት እንደተገዛለት መስክሯል።እንዱሁም 1ኛ ተጠሪ ብር 250,000.00 የሚጠጋ ወጪ አዉጥቼ አስፊፍቼ ስርቼ እየተጠቀምኩ እንደሚገኝ አስረድቻለሁ።አመልካች በሽያጩ ገንዘብ ቤት ተገዝቶለታል በሚል በ1ኛ ተጠሪ የቀረበዉን ክርክር ክድ አልተከራከረም።አመልካች ክሱን ያቀረበዉ ቤቱን ከገዛሁ በኋላ አስፊፍቼ ስለሰራሁ ትልቅ ዋጋ ያወጣል በሚል በቁጭት በመነሳሳት እንጂ በቅን ልቦና ዉጭ የፈጸምኩት ነገር ስላለ አይደለም።ብር 250,000.00 ወጪ አዉጥቼ ተጨማሪ ሶስት ክፍል ስለሰራሁ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1815/1 መሰረት ወደነበርንበት ቦታ መመለስ የማይቻል ሆኗል።ስለሆነም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ዉለ ሉፈርስ አይገባም ብል የወሰነዉ ሕግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ይጽናልኝ በማለት ተከራክሯል።
2ኛ ተጠሪ በቀን 21/05/2013ዓ/ም በተጻፈ መልሷ 1ኛ ተጠሪ ቤቴን ጠያይቆ መጥቶ ደርዬዎች ስለሚያስቸግሩሽ ሽጭልኝ በማለት በማባበል እንዱሸጥለት አድርጓል።ለአቅመ አዲም ያልደረሰ ልጅ ቤት መሸጥ እንደማይችልና እኔም በእናትነቴ ብቻ ቤቱን መሸጥ እንደማልችል ስላወቀ 1ኛ ተጠሪ እኔን በማታለል ልጄ ምንም በማያወቅበት እድሜ ላይ እያለ ዉክልና እንዱሰጠኝ አድርጎ በሕጋዊ መንገድ እንደገዛ በማስመሰል ያደረገዉ ዉል ነዉ።ቤቱን በብር 300,000.00 እንደገዛ አስመስል አስፈረመኝ እንጂ ቤቱን የገዛዉ በብር 40,000.00 ነዉ።ቋሚ ንብረት ለመሸጥ እናት መሆነ ብቻ በቂ አይደለም።ስለሆነም በአመልካች አቤቱታ ላይ የተገለጸዉ ሁለ እዉነት ስለሆነ በጠየቀዉ መሰረት ቢወሰንለት አልቃወመም በማለት መልሷን ሰጥታለች።አመልካችም የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት የያዘዉን ማስቀረቢያ ነጥብ ከግምት በማስገባት በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ከኦሮሚያ ክልል ቤተሰብ ሕግ እና ከላልች አግባብነት ካላቸዉ ሕግጋት ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረተዉ በዉርስ ያገኘዉን በክሱ የተጠቀሰዉን ቤት 2ኛ ተጠሪ ሞግዚቱ ሆና ስታስተዲድር በነበረችበት ጊዜ ተጠሪዎች እድሜዬ ለአካለመጠን እንዲልደረስኩ እያወቁ የዉክልና ሥልጣን ለ2ኛ ተጠሪ እንድሰጥ በማድረግ ተጠሪዎች በፈጸሙት የሽያጭ ዉል 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ቤቴን ከሕግ ዉጭ በሆነ አኳኋን ለ1ኛ ተጠሪ ስላስተላለፈችና ከሽያጩም የተገኘዉ ገንዘብ ለእኔ ጥቅም ስላልዋለ ዉለ ፈርሶ ቤቱን እንዱያስረክቡኝ ይወሰንልኝ የሚል ዲኝነት በመጠየቅ ነዉ። 1ኛ ተጠሪ አመልካች ለ2ኛ ተጠሪ ዉክልና ሲሰጥና የቤት ሽያጭ ዉል በተደረገበት ጊዜ በ2007ዓ/ም የአመልካች እድሜ 18 አመት ሆኖታል፤2ኛ ተጠሪ ከአመልካች ባገኘችዉ የዉክልና ሥልጣን በመጠቀም በብር 300,000.00 ሽጣልኝ ከብር 250,000.00 ብር በላይ ወጪ አዉጥቼ ተጨማሪ ክፍል ቤቶችን ስለገነባሁ ዉለ ወደማይፈርስበት ደረጃ ላይ ስለደረሰ እና የቤቱ ዋጋ ጨምሯል በሚል ፍላጎት የቀረበ ክስ ስለሆነ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።2ኛ ተጠሪ ደግሞ አመልካች ዉክልና በሰጣት ጊዜ የአመልካች እድሜ 14 ዓመት እንደነበርና በነበራት ማኅበራዊ ችግር ምክንያት 1ኛ ተጠሪ ቤቱን እንድትሸጥለት ጠይቆ ቤቱን በብር 40,000.00 ብቻ ገዝቶ እያለ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት አስቦ ቤቱ በብር 300,000.00 እንደተሸጠ አድርጎ የተፈጸመ የቤት ሽያጭ ዉል እንደሆነ በመግለጽ ተከራክራለች። አመልካችም ቤቱ የተሸጠዉ በብር 40,000.00 ሆኖ እያለ በብር 300,000.00 እንደተሸጠ ተደርጎ በዉለ ተጠቅሷል በማለት ተከራክራል።ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ዲኝነት ሥልጣን ያየዉ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ ያየዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ለሞግዚቱ ለ2ኛ ተጠሪ የዉክልና ሥልጣን በሰጠበት ጊዜም ሆነ ይህንን የዉክልና ሥልጣን በመጠቀም አመልካች በዉርስ ያገኘዉን ቤት 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ በሸጠችበት በ2007 ዓ/ም አመልካች እድሜዉ ለአካለመጠን እንዲልደረሰ ወይም እድሜዉ 16 ዓመት እንደነበር በሳይንሳዊ ዘዳ በምርመራ ያረጋገጡት ፍሬ ነገር ነዉ።ከግራ ቀኙ ክርክር እና በማስረጃ ከተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር በመነሳት የዚህን ችልት ዉሳኔ የሚሻዉ ጭብጥ አመልካች እድሜዉ ለአካለመጠን ሳይደርስ ሞግዚቱ ለሆነችዉ 2ኛ ተጠሪ እንዱሰጥ በተደረገዉ የዉክልና ሥልጣን በዉርስ ያገኘዉን ቤት ለ1ኛ ተጠሪ በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገዉ ዉል ሉፈርስ አይገባም ተብል በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመወሰኑ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን የሚመለከት ነዉ።
ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉል የተላለፈዉ ቤት የሚገኘዉ እና ተዋዋዮች በተለይም አመልካች ዉለ በተደረገበት ጊዜ ሲኖር የነበረዉ በኦሮሚያ ክልል ዉስጥ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ በዋናነት ተፈጻሚነት ያለዉ የኦሮሚያ ክልል የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 83/1999 ሲሆን፣እንደአግባብነታቸዉ በፍትሐ ብሓር ሕግ ስለዉልና ስለዉክልና የተደነገጉ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ሉሆኑ ይችላለ።
በኦሮሚያ ክልል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 316 ስር አካለመጠን ያልደረሰ ልጅ ከሥልጣኑ በላይ የሚፈጽማቸዉ ሕጋዊ ድርጊቶች ሁለ ፈራሽ እንደሆኑ ተደንግጓል።ከላይ እንደተመለከተዉ አመልካች ለሞግዚቱ የዉክልና ሥልጣን በሰጠበት ጊዜ በ2007ዓ/ም እድሜዉ ለአካለመጠን እንዲልደረሰ ወይም እድሜዉ 16 ዓመት እንደነበር በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።እንደሚታወቀዉ ዉክልና ዉል በመሆኑና አመልካች የሰጠዉም የዉክልና ሥልጣን ግዙፍ የሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሆነዉን መኖሪያ ቤቱን 2ኛ ተጠሪ በሽያጭ ማስተላለፍ ትችል ዘንድ ሥልጣን የሚሰጣት በመሆኑ ዉክልና የተሰጠበት ጉዲይ ለአመልካች እንደእለት ጉዲይ(Acts of everyday life) ሉቆጠር የሚችል አይደለም።በመሆኑም በተሻሻለዉ የኦሮሚያ ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 316 እና 310 ጣምራ ንባብ መሰረት አመልካች የመኖሪያ ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል የዉክልና ሥልጣን ለ2ኛ ተጠሪ በሰጠበት ጊዜ እድሜዉ ለአካለመጠን ያልደረሰ በመሆኑ ያለፍርድ ቤት ፈቃድ የዉክልና ሥልጣን መስጠት ስለማይችል ለ2ኛ ተጠሪ የሰጠዉ የዉክልና ሥልጣን ፈራሽ ወይም ሕጋዊ ዉጤት የላለዉ (shall be of no effect) ነዉ።
በልላ በኩል ከክርክሩ እንደተረዲነዉ የአመልካች አባት መሞቱን ተከትል 2ኛ ተጠሪ በእናትነቷ የአመልካች አሳዲሪና ሞግዚት ሆኖ ለክሱ መነሻ በሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉል የተሸጠዉን ቤት ስታስተዲድር ቆይታለች።2ኛ ተጠሪ በዚህ አግባብ የአመልካች አሳዲሪና ሞግዚት በመሆን የአመልካችን ንብረት የማስተዲደር መብት እና ሥልጣን እንዲላት በክልለ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 237፣286 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።2ኛ ተጠሪ የአመልካችን መኖሪያ ቤት ለ1ኛ ተጠሪ በሽያጭ ያስተላለፈችዉ በዉክልና ሥልጣን ነዉ ወይስ በሞግዚትነት ሥልጣን ነዉ የሚለዉን ቀጥለን የምንመለከተዉ ሆኖ 2ኛ ተጠሪ የሞግዚትነት ሥልጣኗን ተግባራዊ ማድረግ ያለባት የሕጻኑን(የአመልካችን) ሀብትና ንብረት ነክ ጥቅሞቹን ሉያስከብር በሚችል መልኩ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ በክልለ ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 286/2 ስር ከተደነገገዉ መገንዘብ ይቻላል። ሞግዚት የሞግዚትነት ሥልጣኑን በሕጉ አግባብ ተግባራዊ አድርጓል ወይስ አላደረገም የሚለዉን ጉዲይ በተመለከተ መርምረዉ ዉሳኔ የሚሰጡ አካላት ፍርድ ቤትን ጨምሮ የሚሰጡት ዉሳኔ የሕጻኑን ደህንነትና መልካም አስተዲደግ ወይም ጥቅሙን(best interest of child) የሚያስቀድም መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።(የኢፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት እና የኦሮሚያ ክልል የተሻሻለዉ ሕገ መንግስት አንቀጽ 36/2 እና የኦሮሚያ ክልል የተሻሻለዉ ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 286/2 እና 235 ይመለከቷል።) 2ኛ ተጠሪ የአመልካችን መኖሪያ ቤት ለ1ኛ ተጠሪ በሽያጭ ያስተላለፈችዉ በዉክልና ሥልጣን ነዉ ወይስ በሞግዚትነት ሥልጣን የሚለዉን በስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ ከተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር አንጻር መርምረናል።በክልለ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 322 ስር እንደተደነገገዉ 2ኛ ተጠሪ በኃላፉነት ከማይጠየቁበት ምክንያቶች ዉስጥ አንደ ለአመልካች ጥቅም ለፈጸመችዉ ሕጋዊ ተግባራት ነዉ።ሕጋዊ ተግባራት የሚባለት ደግሞ በሕግ የተጣለ ግዳታዎችንና ስርዓቶችን በመጠበቅ የተፈጸሙ ተግባራት እና ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ ናቸዉ የተባለትን ተግባራት አለመፈጸም ነዉ። 2ኛ ተጠሪ የአመልካች ሞግዚትና አሳዲሪ በመሆኗ ለአመልካች መልካም አስተዲደግ ይረዲ ዘንድ የአመልካችን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ የአመልካችን ሀብት እና ንብረት የምትጠቀምበትን መንገድ መወሰን ትችላለች።
ይህም ማለት ለአመልካች እድገት ንብረት መሸጥ የግድ ሲል በሕግ የተጣለ ግዳታዎችን በመወጣት በሕግ የተዘረጋዉን ሥርዓት በመከተል ንብረቱን በመሸጥ ለአመልካች ጥቅም ማዋል ትችላለች ማለት ነዉ።ከእዚህ ጋር ተያይዞ 2ኛ ተጠሪ እንደሞግዚት በፍርድ ቤት ፈቃድና የፍርድ ቤት ፈቃድ መጠየቅ ሳያስፈልጋት በሽያጭ ልታስተላለፍ የምትችለዉ ንብረት አይነቶች ምንድንናቸዉ የሚለዉን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል።በክልለ ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 294 ላይ በድንጋጌዉ ርእስና በይዘቱ እንደተመለከተዉ ሞግዚት መሸጥ የሚችለዉ የሚንቀሳቀሱ ግዙፍ የሕጻኑን ንብረቶች ፣አክሲዮኖችንና የገንዘብ ሰነድች ተብለዉ የተጠቀሱትን ንብረቶችን እንደሆነ በግልጽ ተዘርዝሮ ተመልክቷል።ከዚህ ድንጋጌ መንፈስና ይዘት መረዲት እንደሚቻለዉ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ለመሸጥ ሞግዚት የፍርድ ቤትን ፈቃድ አስቀድሞ ማግኘት እንዲበት ሕጉ አያስገድደዉም።
በልላ በኩል ከተዘረዘሩት ንብረቶች መካከል የማይንቀሳቀስ ንብረት አለመካተቱ ሲታይ በሕጉ በግልጽ ሞግዚት የማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሸጥ አስቀድሞ የሚመለከተዉን ፍርድ ቤት ማስፈቀድ እንዲለበት ባይደነገግም የማይንቀሳቀስ ንብረት በአገራችን ካለዉ ከፍተኛ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ፊይዲ አንጻር ሞግዚት ፍርድ ቤትን ማስፈቀድ ሳያስፈልገዉ በፈለገዉ ጊዜ የሕጻኑን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ ይችላል የሚል አቋም በሕግ አዉጪዉ ተይዟል ብል ለመደምደም የሚቻል አይደለም።በመሆኑም ሞግዚት ለሕጻኑ አስተዲደግ የሕጻኑን የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጥ የግድ እንደሚል ካመነ በሽያጭ ከማስተላለፈ በፉት የፍርድ ቤት ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል ማለት ነዉ።ከዚህም በተጨማሪ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ ቁ.46490 መጋቢት 21 ቀን 2002 ዓ/ም እና በሰ/መ/ እና መስከረም 24 ቀን 2008ዓ/ም በሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሞግዚት የማይንቀሳቀስ ንብረት ለልጆች መልካም አስተዲደግና ጥቅም የሸጠ መሆኑ ከተረጋገጠ የሽያጭ ውል ለማፍረስ የሚያስችል በቂ ምክንያት አይደለም በማለት ወስኗል። ይህ ማለት የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭን በተመለከተ የሽያጭ ውለ ሉፈርስ አይገባም የሚል ድምዲሜ ላይ መድረስ የሚቻለዉ ሽያጩ የተከናወነዉና ከሽያጩ የተገኘዉ ገንዘብ ያለበት ለልጆች ቅጥም የዋለ መሆን ተጣርቶ ከተረጋገጠ በኋላ መሆኑን ለማሳየት እንጂ በማንኛዉም ጊዜ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ሞግዚት የህጻኑን የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሸጥ ሥልጣን አለዉ የሚል ትርጉም መሰጠቱን የሚያስገነዝብ አይደለም።
በያዝነዉ ጉዲይ ንብረትነቱ የአመልካች የሆነዉ መኖሪያ ቤት በ2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ በሽያጭ የተላለፈዉ 2ኛ ተጠሪ በነበራት የሞግዚትነት ሥልጣን ሳይሆን አመልካች አድሜዉ 16 አመት ሆኖ እያለ በሰጣት ቤቱን የመሸጥ የዉክልና ሥልጣን መሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።በስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ እንደተረጋገጠዉ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን በሞግዚትነት ሥልጣን ሽጣ ቢሆን ኖሮ የአመልካች እድሜ 18 ዓመት ሳይሞላዉ 18 ዓመት እንደሆነዉ በማስመሰል ለ2ኛ ተጠሪ ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል የዉክልና ሥልጣን እንዱሰጣት ማድረግ ባላስፈለገ ነበር። አመልካች ለ2ኛ ተጠሪ የሰጠዉ የዉክልና ሥልጣን ተረጋገጦ የተመዘገበዉ በአዱስ አበባ ከተማ ዉስጥ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት ከሰነደ በመረጋገጡ አመልካች የዉክልና ሥልጣን ለመሰጠት የሚያስችል ችልታ እንዲለዉ(እድሜዉ ለአካለመጠን መድረሱን) የማረጋገጥ ኃላፉነት በሰነድች ማረጋገጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ 3፣9(1/ለ) እና 14 መሰረት የዉክልና ሥልጣኑን አረጋግጦ የመመዝገብ ሥልጣን የተሰጠዉ የፋዳራል የሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ነዉ። ይህም የሚያሳየዉ በመርህ ደረጃ 1ኛ ተጠሪ ከማያዉቀዉ ሰዉ ጋር ያደረገዉ ዉል ቢሆን ለ2ኛ ተጠሪ የተሰጣት የዉክልና ሥልጣን በሚመለከተዉ አካል የተመዘገበና ቤት ለመሸጥ የሚያስችል ልዩ የዉክልና ሥልጣን እንዲላት ከማረጋገጥ ባለፈ የወካዩን እድሜ የማረጋገጥ ኃላፉነት እንደማይኖርበት ነዉ።ሆኖም ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ መርምሮና መዝኖ አመልካች ለ2ኛ ተጠሪ ዉክልና ሲሰጥ አመልካች አካለመጠን ያልደረሰ መሆኑን 1ኛ ተጠሪ እያወቀ አመልካች ለ2ኛ ተጠሪ ዉክልና መስጠት እንዱችል መታወቂያ እንዱያወጣና የዉክልና ሥልጣን ማስረጃ ወደተመዘገበበት መስሪያ ቤት በመዉሰድ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ተሳትፍ ማድረጉን ከምስክሮች ቃል አረጋግጧል።
ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በማስረጃ ከተረጋገጠዉ መገንዘብ የሚቻለዉ አመልካች ለ2ኛ ተጠሪ ዉክልና እንዱሰጥ ሲደረግም ሆነ 2ኛ ተጠሪ የዉክልና ሥልጣኑን ተጠቅማ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የቤት ሽያጭ ዉለ ስትፈጸም አመልካች ለአካለመጠን እንዲልደረሰ 1ኛ ተጠሪ ያዉቅ እንደነበር ነዉ።በዚህ መሰረት 1ኛ ተጠሪ አመልካች ለአካለመጠን አለመድረሱን ያዉቅ ከነበረ በክልለ የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 318/2 ስር እንደተደነገገዉ የአመልካችን አላዋቂነት መጠቀሙን ስለሚያሳይ የቤት ሽያጭ ዉለን ከ2ኛ ተጠሪ ጋር የፈጸመዉ በቅን ልቦና ነዉ ብል ለመደምደም አይቻልም። እንዱሁም አመልካች እድሜዉ ለአካለመጠን ሳይደርስ እንደደረሰ ተደርጎ መታወቂያ በማዉጣት የዉክልና ሥልጣን እንዱሰጥ መደረጉ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማስረጃ ተመዝኖ የተረጋገጠ ቢሆንም ባይረጋገጥ እንኳን በክልለ የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 321/1 መሰረት አካለመጠን ያልደረሰ ልጅ አካለመጠን ሳይደርስ ደርሻለሁ ብል ቢናገርም እንኳን ይህን በመናገሩ ብቻ አካለመጠን ባለመድረሱ ምክንያት በሕግ የሚደረግለትን ጥበቃ ሉያጣ አይችልም።በመሆኑም 1ኛ ተጠሪ አመልካች ለአካለመጠን ያልደረሰ መሆኑን እያወቀ እድሜዉ 18 ዓመት ያልሞላዉ አመልካች ዉክልና ለ2ኛ ተጠሪ እንዱሰጥ በማድረግ በመቀጠልም 2ኛ ተጠሪ ቤቱን እንድትሸጥለት ያደረገዉ የቅን ልቦና ጉድለት ያለበት መሆኑን ያሳያል።በዚህ አኳያ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ዉለን ያደረገዉ በቅን ልቦና እንዲልሆነ አመላክቶ የሰጠዉ ዉሳኔ የሕግ ድጋፍ ያለዉ በመሆኑ የሚነቀፍ አይደለም።
በተጨማሪም 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ለ1ኛ ተጠሪ በሽያጭ ያስተላፈችዉ አካለመጠን ያልደረሰዉ አመልካች በሰጣት የዉክልና ሥልጣን እንጂ በሞግዚትነት ሥልጣኗ አለመሆኑ የተረጋገጠ ቢሆንም የቤት ሽያጭ ዉለን በሞግዚትነት ሥልጣኗ ፈጽማለች ተብል ቢታሰብ እንኳን በተሻሻለዉ የክልለ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 323 መሰረት የሕግ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ሞግዚቱ ለሚፈጽማቸው ድርጊቶች፤ ወኪል የሆነ ሰው ከተሰጠው ሥልጣን በላይ በሚሰራበት ጊዜ አግባብነት ያላቸው የውክልና ሕግ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንደሚሆኑ ተደንግጓል።በዚህ መሰረት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2207/1 ስር ተወካዩ ከስልጣኑ ውጭ የሰራው ስራ በቅን ልቡና ሆኖ ሲገኝ ሥራውን ወካዩ እንዱያጸድቅለት እንደሚደረግ ተደንግጓል።
በዚህ አግባብ የአመልካች ሞግዚት የሆነችዉ 2ኛ ተጠሪ "ቅን ልቡና" መታየት ያለበት የቤት ሽያጭ የፈጸመችዉ ለአመልካች ጥቅም ጥቅም ነዉ ወይስ አይደለም? ከሚል አንጻር መሆን አለበት።ከዚህ ጋር በተያያዘም በሰ/መ/ አስገዲጅ ትርጉም ተሰጥቷል። ከዚህ አንጻር 2ኛ ተጠሪ ከቤት ሽያጭ ዉለ የተገኘዉን ገንዘብ ለአመልካች ጥቅም አዉያለሁ በማለት አልተከራከረችም፤ይህንን የሚያስረዲ ማስረጃ በማንኛዉም ተከራካሪ በስር ፍርድ ቤት ስለመቅረቡ ግራ ቀኝ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክርክር አያሳይም።እንዱሁም ከቤቱ ሽያጭ የተገኘ ገንዘብ ለአመልካች ጥቅም መዋለን የሚያመለክት ማስረጃ መቅረቡን የሥር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ ያረጋገጡት ነገር እንደላለ አረጋግጧል።ስለሆነም ከዚህም አንጻር ከሽያጩ የተገኘዉ ገንዘብ ለአመልካች ጥቅም አልዋለም በሚል ዉለ እንዱፈርስ ጉዲዩን በይግባኝ ያየዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድምዲሜ ላይ የደረሰዉ ማስረጃን መርምሮ የመመዘን ሥልጣኑን በመጠቀም በመሆኑና የማስረጃ ምዘና መርህን ተግባራዊ ከማድረግም አንጻርም የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ የቤት ሽያጭ ዉለ ሉፈርስ ይገባል ሲል የደረሰበት ድምዲሜ ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ ብለናል።
በልላ በኩል ከላይ በተመለከተዉ መሰረት የቤት ሽያጭ ዉለ ሉፈርስ ይገባል ተብል ጉዲዩን በይግባኝ ባየዉ የከልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠዉ ዉሳኔ ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ የሚባል ከሆነ የዉለ መፍረስ ዉጤት ምን ላሆን ይገባል የሚለዉ ቀጥል ዉሳኔ የሚሻ ነጥብ።አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ቤቱ ለ1ኛ ተጠሪ በሽያጭ የተላለፈዉ በብር 40,000.00 እንጂ በብር 300,000.00 አይደለም ብለዉ ሲከራከሩ 1ኛ ተጠሪ ደግሞ ቤቱን በብር 300,000.00 መግዛቱን በመግለጽ ተካራክሯል።እንዱሁም ከስር ጀምሮ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን ከገዛ በኋላ ብር 250,000.00 ተጨማሪ ወጪ አዉጥቶ ተጨማሪ ክፍልችን መገንባቱን በመግለጽ ተከራክሯል።
የዉል መፍረስ በዉል የተቋቋሙ መብቶችና ግዳታዎች እንዱቋረጡ ወይም ተፈፃሚነት እንዲይኖራቸዉ ማድረግን የሚያስከትል ስለመሆኑ በፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 1807/ሀ እና 1815 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ዉል ሲሰረዝ ወይም ሲፈርስ ተዋዋዮች በተቻለ መጠን ዉለ ከመደረጉ በፉት ወደነበሩበት ሁኔታ እንዱመለሱ እና ዉለን ለመፈጸም የተሰራ ሁለ ቀሪ ሆኖ በማናቸዉም አኳኋን ዉጤት እንደላለዉ የሚደነግገዉ የሕጉ አንቀጽ 1815 ድንጋጌ በተለይ ሲታዩ በዉል መሰረት አንደ ለላላዉ የፈጸመዉ ተግባር ካለ ቀሪ ተደርጎ ግራ ቀኝ ከዉለ በፉት ወደ ነበሩበት ሁኔታ እንዱመለሱ ማድረግ የግድ የሚል መሆኑን ነዉ። በመሆኑም ዉለ አንድን ንብረት በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገ ከሆነ እና ዉለ የማይረጋበት ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠ ዉጤቱ የሚሆነዉ ንብረቱን ገዝቶ በዉለ መሰረት የተረከበዉ ተዋዋይ ንብረቱን ለሻጩ መልሶ እንዱያስረክብ፣ ሻጩም ደግሞ በዉለ መሰረት የተቀበለዉ ገንዘብ ካለ ገንዘቡን ለገዥዉ እንዱመልስ ማድረግ ነዉ። ይህም ማለት ግራ ቀኝ የተቀባበለትን ነገር ባለበት ሁኔታ አንደ ለላላዉ እንዱመልስ ከማድረግ ዉጪ ሻጩ በዉለ መሰረት ከተቀበለዉ ገንዘብ በላይ ገዥዉም ደግሞ ከተረከበዉ ንብረት በላይ አንደ ለላላዉ ለመመለስ የማይገደደ መሆኑን ነዉ። በተሻሻለዉ የክልለ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 319 ስር አካለመጠን ካልደረሰ ልጅ ጋር የሚደረግ ዉል ሲፈርስ የሚኖረዉን ዉጤት በተመለከተ የተደነገገዉም ይህንን በፍ/ብ/ሕጉ የተደነገገዉን የሚደግፍ ነዉ።በመሆኑም 1ኛ ተጠሪ የሽያጭ ዉለ በተደረገበት ጊዜ የነበረዉን ቤት ለአመልካች ሉያስረክብ ይገባል ብል ጉዲዩን በይግባኝ ያየዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ ብለናል።
ላላዉ ከላይ እንደተመለከተዉ በፍ/ብ/ ሕጉ ቁጥር 1815 ስር የተደነገገዉ ዉለ በመፍረሱ ምክንያት ግራ ቀኝ የሚኖራቸዉ መብትና ግዳታ ሲሆን ተጠሪ በቦታዉ ላይ በእራሱ ወጪ የገነባዉ ቤት በዚህ ድንጋጌ ማዕቀፍ ዉስጥ የሚታይ አይሆንም። በፍ/ብ/ ሕግ ቁጥር 1818 ድንጋጌ መሰረት ዉለ ከመፍረሱ የተነሳ ንብረትን የመመለስ ግዳታ ያለበት ሰዉ ንብረቱን ለዉጦ ወይም በዚሁ ላይ ወጪ አድርጎ እንደሆነ ከዚህ መለዋወጥ ወይም ወጪ የተነሳ ያለትን መብቶች በከዉል ዉጪ ኃላፉነት ድንጋጌዎች መሰረት መጠየቅ ይችላል። እንደሚታወቀዉ በዉል አንድ ሰዉ አንድን ንብረት በእጁ ካስገባ በኋላ በእራሱ ወጪ የተለያዩ ማሻሻያዎችን ያደረገ እንደሆነ በእራሱ ወጪ ተጨማሪ ነገር የሰራዉ ተዋዋይ ንብረቱን መልሶ ሲያስረክብ ከነማሻሻያዎቹ ለላላኛዉ ተዋዋይ ሉያስረክብ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል። ይህ መሆኑ በአንድ በኩል ንብረቱ የተመለሰለት ሰዉ ያላግባብ እንዱበለጽግ፤ በልላ በኩል ደግሞ ንብረቱን የማስረከብ ግዳታ ያለበት ወገን ያለአግባብ ተጎጂ ላሆን የሚችልበት ዕድል ሉኖር ይችላል። የፍ/ብ/ሕጉ ቁጥር 1818 ድንጋጌም ለእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች መፍትሓ የመስጠት ዓላማ ያደረገ በመሆኑ የድንጋጌዉ አፈፃፀምም ከላይ በተመለከተዉ ምክንያት ሉፈጠር የሚችለዉን ተወዲዲሪ ጥቅም (computing interests) ማስታረቅ በሚያስችል መልኩ ላሆን ይገባል። በዚህ መሰረት በያዝነዉ ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ በእጁ በገባዉ ይዞታ ላይ የሰራዉ ተጨማሪ ክፍል ቤቶች ካለ ሁለት አማራጮች ይኖረዋል። አንደኛዉ አማራጭ በይዞታዉ ላይ በእራሳቸዉ ወጪ የሰሩትን ቤት አፍርሶ ባድ ቦታዉን ብቻ ለአመልካች ማስረከብ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ በተጨማሪነት በቦታዉ ላይ የተሰራዉን ቤት እዚያዉ በመተዉ ቤቱ የተሰራበትን ወጪ አመልካች እንዱከፍል መጠየቅ ነዉ። ተጠሪ ሁለተኛዉን አማራጭ ከመረጠ ይህ ጥያቄዉ የሚስተናገደዉ በፍ/ብ/ ሕጉ ቁጥር 1818 ላይ በተመለከተዉ ይሆናል።ከዚህ አንጻር ጉዲዩን በይግባኝ ያየዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1704/1 እና 1808/1 መሰረት የቤት ሽያጭ ዉለ እንዱፈርስ እና 1ኛ ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች እንዱያስረክብና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1815/1 መሰረት አስቀድሞ ወደነበሩበት እንዱመለሱ ብል ሲወስን የሚመለሰዉ የሽያጩ ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ ግራ ቀኙ በመካካዲቸዉ የቤት ሽያጭ ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት በዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ ባለመሆኑ ይዘቱ ባከራከረ ጊዜ በዉለ ላይ የተመለከቱ ምስክሮችን በመስማትና በልላ ማስረጃ ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2009 ስር የተደነገገዉ ያሳያል።ስለሆነም ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትክክለኛዉን ቤቱ የተሸጠበትን ገንዘብ መጠን በማስረጃ ማረጋገጡ የሕግ ድጋፍ ያለዉ ነዉ። በዚህም መሰረት በቤት ሽያጭ ዉለ ላይ ቤቱ በብር 300,000.00 እንደተሸጠ ቢገለጽም ቤቱ በእርግጥ በብር 40,000.00 ብቻ እንደተሸጠና 1ኛ ተጠሪም ለ2ኛ ተጠሪ የሰጠዉ ብር 40,000.00 ብቻ እንደሆነ በምስክሮች ቃል አረጋግጦ 2ኛ ተጠሪ ብር 40,000.00(አርባ ሺህ ብር)ለ1ኛ ተጠሪ እንድትከፍል የሰጠዉ ዉሳኔ ሕግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የሚነቀፍበትን ምክንያት አላገኘንም።
ሲጠቃለል አመልካች እድሜዉ ለአካለመጠን ሳይደርስ በዉርስ ያገኘዉን መኖሪያ ቤት 2ኛ ተጠሪ በሽያጭ እንድታስተላልፍ የሰጠዉ የዉክልና ሥልጣን ሕጋዊ ዉጤት የለዉም።ይህንን ሕጋዊ ዉጤት የላለዉን የዉክልና ሥልጣን በመጠቀም 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ቤቱን በሽያጭ ማስተላለፎ ተረጋግጦ እያለ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት 1ኛ ተጠሪ ቤቱን የገዛዉ ዉክልና ካላት 2ኛ ተጠሪ በመሆኑ አመልካች እድሜዉ ለአቅመ አዲም ደርሷል ወይስ አልደረሰም እንዱሁም ዉክልና መስጠት ይችል ነበር የሚለ ጭብጦች ተይዘዉ ሉጣሩ አይገባም በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር የከፍተኛዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ በማጽናት የሰጠዉ ዉሳኔ በፋዳራለም ሆኖ በክልል ሕገ መንግስት እንዱሁም በተሻሻለዉ የክልለ ቤተሰብ ሕግ በወቅቱ ሕጻን ለነበረዉ አመልካች የተደረገለትን ሕጋዊ ጥበቃ ያላገናዘበ እና ለሕጻን ጥቅም አጽንኦት ሰጥቶ እንዱወስን በሕግ የተጣለበትን ግዳታ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ የአመልካችን መኖሪያ ቤት ለ1ኛ ተጠሪ በሽያጭ ያስተላለፈችዉ በአመልካች ስም ሆኖ እያለ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት 2ኛ ተጠሪ ዉለን ለመፈጸም ያስቻላትን የሥልጣን ምንጭ ሕጋዊነት መመርመር አያስፈልግም ብል የደረሰበት ድምዲሜ የወካይና የተወካይ ግንኙነት ጽንሰ ሀሳብና ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተሻሻለዉ የክልለ ቤተሰብ ሕግ እና በፍ/ብ/ሕጉ የተደነገገዉን ያገናዘበ ባለመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ አተገባበር ስህተት ነዉ።በተጨማሪም አመልካች የዉክልና ሥልጣን ለ2ኛ ተጠሪ ሲሰጥም ሆነ የቤት ሽያጭ ዉለ ሲደረግ ለአካለመጠን እንዲልደረሰ 1ኛ ተጠሪ እያወቀ አመልካች ለ2ኛ ተጠሪ የዉክልና ስልጣን እንዱሰጥ በማድረግ ሂደት ተሳትፍ ማድረጉ ስለተረጋገጠ አመልካች በቅን ልቦና የፈጸመዉ ዉል ካለመሆኑም በተጨማሪ 2ኛ ተጠሪም የአመልካች ንብረት የሆነዉን ቤት በሽያጭ ያስተላለፈችዉ ለአመልካች ጥቅም ስለመሆኑም ሆነ ከቤቱ ሽያጭ የተገኘዉን ገንዘብ ለአመልካች ጥቅም ያዋለች ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በማለት ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዲሜ ሕግንና ማስረጃን መሰረት ያደረገ ሆኖ እያለ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያለዉ ስልጣን መሰረታዊ የሕግ ስህተት ካለ መርምሮ ማረም ብቻ ሆኖ እያለ በራሱ ማስረጃ ወደመመርመር ዉስጥ ገብቶ ከቤቱ ሽያጭ የተገኘዉ ገንዘብ ለአመልካች ጥቅም መዋለ ተረጋግጧል ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።በልላ በኩል የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ዉለ እንዱፈርስ መወሰኑ ተገቢ ቢሆንም ግራ ቀኙ ወለ ከመደረጉ በፉት ወደነበሩበት የሚመለሱበትን አግባብ ሲወስን 1ኛ ተጠሪ ተጨማሪ ክፍል ቤቶችን ሰርቻለሁ ብል ካሰማዉ ክርክር አንጻር በመግለጽ ዉሳኔ አለመስጠቱ ሉታረም የሚገባዉ ስህተት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 15/07/2012ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 18/02/2012 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 14/05/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሻሽሎል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ከላይ በፍርደ መግቢያ ላይ የተጠቀሰዉን መኖሪያ ቤት ለመሸጥ 2ኛ ተጠሪ ከአመልካች ያገኘችዉን የዉክልና ስልጣን የማይጻና ነዉ በማለት በዚህ የዉክልና ሥልጣን 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በቀን 24/10/2007ዓ/ም የፈጸመችዉ የቤት ሽያጭ ዉል እንዱፈርስ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች እንዱያስረክብ እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) እንድትከፍል የሰጠዉ ዉሳኔ ጸንቷል።
1ኛ ተጠሪ በተሸጠዉ ቤት ተጨማሪ ክፍልችን ገንብቶ ከሆነ ክፍልቹን ለመስራት ያወጣዉን ወጪ በፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 1818 መሰረት አመልካች እንዱከፍለዉ ክስ በማቅረብ ዲኝነት የመጠየቅ መብት አለዉ ብለናል።
በዚህ ችልት የወጣ ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዉሳኔዉ መሰረት እንዱፈጽም ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የውሳኔው ግልባጭ ይተላለፍ።ለግራ ቀኙም የዉሳኔዉ ግልባጭ እንዱሰጣቸዉ ሲያመለክቱ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.