የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የሚደረግ የሽያጭ ዉል ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ መመዝገብ እንዲለበት ህጉ ሲደነግግ ገዥዉ ዉለ እንዱመዘገብ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ሲቀርብ ንብረቱ በሻጭ ስም መመዝገብ አለመመዝገቡን ወይም ሻጩ ዉለን ለማድረግ ህጋዊ መብት ያለዉ መሆን አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን በንብረቱ ላይ ዕዲ እና እገዲ አቶ ሶሪ ጉተማ እና እነ ወ/ሮ ሀረገወይን ተ/ጽዮን (2 ሰዎች) መሆን ያለመሆኑንም ለማጣራት ዕድል ያገኛል በሚል በመሆኑ ማንኛዉም ጠንቃቃ ገዥ ዉል ሲዋዋል ተገቢዉን ጥንቃቄ እንዱያደርግ የሚጠበቅበት ስለመሆኑ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት የሆነ ቤት ያለ አንደኛው ተጋቢ ፉቃድና ስምምነት ለሦስተኛ ወገን እንዲይተላለፍ በፍርድ ቤት አስቀድሞ እግድ የተሰጠበት ስለመሆኑ ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ ተረጋግጦ እያለ፣ የሽያጭ ዉለም መመዝገቡም ሆነ የሚመለከተዉ አካል ዉለን ሲመዘግብ ወይም ሲያረጋግጥ ተገቢዉን ጥንቃቄ ሳያደርግ ቤት በሽያጭ በመተላለፈ የገዛ ሰው እንደ አንድ ጠንቃቃ ገዥ ማድረግ የሚገባዉን ጥንቃቄ አለማድረጉን የሚያሳይና አስቀድሞ የተቋቋመ የላላ ሰዉ መብትና ጥቅም ያለበትን የማይንቀሳቀስ ንብረት በመግዛት የተደረገ ዉል ጸንቶ የማይቀጥል ስለመሆኑ የፍትሐ ብሓር ህግ አንቀጽ 1543-1566 እና 1185
No summary available.
የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- አቶ ሶሪ ጉተማ ተጠሪዎች-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገ ዉል በህግ ተቀባይነት ባለዉ ምክንያት ሉፈርስ ወይም ዉለ ዉጤት እንዲይኖረዉ ላደረግ የሚችልበት ሁኔታ ቢኖርም የሦስተኛ ወገንን መብትና ጥቅም ለመጠበቅ ሲባል ጸንቶ ሉቀር የሚችልበትን ሁኔታ የሚመለከት ነዉ።
ክርክሩ የተጀመረው በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ለፍርድ ቤቱ ያቀረበዉን የመቃወም አቤቱታ መነሻ ያደረገ ነዉ። አመልካች ያቀረበዉ የመቃወም አቤቱታ ይዘትም በተጠሪዎች መካከል የነበረዉ ጋብቻ በፍርድ ቤት መፍረሱን ተከትል በተደረገ የንብረት ክርክር የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የተጠሪዎች የጋራ ሀብት ናቸዉ ተብለዉ ዉሳኔ ከሰጠባቸዉ ዉስጥ በሻሸመኔ ከተማ አላለ ቀበላ 10 ውስጥ በ2ኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚታወቅ ቤት 20/07/2009 ዓ.ም በተፃፈ ውል በብር 410,000.00 ከ2ኛ ተጠሪ ወኪል ገዝቼ ዉለም በከተማው አስተዲደር ውል ምዝገባ ክፍል ቀርቦ ከተረጋገጠ በኋላ ስመ ንብረቱ በስሜ ዞሮ ማስረጃ ተሰጥቶኝ እና ተጨማሪ ገንዘብ አውጥቼ ቤት ሰርቼበት አየተጠቀምኩበት እያለ ቤቱ የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ስለሆነ ይካፈለት ተብል መወሰኑ መብቴን ስለሚነካ ውሳኔው ይሻርልኝ የሚል ነዉ።
1ኛ ተጠሪ ለመቃወም አቤቱታዉ በሰጡት መልስ ቤቱ የተጠሪዎች የጋራ ንብረት እንጂ የአመልካች አይደለም፤ ቤቱ ስለመሸጡም አላውቅም። ቤቱ ለአመልካች በሽያጭ ተላልፎል የተባለው በቀን 29/09/2009 ዓ.ም ሲሆን ቤቱ በፍርድ ቤት የታገደው ደግሞ በቀን 22/07/2007 ዓ.ም ነው። 2ኛ ተጠሪ ንብረቱ መታገደን እያወቀ በጋራ ያፈራነውን ሀብት ሉያሳጣኝ ሲል ሆን ብል እንዱሸጥ ያደረገ እና ውለን ያዋዋለው አካልም ቤቱ የታገደ መሆኑን እያወቀ እንዱሸጥ ማድረጉ ተገቢ ስላልሆነ የአመልካች ተቃውሞ ውድቅ ላደረግ ይገባዋል በማለት ተከራክራለች። 2ኛ ተጠሪ በበኩለ እኔና 1ኛ ተጠሪ በ 2005 ዓ.ም ቤቱን ወ/ሮ ቤሩት ቀነዓ ለምትባል ግለሰብ በብር 80,000.00 በመሸጥ ገንዘቡንም ለቤተሰብ ጥቅም ያዋልነው ሲሆን 1ኛ ተጠሪ በውለ ላይ ባትፈርምም መሸጡን ታውቃለች። ቤቱ ከተሸጠ በኋላ የእኔና የ1ኛ ተጠሪ ጋብቻ በቀን 29/02/2006 ዓ.ም በፍርድ ቤት ውሳኔ የፈረሰ ሲሆን የቤቱ ስመ ንብረት ሳይዘዋወር 1ኛ ተጠሪ ቤቱ እንዱታገድ ያደረገች ሲሆን ቤቱ መሸጡን 1ኛ ተጠሪ ታውቃለች። ፍርድ ቤቱ እግደን በቀን 26/06/2007 ዓ.ም ሲያነሳ ስመ ንብረቱን ለማዞር እንዱቻል ቤቱን በመጀመሪያ ለገዛችን ግለሰብ ሙለ ውክልና ሰጥቻት፣ እሷም ለላላ ግለሰብ ውክልና ሰጥታ ቤቱን ለአመልካች ተሸጠ እንጂ እኔ ከአመልካች ጋር ግንኙነት የለኝም። ስምምነቱ ሉፈርስ የሚገባበት ምክንያት የለም። በአቤቱታው መሰረት ለአመልካች ቢወሰንለት ተቃውሞ የለኝም በማለት ተከራክሯል።
የመቃወም አቤቱታዉ የቀረበለት የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶ እንዱሁም ከሚመለከታቸዉ አካላት ተጨማሪ ማስረጃ አስቀርቦ ከመረመረ በኋላ የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት ስለመሆኑ እና 2ኛ ተጠሪ ቤቱ ተሽጦ ለቤተሰቡ የጋራ ጥቅም ስለመዋለ አለማስረዲቱ ተረጋግጦ ተወስኖ እያለ እና ቤቱ እንዲይሸጥ እንዲይለወጥም ታግድ እያለ 2ኛ ተጠሪ ለ3ኛ ወገን ውክልና ሰጥቶ ቤቱ በወኪልቹ አማካኝነት እንዱሸጥ ማድረጉ ያላግባብ ነው፤ ቤቱ የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ነው በማለት የአመልካችን የመቃወም አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘው አመልካች የይግባኝ አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። በመቀጠል የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበ ቢሆንም ውድቅ ተደርጎበታል ። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 26/03/2012 ዓ.ም በተፃፈ 04 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈፅመዋል ያላቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ሰበር ችልት እንዱታረሙለት ጠይቋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም በአጭሩ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ጅምር ቤት በምገዛበት ወቅት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የታገደ መሆኑን የማላውቅ ሲሆን እግድ መኖሩን ማረጋገጥ ህጋዊ ግዳታ ያለበት ሰነድ አረጋጋጩ ሲሆን ለሚደርሰው ጉዲትም ሃላፉነቱን የሚወስደው ይኸው አካል መሆን ሲገባው በቅን ልቦና እና በህጋዊ መንገድ ቤቱን የገዛሁትን አመልካችን የሚጎዲ ውሳኔ በስር ፍርድ ቤቶች መሰጠቱ፤
ተጠሪዎች የውለን አደራረግ ፍርማሉቲ በሚመለከት ክርክር ሳያቀርቡ የስር ፍርድ ቤቶች በራሳቸው ተነሳሽነት በማንሳት መወሰናቸው፤ እንዱሁም ውለ አመልካች እና ተጠሪ በመመሳጠር የፈፀሙት የሽያጭ ዉል ነው የሚል ክርክር በተጠሪዎች ሳይቀርብ የስር ፍርድ ቤቶች ውለ በክፈ ልቦና የተፈፀመ ነው በማለት የደረሱበት መደምደሚያ ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸውን ክርክር በህግ እና በማስረጃ የማጣራት ሃላፉነት አለባቸዉ የሚለዉን መርህ ያልተከተለ በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታዉም በአጣሪ ችልት ተመርምሮ አከራካሪዉን ቤት አመልካች ውክልና ካለው ግለሰብ ላይ ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፉት በተደረገ ውል የገዛ መሆኑን ገልፆ እየተከራከረ የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ስለሆነ ውለ ሉፈርስ ይገባል የመባለን አግባብነት ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ያስቀርባል ተብሎል። በዚህም መሰረት 1ኛ ተጠሪ ባቀረበችው መልስ አመልካች ቤቱ እግድ እያለበት በህገ-ወጥ መንገድ ገዝቶ እያለ ውለ በውል አዋዋይ ፉት የተደረገ በመሆኑ ሉጸና ይገባል ቢልም ይህ ብቻውን ውለን ህጋዊ አያደርገውም፤ ውለ የተፈፀመውም ከቅን ልቦና ዉጪ 1ኛ ተጠሪን ለመጉዲት ታስቦ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሉፀና ይገባዋል በማለት ተከራክራለች። 2ኛ ተጠሪ በበኩለ በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር ላይ የሰጠውን መልስ በማጠናከር ቤቱ ሲሸጥ እግድ እንደላለበት፤ 1ኛ ተጠሪ በውለ ላይ ባትፈርምም በጋራ የሸጥነው በመሆኑ አመልካች ባቀረበው አቤቱታ መሰረት ቢወሰንለት ተቃውሞ የለኝም በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ ሰጥቶ ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት የተጠሪዎች የጋራ ንብረት የነበረ መሆኑ አላከራከረም። አመልካች በመቃወም አቤቱታዉ ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ያደረገዉ ቤቱን መጋቢት 20 ቀን 2009 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ዉል ከ2ኛ ተጠሪ ወኪል መግዛቱንና ዉለንም በሚመለከተዉ አካል ዘንድ አስመዝግቦ የቤቱም ስመ ሀብት ወደ ስሙ ተዛዉሮ ማስረጃ የተሰጠዉ መሆኑን ነዉ። በልላ በኩል በተጠሪዎች መካከል ሲደረግ በነበረዉ የባልና ሚስት ንብረት ክርክር መነሻነት ቀደም ሲል በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት ቤቱን አስመልክቶ በፍርድ ቤቱ ተሰጥቶ የነበረዉ የእግድ ትዕዛዝ ክርክሩ በዉሳኔ መቋጨቱን ተከትል መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ.ም የተነሳ ቢሆንም ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 24 ቀን 2007 ዓ.ም በሰጠዉ ትዕዛዝ ቤቱ ለሦስተኛ ወገን እንዲይተላለፍ በድጋሚ እግድ የሰጠበት ስለመሆኑ በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ሲሆን፣ አመልካችም በዚህ ችልት ባቀረበዉ አቤቱታ ይህን ክድ አይከራከርም። ይህም የሚያሳየዉ አመልካች ቤቱን የገዛዉ እግድ እያለበት መሆኑን ነዉ። አመልካች ይህን ሳይክድ፣ በተለይም ለዚህ ችልት ባቀረበዉ አቤቱታ፣ አጥብቆ የሚከራከረዉ ዉለ ሲደረግ ቤቱ እግድ እንዲለበት እንደማያዉቅ፤ ዉለንም በሚመለከተዉ አካል ዘንድ አስመዝግቦ ተጨማሪ ግንባታ ማካሄደን፣ ይህ በሆነበት ሁኔታ ዉለ ሉፈርስ ይገባል መባለ ያላግባብ መሆኑንና ቤቱ እግድ እያለበት መሸጡ ዉለን ከመመዝገቡ በፉት እግድ ያለበት መሆን ያለመሆኑን የማጣራት በህግ ግዳታ ያለበት አካል ይህን ግዳታዉን ባለመወጣት ዉለን ያረጋገጠዉ አካል ኃላፉነቱን እንዱወስድ ምክንያት ከሚሆን በቀር ዉለን ለማፍረስ ምክንያት ላሆን አይገባም በማለት ነዉ። በዚህም መነሻነት የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሻዉ ጭብጥ ቤቱ ለሦስተኛ ወገን እንዲይተላለፍ በፍርድ ቤት የተሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ ተያይዞ እያለ ቤቱን ለአመልካች ለማስተላለፍ የተደረገዉ ዉል በሚመለከተዉ አካል ዘንድ በመመዝገቡ ብቻ ዉለ ጸንቶ አመልካች የቤቱ ባለቤት ሆኖ ሉቀጥል የሚችልበት ሁኔታ መኖር ያለመኖሩ ነዉ።
ከላይ እንደተገለጸዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት የተጠሪዎች የጋራ ንብረት የነበረ ስለመሆኑ ያላከራከረ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት በኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 84(ሀ) መሰረት ያለ 1ኛ ተጠሪ ስምምነት እና ፍቃድ 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ብቻዉን ለማስተላለፍ መብት የላለዉ በመሆኑ አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ባደረገዉ ዉል መሰረት በገዛዉ ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ ቤት ላይ ባለቤት ሆኖ መቀጠል የሚችል መሆን ያለመሆኑን የመወሰኑ ጉዲይ ለዉለ ሦስተኛ ወገን የሆነችዉንና ከቤቱ ድርሻ ያላትን የ1ኛ ተጠሪን የባለቤትነት መብትና ጥቅም ግምት ዉስጥ ባስገባ መልኩ ላሆን ይገባል። የንብረት ባለቤትነት መብት ከሁለ የሰፊ መብት ሲሆን፣ ይህም መብት ያላግባብ የተያዘን ወይም ለላላ ሰዉ የተላለፈን ንብረት ለማስመለስ ክስ የማቅረብ መብትን እንደሚያጠቃልል በህጉ አንቀጽ 1204(1) እና 1206 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። በተያዘዉ ጉዲይ ምንም እንኳ 1ኛ ተጠሪ በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ ዉል እንዱፈርስ የጠየቀችዉ ዲኝነት ባይኖርም አመልካች በቤቱ ላይ መብት የለዉም፤ ቤቱ የእኔ እና የ2ኛ ተጠሪ ነዉ በማለት የምትከራከረዉ የጋራቸዉ በሆነዉ ቤት ላይ 2ኛ ተጠሪ ብቻዉን መወሰን የማይችል መሆኑንና በዚህም ምክንያት አመልካች የቤቱ ባለቤት እኔ ነኝ ሲል ያቀረበዉ ዉል ህጋዊ ዉጤት የማያስከትል መሆኑን በመግለጽ ነዉ። 1ኛ ተጠሪ ከቤቱ ድርሻ ያላት መሆኑ እንዱሁም ያለ እርሷ ስምምነት ለአመልካች በዉል የተላለፈ መሆኑ ከተረጋገጠ በመርህ ደረጃ ዉለ ህጋዊ ዉጤት የላለዉ ሲሆን፣ በልዩ ሁኔታ ዉለ ህጋዊ ዉጤት ኖሮት አመልካች የንብረቱ ባለቤት ሆኖ ሉቀጥል የሚችለዉ የሽያጭ ዉለን ያደረገዉ ሻጩ የቤቱን ባለቤትነት ለማስተላለፍ የሚያስችለዉ ህጋዊ መብት ያለዉ መሆኑን እንዱሁም ንብረቱ የ3ኛ ወገን መብት ወይም ጥቅም የላለበት መሆኑን እንደ አንድ ጠንቃቃ ገዥ ተገቢዉን ጥንቃቄ ሁለ በማድረግ መሆኑ ሲረጋገጥ ነዉ። ከዚህ ጀርባ ያለዉ የፖሉሲ ምክንያትም ንብረቱ የሻጭ መሆኑን በማመን መግዛቱ ከተረጋገጠ ዉለ እንዲይፈርስ ወይም ንብረቱን የገዛዉ ሰዉ በዉለ ባገኘዉ መብት መሰረት የንብረቱ ባለቤት ሆኖ እንዱቀጥል በማድረግ ግብይቶች ዋስትና እንዱያገኙ ለማድረግ እንደሆነ ይታመናል።
በመሆኑም እንደዚህ ዓይነት ክርክር የቀረበለት ፍርድ ቤት በአንድ በኩል ባለ ሀብቱ በንብረቱ ላይ ያለዉን ከሁለ የሰፊ መብት (widest right) ያላግባብ እንዲያጣ፣ በልላ በኩል ገዥዉ ንብረቱን የገዛዉ ተገቢዉን ጥንቃቄ አድርጎ በርግጥም ንብረቱ የሻጩ ነዉ በሚል ወይም የላላ ሰዉ መብትና ጥቅም የለበትም በሚል እምነት መሆኑ ከተረጋገጠ በተቻለ መጠን ዉለ እንዲይፈርስ በማድረግ ግብይቶች ዋስትና (security of transactions) እንዱያገኙ በማድረግ ሁለቱንም ተወዲዲሪ ጥቅሞች (computing interests) አመዛዝኖ ዉሳኔ ላይ የመድረስ ኃላፉነት ይኖርበታል። ግዥዉ የተፈጸመዉ ተገቢዉ ጥንቃቄ ተደርጎ ነዉ በሚል ምክንያት ዉለ ጸንቶ እንዱቀጥል የሚደረገዉ የገዥዉ መብት ከባለንብረቱ፣ ወይም አስቀድሞ በንብረቱ ላይ መብትና ጥቅም ካገኘዉ ሰዉ፣ በላይ በመሆኑ ሳይሆን የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚደረጉ ግብይቶች ጥያቄ ዉስጥ እንዲይገቡ ጥበቃ በማድረግ አጠቃላይ የማህበረሰቡን (general public interest) ጥቅም ለማረጋገጥ በመሆኑ የማጣራቱ ሂደት ይህን ሁለ ግምት ዉስጥ ባስገባ መልኩ በጥንቃቄ ሉከናወን ይገባል። ንብረቱን የገዛ ሰዉ እንዱያደርግ የሚጠበቅበት የጥንቃቄ ደረጃ እስከምን ድረስ ነዉ? የሚለዉን መለየቱ ቀላል ባይሆንም፣ በተለይም የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚገዛ ሰዉ ንብረቱን ከመግዛቱ በፉት ንብረቱ እርሱ የሚፈልገዉ ዓይነት መሆኑን ብልም በርግጥም የሻጩ መሆኑን ወይም ሻጩ ንብረቱን ለመሸጥ በህግ ስልጣን ያለዉ መሆን ያለመሆኑን ለማረጋገጥ ተገቢዉን ሁለ ካደረገ በኋላ የገዛ ስለመሆኑ የተለያዩ አካባቢያዊ ሁኔታዎችን ግምት ዉስጥ በማስገባት መመዘን ያስፈልጋል። የተሸጠዉ ንብረት የሦስተኛ ወገን መብትና ጥቅም ያለበት መሆኑ ከተረጋገጠ፣ ቤቱን የገዛዉ ተገቢዉን ጥንቃቄ አድርጎ መግዛቱን የማስረዲቱ ሸክም የገዥዉ እንጂ የባለንብረቱ ወይም ከንብረቱ መብትና ጥቅም አለኝ የሚል ወገን አለመሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል። ጠንቃቃ ገዥ በሚል መስፈርት የሦስተኛ ወገንን ንብረት በሻጭ ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል ጸንቶ እንዱቀጥል ወይም ገዥዉ የንብረቱ ባለቤት ሆኖ እንዱቀጥል የሚደረገዉ በልዩ ሁኔታ (exception) በመሆኑ በጠባቡ መተርጎም እንዲለበትም ይታመናል።
ከስሙም መረዲት እንደሚቻለዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት በባህርዉ በሆነ ቦታ ላይ ተወስኖ የሚቆይ ንብረት (fixed asset) በመሆኑ ከአንድ ቦታ ወደ ላላ ቦታ ማንቀሳቀስ ስለማይቻል ጥበቃ የሚያገኘዉ በምዝገባ እንደሆነ ይታወቃል። በዚህም መሰረት የአገራችን የፍትሐብሕር ፍትሕ ሥርዓት የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባ ለዜጎች የንብረት መብት ጥበቃ ከማድረግ አንፃር ፊይዲዉ የጎላ ስለመሆኑ ግምት ዉስጥ በማስገባት በፍትሐብሕር ህጉ የተለያዩ አንቀፆቹ ስለ ምዝገባ ይደነግጋል (አንቀጽ 1553-1646 እንዱሁም 1723፣ 2878 እና 3052 ይመለከቷል)። የህጉ አንቀጽ 10 (Title 10) በተለይ ሲታይ በመሰረታዊነት ሁለት የምዝገባ ዓይነቶች እንዲለ የሚያስገነዝብ ነዉ፤ አንደኛዉ የህጋዉያን ተግባራት ምዝገባ (registration of juridical acts) ሲሆን ሁለተኛዉ የባለቤትነት ምዝገባ (registration of ownership) ናቸዉ። የመጀመሪያዉ ዓይነት ምዝገባ የሽያጭ ዉልን ጨምሮ የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚቋቋሙትን የተለያዩ መብቶችና ግዳታዎችን የሚመለከት ነዉ (በህጉ ከአንቀጽ 1567-1574 ይመለከቷል)። ይህ እንደ አጠቃላይ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ዉል በሦስተኛ ወገን ላይ መቃወሚያ ይሆን ዘንድ ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ መመዝገብ እንዲለበት የህጉ አንቀጽ 2878 ድንጋጌ ያስገነዝባል። እነዚህ ድንጋጌዎች የየራሳቸዉ የሆኑ ዓላማዎች የሚኖሩት ቢሆንም፤ አጠቃላይ ዓላማቸዉ ግን ለማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ልዩ ጥበቃ በመስጠት እነዚህን ንብረቶች በተመለከተ ባለይዞታዉ መብቱን ሲያገኝ ወይም ንብረቱ በሆነ ምክንያት ወደ ላላ ሦስተኛ ወገን በሚያስተላልፍበት ወቅት የመመዝገብ ስልጣን በተሰጠዉ መንግስታዊ አካል ካልተመዘገበ ህግ ፉት የሚጸና መብት እንዲይኖረዉ በማድረግ ዜጎች በዚህ ግዙፍነት ያለዉ ንብረት ያላቸዉን መብት ከፍላጎታቸዉ ዉጪ በሆነ መንገድ እንዲያጡ ጥበቃ ለመስጠት፤ ብልም ንብረቱን የሚገዛ ወይም በንብረቱ ላይ ማናቸዉንም መብት ማቋቋም የሚፈልግ ሦስተኛ ወገን ንብረቱ ያለበትን ሁኔታ ወይም በንብረቱ ላይ አስቀድሞ የተቋቋመ መብትና ግዳታ መኖር አለመኖሩን እንዱያዉቅ ለማድረግ ነዉ።
ስለሆነም ከማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባ እና የሚያስከትለዉን ዉጤት በተመለከተ የሚደረግ ክርክር ይህንኑ ከግምት ዉስጥ ባስገባ መልኩ እልባት ሉሰጠዉ ይገባል።
በተያዘዉ ጉዲይ ከላይ እንደተገለጸዉ አመልካች ቤቱን ከመግዛቱ አስቀድሞ ቤቱ ለሦስተኛ ወገን እንዲይተላለፍ በፍርድ ቤት ታግዶል። የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባን አስመልክቶ ከላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ታሳቢ የሚያደርጉት የሚመለከታቸዉ አካላት ምዝገባዉን ሲያከናዉኑ በህግ አግባብ እንዱያደርጉ የሚጠበቅባቸዉ ጥንቃቄ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከንብረቱ መብትና ጥቅም የተላለፈለት ሰዉም ለንብረቱ መተላለፍ ምክንያት የሆነዉን ህጋዊ ተግባር (juridical act) እንዱሁም የባለቤትነት መብቱን ሲያስመዘግብ (አንቀጽ 1543-1566 እና 1185 ማየት ይቻላል) በንብረቱ ላይ አስቀድሞ የተቋቋመ መብት ወይም ጥቅም ወይም ንብረቱ ለላላ እንዲይተላለፍ የሚከለክል ወይም የንብረቱን መተላለፍ አጠራጣሪ የሚያደርገዉ ሰነድ ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ዉስጥ የሚገኝ መሆን ያለመሆኑን በጥንቃቄ የማጣራት ኃላፉነት ያለበት መሆኑን ነዉ። የፍትሐብሕር ህጉ በአንቀጽ 1561 ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገቦች ለህዝብ ግልጽ መሆን እንዲለባቸዉ የደነገገዉም በዚሁ ምክንያት እንደሆነ ይታመናል። ስለሆነም የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የሚደረግ የሽያጭ ዉል ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ መመዝገብ እንዲለበት ህጉ ሲደነግግ ገዥዉ ዉለ እንዱመዘገብ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ሲቀርብ ንብረቱ በሻጭ ስም መመዝገብ አለመመዝገቡን ወይም ሻጩ ዉለን ለማድረግ ህጋዊ መብት ያለዉ መሆን አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን በንብረቱ ላይ ዕዲ እና እገዲ ያለበት መሆን ያለመሆኑንም ለማጣራት ዕድል ያገኛል በሚል መነሻ እንደሆነ መገንዘቡ ተገቢ ነዉ። ይህ ማንኛዉም ጠንቃቃ ገዥ እንዱያደርግ የሚጠበቅበት ነዉ። በልላ በኩል ንብረቱ አስቀድሞ ለላላ ሰዉ የተላለፈ መሆኑን ወይም ሻጩ የንብረቱን ባለቤትነት ለማስተላለፍ የሚያስችለዉ ሙለ መብት እንደለላዉ ወይም ንብረቱ እዲ እና እገዲ ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ እያለ ይህን ሳያረጋግጥ ዉለን በንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ ያስመዘገበ ሰዉ ከአንድ ጠንቃቃ ገዥ የሚጠበቀዉን ጥንቃቄ ላለማድረጉ አመላካች ነዉ። በዚህም ምክንያት የህግ ጥበቃ የማይሰጠዉ በመሆኑ ዉለ ጸንቶ የሚቀጥልበት ወይም በዉለ መሰረት ባገኘዉ ንብረት ላይ ባለሀብት ሆኖ ሉቀጥል የሚችልበት ሁኔታ ጥያቄ ዉስጥ የሚገባ ነዉ።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ አመልካች የሽያጭ ዉለን ከማድረጉ በፉት ቤቱ ወደ ሦስተኛ ወገን እንዲይተላለፍ በፍርድ ቤት የተሰጠ እግድ ከመዝገቡ ጋር የተያያዘ መሆኑ ተረጋግጧል፤
አመልካች እንደ አንድ ጠንቃቃ ገዥ ዉለን ከማድረጉ በፉት ከቤቱ ጋር በተያያዘ ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ የተመለከቱትን ሰነድች ማየት ቢችል ኖሮ በቤቱ ላይ እግድ መኖሩን በቀላለ ይደርስበት ነበር። ይህን ማድረግ ሲገባዉ የሽያጭ ዉለን ማድረጉ አመልካች አንድ ጠንቃቃ ገዥ እንዱያደርግ የሚጠበቅበትን ግዳታ አለመወጣቱን የሚያሳይ ነዉ። ይህ በሆነበት ሁኔታ ዉለ መመዝገቡ ብቻዉን አመልካች ዉለን ሲያደርግ ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረጉን የሚያሳይ ባለመሆኑ በዉለ ምክንያት የቤቱ ባለቤት ሆኖ ሉቀጥል የሚችልበት ሁኔታ የለም። ዉለ መመዝገቡም ሆነ የሚመለከተዉ አካል ዉለን ሲመዘግብ ወይም ሲያረጋግጥ ተገቢዉን ጥንቃቄ አለማድረጉ ዉለ እንዱጸና ምክንያት ላሆን አይችልም። ስለሆነም አመልካች በዚህ ረገድ የሚያቀርበዉ መከራከሪያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባ አስፈላጊ የሆነበትን መሰረታዊ ዓላማ እንዱሁም አስቀድሞ የተቋቋመ የላላ ሰዉ መብትና ጥቅም ያለበትን የማይንቀሳቀስ ንብረት በመግዛት የተደረገ ዉል ጸንቶ ሉቀጥል የሚችልበትን ሁኔታ ከግምት ዉስጥ ያስገባ ባለመሆኑ ተቀባይነት ያለዉ ክርክር ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ሆኖ ያለ 1ኛ ተጠሪ ፉቃድና ስምምነት ለአመልካች በሽያጭ የተላለፈ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ንብረቱ አስቀድሞ እግድ የተሰጠበት ስለመሆኑ ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ እያለ አመልካች ቤቱን መግዛቱ እንደ አንድ ጠንቃቃ ገዥ ማድረግ የሚገባዉን ጥንቃቄ አለማድረጉን የሚያሳይ በመሆኑ ዉለ ጸንቶ የማይቀጥል በመሆኑ እና በዚህም ምክንያት አመልካች የቤቱ ባለቤት ሆኖ ሉቀጥል የሚችልበት የህግ ምክንያት ባለመኖሩ የአመልካችን የመቃወም አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በትዕዛዝ የጸናዉ ዉሳኔ በአግባቡ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 10/08/2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፣ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 13/10/2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ችልት እንዱሁም ሰበር ሰሚዉ ችልት በቀን 02/03/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንተዋል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.