በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ ነፃ እና ገለልተኛ የዲኝነት አካል በየደረጃው ማቋቋም ያስፈለገው ሰዎች ነፃና ገለልተኛ በሆነ አካል ፉት ቀርበው መብታቸውን በማስከበር ዲኝነታዊ መፍትሄ ማግኘት እንዱችለ፣ በህግ ፉት እኩል ጥበቃ እና ፍትህ የማግኘት መብታቸውን ለማስከበር እንዱሁም ላልች የሰዎችን ሰብዓዊና ዱሞክራሲያዊ መብቶች ለማስከበር በመሆኑ የክልል ፍርድ ቤቶች በህግ በታወቀ ምክንያት በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን የውክልና ሥልጣን መጠቀምና ለዜጎች ፍትህ መስጠት በማይችለበት ሁኔታ ላይ ሲሆኑ እና ጉዲዩም የፍደራል ጉዲይ ሲሆን የሰዎችን ፍትህ የማግኘት መብት፣ እኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት እና ላልች መብቶችን ለማስከበር የፍደራል ፍርድ ቤቶች በቀጥታ ጉዲዩን ተቀብለው የመዲኘት ሥልጣን ኦሮሚያ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር እና እነ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ (2 ሰዎች) ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 25፣ 37/1፣ እና አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ፤ የተባበሩት መንግስታት የሰበዓዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights) አንቀጽ 7፣8 እና 10 እንዱሁም የዓለም አቀፍ የሲቪልና ፓለቲካ መብቶች ቃልኪዲን (International Covenant on Civil and Political Rights/ICCPR) አንቀጽ 2(3/ሀ እና ለ)፣ 26
No summary available.
ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ኦሮሚያ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ተጠሪዎች፡- 1/ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ 2/ አዋሽ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ከውል ውጭ ኃላፉነትን መሰረት ያደረገ ሲሆን የተጀመረዉ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆኖ አመልካች ከሳሽ 1ኛ ተጠሪ ተከሳሽ 2ኛ ተጠሪ ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል። አመልካች ከደንበኛው ከወ/ሪት ብርሃን ገ/ጻድቃን ግደይ ጋር በተዋዋለዉ የኢንሹራንስ ዉል የሰላዲ ቁጥሩ 3- 05135 ትግ ለሆነ ተሽከርካሪ ከቀን 19/11/2006ዓ/ም እስከ 18/11/2007ዓ/ም ድረስ ጸንቶ የሚቆይ እስከ ብር 1000,000.00 ካሳ ለመክፈል የመድን ሽፊን ሰጥቷል። ይህ ተሽከርካሪ በጉዞ ላይ እያለ በትግራይ ክልል ክልታ አዉላዕል ወረዲ ሐዉዛ ተብል በሚጠራ አካባቢ በቀን 28/08/2007ዓ/ም ንብረትነቱ የ1ኛ ተጠሪ የሆነ በሰላዲ ቁጥር 35-3337 የሆነ ተሽከርካሪ መስመሩን ለቆ ወደ አመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ መስመር 1.20 ሜትር በመግብት የአመልካችን ደንበኛ ተሽከርካሪ ገጭቶ ጉዲት አድርሶበታል። ተሽከርካሪዉ ከወደቀበት በክሬን ተንስቶ ወደ አዱስ አበባ እንዱመጣ ተደርጎ የደረሰበትን ጉዲት ለማስጠገን የሚያስፈልገዉ ወጪ ተጣርቶ የጥገና ወጪዉ ከገበያ ላይ ተሽከርካሪዉን ከሚገዛበት ዋጋ በላይ በመሆኑ የቅሪት አካለ ዋጋ፣ የአደጋ ተቀናሽ(excess) እና ላልች ወጪዎች ተቀንሶ አመልካች ለደንበኛዉ ብር 505,363.00 መክፈለን በመግለጽ 1ኛ ተጠሪ ከ9% ሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱተከለት ዲኝነት ጠይቋል።
1ኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስ አመልካች በደንበኛው ተሽከርካሪ ላይ ጉዲት ስለመድረሱ ተዓማኒነት ባለዉ ማስረጃ አስደግፍ ያላቀረበ በመሆኑ ክሱ ዉድቅ ላሆን ይገባል። አመልካች የደንበኛው ተሽከርካሪ የእርጅና ዋጋ ሳይቀንስ የገበያ ዋጋ ግምት ብል ያቀረበው የገንዘብ መጠን በትክክል የገበያ ጥናት ያልተደረገበት ነው። የተሽከርካሪውን ቅሪት በጣም በዝቅተኛ ዋጋ ሽጦ ይህንን ልዩነት ተቀናሽ አድርጎ ተጠሪ እንዱከፍል መጠየቁ ተገቢ አይደለም። እንዱሁም የኢንሹራንስ ሽፊን የሰጠዉ 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ እንዱገባ በመጠየቅ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም የአሁን 2ኛ ተጠሪ በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ የሰጠዉን ትእዛዝ ተከትል 2ኛ ተጠሪ በሰጠዉ መልስ ከኃላፉነት መጠን ጋር በተያያዘ የ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ በ3ኛ ወገኖች ንብረት ላይ ለሚያደርሰው ጉዲት ወጪና ኪሳራን ጨምሮ እስከ ብር 100,000.00 ለመክፈል ግዳታ ስለገባ ከዚህ በላይ ልጠየቅ አይገባም። ግጭቱ ሉፈጠር የቻለው በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ጥፊት እንጂ በተጠሪ ተሽከርካሪ እንዲልሆነ እና አመልካች ያቀረበው የትራፉክ ፖሉስ አደጋ ሪፖርትም ትክክለኛ ያልሆነ እና እንዱታረም የተጠየቀበት ስለሆነ ይህንን ማስረጃ መሰረት በማድረግ አመልካች ያቀረበው ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል። እንዱሁም የተጠየቀው የጉዲት ካሳ ግምት የተጋነነ ነው።
የአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ የ2010 ስሪት እንደሆነ ከአምስት ዓመታት በላይም አገልግልት የሰጠ እና አመቺ ባልሆነ መንገድ እና መልከዓ ምድር ሲነዲ የቆየ ስለሆነ ቢያንስ የተሽከርካሪ አካል ላይ በአዱስ መለዋወጫ ሲተኩ ከ40-50 % የእርጅና ቅናሽ መደረግ ነበረበት። በተሽከርካሪው ዉስጣዊ ክፍለ ሉደርስ የሚችለዉ ጉዲት ከብር 95,000.00 እስከ ብር 175,000.00 መሆኑ ተገምቶ እያለ አመልካች ተፈቶ ባልታየበት ሁኔታ አመልካች አጋኖ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም። የቅሪት አካለ በብር 275,000.00 በባለሙያ ተገምቶ እያለ አመልካች በብር 120,000.00 ቀንሶ መሸጡ የጉዲት ኪሳራ ካሳ መቀነስ ሲገባው አልቀነሰም የሚለትንና ላልች የካሳ መጠን የሚመለከት መከራከሪያ በማቅረብ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮች ሰምቶና ማስረጃዎቻቸዉን መርምሮና መዝኖ በቀን 26/02/2012 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ በአመልካች ደንበኛ እና በ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪዎች መካከል ግጭት ሉከሰት የቻለዉ በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ጥፊት ምክንያት መሆኑን በተሻለ ሁኔታ ሚዛን በሚደፊ ማስረጃ ተረጋግጧል በማለት በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት 1ኛ ተጠሪ ካሳ የመክፈል ኃላፉነት የለበትም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚችልት አቅርቦ ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 12/02/2014 ዓ/ም በተሰጠው ውሳኔ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ጉድለት የለበትም ሲል በማጽናት ወስኗል።
አመልካች በቀን 04/05/2014 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉም ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ፡በመንገድ ትራንስፖርት ትራፉክ መቆጣጠሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀፅ 85(3/ሀ እና ለ) መሰረት በበላይ ትራፉክ ፖሉስ ፅ/ቤት ወይም በይግባኝ ጉዲዩን የማየት ስልጣን ባለው አካል ካልሆነ በስተቀር በትራፉክ ፖሉስ ልዩ እውቀት ላይ ተመስርቶ የቀረበውን የትራፉክ ፕላን ዉድቅ ማድረግ እንደማይቻል ተደንግጓል። የመቀላ ዩኒቨርሲቲ መካኒካል መሀንዱሶች የ1ኛ ተጠሪ ሰራተኞች የሆኑት አደጋው ሲደርስ በቦታው ስላልነበሩ የአይን ምስክሮች አልነበሩም።የ1ኛ ተጠሪ ምስክሮችና የመቀላ ዩኒቨርሲቲ መካኒካል መሐንዱሶች በትራፉክ መርማሪ ፖሉስ የተሰራዉን የትራፉክ ፕላን ለመሻር በሕግ የተሰጣቸዉ ሥልጣን የላቸዉም።የስር ፍርድ ቤት የመቀላ የኒቨርሲቲ መካኒካል መሐንዱሶች የሰጡትን ማስረጃና የ1ኛ ተጠሪን ምስክሮች ምስክርነት ቃል ተቀብል የትራፉክ ፖሉሲ ያነሳዉን የአደጋ ፕላን ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ ከላይ የተጠቀሰዉን ደንብ እና በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። የመቀላ ዩኒቨርሲቲ መካኒካል መሀንዱሶች ግጭቱን በተመለከተ ሰሩ የተባለው ሶፍትዌር አደጋው ከደረሰና ተሽከርካሪዎቹ ከቦታው ከተነሱ ከ2 ዓመት ተኩል በኋላ የተሰራ በመሆኑ የትራፉክ ሪፖርቱን ለማስተባበል ብቃት የላለዉና በንድፈ ሀሳብ ላይ ተመሰረተ ማስረጃ ነዉ።መካኒካል ምህንድስና ስለማሽን ንድፈ ሃሳብ አሰራር ወይም አመራረት እና ጥገና የሚያጠና ትምህርት ዘርፍ እንጂ የትራፉክ ደንብ በመተላለፍ ቀኝ ዘርዝን ትቶ ወደ ግራ መግባትና ከፉት ለፉት የሚመጣን ተላላፉ ተሸከርካሪ አለመኖሩን ሳያረጋግጥ በማለፍ ገጭቷል የተባለዉን አከራከሪ ነጥብ የሚያጠና የትምህርት ዘርፍ ባለመሆኑ ከዚህም አኳያ ሲታይ የስር ፍርድ ቤት በመካኒካል መሐንዱሶች የቀረበዉን ማስረጃ መሰረት አድርጎ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ይታረምልን በማለት አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች ከትራፉክ ፖሉስ የተሰጠውን ማስረጃ መሰረት በማድረግ በ1ኛ ተጠሪ አሽከርካሪ ጥፊት በደንበኛዉ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ለደንበኛዉ የከፈለዉ ካሳ ብር 505,363.00 እንዱተካለት ያቀረበዉን ክስ የስር ፍርድ ቤት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መካኒካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የቀረበዉን መረጃ መሰረት አድርጎ ዉድቅ በማድረግ የሰጠውን ውሳኔ ከመሰረታዊ የክርክር አመራርና ማስረጃ ምዘና መርህ አንፃር ተጠሪዎች ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱት ተጠሪዎች በቀን 22/07/2014 ዓ/ም በተናጠል የተፃፈ መልሳቸውን ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ፡አመልካች ያቀረበው የትራፉክ ፕላን በተገቢው ሁኔታ ያልተሰራና በአደጋው ቦታ ከነበረው እውነታ ጋር በተጣረሰ እና አጠራጣሪ በሆነ መልኩ የተሰራ ሪፖርት በመሆኑ በ2ኛ ተጠሪ ተጽፍ ቅሬታ ለትግራይ ክልል ፖሉስ ኮሚሽን ቀርቧል። ይህ ቅሬታ ቀርቦ እያለ የአመልካች ደንበኛ ሹፋር ለደረሰበት ጉዲት ካሳ ይከፈለኝ ሲል በ1ኛ ተጠሪ ላይ በትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ባቀረበው ክስ መነሻ ፍርድ ቤቱ ይህ የትራፉክ ፕላን አጠራጣሪና ቅሬታ የቀረበበት መሆኑን ከግምት በማስገባት በጉዲዩ ላይ ወገንተኛ ያልሆነና ሚዛናዊ ሙያዊ አስተያየት እንዱሰጥበት ለማስቻል ከክልለ ፖሉስ ኮሚሽን በተወኩ የትራፉክ ፖሉስ አባላት እንዱሁም ከመቐላ ዩኒቨርሲቲ በተውጣጡ ባለሙያዎች በጋራ በተዋቀረ ኮሚቴ የአደጋው መንስዔ ተጣርቶ ለፍርድ ቤቱ እንዱቀርብ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የአደጋውን መንስኤ በቪዱዮ በተደገፈ ሲሙላሽን በግልፅና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያስረዲ ሙያዊ ትንታኔ ቀርቦለታል።በሰ/መ/ ላይ በተሰጠ የሕግ ትርጉም ላይ እንደተመለከተዉ የሙያ ምስክርነት የሚሰጠዉ በቀጥታ ድርጊቱን በአይን በማየት ሳይሆን በሙያ ተመርምሮ የሚሰጥ ቀጥተኛ ያልሆነ ማስረጃ ወይም የሙያተኛ አስተያየት በመሆኑ ሙለ ለሙለ እምነት ሉጣልበት የሚችል ማስረጃ አይደለም።የትራፉክ ፖሉሲ የአደጋ ሪፖርትም አደጋዉ ከደረሰ ከሰዓታት በኋላ ከአደጋዉ ቦታ በደረሰ የትራፉክ ፖሉስ የተሰራ በመሆኑ አደጋዉ ከደረሰበበት ቦታ አቀማመጥ አንጻር የተሻለ የሙያ ሀሳብ ሉያቀርቡ የሚችለ ባለሙያዎች ያለበት ኮሚቴ ተዋቅሮ አደጋዉ የተከሰተበት ሁኔታ በሳይንሳዊ ሙያ ተመርምሮ አደጋዉ የደረሰዉ በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ጥፊት ነዉ የሚል ማስረጃ በመቅረቡ የስር ፍርድ ቤት ይህንን ማስጃና የምስክሮች ቃል መሰረት በማድረግ ተጠሪዎች አመልካች ካሳ የመክፈል ኃላፉነት የለባቸዉም ሲል በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም።የመቀላ ዩኒቨርሲቲ መካኒካል ምህንዱስና ትምህርት ክፍል ያቀረበዉ ሪፖርት የትራፉክ ፖሉስ ሪፖርትን የመሻር ሥልጣን የለዉም ሲል ያቀረበዉም ክርክር ሪፖርቱ የቀረበበትን አግባብ ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የለዉም።እንዱሁም የመካኒካል መሀንዱስና ትምህርት ዘርፍ ልዩ ልዩ ዘርፍ ያለዉ በመሆኑና ካለት ዘርፍች መካከል ኃይልን እና እንቅስቃሴን የሚያጠና ዲይናሚክስ (Dynamics) የሚባል ዘርፍ ስላለዉ በተያዘዉ ጉዲይ አደጋ የደረሰበት ቦታ ፣መንገድ ስፊት፣ተሽከርካሪዎቹ የወደቁበት ቦታ፣የአደጋዉ ስፍራ አቀማመጥ ከትራፉክ ፖሉስ ሪፖርት ላይ በመዉሰድ ለአደጋዉ መንስኤ የሆነዉ የትኛዉ ተሽከርካሪ ነዉ የሚለዉን ለይተዉ ሙያዎ አስተያየት ለማቅረብ ብቃት ስላላቸዉ አመልካች ከዚህም አኳያ ያቀረበዉ ክርክር ተገቢ አይደለም።ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ማስረጃዎችን መዝኖ ለደረሰዉ ጉዲት የ1ኛ ተጠሪ አሽከርካሪ ጥፊት የለበትም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ በመወሰኑ ከማስረጃ ምዘና አኳያ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል።አመልካችም በቀን 08/07/2014 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተገለጸዉ የግራ ቀኙን ክርክርና በጉዲዩ ላይ የተሰጡ ዉሳኔዎችን የሚመለከት ሲሆን እኛም 1) የስር የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱን ተቀብል የመዲኘት ሥልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? 2) የስር ፍርድ ቤት ክሱን ተቀብል መዲኘቱ ተገቢ ነዉ የሚባል ከሆነ አመልካች የኢንሹራንስ ዉል መሰረት በማድረግ ለደንበኛ በካሳ መልክ የከፈለዉ ገንዘብ እንዱተካለት ያቀረበዉን ክስ ዉድቅ አድርጎ በመወሰኑ ከማስጃ ምዘና መርህ አተገባበር አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግና ከሰበር ሰሚ ችልት አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
በመጀመሪያም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱን ተቀብል የመዲኘት ሥልጣን ያለዉ መሆን አለመሆኑን መርመረናል።እንደመረመርነዉም አመልካች በ1ኛ ተጠሪ ላይ በቀን 02/06/2009ዓ.ም ጽፍ ክስ የመሰረተዉ የመድን ሽፊን የሰጠዉን የደንበኛዉ ንብረት የሆነ በሰላዲ ቁጥሩ 3-05135 ትግ የሚታወቅ ተሽከርካሪ ንብረትነቱ የ1ኛ ተጠሪ የሆነ ከተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓዝ ተሽከርካሪ በትግራይ ክልል ክልታ አዉላዕል ወረዲ ሐዉዛ ተብል በሚጠራ አካባቢ ከመስመሩ በመዉጣት ገጭቶ ጉዲት በማድረሱ ለደንበኛዉ በኢንሹራንስ ዉለ መሰረት ካሳ መክፈለን በመግለጽ በካሳ መልክ የከፈለዉ ገንዘብ እንዱተካለት ዲኝነት በመጠየቅ ነዉ። የስር የፋዳራል ከፍተኛ ጉዲዩን ከስረ ነገሩ አንጻር መርምሮ በአመልካች ደንበኛ ተሸካሪ ላይ ጉዲቱ የደረሰዉ በ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ጥፊት አይደለም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።
በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 78/2 መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2/3ኛ ድምጽ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዱደራጅ እስካልወሰነ ድረስ የፋዳራል ከፍተኛና የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን በውክልና ለክልል ፍርድ ቤቶች ተሰጥቷል። ምላሽ የሚያስፈልገው ጉዲይ በውክልና በተሰጠ ሥልጣን ላይ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አላቸው ወይስ የላቸውም? የሚለው ጉዲይ ነው። ክርክሩን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቶች ኃላፉነት ሲሆን በዚህ ሂደት ፍርድ ቤቶች በቀዲሚነት መመርመር ከሚጠበቅባቸዉ ጉዲዮች መካከል ጉዲዩ ላይ ለመወሰን ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑ መርምሮ መወሰን ዋነኛው ነው። የፍርድ ቤት ሥልጣን ብሓራዊ የመዲኘት ሥልጣን (judicial jurisdiction)፣ የሥረ-ነገር ሥልጣን (material jurisdiction) እና የግዛት ወይም አካባቢያዊ ሥልጣን (local or territorial jurisdiction) በሚል የተከፊፈለ ነው።
ኢትዮጵያ የፋዳራል የመንግሥት አወቃቀር ሥርዓትን በ1987 ዓ/ም በወጣው የኢፋዱሪ ሕገመንግሥት መከተሎን ተከትል ሥልጣን በክልልችና በፋዳራል መንግሥት የተከፊፈለ ስለመሆኑ በሕገመንግሥቱ ከአንቀጽ 50-52 ላይ ተመልክቷል። በዚህም ክልልች በሥልጣናቸው ሥር ባለ ጉዲዮች ለዓላዊ ሥልጣን አላቸው። ክልልች እንደ ፋዳራል መንግሥት ሕግ-አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና የዲኝነት አካል ያደራጃለ። በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 78 መሰረት የዲኝነት አካለ በፋዳራል እና በክልል መንግሥት ደረጃ መቋቋሙ እና በአንቀጽ 80(1)(2) ላይ በፋዳራል ጉዲዮች የፋዳራል ፍርድ ቤት፤ በክልላዊ ጉዲዮች የክልል ፍርድ ቤት የመጨረሻ ሥልጣን ያለው መሆኑ መመልከቱ በፋዳራልና በክልል መንግሥታት መካከል የፍርድ ቤት የሥልጣን ክፍፍል እንዲለ ያሳያል። የፋዳራል ወይም የክልል ጉዲዮች የሚለው በጉዲይ ዓይነት የተከፊፈለ ሥልጣን ስለሆነ የፍርድ ቤቶች ሥልጣን የተለየው የሥረ-ነገር ሥልጣንን መሰረት ያደረገ ቢመስልም ጉዲዩ ከለዓላዊ ሥልጣን እና ክልላዊ ጉዲይ በፋዳራል ፍርድ ቤት ቢታይ ከጣልቃገብነት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ጉዲዩ የብሓራዊ ዲኝነት ሥልጣንን የሚያስነሳ ነው። በፋዳራል መዋቅር የብሓራዊ የዲኝነት ሥልጣን መሰረቱ ዓለምአቀፍ ሕግ ሳይሆን ሕገ-መንግሥት ነው። ሕገ-መንግሥቱ የፋዳራልና የክልል ፍርድ ቤቶች ያቋቋመና አንደ የላላዉን ሥልጣን አክብረው ለማስከበርም ግዳታ የጣለ ነው።ይህንን ጉዲይ ከአለም አቀፍ አጠቃላይ መርሆዎች አንጻር ሳይሆን በፋዳራልና በክልል መንግሥታት መካከል ከሚኖረዉ ግንኙነት አንጻር አጥበን ያየን እንደሆነ በአንድ ሀገር ያለና በሕገ-መንግሥቱ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማሕብረሰብ ለመፍጠር በሚሰሩ ተቋማትና ዜጎች ላይ፣ የተለያየ ሥልጣን ቢሆንም የጋራ የሆኑ ጉዲዮች ደግሞ ባላቸው ተቋማት መካከል የሚነሳ ስለሆነ የተለየ ያደርገዋል።
ይኸዉም በፋዳራል መዋቅር የፋዳራል መንግሥት ለዓላዊነቱ በመላው የኢትዮጵያ ግዛት ነው። ነገር ግን በግዛቱ ሥር ሁለንም በፈቃደ መወሰንና መፈጸም የሚችል ሳይሆን በግልጽ በሕግ በተዘረጋው ሥርዓት ሥልጣኑን የሚጠቀም መሆኑን የሚመለከት ነው። ለክልል ፍርድ ቤት ሥልጣን መሰረቱ ግን በግዛት ክልል ሥር ያለ ሰውና ንብረት መሆን አለመሆኑን መሰረት ያደረገ (limited sovereignty) ነው።
በሕገ-መንግሥቱ የሥልጣን ክፍፍለም የክልል ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የፋዳራል ጉዲዮችን በውክልና ማየት የሚችለ ሲሆን ክልላዊ ጉዲዮች በክልልች ለዓላዊ ሥልጣን ክልል ውስጥ (exclusive jurisdiction of state courts) ያለ በመሆኑ፤ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 80(3/ሀ) ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ማየት አይችለም። ይሕም ክልላዊ ጉዲዮች ላይ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች የመዲኘት ሥልጣን (judicial jurisdiction) የላላቸው መሆኑን ሲያሳይ በውክልና እና በጣምራ ሥልጣናቸው ከሚመለከቱት በሥተቀር የክልል ፍርድ ቤቶች የፋዳራል ጉዲዮችን ማየት አይችለም። ከዚህ ጋር ተያይዞ መመርመር ያለበት በሕገ-መንግሥቱ የተመለከተው የፍርድ ቤቶች የጣምራነት ሥልጣን (concurrent jurisdiction) እና የፋዳራል ጉዲዮች የሚወሰኑበት ሥርዓት ነው። የፋዳራል ጉዲዩች ምን እንደሆኑ በሕገ-መንግሥቱ ያልተወሰነ ቢሆንም የተያዘዉ ጉዲይ ለስር ፍርድ ቤት በቀረበበት ጊዜ ተፈጻሚ ሲሆን በነበረዉ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 3 መሰረት የፋዳራል ጉዲዮች ሕገመንግሥቱን፣ የፋዳራል መንግሥት ሕጎችንና ዓለም አቀፍ ሥምምነቶችን መሰረት ያደረጉ ጉዲዮች (based on laws)፤ በፋዳራል ሕግ ተገልጸው በተወሰኑ ባለጉዲዮች (parties) እና በሕግ በተገለጹ ቦታዎች (places) ላይ የሚነሱ ጉዲዮች ናቸው። በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 4 እና 5 መሰረት የተዘረዘሩት የፋዳራል ፍርድ ቤት በብቸኝነት ሥልጣኑ የሚመለከታቸው ሕግንና ባለጉዲዮችን መሰረት አድርጎ የተለዩ የፋዳራል ጉዲዮች ሲሆን በላልች ሕጎች በግልፅ ለፋዳራል ፍርድ ቤት የተሰጡ ጉዲዮችን ይጨምራል። የአዋጁን አንቀጽ 11 እና ተከታዮችን ስንመለከት ደግሞ ቦታን መሰረት በማድረግ አዱስ አበባና ድሬዲዋ ከተሞች ላይ የሚነሡ ጉዲዮች የፋዳራል ፍርድ ቤት የሚመለከታቸው የፋዳራል ጉዲዮች እንደሆኑ ተደንግጓል።
በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 3 መሰረት ሕግን መሰረት አድርጎ የተለዩት የፋዳራል ጉዲዮች ውስጥ የፋዳራል መንግሥት ሕጎችን መሰረት ያደረጉ ጉዲዮች ያለበት በመሆኑና በአዋጁ የትርጉም ክፍል አንቀጽ 2/3 ላይ የፋዳራል መንግሥት ሕጎች ማለት በሕግ በተሰጠው ሥልጣኑ ክልል ሥር ያለ ነባር ሕጎችን የሚጨመር መሆኑ ሲታይ በሕግ በግልጽ የፋዳራል ፍርድ ቤት ሥልጣን ሥር ከተመለከቱት ሕግን መሰረት ያደረጉ ጉዲዮች እና በፋዳራል ሥልጣን ሥር እንዱታዩ ከተወሰኑት ባለጉዲዮች ውጭ ያለ የፋዳራል ሕግን መሰረት ያደረጉ ጉዲዮች የፋዳራልና የክልል ፍርድ ቤቶች በጣምራ ሥልጣናቸው የሚመለከቷቸው ናቸው። ሥለሆነም የፋዳራል ሕግን መሰረት ያደረጉ ላልች ጉዲዮች እንደተነሱበት ቦታ የፋዳራል ፍርድ ቤት ወይም የክልል ፍርድ ቤት በክልላዊ ሥልጣኑ ሉመለከተው ይችላል።
በሕገ መንግስቱ በአገራችን የተዘረጋዉን የፋዳራል ሥርዓት መሰረት ተደርጎ የተዋቀረው የዲኝነት ሥልጣን የፋዳራል እና የክልል ፍርድ ቤቶች ካላቸው የጣምራነት ሥልጣን ባለፈ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 78/2 እና 80(4-6) የፋዳራል ፍርድ ቤት በብቸኝነት ሥልጣኑ የሚመለከታቸውን ጉዲዮች የክልል ጠቅላይና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በውክልና እንዱመለከቱ ሥልጣን ሰጥቷል። ይህም ሕገመንግሥቱ የክልል ፍርድ ቤቶችን ማብቃትን (empowerment)፣ተደራሽነትን፣ የክልልችን ተሳትፍ ማሳደግ ላይ ዓላማ ያለውና ተቋሞቻቸው ላይ አመኔታ ያለው መሆኑን ያረጋግጣል። በሕገ-መንግሥቱ የዲኝነት አካል በፋዳራልና በክልል ደረጃ በየእርከኑ መዋቀሩ ሲታይ አደረጃጀቱ በተዋረድ ያለ የትይዩ አቀራረጽ (dual system) ያለው ቢሆንም የፋዳራልና የክልል ጉዲይን የክልል ፍርድ ቤቶች መመልከታቸው የተደባለቀ (integrated system) እንደሚከተልም ያሳያል።
የክልል ፍርድ ቤቶች በጣምራ ሥልጣናቸው በክልል ግዛታቸው የተነሱ ጉዲዮች የመመልከት ሥልጣን ያላቸው በመሆኑ የፋዳራል ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አይኖረውም። ጉዲዩ በክልል ፍርድ ቤት የሚታየው ጉዲዩ የተነሳበትን ቦታና ተከራካሪውን መሰረት በማድረግ ነው። የጣምራነት ሥልጣን መሰረቱ የፋዳራል መንግሥት ሕግን መሰረት ያደረገ የፋዳራል ጉዲይ በመሆኑ የፋዳራል ፍርድ ቤት በፋዳራል ጉዲይ ላይ ብሓራዊ የመዲኘት ሥልጣን የለውም ልባል አይችልም። ነገር ግን በፋዳራል ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 25/1988 አቀራረጽ መሰረት ከተለዩት ውስን የፋዳራል ፍርድ ቤት ሥልጣኖች ውጭ ያለ በክልል ግዛት የሚነሱ ጉዲዮችን የክልል ፍርድ ቤቶች እንዱመለከቷቸው የተተወ በመሆኑ ጉዲዩ የሥረ-ነገር ሥልጣን ጥያቄ የሚያስነሳ ይሆናል።
በተመሳሳይ የክልል ፍርድ ቤቶች በፋዳራል ፍርድ ቤት በብቸኝነት እንዱታዩ የተለዩ ጉዲዮችን (exclusive jurisdiction) በግዛታቸው በተከሰቱ ጉዲዮች፣ ባለ ሰዎች ወይም ንብረቶች ጋር የሚነሱ ሲሆን በውክልና (delegation) እንዱመለከቱ በሕገ-መንግሥት ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። በክልል የሚነሱ የፋዳራል ጉዲዮች ላይ ጉዲዩ የፋዳራል በመሆኑ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ብሓራዊ የመዲኘት ሥልጣን አላቸው። በፋዳራል ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 4 እና 5 የተመለከቱት የፋዳራል ጉዲዮችን በተከታዮቹ ድንጋጌዎች ለፋዳራል ፍርድ ቤቶች የሥረ-ነገር ሥልጣናቸውን ያከፊፈለ በመሆኑ ይሄዉ ሕግ መሰረት ተደርጎ ሲታይ የፋዳራል ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመዲኘት የሥረ-ነገር ሥልጣን እንዲለው ያሳያል። የአፊር፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሶማላና የደቡብ ብሓሮች፣ ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልልች በሕገ-መንግሥቱ የተሰጣቸዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ሥልጣን በውክልና በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶቻቸዉ የማየት ሥልጣን በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማደራጃ አዋጅ ቁጥር 322/1995 ሲነሳ በእነዚህ ክልልች የፋዳራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት መደራጀቱ ታወጀ እንጂ በአምስቱ ክልልች ግዛቶች የሚነሱ ጉዲዮችን የመመልከት የሥረ-ሥልጣን እንደ አዱስ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አለመሰጠቱ ቀድሞውንም በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 መሰረት የሥረ-ነገር ሥልጣን ተወስኖ ያደረ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነዉ። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከአዱስ አበባና ድሬዲዋ ከተሞች ውጭ በእነዚህ ክልልች ሲደራጅ የማስቻያ ቦታው የተወሰነ በመሆኑ ጉዲዮችን ለማየት የግዛት ክልል ሥልጣን ያገኛል።በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት ከተጠቃሾቹ ክልልች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዉክልና ስልጣን ቢነሳም የእነዚህ ክልልች የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዉክልና ሥልጣንም ሆነ የላልቹ ክልልች የዉክልና ሥልጣን በሕገ መንግስቱ በተደነገገዉ አግባብ እስካሁን አልተነሳም። ይሕም የክልል ፍርድ ቤቶች በግዛታቸው ባለ ሰዎቸ ወይም ንብረቶች ጋር የሚነሳ በውክልና የሚመለከቱትን የፋዳራል ጉዲይ ውክልናቸው ሳይነሳ ጉዲዩ ለፋዳራል ፍርድ ቤት ቀርቦ ከታየ በሕገ-መንግሥቱ የተመለከተውን የፍርድ ቤቶች የጣምራነት ሥልጣን (concurrent jurisdiction) አለመከተል ስለሚሆን ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ይሆናል።
በዚህ መልኩ በሕገ-መንግሥቱ ለክልልች የተሰጠዉን ሥልጣን አተገባበር በተመለከተ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በቀን 22/04/2013 ዓ/ም እና የሰ/መ/ እና በቀን 05/02/2014 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ እንደተገለጸዉ በሕገ-መንግሥቱ የተመለከተው የፍርድ ቤቶች የጣምራነት ሥልጣን (concurrent jurisdiction) በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ከተመለከተው የግዛት ክልል ሥልጣን የተለየ አተገባበርና ውጤት ያለው እንደሆነ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
በመሆኑም ጉዲዩ በሥነ-ሥርዓት ሕጉ እንደተቀረጸው የግዛት ክልል ሥልጣን በዋነኛነት አመቺነትን ብቻ መሰረት ያደረገ ስለሆነ አመቺ እስከሆነ ድረስ በፋዳራል ፍርድ ቤት ላታይ ይችላል ከተባለ በሕገመንግሥቱ የክልል ፍርድ ቤቶች ውክልና ሉነሳ የሚችለው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2/3ኛ ድምጽ ብቻ ስለመሆኑ በአንቀጽ 78/2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፤ የክልል ፍርድ ቤቶች በሕገ-መንግሥቱ የተሰጣቸውን የውክልና ሥልጣን በሕጉ በተገለጸው አግባብ ሳይነሳ በፍርድ ቤቶች ውክልናውን የማንሳት ውጤት ያስከትላል። ሕገ- መንግሥቱ የፋዳራል ጉዲይን በውክልና በክልል ፍርድ ቤቶች እንዱታይ በማድረግ ሉያሳካው የፈለገው ዓላማም ከግብ እንዲይደርስ ያደርጋል።
በተጨማሪም ጉዲዩን የሚመለከተው ፍርድ ቤት ሥልጣን የሚወሰነው በሕግ ሆኖ እያለ በክልል ፍርድ ቤት በውክልና ላታይ የሚችል ሥልጣን በፋዳራል ፍርድ ቤት የሚቀርብ ከሆነ ተከራካሪዎች ክሱን የሚያቀርቡበት ፍርድ ቤት የፋዳራል ወይስ የክልል ፍርድ ቤት መሆን አለበት የሚለዉን በራሳቸው ምርጫ እንዱወስኑ (forum shopping) ስለሚያደርግ ተገቢ ያልሆነ የዲኝነት አሰጣጥ ሥርዓት እንዱፈጠር ዕድል ይፈጥራል። ስለሆነም በእነዚህ ምክንያቶች የክልል ጠቅላይ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በሕገ-መንግሥቱ የፋዳራል ጉዲዮችን በውክልና እንዱመለከቱ የተሰጣቸው ሥልጣን መሰረቱ የፋዳራል አወቃቀር በመሆኑ ውክልናቸው በሕግ እስካልተነሳ ድረስ ጉዲዮቹ ለፋዳራል ፍርድ ቤት ሉቀርቡ አይችለም። ጉዲዮቹ ቀርበው በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ከታዩ ውጤቱም አስገዲጅነት ያለውን የፍርድ ቤት ሥልጣን ክፍፍል የሚጥስ ስለሆነ ጉዲዩ በየትኛውም ደረጃ ፍርድ ቤት ሲደርስ በተከራካሪዎች ሆነ በፍርድ ቤቱ የሥልጣን ጥያቄው ተነስቶ ክሱ ውድቅ ላደረግ እና ከዚህ ሥርዓት ዉጭ የተሰጠ ዉሳኔ ካለም ሉሻር ይገባል።
ይህ ከላይ የተመለከተዉ የሕግ ትርጉም ተግባራዊ መደረግ የሚችለዉ ጉዲዩን ለመመልከት ሥልጣን ያለዉ ክልል መደበኛ የዲኝነት አገልግልት በሚሰጥበት ሁኔታ ላይ ሲሆን ብቻ እንደሆነ ግልጽ ነዉ።
አከራካሪ የሚሆነዉ አንድ ክልል በተለያየ ምክንያት በክልለ ዉስጥ መደበኛ የዲኝነት ሥልጣን መስጠት በማይችልበት ሁኔታ ላይ ከሆነ በሕገ-መንግሥቱ የተመለከተው የፍርድ ቤቶች የጣምራነት ሥልጣን (concurrent jurisdiction) አተገባበር ምን መሆን አለበት የሚለዉ ከሰዎች ፍትህ ከማግኘት እና በሕግ ፉት እኩል ጥበቃ ከማግኘት መብቶች ጋር ተገናዝቦ ታይቶ ምላሽ ማግኘት ይኖርበታል።
እንደሚታወቀዉ ፍትህ የማግኘት መብት (Right to Access to Justice) በራሱ ሰብዓዊ መብት ሆኖ በተሟላ መልኩ ላልች ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር የሚያስችል መሰረታዊ መብት ነዉ።ይህ መብት ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸዉና ባጸደቀቻቸዉ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕግጋት ፣ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶችና ዓለም አቀፍ ሰነድች መርሆዎች ላይ እዉቅና ያገኘ መብት ነዉ።ለአብነት ለመጥቀስ ያህል በዓለም አቀፍ የሲቪልና ፖሉቲካ መብቶች ቃልኪዲን(International Covenant on Civil and Political Rights/ICCPR) አንቀጽ 2(3/ሀ እና ለ) 26 ላይ ማንኛዉም ሰዉ ፍትሕ የማግኘት መብት እና በሕግ ፉት እኩል ሆኖ የመታየትና እኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት እንዲለዉ ደንግጓል።እነዚህን ድንጋጌዎች አተገባበር በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ እንዲብራራዉ አገራት ሰዎች መብቶቻቸዉ ሲጣስ አቤቱታ አቅርበዉ ዲኝነታዊ መፍትሓ እንዱሰጣቸዉ መጠየቅ የሚችለበትንና ዉጤታማ ፍትህ የሚያገኙበትን ተደራሽና ሥልጣን ያለዉን አካል በሕግ ስርዓታቸዉ የማቋቋምና የማመቻቸት ግዳታ አለባቸዉ።እንዱሁም በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ(Universal Declaration of Human Rights) አንቀጽ 7፣8፣እና 10 ላይ እንደተመለከተዉ ማንኛዉም ሰዉ በአገራት ሕግ ወይም ሕገ መንግስት በተደነገገዉ አግባብ ነጻና ገለልተኛ በሆነ አካል ፉት ቀርቦ መብቱን ለማስከበር የሚያስችል ዲኝነታዊ መፍትሄ የማግኘት እና በሕግ ፉት እኩል ጥበቃ የማግኘት መብት እንዲለዉ ተደንግጓል።
በተመሳሳይ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 25 ላይ ሁለም ሰዎች… በመካከላቸዉም ማንኛዉም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በሕግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል ሲል ደንግጓል።እንዱሁም ማንኛዉም ሰዉ በፍርድ ሉወሰን የሚገባዉን ጉዲይ ለፍርድ ቤት ወይም ለላላ በሕግ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠዉ አካል የማቅረብና ዉሳኔ የማግኘት መብት እንዲለዉ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 37/1 ስር ተደንግጓል።በተጨማሪም ሕገ መንግስቱ ማንኛዉም ሰዉ እነዚህንና ላልች መብቶቹን የሚያስከብርበትን ነጻና ገለልተኛ ፍርድ ቤቶችን በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ አቋቁሟል።
በያዝነዉ ጉዲይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ጉዲይ ከዉል ዉጭ ኃላፉነትን መሰረት ያደረገ የጉዲት ካሳ ለማስከፈል የቀረበ ክስን መሰረት ያደረገ ሆኖ ለክሱ ምክንያት የሆነዉ ጉዲት በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ ላይ የደረሰዉ በትግራይ ክልል ዉስጥ በሚገኝ ስፍራ በደረሰ የተሽከርካሪ ግጭት ምክንያት ነዉ።አደጋዉ የደረሰዉ በቀን 28/08/2007ዓ/ም ሲሆን አመልካች ለደንበኛዉ የከፈለዉ ካሳ እንዱተካለት በደንበኛዉ በመዲረግ በ1ኛ ተጠሪ ላይ ክስ መስርቶ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱን ያቀረበዉ ደግሞ በቀን 02/06/2009ዓ/ም ነዉ።በዚህ ጊዜ በትግራይ ክልል መንግስት እና በፋዳራል መንግስት መካከል ጤናማ ግንኙነት የነበረበት ጊዜ በመሆኑና የትግራይ ክልል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የዲኝነት አገልግልት እየሰጡ የሚገኙበት ጊዜ ነበር።በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ጉዲት በደረሰ ጊዜ ክሱ የሚቀርበው ጉዲቱ በደረሰበት ሥፍራ በሚገኝ ፍርድ ቤት መሆኑን ስለግዛት ክልል በሚደነግገው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 27/1 ላይ ተመልክቷል። ይሕም ክሱ በትግራይ ክልል ዉስጥ በሚገኝ ፍርድ ቤት እንደሚታይ ያስረዲል። በልላ በኩል የተከራካሪዎችን ማንነት ስንመለከት አመልካችና 2ኛ ተጠሪ በፋደራል መንግሥቱ የተመዘገቡ የንግድ ድርጅቶች መሆናቸዉ እንዱሁም 1ኛ ተጠሪም በፋዳራል መንግስት የተመዘገበ በጎ አደራጊ ማኅበር መሆኑ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5/6 መሰረት ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን ያለው የፋዳራል ፍርድ ቤት ስለመሆኑ ያስገነዝባል። በዚህ ምክንያት ጉዲዩ የፋዳራል ጉዲይ ቢሆንም ጉዲዩ የተነሳው በትግራይ ክልል በመሆኑ በሕገ-መንግሥቱ በተሰጠው ውክልና መሰረት ክስ ከቀረበበት ገንዘብ መጠን አንጻር ጉዲዩ መታየት ያለበት በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው።በመሆኑም አመልካች ከላይ በተመለከተዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም እና በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/2 መሰረት ክሱን ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ ሲገባዉ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረቡም ሆነ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በትግራይ ክልል ዉስጥ የተከሰተን ከዉል ዉጭ የሆነ ኃላፉነትን መሰረት ያደረገ የካሳ ጉዲይ የሚመለከት ክስ በዉክልና ሥልጣን በትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላታይ የሚገባዉ ነዉ ብል ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ ጉዲዩን በስረ ነገሩ ተመልከቶ ዉሳኔ መስጠቱ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።
ሆኖም የትግራይ ክልል የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት በሚቃረን አኳኋን በክልለ ምክር ቤት የምርጫ ሕግ በሚል አዋጅ ቁጥር 352/2012ን በማዉጣት፣ የምርጫ ኮሚሽን በማቋቋም እና ክልላዊ ምርጫ ማካሄደ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት የሚቃረን ስለሆነ ይህ አዋጅም ሆነ ይህንን አዋጅ ተከትል የተደረገዉ ምርጫም ሆነ የተቋቋመ የክልል መንግስት ኢ-ሕገ መንገስታዊ ስለሆነ ማንኛዉም ሕጋዊ ዉጤት እንደላለዉና ከፋዳራል መንግስት ጋር ኦፉሴላዊ ግንኙነት ማድረግ እንደማይችል የኢ.ፋ.ዱ.ሪ.
ፋዳሬሽን ምክር ቤት ነሐሴ 30 ቀን 2012ዓ/ም ባካሄደዉ አስቸኳይ ስብሰባ ዉሳኔ አስተላልፎል።ከዚህ በኋላም በተፈጠረ ግጭትና ይህንን ተከትል በፋዳራል መንግስቱ በተወሰደ ሕግ የማስከበር እርምጃ በትግራይ ክልልና በፋዳራል መንግስት መካከል ኦፉሴሉያዊ ግንኙነት እየተደረገ አይደለም። በዚሁ መልኩ ግንኙነቱ የተቋረጠዉ በክልለና በፋዳራል አስፈጻሚ አካላትና ከምክር ቤቶች ጋር ብቻ ሳይሆን በፋዳራል ፍርድ ቤቶችና በክልለ ፍርድ ቤቶች መካከል ያለዉ ዲኝነታዊና አስተዲደራዊ ጉዲዮች ግንኙነት ጭምር እስካሁን ተቋርጦ ይገኛል። በተጨማሪም በክልለና በአካባቢዉ የሰላምና መረጋጋት እጦት ችግር ምክንያት ወደ ክልለና ከክልለ ወደ ላልች የአገራችን ክፍል የሰዎች ዝዉዉር የተገደበ ሆኗል። እነዚህም እዉነታዎች በገሀድ (በተግባር) የሚታይ በመሆኑ ችልቱ የዲኝነት ግንዛቤ(judicial notice) የወሰደበት ጉዲይ ነዉ። በዚህ ምክንያት በአሁኑ ጊዜ የትግራይ ክልል ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸዉን የዉክልና ሥልጣን ተግባራዊ ማድረግ በማይችለበት ሁኔታ ላይ መሆናቸዉን ተገንዝበናል።
ከላይ እንደተመለከተዉ ምንም እንኳን ክሱ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረበበት ጊዜ ጉዲዩን በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 80/2 መሰረት የመዲኘት የዉክልና ሥልጣን ያለዉ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመሆኑ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን የለኝም በማለት ክሱን ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ ክሱን ተቀብል ጉዲዩን በስረ ነገሩ ተመልክቶ ዉሳኔ መስጠቱ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ቢሆንም በዚህ ምክንያት የስር ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 9 መሰረት በዚህ ችልት ቢሻር አመልካች ክሱን ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ ስለማይችል ፍትህ የማግኘት መብቱን ያጣል። እንዱሁም ተመሳሳይ የፋዳራል ጉዲይ ያላቸዉ ላልች ሰዎች መሰል ችግር በላለባቸዉና የዉክልና ሥልጣን ባላቸዉ ክልልች በሚገኙ ፍርድ ቤቶች ክስ አቅርበዉ እንዱሁም የክሱ ምክንያት የተከሰተዉ በአዱስ አበባ እና በድሬ ዲዋ ከተሞች ሲሆን ደግሞ በቀጥታ ለፋዳራል ፍርድ ቤቶች ክስ በማቅረብ ዲኝነታዊ መፍትሄና የሕግ ጥበቃ ሲያገኙ አመልካች ደግሞ የክሱ ምክንያት የተከሰተዉ በትግራይ ክልል በመሆኑና ክልለ ከፋዳራል መንግስት ጋር ያለዉ ግንኙነት በተቋረጠበት ሁኔታና በጸጥታ ችግር ምክንያት የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 80/2ን መሰረት በማድረግ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ዉሳኔ ሽሮ መተዉ ደግሞ በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ሰነድችና በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት ጥበቃ የተሰጣቸዉን የአመልካችን ፍትህ የማግኘት መብት ከማሳጣትም ባለፈ ሰዎች ሁለ በመካከላቸዉ ማንኛዉም ልዩነት ሳይደረግባቸዉ እኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸዉ የሚለዉን በሚቃረን አኳኋን በዚህ ረገድ የአመልካችን መሰረታዊ መብት ማሳጣት ይሆናል።
ስለሆነም በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ ነጻ እና ገለልተኛ የዲኝነት አካል በየደረጃዉ ማቋቋም ያስፈለገዉ እነዚህንና ላልች የሰዎችን ሰብዓዊና ዱሞክራሲያዊ መብቶች ለማስከበር በመሆኑ የክልል ፍርድ ቤቶች በሕጋዊ ምክንያት በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸዉን የዉክልና ሥልጣን መጠቀምና ለዜጎች ፍትህ መስጠት በማይችለበት ሁኔታ ላይ ሲሆኑ እና ጉዲዩም የፋዳራል ጉዲይ ሲሆን የሰዎችን ፍትህ የማግኘት መብት ፣ እኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት እና ላልች መብቶችን ማስከበር እንዱችለ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች በቀጥታ ጉዲዩን ተቀብለዉ የመዲኘት ሥልጣን አላቸዉ ብለናል። በተጨማሪም አመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአሁኑ ጊዜ መደበኛ የዲኝነት ሥራ እየሰራ ባለመሆኑ ቀጥል ክሱን ማቅረብ የሚችለዉ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ በሆነበት ሁኔታ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱ በቀረበለት ጊዜ በቀጥታ ክሱን ተቀብል ለመዲኘት ሥልጣን አልነበረዉም በሚል መነሻ ብቻ ዉሳኔዉ የሚሻር ከሆነ በአንድ ክርክር ተመሳሳይ የሆነ የጊዜ፣ የገንዘብና የሰዉ ጉልበት(ሀብት) ብክነት እንዱከሰት በማድረግ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ዓላማ እንዲይሳካ ያደርጋል። በመሆኑም እነዚህን ምክንያቶች ከግምት በማስገባት የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ሕገ መንግስታዊ የሆነዉን የፍርድ ቤቶች የዉክልና ሥልጣን የተከተለ አይደለም በሚል ምክንያት ሉሻር አይገባም ብለናል።
ሁለተኛዉን ጭብጥ እንደመረመርነዉም አመልካች በደንበኛዉ ተሽከርካሪ ላይ ጉዲት የደረሰዉ በ1ኛ ተጠሪ አሽከርካሪ ጥፊት ንብረትነቱ የ1ኛ ተጠሪ በሆነ ተሽከርካሪ ተገጭቶ ስለሆነ ለደንበኛዬ የከፈልኩትን ካሳ 1ኛ ተጠሪ ሉተካልኝ ይገባል በማለት ክስ የመሰረተ ሲሆን 1ኛ ተጠሪም ሆነ 2ኛ ተጠሪ ጉዲቱ በ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ጥፊት የደረሰ ባለመሆኑ አመልካች ለደንበኛዉ የከፈለዉን ካሳ የመተካት ኃላፉነት የለብንም በማለት ተከራክረዋል። አንድን ፍሬ ነገር ማስረጃ አቅርቦ የማስረዲት ሸክምን ከሚመለከተዉ መሰረታዊዉ መርህ (Basic Principle of Burden of Proof) መረዲት እንደሚቻለዉ አንድ አከራካሪ ፍሬ ነገር አለ ወይም የለም ብል የሚከራከር ሰዉ ፍሬ ነገሩ መኖሩን ወይም አለመኖሩን ተገቢነትና ተቀባይነት ያለዉን ማስረጃ በማቅረብ የማስረዲት ሸክም(ግዳታ) አለበት።
(የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 258-260 እና የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2001 ይመለከቷል)። በተያዘዉ ጉዲይ በአመልካች የደንበኛ ተሽከርካሪ ላይ የመገጨት አደጋ የደረሰበትና በዚህ መነሻ ካሳ የተከፈለበት ጉዲት ሉደርስ የቻለዉ በ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ጥፊት ምክንያት መሆኑን በቀዲሚነት ማስረዲት ይኖርበታል። በመቀጠልም ተጠሪዎች እንደነገሩ ሁኔታ በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ ላይ ጉዲት የደረሰዉ የ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ጥፊት ምክንያት እንዲልሆነ ማስረዲት ይኖርባቸዋል። ግራ ቀኙ በዚህ መልኩ የማስረዲት ሸክም ያለባቸዉ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ማስረጃ የመስማት፣የመመርመርና የመመዘን ሥልጣን ያላቸዉ ፍርድ ቤቶችም በግራ ቀኙ በቀረቡ ማስረጃዎች ሳይገደቡና የገለልተኛነት ሚናቸዉንም ሳይተላለፈ አንጻራዊ እዉነታን የማፈላለግ ኃላፉነታቸዉን መወጣት በሚያስችላቸዉ መልኩ በተከራካሪ ወገኖች ሆነ በራሳቸዉ አነሳሽነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 136 ፣ 145/1፣249 ፣264 (1 እና 2) እና 345 መሰረት ተጨማሪ ምስክሮችን፣የሰነድ ማስረጃዎችን፣ የሙያ ምስክሮችን አስቀርበዉ መስማትና መመርመር ይችላለ።
በያዝነዉ ጉዲይ አመልካች ለደንበኛዉ ካሳ እንዱከፍል ያደረገዉ ጉዲት በደንበኛዉ ተሽከርካሪ ላይ የደረሰዉ የ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ጥፊት ምክንያት መሆኑን ለማስረዲት ያቀረበዉ ማስረጃ በወቅቱ ስለአደጋዉ ክስተት በትራፉክ ፖሉስ የተነሳዉን የአደጋ ፕላን እና ሪፖርት ሲሆን ተጠሪዎች ደግሞ ይህ አመልካች ያቀረበዉ ማስረጃ በአደጋዉ ምክንያት በሰዉ ላይ ለደረሰ አደጋ ካሳ ለማስከፈል በቀረበ ክስ መነሻ በትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተከፈተ መዝገብ ላይ በተሰጠ ትዕዛዝ የመቀላ ዩኒቨርስቲ ባለሙያዎችና የትራፉክ ፖሉሶች ያለበት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እንዱጣራ ተድርጓል። ኮሚቴዉ የአደጋዉ መንስኤ የ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ጥፊት ነዉ ተብል አስቀድሞ የቀረበዉ የትራፉክ ፖሉሲ የአደጋ ፕላንና ሪፖርት ትክክል እንዲልሆነና ለአደጋዉ መንስኤ የሆነዉን ጥፊት የፈጸመዉ የአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ እንደሆነ አረጋግጠዉ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት በማስረጃነት በመመርመርና የምስክሮችን ቃል ጭምር በመመዘን ጉዲቱ የደረሰዉ በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ጥፊት ምክንያት በመሆኑ ተጠሪዎች ክስ የቀረበበትን ካሳ የመክፈል ኃላፉነት የለባቸወም ሲል ክሱን ዉድቅ አድርጓል።
እንደሚታወቀዉ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ሀ) እና በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/4 እና 10 መሰረት ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠዉ ሥልጣን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ዉሳኔ እንዱያርም ነዉ። ሰበር ችልት የማስረጃ አቀራረብን፣ አግባብነትንና ተቀባይነትን (Production, relevancy and admissibility of evidence)እንዱሁም የማስረዲት ሸክምንና የማስረጃ ምዘናን (burden of proof and weight of evidence) የሚመለከቱ መሰረታዊ መርሆዎች በግልጽ ተጥሶ የተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ መኖሩን አረጋግጦ ስህተቱ እንዱታረም ሉወስን ከሚችል በስተቀር ተከራካሪ ወገኖች ማስረጃ ለመቀበል፣ለመስማትና ለመመዘን ሥልጣን ለተሰጣቸዉ የስር ፍርድ ቤቶች አቅርበዉ ማስረጃዎቹ ተመርምረዉና ተመዝነዉ የተደረሰዉን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ወደ ጎን በመተዉ ማስረጃዎችን በድጋሚ የመመዘን ተግባር ዉስጥ በመግባት ማስረጃዎችን በመመርመርና በመመዘን አከራካሪ የሆነዉ ፍሬ ነገር መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥልጣን አልተሰጠዉም።
ከላይ እንደተመለከተዉ የስር ፍርድ ቤት በዋናነት መሰረት የደረገዉ ማስረጃ በትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትእዛዝ የመቀላ ዩኒቨርሲቲ ባለሙያዎች እና የትራፉክ ፖሉሶች ያለበት ኮሚቴ ተቋቁሞ ተጣርቶ የቀረበዉን ማስረጃ መሰረት በማድረግ ነዉ።በዚህ መልኩ ኮሚቴ ተዋቅሮ የአደጋዉ መነሻ ምክንያት እንዱጣራ የተደረገዉ በመቀላ ዩኒቨርሲቲ ባለሙያዎች አነሳሽነት ሳይሆን በትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተሰጠ ትእዛዝ ነዉ።ከላይ እንደገለጽነዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ መልኩ አንድ አከራካሪ ጭብጥ በባለሙያ ተጣርቶ ማስረጃ እንዱቀርብለት ለማዘዝ እንዱችል የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ይፈቅድለታል።በዚህ መልኩ የቀረበዉ ማስረጃ ደግሞ አመልካች በማስረጃነት ያቀረበዉንና አስቀድሞ የ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ጥፊተኛ እንደሆነ ተገልጾ የቀረበዉ የትራፉክ ፖሉስ የተዘጋጀ የአደጋ ፕላን/ሪፖርት ትክክለኛ ድምዲሜ አይደለም የሚያስብል በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት በሳይንሳዊ መንገድ ስለአደጋዉ መንስኤ የሚያስረዲዉን ኋለኛዉን ማስረጃ መሰረት አድርጎ መወሰኑ ከማስረጃ አቀባበልም ሆነ ምዘና መርሆዎች አተገባበር አንጻር ጉድለት ፈጽሟል የሚያስብል አይደለም።
እንዱሁም አመልካች ከላይ በተመለከተዉ መሰረት የመቀላ ዩኒቨርስቲ ባለሙያዎችና የትራፉክ ፖሉሶች ያለበት ኮሚቴ ተዋቅሮ ተጣርቶ የቀረበዉን ማስረጃ መቀበል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 85(3/ሀ እና ለ) ስር የተደነገገዉን እና በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነዉ በማለት ያቀረበዉንም ክርክር መርምረናል።የመንገድ ትራንስፖርት ትራፉክ መቆጣጠሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 208/2003 በደንብ ቁጥር 395/2009 የተሻሻለ ሲሆን በዚህ በተሻሻለዉ ድንብ አንቀጽ 85 ላይ የተደነገገዉ በጠቅላላዉ በደንብ ተላላፉዎች ላይ ስለሚጣል ቅጣት የተደነገገ ሲሆን በተለይ በንኡስ አንቀጽ 4( ሀ እና ለ) ላይ ደግሞ ደንብ ተላላፉ ነዉ ተብል ቅጣት የተጣለበት ሰዉ ቅሬታ ሲያድርበት መቼ ለማን ቅሬታዉን ማቅረብ እንዲለበት ተደንግጓል። ከዚህ ዉጭ በዚህ ድንጋጌም ሆነ በደንቡ ላልች ክፍልች ላይ ስለአንድ የትራፉክ አደጋ በትራፉክ ፖሉስ የተነሳ የአደጋ ፕላን ወይም የትራፉክ ፖሉስ የአደጋ ሁኔታ ማሳያ ሪፖርት አጠራጣሪ ሆኖ ሲገኝ በፍርድ ቤት ትእዛዝ በልላ ባለሙያ ወይም በልላ የትራፉክ ፖሉስ ባለሙያ ተጣርቶ እንዱቀርብ የሚከለክል ድንጋጌ አልተደነገገም። በትራፉክ ፖሉስ የተዘጋጀ የአደጋ ሁኔታ የሚያሳይ ፕላን/ሪፖርት እንደማንኛዉም የሙያ ምስክርነት ከፍተኛ ዋጋ (high probative value) ተሰጥቶ እንደሚመዘን አጠቃላይ የማስረጃ መርህ የሚያስገድድ ቢሆንም እንዱህ አይነት የሙያ ምስክርነት አጠራጣሪ በሆነ ጊዜ በልላ ባለሙያ የሙያ ምስክርነት ማጣራትን የሚከለክል ወይም አስቀድሞ የመጀመሪያዉ የሙያ ምስክርነት የማይስተባበል ማስረጃ (አሳሪ/conclusive evidence) ነዉ የሚል የሕግ ድንጋጌም ሆነ ከዚህ አንጻር የተሰጠ የሰበር ሰሚ ችልት አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የለም።
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ለዉሳኔዉ መሰረት ያደረገዉ ማስረጃ ተጠቃሹን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ እና የሰበር ሰሚ ችልት አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚጥስ ነዉ በሚል አመልካች ያቀረበዉን ክርክር አልተቀበልንም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ኋለኛዉ የሙያ ምስክርነት ማስረጃ እና የምስክሮች ቃል መሰረት አድርጎና የተሻለ ዋጋ ሰጥቶ በመመዘኑ የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 26/02/2012 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 12/02/2014 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንቷል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለይግባኝ ሰሚዉ ችልትና ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.