ይግባኝ የተባለበት ፍርድ፣ዉሳኔ ወይም ትእዛዝ በይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት የተለወጠ ወይም የተሻሻለ እንደሆነ የተሻሻለዉ ወይም የተለወጠዉ ፍርድ ወይም ዉሳኔ ከመሰጠቱ በፉት በነበረዉ የመጀመሪያ ፍርድ፣ዉሳኔ ወይም ትእዛዝ መሰረት የተወሰደ ነገር እንዱመለስ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየዉ ፍርድ ቤት ተስማሚዉን ትእዛዝ መስጠት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 349
No summary available.
የሰ/መ/ ቀን 25/05/2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ በቀለ ኢሳያስ - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የፍርድ አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን ፍርደን በሚያስፈጽመዉ ፍርድ ቤት ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱ ተጠሪዎች በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት የተፈጸመ ሀራጅ እንዱፈርስ በማመልከት የተከራከሩ ሲሆን 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች የፍርድ ባለመብት በመሆን ፣ከተራ ቁጥር 7 እስከ 9 የተጠቀሱት የፍርድ ባለእዲ በመሆን እንዱሁም አመልካች በሐራጅ የተሸጠዉ ቤት ገዥ በመሆን በክርክሩ የተሳተፈ ናቸዉ። ከክርክሩ እንደተረዲነዉ በፍርድ አፈጻጸም መዝገብ ላይ ባቀረቡት አቤቱታ የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በሟች ወ/ሮ በየነች ንጉሴ ስም በአዱስ አበባ ከተማ ጉለላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 1 ቀጠና 8 ውስጥ የሚገኝ ቤት የውርስ ሀብት እንደሆነ በመግለጽ በወራሾች መካከል በስምምነት ክፍፍል እንዱፈጸም ይህ ካልሆነ በሐራጅ ተሽጦ የፍርድ ባለመብትና ባለእዲ ሆነዉ የተሰየሙ ተከራካሪዎች እኩል እንዱካፈለ በማለት በቀን 06/07/2010 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥቷል። በዚህ ዉሳኔ መሰረት በተሰጠ የፍርድ አፈጻጸም ትእዛዝ በወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ መነሻ አመልካች በጨረታ ተሳትፈዉ በቀን 09/12/2010 ዓ/ም ቤቱን በብር 208,000.00 ገዝተዋል።
አመልካች የሽያጩን ገንዘብ ገቢ አድረገዉ የቤቱ ስመ ሀብት በስማቸዉ ከመዞሩ በፉት ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱ ተጠሪዎች ፍርደን በመቃወም አቤቱታ በማቅረባቸዉ አፈጻጸሙ ታግድ መዝገቡ ተዘግቶ
No topics extracted.