የፍርድ ቤት እግድ የተሰጠበትን ቤት በሽያጭ በማስተላለፍ የሚደረግ የሽያጭ ውል ሕጋዊ ውጤት የላለውና ሉፈርስ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.154 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች፣ የፍትሀ ብሄር ህግ ቁጥር 1808/2
No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 28 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሮ አበበች ዘበርጋ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የፍርድ ቤት እግድ የተሰጠበትን ቤት በሽያጭ ማስተላለፍ የሚኖረዉን ዉጤት በሚመለከት የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በሚል በቀረበ አቤቱታ መነሻ የተደረገ ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ከክርክሩ እንደተረዲነዉ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ባልና ሚስት ሲሆኑ በአዲማ ከተማ ጎሮ ቀበላ ዉስጥ የሚገኝ በካርታ ቁጥር 5522/95 በ200 ካሬ ሜትር ስፊት ላይ የተገነባ የጋራ ሀብት የሆነ ቤት፤ይህ ቤት በአመልካች ስም ተመዝግቦ ይታወቅ የነበረና በ1ኛ ተጠሪ በዉክልና ይተዲደር የነበረ ሲሆን አመልካች በ2008 ዓ/ም ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የነበራቸዉ ጋብቻ እንዱፈርስ የፍቺ ክርክር ሲያደርጉ ይህ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት ታግድ እንዱቆይ ለአዲማ ከተማ ፍርድ ቤት አመልክተዉ ፍርድ ቤቱ በቀን 03/02/2008ዓ/ም በዋለዉ ችልት ቤቱ ታግድ እንዱቆይ ለ4ኛ ተጠሪ ትእዛዝ ሰጥቶ 4ኛ ተጠሪም በቀን 09/02/2008ዓ/ም በጻፈዉ ደብዲቤ በትእዛዙ መሰረት ማገደን ለፍርድ ቤቱ ማሳወቁን እና ዕግደም እስካሁን አለመነሳቱን በመግለጽ መከራከሯን የዉሳኔዎቹ ግልባጭ ያሳያል። ሆኖም 1ኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ እግድ መሰጠቱን እያወቀ የአመልካችን መብት ለማሳጣት በማሰብ ዘመደ ለሆነዉ ለ2ኛ ተጠሪ የዉክልና ስልጣን በመስጠት 2ኛ ተጠሪ የዉክልና ስልጣኑን በመጠቀም የቤቱን ዋጋ ዝቅ በማድረግ ባለቤቱ ለሆነችዉ ለ3ኛ ተጠሪ በብር 170,000.00 በቀን 22/05/2010 ዓ/ም በተደረገ የቤት ሽያጭ ዉል በመፈጸም የቤቱ ስመ ሀብት ወደ 3ኛ ተጠሪ እንዱተላለፍ አድርገዋል በማለት የቤት ሽያጭ ዉለ የተፈጸመዉ በቤቱ ላይ የተሰጠዉን እግድ በመተላለፍ በመሆኑ ዉለ እንዱፈርስ እንዱወሰንላት እና 4ኛ ተጠሪ ወደ 3ኛ ተጠሪ ያዛወረዉን ስመ ሀብት ወደ አመልካች ስም እንዱያዛዉር እንዱወሰንላት ዲኝነት ጠይቃለች።
1ኛ ተጠሪ ለክሱ ባሰማዉ ፍሬ ነገር በሚመለከተዉ ክርክሩ የሽያጭ ዉለ የተፈጸመዉ አመልካች በሰጠችኝ የዉክልና ስልጣን በመሆኑ የሽያጭ ዉለ የተፈጸመዉ ከአመልካች ጋር ነዉ።ቤቱን በቀን 20/01/2008ዓ/ም በተደረገ ዉል ለ2ኛ ተጠሪ በብር 130,000.00 ሽጫለሁ። ቤቱ ሲሸጥ ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችለኝ በአመልካች የተሰጠኝ ዉክልና ጸንቶ ይገኛል። ቤቱ ከተሸጠ በኋላ ገዥዎች ተጨማሪ ግንባታ በማከናወን የቤቱን ስመ ሀብት ወደ ስማቸዉ እንዱዛወር አድርገዋል።በቤቱ ላይ እግድ መሰጠቱን አላዉቅም።የተሰጠ እግድም የለም።የቤቱ ዋጋም ዝቅ አልተደረገም በሚል ክሱ ዉድቅ እንዱደረግ በመጠየቅ ተከራክሯል።
2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በጋራ ባቀረቡት ክርክር አመልካችና 1ኛ ተጠሪ የባልና ሚስት ክርክር ሲያደረጉ በቤቱ ላይ እግድ አልተሰጠበትም።በቤቱ ላይ እግድ አለመኖሩን አጣርተን የገዛነዉ ቤት ነዉ። አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ የሰጠችዉ ዉክልና ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል መሆኑን፣ እንዱሁም ይህ ዉክልና ተወካይ 3ኛ ወገን ለመወከል የሚያስችል ስልጣን የሚሰጥ መሆኑንና 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች በተሰጠዉ ዉክልና መነሻ 2ኛ ተጠሪን በቀን 23/05/2010 /2010 ቤቱን ጭምር መሸጥ እንዱችል በሰጠዉ የዉክልና ስልጣን ዉክልናዉ ያልተሻረ መሆኑን አረጋግጠን የቤቱን ሽያጭ ዋጋ ክፍለን በቅን ልቦን 3ኛ ተጠሪ የገዛሁት ቤት ከመሆኑም በተጨማሪ የቤቱ ስመ ሀብት እዲና እገዲ እንደላለዉ ተጣርቶ በቀን 25/05/2010ዓ/ም ወደ 3ኛ ተጠሪ ስም ዞሮ እንዱመዘገብ ያደረግነዉ ቤት በመሆኑ አመልካች በቤቱ ላይ መብት አለኝ የምትል ከሆነ ድርሻዋን ከ1ኛ ተጠሪ መጠየቅ አሉያም እግድ እያለበት ተሸጧል የምትል ከሆነም ከ4ኛ ተጠሪ ከምትጠይቅ በስተቀር 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪን ልትጠይቅ ስለማትችል ዉለ ሕጋዊ ነዉ ተብል ክሱ ዉድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል።
4ኛ ተጠሪ መጥሪያ ደርሶት ቀርቦ ባለመከራከሩ ክርከሩ 4ኛ ተጠሪ በላለበት እንደታየ የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ያሳያል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ዲኝነት ሥልጣን ያየዉ የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት ፍሬ ነገሩን በተመለከተ በቀን 07/03/2011 ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ 1ኛ ተጠሪ በአመልካች የተሰጠዉን ዉክልና በመጠቀም ለ2ኛ ተጠሪ ዉክልና የሰጠዉ በቀን 23/05/2010 ዓ/ም ሆኖ 2ኛ ተጠሪ ደግሞ የዉክልና ስልጣን አለኝ በሚል ቤቱን ለ3ኛ ተጠሪ በሽያጭ ያስተላለፈዉ በቀን 22/05/2010ዓ/ም የዉክልና ስልጣን ሳይሰጠዉ በመሆኑ የዉክልና ስልጣን ሳይኖር የተፈጸመ የቤት ሽያጭ ዉል ከሕግ ዉጭ የተፈጸመ ዉል እንደሆነ፤ እንዱሁም በቤቱ ላይ እግድ ተሰጥቶበታል የተባለበትን መዝገብ የሆነዉን መዝገብ ከአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት አስቀርቦ እንደተመለከተና በመዝገቡ ላይ ፍርድ ቤቱ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት ታግድ እንዱቆይ በቀን 03/02/2008ዓ/ም ትእዛዝ ሰጥቶ ለ4ኛ ተጠሪ ማሳወቁንና እግደ አለመነሳቱን ከመዝገቡ ማረጋገጡን፤ እግደ ጸንቶ እያለ በቀን 22/05/2010ዓ/ም የቤት ሽያጭ ዉል ተፈጽሞ የቤቱ ስመ ሀብት በቀን 25/05/2010ዓ/ም ወደ 3ኛ ተጠሪ መዛወሩን ማረጋገጡን፤ እንዱሁም የቤቱን ማህደር አስቀርቦ በማህደሩ ዉስጥ የእግድ ትእዛዙ መኖሩን ማረጋገጡን በመግለጽ እግደ እያለ 3ኛ ተጠሪ ቤቱን መግዛታቸዉ ቤቱን በቅን ልቦና ገዝተዋል አያስብልም በሚል በ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች መካከል የተፈጸመዉ የቤት ሽያጭ ዉል እና በ3ኛ ተጠሪ ስም የተመዘገበዉ የባለቤትነት መብት ፈርሷል በማለት አመልካችና 1ኛ ተጠሪ የቤቱ ባለቤቶች ናቸዉ ሲል ወስኗል።
በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ይግባኝ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 03/08/2011ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ በቁጥር 5562/2005 በቀን 15/12/2005 የሰጠችዉ ዉክልና ቤቱን የመሸጥ ስልጣን የሚሰጠዉ ዉክልና በመሆኑና ዉክልናዉ እስካሁን ጸንቶ የሚገኝ በመሆኑ አመልካች ዉክልናዉ በሕግ አግባብ እንዱሻር ባላደረገችበት የዉክልና ዉለ ተፈጻሚ እንዲይሆን ያሰማችዉ ክርክር የሕግ መሰረት እንደላለዉ፤ እንዱሁም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት 1ኛ ተጠሪ በቀን 23/05/2010 ዓ/ም 2ኛ ተጠሪ ይህንን ቤት መሸጥ መለወጥ የሚያስችለዉን የዉክልና ስልጣን እንደሰጠዉ፣ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ የተሰጠዉን ሙለ ዉክልና በመጠቀም በቀን 23/05/2010ዓ/ም በተጻፈ የሽያጭ ዉል ለ3ኛ ተጠሪ በመሸጡ ዉለ ጸድቆ ስመ ሀብቱ ወደ 3ኛ ተጠሪ መተላለፈን ማረጋገጡን ፤ በቤቱ ማህደር ዉስጥም ተሰጠ የተባለዉ እግድ እንዲልተገኘ በመጥቀስ እግደ በማህደሩ ዉስጥ አልተገኘም እንጂ እግደ ቢኖር እንኳን እግደ በማህደሩ ዉስጥ መኖር አለመኖሩን መመርመር የከተማ አስተዲደሩ ስራ በመሆኑ የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ማህደሩን ወስደዉ መመርመር ስለማይችለ አመልካች በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2183 እና 2184 መሰረት የዉክልና ስልጣኑን ባላሻረችበት 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ከላይ በተገለጸዉ መሰረት የገዙትንና በስማቸዉ ያስመዘገቡት ቤት ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት የዉክልና ስልጣኑ የሚያስከትለዉን ዉጤት ሳያገናዝብ እና በቤቱ ማህደር ዉስጥ እግደ መኖሩን ሳያረጋግጥና ማህደሩን መመርመር 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎችን የማይመለከት ጉዲይ ሆኖ እያለ ዉለ እንዱፈርስ መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በመሻር 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ቤቱን በሕጋዊ መንገድ በቅን ልቦና ስለገዙ ዉለ ሉፈርስ አይገባም በማለት ወስኗል።
አመልካች ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ያቀረበች ቢሆንም ችልቱ በመ/ ላይ በቀን 30/08/2011 ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ትእዛዝ ለሰበር ችልት አያስቀርብም በማለት አቤቱታዋን ሰርዟል።አመልካች ከላይ በተጠቀሰዉ መሰረት በተሰጠ ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል በቀን 21/09/2011 ዓ/ም ጽፈዉ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት እንዲይሸጥ ላሳግድ የቻልኩት ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ከነበረን የጋብቻ ፍቺ ክርክር መነሻ 1ኛ ተጠሪ (ባለቤቴ) በነበረዉ የዉክልና ስልጣን ቤቱን ይሸጥብኛል በሚል ጥርጣሬ ነዉ።2ኛ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት መሸጥ እንዱችል በ1ኛ ተጠሪ ዉክልና የተሰጠዉ በቀን 23/05/2010ዓ/ም ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ግን የሽያጭ ዉለን ባለቤቱ ከሆነችዉ 3ኛ ተጠሪ ጋር ያደረገዉ በቀን 22/05/2010ዓ/ም ዉክልና ሳያገኝ በመሆኑ በዚህ ምክንያት ዉለ ሉፈርስ ይገባል ተብል የተወሰነዉን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ፤ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 03/02/2008ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ እንዲይሸጥ እንዲይለወጥ በማንኛዉም መንገድ ወደ 3ኛ ወገን እንዲይተላለፍ ታግድ እንዱቆይ ትእዛዝ ተሰጥቶበት 4ኛ ተጠሪ በቀን 09/02/2008ዓ/ም በጻፈዉ መልስ በትእዛዙ መሰረት ቤቱን ማገደን ለፍርድ ቤቱ ማሳወቁን፤ እንዱሁም እግደ አለመነሳቱን የአዲማ ልዩ ዞን መዝገቡን አስቀርቦ ተመልክቶ አረጋግጦ እግደ ጸንቶ እያለ የተፈጸመ የቤት ሽያጭ ዉል እንዱፈርስ የሰጠዉ ተገቢ ዉሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንደሆነ፤ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቤቱ ፊይል ዉስጥ እግደ እያለና እግድ የተሰጠበትን ፊይል መርምሮ ያገደዉ አካል እግድ የለበትም የሚል ማረጋገጫ ሳይሰጥበት በቤቱ ማህደር ዉስጥ እግደ የለም ቢኖር እንኳን መኖር አለመኖሩን የማረጋገጥ ኃላፉነት የከተማ አስተዲደር ሥራ እንጂ የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ኃላፉነት አይደለም በሚል 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ከራስ ጋር ያደረጉትን የጥቅም ግጭት ያለበት የሽያጭ ዉል መሆኑ ጭምር ተረጋግጦ እንዱፈርስ የተሰጠዉን ዉሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚና ሰበር ሰሚ ችልቶች የሰጡት ዉሳኔዎች ይሻርልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የንብረት ክርክር ላይ በነበሩበት ጊዜ ክርክር ያስነሳዉ ቤት በፍርድ ቤት ታግድ እያለ ይህ እግድ ሳይነሳ በሽያጭ ለ3ኛ ወገን ተላልፎል ተብል መወሰኑ ከፍርድ በፉት ከሚሰጥ እግድ ዓላማ እና አፈጻጸም አንጻር አግባብ ስለመሆኑ እና በተሰጠዉ እግድ መሰረት የሚመለከተዉ አካል ቤቱን ስለማገደ እግደን ለሰጠዉ ፍርድ ቤት መልስ ሰጥቶ እያለ እግደ የቤቱ መዝገብ ዉስጥ የለም የተባለበት ሁኔታን ለማጣራት ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ብል ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በሚከተለዉ መሰረት መልሳቸዉን በማቅረብ ተከራክረዋል።
1ኛ ተጠሪ በቀን 29/11/2011ዓ/ም በተጻፈ መልሳቸዉ አመልካች ቤቱ ታግድ እያለ እንደተሸጠ በመግለጽ የተከራከረች ቢሆንም ቤቱ የተሸጠዉ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ በሰጠችኝ ቤቱን መሸጥ መለወጥ በሚያስችል ዉክልና እግደ ከመሰጠቱ በፉት ከአመልካች ጋር አብረን በቀን 20/01/2008ዓ/ም ሽጠን በጋብቻ ዉስጥ ገንዘቡን ከተጠቀምን በኋላ ዉክልና መስጠቷን ሳትክድ አመልካች በቀን 20/01/2008ዓ/ም የተደረገዉ ዉል ሳይፈርስ ከዚህ በኋላ የተደረገ ዉል እንዱፈርስ መጠየቋ ተገቢነት የለዉም። አመልካች የፍቺ ክርክር ባደረግንበት መዝገብ ላይ የነበረንን ክርክር በእርቅ ጨርሰን አብረን እየኖርን እያለ ከ2 ዓመት በኋላ ቤቱ ታግድ ነበር በማለት የምታነሳዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም።በቤቱ ማህደር ዉስጥ ምንም እግድ ባለመኖሩና ቤቱ ጅምር ቤት በመሆኑ በቅን ልቦና በብር 170,000.00 ከተሸጠ በኋላ ገዥ ጅምር ቤቱን አፍርሳ በአዱስ መልክ ከ1,500,000.00 ብር በላይ ወጪ አዉጥታ ገንብታ ወደ ስሟ አዛዉራ እየተጠቀመች እያለ አመልካች ጉዲት ሳይደርስባት አለአግባብ ለመበልጸግ ያቀረበችዉ ክስ መሆኑ ተረጋግጦ ክሱ ዉድቅ መደረጉ ተገቢ በመሆኑ ያቀረበችዉ የሰበር አቤቱታ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።
2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በጋራ በቀን 29/11/2011 ዓ/ም በተጻፈ መልሳቸዉ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ ዉክልና የሰጠችዉ በቀን 15/2/2005ዓ/ም ሲሆን ይህንን የዉክልና ስልጣን በመጠቀም 1ኛ ተጠሪ 2ኛ ተጠሪን የወከለዉ በቀን 23/05/2010 ዓ/ም ነዉ። ቤቱ ከእዲና እገዲ ነጻ መሆኑን የቤቱ ፊይል ከሚገኝበት ከአሁን 4ኛ ተጠሪ አረጋግጠን ዉለን ዉል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠዉ አካል ፉት ቀርበን በቀን 24/05/2010ዓ/ም ተዋዉለናል። ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉለ እንዱፈርስ ሲወስን በአከራካሪዉ ቤት ላይ እግድ መኖሩን ከ4ኛ ተጠሪ አስቀርቦ አላረጋገጠም። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግን የቤቱን ፊይል ከ3ኛ ተጠሪ በትእዛዝ አስቀርቦ በማጣራት በቤቱ ፊይል ላይ እግድ እንደላለና እግደ አለ ቢባል እንኳን የቤቱን ፊይል መመርመር የገዥ ሳይሆን የከተማ አስተዲደሩ እንደሆነና ቤቱም የተሸጠዉ አመልካች በሰጠችዉ ልዩ ዉክልና እንደሆነና 3ኛ ተጠሪ ቤቱን በቅን ልቦና መግዛቴን በማረጋገጥ ዉለ ሉፈርስ አይገባም በቤቱ ላይ አመልካች ያላትን መብት ያሳጣት ወገን ካለ መጠየቅ ትችላለች ብል የሥር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በመሻሩ የፈጸመዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም። እግደ መኖሩን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች አናዉቅም ለማወቃችን በስር ፍርድ ቤት የቀረበ ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም።እግድ በቤቱ ፊይል ላይ አለመኖሩን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባረጋገጠበት ሁኔታ ይህ ችልት ተጠሪዎች እግደ መኖሩን ያዉቁ ነበር ወይስ አይደለም የሚለዉን የማስረጃ ክርክር ተቀብል ማስረጃ የመመዘን ስልጣን የለዉም።3ኛ ተጠሪ በ4ኛ ተጠሪ ዘንድ ካለዉ የቤቱ ማህደር እግድ እንደላለ አረጋግጠን ቤቱን በቅን ልቦና ከገዛሁ እና ስመ ሀብቱን በስሜ ካስመዘገብኩ በኋላ ብር 1,500,000.00 በላይ ወጪ አዉጥቼ ተጨማሪ ግንባታ በመፈጸም ቤቱን በመያዣነት በመስጠት ከብድርና ቁጠባ ተቋም ከፍተኛ ገንዘብ ተበድሬበታለሁ። በዚህ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ቤት ስለሆነ አመልካች ዉል እንዱፈርስላት መጠየቋ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ፣15551፣39336 እና 47378 ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ የሚቃረን በመሆኑ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዉለ አይፈርስም ተብል መወሰኑ የሚነቀፍ አይደለም እንዱባልልን። በሽያጭ ዉለ አናት ላይ ዉለ የተዘጋጀበት ቀን ጥር 22 ቀን 2010 ዓ/ም ተብል የተጻፈ ቢሆንም ዉለን በዉል አዋዋይ ፉት የተፈራረምንበት ቀን 24/05/2010ዓ/ም በመሆኑ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በሰጠዉ ትርጉም እና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2015/ሀ መሰረት ዉለ የተደረገበት ቀን ጥር 24 ቀን 2010 ዓ/ም በመሆኑ አመልካች ከዚህ አንጻር ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም።እንዱሁም ባል ከሚስት ፍቃድ ዉጭ ንብረቱን ሽጦ ቢገኝ የተሸጠዉ ቤት ወደ ገዥ ተዛዉሮ ከተገኘ ሚስት በተሸጠዉ ቤት ያጣችዉን ድርሻ ከባሎ መጠየቅ ከምትችል በስተቀር 3ኛ ወገን መጠየቅ እንደማትችል በኦሮሚያ ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 114 እና 115 የተደነገገዉን በመጥቀስ የፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ አስገዲጅ ትርጉም ስለሰጠ አመልካች ባላ ቤቱን አላግባብ ሽጦብኛል የምትል ከሆነ ከባሎ መጠየቅ ከምትችል በስተቀር ዉል ይፍረስልኝ በማለት መጠየቅ አትችልም ተብል አቤቱታዋ ዉድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች ከተራ ቁጥር 1-3 በተጠቀሱ ተጠሪዎች በቀረበ መልስ ላይ በቀን 30/01/2012ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል። 4ኛ ተጠሪ መጥሪያ ደርሶት ባለመቅረቡ ክርክሩ በላለበት ተሰምቷል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠ ዉሳኔና ትእዛዝ ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደተመረመረዉም 1ኛ ተጠሪ እና አመልካች ባልና ሚስት የነበሩ ሲሆን ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ በአዲማ ከተማ ጎሮ ቀበላ ዉስጥ የሚገኝ በካርታ ቁጥር 5522/95 በአመልካች ስም ተመዝግቦ የነበረዉና በ200 ካሬ ሜትር ስፊት ላይ የተገነባ ነዉ የተባለዉ ቤት ደግሞ አመልካችና 1ኛ ተጠሪ በጋብቻ ወቅት ያፈሩት የጋራ ሀብት የሆነ ንብረት አንደነበር በስር ፍርድ ቤቶች በተደረገ ክርክር የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። እንዱሁም 1ኛ ተጠሪ ይህንን ቤት መሸጥ እንዱችልና ይህንኑ ስልጣኑን ለ3ኛ ወገን በዉክልና ማስተላለፍ እንዱችል የሚፈቅድ በቁጥር 5562/2005 በቀን 15/12/2005 የተመዘገበ የዉክልና ስልጣን አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ መስጠቷን በግራ ቀኝ የታመነና በማስረጃ ጭምር የተረጋገጠ ፍሬ ነገር መሆኑን ከክርክሩ ተረድተናል። ይህ በእንዱህ እንዲለ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ የጋብቻ ፍቺ ክርክር ሲያደርጉ በነበሩበት ጊዜ በአመልካች ጠያቂነት በዚህ መዝገብ ላይ በቀን 03/02/2008 ዓ/ም በዋለዉ ችልት የአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት አከራካሪዉ ቤት እንዲይሸጥ፣እንዲይለወጥ በማናቸዉም መንገድ ለ3ኛ ወገን እንዲይተላለፍ እግድ መስጠቱንና እግደም እንዱነሳ ተለዋጭ ትእዛዝ አለመስጠቱን የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እግድ ተሰጠ የተባለበትን መ/ ከአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት አስቀርቦ ማረጋገጡን የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል።
1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ያገኙትን ከላይ የተጠቀሰዉን የዉክልና ስልጣን በመጠቀም 2ኛ ተጠሪ አከራካሪወን ቤት መሸጥ መለወጥ እንዱችለ በቀን 23/05/2010 /2010 በተመዘገበ የዉክልና ስልጣን 2ኛ ተጠሪን መወከላቸዉም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። በዚህ አግባብ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ባገኙት ዉክልና ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት ለ3ኛ ተጠሪ መሸጣቸዉንና ሽያጩን ተከትል በአመልካች ስም ተመዝግቦ የነበረዉ የቤቱ ስመ ሀብት ወደ 3ኛ ተጠሪ ተላልፍ እንደሚገኝም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ሲሆን አመልካች እንዱፈርስ ዲኝነት የጠየቁበት የቤት ሽያጭ ዉልም ይኸዉ የቤት ሽያጭ ዉል ነዉ።
ከላይ በተገለጸዉ መሰረት የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች መኖራቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ የቤት ሽያጭ ዉለ የተፈጸመበት ቀን መቼ ነዉ የሚለዉ እና ተጠሪዎች የቤት ሽያጭ ዉለን የፈጸሙት በቤቱ ላይ የተሰጠዉ እግድ መኖሩንና እግደ አለመነሳቱን እያወቁ ነዉ ወይስ አይደለም ? በቤቱ ላይ የተሰጠ እግድ መኖሩን እያወቁ ወይም እግደ መነሳቱን ሳያረጋግጡ የተፈጸመ ዉል ነዉ የሚባል ከሆነ ዉለ ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለ ጉዲዮች ግራ ቀኙን ያከራከሩ ጭብጦች ናቸዉ።
ዉለ የተፈጸመበትን ቀን በተመለከተ አመልካች ይፍረስልኝ እያለች ያለችዉ የቤት ሽያጭ ዉል 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ የተሰጠዉን የዉክልና ስልጣን በመጠቀም ፈጸመ የተባለዉን የቤት ሽያጭ ዉል በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በቀን 20/01/2008ዓ/ም ያደረኩት የቤት ሽያጭ ዉል እያለ ከዚህ በኋላ የተደረገዉ የቤት ሽያጭ ዉል እንዱፈርስ መጠየቁ ተገቢ አይደለም በሚል የተከራከረ ቢሆንም 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በቀን 20/01/2008ዓ/ም በተደረገ የቤት ሽያጭ ዉል ቤቱን ገዝቻለሁ በሚል ግልጽ ክርክር ያላነሳ በመሆኑ ከዚህ አኳያ 1ኛ ተጠሪ ያቀረበዉን ክርክር አልፈነዋል። አመልካች እንዱፈርስ ዲኝነት የጠየቀችበት ዉል የተፈጸመዉ በቀን 22/05/2010 ዓ/ም ነዉ በማለት የተከራከረች ሲሆን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ በዉለ ሰነድ ላይ ቀን 22/05/2010 ዓ/ም ተብል የተጻፈዉ የዉል ሰነደ የተዘጋጀበት ቀን እንጂ ዉለ የተፈጸመበት ቀን አይደለም ፤ በቀን 22/05/2010 ዓ/ም የተዘጋጀዉ ዉል በዉል አዋዋይ በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ አካል ፉት ተዋዋዮች ፈርመንበት ተረጋግጦ የተመዘገበዉ በቀን 24/05/2010 ዓ/ም በመሆኑ ዉለ እንደተደረገ የሚቆጠረዉ ዉለ በዉል አዋዋይ ፉት ቀርቦ ተፈርሞ በተመዘገበበት ቀን ነዉ በሚል ተከራክረዋል።
ከዚህ አኳያ የቀረበዉን ክርክር መርምሮ የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን ክርክር በመቀበል ዉለ የተፈጸመዉ በቀን 22/05/2010 ዓ/ም በመሆኑና 1ኛ ተጠሪ ደግሞ ለ2ኛ ተጠሪ የዉክልና ስልጣን የሰጠዉ በቀን 23/05/2010 ዓ/ም ነዉ በሚል 3ኛ ተጠሪ የዉክልና ስልጣን ባልተሰጠዉ ጊዜ የቤት ሽያጭ ዉለን መፈጸሙ ዉለን የሚያፈርስ ምክንያት ነዉ ብል የወሰነ ቢሆንም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ማስረጃ መርምሮ የቤት ሽያጭ ዉለ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ባገኙት ዉክልና በቀን 23/05/2010 ዓ/ም ተፈጽሞ ወዱያዉ ዉለ ስልጣን ባለዉ አካል መጽደቁ ተረጋግጧል በሚል የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ ሽሯል። አመልካችም ዉለ በዉል አዋዋይ ተረጋግጦ በቀን 24/05/2010 ዓ/ም አልተመዘገበም (authenticate አልተደረገም) በሚል በግልጽ ክዲ አልተከራከረችም።
እኛም ከዚህ አንጻር የቀረበዉን ክርክር እንደመረመርነዉ እንዱፈርስ ዲኝነት የተጠየቀበት የቤት ሽያጭ ዉል የተፈጸመዉ በሕግ ስልጣን በተሰጠዉ ዉል አዋዋይ ፉት መሆኑ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። በዉል አዋዋይ ፉት ዉል ከሚደረግበት ዓላማዎች መካከል አንደ ዉለ የተደረገበትን እርግጠኛ ቀን ማረጋገጥ ነዉ። በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2015/ሀ ስር በተደነገገዉ መሰረት የሽያጭ ዉል በዉል አዋዋይ ፉት ተደርጎ ከሆነ የሽያጭ ዉለ ተፈጽመ የሚባልበት እርግጠኛ ቀን ዉለ በሕግ ስልጣን በተሰጠዉ ዉል አዋዋይ ፉት ቀርቦ ተረጋግጦ የተመዘገበበት ቀን ነዉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በቀን 23/03/2001 ዓ/ም በተመሳሳይ ጉዲይ አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል። በዚህ መልኩ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሚሰጠዉ ዉሳኔ የፋዳራል ፍርድ ቤቶችን አዋጅ ለማሻሻል በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2/1 መሰረት በየትኛውም ደረጃ ላይ በሚገኙ ፍርድ ቤቶች ዘንድ አስገዲጅነት ያለዉ ነዉ። በዚህ መሰረት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉል በዉል አዋዋይ ፉት ተረጋግጦ የተመዘገበበት ቀን 1ኛ ተጠሪ ለ2ኛ ተጠሪ አከራካሪዉን ቤት የመሸጥ የመለወጥ የዉክልና ስልጣን ከሰጡ በኋላ እንደሆነ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ማስረጃ መርምሮ ያረጋገጠዉ ፍሬ ነገር በመሆኑ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በድጋሚ የሰነድ ማስረጃዎቹን ለመመርመር የሚያስችል ሥልጣን ስለላለዉ ከዚህ አኳያ በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉል የተደረገዉ ለ2ኛ ተጠሪ ዉክልና ከመሰጠቱ በፉት ነዉ በሚል እንደ አንድ የዉል ማፍረሻ ምክንያት የተደረሰበትን ድምዲሜ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሻሩ ተገቢ በመሆኑ በዚህ ረገድ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አላገኘንም።
ተጠሪዎች የቤት ሽያጭ ዉለን የፈጸሙት በቤቱ ላይ የተሰጠዉ እግድ መኖሩንና እግደ አለመነሳቱን እያወቁ ነዉ ወይስ አይደለም ? በቤቱ ላይ የተሰጠ እግድ መኖሩን እያወቁ ወይም እግደ መነሳቱን ሳያረጋግጡ የተፈጸመ ዉል ነዉ የሚባል ከሆነ ዉለ ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለት አከራካሪ ነጥቦች እንደሚከተለዉ መርምረናል።
ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 154 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለዉ በፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ የሚሰጠዉ ተከሳሹ የባለመብቶችን ጥቅም ለመጉዲት ሲል ንብረቱን ለላላ ሰዉ አሳልፍ ለመስጠት ወይም ለመሸጥ ወይም ለማሸሽ ወይም ለማባከን ወዘተ ማቀደ በመሀላ ቃል በተረጋገጠ አቤቱታ በማስረዲት ሲጠየቅ በክርክሩ ሂደት ረቺ ለሚሆነዉ ወገን ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ንብረቱ እንዲለ እንዱቆይ፣ ከመጥፊት እንዱድን፣ እንዲይበላሽ፣ ለላላ ሰዉ ተላልፍ እንዲይሰጥ ገደብ ለመጣል ካለዉ ዓላማ የሚሰጥ ትእዛዝ ነዉ። አንድ ሰዉ በሕግ አግባብ ለላላ ሰዉ ሉያስተላልፍ የሚችለዉ መብት በሕግ ወይም በፍርድ ገደብ ያልተጣለበትና ያለዉ መብት መሆን አለበት።ይህም ማለት ሕግ ጥበቃ የሚያደርገዉ አንድ ሰዉ ያለዉን መብት እና በሕግ ወይም በፍርድ ገደብ ያልተጣለበትን መብት የሚያስተላልፍ ሕጋዊ ተግባር ሲፈጽም ነዉ። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 156/1 ስር በተደነገገዉ መሰረት ደግሞ በፍርድ ቤት የተሰጠዉን የማገጃ ትእዛዝ አለማክበር በወንጀል ሕጉ መሰረት ወንጀል ሆኖ የሚያስቀጣ ተግባር ጭምር ነዉ።
በተያዘዉ ጉዲይ አከራካሪዉ ቤት ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉል ከመሸጡ በፉት የአመልካችና የ1ኛ ተጠሪ የጋራ ሀብት የነበረ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት በአመልካችና በ1ኛ ተጠሪ መካከል በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት በነበረዉ በመ/ በሚታወቅ የጋብቻ ፍቺ ክርክር መዝገብ ላይ እንዲይሸጥ፣እንዲይለወጥ በማናቸዉም መንገድ ለ3ኛ ወገን እንዲይተላለፍ በቀን 03/02/2008 ዓ/ም በተሰጠ የእግድ ትእዛዝ በማሳገዶ ትእዛዙ ለ4ኛ ተጠሪ ደርሶት 4ኛ ተጠሪም እግደን መመዝገቡን ገልጾ በቀን 09/02/2008ዓ/ም በጻፈዉ ምላሽ ለፍርድ ቤቱ አሳዉቋል በማለት ተከራክራለች።ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱ ተጠሪዎች ደግሞ እግደ በተጠቀሰዉ መዝገብ ላይ መሰጠቱንና 4ኛ ተጠሪም እግደን መዝግቤያለሁ ማለቱን አናዉቅም፤ በቤቱ ማህደር ዉሰጥ እግድ አለመያያዙን አጣርተን የፈጸምነዉ ዉል ነዉ በማለት ከመከራከራቸዉ በስተቀር በተጠቀሰዉ መዝገብ ላይ አከራካሪዉ ቤት ታግድ እንዱቆይ እግድ አልተሰጠም በሚል በግልጽ ክደዉ ያሰሙት ክርክር የለም።
እንዱሁም 4ኛ ተጠሪ እግደን እንዱያዉቅ እግደን የሰጠዉ ፍርድ ቤት ባዘዘዉ መሰረት 4ኛ ተጠሪ በቀን 09/02/2008 ዓ/ም ለፍርድ ቤቱ በጻፈዉ ምላሽ በትእዛዙ መሰረት በቤቱ ላይ የተሰጠዉን እግድ መመዝገቡን አሳዉቋል ተብል በአመልካች የቀረበዉን ክርክር ተጠሪዎች ከስር ጀምሮ በዚህ ችልት ጭምር ክደዉ አልተከራከሩም። 4ኛ ተጠሪ በቀን 09/02/2008 ዓ/ም እግደን ለሰጠዉ ለአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት በጻፈዉ ምላሽ በትእዛዙ መሰረት በቤቱ ላይ የተሰጠዉን እግድ መመዝገቡን እንዲረጋገጠ በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረጋግጦ ተወስኖ እያለ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪ ፍርድ ቤቱ አላረጋገጠም በሚል ይህንን የፍርድ ቤቱን ድምዲሜ ሉያፈርስ የሚችል ምንም አግባብነትና ተቀባይነት ያለዉ ማስረጃ በስር ፍርድ ቤት አቅርበዉ ባላስረደበት ያሰሙት ክርክር የሕግ መሰረት ያለዉ አይደለም።
በቤቱ ላይ ተሰጠ የተባለዉ እግድ መኖር አለመኖሩን እንዱሁም እግደ ካለ መነሳት አለመነሳቱን ለማረጋገጥ የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ የተሰጠበት የሆነ መዝገብ አስቀርቦ በመመልከት በመዝገቡ ላይ አከራካሪዉ ቤት እንዲይሸጥ በቀን 03/02/2008 ዓ/ም የእግድ ትእዛዝ መሰጠቱንና ይህም የእግድ ትእዛዝ በልላ ተለዋጭ ትእዛዝ አለመነሳቱን አረጋግጧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዉሳኔዉ ላይ በዚህ መልኩ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተረጋገጠዉ እዉነት እንዲልሆነ ወይም እግደ መነሳቱን ማረጋገጡን በመግለጽ የሰጠዉ ዉሳኔ የለም።
በልላ በኩል እግድ በተሰጠበት መዝገብ ላይ የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ተከራካሪ ወገኖች ባለመሆናቸዉ በመዝገቡ ላይ እግድ መሰጠቱን በቀጥታ ያዉቃለ ተብል ባይገመትም 1ኛ ተጠሪ ግን በመዝገቡ ላይ ተከራካሪ ወገን በመሆናቸዉ 4ኛ ተጠሪ ደግሞ እግደን በመመዝገብ በመሳተፈ (በቤቱ ማህደር እንዱያያዝ ማድረጉ በመረጋገጡ) በቤቱ ላይ የተሰጠዉ እግድ መኖሩን እንደሚያዉቁ ተረድተናል። እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ በዉክልና ስልጣን ቤቱን ለ3ኛ ተጠሪ ሲሸጡ የቤት ሽያጩን በወካይ ስም ስለተዋዋለ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በነበራቸዉ በዚህ ግኝኑነት በቤቱ ላይ ተሰጥቶ የነበረዉን እግድ ያዉቁ እንደነበር ያመላክታል። በተጨማሪም ተጠሪዎች የቤት ሽያጭ ዉል ሲፈጽሙ በቤቱ ላይ የተሰጠ እግድ እንደላለ ከ4ኛ ተጠሪ አረጋግጠን በቅን ልቦና የፈጸምነዉ ዉል ነዉ በሚል ከመከራከራቸዉ በስተቀር በቤቱ ላይ እግድ አልተሰጠም ወይም ተሰጥቶ የነበረዉ እግድ ተነስቷል በሚል ይህንን ክርክራቸዉን የሚደግፍ ማስረጃ ከ4ኛ ተጠሪ ወይም ጉዲዩ ከሚመለከታቸዉ ላላ የአስተዲደር አካላት ተሰጥቶናል በሚል በማስረጃ አስደግፈዉ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን እና በይግባኝ ላዩት ለክልለ ፍርድ ቤቶች ያሰሙት ክርክር ስለመኖሩ የስር ክርክር ግልባጭ አያሳይም።
እንዱሁም የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአከራካሪዉ ቤት ላይ የተሰጠዉን እግድ በሚመለከት እግድ መሰጠቱን፣4ኛ ተጠሪ እግደን መመዝገቡን በመግለጽ እግደን ለሰጠዉ ፍርድ ቤት አሳዉቆ የነበረ መሆኑንና እግደም እንዲልተነሳ እግደ ከተሰጠበት መዝገብና ከቤቱ ማህደር በማረጋገጥ የደረሰበትን ድምዲሜ ሉያስተባብል የሚችል ተቃራኒ ማስረጃ ሳይቀርብለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እግደ ቢኖር እንኳን የቤቱን ማህደር በመመርመር እግድ መኖር አለመኖሩን የማረጋገጥ ኃላፉነት የከተማ አስተዲደሩ እንጂ የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች አይደለም በሚል ቤቱን በዉክልና የሸጠዉም ሆነ የቤቱ ገዥ ቤቱ ከእዲና እገዲ ነጻ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ከሚመለከተዉ አስተዲደር አካል እንዱሰጣቸዉ የማድረግ ኃላፉነት እንደላለባቸዉ አድርጎ በመዉሰድ አንድ ጠንቃቃ ገዥ ሉያደርገዉ የሚገባዉን ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ እንደላለበትና 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪም ከዚህ አኳያ ተገቢ ጥንቃቄ አለማድረጋቸዉን ካመላከተ በኋላ የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በመሻር መወሰኑ የሕግ ድጋፍ ያለዉ አይደለም።
በተጨማሪም ምንም እንኳን አመልካች 1ኛ ተጠሪ ቤቱን መሸጥና ላልች ተግባራትን መፈጸም እንዱችል በቁጥር 5562/2005 በቀን 15/12/2005 ተመዝግቦ በአመልካች ዉክልና የተሰጠዉ ቢሆንም አመልካች በመ/ ላይ ቤቱ እንዲይሸጥ በቀን 03/02/2008 ዓ/ም የእግድ ትእዛዝ ሲያሰጡ ከዚህ የዉክልና ስልጣን ላይ ቤቱን የመሸጥ ፣የመለወጥ እና በማናቸዉም ሁኔታ ወደ 3ኛ ወገን የማስተላለፍ እና እነዚህን ተግባራት ላላ 3ኛ ወገን ወክል ለማስፈጸም የሚያስችል የ1ኛ ተጠሪ የዉክልና ሥልጣን መገደቡን ያሳያል። በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2208 ስር ተወካዩ ከወካዩ ጋር በሚያስተሳስረዉ ግንኙነት ዉስጥ ጥብቅ የሆነ የቅን ልቦና ሉኖረዉ እንደሚገባና የዉክልናዉ ሥልጣን የሚያስቀሩትን ምክንያቶች… ለወካዩ አሳብ ማቅረብና ማሳታወቅ እንዲለበት ተደንግጓል።ከዚህ አንጻር ሲታይ 1ኛ ተጠሪ በአመልካች በተሰጣቸዉ ዉክልና በራሱ በወካይነት ሲሰራም ሆነ 2ኛ ተጠሪ ወክል ሲያሰራ ጥብቅ በሆነ የቅን ልቦና ሉሰራና በተለይም ቤቱን መሸጥ ቢያስፈልግ በቤቱ ላይ የተሰጠዉ እግድ እንዱነሳ ለአመልካች ማሳወቅና እግደ ከተነሳ በኋላ ቤቱ እንዱሸጥ ማድረግ ሲገባዉ በእግደ ምክንያት ቤቱን በራሱ ወይም ላላ ሰዉ ወክል እንዱሸጥ የተሰጠዉ የዉክልና ስልጣን ቀሪ ሆኖ (ተገድቦ) እያለ ለአመልካች ሳያሳዉቅ በ2ኛ ተጠሪ አማካኝነት ቤቱ እንዱሸጥ ማድረጉ ሕጉ የጣለበትን ጥብቅ የሆነ የቅን ልቦና መርህ መጣሱን የሚያሳይ ነዉ። በመሆኑም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ1ኛ ተጠሪን የዉክልና ስልጣን ከዚህ አንጻር ሳይመረምር አመልካች ዉክልናዉን እስካላሻረች ድረስ 1ኛ ተጠሪ በዉክልና ስልጣን በራሱም ሆነ በ2ኛ ተጠሪ አማካኝነት ቤቱን በመሸጥ ያደረገዉ ዉል በጸና ዉክልና የተፈጸመ ዉል በመሆኑ ሉፈርስ አይገባም ሲል የደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሆነ የዉክልና ስልጣን አፈጻጸም ባህርይ ያላገናዘበ በመሆኑሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ።
እንዱሁም ምንም እንኳን ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉል በሕግ ስልጣን በተሰጠዉ ዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ ቢሆንም በዚህ አግባብ በተደረገ ዉል የተሸጠዉ ቤት እንዲይሸጥ እግድ የተሰጠበት በመሆኑና የፍርድ ቤትን እግድ በመጣስ የሚፈጸም ተግባር በወንጀል ጭምር የሚያስጠይቅ ሕገ ወጥ ተግባር በመሆኑ ዉለ በዉል አዋዋይ ፉት መደረጉ ከመነሻዉ ሕገ ወጥ የሆነን ተግባር ሕጋዊ ሉያደርግ የሚችል አይደለም። ሕግ ለግብይት ሥርዓት ጥበቃ የሚያደርገዉ ግብይቱ ሕግን ተከትል ሲፈጸም ብቻ ነዉ። ከላይ እንደተመለከተዉ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በቤቱ ላይ የተላለፈዉ እግድ ጸንቶ እያለና በቤቱ ላይ የተሰጠዉ እግድ ተነስቷል ወይም በቤቱ ማህደር ዉስጥ ተመዝግቦ አይታወቅም የሚል ማረጋገጫ ሳይሰጣቸዉና ይህንን የሚያሳይ ማስረጃ ሳይዙ የቤት ሽያጭ ዉለን በመፈጸማቸዉ ተገቢዉን ጥንቃቄ ሳያደርጉ ለፈጸሙት ግብይት ሕግ ጥበቃ አያደርግላቸዉም። የፍርድ ቤቱን የእግድ ትእዛዝ በመጣስ ወንጀል ጠቀስ ተግባር ተፈጽሞ የተደረጉ ግብይቶች ወይም ዉልች ጸንተዉ እንዱቀጥለ ማድረግ ሕገ ወጥ ተግባራትን በማበረታታት የሕግ የበላይነት እንዱጠፊ የሚያደርግ በመሆኑ ሉታረም ይገባል። እንዱሁም የሚንቀሳቀስ ንብረት ካልሆነ በስተቀር የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ዉል በቅን ልቦና የተደረገ ነዉ ተብል በሕግ ጥበቃ የሚደረግበት የሕግ ስርዓት ስለላለን ከዚህም አንጻር ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱ ተጠሪዎች የሚያነሱት ክርክርና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ቤቱን በቅን ልቦና ስለገዙ የቤት ሽያጭ ዉለ ሉፈርስ አይገባም በሚል መወሰኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።
በልላ በኩል 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በዚህ የሰበር ችልት ደረጃ የቤት ሽያጭ ዉል ከፈጸሙ በኋላ ከብር 1,500,000.00 በላይ የሆነ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ተጨማሪ ግንባታ መፈጸማቸዉን በመግለጽ የተከራከሩ ቢሆንም 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ይህንን ክርክራቸዉን ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ዲኝነት ስልጣንና በይግባኝ ባዩት በክልለ ፍርድ ቤቶች አንስተዉ የተከራከሩ ስለመሆኑ የፍርድ ቤቶቹ ዉሳኔዎች ይዘት አያሳዩም።ይህንን የሚመለከት በማስረጃ ሉረጋገጥ የሚገባ አዱስ የፍሬ ነገር ክርክር በዚህ ችልት ደረጃ አንስተዉ እንዱከራከሩና ችልቱም እንዱህ አይነት ክርክር ሰምቶ እንዱወስን የሚፈቅድ የሕግ ስርዓት የለም። ከዚህ አንጻር ምንም እንኳን 1ኛ ተጠሪ ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ የቤቱ ገዥ ተጨማሪ ግንባታ ፈጽመዋል የሚል ክርክር ያነሳ ቢሆንም እንዱህ አይነት ክርክር 1ኛ ተጠሪ አንስቶ ለመከራከር የሚያስችል መብትና ጥቅም የላለዉ ከመሆኑም በተጨማሪ ስለ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ሆኖ እንዱህ አይነት ክርክር ለማንሳት በስነ ስርዓት ሕጉ የተዘረጋዉ የክርክር አቀራረብ ስርዓት አይፈቅድለትም።በመሆኑም ምን እንኳን በፍ/ብ/ሕጉ ቁጥር 1817/1 ስር ዉል ሲፈርስ ወይም ሲሰረዝ ተዋዋዮች ወደነበሩበት የመመለስ መርህ ተግባራዊ ማድረግ የማይቻል ከሆነ ወይም ለአንደኛዉ ተዋዋይ ከፍተኛ ጉዲት የሚያስከትል ከሆነ ዉለን ለመፈጸም የተከናወኑ ተግባራት ጸንተዉ እንዱቆዩ ላደረግ እንደሚገባ የተደነገገ ቢሆንም 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የተጠቀሰዉን ገንዘብ ያህል ወጪ አድርገዉ ተጨማሪ ግንባታ በመፈጸማቸዉ ዉለን አፍርሶ ወደነበሩበት እንዱመለሱ ማድረግ ከፍተኛ ጉዲት እንደሚያስከትልባቸዉ በመግለጽ በስር ፍርድ ቤቶች የሥነ ስርዓት ሕጉ በሚያዘዉ መሰረት ያቀረቡት ክርክር ባለመኖሩ ከዚህም አኳያ የቀረበዉ ክርክር በሰበር ችልት ደረጃ ላታይ የማይችል ፍሬ ነገርን የሚመለከት ክርክር በመሆኑ አልተቀበልንም።ይህ ማለት ግን 3ኛ ተጠሪ የደረሰባቸዉ ጉዲት ካለ በሚመለከተዉ ሰዉ ላይ ክስ በማቅረብ ከመጠየቅ ይህ ፍርድ ሉያግዲቸዉ አይችልም።
በአጠቃላይ አመልካች በፍርድ ኃይል እንዱፈርስላቸዉ ዲኝነት የጠየቁበት የቤት ሽያጭ ዉል አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በጋብቻ ዉስጥ ያፈሩት በአመልካች ስም ተመዝግቦ የሚገኝና እንዲይሸጥ ፣እንዲይለወጥ እንዱሁም በማናቸዉም መንገድ ለ3ኛ ወገን እንዲይተላለፍ በፍርድ ቤት እግድ በተሰጠበት ቤት ላይ እግደ ሳይነሳ እና እግደ ስለመነሳቱ ሳይረጋገጥ የፍርድ ቤትን የእግድ ትእዛዝ በመተላለፍ ከሕግ ዉጭ የተፈጸመ ዉል መሆኑ ተረጋግጧል። እንዱሁም የቤት ሽያጭ ዉለ በተፈጸመበት ቀን በቤቱ ማህደር ዉስጥ እግደ እንዲልነበረ ወይም ደግሞ የነበረዉ እግድ ተነስቶ እንደነበር የሚያሳይ ከአስተዲደር አካል የተሰጣቸዉን ማስረጃ ተጠሪዎች ለክልለ ፍርድ ቤቶች በማቅረብ ተገቢዉን ጥንቃቄ አድርገዉ የፈጸሙት ግብይት መሆኑን ማስረዲታቸዉን የፍርድ ቤቶቹ ዉሳኔዎች ግልባጭ አያሳይም።4ኛ ተጠሪም መጥሪያ ቢደርሰዉም ከስር ጀምሮ ቀርቦ ባለመከራከሩ የቤት ሽያጭ ዉለ ሲፈጸም በቤቱ ላይ የተሰጠዉ እግድ በአስተዲደሩ አይታወቅም ወይም እግደ ተነስቶ ነበር የሚል ክርክር ከ4ኛ ተጠሪ በኩል አልቀረበም። የሽያጭ ዉለ ከተፈጸመ በኋላ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን ያየዉ የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በቤቱ ማህደር ዉስጥ እግድ መኖሩንና አለመነሳቱን ማህደሩን አስቀርቦ ተመልክቶ ባረጋገጠበት ሁኔታ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በይግባኝ ባየበት ጊዜ የቤቱን ማህደር አስቀርቦ ተመልክቷል ቢባል እንኳን አስቀርቦ በተመለከተበት ጊዜ በማህደሩ ዉስጥ እግደ አለመኖሩ ቤቱ በተሸጠበት ጊዜ በማህደሩ ዉስጥ እግደ አልነበረም ወደሚል ድምዲሜ የሚያደርስ ባለሆነበት በዚህ ምክንያት ዉለ ሉፈርስ አይገባም በማለት መወሰኑ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል።ስለሆነም በቤቱ ላይ የተፈጸመዉ የቤት ሽያጭ ዉል በቤቱ ላይ የተሰጠዉ እግድ ጸንቶ እያለ የተፈጸመ በመሆኑ በሕግና በፍርድ ጥበቃ የተደረገለትን አመልካች በቤቱ ላይ ያላቸዉን የባለቤትነት መብት የሚያሳጣ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር1808/2 መሰረት ሉፈርስ ይገባል ሲል የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ ሆኖ እያለ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ዉለ ሉፈርስ አይገባም ብል መሻሩና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ስህተቱን ማረም ሲገባዉ የቀረበለትን የሰበር አቤቱታ በትእዛዝ መዝጋቱ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 03/08/2011ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 30/08/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 07/03/2011 ዓ/ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት በተደረገ ክርክር መነሻ ያወጡትን ወጪ የየራሳቸዉን እንዱችለ ወስነናል።
ትእዛዝ
በዚህ መዝገብ ላይ በቀን 08/11/2011 ዓ/ም በዋለዉ ችልት በተሰጠ ትእዛዝ በአዲማ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ እየታየ ያለዉ አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ የተሰጠዉ ትእዛዝ ተነስቶ በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 07/03/2011 ዓ/ም በተሰጠ ዉሳኔ መሰረት እንዱፈጸም ታዟል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.