ከአንድ በላይ ዳኞች በተሰየሙበት ችልት የችልቱ ዳኞች ተሟልተው በጉዲዩ ላይ ውይይት አድርገው በሙለ ድምጽ ወይም በአብላጫ ድምጽ ለመወሰን አቋም ሳይዙ ከተሰየሙት ዳኞች ከፉልቹ ብቻ ፈርመው የሚሰጡት ውሳኔ/ትዕዛዝ የስነ ስርዓት ጉደለት (irregular proceedings) ያለበት ስለመሆኑ በዲኝነት ታይቶ የተሰጠ የሥነ ሥርዓት ጉድለት (irregular proceedings) ያለበት ውሳኔ/ትዕዛዝ የማረም ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ወይም ችልት ቀርቦ በሚሰጥ ዲኝነት ይታረማል እንጂ በተከራካሪ ጀፍር ኮንስትራክሽን እና አስማማዉ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር አመልካችነት ወይም በፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት አነሳሽነት በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት በሚሰጥ አስተዲደራዊ ውሳኔ በሚደራጅ ችልት በድጋሚ ታይቶ እንዱታረም ማድረግ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 209/1 እና 211/2፣ አዋጅ ቁጥር 25/1988 (በአዋጅ ቁጥር 138/1991፣ በአዋጅ ቁጥር 254/1993 እንተሻሻለው እና በአዋጅ ቁጥር 454/1997 እንደገና እንደተሻሻለው) አንቀጽ 16(2/ሀ)፣ 18(ሀ/1)፣ 21፣ 22 እና 27(/1/ሐ) እንዱሁም የተሻሻለው የፍደራል ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 684/2002 አንቀጽ 6(1/ሰ)
No summary available.
መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ኑረዱን ከዱር ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ጀፍር ኮንስትራክሽን ተጠሪ፡- አስማማዉ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የግንባታ ሥራ ዉል አፈጻጸምን መሰረት ላደረገዉ ክርክር የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብል የቀረበ አቤቱታ መነሻ ያደረገ ሆኖ ይህ ዉሳኔ የተሰጠዉ ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት ተብል የሚወሰንበትን ሥርዓትና በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት አንድ ጉዲይ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩት ለማድረግ በሕግ የተሰጣቸዉ ሥልጣን ተግባራዊ የሚሆነዉ መቼና በምን ሁኔታ ነዉ የሚለትን ጭብጦች በተመለከተ ነዉ።
አመልካች በግልግል ዲኝነት ጉባኤ በተጠሪ ላይ በመሰረተዉ ክስ ከተጠሪ ጋር በቀን 20/01/2006ዓ/ም በፈጸመዉ የሕንጻ ግንባታ ዉል ሁለት ምድር ቤቶች፣አንድ የመነሻ ፍቅና ዘጠኝ ፍቆች ያለት የሆቴል ሕንጻ በጠቅላላ ዋጋ በብር 44,475,608.75 ለመገንባት ተስማምቶ የዋጋዉን 10% ቅድመ ክፍያ ተቀብሎል።ተጠሪ አንድ ተጨማሪ ፍቅ እንዱጨመር በመጠየቁ የዱዛይን ክለሳ ከተደረገ በኋላ በአመልካች ለተሰራዉ ስራ ክፍያ ተጠይቆ አምስት ጊዜያዊ የክፍያ ምስክር ወረቀቶች (Interim payment certificates) ተዘጋጅተዉ በተዋዋዮችና በአማካሪ መሐንዱሱ በጊጋር ኮንሰልት እየጸደቁ ቢቀርቡም ተጠሪ በመጀመሪያዉ የክፍያ ምስክር ወረቀት የተጠየቀዉን ቢከፍልም ከሁለተኛ የክፍያ ምስክር ወረቀት ያልተከፈለዉን ቀሪ ክፍያ፣ ከሶስተኛ እስከ አምስተኛ ምስክር ወረቀቶች የተጠየቀዉን ክፍያ አልከፈለም።በዉለ ጠቅላላ ሁኔታዎች አንቀጽ 59.2.4 መሰረት ክፍያ አለመፈጸም ዉለን ለማቋረጥ የሚያበቃ መሰረታዊ የዉል ጥሰት ነዉ።በተጨማሪም ተጠሪ የዉለን አንቀጽ 59.2.2 በመተላለፍ ሥራዉ ከ28 ቀናት በላይ እንዱቆም አድርጓል።በእነዚህ ምክንያቶች አመልካች ዉለን በማቋረጥ በዉለ ላይ በመጀመሪያ ጉዲዩ ለአማካሪ መሐንዱስ ታይቶ መወሰን ስላለበት ለአማካሪ መሐንዱሱ አቅርቦ ማስወሰኑን ገልጾ ከሁለተኛ ክፍያ ምስክር ወረቀት ሳይከፈል የቀረዉን፣ ከሶስተኛ እስከ አምስተኛ ምስክር ወረቀቶች ተጠይቆ ያልተከፈለዉን ብር 9,282,136.82፣ክፍያ ለዘገየበት ጊዜ የታሰበ ወለድ ብር 1,022,707.50፣የቀረ የትርፍ ጥቅም ብር 1,695,261.09፣ሥራዉ በመዘግየቱ ያስከተለ ተጨማሪ ወጪ ብር 1,770,691.38፣ተቀንሶ የተያዘ ክፍያ ብር 874,183.94፣በግንባታ ስፍራ የሚገኙ ቁሳቁሶች ዋጋ ብር 31,344.16፣ተጨማሪ እሴት ታክስ(ተ.እ.ታ) ብር 655,722.02 በድምሩ ብር 14,447,339.50 ተጠሪ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪ ለክሱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም በሰጠዉ የፍሬ ነገር መልስ ዉለ ከተቋረጠ በኋላ ጊዜያዊ የክፍያ ምስክር ወረቀት መሰረት በማድረግ (የመጨረሻ የክፍያ ምስክር ወረቀት ባለመሆኑ) ክፍያ አልተፈጸመም በሚል ምክንያት ክስ መመስረት አይችልም። አማካሪ መሀንዱሱ የክፍያ ምስክር ወረቀቶቹን ያጸደቀዉ በአመልካች ጋር በመመሳጠር ነዉ።ይህ በመታወቁ አማካሪ መሐንዱሱ በልላ ላይፍ ኮንሰልት በተባለ አማካሪ መተካቱ ለአመልካች ተገልጾለት እያለ ለዚህ አማካሪ አመልካች የክፍያ ጥያቄ አላቀረበለትም።በዉለ አንቀጽ 43.1 መሰረት የወለድ ጥያቄዉ በአማካሪ መሐንዱሱ ያልጸደቀ በመሆኑ ተቀባይነት የለዉም።በኋለኛዉ አማካሪ መሐንዱስ በተዘጋጀዉ የማጠቃለያ ክፍያ ምስክር ወረቀት አመልካች የሰራዉ ሥራ ሙለ በሙለ ግድፈት ያለዉ(Defective)መሆኑ ስለተረጋገጠ በዉለ ጠቅላላ ሁኔታዎች አንቀጽ 57 እና 60/2 መሰረት አመልካች ሉያነሳዉ የሚችል የክፍያ ጥያቄ አይኖርም።አማካሪ መሀንዱሱ ባጸደቀዉ የመጨረሻ ክፍያ የምስክር ወረቀት አመልካች በዉለና በዉለ መሰረት በጸደቁት የሥራ ለዉጥ ትእዛዞች (Variation Orders)መሰረት የሰራዉ ሥራ ዋጋ ብር 11,563,316.00 ሲሆን የተከፈለዉ ከተ.እ.ታ በፉት ብር 11,311,995.00 ነዉ።በአጠቃላይ አመልካች የሕንጻዉን የመዲረሻ ወለል(Lobby entrance floor)ከዋናዉ የቦላ መንገድ ጋር በእኩል ከፍታ መስራት ሲገባዉ ከመንገደ በላይ 1.34 ሜትር አስበልጦ በመስራቱ ሕንጻዉ ለታቀደለት ተግባር እንዲይዉል ስለሚያደርገዉ በዱዛይኑ መሰረት እንዱያስተካክል ተጠይቆ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።የመሰረቱ የኮንክሪት ንጣፍ፣የግድግዲ አፈር መጠበቂያ ስራዉ፣ እና የኮንክሪት ምሰሶዎች በሕግ የተቀመጠዉን ደረጃ በጠበቀ አኳኋን አልተሰሩም።እንዱሁም የዉሃ መከላከያ ጥጋቱ በሸክላ መሰራት ሲገባዉ ዉስጡ ክፍት በሆነ ብልኬት የተሰራ በመሆኑ እነዚህ ግድፈቶች ሕንጻዉን በማይጠገንበት ደረጃ ያደረሱ ስለሆኑና ይህም በአመልካች ጥፊት የደረሰ በመሆኑ በዉለ መሰረት ለአመልካች ክፍያ አይገባዉም በማለት ተከራክሯል።
እንዱሁም ተጠሪ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በማቅረብ የግንባታ ሥራዉ በአግባቡ አልተሰራም በማለት አስቀድሞ ለአመልካች የተከፈለ ገንዘብ እንዱመለስለት፣የካሳ ክፍያና የተሰራዉ ሥራን ለማስፈረስ የሚያስፈልግ ወጪ ጨምሮ በድምሩ ብር 17,126,759.00 እንዱከፈለዉ ዲኝነት ጠይቋል።አመልካች ለተከሳሽ ከሳሽነቱ ክስ በሰጠዉ መልስ ለተከሳሽ ከሳሽነቱ ክስ መሰረት ያደረገዉ ላይፍ ኮንሰልት የተባለዉ አማካሪ መሐንዱስ የሰራዉን ሪፖርት ነዉ።ተጠሪ አማካሪ መሐንዱሱን የቀጠረዉ ዉለ ከተቋረጠ ከረጅም ጊዜ በኋላ በመሆኑና ግንባታዉን ሲቆጣጠርና ዉለን ሲያስተዲድር የነበረዉ ጊጋር የተባለዉ አማካሪ መሐንዱስ የቁጥጥር ሥራዉን ሰርቶ ክፍያዉን ያጸደቀ በመሆኑ ግንባታዉን ተቆጣጥሮ ያልሰራዉን መሐንዱስ አማካሪ አድርጎ መቅጠሩም ሆነ ይህ አማካሪ ያቀረበዉን ሪፖርት መሰረት አድርጎ ያቀረበዉ ክስ የሕግም ሆነ የዉል ድጋፍ ስለላለዉ ክሱ ዉደቅ ላሆን ይገባል የሚለትንና ላልች መከራከሪያዎችን በማንሳት ክሱ ዉድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል።
የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የግራ ቀኙን ክርክር፣ምስክሮች፣የሙያ ምስክርነት በመስማት እና የሰነድ ማስረጃዎች በመመርመር በቀን 18/01/2011ዓ/ም በአብላጫ ድምጽ በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ ዉለ ከተቋረጠ በኋላ ላይፍ ኮንሰልት የተባለዉን አማካሪ ስለቀጠረ ይህ አማካሪ በቀጣይ የሚኖረዉን የግንባታ ሂደት በተመለከተ የሙያ ድጋፍ ላሰጥ ከሚችል በስተቀር በግራ ቀኙ መካከል በነበረዉ ዉል መነሻ የተሰራዉን ግንባታ በተመለከተ ወደ ኋላ ተመስርቶ አማካሪ መሐንዱስ መሆን ስለማይችል ይህ አማካሪ መሀንዱስ ያዘጋጃቸዉን ማስረጃዎች ተቀባይነት የለዉም በማለት እነዚህን ማስረጃዎች መሰረት በማድረግ ተጠሪ ያቀረበዉን ክርክር ዉድቅ አድርጓል።አመልካች የግንባታ ሥራዉን በዉለ እና በዱዛይኑ መሰረት ባለመስራቱ እና የተሰራዉ የሕንጻ ግንባታ ጉድለት ያለበት ሆኖ እያለ ዉለን አለአግባብ አቋርጧል በማለት አመልካች በክፍያ ምስክር ወረቀቶቹ ሉከፈለኝ ይገባል ሲል የጠየቀዉን እና ለላልች በክሱ የጠየቃቸዉ ክፍያዎች እንዱሁም በግንባታ ሥፍራ ቀርተዋል የተባለ እቃዎች ከነዋጋ ግምታቸዉ በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በማለት ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።ተጠሪ ያቀረቡትን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በተመለከተ በአመልካች የተሰራዉ ግንባታ ሥራ ላይ ያለዉ ጉድለት በተጨማሪ ሥራ ሉስተካከል እንደሚችል በማስረጃ በመረጋገጡና ይህም በተጠሪ ላይ ተጨማሪ ኪሳራ ስለሚያስከትልበት አመልካች ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ የክፍያ ምስክር ወረቀቶች እንዱከፈለዉ ጠይቆ ሳይከፈለዉ የቀረዉ ብር 7,461,146.02 ተጠሪ ጉድለቱን ለማስተካከል የሚደርስበትን ኪሳራ ለመካስ በቂ ነዉ በማለት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2102/1 የተደነገገዉን በመጥቀስ በርትእ በመወሰን ለተጠሪ የሚከፈል ክፍያ የለም በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሁለቱም ወገኖች በተለያዩ መዝገቦች ላይ ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ በመ/ ላይ በቀን 30/01/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ የሰጠዉን ዉሳኔ በማሻሻል የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ በላይፍ ኮንሰልት የቀረበዉን ሙያዊ አስተያየት ሳይቀበል ከግራ ቀኙ የቀረቡትንና ላልች ማስረጃዎችን መሰረት አድርጎ የግራ ቀኙን ክርክር ማየቱ ተገቢ ነዉ።እንዱሁም የግልግል ዲኝነት አካለ አመልካች የሰራዉ ግንባታ ጉድለት አለበት በማለት እንዱሁም አመልካች እንዱከፈለዉ የጠየቀዉ የተለያዩ ክፍያዎች ሉከፈለዉ አይገባም ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ ነዉ በማለት ወስኗል።በልላ በኩል የተለያዩ ጭብጦችን በመያዝ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ ግራ ቀኙ በሚመርጡት ወይም በልላ ገለልተኛ ኮሚቴ ወይም በባለሙያ እንዱጣራ አድርጎ የመሰለዉን እንዱወስን ጉዲዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 343/1 መሰረት ለግልግል ዲኝነት ጉባኤ መልሶለታል።
አመልካች በቀን 09/03/2012 ዓ/ም በ20 ገጽ ላይ የተጸፈ የሰበር የአቤቱታ ያቀረበዉ ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጡ ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ሲሆን ይዘቱ በአጭሩ፡-የግንባታ ሥራዉን የሚቆጣጠረዉና ዉለን የሚያስተዲድረዉ አማካሪ መሐንዱስ በኩል አመልካች የሰራዉ ግንባታ ጉድለት አለበት በሚል አልተረጋገጠም።በሁለቱም በኩል ያለት የሕንጻዉ መግቢያዎች በየአቅጣጫዉ ካለዉ መንገድ ጋር ታሳቢ ተደረጎ ዱዛይን የተሰራዉ ዋናዉ የቦላ መንገድ እንደገና ከመሰራቱ በፉት ሲሆን የቦላ መንገድ ፈርሶ እንደ አዱስ በመሰራቱና መንገደ ቀድሞ ከነበረበት ዝቅ በማለቱ ምክንያት የሕንጻዉ ሁለቱ መግቢያዎች በኩል ያለዉ የመንገድ ከፍታ ቢለያይም ይህንን ታሳቢ በማድረግ በአማካሪ መሐንዱሱ በተሰጠ ማስተካከያ መሰረት በአመልካች ግንባታ ተፈጸመ እንጂ በአመልካች ጥፊት ምክንያት የተፈጠረ ጉድለት አይደለም።ተጠሪ በአማካሪ መሐንዱሱ በጸደቁት ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ የክፍያ ምስክር ወረቀቶች የተጠየቁ ክፍያዎች ቅሬታ ካለዉ ለአማካሪ መሐንዱሱ በማቅረብ ከማሳረም በስተቀር ክፍያዉን አልፈጽምም ማለት ስለማይችልና አማካሪ መሀንዱሱ የተሰራዉ ስራ ትክክል መሆኑን አረጋግጦ እያለ ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ የክፍያ ምስክር ወረቀቶች የተጠየቀዉን ክፍያ ተጠሪ እንዱከፍል አለመወሰኑ በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን አስገዲጅ ትርጉም እና የዉለን አንቀጽ 24 የሚቃረን ነዉ።ተጠሪ ግንባታዉ እንዱቆም የሰጠዉ ትእዛዝ በ28 ቀናት ዉስጥ አለማንሳቱና በአማካሪ መሃንዱሱ የተፈረሙ የክፍያ ምስክር ወረቀቶችን በ90 ቀናት ዉስጥ አለመክፈለ መሰረታዊ የዉል ጥሰት በመሆኑ በአማካሪ መሃንዱስ የተረጋገጡ ክፍያዎች ከ13.75 ወለድ ጋር ለአመልካች እንዱከፈል አለመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።እንዱሁም በክሱ የተጠየቁ ላልች ክፍያዎች ለአመልካች ሉከፈል እንደሚገባ ዉልንና ሕግን መሰረት በማድረግ በማስረጃ ተድግፍ ተጠይቆ እያለ በግልግል ዲኝነት ጉባኤዉና በይግባኝ ሰሚዉ ችልት ዉድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።የተጠሪ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱን ያቀረበዉ የግንባታ ሥራዉን ሲቆጣጠርና ዉለን ሲያስተዲድር ባልነበረ እና የግንባታ ዉለ ከተቋረጠ ከረጅም ጊዜ በኋላ የተቀጠረዉ አማካሪ ያቀረበዉን ማስረጃ መሰረት በማድረግ በመሆኑ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ዉድቅ መደረግ ነበረበት።ዉሳኔዎቹ ተሽረዉ በድምሩ ብር 14,447,339.40 ከነወለደ ለአመልካች ሉከፈል ይገባል ተብል ይወሰንልኝ በማለት አቤቱታዉን አቅርቧል።
አንደኛ ሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ በቀን 30/06/2012 ዓ/ም በሁለት ዳኞች ተፈርሞ በኮምፒዩተር በተዘጋጀ የትእዛዝ ፍርም ላይ ተፈርሞበት ትእዛዝ መሰጠቱን መዝገቡ ያሳያል።የትእዛዙ ይዘትም፡- ‛በቀረበዉ የሰበር አቤቱታ በግልግል ዲኝነት ጉባኤና በይግባኝ ሰሚዉ ችልት በተሰጡ ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተሰርቷል ለማለት የሚያስችል እንዲልሆነ ገልጾ ጉዲዩ ለሰበር ችልት የሚያስቀርብ አይደለም ብለናል። መዝገቡ ስለተዘጋ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ“ የሚል ይዘት ያለዉ ሲሆን በተጨማሪም በዚሁ ትእዛዝ በእጅ በእስክርብቶ ተጽፍ ‛የሐሳብ ልዩነት ከመሰጠቱ በፉት ለመነጋገር“ የሚል ጽሁፍ እንደተጨመረበትና በችልቱ ከተሰየሙት ሶሰት ዳኞች መካከል ሰብሳቢዉ ዲኛ በትእዛዙ ላይ ፊርማቸዉን እንዲላኖሩ መዝገቡ ያሳያል።
በልላ በኩል አመልካች በቀን 14/07/2012 ዓ/ም ለፍርድ ቤቱ ፕሬዚዲንት በጻፈዉ አቤቱታ ‛… የሰበር አቤቱታ አቅርቤ መዝገቡ ለተመራለት ለ1ኛ ሰበር አጣሪ ችልት ቅሬታዬን ያሰማሁ ቢሆንም በዲኝነት ሥራ ፍጹም ባልተለመደ መልኩ ችልቱ እስከ ዛሬ ድረስ በቅሬታዬ ላይ ምንም አይነት ትእዛዝ ሳይሰጥበት መዝገቡም ከቀጠሮ ዉጪ ሆኖ በመንከራተት ላይ እገኛለሁ…በግልግል ዲኝነት አካልና በይግባኝ ሰሚዉ ችልት የተሰጠዉ ዉሳኔ ሰበር ሰሚ ችልት አስቀድሞ የሰጠዉን አስገዲጅ ዉሳኔ የሚቃረን በመሆኑ የፍትህ መጓደልን ያስከተለ ፍርድ ሆኖ እያለ ሳይታረምና መዝገቡ ከነጭራሹ ከቀጠሮ ዉጪ መሆኑ ተገቢነት የላለዉ ስለሆነ ክብርነቶዎ ይህንኑ ተገንዝበዉልኝ ሕጉ በሚፈቅደዉ አግባብ ጉዲዩ ታይቶ ተገቢዉ ትእዛዝ እንዱሰጥ አመለክታለሁ።“ሲል ጠይቋል።ይህንን ተከትል የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዲንት አቤቱታዉን በማጠፍ የሚከተለዉን በማስፈር፡- ‛በዚህ ጉዲይ ላይ በችልቱ ዳኞች የሀሳብ ልዩነት ስለተከሰተ እና ጉዲዩም ወሰብሰብ ስለሚል ሁለት ዳኞች (ዳኞች በስም ተጠቅሰዋል) ተጨምረዉ በአምስት እንዱታይ ታዟል።“ በጊዜዉ ለነበሩት ለ1ኛ ሰበር አጣሪ ችልት ሰብሳቢ ዲኛ አቤቱታዉን መርተዋል።
በመቀጠልም በችልቱ በነበሩት ሶስት ዳኞች ላይ ሁለት ዳኞች ተጨምረዉ አምስት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት የሰበር አቤቱታዉ ተመርምሮ በግልግል ዲኝነት አካለና በይግባኝ ሰሚዉ ችልት በተሰጡ ዉሳኔዎች ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ያለዉን ነጥቦች በመለየት ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ እንዱታይና ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ በአብላጫ ድምጽ በቀን 29/07/2012ዓ/ም ትእዛዝ ሰጥቷል።ከተሰየሙት አምስት ዳኞች ሁለቱ ዳኞች አስቀድሞ በሰጠነዉ ትእዛዝ በነበረን አቋማችን ጸንተናል በማለት በሀሳብ ተለይተዋል። ይህንን ተከትል ተጠሪ በቀን 02/10/2012ዓ/ም የአመልካች አቤቱታ በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገዉ ፍጹም ከሕግ እና ከሥነ ሥርዓት ዉጪ ነዉ ያለበትን ምክንያት እና ዋናዉን ጉዲይ የሚመለከት መከራከሪያ በ13 ገጽ ጽፍ ያቀረበ ሲሆን አቤቱታዉ ለዚህ ችልት እንዱቀርብ የተደረገበት አግባብ ከሕግ ዉጪ ነዉ ያለበትን ምክንያት በአጭሩ በሚከተለዉ መልኩ አቅርቧል፡አመልካች ያቀረበዉን የሰበር አቤቱታ አቅርቦና ሶስት ዳኞች ለተሰየሙበት ችልት ካስረዲ በኋላ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት የሚያስችል ባለመሆኑ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት አያስቀርብም ሲል በቀን 30/06/2012ዓ/ም በአብላጫ ድምጽ ወስኖ መዝገቡ እንዱዘጋ አዟል። በአብላጫ ድምጽ የተሰጠዉ ዉሳኔ በፍርድ ቤቱ ድህረገጽ ላይ ከመለጠፈም በተጨማሪ በፍርድ ቤቱ የመረጃ ቋት (data base) እና በፍርድ ቤቱ አጭር የስልክ ቁጥር 992 በአጭር መልእክት(SMS) ተገልጾልናል። የልዩነት ሀሳብ መጻፍ የነበረባቸዉ ዲኛ የልዩነት ሀሳብ ጽፈዉ መዝገቡን ሳይመልሱ አዘግይተዋል።ከዚህ በኋላ አመልካች በቀን 14/07/2012ዓ/ም ፍትህ ተጓደለብኝ የሚል አቤቱታ አቅርበዉ የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዲንት በአብላጫ ድምጽ ዉሳኔ በተሰጠበት ጉዲይ ‛የሀሳብ ልዩነት ስለተከሰተ እና ጉዲዩም ዉስብስብ ነዉ በሚል ምክንያት ጉዲዩን አምስት ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩት በማለት በማዘዝ“ ጉዲዩ በድጋሚ እንዱታይ ለማድረግ በሕግ ሥልጣን አልተሰጣቸዉም።የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት አንድን ጉዲይ አምስት ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩ ማድረግ እንዱችለ ሕጉ ሥልጣን የሚሰጣቸዉ ጉዲዩ ዉሳኔ ከማግኘቱ በፉት እንጂ ጉዲዩ ላይ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ አይደለም።በተያዘዉ ጉዲይ በተሰጠ ዉሳኔ ለሰበር ሰሚ ችልት የሚያስቀርብ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈጸመም ተብል በአብላጫ ድምጽ ዉሳኔ የተሰጠ በመሆኑ ከዚህ በኋላ አምስት ዳኞች ተሰይመዉ ጉዲዩን እንዱያዩ በማድረግ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ እንዱታይ የተደረገበት አግባብ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 22 መሰረት የተሰጠ ዉሳኔ ዉጤት አልባ አድርጓል። ይህም በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 79/3 እና በአለም አቀፍ እና አህጉራዊ ስምምነቶች ዳኞች የዲኝነት ተግባራቸዉን በሙለ ነጻነት ያከናዉናለ ከሕግ በስተቀር በልላ ሁኔታ አይመሩም በማለት የደነገጉትን መርሆ እና የሕግ የበላይት የጣሰ ነዉ።በመሆኑም የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዲንት በቀን 22/07/2012ዓ/ም ጉዲዩ በአምስት ዳኞች እንዱታይ የሰጡት ትእዛዝም ሆነ በዚህ መነሻ አምስት ዳኞች ተሰይመዉ በአብላጫ ድምጽ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ እንዱታይ የሰጡት ትእዛዝ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9/1 መሰረት ተፈጻሚነት የለዉም በማለት ከሥነ ሥርዓት ዉጪ በሆነ አግባብ የቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ዉድቅ እንዱደረግ በመጠየቅ መልሱን በመስጠት ተከራክሯል።
አመልካች በቀን 17/02/2013ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ በአብላጫ ድምጽ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት አያስቀርብም ተብል ተወስኖ አቤቱታዉን ላቀረበዉ አመልካች በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ 180 እና 181 መሰረት ተነብቦ የተገለጸልን ዉሳኔ ወይም ትእዛዝ የለም። ተጠሪ በሁለት ዳኞች ተሰጠ ባለዉ ትእዛዝ
መጥሪያ ስናወጣ ነዉ።በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 181 መሰረት ለተከራካሪ ወገኖች ያልተገለጸ ዉሳኔ እንደረቂቅ እንጂ እንደ ዉሳኔ ሉቆጠር አይችልም። አመልካች የሰበር አቤቱታ ካቀረብኩና ከተሰማሁ በኋላ መዝገቡ ላይ ትእዛዝ ባለመሰጠቱ ስመላለስ በዳኞች ጉዲዩ ለሰበር አያስቀርብም ተብል መዝገቡ ተዘግቷል በሚል ስላልተገለጸልኝ ለፍርድ ቤቱ ፕሬዚዲንት አቤቱታ አቅርቤ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 21/1 ስር በተሰጣቸዉ ስልጣን መሰረት በጉዲዩ ላይ የተሰጠ ዉሳኔ እንደላለ አረጋግጠዉ ጉዲዩን አምስት ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩ ያደረጉት በሕግ በተሰጣቸዉ ስልጣን በመሆኑ ተጠሪ ያለአግባብ አቤቱታ ስላቀረበ ሥነ ሥርዓታዊ እርምጃ ሉወሰድበት ይገባል።ተጠሪ አያስቀርብም በሚል ተገልጿል ብል የገለጸዉ በዲታ ቤዝ ሰራተኞች በተፈጠረ ስህተት መሆኑ ተረጋግጦ ስህተቱ ስለታረመ አምስት ዳኞች ተሰይመዉ የተሰጠ ትእዛዝ ሕጉን የተከተለ ነዉ በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክር፣ በግልግል ዲኝነት አካል እና በይግባኝ ሰሚ ችልት የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት እና ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለበትን አግባብ የሚያሳይ ሲሆን እኛም ዋናዉ ጉዲይ ከመመርመሩ በፉት ተጠሪ የሰበር አቤቱታዉ ለዚህ ችልት የቀረበዉ በሕግ ከተደነገገዉ ሥነ ሥርዓት አግባብ ዉጭ ነዉ በማለት ባቀረበዉ መከራከሪያ መነሻ ለተደረገዉ ክርክር አስቀድሞ ዉሳኔ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን በማመን 1) ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት ብል እንዱወስን መዝገቡ የተመራለት አጣሪ ችልት አስቀድሞ ሰጠ የተባለዉ ትእዛዝ የሚኖረዉ ሕጋዊ ዉጤት ምንድን ነዉ? 2) የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት አንድ ጉዲይ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት ችልት እንዱታይ ለማድረግ በሕግ የተሰጣቸዉ ሥልጣን ተግባራዊ የሚሆነዉ መቼና በምን ሁኔታ ነዉ? እንዱሁም 3) ጉዲዩ ለዚህ ችልት ቀርቦ እንዱታይ የተደረገዉ በሕግ የተዘረጋዉን ሥነ ሥርዓት በመከተል ነዉ ወይ ? የሚለ ጭብጦችን በመያዝ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
በመጀመሪያም ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት ብል እንዱወስን መዝገቡ የተመራለት ሰበር አጣሪ ችልት አስቀድሞ ሰጠ የተባለዉ ትእዛዝ የሚኖረዉ ሕጋዊ ዉጤት ምንድን ነዉ?በሚል የያዝነዉን ጭብጥ መርምረናል።በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 22/1 ስር በተደነገገዉ መሰረት አንድ ዉሳኔ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 10 መሰረት በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር የሚሰማዉ አስቀድሞ ሦስት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የተሰየሙበት ችልት ዉሳኔዉ ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት ብል ሲወስን ነዉ።በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ የመጨረሻ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ወይስ አይደለም የሚል ጭብጥ መርምሮ ሰበር ሰሚ ችልት መወሰን የሚችለዉ ሦስት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የተሰየሙበት ችልት(በተለምድ ሰበር አጣሪ ችልት የሚባለዉ) ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት ብል ሲወስን ነዉ።በዚህ ድንጋጌ ሶስት ዳኞች የተሰየሙበት የሚለዉ የሕጉ ይዘት የሚያሳየዉ ሶስቱም ዳኞች አመልካቹ ያቀረበዉን አቤቱታና ዉሳኔዉን መርምረዉና እንደነገሩ ሁኔታ አመልካቹን በመስማት ተወያይተዉ በጉዲዩ ላይ ዉሳኔ መስጠት እንዲለባቸዉ ነዉ። በተጠቃሹ ድንጋጌ መሰረት ሰበር አጣሪ ችልት የሰበር አቤቱታዉንና ለአቤቱታዉ መሰረት የሆነዉን ዉሳኔ መርምሮ ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት ወይም የለበትም ብል የሚሰጠዉ ትእዛዝ እንደ ዉሳኔ የሚቆጠር ነዉ።በአዋጅ ቁጥር 25/1988 ላይ ሰበር አጣሪ ችልት ዉሳኔ የሚሰጥበት ጊዜ፣ዉሳኔ የሚሰጥበት ሁኔታና የዉሳኔዉ ይዘት(ፍርም) ምን ላሆን እንደሚገባ በግልጽ አልተደነገገም።በመሆኑም አንድን የሕግ ድንጋጌ እንደነገሩ ሁኔታ አገናዝቦ ተግባራዊ ማድረግን የሚፈቅደዉን መርህ (Principle of mutatis mutandis) የሰበር ባህሪይን ባገናዘበ መልኩ በመጠቀም እንደ ጉዲዩ አይነት ስለ ፍርድ ዉሳኔ አሰጣጥ እና አጻጻፍ እንዱሁም ዉሳኔዉ ስለሚነበብበት አግባብ በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት እና በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግጋት የተደነገገዉን እንደ አግባብነቱ ተግባራዊ እንዱያደርግ ይጠበቃል።የተያዘዉ ጉዲይ የፍትሐ ብሓር ጉዲይ በመሆኑ ስለፍርድ ዉሳኔ አሰጣጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 180 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች የተመለከተዉን እንደ አግባብነታቸዉ ተፈጻሚ ማድረግ ያስፈልጋል።
በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 12/1 ላይ እንደተደነገገዉ የመንግስት አሰራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት።ፍርድ ቤት አንደኛዉ የመንግስት አካል እንደመሆኑ በሕግ በተደነገገ ልዩ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር የሚሰጠዉን የዲኝነት አገልግልት ለተከራካሪ ወገኖች ብቻ ሳይሆን ለሕዝብ ግልጽ በሆነ አኳኋን መተግበር ይኖርበታል።ይህንን ግዳታዉን ለመወጣት ከሚከተልባቸዉ ሥነ ሥርዓቶች መካከል ክርክሮችን በግልጽ ችልት መስማት እና ለክርክሮች የሚሰጠዉን እልባት ለተከራካሪ ወገኖች ግልጽ በሆነ አኳኋን መስጠትና መግለጽ(ማሳወቅ)አንደ ነዉ።በተለይ ከፍርድ ዉሳኔ አሰጣጥና ዉሳኔዉን ከማሳወቅ/ከመግለጽ ጋር በተያያዘ የሰበር አጣሪ ችልት የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ ከሰማና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የተባለዉን ዉሳኔ ከመረመረ በኋላ ወዱያዉኑ ወይም በሚወስነዉ አጭር ቀነ ቀጠሮ በግልጽ ችልት ዉሳኔ መስጠት እንዲለበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 180 ስር የተደነገገዉ ያስገነዝባል።እንዱሁም የሚሰጠዉ ዉሳኔ ወይም ትእዛዝ በጽሁፍ ተዘጋጅቶ በአስቻለት ዳኞች/ዲኛ ተፈርሞ ለተከራካሪ ወገኖች መነበብ እንዲለበት እና በአብላጫ ድምጽ የተሰጠ ዉሳኔ ከሆነም ገዥ የሚሆነዉ ዉሳኔ አብላጫ ቁጥር ባላቸዉ ዳኞች የተወሰነዉ ሆኖ በሀሳብ የተለየዉ ዲኛ የልዩነት ሀሳቡን በጽሁፍ ማስፈር እንዲለበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 181(1 እና 2) ስር የተደነገገዉ ያሳያል።
በተጨማሪም ዉሳኔ ለተከራካሪዎች በንባብ ከማሰማት ጋር በተያያዘ ዉሳኔዉን የሰጡ ዳኞች በዉሳኔዉ ላይ ፊርማቸዉን እስካኖሩ ድረስ ላላ ዲኛ ዉሳኔዉን በንባብ ሉያሰማ ይችላል(በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 181/3 ይመለከቷል)።
በያዝነዉ ጉዲይ መዝገቡ እንደሚያሳየዉ ሶስት ዳኞች በተሰየሙበት በሁለት ዳኞች ተፈርሞ በቀን 30/06/2012 ዓ/ም በተጻፈ ትእዛዝ የሰበር አቤቱታ በቀረበበት ዉሳኔ ላይ ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንዲልተፈጸም ተገልጾ መዝገቡ እንዱዘጋ መታዘዙን መዝገቡ ያሳያል። በዚሁ ትእዛዝ ላይ በእጅ በእስክሪብቶ ተጽፍ ‛የሐሳብ ልዩነት ከመሰጠቱ በፉት ለመነጋገር“ የሚል ጽሁፍ እንደተጨመረበትና በችልቱ ከተሰየሙት ሶሰት ዳኞች መካከል ሰብሳቢዉ ዲኛ በትእዛዙ ላይ ፊርማቸዉን እንዲላኖሩ አረጋግጠናል።በሕግ ስለዳኞች አሰያየም ሲደነገግ ከግምት የሚገቡ መሰረታዊ ሁኔታዎች የጉዲዩን የክብደት ደረጃ፣ ዉስብስብነት፣ጉዲዩ በተከራካሪዎችና በአጠቃላዩ ሕብረተሰብ ላይ የሚኖረዉን አዉንታዊም ሆነ አለታዊ ፊይዲ እና የመሳሰለትን ምክንያቶች ሲሆኑ የሚሰየሙት ዳኞች ቁጥር ብዛት ሦስትና ከሦስት በላይ እየተደረገ በሕግ የሚደነገግበት ዓላማ ደግሞ የዲኞቹ ቁጥር ሲጨምር በዳኞች መካከል በሚደረግ ዉይይትና በጋራም ሆነ በተናጠል ዲኞቹ በጉዲዩ ላይ በሚያደርጉት ምርምር አከራካሪዉን ፍሬ ነገር በአግባቡ በመለየት ለሚያከራክረዉ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለዉን ሕግ በአግባቡ በመለየትና በመተርጎም እና/ወይም ተፈጻሚ በማድረግ በአንጻራዊነት ትክክለኛ ዉሳኔ መስጠት ይቻላል በሚል እምነት ነዉ።ከዚህ አንጻር በቀን 30/06/2012 ዓ/ም ተጽፍና በሁለት ዳኞች ተፈርሞ በመዝገቡ ዉስጥ የተቀመጠዉን ትእዛዝ ስንመለከት ትእዛዙ በአንድ በኩል ከተሰየሙት ሶስት ዳኞች ሁለቱ በመፈረማቸዉ አብላጫ ቁጥር ባላቸዉ ዳኞች ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈጸመበትም ተብል ድምዲሜ ላይ መደረሱን አመላካች ሲሆን በልላ በኩል ከሦስቱ ዳኞች አንደኛዉ ዲኛ ‛የሐሳብ ልዩነት ከመሰጠቱ በፉት ለመነጋገር“ በሚል ያሰፈሩት ሀሳብ ዲኛዉ የልዩነት ሀሳባቸዉን እንዲሰፈሩ እንዱቆጠር የሚያደርግ መግለጫ ሳይሆን በጉዲዩ ላይ ዉሳኔ ከመሰጠቱ በፉት በሶስቱም ዳኞች መደረግ የነበረበት ዉይይት አለመጠናቀቁን የሚያሳይ ሀሳብ ነዉ።ከዚህ በመነሳት በቀን 30/06/2012 ዓ/ም በመዝገቡ ላይ በተሰጠዉ ትእዛዝ ላይ ከዳኞች ቁጥር አኳያ ሦስት ዳኞች በስም ቢጠቀሱም በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 22/1 ስር ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈጸም አለመፈጸሙ መወሰን ያለበት ሦስት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት ነዉ የሚለዉን በሚቃረን መልኩ ከሶስቱ ዳኞች አንደኛዉ ዲኛ በተሟላ ሁኔታ ጉዲዩን ሳይመረምሩና በጉዲዩ ላይ መደረግ ያለበት ዉይይት ሳያልቅ የተሰጠ ትእዛዝ በመሆኑ ባልተሟለ ዳኞች እንደተሰጠ ትእዛዝ የሚቆጠር በመሆኑ የሥነ ሥርዓት ጉድለት (irregular proceedings) ያለበት ነዉ የሚል ድምዲሜ ላይ ደርሰናል።ስለሆነም በሕጉ ሶስት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት ለሰበር አቤቱታዉ መሰረት የሆነዉ ዉሳኔ ተመርምሮ ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩ መወሰን አለበት ተብል በተደነገገዉ መሰረት የተሰየሙት ሦስቱም ዳኞች ተወያይተዉበት በጉዲዩ ላይ በማያሻማ አኳኋን በሙለ ድምጽ ወይም በአብላጫ ድምጽ ለመወሰን በሚያስችል መልኩ በቂ ዉይይት አድርገዉ ድምዲሜ ላይ ባልደረሱበት የሚሰጥ ዉሳኔ ሕጉ ታሳቢ ያደረገዉን ዓላማ የማያሳካ እና ባልተሟለ ዳኞች እንደተሰጠ ዉሳኔ/ትእዛዝ የሚቆጠር በመሆኑ ሕጋዊ ዉጤት ሉሰጠዉ የሚገባ አይደለም።የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሰ/መ/ ላይ (በቅጽ 13 ላይ እንደታተመዉ)“የዳኞች ቁጥር ሳይሟላ የሚሰጠዉ ትእዛዝ ወይም ዉሳኔ ሕጋዊ ዉጤት ሉኖረዉ እንደማይገባ የሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ይህንኑ የሚያስገነዝብ ነዉ።
ከላይ እንደተገለጸዉ በመዝገቡ ላይ በቀን 30/06/2012ዓ/ም የተሰጠዉ ትእዛዝ የሥነ ሥርዓት ጉድለት ያለበት ነዉ በሚል የደረስነዉ ድምዲሜ እንዲለ ሆኖ ይህ ትእዛዝ ለተከራካሪ ወገኖች ተነብቦላቸዋል ወይስ አልተነበበላቸዉም?ያለመነበብ ዉጤት ምንድን ነዉ?የሚለ ነጥቦችም ክርክር የተነሳባቸዉ ስለሆኑ የዚህን ችልት ምላሽ የሚሹ ናቸዉ። በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 181/3 ስር እንደተደነገገዉ በመርህ ደረጃ የተሰጠዉ ዉሳኔ/ትእዛዝ ለተካራከሪ ወገኖች መነበብ አለበት። ይሕም የዲኝነት ሥራ ግልጸኝነትን የሚያረጋግጥ ነዉ። በልላ በኩል ዉሳኔዉን የሰጡት ዳኞች ወይም ላላ ዲኛ ዉሳኔዉን በንባብ ባላሰሙበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ስልክና መሰል የኢንፍርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖልጂ መሣሪያዎችን በመጠቀም በዘረጋዉ አሰራር መሰረት ዉሳኔዉን ለተከራካሪ ወገኖች በማድረስ ወይም በመግለጽ ያሳወቀ ከሆነ ዉሳኔዉን በሰጡት ዳኞች ዉሳኔዉ ባለመነበቡ ብቻ ዉሳኔዉ ሕጋዊ ዉጤት እንዲይኖረዉ የሚያደርግ የሕግ መሰረት የለም።በተጨማሪም ተከራካሪ ወገኖች ባለመቅረባቸዉ ምክንያት በንባብ ማሰማት የማይቻልበት ሁኔታ ሉኖር ስለሚችል ዉሳኔ በንባብ አለማሰማት የአንድን ዉሳኔ ሕጋዊ ዉጤት ሉያስቀር የሚችል አይደለም። በጸና አኳኋን ያልተሰጠ ዉሳኔ ወይም የሥነ ሥርዓት ጉድለት ያለበት ዉሳኔም ስለተነበበ ብቻ መታረም ባለበት ሥርዓት ሉታረም አይችልም ወደሚል ድምዲሜ መድረስ አይችልም። በተያዘዉም ጉዲይ ፍርድ ቤቱ ስልክና መሰል የኢንፍርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖልጂ መሣሪያዎችን በመጠቀም በዘረጋዉ አሰራር መሰረት በቀን 30/06/2012 ዓ/ም የተሰጠዉን ትእዛዝ ለተከራካሪዎች ማሳወቁን ስለተገነዘብን ዉሳኔዉ አለመነበቡ ብቻዉን ትእዛዙ የለም የሚያስብል ወይም ትእዛዙን እንደረቂቅ የሚያስቆጥር አይደለም።በመሆኑም በዚህ መዝገብ ላይ በቀን 30/06/2012 ዓ/ም የተሰጠዉ ትእዛዝ በዲኝነት ታይቶ ሉታረም የሚችል የሥነ ሥርዓት ጉድለት እንዲለበት ትእዛዝ ከሚቆጠር በስተቀር ትእዛዙ ለተከራካሪ ወገኖች ባለመነበቡ ብቻ አብላጫ ቁጥር ባላቸዉ ዳኞች በተፈረመበት ሁኔታ እንደረቂቅ እንዱቆጠር የሚያደርግ የሥነ ሥርዓት ሕግ አግባብ ባለመኖሩ ከዚህ አኳያ አመልካች ያቀረበዉን ክርክር አልተቀበልንም። ይህ ማለት ግን ከላይ በተጠቀሰዉ ምክንያት ባልተሟለ ዳኞች ያተሰጠ ትእዛዝ ስልክና መሰል የኢንፍርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖልጂ መሳሪያዎችን በመጠቀም ተከራካሪዎች እንዱያዉቁት በመደረጉ ብቻ ትእዛዙ የስነ ሥርዓት ጉድለት የለዉም ወደሚል ድምዲሜ ተደርሷል ማለት እንዲልሆነ ልብ ይሎል።
ከላይ እንደተመለከተዉ በሰበር አጣሪ ችልቱ በቀን 30/06/2012 ዓ/ም የተሰጠዉ ትእዛዝ ባልተሟለ ዳኞች የተሰጠ በመሆኑ ሕጋዊ ዉጤት የለዉም ከተባለ ትእዛዙ ሕጋዊ ዉጤት የለዉም የሚል ዉሳኔ መቼ፣ በምን አግባብና በማን ላሰጥ ይገባል የሚለዉ ጭብጥ የዚህን ችልት ምላሽ የሚሻ ላላዉ ጭብጥ ነዉ። እንደሚታወቀዉ የዲኝነት ነጻነት በዓለም አቀፍ ሕግጋት፣ በኢ.ፉ.ዱ.ሪ ሕገ መንግሥትና በተለያዩ አገራዊ ሕግጋት እዉቅና የተሰጠዉና ጥበቃ የተደረገለት መርህ ነዉ።በተለይ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 78/1 እና 79(2 እና 3) ስር ስለፍርድ ቤቶች ተቋማዊ ነጻነት እና የዳኞች ግላዊ ነጻነት በተመለከተ እንደተደነገገዉ ፍርድ ቤቶች ከማንኛዉም የመንግሥት አካል፣ከማንኛዉም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛዉም ላላ ተጽእኖ ነጻ እንደሆኑና ዳኞችም ከሕግ በስተቀር በልላ ሁኔታ ሳይመሩ የዲኝነት ተግባራቸዉን በሙለ ነጻነት እንደሚያከናዉኑ ተደንግጓል።በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 (በአዋጅ ቁጥር 138/1991 እና በአዋጅ ቁጥር 454/1997 እንደተሻሻለዉ) አንቀጽ 16(2/ሀ) ፣18(ሀ/1) እና 21/1 እንዱሁም በተሻሻለዉ የፋዳራል ዳኞች አስተዲደር ጉባዔ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 684/2002 አንቀጽ 6(1/ሰ) ስር እንደተደነገገዉ ዳኞችን በየችልቱ መድቦ የማሰራት ሥልጣንና ተግባር በፍርድ ቤቶች ተቋማዊ ነጻነት ማእቀፍ ዉስጥ የሚታይ በመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት እና/ወይም የዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ሥልጣንና ተግባር ነዉ። የዲኝነት ነጻነት መርህ ዳኞች በተመደቡበት ችልት የዲኝነት ተግባራቸዉን ከማናቸዉም ተጽእኖ ወይም ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነዉ እንዱያከናዉኑ በዳኞች ላይ ግዳታ የሚጥል ነዉ። የፍርድ ቤቶች ፕሬዚዲንቶችም አግባብ ባለዉ ሕግ በተደነገገዉ መሰረት በችልት ተሰይመዉ ሉሰሩ የሚችለ ቢሆንም ላልች ዳኞች ተሰይመዉ በዲኝነት በሚያዩት ጉዲይ የዲኝነት ተግባራቸዉን በነጻነት እንዲይተገብሩ ከሚያደርጉ ጣልቃ ገብነት ራሳቸዉን መቆጠብና ላላ ማንኛዉም ሰዉ የዲኝነት ነጻነትን የሚነካ ተግባር እንዲይፈጽም መከላከል ይጠበቅባቸዋል። ዳኞችን ከሚያስተዲድር አካልም ይሄዉ ይጠበቃል።
በያዝነዉ ጉዲይ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በቀን 30/06/2012 ዓ/ም በመዝገቡ ላይ የተሰጠዉ ትእዛዝ ከላይ ተደጋግሞ እንደተገለጸዉ ባልተሟለ ዳኞች የተሰጠ ትእዛዝ በመሆኑ የሥነ ሥርዓት ጉድለት (irregular proceedings) ያለበት ነዉ። በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 209/1 እና 211/2 ስር ከተደነገገዉ መንፈስና ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለዉ የሥነ ሥርዓት ጉድለት ያለበት ትእዛዝ ከእነጉድለቱም ቢሆን ጉዲዩ በዲኝነት ታይቶ የተሰጠ ትእዛዝ በመሆኑ የማረም ሥልጣን ላለዉ ፍርድ ቤት ወይም ችልት ቀርቦ በሚሰጥ ዲኝነት የሚታረም እንጂ በተከራካሪ ወገኖች አመልካችነት ወይም በፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት አነሳሽነት ታይቶ በፕሬዚዲንት በሚሰጥ አስተዲደራዊ ዉሳኔ እንዱታረም የሚፈቅድ የሕግ አግባብ የለም። በዚህ አግባብ ሥርዓቱን ጠብቆ ካልተሻረ ከእነጉድለቱም ቢሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ሕግ ቁጥር 212 መሰረት የጸና ይሆናል። ይሕ በቀን 30/06/2012 ዓ/ም የተሰጠዉ ትእዛዝ በምን አግባብ ሉታረም ይችላል የሚለዉን የተመለከትን እንደሆነ ይህ ትእዛዝ የሥነ ሥርዓት ጉድለት ተፈጽሞ የተሰጠና ትክክለኛ ፍርድ ከመስጠት የሚያግድ ሆኖ ከታየ ትእዛዙን በመሻር(ትእዛዙ እንዲልተሰጠ በመቁጠር) ጉዲዩ እንደገና እንዱታይ የሚያደርግ ትእዛዝ በመስጠት ማረም ይቻላል(የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 211/2 ይመለከቷል)።በግልጽ እንደሚታየዉ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 211/2 ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሚጠቀመዉ ድንጋጌ ነዉ። ሆኖም እስካሁን ሰበር ችልት የሚመራበት ልዩ ሥነ ሥርዓት ስላለ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 211/2 ስር የተደነገገዉን አንድን የሕግ ድንጋጌ አገናዝቦ ተግባራዊ በማድረግ መርህ (mutatis mutandis) መሰረት ከሰበር ባህሪ አንጻር በማገናዘብ በሰበር በሚታይ ጉዲይ ላይም ተፈጻሚ ማድረግ ይገባል። በመሆኑም በዚህ መዝገብ ላይ በቀን 30/06/2012ዓ/ም የተሰጠዉ ትእዛዝ ባልተሟለ ዳኞች የተሰጠ በመሆኑ የሥነ ሥርዓት ጉድለት ስላለበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 211/2 መሰረት ሉሻር የሚገባዉ ነዉ ብለናል።
በልላ በኩል በአዋጅ ቁጥር 25/1988 (በአዋጅ ቁጥር 454/1997 እንደገና እንደተሻሻለዉ)አንቀጽ 21 ስር ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩ ከማድረግ አንጻር ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት የተሰጠዉ ስልጣን ተፈጻሚ የሚሆነዉ መቼና በምን ሁኔታ ነዉ የሚለዉን መመርመር ያስፈልጋል። በአዋጁ አንቀጽ 21 ስር በተለያዩ ምክንያቶች በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት ትእዛዝ እና በሕጉ በተጠቀሱት ምክንያቶች ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ የሚያዩባቸዉ ጉዲዮች ተመልክቷል።በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 ስር በተደነገገዉ መሰረት የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት በራሳቸዉ አነሳሽነት ወይም በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ችልት አሳሳቢነት ወይም ከተከራካሪ ወገኖች በአንደ ጥያቄ ሲቀርብላቸዉ አንድን ጉዲይ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩት ለማድረግ ይችላለ።በዚህ ድንጋጌ የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዲንት አንድ ጉዲይ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩ ሉያደርጉ የሚችለት የትኞቹን ጉዲዮች እንደሆነ በግልጽ ባይደነገግም ከንኡስ አንቀጽ 2 ጋር አገናዝበን ካየን በንኡስ አንቀጽ 2 ስር ከተጠቀሱት ጉዲዮች ዉጭ በላልች ጉዲዮች ለማሳያነትም ጉዲዩ ዉስብስብ ነዉ ብለዉ ሲያምኑ ወይም ደግሞ አምስት ዳኞች ተሰይመዉ ቢያዩ ትክክለኛ ፍርድና የሕግ ትርጉም ላሰጥ ይችላል ብለዉ ሲገምቱ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩት ማድረግ ይችላለ።ከዚህ አንጻር የያዝነዉን ጉዲይ ስንመለከት አመልካች በቀን 14/07/2012 ዓ/ም ለፍርድ ቤቱ ፕሬዚዲንት በጻፈዉ አቤቱታ ጉዲዩ በአምስት ዳኞች ይታይልኝ በማለት በግልጽ አልጠየቀም። በተጨማሪም ጉዲዩን ሲመለከት የነበረዉ ሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩ እንዱደረግ ማሳሰቡን መዝገቡ አያሳይም።ይልቁንም ከመዝገቡ የተገነዘብነዉ ጉዲዩን አምስት ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩ የተደረገዉ በፍርድ ቤቱ ፕሬዚዲንት አነሳሽነት አመልካች በቀን 14/07/2012 ዓ/ም ጽፍ ላቀረበዉ አቤቱታ በተሰጠ ምላሽ ለሰበር አጣሪ ችልት ሰብሳቢዉ ዲኛ በሰጡት ትእዛዝ ነዉ።ይህም ለፍርድ ቤቱ ፕሬዚዲንት በአዋጁ አንቀጽ 21/1 የተሰጠ ሥልጣን በመሆኑ ከዚህ አንጻር የተፈጸመ ስህተት አላገኘንም።
ነገር ግን የአዋጁ አንቀጽ 21/1 የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት አንድን ጉዲይ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩ ሉያደርጉ የሚችለት መቼ ነዉ የሚለዉን በግልጽ አላመላከተም።
ይህም የሆነበት ምክንያት የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዲንት እየታየ ባለዉ አከራካሪ ጉዲይ ላይ ጉዲዩን ሲያዩ በነበሩት በችልቱ ዳኞች በሙለም ሆነ በአብላጫ ድምጽ የመጨረሻ ልባል የሚችል ትእዛዝ ወይም ዉሳኔ ከመሰጠቱ በፉት በማንኛዉም ጊዜ ጉዲዩን ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩት ለማድረግ ይችለ ዘንድ ሰፉ ሥልጣን ለመስጠት ታስቦ እንደሆነ ይታመናል።በመሆኑም የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዲንት በዚህ ረገድ የተሰጣቸዉን ሥልጣን ከመጠቀማቸዉ በፉት አስቀድሞ ጉዲዩ ተመርቶላቸዉ ጉዲዩን በዲኝነት ሲያዩ የነበሩት ዳኞች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ትእዛዝ/ዉሳኔ አለመኖሩን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።እንዱሁም አስቀድመዉ ጉዲዩን በዲኝነት ሲያዩ የነበሩ ዳኞች የሰጡትን ትእዛዝ/ዉሳኔ ዋጋ በሚያሳጣ አኳኋን ያንኑ ጉዲይ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ እንዱዲኙ ማድረግ እንዱችለ ተጠቃሹ ደንጋጌ ሥልጣን አይሰጣቸዉም።ከላይ እንደገለጽነዉ በቀን 30/06/2012ዓ/ም የተሰጠዉ ትእዛዝ የሥነ ሥርዓት ጉድለት ያለበት ትእዛዝ መሆኑ የተረጋገጠ ቢሆንም መታረም ያለበት በሥነ ሥርዓት ሕጉ መሰረት በዲኝነት ታይቶ በመሆኑ ከዚህ ዉጭ በሆነ አኳኋን የሥነ ሥርዓት ጉድለት ያለበትን ትእዛዝ በአስተዲደራዊ ዉሳኔ ዉጤት እንዲይኖረዉ ማድረግ በሕግ ከተዘረጋዉ ስርዓት ዉጭ በዳኞች የተሰጠ ትእዛዝ/ዉሳኔ እንዲይፈጸም የሚያደርግ ዉጤት በማስከተል የዲኝነት ነጻነት መርህን ስለሚቃረን ተቀባይነት የሚሰጠዉ የዲኝነት ሥራ አመራር አይደለም።በመሆኑም በቀን 30/06/2012ዓ/ም የተሰጠ ትእዛዝ ያለበት ጉድለት በዲኝነት ታይቶ ሳይታረም ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ ጉዲዩን እንዱመረምሩ አስተዲደራዊ ዉሳኔ መስጠት በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 21/1 ስር የተሰጠዉን ሥልጣን በዲኝነት ሥራ ጣልቃ በሚያስገባ መልኩ በሰፉዉ በመተርጎም ተግባራዊ ማድረግ ስለሚሆን እና በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 22/1 ስር የሰበር አቤቱታ ስለሚመረመርበትና ለሰበር የሚያስቀርብ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ተብል የሚወሰንበትን ሥነ ሥርዓት አለመከተል ስለሆነ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።
በተጨማሪም ጉዲዩ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት ችልት እንዱታይ የሚደረግበት ዓላማ ጉዲዩን በአብላጫ ድምጽ መወሰን እንዱቻል ብቻ ሳይሆን ከጉዲዩ ባህርይ አንጻር ከአምስት ያላነሱ ዳኞች አከራካሪ የሆነዉን የሕግና የፍሬ ነገር ጉዲይ ቢመረምሩ አከራካሪዉን ነጥብ በአግባቡ በመለየት ሕግን መሰረት ያደረገ ፍትሀዊ ዉሳኔ ይሰጣለ ተብል ስለታመነ ነዉ። በዲኝነት አገልግልት አሰጣጥ ዳኞች የቀረበላቸዉን ጉዲይ በገለልተኛነት አይተዉ ዉሳኔ እንዱሰጡ ይጠበቃል።ገለልተኝነት ከሚረጋገጥበት መንገድ አንደ አንድን ጉዲይ በዲኝነት የሚያዩ ዳኞች በዲኝነት የሚያዩትን ጉዲይ አስቀድመዉ በዲኝነት በማየትም ሆነ በልላ ሁኔታ አቋም ያልያዙበትና ይሕንንም አቋማቸዉን ለሕዝብ ይፊ ያላደረጉ መሆን እንዲለባቸዉ በማድረግ ነዉ(አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 27(1/ሐ) ይመለከቷል)። ስለሆነም የሚሰየሙት አምስት ዳኞች ጉዲዩን አስቀድመዉ በዲኝነት አይተዉ አቋም የያዙ መሆን የለባቸዉም።
ሆኖም በያዝነዉ ጉዲይ ለሰበር ሰሚ ችልት የሚያስቀርብ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈጸመበትም ብለዉ አስቀድሞ በቀን 30/06/2012ዓ/ም በተሰጠ ትእዛዝ አቋም የያዙ ዳኞች በድጋሚ በዚያዉ ጉዲይ ላይ ተሰይመዉ እንዱያዩ መደረጉ የገለልተኛነት መርህን ያላገናዘበ ከመሆኑም በተጨማሪ እነዚሁ ጉዲዩን የሚያዉቁ ዳኞች በተሰየሙበት ጉዲዩ መታየቱ ከዳኞች ቁጥር አንጻር ሲታይም በሕጉ አግባብ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዋል ብል ለመደምደም የሚያስችል አይደለም።
ሲጠቃለል በመዝገቡ ላይ አስቀድሞ ከተሰየሙት ሶስት ዳኞች አብላጫ ቁጥር ያላቸዉ የችልቱ ዳኞች ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈጸመበትም በማለት በቀን 30/06/2012 ዓ/ም በሰጡት ትእዛዝ መዝገቡ እንዱዘጋ ያዘዙ ቢሆንም በዚህ አግባብ በሁለቱ ዳኞች የተወሰነዉ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 22/1 መሰረት ከችልቱ ሶስተኛ ዲኛ ጋር ተገቢዉ ዉይይት ሳያደርግና የሶስተኛዉን ዲኛ የመወሰን ሥልጣን በሚያሳጣ መልኩ በመሆኑ ባልተሟለ ዳኞች የተሰጠ ትእዛዝ ነዉ ብለናል።ይህም የዉሳኔ አሰጣጥ ከትክክለኛ የዉሳኔ አሰጣጥ ተቃራኒ እና የሥነ ሥርዓት ጉድለት ያለበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።እንዱሁም ይህ የሥነ ሥርዓት ጉድለት ያለበት ትእዛዝ በዲኝነት ታይቶ ባልታረመበት ይህንን ትእዛዝ ዋጋ በሚያሳጣ መልኩ ጉዲዩን ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩ አስተዲደራዊ ዉሳኔ መሰጠቱና ጉዲዩን አምስት ዳኞች መርምረዉ በአብላጫ ድምጽ በተሰጠ ትእዛዝ ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ተብል የታዘዘዉም በአዋጁ አንቀጽ 21/1 እና 22/1 ስር የሰበር አቤቱታ ስለሚመረመርበትና ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል? አልተፈጸመም ?የሚለዉን መርምሮ ለመወሰን የተዘረጋዉን ሥነ ሥርዓት ካለመከተለም በተጨማሪ ለዚህ ችልት የቀረበበት አግባብ የዲኝነት ነጻነት መርህን የሚቃረን በመሆኑ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።በልላ በኩል በተፈጠረዉ የሥነ ሥርዓት ጉድለት ምክንያት የሰበር አቤቱታዉ በአግባቡ ባለመመርመሩና ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ወይም አልተፈጸመም የሚል ዉሳኔ በሕግ በተዘረጋዉ ሥርዓት መሰረት ባለመሰጠቱ ምክንያት በተከራካሪ ወገኖች ላይ ፍትህ ሉዛባ ወይም ሉጓደል ስለማይገባ የሥነ ሥርዓት ጉድለት ያለበት ትእዛዝ እና ይህንን ተከትል አምስት ዳኞች ተሰይመዉ የሰጡት ትእዛዝ ተሽሮ አመልካች የሰበር አቤቱታዉን የዲኝነት ክፍያ መክፈል ሳይጠበቅበት አስቀድሞ በከፈለዉ ዲኝነት በአዱስ መዝገብ ላይ አቅርቦ ላታይለት ይገባል ብለናል። አመልካች በዚህ አግባብ አቤቱታ ሲያቀርብ በልላ የመዝገብ ቁጥር አዱስ መዝገብ ተከፍቶ አስቀድሞ ጉዲዩን ያላዩ ዳኞች በሕጉ በተመለከተዉ አግባብ በተሰየሙበት ችልት አቤቱታዉ ተመርምሮ ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ወይስ አልተፈጸመም በሚለዉ ጭብጥ ላይ ተገቢዉ ዉሳኔ ላሰጥበት ይገባል ብለናል።በመሆኑም በአብላጫ ድምጽ ተከታዩ ተወስኗል።
በዚህ መዝገብ ላይ በቀን 30/06/2012 ዓ/ም እና በቀን 29/07/2012 ዓ/ም የተሰጡ ትእዛዛት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 211/2 መሰረት ተሰርዘዋል።
አመልካች የሰበር አቤቱታዉን አስቀድሞ በከፈለዉ ዲኝነት በድጋሚ ማቅርብ እንዱችል መብት ተጠብቆለታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ሲያቀርብ አቤቱታዉ በአዱስ መዝገብ ላይ በልላ የመዝገብ ቁጥር እንዱከፈትና አስቀድሞ ጉዲዩን ያላዩ ዳኞች ለተሰየሙበት አጣሪ ችልት እንዱመራና ችልቱም አቤቱታዉንና ዉሳኔዉን መርምሮ ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ወይስ አልተፈጸመም በሚል ነጥብ ላይ ሕግን መሰረት ያደረገ ዉሳኔ ይስጥበት ብለናል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
ከላይ በዉሳኔ ተራ ቁጠር 2 ላይ በተመለከተዉ መሰረት ጉዲዩ በሚመራለት ችልት ዉሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ የዉሳኔዉ ክፍል ብቻ ጉዲዩ ለሚመራለት ችልት ላቀርብ ይገባል። ሆኖም የፍርድ ዉሳኔዉ ግልባጭ ለግራ ቀኙ ሲጠይቁም ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል።ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
እኛ ስማችን በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተሰየምን ዳኞች ጉዲዩ ለሰበር ችልት የቀረበበት አግባብ የሥነሥርዓት ጉድለት (procedural irregularity) የተፈፀመበት እና የዲኝነት ነፃነት የሚቃረን ነው በሚል ተጠሪ ያቀረበውን መቃወሚያ በአብላጫ ድምጽ ተቀባይነት ማግኘቱ ላይ ባለመስማማት የልዩነት ሀሳባችንን እንደሚከተለው አስፍረናል።
የክርክሩ መነሻ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገ የግንባታ ዉል አፈጻጸም የሚመለከት ሲሆን የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሟል በሚል አመልካች ለሰበር ያቀረበው አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ያስቀርባል ተብል ተጠሪ በመልስ እንዱሰጥ መደረጉን ተከትል ተጠሪ ባቀረበዉ መልስ ላይ ጉዲዩ ለሰበር ችልት የቀረበው ከሕግ እና ከሥነ-ሥርዓት ዉጪ ነው በሚል መቃወሚያ አቀርቧል።
የተጠሪ መቃወሚያ መሰረት ያደረገዉ የአመልካች አቤቱታ ሦስት ዳኞች በተሰየሙበት ሰበር አጣሪ ችልት ተሰምቶ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም በተሰጠ ትዕዛዝ ጉዲዩ ለሰበር አያስቀርብም ተብል በአብላጫ ድምፅ ተወስኖ መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት እንዱመለስ ከተባለ በኋላ የልዩነት ሀሳብ ያላቸው ዲኛ ልዩነት ሀሳብ አስፍረው መዝገቡን መመለስ ሲገባቸው አዘግይተዋል።አመልካች በዚህ አጋጣሚ መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ለፋደራል ጠ/ፍርድ ቤት ፕሬዝዲንት አቤቱታ አቅርቦ ፕሬዝዲንቷም ከህግ ውጪ አምስት ዳኞች እንዱያዩት አድርገዋል።ይህም አካሄድ የዲኝነት ነፃነትና የሕግ የበላይነት የሚፃረር ነው፤ስለዚህም አምስት ዳኞች ተሰይመዉ በአብላጫ ድምፅ ጉዲዩ ለሰበር እንዱቀርብ የሰጡት ትዕዛዝ ተፈፃሚነት የለውም ተብል ውድቅ እንዱደረግ የሚል ነው።ተጠሪ ያቀረበዉ መቃወሚያ ላይ በአመልካች በኩል የቀረበው መከራከሪያ ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገው በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 21 መሰረት ስለመሆኑ በመግለፅ በአቀራረቡ ላይ የተፈፀመ የሥነሥርዓት ጉድለት የለም በሚል መቃወሚያው ውድቅ ተደርጎ በስረ ነገር ክርክር ላይ ውሳኔ እንዱሰጥ አመልክቷል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ አምስት ዳኞች በተሰየሙበት አጣሪ ችልት ተመርምሮ ለሰበር የቀረበበት ሂደት በመቃወም ተጠሪ ያቀረበዉ መከራከሪያ ተቀባይነት አለዉ ወይስ የለዉም (objection sustainable or not) የሚለውን ጭብጥ ችልቱ መርምሯል።ተጠሪ ያቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት አለው ሲል አብላጫው ድምፅ የደረሰበት ድምዲሜ ተገቢ አይደለም የምንልበትን ምክንያት አግባብነት ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ እንመለከታለን።
በመሰረቱ የሰበር ሥርዓት ዋነኛ ዓላማ ወጥነትና ተገማችነት ያለው የሕግ አተገባበር እና አተረጓጎም እንዱረጋገጥ ማድረግ ነው።በልላ አነጋገር የሰበር ሥርዓት ተቀዲሚ ተግባር በአንድ ጉዲይ የቀረቡትን ተከራካሪ ወገኖች መብትና ግዳታ ከማረጋገጥ ባሻገር በክርክር አመራር ስርዓት ወይም ሂደት እና በሚሰጠዉ ዉሳኔ ላይ ህጋዊነት እና የህግ የበላይነት መከበሩን እና ህጎች በሁለም ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጻሚ መደረጋቸዉን በማረጋገጥ ሰዎች በፍትህ ስርዓቱ ላይ እምነት እንዱኖራቸዉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነዉ።ለዚህም ነዉ የሰበር ስርዓት ዓላማ ከተከራካሪ ወገኖች ፍላጎት ወይም በአንድ መዝገብ ከቀረበዉ ክርክር ባሻገር ተገማች የሆነ ፍርድ ማረጋገጥ ነዉ የሚባለዉ።የሰበር ሥርዓት በፋደራልም ሆነ በክልል ፍርድ ቤቶች ተግባራዊ እንዱደረግ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት መደንገጉ ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት ታስቦ እንደሆነ እሙን ነው።ይህንኑ ህገ መንግስት ድንጋጌ ተከትል የወጡት የፍደራል ፍርድ ቤቶች እንዱሁም የክልል ፍርድ ቤቶች አዋጆች የሰበር አቤቱታ አቀራረብ ሥርዓት የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ይዘዉ እናገኛለን።በእርግጥ ህጎቹ አስፈላጊና ዝርዝር ድንጋጌዎችን አሟልተዉ ባለመቀረጻቸዉ በክርክር አመራር ረገድ እንደአግባብነቱ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ወይም የወንጀል ስነ ስርዓት ህግ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንደሚደረጉ ይታወቃል።
የፍደራል ፍርድ ቤቶችን በተመለከተ የሰበር ሥልጣንና እና የአቤቱታ አቀራረብ ሥርዓት መሰረታዊ ድንጋጌዎች በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 10 እና 22 ስር የተደነገገ ሲሆን ተጨማሪ መሰረተ ሀሳቦች በማሻሻያ አዋጆችም ተካተዉ እናገኛለን።በዚህ ረገድ የሰበር ችልቱ የህግ ትርጉም አስገዲጅነት (binding effect) እንዱኖረዉ አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(4) ላይ የተደነገገዉ ተጠቃሽ ነዉ።በአዋጅ ቁጥር 25/88 እንደተደነገገው በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠ የመጨረሻ ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል አቤቱታ ሲቀርብ ጉዲዩ ለሰበር የሚቀርበው ሦስት የጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች የተሰየሙበት ችልት አቤቱታውን መርምሮ ውሣኔው ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ብል ሲወስን ስለመሆኑ በአንቀፅ 10 እና 22(1) ላይ ተመልክቷል። ችልቱ አቤቱታዉን መርምሮ ዉሳኔዉ ለሰበር የሚያበቃ የሕግ ስህተት የለውም ብል ካመነ አቤቱታውን ዉድቅ ማድረግ እንደሚችል የዚህ ድንጋጌ ተቃራኒ ንባብ ያስገነዝባል።ስለሆነም የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አለው ወይም የለውም የሚል ውሳኔ የሚሰጠው ሦስት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት (በተለምድ ሰበር አጣሪ ችልት ተብል የሚታወቀዉ ማለት ነዉ) እንደመሆኑ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓትም በአዋጁ የተለየ ድንጋጌ ባለመኖሩ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ የሚመራ መሆኑ ልብ ይለዋል።የሰበር አጣሪ ችልት ውሳኔ እንደማናቸውም የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሚታይ እና የፍርድ አሰጣጥና አፃፃፍ ሥርዓት ተከትል መፈፀም እንዲለበት አከራካሪ አይደለም።በዚህ ረገድ ዉሳኔዉ ስርዓቱን ያሟላ መሆን አለመሆኑ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 180 እና 181 አንጻር መታየት አለበት ሲል አብላጫ ድምጽ የሰጠዉ ምክንያት እኛም የምንስማማበት ነዉ።
በተያዘው ጉዲይ አቤቱታዉ የተመራለት ሦስት ዳኞች የተሰየሙበት ሰበር አጣሪ ችልት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ሰምተዉ በ30/06/2012 ዓ.ም አቤቱታዉ ለሰበር አያስቀርብም በማለት በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ ሰጥተዋል የሚል መከራከሪያ ነጥብ በተጠሪ በኩል ቀርቧል።መዝገቡ ጋር የተያያዘዉ ትእዛዝ ይዘት ሲታይ በተጠቀሰው ዕለት በመዝገቡ ላይ ከተሰየሙት ሶስት ዳኞች ሁለቱ ዳኞች አቤቱታዉ ለሰበር አያስቀርብም በሚል ትእዛዝ ሰጥተዉ ፊርማቸዉን ያኖሩ ቢሆንም አንደኛው ዲኛ ‛የሀሳብ ልዩነት ከመሰጠቱ በፉት ለመነጋገር“ (ሰርዝ የተጨመረበት) የሚል ጽሁፍ የሰፈረበት ስለመሆኑ እንጂ ዲኛዉ የልዩነት ሀሳባቸው አልገለፁም ወይም በአብላጫ ድምፅ ተስማምተው ፊርማቸውን አላስቀመጡም።
ይህም፣ በአብላጫዉ ድምጽ ዉሳኔ ላይ እንደተመለከተዉም በጉዲዩ ላይ በቂ ዉይይት ተደርጎ የሁለም ዳኞች ሃሳብ በአግባቡ ተንሸራሽሮ አቋም ያልተያዘበት መሆኑን አመላካች ነዉ። በጉዲዩ ላይ ውይይት አለመጠናቀቁን ብቻ ሳይሆን በችልቱ የተሰየሙት ሦስት ዳኞች በተመሳሳይ ድምፅ ወይም በአብላጫ ድምፅ ዉሳኔ ስለመስጠታቸው በፊርማቸው ያላረጋገጡ መሆኑንም የሚያሳይ ነዉ። ከላይ እንደተመለከትነው የሰበር አጣሪ ችልት ውሳኔ ሰጥቶበታል ልባል የሚችለው በችልቱ የተሰየሙት ሦስቱም ዳኞች በአብላጫ ድምጽ ወይም በተመሳሳይ (ያለ ልዩነት) ድምጽ ውሳኔ መስጠታቸውን በፊርማቸው ማረጋገጥ ሲችለ ነው።የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 181(2 እና 3) ይመለከታል።በመሆኑም የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ተሰጥቷል የተባለው ውሣኔ በሦስት ዳኞች ፊርማ ያልተረጋገጠ ስለሆነ ውሳኔ ያገኘ ጉዲይ ነው ልባል አይችልም። ከዚህም ጋር በተያያዘ ባልተሟላ ዲኛ የተሰጠ ውሳኔ እንዲልተሰጠ ይቆጠራል ሲል ይህ ሰበር ችልት የሰጠው የህግ ትርጉም ይህንኑ ሀሳብ የሚያጠናክር ነው። ሰበር መ/ ቅጽ 13 ይመለከታል።ስለሆነም በዚህ ጉዲይ ላይ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ አብላጫው ድምፅ እንደሚለው የሥነ-ሥነዓት ጉድለት (procedural irregularity) ያለበት ነዉ ተብል በስነ ስርዓት ህጉ የሚታረም ጉዲይ ብቻ ሳይሆን ባልተሟላ ዲኛ የተሰጠ ዉሳኔ ስለሆነ ዉሳኔው እንዲልተሰጠ ይቆጠራል የሚል አቋም ወስደናል።
ጉዲዩ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ አመልካች መዝገቡ ባልታወቀ እና ባልተለመደ ሁኔታ ከቀጠሮ ውጪ ሆኖ በመቆየቱ ፍትህ ተጓድልብኛል በሚል በ14/7/2012 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ ፕሬዝዲንት ማቅረባቸውን ተለትል በዚህ አቤቱታ መነሻ መዝገቡ ላይ ተጨማሪ ሁለት ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩት መደረጉን መዝገቡ ያሳያል። የፍደራል ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዲንት አምስት ዳኞች እንዱያዩት ማድረጋቸው ከህግ ዉጪ ነው ሲል ተጠሪ ያቀረበው መከራከሪያ በአብላጫ ድምፅ ተቀባይነት ማግኘቱ ላይ አልተስማማንም።በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ችልቶች በአንድ ጉዲይ ላይ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመዉ እንዱያዩት የሚደረገዉ በሁለት አግባብ ወይም መንገድ ስለመሆኑ ከአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 21(1 እና 2) ድንጋጌዎች የምንገዘበዉ ጉዲይ ነዉ። አንደኛዉ የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት ተብል በሰበር ችልት የሚታይበትን አግባብ አስመልክቶ በህግ የተመለከቱ ሁኔታዎችን ተከትል ሲሆን ሁለተኛዉ ጉዲይ ደግሞ ለፍርድ ቤቱ ፕሬዚዲንት በተሰጠዉ ስልጣን የሚወሰን ይሆናል። አንድ ጉዲይ በአምስት ዳኞች እንዱታይ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ለወስንበት አግባብ የሚደነግገዉ የአዋጁ አንቀጽ 21/1/ የፋዳራል ጠ/ፍርድ ቤት ፕሬዝዲንት በራሱ አነሳሽነት ወይም በፋደራል ጠ/ፍርድ ቤት ችልት አሳሳቢነት ወይም ከተከራካሪ ወገኖች ባንደ ጥያቄ ሲቀርብለት አንድን ጉዲይ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመው እንዱያዩት ማድረግ እንደሚችል ተመላክቷል። ይህ ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነዉ በየትኛዉ ችልት እና ጉዲይ ላይ ነዉ የሚለዉን ድንጋጌዉ በግልጽ ለይቶ ያላስቀመጠ በመሆኑ ሉኖረዉ የሚችለዉ አንድምታ ከሶስቱ አንደኛዉ ምክንያት መኖሩ ሲረጋገጥ በየትኛዉም የፍርድ ቤቱ ችልት እና በማናቸዉም ጉዲይ ላይ ተፈጻሚ ለማድረግ እንደሚቻል ለፍርድ ቤቱ ፕሬዝዲንት የተተወ ፈቅደ ስልጣን መሆኑን ያሣያል።ነገር ግን የዚህ ፈቅደ ስልጣን አተገባበር የዲኝነት ነጻነትን በማይነካ አኳኋን በጥንቃቄ እና በጠባቡ ተግባራዊ መሆን እንዲለበት ይታመናል።
በተያዘውም ጉዲይ አቤቱታዉ አምስት ዳኞች ተሰይመዉ በሰበር አጣሪ እንዱታይ የተደረገው በአመልካች አቤቱታ መነሻ ስለመሆኑ መዝገቡ ያሣያል።
ከላይ እንደተመለከትነው ሦስት ዳኞች የተሰየሙበት ሰበር አጣሪ ችልት በአንድ በኩል ተጨማሪ ዉይይት እንዱደረግበት በተገለጸበት ትዕዛዝ ላይ ጉዲዩ ዉይይት ተደርጎበት አቋም እንደተያዘበት ተደርጎ በሁለቱ ዳኞች መፈረሙ፣ በልላ በኩል ደግሞ መዝገቡ ሳይመለስ በእንጥልጥል ላይ መቆየቱ አመልካች ሂደቱን እንዱጠራጠር ምክንያት ይሆናል። በዉጤቱ ላይ አመኔታ እንዲይኖረዉም ምክንያት ይሆናል።
አዋጁ ከላይ በተመለከተዉ ድንጋጌ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት አንድ ጉዲይ በአምስት ዳኞች እንዱታይ መወሰን እንደሚችል ስልጣን ከተሰጠባቸዉ ምክንያቶች ዉስጥ አንደ በእንደዚህ መሰል ጉዲዮች ምክንያት ሉፈጠር የሚችለዉን የፍትሕ መጓደል ሉኖር የሚችልበትን ሁኔታ ለማስቀረት እንደሆነ ይታመናል። ስለሆነም ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ በሚል ጊዜ በመውሰደ እና መዝገቡ በእንጥልጥል በመቆየቱ ፍትህ ተጓድልብኛል በሚል አመልካች ያቀረበዉን አቤቱታ ፕሬዝዲንቷ ተቀብለዉ ጉዲዩ በአምስት ዳኞች እንዱታይ ማድረጋቸው ውሳኔ ባገኘ ጉዲይ ጣልቃ እንደመግባት የሚያስቆጥር ሆኖ አላገኘንም። ይልቁንም የጉዲዩ ባህርይ እና የቀረበዉን አቤቱታ መሰረት በማድረግ አምስት ዳኞች እንዱያዩት ማድረጋቸዉ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 16/1/ እና 21/1/ መሰረት ያደረገ ሆኖ አግኝተነዋል።
እንዱሁም ቀደም ሲል ሁለቱ ዳኞች የሰጡት ዉሳኔ ባልተሟላ ዲኛ የተሰጠ ዉሳኔ በመሆኑ እንዲልተሰጠ ይቆጠራል የሚለዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ዲኞቹ የሰጡት ዉሳኔ በፍርድ ቤቱ ድረገጽ (web site) እና መረጃ ቋት (data base) ተመዝግቧል የሚለዉ የተጠሪ ክርክር ስንመለከት በስነ ስርዓት ህጉ የተደነገገዉን የዉሳኔ አሰጣጥ ስርዓት ተከትልና ተሟልቶ የተሰጠ ዉሳኔ አለመሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ በፍርድ ቤቱ ድረገጽ መለቀቁም ሆነ በመረጃ ቋት መመዝገቡ በራሱ ዉሳኔዉን የተሟላ እና አስገዲጅ ሉያደርገዉ አይችልም። ከዚህም በተጨማሪ መረጃዉ የተለቀቀበት አካሄድ ስህተት እንደነበር እና ስህተቱም የተፈጠረዉ በፍርድ ቤቱ የመረጃ ክፍል ሰራተኞች ስለመሆኑ በወቅቱ ከፍርድ ቤቱ የተሰጠዉ መግለጫ ያሣያል። የችልቱ ዳኞች ቀደም ሲል በቂ ውይይት አድርገዉ አቋም የወሰደበት መሆኑን ካመኑበት ከላልች ዳኞች ጋር በድጋሚ አንሰየምም ወይም ከችልቱ እንነሳለን ማለት ይጠበቅባቸዉ ነበር። በልላ በኩል ሁለቱ ዳኞች በጉዲዩ ላይ ከላልች ዳኞች ጋር ተሰይመው ማየታቸው አስቀድሞ የመጨረሻ ውሳኔ አለመስጠታቸው እንዱሁም በጉዲዩ ላይ በቂ ዉይይት ተደርጎበት በአግባቡ ሃሳብ ተንሸራሽሮበት አቋም ያልተያዘበት መሆኑን የሚያሳይ ነው። ስለዚህም በዚህ ጉዲይ በ30/06/2012ዓ.ም የመጨረሻ ዉሳኔ ተሰጥቶበት እና መዝገቡ ተዘግቶ
No topics extracted.