በሕግ የውክልና ስልጣን መስጫ ሰነድ አረጋግጦ አንዱመዘግብ ስልጣን በተሰጠው አካል ያልተረጋገጠና ያልተመዘገብ የውክልና ስልጣን ማስረጃ በመያዝ ላላ ሰው ወክል ለመሟገት የቀረበን ሰው ለመወከል ብቁ የሚያደርግህን የውክልና ስልጣን ማስረጃ ይዘህ አልቀረብክም ብል አፍሪካ ጁስ ቲቢላ አ.ማ እና እነ አቶ ታደ ጫላ (7 ሰዎች) ቤቱ ሉያስናብተው የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 63/1፣ አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ 9(1/ለ) እና አዋጅ ቁጥር 110/1990 10/1 አስቀድሞ መከላከያ መልሱን ያላቀረብ ተከሳሽ ክሱ በሚሰማበት ቀን የፍትሀ ብሄር ስነ ስርዓት ህግ አንቀጽ 137ን ጠቅሶ ከማስረጃ መግለጫ ጋር የሚያቀርበው የሰነድ ማስረጃ ይያያዝልኝ ጥያቄ በስነ ስርዓት ህጉ መሰረት ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ
No summary available.
የሰ/መ/ ሀምላ 28 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አፍሪካ ጁስ ቲቢላ አ.ማ ተጠሪዎች፡- 1/ አቶ ታደ ጫላ 2/ አቶ ቴዎድሮስ ስጣርጌ 3/ አቶ አለማየው ደጀን 4/ አቶ ቴዎድሮስ አስማማው 5/ አቶ ሰለሞን አባተ 6/ አቶ ፊኖስ አንዲሳ 7/ አቶ አብደልናስር መሀመድ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአመልካች መልስ የመስጠት መብቱ የታለፈበት አግባብና ከዚህ በኋላ ክሱ በተሰማበት እለት የሰነድ ማስረጃ እንዱያያዝለት ያቀረበዉ አቤቱታ ተቀባይነት እንዲያገኝ የተደረገበት አግባብ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ በሚል በቀረበ አቤቱታ መነሻ የተደረገ ክርክር የሚመለከት ሲሆን ጉዲዩ በመጀመሪያ በታየበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪዎች በአመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በተለያየ የስራ መደብ ሲያገለግለ ቆይተዉ ከሕግ ዉጭ እንዲሰናበታቸዉ በመግለጽ ከተራ ቁጥር 1-5 ለተጠቀሱ ተጠሪዎች የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸዉ 6ኛ እና 7ኛ ተጠሪዎችን ደግሞ ወደ ሥራቸዉ እንዱመልሳቸዉ እንዱወሰንላቸዉ ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካች ለክሱ ያለዉን መልስ ሬጅስትራር ጽ/ቤት ቀርቦ እንዱሰጥ ታዞ አመልካችን ወክል ወደ ፍርድ ቤት የቀረበዉ ሰዉ ዉክልና ይዞ ባለመገኘቱ እንዱሁም ከመልሱ ጋር አያይዞ ያቀረባቸዉ ሰነድች የቴምብር ቀረጥ ተክፍልበት ተሟልቶ አለመቅረቡን በመግለጽ መልሱን ሬጅስትራር ሳይቀበለዉ ቀርቷል።ከዚህ በኋላ አመልካች ለችልቱ አቤቱታ አቅርቦ ችልቱ በቀን 17/04/2011ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ አመልካች መልሱን እንዱያቀርብ በታዘዘበት ቀነ ቀጠሮ የዉክልና ሰነድ የያዘ ተወካይ ያላቀረበበትንም ሆነ ከመልሱ ጋር ተያይዞ የሚቀርበዉን የሰነድ ማስረጃዎች የቴምብር ቀረጥ ከፍል አሟልቶ ያላቀረበበትን ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ሳይገልጽና ይህንን አሟልቶ ማቅረብ የራሱ ግዳታ ሆኖ ሳለ በራሱ ጉድለት ምክንያት መልስ በጽሁፍ ሳያያይዝ በመቅረቱ ተጨማሪ ጊዜ የሚሰጥበት የሕግ አግባብ የለም በማለት የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 196/3ን በመጥቀስ የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ አድርጓል።
በመቀጠል አመልካች ፍርድ ቤቱ ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ክስ ለመስማት በቀጠረበት እለት የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 137ን በመጥቀስ የሰነድ ማስረጃዎች ከመዝገቡ ጋር እንዱያያዝለት ጠይቆ ፍርድ ቤቱ በቀን 20/06/2011ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ አመልካች መልሱን በጽሁፍ የማቅረብ መብቱ ስለታለፈ መልስ የመስጠት መብቱ ከታለፈ በኋላ የሰነድ ማስረጃ እንዱያያዝለት ያቀረበዉ ጥያቄ የሥነ ሥርዓት ሕጉን የተከተለ አይደለም በማለት ዉድቅ አድርጓል። ዋናዉን ጉዲይ በተመለከተም በመ/ ላይ በቀን 21/09/2011 ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች ተጠሪዎችን ከሕግ ዉጭ አሰናብቷል በማለት ከተራ ቁጥር 1-5 ለተጠቀሱ ተጠሪዎች በአዋጅ ቁጥር 377/1996 ሕገወጥ ስንብትን ተከትል የሚከፈለ ክፍያዎች እንዱከፈላቸዉ እንዱሁም 6ኛ እና 7ኛ ተጠሪዎችን ወደ ሥራ መደባቸዉ እንዱመልሳቸዉ ወስኗል።በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኙን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ በቀን 20/02/2012 ዓ/ም በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 337 መሰረት በሰጠዉ ብይን ይግባኙን ሰርዟል። አመልካች በቀን 28/02/2012 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጡ ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
አመልካች በስር ፍ/ቤት የመከላከያ መልሳችንን በቀጠሮ ሰዓት ይዘን የቀረብን ሲሆን ፍ/ቤቱ ግን የውክልናው ደብዲቤ በሰነድችና ማረጋገጫ አልተረጋገጠም የቀረበውም መልስ ቴምብር አልተለጠፈባቸውም ሲል በአመልካች ጉድለት ባልሆነ ምክንያት መልስ የማቅረብ መብታችንን አልፎል።
ይህንን ተከትል ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ይረዲ ዘንድ መልሳችንን በአቤቱታ አስደግፈን አቅርበን ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አመልካች መልሱን እንዱያቀርብ ማድረግ ሲገባው ጥያቄያችንን ውድቅ ማድረጉ የስር ፍርድ ቤት ያለበቂ እና ህጋዊ ምክንያት ባልሆነበት ስነ ስርዓታዊ የሆነውን እንደ ጉድለት በመውሰድ መሰረታዊ የሆነውን መልስ የማቅረብ መብታችንን እንድናጣ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 137 በሚፈቅደው መሰረት ክስ በሚሰማበት ወቅት ከተራ ቁጥር 1ኛ እስከ 3ኛ የተጠቀሱ ተጠሪዎች የስራ መሪ መሆናቸውንና ስንብቱ ሕገ ወጥ ነዉ የሚባል ቢሆን እንኳን ለ2ኛ ፣3ኛ ፣6ኛ እና 7ኛ ተጠሪዎች ደግሞ የስራ ውላቸው ከሕግ ውጪ ነው ቢባል እንኳን በሕግ አግባብ ሉፈጸምላቸው የሚገባው ማንኛውም ክፍያ የተፈፀመላቸው መሆኑን፤ እንዱሁም 1ኛ፣4ኛ እና 5ኛ ተጠሪዎች የፈፀሙትን ጉልህ የስራ ግድፈት ከሚያሳይ ዝርዝር አቤቱታ ጋር ያቀረብነዉን የሰነድ ማስረጃዎች የስር ፍርድ ቤት አይያያዝም በማለት ጥያቄያችንን ዉድቅ ማድረጉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 137ን እና በሰ/መ/ የሰጠውን አስገዲጅ ትርጉም የሚቃረን በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ተብል ይታረምልን በማለት አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች መልስ እንዱያቀርብ በተቀጠረበት ቀን ሬጅስትራር ሳይቀበለው መቅረቱ ለችልቱ አመልክቶ እያለ መልስ የመስጠት መብቶ ታልፍ የተወሰነበትን አግባብነት ከመደመጥ መብት አንፃር እንዱጣራ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ብል ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በቀን 07/04/2012 ዓ/ም የተፃፈ በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ አቅርበዋል።
አመልካች በተሰጠዉ ጊዜ መልሱን ይዞ ባለመቅረቡ መብቱ እንደታለፈበት የስር ፍርድ ቤት መዝገብ በግልፅ ያስረዲል።ሰበር አጣሪ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲል የያዘዉ ጭብጥ አመልካች መልሱን አቅርቦ ነበር ወይስ አይደለም የሚል ፍሬ ነገርን አጣርቶ መወሰንን የሚጠይቅ በመሆኑ በሰበር ችልት የሚታይ ባለመሆኑ ዉድቅ ይደረግልን።አመልካች በስር ፍርድ ቤት ሬጅስትራር በሰዓቱ ሳያቀርብ በመቅረቱ እና መልስ ባለማቅረቡ ከጅምሩ መልስ የማቅረብ መብቱን በራሱ ጊዜ እንደተወዉ ያስቆጥረዋል እንጂ የመደመጥ መብቱን ፍርድ ቤቱ ሳያከብርለት እንደቀረ አያሳይም። ይህም ለቀጠሮው ምክንያት የሆነ መሰረታዊ ጉዲይ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ስነ ስርዓት ሕጉ በሚፈቅደው መልኩ የማቅረብ መብቱን ሉያልፈው ችሎል።አመልካች በከፍተኛ ቸልተኝነት ወይም መልስ ለማቅረብ ፈቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ በስር ፍርድ ቤት የተከናወኑት ቀጠሮ ቀናቶች በግልፅ የሚያስረደት የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን የመደመጥ መብቱን ለማስከበር ጥረት ማድረጉን የሚያሳይ በመሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ተብል የአመልካች አቤቱታ ዉድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል።አመልካችም በቀን 01/05/2012ዓ/ም በተፃፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ያያዘዉን ጭብጥ እና አመልካች ክሱ በተሰማበት እለት ከመዝገቡ ጋር የሰነድ ማስረጃ እንዱያያዝለት ያቀረበዉ ጥያቄ ዉድቅ ተደርጎ በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጡ ዉሳኔዎች የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም አመልካች ለቀረበበት ክስ መከላከያ መልሱን በፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር ጽ/ቤት ዘንድ ቀርቦ እንዱሰጥ በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ መከላከያ መልሱን ይዞ የቀረበዉ ተወካይ የተሟላ የዉክልና ስልጣን ማስረጃ ይዞ እንዲልቀረበና ይህ የዉክልና ስልጣን ማስረጃ ሳይዝ የቀረበዉ ሰዉ ለሬጅስትራር ካቀረበዉ መልስ ጋር አያይዞ ያቀረበዉ የሰነድ ማስረጃ የቴምብር ቀረጥ የተከፈለበት መሆኑን ማረጋገጫ የሚሆን ቴምብር የተለጠፈበት ባለመሆኑ የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር አልቀበልም ብል እንደመለሰለት ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ ተመልክተናል ።
በፍትሐብሕር ክርክር ባለጉዲዩ ራሱ ቀርቦ እንዱከራከር ፍርድ ቤት ካላዘዘ በስተቀር ወይም ራሱ እንዱቀርብ የሚያስገድድ ሕግ ከላለ ራሱ ለመቅረብ የማይችል ወይም የማይፈቅድ ሲሆን ነገሩን ለማስረዲት ወይም ለመከራከር ለሚጠየቀዉ ሁለ በቂ መልስ ለመስጠት የሚችል ሰዉ በዋናዉ ባለጉዲይ ተተክቶ በነገረ ፈጅነት ፣በወኪልነት እና በጠበቃነት መከራከር እንደሚችል በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 57 ስር ከተደነገገዉ መረዲት ይቻላል።እንዱሁም ተሟጋች ስለማቆም በሚደነግገዉ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 63(1 እና 2) ስር እንደተመለከተዉ ከሳሽም ሆነ ተከሳሽ ስለራሱ ሆኖ እንዱከራከርለት ለሚፈልግ ሰዉ እንደራሴነት ካልሰጠዉ ወይም ነገረ ፈጅ ሆኖ እንዱሰራ ቀጥሮት ወኪል አድርጎ በመሾም የጽሁፍ ዉክልና ካልሰጠዉ በስተቀር ይህ ሰዉ ስለላላ ሰዉ ጉዲይ (ማንኛዉንም ተከራካሪ ወገን ወክል) ፍርድ ቤት ቀርቦ ለመከራከር እንደማይችልና ይህም የዉክልና ስልጣን ማስረጃ ከክሱ ወይም ከመልሱ ጋር ቀርቦ ክርክሩ በሚደረግበት የፍርድ ቤቱ መዝገብ ዉስጥ መቀመጥ እንዲለበት ተደንግጓል። በእነዚህ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎች ላይ ዉክልናዉ በጽሁፍ የተሰጠና በወካዩ የተፈረመ መሆን እንዲለበት የተደነገገ ቢሆንም የዉክልና ስልጣን ማስረጃዉ በሕግ ስልጣን በተሰጠዉ ዉል አዋዋይ አካል ተረጋግጦ መመዝገብ እንዲለበት አልተደነገገም።አንድ ተከራካሪ በሕግ ስልጣን በተሰጠዉ ዉል አዋዋይ አካል ተረጋግጦ ያልተመዘገበ ነገር ግን በጽሁፍ በተደረገ የዉክልና ስልጣን ማስረጃ ላይ ፈርሞበት ለተወካዩ ዉክልና ቢሰጥና የተወከለዉ ሰዉ ይህንኑ ይዞ ለፍርድ ቤቱ ቢያቀርብ ፍርድ ቤቱ አልተሟላም ብል ተወካይ ነኝ ሲል የቀረበዉን ሰዉ እንደተወካይ ሳይመዘግብ ያሰናብተዋል ወይስ ሰነደን ተቀብል ተከራካሪዉን ወክል እንዱከራከር ይፈቅድለታል የሚለዉን ከላልች ሕጎች አንጻር መመርመር ያስፈልጋል።
በሰነድች ማረጋገጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 922/2008 ስር አንቀጽ 9(1/ለ) ስር በግልጽ እንደተመለከተዉ የዉክልና ሥልጣን መስጫ ሰነድ በዚህ አዋጅ ሰነድችን እንዱያረጋግጥና እንዱመዘግብ ሥልጣን ለተሰጠዉ አካል ቀርቦ ተረጋግጦ መመዝገብ እንዲለበት ተደንግጓል። በዚሁ አንቀጽ የመግቢያ ዐረፍተ ነገር ላይ እንደተመለከተዉ የዉክልና ሥልጣን መስጫ ሰነድ በአዋጁ በተመለከተዉ መሰረት ካልተረጋገጠና ካልተመዘገበ ሕጋዊ ዉጤት እንደማይኖረዉ ተደንግጓል። ይህ ስነ ስርዓት እንዱፈጸም ሕግ አዉጪዉ የደነገገበት ምክንያት ዉክልና ሰዎች በራሳቸዉ መፈጸም የማይችለትን ሕጋዊ ተግባራት በልላ ሰዉ ማስፈጸም የሚችለበትን ሁኔታ የሚያመቻች የዉል አይነት ከመሆኑም በተጨማሪ መብትና ጥቅም የማስተዲደር፣ የማስተላለፍ እንዱሁም የወካዩ መብትና ጥቅም እንዲይጎዲ የመጠበቅና መሰል ተግባራት እንዱፈጸም ለተወካዩ ሥልጣን የሚሰጥ ሰነድ በመሆኑ ለወካዩ ፣ ለሦስተኛ ወገን መብትና ጥቅም እንዱሁም በዉክልና ሥልጣን የሚደረጉ ግብይቶች በማሳለጥ ለንግድ እንቅስቃሴዉና ተሳታፉዎቹ ጥበቃ ለማድረግ እንደሆነ ይታመናል።
ከዚህም በተጨማሪ የዉክልና ሥልጣን መስጫ ሰነድ ሥልጣን ባለዉ አካል ተረጋግጦ እንዱመዘገብ የሚፈለግበት ላላዉ ምክንያት በቴምብር ቀረጥ አዋጅ ቁጥር 110/1990(በአዋጅ ቀጥር 612/2001 እንደተሻሻለዉ) አንቀጽ 3/11 መሰረት የቴምብር ቀረጥ ለማስከፈል ጭምር ነዉ። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የቴምብር ቀረጥ ሳይከፈልበት የቀረበ የዉክልና መስጫ ሰነድ(ላልች ሰነድችንም እንደሚጨምር ልብ ይሎል) ከ10 ብር ያላነሰ ሁለት እጥፍ የቴምብር ቀረጥ ከተከፈለበት በኋላ ላላ ጊዜ በማስረጃነት ላቀርብ የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሕግ ማስረጃ የመቀበል ሥልጣን ባለዉ ሰዉ ወይም የመንግስት መሥሪያ ቤት ዘንድ በማስረጃነት ተቀባይነት እንደማይኖረዉ፣ ምልክት አደማይደረግበት ወይም ማረጋገጫ አንደማይሰጥበትም በዚሁ ሕግ አንቀጽ 10(1 እና 4) ስር ተደንግጓል። በመሆኑም በሕግ የዉክልና ሥልጣን መስጫ ሰነድ አረጋግጦ እንዱመዘገብ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ያልተረጋገጠና ያልተመዘገበ የዉክልና ሥልጣን ማስረጃ በመያዝ ላላ ሰዉ ወክል ለመሟገት የቀረብን ሰዉ ለመወከል ብቁ የሚያደርግህን የዉክልና ሥልጣን ማስረጃ ይዘህ አልቀረብክም ብል ፍርድ ቤቱ ሉያሰናብተዉ ይገባል።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመጣ አመልካች ሕጋዊ ሰዉነት የተሰጠዉ ሰዉ እንደመሆኑ የቀረበበትን ክስ መከላከል የሚችለዉ በተፈጥሮ ሰዉ በመወከል ስለሆነ ለቀረበበት ክስ ሬጅስትራር ጽ/ቤት ቀርቦ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘዉ መሰረት መልሱን ማቅረብ የሚችለዉ ለሚሟገትለት ሰዉ በሕግ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል የተረጋገጠና የተመዘገበ የዉክልን ሥልጣን ማስረጃ በመስጠት ላሆን ይገባዋል።በዚህ አግባብ ለሚሟገትለት ሰዉ የዉክልና ሥልጣን ማስረጃ ካልሰጠ መልሱን ይዞ የቀረበዉ ሰዉ በሱ የተወከለ ሰዉ መሆኑን ለማረጋገጥ ስለሚያዲግት ለራሱ መብት ጥበቃ ለማድረግ እና የዉክልና ሥልጣን መስጫ ሰነደ ያልተረጋገጠና ያልተመዘገበ በመሆኑ የቴምብር ቀረጥ ስላልተከፈለበት ከላይ በተጠቀሱ ሕጎች ድንጋጌዎች መሰረት የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር በሰነደ ላይ ምልክት አድርጎበት ከመዝገቡ ማያያዝ አይችልም።
እንዱሁም አመልካች ከመልሱ ጋር አያይዞ ያቀረባቸዉ ሰነድች በአዋጅ ቁጥር 110/1990 (ከአዋጁ ጋር የተያያዘዉን ሰንጠረዥ ጨምሮ) የቴምብር ቀረጥ ሉከፈልባቸዉ የሚገቡ ሰነድች አይደለም ብል አመልካች ያሰማዉ ክርክር ባለመኖሩ ከመልሱ ጋር አያይዞ ያቀረባቸዉ ሰነድች ከመዝገቡ ጋር ሉያያዙ የሚችለት የቴምብር ቀረጥ ሉከፈልባቸዉ ለሚገቡ ሰነድች የቴምብር ቀረጥ የተከፈለባቸዉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ቴምብር ካልተመታበት ከላይ በተጠቀሰዉ አዋጅ ቁጥር 110/1990 አንቀጽ 10/1 መሰረት በመዝገቡ ሉያያዙ አይችለም። ስለሆነም የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር አመልካችን ወክል የቀረበዉን ሰዉ እንደ አመልካች ተወካይ ቆጥሮ ይዞ የቀረበዉን ያልተመዘገበዉን የዉክልና ሥልጣን ማስረጃ እና የቴምብር ቀረጥ ያልተከፈለባቸዉን ከመከላከያ መልሱ ጋር ተያይዘዉ የቀረቡ ሰነድችን በመዝገቡ አለማያያዙ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 63/1 ፣ አዋጅ ቁጥር 922/2008 ስር አንቀጽ 9(1/ለ) እና አዋጅ ቁጥር 110/1990 አንቀጽ 10/1 ስር የተደነገገዉ ስለማይፈቅድለት ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ ከሚባል በስተቀር የሚነቀፍ አይደለም።
በተጨማሪም ስለጊዜ እና ስለቀጠሮ አወሳሰን በሚደነግገዉ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጋችን ክፍል በሚገኘዉ አንቀጽ 196/3 ስር እንደተደነገዉ ተጨማሪ ጊዜ ወይም ተለዋጭ ቀጠሮ እንዱሰጠዉ የሚጠይቅ አመልካች ሉፈጽም የሚገባዉን ነገር በመጀመሪያ በተሰጠዉ የጊዜ ዉሳኔ ዉስጥ ሳይፈጽም የቀረዉ ከአቅሙ በላይ ባልሆነ ምክንያት ሳይሆን በሥራ ብዛት፤ በዝንጋታ፤ በቸልተኝነትና በራሱ ጉድለት መሆኑ የታወቀ አንደሆነ አዱስ የጊዜ መራዘም ዉሳኔ እንደማይሰጥ በግልጽ ተደንግጓል።
አንደሚታወቀዉ የሥነ ሥርዓት ሕጉ ዓላማ ክርክሮች ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ እና በአነስተኛ ወጪ(በሂደቱ ተሳታፉ ለሚሆን የሰዉ ሀብትና ቁሳቁስ የሚወጣ ወጪና በክርክሩ ምክንያት የሚደርስ ኪሳራ አነስተኛ በሆነ ሁኔታ) ታይተዉ ፍትሐዊ ዉሳኔ በመስጠት ለክርክሮች እልባት ማስገኘት ነዉ።ይህ የሥነ ሥርዓት ሕጉ ዓላማ ሉሳካ የሚችለዉ ክርክሮች የተቀመጠላቸዉን ሂደቶች ተከትለዉና ለሂደቶቹ ጥበቃ ለማድረግ የተዘረጋዉ ሥርዓትና ድንጋጌዎች በጥብቅ ዱስፕሉን ተጠብቀዉ ሲፈጸሙ ብቻ ነዉ። በሕጉ የተዘረጋዉ ሥነ ሥርዓት የተከራካሪ ወገኖችን የመሰማትና ፍትህ የማግኘት መብት በማስጠበቅ መሰረታዊ ሕጎች ላይ የተረጋገጡ መብቶችና ጥቅሞች ተግባራዊ ይሆናለ ተብል ታምኖባቸዉ በመሆኑ የተከራካሪ ወገኖች የመሰማትና ፍትህ የማግኘት መብት የሥነ ሥርዓት ሕጉን ድንጋጌዎች ጠብቆ ዲኝነት በሚስጥበት ሂደት የሚረጋገጥ ነዉ።
አመልካች ከላይ በተመለከተዉ መሰረት ወደ ፍርድ ቤቱ መልስ እንዱያቀርብለት የላከዉ ሰዉ ያቀረበዉ የዉክልና ሥልጣን ማስረጃና መልስ የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር ሳይቀበለዉ በመቅረቱ መልሱን እንዱያቀርብ በተሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ ሳያቀርብ ቀርቷል። ይህም ተገቢ መሆኑን ከላይ ተመልክቷል።
በመቀጠል አመልካች ችልቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ መልሱን እንዱቀበለዉ ለችልቱ አቤቱታ አቅርቦ ችልቱ አቤቱታዉን ለተጠሪዎች እንዱያደርስ ትእዛዝ ሰጥቶት በተሰጠዉ ጊዜ አመልካች ለተጠሪዎች ሳያደርስ ቢቀርም ፍርድ ቤቱ በድጋሚ እንዱያደርስ ትእዛዝ ሰጥቶና የተጠሪዎችን አስተያየት ሰምቶ በሰጠዉ ትእዛዝ አመልካች መልሱን እንዱያቀርብ በታዘዘበት የመጀመሪያዉ ቀነ ቀጠሮ የዉክልና ሰነድ የያዘ ተወካይ ያላቀረበበትንም ሆነ ከመልሱ ጋር ተያይዞ ላቀረበዉ የሰነድ ማስረጃዎች የቴምብር ቀረጥ ከፍል አሟልቶ ያላቀረበበትን ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት አለመግለጹን፤ አሟልቶ የማቅረብ ግዳታ የራሱ ሆኖ ሳለ በራሱ ጉድለት ምክንያት መልስ በጽሁፍ ሳያያይዝ በመቅረቱ ተጨማሪ ጊዜ የሚሰጥበት የሕግ አግባብ የለም በማለት አቤቱታዉን ዉድቅ አድርጓል። ይህም ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 196/3 አንጻር ሲታይ አመልካች ማሟላት ያለበትን ነገር በማሟላት መልሱን በመጀመሪያ በተሰጠዉ ቀጠሮ ሳያቀርብ የቀረዉ ከአቅሙ በላይ የሆነ ምክንያት ገጥሞት እንደሆነ ለፍርድ ቤት ካላስረዲ በስተቀር ተለዋጭ ቀጠሮ ሉሰጠዉ አይችልም። የገጠመዉን ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ማስረዲት ካልቻለ በመጀመሪያዉ ቀጠሮ አሟልቶ ያልቀረበዉ በሥራ ብዛት፤ በዝንጋታ፤ በቸልተኝነትና በራሱ ጉድለት እንደሆነ ስለሚያሳይ የሥር ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ አልሰጥህም ማለቱ የሕጉን ዓላማ የሚያሳካ በመሆኑ የሕግ ድጋፍ ያለዉ ነዉ። ስለሆነም የአመልካች የመሰማትና ፍትህ የማግኘት መብት ሉጠበቅ የሚገባዉ ክርክሮችን በዘፈቀደ በመምራት ሳይሆን የሥነ ሥርዓት ሕጉ በዘረጋዉ ሥነ ሥርዓት ማእቀፍ ዉስጥ በመሆኑ ከዚህም አኳያ በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ ስህተት አላገኘንም።
በመቀጠል አመልካች ክሱ በተሰማበት እለት ክሱን ለመከላከል ያቀረብኳቸዉን የሰነድ ማስረጃዎች የስር ፍርድ ቤት ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 137 ስር የተደነገገዉን የሚጥስ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ በሚል ያቀረበዉን አቤቱታ በተመለከተ የያዝነዉን ጭብጥ መርምረናል። አመልካች በዚህ መልኩ ያቀረበዉን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለዉ የቀረዉ አመልካች መልሱን በጽሁፍ የማቅረብ መብቱ ስለታለፈ መልስ የመስጠት መብቱ ከታለፈ በኋላ የሰነድ ማስረጃ እንዱያያዝለት ያቀረበዉ ጥያቄ የሥነ ሥርዓት ሕጉን የተከተለ አይደለም በማለት መሆኑን መዝገቡን አስቀርበን በመመልከት አረጋግጠናል።
ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 223/1፣ 234/1 እና 145 ጣምራ ንባብ መገንዘብ እንደሚቻለዉ ተከሳሽ ክርክሩ በሚሰማበት ጊዜ ክርክሩን የሚያስረደለት የሰነድ ማስረጃዎች ካለት የሰነድ ማስረጃዎቹን ዘርዝሮና የሚያስረደለትን ፍሬ ነገር ለዚህ በተዘጋጀ የማስረጃ መግለጫ ላይ አመላክቶ እንዱሁም ሰነድቹ በእጁ የማይገኙና በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ የሚቀርቡ ከሆነም ይህንኑ በመግለጽ በእጁ የሚገኙት ሰነድች ትክክለኛ ግልባጭ ከመከላከያ መልሱ ጋር አያይዞ ማቅረብ እንዲለበት በአስገዲጅነት ተደንግጓል።
በልላ በኩል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 137(1-3) ስር እንደተደነገገዉ ተከራካሪ ወገኖች በእጃቸዉ የሚገኘዉን ወይም ለማቅረብ የሚችለትን ወይም ለክርክራችን ይጠቅመናል ብለዉ የሚያምኑበትን ወይም ፍርድ ቤቱ እንዱቀርብ የጠየቀዉንና አስቀድመዉ ፍርድ ቤት ያላቀረቡትን የጽሁፍ ማስረጃ ሁለ ዝርዝራቸዉንና ብዛታቸዉን ከሚገልጽ ጽሁፍ ጋር በመጀመሪያዉ ቀነ ቀጠሮ [ክሱን ለመስማት በተያዘዉ ቀነ ቀጠሮ] ወይም ከዚህ ቀነ ቀጠሮ በፉት ማቅረብ እንደሚችለ ተደንግጓል። ይህ ድንጋጌ ከሳሽም ሆነ ተከሳሽ የጽሁፍ ማስረጃ ለማቅረብ ሲፈልጉ የሚጠቀሙት እንደመሆኑ በዚህ አግባብ የተቀረጸበት ምክንያት ከሳሽም ሆነ ተከሳሽ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 223/1 መሰረት አስቀድሞ እንደ ቅደም ተከተላቸዉ የክስ አቤቱታ እና መከላከያ መልሳቸዉን ማቅረብ እንዲለባቸዉ ታሳቢ ያደረገ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ አንድ የፍትሐብሕር ክርክር የሚጀምረዉ የፍትሐብሕር ክስ አቤቱታ በሕጉ በተዘረጋዉ ስርዓት በጽሁፍ አስቀድሞ ከቀረበ በኋላ በመሆኑ ይህ መስፈርት ለከሳሽ አስቸጋሪ አይደለም። ተከሳሹ ግን በተለያየ ምክንያት መከላከያ መልሱን የማያቀርብበት ሁኔታ ስለሚኖር ተከሳሽ አስቀድሞ መከላከያ መልሱን በስነ ስርዓት ሕጉ መሰረት በጽሁፍ ያላቀረበ ከሆነ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 137ን በመጥቀስ ማስረጃ ይያያዝልኝ በማለት የሚያቀርበዉ ክርክር በዚህ ድንጋጌ በስተጀርባ ታሳቢ የተደረገዉን ቅድመ ሁኔታ ስለማያሟላ ተቀባይነት ሉሰጠዉ አይገባም። ምክንያቱም በተለያዩ ምክንያቶች ተከሳሽ መከላከያ መልሱን በተሰጠዉ ጊዜ ማቅረብ ካልቻለ ወይም የመከላከያ መልሱን የማቅረብ መብቱ ከታለፈ የሰነድ ማስረጃ የሚቀርበዉ በመከላከያ መልሱ ላይ ክድ መልስ የሰጠበትን ፍሬ ነገር ለመከላከል እንደመሆኑ አንድን ፍሬ ነገር ክድ መልስ ባልሰጠበት ሁኔታ ክሱ በሚሰማበት ጊዜ የሰነድ ማስረጃዎች እንዱያያዝለት የሚያቀርበዉ ጥያቄ ምን ለመከላከል እንደሆነ በግልጽ የሚታወቅ ባለመሆኑ ከዚህ አኳያ ማስረጃ ይያያዝልኝ ብል የሚነሳዉ ክርክር አመክኖያዊ ካለመሆኑም በተጨማሪ ጥያቄዉን መቀበል በሥነ ሥርዓት ሕጉ የተዘረጋዉን የክርክር አመራር ሂደቱን የሚያፊልስ በመሆኑ ነዉ።
ከዚህ በተጨማሪ አስቀድሞ በራሱ ጉድለት (ቸልተኝነት) መከላከያ መልሱን ያላቀረበ ተከሳሽ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 137ን በመጥቀስ ማስረጃዎቹ ምን እንደሚያስረደለት ከሚገልጽ ጽሁፍ ጋር የሰነድ ማስረጃዎች እንዱያቀርብ መፍቀድ በሕጉ የተደነገገዉን ስርዓት ተከትለዉ የመከላከያ መልሳቸዉንና ከመከላከያ መልሳቸዉ ጋር ያላቸዉን የሰነድ ማስረጃ ማቅረብ እየቻለ በቀጣይ ባለዉ ሂደት እናቀርባለን የሚለ ግደየለሽ ተከራካሪዎችን የማበራከት ዉጤት ስለሚኖረዉና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 223/1 እና 234/1 ድንጋጌዎችን ዉጤታማ ተፈጻሚነት ስለሚቀንስ አስቀድሞ መከላከያ መልሱን ያላቀረበ ተከሳሽ ክሱ በሚሰማበት ቀን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 137ን ጠቅሶ ከማስረጃ መግለጫ ጋር የሚያቀርበዉ የሰነድ ማስረጃ ይያያዝልኝ ጥያቄ የሥነ ሥርዓት ሕጉ ድጋፍ ያለዉ አይደለም።ስለሆነም ከዚህም አኳያ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች መልሱን በጽሁፍ የማቅረብ መብቱ ስለታለፈ መልስ የመስጠት መብቱ ከታለፈ በኋላ የሰነድ ማስረጃ እንዱያያዝለት ያቀረበዉ ጥያቄ የሥነ ሥርዓት ሕጉን የተከተለ አይደለም በማለት ዉድቅ በማድረጉና በዚህ ላይ የቀረበዉ ይግባኝ በመሰረዙ የተፈጸመ ስህተት አላገኘንም።በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን መከላከያ መልስ እና የሰነድ ማስረጃዎች ይያያዝልኝ አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ በመ/ ላይ በቀን 21/09/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለዉ ችልት በመ/ ላይ በቀን 20/02/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንተዋል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ።የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ ይመለስ።
በዚህ መዝገብ ላይ በቀን 10/03/2012 ዓ/ም የተሰጠዉ እግድ ተነስቷል ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.