በፍትሐ ብሓር ህግ አንቀጽ 1179 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ተፈፃሚነት የሚኖረዉ በባለይዞታዉ እና ይዞታዉን ይዞ ቤት በሰራ ሰዉ መካከል የታወቀ ግንኙነት በላለበት ሁኔታ ብቻ በመሆኑ የባድ ቦታ ሽያጭ ዉል መፍረሰን ተከትል በቦታዉ ላይ የተሰራ ቤት ህጋዊ ዉጤትን አስመልክቶ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉ የፍትሐ ብሓር ህግ አንቀጽ 1818 እነ ወ/ሮ ትርንጎ ገመቹ (3 ሰዎች) እና እነ ወ/ሮ ብርሀኔ ገመቹ (2 ሰዎች)
No summary available.
የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ይህ ጉዲይ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ ከተደረገ ዉል ይዘት ጋር በተገናኘ ክርክር ሲኖር የዉለን ይዘት ለማስረዲት ላቀርብ የሚገባዉን ማስረጃ የሚመለከት ነዉ።
የጉዲዩም መነሻ የአሁን ተጠሪዎች ከሳሽ በመሆን በአመልካቾች ባቀረቡት ክስ በሟች እናታችን ወ/ሮ ነዱ ሆርድፊ ስም በሱለልታ ከተማ ቀሶ ወሰርቢ ቀበላ ልዩ ቦታው ሹፈኔ ተብል ከሚጠራው ስር የሚገኝ መጠኑ 1.260 ሄክታር የሆነውን መሬት 1ኛ አመልካች እና ከላላዋ እህታችን ወርቄ ገመቹ ጋር በውርስ አግኝተን በቀን 01/06/2005 ዓ.ም ባደረግነው የውል ስምምነት እያንዲንዲችን 2565 ካ.ሜ ደርሶን የተከፊፈልን ቢሆንም በግንቦት ወር 2007 ዓ.ም 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች እንዱሁም የስር 2ኛ ተከሳሽ የነበሩ ግለሰብ በተጠሪዎች ድርሻ ላይ አጥር ሰርተው ይዘውብናል፤ ይዞታችንን ለምን እንደያዙ ብንጠይቃቸው ከ1ኛ አመልካች ላይ ገዝተው እንደሆነና የስር 5ኛ ተከሳሽ የነበረው የሱለልታ ከተማ አስተዲደርም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንደሰጣቸው ገልጸውልናል። ውለን እንዱያሳዩን ስንጠይቃቸው እኛም በ9500 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ያለውን ባለ 30 ቆርቆሮ ቤት እንደሸጥንላቸው የሚያሳይ በሀሰት የተዘጋጀ በቀን 02/08/2002 ዓ.ም የተፃፈ ውል ይዘው ቀርበዋል። በቀን 28/04/2007 ዓ.ም 1ኛ አመልካች መሬቱን መንግስት ለልማት ስለሚፈልገው ካሳ ለመውሰድ ቅጽ መሙላች አለባችሁ በማለት ጠርታን የተለያዩ ወረቀቶች ላይ የፈረምን ሲሆን አመልካቾች ያቀረቡት ውል ላይ ያለው ፊርማ የእኛ ሆኖ እንኳን ቢገኝ ተጭበርብረን የፈረምነው እና ሽያጩም ባድ መሬትን የሚመለከት በመሆኑ ህገ-ወጥ ስለሆነ ውለ ተሰርዞ መሬታችንን እንዱለቁ ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካቾች በሰጡት መልስ 1ኛ አመልካች ከተጠሪዎች ጋር ያደረግኩት ውል ስለላለ በእኔ ላይ የቀረበው ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት፣ 2ኛ አመልካች ዉለ ከተደረገ ሰባት ዓመት ስለሞላው ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት፣ 3ኛ አመልካች ደግሞ ተጠሪዎች መሬቱ የእነሱ ስለመሆኑ ያቀረቡት ምንም ማስረጃ ስለላለ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚለ መቃወሚያዎችን አቅርበዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ የሱለልታ ወረዲ ፍርድ ቤትም የተከሳሾችን የመጀመሪያ መቃወሚያ ተቀብል ክሱን በብይን ውድቅ ያደረገዉ ቢሆንም ጉዲዩን በይግባኝ ያየው በፉንፍኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይኑን በመሻር በፍሬ ነገሩ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ የመሰለውን እንዱወስን ጉዲዩን መልሶ ለወረዲ ፍርድ ቤቱ ልኮለታል። በዚሁም መሰረት በጉዲዩ ላይ ግራ ቀኙን ያከራከረውና እና ማስረጃ የሰማው የወረዲ ፍርድ ቤቱ ተጠሪዎች በይዞታው ላይ ያለውን ቤት ከ1ኛ አመልካች እና ከእህታቸው ወርቄ ገመቹ ጋር በጋራ በመሆን ባደረጉት ውል በብር 390,000.00 የሸጡ መሆናቸው በቀረበው ውል እና በምስክሮች ቃል መረጋገጡን ጠቅሶ አመልካቾች ይዞታውን ሉለቁ አይገባም በማለት የተጠሪዎችን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል።
ተጠሪዎች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በበኩለ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው እና በቀን 02/08/2002 ዓ.ም የተደረገው ውል በባድ ቦታ ላይ የተደረገ እና ቀኑ በሀሰት ወደ ኋላ ተደርጎ የተፈረመ ስለሆነ እንዱሰረዝ እና አመልካቾችን ጨምሮ በስር ፍርድ ቤት 4ኛ ተከሳሽ የሆነው ግለሰብ በይዞታው ላይ የሰሩትን ግንባታ አፍርስው ይዞታውን እንዱለቁ ሲል ወስኗል። አመልካቾች በበኩላቸው በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በይግባኙ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ውለ በይዞታው ላይ የተሰራውን ቤት ተጠሪዎች ስለመሸጣቸው ገልጾ እያለ እና በምስክርም ተረጋግጦ እያለ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በባድ መሬት ላይ የተደረገ የሽያጭ ውል ነው በማለት ውለን መሰረዙ አግባብ አይደለም በማለት የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመሻር የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማፅናት ወስኗል። ተጠሪዎች በበኩላቸው በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ችልቱም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር አመልካቾች ግንባታውን አፍርሰው ይዞታውን ለተጠሪዎች እንዱመልሱ፤
ተጠሪዎች ደግሞ የተቀበለትን ብር 390,000.00 እንዱመልሱ ሲል ወስኗል። አመልካቾች ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነውን የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም ይህንኑ ለማስለወጥ ነው።
አመልካቾች በቀን 20/05/2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት 04 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈፅመዋል ያሎቸውን ስህተቶች ዘርዝረው በማቅረብ እንዱታረሙላቸው ጠይቀዋል።
የአቤቱታቸዉ ይዘትም በአጭሩ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ውለ በይዞታው ላይ የተሰራውን ባለ 30 ቆርቆሮ ቤት በግዢ ለአመልካቾች የተላለፈልን ስለመሆኑ ተገልጾና በምስክሮችም ጭምር ተረጋግጦ እያለ ሽያጩ የባድ መሬት ሽያጭ ስለሆነ ውለ ፈራሽ ነው በማለት መወሰናቸው፣ ተጠሪዎች 1ኛ አመልካች አሳስታን ውለ ላይ አስፈርማናለች ብለው ቢከራከሩም ስለመሳሳታቸው በማስረጃ ሳያስረደ በብር 2,000,000.00 ወጪ የሰራነውን ቤት አፍርሳችሁ ይዞታውን መልሱ መባለ፣ በ 9500 ካ.ሜ ላይ የተሰራን ቤት መግዛት መሬቱን ለመግዛት ያለን ሀሳብ ያመለክታል መባለ ውለን ያለገናዘበ እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩ በአጣሪ ችልት ተመርምሮ በግራ ቀኙ መካከል የቤት ሽያጭ ውል የተፈፀመ ለመሆኑ በቀን 02/08/2002 ዓ.ም የተደረገው ውል ቀርቦ እያለ ውለ የተደረገው በጋራ መሬት ስለሆነ ፈራሽ ነው ተብል የተወሰነበት አግባብ መጣራት አለበት በሚል ለዚህ ሰበር ችልት ቀርቧል። በዚሁም መሰረት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ በቀን 18/02/2013 ዓ.ም ጽፈው በሰጡት መልስ አመልካቾች ተደርጓል የሚለት ውል ላይ የሰፈረው ቀን ወደ ኋላ ተደርጎ የተፃፈ ሲሆን በጊዜውም መሬቱ ቤት የላለበት የእርሻ መሬት ነበረ፤ እስከ 2005 ዓ.ም ድረስም ቤት አልነበረበትም፤ የቀረበው ውልም በሀሰት የተዘጋጀ እንጂ እኛ የፈረምንበት አይደለም በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ብር 390,000.00 ለአመልካቾች እንድንመልስ ከሰጠው ውሳኔ ውጪ ሉፀና ይገባዋል በማለት ተከራክረዋል።
አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተው ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ከተያዘው ጭብጥ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
እንደመረመረዉም ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ለጠየቁት ዲኝነት መሰረት ያደረጉት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ይዞታ በዉርስ ከተከፊፈለ በኋላ ያደረጉት የሽያጭ ዉል ሳይኖር ወይም የተጭበረበረ የሽያጭ ዉል ሰነድ መሰረት በማድረግ ይዞታዉን የአሁን 1ኛ አመልካች ለ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ማስተላለፎን እና ሽያጩም በባድ ቦታ ላይ የተደረገ መሆኑን በመጥቀስ ሲሆን፤ አመልካቾች በበኩላቸዉ ቤቱን የገዙት በተጠሪዎች ስምምነት መሆኑንና የተሸጠዉም ቤት እንጂ ባድ ቦታ አለመሆኑን በመግለጽ ክሱ ዉድቅ ሆኖ እንዱወሰንላቸዉ መከራከራቸዉን ለመገንዘብ ተችሎል። ይህም የሚያሳየዉ በግራ ቀኝ መካከል የተደረገ የሽያጭ ዉል በተጠሪዎች መደረጉን እንዱሁም ተደረገ የተባለዉ የሽያጭ ዉልም ቤትን ወይም ባድ ቦታን የሚመለከት መሆን ያለመሆኑም ግራ ቀኝን ያከራከረ ነጥብ መሆኑን ነዉ። ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ይዞታ ቀደም ሲል የተጠሪዎች፣ የ1ኛ አመልካች እና የላላ አንድ እህታቸዉ የዉርስ ድርሻ የነበረ መሆኑ አላከራከረም። ይዞታዉ በህጋዊ መንገድ ለ2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ተላልፎል ማለት የሚቻለዉ የሽያጭ ዉለ በተጠሪዎች ስምምነት ወይም ይሁንታ የተደረገ መሆኑ ሲረጋገጥ ነዉ። ከዚህም አልፍ በኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(3) መሰረት የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት በሽያጭ ማስተላለፍ የተከለከለ በመሆኑ እና በዚህም ምክንያት ባድ ቦታን አስመልክቶ የሚደረግ የሽያጭ ዉል በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1716 መሰረት ህገ ወጥ ዉል ነዉ።
ስለሆነም 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በቤትና ቦታዉ ላይ መብት ኖሯቸዉ ይዘዉ መቀጠል የሚችለት ዉለ በተጠሪዎች ይሁንታ ወይም ስምምነት የተደረገ መሆኑ እንዱሁም የዉለ ይዘት ቤትን እንጂ ባድ ቦታን የማይመለከት መሆኑ ሲረጋገጥ ነዉ። ከዚህ አንፃር የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሻዉ መሰረታዊ ጭብጥ ዉለ ስለመደረጉ ብልም ዉለ ባድ ቦታን ሳይሆን ቤትን የሚመለከት መሆን አለመሆኑን ለማስረዲት ላቀርብ የሚገባዉ ማስረጃ ምን ዓይነት ላሆን ይገባዋል? የሚለዉ ነጥብ ነዉ። ይህንንም ጉዲዩ ዉለ የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት መሆኑን ከግምት ዉስጥ በማስገባት እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደሚታወቀዉ የአገራችን የፍትሐብሕር ፍትሕ ሥርዓት የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባ ለዜጎች የንብረት መብት ጥበቃ ከማድረግ አንፃር ፊይዲዉ የጎላ ስለመሆኑ ግምት ዉስጥ በማስገባት በፍትሐብሕር ህጉ የተለያዩ አንቀፆቹ ስለ ምዝገባ ይደነግጋል (አንቀጽ 1553-1646 እንዱሁም 1723፣ 2878 እና 3052 ይመለከቷል)። እነዚህ ድንጋጌዎች የየራሳቸዉ የሆኑ ዓላማዎች የሚኖሩት ቢሆንም፤
አጠቃላይ ዓላማቸዉ ግን ለማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ልዩ ጥበቃ በመስጠት እነዚህን ንብረቶች በተመለከተ ባለይዞታዉ መብቱን ሲያገኝ ወይም ንብረቱ በሆነ ምክንያት ወደ ላላ ሦስተኛ ወገን በሚያስተላልፍበት ወቅት የመመዝገብ ስልጣን በተሰጠዉ መንግስታዊ አካል ካልተመዘገበ ህግ ፉት የሚጸና መብት እንዲይኖረዉ በማድረግ ዜጎች በዚህ ግዙፍነት ያለዉ ንብረት ያላቸዉን መብት ከፍላጎታቸዉ ዉጪ በሆነ መንገድ እንዲያጡ ጥበቃ ለመስጠት፤ ብልም ንብረቱ ወይም ንብረቱን የሚመለከቱ መብቶች በዉል ሉተላለፈ የሚችለ መሆን ያለመሆኑንም በማጣራት የዉለን ህጋዊነት ለማረጋገጥ ጭምር ስለመሆኑ ከየድንጋጌዎቹ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበዉ ነዉ። የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ ከሚከናወኑት ህጋዉያን ተግባራት ጋር በተያያዘ ምዝገባ ወይም ዉለ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ እንዱረጋገጥ የግድ ከሚልባቸዉ ዉስጥም አንደ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1723(1) ስር የተመለከተዉ ድንጋጌ ሲሆን፣ በዚህ ድንጋጌ መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለማስተላለፍ የሚደረጉ ዉልች በጽሐፍና ዉል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠዉ አካል ፉት መሆን አለበት። ህግ አዉጪዉ ይህ እንዱሆን የፈለገበት ምክንያትም ዉለ በተዋዋዮች መካከል ስለመደረጉ ለማረጋገጥ (certainty in transactions) ስለመሆኑ በዙሪያዉ ከተፃፈት አንዲንድ ጽሐፍች መገንዘብ የሚቻል ሲሆን፤ ይህ ሰበር ችልትም በሰ/መ/ ላይ በሰጠዉ የህግ ትርጉም በዚህ ድንጋጌ መሰረት የሚከናወን የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ምዝገባ ዓላማ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ዉል መኖሩን ለማስረዲት ስለመሆኑ ወስኗል።
በልላ በኩል ተከራካሪ ወገኖች ዉለ መደረጉን ተማምነዉ ነገር ግን የዉለን ይዘት አስመልክቶ የተለያዩ መከራከሪያዎችን ሉያቀርቡ ይችላለ። በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2005 በጽሐፍ ሰነደ ላይ ስለሚገኘዉ የስምምነት ቃል እንዱሁም ስለተፃፈዉ ቀን በተፈራራሚዎቹ መካከል ሙለ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ይደነግጋል። ይሁንና ይህ ላሆን የሚችለዉ እንደ ዉለታዉ ዓይነት የጽሐፍ ዉል አደራረግን ሥርዓት አስመልክቶ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1678(ሐ) እና 1719(1) መሰረት አስፈላጊ የሆነዉን የዉል አደራረግ ሥርዓት አሟልቶ የያዘ ስለመሆኑ ከግምት ዉስጥ ሉገባ ይገባል።
ከላይ እንደተመለከተዉ የዉል አደራረግ ሥርዓት በተለየ አኳኋን እንዱደረግ በህግ ከተመለከተዉ ዉስጥ አንደ የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚደረግ ዉል በጽሐፍ ሆኖ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ መረጋገጥ እንዲለበት የሚደነግገዉ የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1723(1) ድንጋጌ ነዉ። በመሆኑም የዉለን ይዘት አስመልክቶ ማለትም ዉለ የተደረገዉ መቼ ነዉ? የሽያጭ ዉል ከሆነ በምን ያህል ዋጋ ነዉ የተደረገዉ? ለዉለ ምክንያት የሆነዉ ምን ዓይነት ንብረት ነዉ? የትስ የሚገኝ ነዉ? የሚለት እና መሰል የይዘት ክርክሮች የተነሱ እንደሆነ ይህን ለማጣራት ላቀርብ የሚገባዉ ማስረጃ ዓይነትም በጽሐፍ ሆኖ ዉል ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ አካል ፉት የተደረገ ዉል ላሆን ይገባል። ይህን አስመልክቶም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ መደረጉን ብልም የሽያጭ ዉለን ይዘት አስመልክቶ የሚነሳን ክርክር ለማስረዲት ላቀርብ የሚገባዉ ማስረጃ ዉለ ዉል ለማማዋል ስልጣን በተሰጠዉ አካል ዘንድ ቀርቦ መመዝገቡን ወይም መረጋገጡን የሚያሳይ ላሆን የሚገባዉ መሆኑን እና ለእንደዚህ ዓይነት ክርክር የሰዉ ምስክር ወይም ላላ ማስረጃ አቅርቦ ማስረዲት የማይቻል መሆኑን ነዉ።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ አመልካቾች ዉለ መደረጉንና የዉለም ይዘት ባድ ቦታን ሳይሆን ቤትን የሚመለከት መሆኑን የሚያሳይ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1723(1) መሰረት ዉል ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ አካል ዘንድ የተረጋገጠ ወይም የተመዘገበ ዉል ያቀረቡ ስለመሆኑ መዝገቡ አያሳይም።
ስለሆነም በእርግጥም ተደረገ የተባለዉ ዉል የተጠሪዎችን ስምምነት መሰረት ያደረገ ስለመሆኑ ጥያቄ ዉስጥ የሚያስገባ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ዉለ ቤትን የሚመለከት ስለመሆኑ አመልካቾች ከላይ በተመለከተዉ አግባብ ያቀረቡት ማስረጃ ከላለ የዉለ ይዘት ባድ ቦታን ሳይሆን ቤትን የሚመለከት ነዉ በሚል ድምዲሜ ላይ ለመድረስ አይቻልም። ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ ባድ ቦታን የሚመለከት ዉል ደግሞ በህግ ፉት ተፈፃሚነት የላለዉ በመሆኑ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በዉል መሰረት ይዘናል በሚለት ይዞታ ላይ ባለይዞታ ሆኖ ሉቀጥለ የሚችለበት ሁኔታ አይኖርም። በመሆኑም የስር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ከዚህ አንፃር ማየት ሲገባዉ ዉለን ለማስረዲት የግራ ቀኝን ምስክሮች እና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን መሰረት ማድረጉ የጉዲዩን ልዩ ባህሪ መሰረት ያላደረገ የማስረጃ አቀባበል በመሆኑ ስህተት ቢሆንም፣ ዉለ ሉጸና አይገባም በሚል ዉለ ፈርሶ አመልካቾች የያዙትን መሬት ሉለቁ ይገባል በሚል የሰጡት ዉሳኔ ከዉጤት አንፃር ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም።
ላላዉ መታየት የሚገባዉ ነጥብ በቦታዉ ላይ ወጪ አወጥተን ቤት ሰርተናል በማለት 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች የሚያቀርቡት ክርክር ነዉ። ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤትና ቦታ የሚገኘዉ በሱለልታ ከተማ አስተዲደር ስር መሆኑ አላከራከረም። 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ቤትና ቦታዉን ይዘን በቦታዉ ላይ ገንብተናል ለሚለት ቤት ምክንያት የሆነዉ ዉል ከላይ በተመለከተዉ ምክንያት ህጋዊ ዉጤት የላለዉ በመሆኑ ይዞታዉን ይዞ የመቀጠል መብት የላቸዉም። የዉል መፍረስ በዉል የተቋቋሙ መብቶችና ግዳታዎች እንዱቋረጡ ወይም ተፈፃሚነት እንዲይኖራቸዉ ማድረግን የሚያስከትል ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1807(ሀ) እና 1815 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
ዉል ሲሰረዝ ወይም ሲፈርስ ተዋዋዮች በተቻለ መጠን ዉለ ከመደረጉ በፉት ወደነበሩበት ሁኔታ እንዱመለሱ እና ዉለን ለመፈጸም የተሰራ ሁለ ቀሪ ሆኖ በማናቸዉም አኳኋን ዉጤት እንደላለዉ የሚደነግገዉ የህጉ አንቀጽ 1815 ድንጋጌ በተለይ ሲታዩ በዉል መሰረት አንደ ለላላዉ የፈጸመዉ ተግባር ካለ ቀሪ ተደርጎ ግራ ቀኝ ከዉለ በፉት ወደ ነበሩበት ሁኔታ እንዱመለሱ ማድረግ ግዳታ መሆኑን ነዉ። በመሆኑም ዉለ አንድን ንብረት በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገ ከሆነ እና ዉለ የማይረጋበት ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠ ዉጤቱ የሚሆነዉ ንብረቱን ገዝቶ በዉለ መሰረት የተረከበዉ ተዋዋይ ንብረቱን ለሻጩ መልሶ እንዱያስረክብ፣ ሻጩም ደግሞ በዉለ መሰረት የተቀበለዉ ገንዘብ ካለ ገንዘቡን ለገዥዉ እንዱመልስ ማድረግ ነዉ። ይህም ማለት ግራ ቀኝ የተቀባበለትን ነገር ባለበት ሁኔታ አንደ ለላላዉ እንዱመልስ ከማድረግ ዉጪ ሻጩ በዉለ መሰረት ከተቀበለዉ ገንዘብ በላይ ገዥዉም ደግሞ ከተረከበዉ ንብረት በላይ አንደ ለላላዉ ለመመለስ የማይገደደ መሆኑን ነዉ።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ህጋዊ ዉጤት የማያስከትል መሆኑ ተረጋግጦ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት እንዱፈርስ በተወሰነዉ ዉል መነሻነት በእጃቸዉ ባስገቡት ይዞታ ላይ በእራሳቸዉ ወጪ ተጨማሪ ቤቶችን የገነቡ መሆኑን ገልጸዉ ይከራከራለ። በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1815 መሰረት ዉለ በመፍረሱ ምክንያት 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በዉለ ምክንያት በእጃቸዉ የገባዉን ይዞታ ለተጠሪ የማስረከብ ግዳታ እንዱሁም በዉለ ምክንያት የከፈለት ገንዘብ እንዱመለስላቸዉ የመጠየቅ መብት ያላቸዉ ሲሆን፣ ተጠሪዎች በበኩላቸዉ ገንዘቡን የመመለስ ግዳታ እንዱሁም 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በእጃቸዉ ያስገቡትን ይዞታ መልሰዉ እንዱያስረክቧቸዉ የመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል፤ ይህ ዉለ በመፍረሱ ምክንያት ግራ ቀኝ የሚኖራቸዉ መብትና ግዳታ ሲሆን፣ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በቦታዉ ላይ በእራሳቸዉ ወጪ የገነቡት ቤት በዚህ ማዕቀፍ ዉስጥ የሚታይ አይሆንም። በዚህ ረገድ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በእጃቸዉ በገባዉ ቤትና ይዞታ ላይ የሰሩትን ተጨማሪ ግንባታ አስመልክቶ ሁለቱ አማራጮች ይኖራቸዋል። አንደኛዉ አማራጭ በይዞታዉ ላይ በእራሳቸዉ ወጪ የሰሩትን ቤት አፍርሰዉ ባድ ቦታዉን ብቻ ለተጠሪዎች ማስረከብ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ በተጨማሪነት በቦታዉ ላይ የተሰራዉን ቤት እዚያዉ በመተዉ ቤቱ የተሰራበትን ወጪ ተጠሪዎች እንዱከፍለ መጠየቅ ነዉ። አመልካቾች ሁለተኛዉን አማራጭ ከመረጡ ይህ ጥያቄአቸዉ የሚስተናገደዉ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1818 ላይ በተመለከተዉ አግባብ ነዉ።
በፍትሐ ብሓር ህጉ አንቀጽ 1818 ድንጋጌ መሰረት ዉለ ከመፍረሱ የተነሳ ንብረትን የመመለስ ግዳታ ያለበት ሰዉ ንብረቱን ለዉጦ ወይም በዚሁ ላይ ወጪ አድርጎ እንደሆነ ከዚህ መለዋወጥ ወይም ወጪ የተነሳ ያለትን መብቶች በከዉል ዉጪ ኃላፉነት ድንጋጌዎች መሰረት መጠየቅ ይችላል። እንደሚታወቀዉ በዉል አንድ ሰዉ አንድን ንብረት በእጁ ካስገባ በኋላ በእራሱ ወጪ የተለያዩ ማሻሻያዎችን ያደረገ እንደሆነ በእራሱ ወጪ ተጨማሪ ነገር የሰራዉ ተዋዋይ ንብረቱን መልሶ ሲያስረክብ ከነማሻሻያዎቹ ለላላኛዉ ተዋዋይ ሉያስረክብ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል። ይህ መሆኑ በአንድ በኩል ንብረቱ የተመለሰለት ሰዉ ያላግባብ እንዱበለጽግ፣ በልላ በኩል ደግሞ ንብረቱን የማስረከብ ግዳታ ያለበት ወገን ያላግባብ ተጎጂ ላሆን የሚችልበት ዕድል ሉኖር ይችላል። የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1818 ድንጋጌም ለእነደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች መፍትሓ የመስጠት ዓላማ ያደረገ በመሆኑ የድንጋጌዉ አፈፃፀምም ከላይ በተመለከተዉ ምክንያት ሉፈጠር የሚችለዉን ተወዲዲሪ ጥቅም (computing interests) ማስታረቅ በሚያስችል መልኩ ላሆን ይገባል። በመሆኑም በተያዘዉ ጉዲይ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ዉለን ተከትል በእጃቸዉ በገባዉ ይዞታ ላይ ቤት ገንብተዉ ከሆነ ቤቱን ለመገንባት ያወጡትን ወጪ ተጠሪዎች እንዱከፍሎቸዉ መጠየቅ ይችላለ። ይህ የዲኝነት ጥያቄም የገንዘብ መጠኑ (ግምቱ) ተገልጾ ዲኝነት ተከፍልበት የሚጠየቅ ነዉ። 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በቦታዉ ላይ የሰሩት ቤት ግምት ጠቅሶ ከማቅረብ ዉጪ ተጠሪዎች ቤቱን ለመስራት ያወጡትን ወጪ እንዱከፍሎቸዉ እንዱወሰንላቸዉ ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ ስለመኖሩ መዝገቡ አያሳይም።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1179 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ተፈፃሚነት የሚኖረዉ በባለይዞታዉ እና ይዞታዉን ይዞ ቤት በሰራ ሰዉ መካከል የታወቀ ግንኙነት በላለበት ሁኔታ ብቻ በመሆኑ ዉለ መፍረሱን ተከትል 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በቦታዉ ላይ የሰሩት ቤት ህጋዊ ዉጤትን አስመልክቶ ተፈፃሚነት ያለዉ ድንጋጌ አይደለም፤ ይልቁንም ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉ ከላይ የተመለከተዉ የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1818 ድንጋጌ ነዉ። ከዚህም አልፍ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቦታ በከተማ ዉስጥ የሚገኝ መሆኑ በመረጋገጡ የገጠር መሬትን አስመልክቶ አሁን በስራ ላይ ያለዉ አዋጅ ቁጥር 130/99 በጉዲዩ ላይ ተፈፃሚነት አይኖረዉም። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የፍትሐብሕር ህጉን አንቀጽ 1179 እንዱሁም የገጠር መሬት የገዛ ሰዉ ቤቱን አፍርሶ መሄድ እንዲለበት አዋጅ ቁጥር 130/99 ላይ የተመለከተዉን በዋቢነት በመጥቀስ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች የሰሩትን ቤት አፍርሰዉ ሉሄደ ይገባል በሚል የደረሰበት ድምዲሜ የጉዲዩን መሰረታዊ ባህሪ ከግምት ዉስጥ ያላስገባ ድንጋጌ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
በአጠቃላይ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ይዞታ የያዙት በህግ ፉት ተቀባይነት በላለዉ ዉል መሰረት በመሆኑ ዉለ ፈርሶ ይዞታዉ ለተጠሪዎች ሉመለስ ይገባል በሚል በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠዉ ዉሳኔ በአግባቡ ሆኖ ነገር ግን 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በቤቱ ላይ የሰሩትን ቤት ሉያፈርሱ ይገባል በሚል የተሰጠዉ ዉሳኔ በአግባቡ ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በቀን 16/03/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
ዉለ ፈራሽ ነዉ በሚል 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ይዞታ ለተጠሪዎች ሉመለስ ይገባል በሚል የተሰጠ የዉሳኔ ክፍል ጸንቷል፤ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በቦታዉ ላይ ለሰሩት ቤት ያወጡትን ወጪ ሉጠይቁ አይችለም በሚል ምክንያት ቤቱን አፍርሰዉ ሉሄደ ይገባል በማለት የተሰጠ የዉሳኔ ክፍል ተሽሯል።
2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች በቦታዉ ላይ የሰሩት ቤት ካለ ቤቱን ለመስራት ያወጡትን ወጪ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1818 መሰረት ተጠሪዎች እንዱከፍሎቸዉ ዲኝነት የመጠየቅ መብት አላቸዉ ተብሎል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።