በፍትሀ ብሄር ሥነ-ሥርዓት ህግ ከአንቀጽ 342-344 ያለት ድንጋጌዎች በሥረ-ነገረ ታይቶ የተወሰነ ጉዲይ በተቻለ መጠን ወደ ሥር ፍርድ ቤት ሳይመለስ ጭብጡን በይግባኝ ሰሚ ችልት በኩል እንዱለወጥ ተደርጎ ክርክሩ እንዱቋጭ የሚያዝ፣ መጣራት የሚገባው ነገር ካለ ግን ግራ ቀኙና ማስረጃዎች በቅርብ በሚገኙበትና ጉዲዩ በተጀመረበት ፍርድ ቤት እንዱታይ እድል የሚሰጥ፤ የተጣራው ውጤት ሲቀርብም አዱስ የይግባኝ መዝገብ ሳይከፈት ቀድሞ በተመለሰበት መዝገብ ተጠቃል ፍርድ የሚሰጥበት እንጂ ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩ እንደገና እንዱጣራ በሰጠው ውሳኔም ሆነ የሥር ፍርድ ቤት አጣርቶ በደረሰበት ድምዲሜ ላይ የይግባኝም ሆነ የሰበር አቤቱታ የማይቀርብበትና ተጠቃል ሲመጣ በሰበር አቤቱታ የሚታይ ስለመሆኑ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343 መሰረት ይግባኝ የቀረበለት ፍርድ ቤት ጉዲዩ በፍሬ ነገር የሚጣራና የሥር ፍርድ ቤት እንዱመለከተው የሚመለስ ከሆነ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ፍርድ የሚሰጥበት ሳይሆን ተጣርቶ እንዱቀርብለት ባዘዘው መሰረት የሥር ፍርድ ቤት አጣርቶ እስኪልክ ውጤቱን የሚጠብቅበትና መዝገቡን ለጊዜው በመዝጋት ውጤቱን ወ/ሮ ታንጉት ዱበኩለ እና እነ አቶ ይታያል ዱበኩለ (2 ሰዎች) እንጂ ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤት እንደ አዱስ እንደገና በሕግ አግባብ የመሰለውን እንዱወስን መመለስ የሥነ-ሥርዓት ሕጉ ከሚያዘው ውጪ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩን እንደገና ተመልክቶ ማስረጃ በማጣራትና ተገቢ ያለውን እርምጃ በመውሰድ ለመለሰለት ፍርድ ቤት አባሪ በማድረግ የሚመለስበት ሥርዓት ማስረጃ ማጣራትና መመዘን የሚጠይቅ ተግባር ከሆነ ሰበር ሰሚ ችልት ይህን የማድረግ ሥልጣን ስለላለው የሥር ፍርድ ቤት አዱስ ያጣራውን አባሪ አድርጎ ሳይልክ ቀድሞ ከተሰማው ማስረጃና ክርክር ጋር አጣምሮ እንደ አዱስ ውሳኔ የሚሰጥበት እንጂ ለሰበር ችልት ሉመለስ የማይችል ስለመሆኑ
No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሮ ታንጉት ዱበኩለ ተጠሪ፡-
የሰበር መዝገቡ የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ። አመልካች ያቀረቡት ክስ በአዱስ ዓለም ወረዲ በሚገኘው ይዞታዬ ላይ ያለን የባህር ዛፍ አትክልት ተጠሪዎች ቆርጠው ስለወሰደ ግምቱን ብር 100,000.00 እንዱከፍለኝ የሚል ነው። ተጠሪዎች ያቀረቡት መልስ የአመልካችን ባህር ዛፍ ቆርጠን ጉዲት ያላደረስን በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል። በአማራ ክልል የአዱስ ዓለም ንዐስ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጉዲዩን መርምሮ አመልካች ላይ ለደረሰው የንብረት ጥቅም ጉዲት ተጠሪዎች ብር 15,000.00 እንዱከፍለ ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም ወስኗል። አመልካች በጉዲት መጠኑ ላይ ባለመስማማት ይግባኝ ለምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በመዝገብ ሕዲር 25 ቀን 2011 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ የደረሰው ጉዲት ግራ ቀኙ በመረጧቸው ገለልተኛ ሽማግላዎች እንዱገመትና ቀድሞ ከተሰሙት ምስክሮች ቃል ጋር በመመዘን በጉዲዩ ላይ እንደገና ውሳኔ እንዱሰጥበት ለወረዲ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት መልሶታል። የአዱስ ዓለም ንዐስ ወረዲ ፍርድ ቤት የደረሰውን ጉዲት ካስገመተ በኋላ ለአመልካች ብር 8,000.00 ከወጭና ኪሣራ ጋር እንዱከፈላቸው ግንቦት 12 ቀን 2011 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች ያቀረቡትን ይግባኝ የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዟል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት የአመልካች የሰበር አቤቱታን በአብላጫ ድምጽ ለሰበር ሰሚ ችልቱ አያስቀርብም በማለት ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ተጠሪዎች የጉዲት ካሣ ብር 15,000.00 እንዱከፍለ በተሰጠው ውሳኔ ላይ ያቀረቡት ይግባኝ የለም። ካሣው አንሷል በማለት ይግባኝ ያቀረብኩት አመልካች ሆኜ እያለ የመጀመሪያ ቅሬታዬን ባላገናዘበ መልኩ ቀድሞ ከተወሰነው በታች ብር 8,000.00 እንዱከፈለኝ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት የሚል ነው። የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ አመልካች ባቀረቡት ይግባኝ መነሻነት ግምቱ እንደገና እንዱሰራ ጉዲዩ ሲመለስ ቀድሞ ከተወሰነው በታች መወሰኑ ሕጋዊነቱን ለማጣራት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ በማዘዙ ተጠሪዎች መጥሪያ ደርሷቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት ታይቷል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ክርክሩ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ተከትል የተመራ መሆን አለመሆኑን? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች ያቀረቡት ክስ በአዱስ ዓለም ወረዲ በሚገኘው ይዞታዬ ላይ ያለን የባህር ዛፍ አትክልት ተጠሪዎች ቆርጠው ስለወሰደ ግምቱን ብር 100,000.00 እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ የሚል ሲሆን ተጠሪዎች የሚከራከሩት የአመልካችን ባህር ዛፍ ቆርጠን ጉዲት ያላደረስን በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት አመልካች ላይ ለደረሰው የንብረት ጥቅም ጉዲት ተጠሪዎች ብር 15,000.00 እንዱከፍለ ሲወስን አመልካች በጉዲት መጠኑ ላይ ባለመስማማት ይግባኝ አቅርበው ይግባኝ ሰሚ ችልት የደረሰው ጉዲት ግራቀኙ በመረጧቸው ገለልተኛ ሽማግላዎች እንዱገመትና ቀድሞ ከተሰሙት ምስክሮች ቃል ጋር በመመዘን በጉዲዩ ላይ እንደገና ውሳኔ እንዱሰጥበት ለወረዲ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት መልሶታል። ጉዲዩ የተመለሰለት ፍርድ ቤትም የደረሰውን ጉዲት ካስገመተ በኋላ ለአመልካች አስቀድሞ ከተወሰነው ካሣ በመጠኑ የሚያንስ ብር 8,000.00 እንዱከፍል ውሳኔ ሰጥቷል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታም ተጠሪዎች ይግባኝ ባላቀረቡበት ሁኔታ አስቀድሞ ከተወሰነው ካሣ በታች መወሰኑ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ አይደለም በማለት ነው። መመርመር ያለበት ጭብጥም የሥር ፍርድ ቤቶች የክርክር አመራር ሥርዓት ነው። ክርክሩን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፉነት ሲሆን በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ዓላማዎች የሆኑትን እንደ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግ፣ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትህ፣ ክርክርን ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት የመሳሰለትን ማሳካት ስለማይቻል የተከራካሪዎችን መብት ይነካል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከው ፍርድ ቤት ክሱን በሥረ-ነገሩ አከራክሮና ማስረጃ ሰምቶ ለአመልካች ተገቢ ነው ያለውን ካሣ ወስኗል። አመልካች በካሣ መጠኑ ላይ ይግባኝ በማቅረባቸው ይግባኝ ሰሚ ችልቱ ጉዲዩ እንደገና ተጣርቶ እንዱወሰን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
343(1) መሰረት ለሥር ፍርድ ቤት መልሶታል።
በሥነ-ሥርዓት ሕጉ ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩን ወደሥር ፍርድ ቤት የሚመለስበት ሁኔታ የመጀመሪያው በአንቀጽ 341(1) የተመለከተ ሲሆን ይህም የሥር ፍርድ ቤት ወደ ሥረ-ነገሩ ሳይገባ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ከሰጠና ውሳኔው በይግባኝ ሰሚ ችልት ከተለወጠ ሉመረምራቸው የሚገቡ ነጥቦችን በመለየት ጉዲዩን የሚመለስበት ሥርዓት ነው። ሁለተኛው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343 እና 344 ላይ የተደነገገው በዚህ ችልትም ለተያዘው ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለው ሲሆን ውሳኔው በሥረ-ነገሩ የሰጠው ፍርድ ቤት መያዝ የሚገባውን ጭብጥ ባለመያዙና ማጣራት የሚገባውን ፍሬ ነገር በተገቢው ሁኔታ ሳያጣራ ሲወሰን ይግባኝ ሰሚ ችልቱ እንደገና እንዱመረምርና ማስረጃ እንዱሰማ ጉዲዩ የሚመለስበት ሥርዓት ነው። የሥር ፍርድ ቤት መያዝ የሚገባውን ጭብጥ አለመያዙ ሁልጊዜ ጉዲዩ እንደገና እንዱታይ ለመመለስ በቂ ምክንያት አይደለም። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
342 እንደተመለከተው በሥር ፍርድ ቤት የቀረበው ማስረጃ በቂ ከሆነ የተያዘውን ጭብጥ በማሻሻል ወይም በመለወጥ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ሳይመለስ የመጨረሻ ፍርድ ላሰጥ ይገባል። ይህም የሥነ-ሥርዓት ሕጉ ጊዜና ወጪ ቆጣቢ በሆነ አግባብ ክርክሩ እንዱመራ ያለውን ዓላማ ያሳያል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 342 መሰረት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሚሰጠው ፍርድ የመጨረሻ መሆኑ መገለጹ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት የሚሰጠው ፍርድ የመጨረሻ አለመሆኑን የሚያስገነዝብ ነው።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት ጉዲዩ ሲመለስ የሥር ፍርድ ቤት ያጣራውን ማስረጃ፣ የወሰደውን እርምጃና ለነገሩ አወሳሰን ምክንያት ያደረገውን በመግለጽ ለይግባኝ ሰሚ ችልት እንደሚልክ በድንጋጌው ንዐስ ቁጥር ሁለት ላይ ተመልክቷል። የሥር ፍርድ ቤት አጣርቶ የሚልከው ማስረጃ ሆነ ማናቸውም ዓይነት ውሳኔ የቀድሞው መዝገብ አባሪ ሆኖ እንደሚቆጠር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(2) ላይ ተገልጿል። ሥለሆነም ይግባኝ ሰሚ ችልት የመጨረሻ ፍርድ የሚሰጠው የመዝገቡ አባሪ ተሟልቶ ውጤቱ ከቀረበለት በኋላ ነው። በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 344(1) መሰረት የሥር ፍርድ ቤት በአዱስ አጣርቶ በላከው የመዝገቡ አባሪ ላይ መቃወሚያ ያለው ወገን ክርክሩን (አስተያየቱን) የሚያቀርበው ይግባኝ ሰሚ ችልት በሚወስነው ጊዜ መሆኑ ተመልክቷል። የሥር ፍርድ ቤት የሚልከው አባሪ እንደ አዱስ ውሳኔ የማይቆጠርና ራሱን ችል ይግባኝ የማይባልበት በመሆኑ አዱስ የይግባኝ መዝገብና ቅሬታ የሚቀርብበት አይደለም። በመሆኑም ይግባኝ ሰሚ ችልት አዱስ በመጣው የመዝገብ አባሪ ላይ ግራ ቀኙ ክርክር እንዱያደርጉበት እድል ከሰጠ በኋላ አስቀድሞ ከተከፈተው የይግባኝ መዝገብና ክርክር ጋር መርምሮ በይግባኙ ላይ ውሳኔ ይሰጣል።
የሥነ-ሥርዓቱ ሕጉ ከ342-344 ያለት ድንጋጌዎች በሥረ-ነገሩ ታይቶ የተወሰነ ጉዲይ ላይ በተቻለ መጠን ወደ ሥር ፍርድ ቤት ሳይመለስ ጭብጡን በይግባኝ ሰሚ ችልቱ በኩል እንዱለወጥ ተደርጎ ክርክሩ እንዱቋጭ የሚያዝና መጣራት የሚገባው ነገር ካለ ግን ግራ ቀኙ ሆኑ ማስረጃዎች በቅርብ በሚገኙበትና ጉዲዩ በተጀመረበት ፍርድ ቤት እንዱታይ እድል የሚሰጥና የተጣራው ውጤት ሲቀርብም አዱስ የይግባኝ መዝገብ ሳይከፈት ቀድሞ በተመለሰበት መዝገብ ተጠቃል እንዱታይ መደረጉ የሥነሥርዓት ሕጉ ክርክርን ውጤታማ፣ ወጪና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ ሁኔታ እንዱመራ ያለውን ሃሳብ ያሳያል።
በፍርድ ቤቶች በተግባር የሚሰራበት የተሰማው ማስረጃ በቂ ሆኖ የተያዘው ጭብጥ ስህተት በመሆኑ ብቻ ጉዲዩ የሚመለስበት ሥርዓት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 342ን ድንጋጌ ያልከተለና ሉታረም የሚገባው ነው።ጉዲዩ በፍሬ ነገሩ የሚጣራና የሥር ፍርድ ቤት እንዱመለከተው በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343 መሰረት የሚመለስ ከሆነም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ፍርድ የሚሰጥበት ሳይሆን የሥር ፍርድ ቤት አጣርቶ እስኪልክ ውጤቱን የሚጠብቅበትና የሥር ፍርድ ቤት ባጣራው ነጥብ ሆነ በወሰደው እርምጃ ላይ አዱስ ይግባኝ ሳይቀርብበበት ከቀድሞ ይግባኝ መዝገብ ጋር አባሪ በመሆን የሚቀርብ ነው። ተጣርቶ ከቀረበ በኋላ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤቱ አንድ ላይ ፍርድ የሚሰጥበት ነው። በፍርድ ቤቶች ያለው አተገባበሩ ግን ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩ እንደገና እንዱጣራ በሰጠው ውሳኔ ሆነ የሥር ፍርድ ቤት አጣርቶ በደረሰበት ድምዲሜ ላይ በሀለቱም ውሳኔዎች ላይ ይግባኝ ሆነ የሰበር አቤቱታ በማቅረብ አንድ ጉዲይ የተለያዩ ፍርድ ቤቶች ላይ እንዱታይ የሚያደርግ አላስፈላጊ የፍርድ ቤቱን ሆነ የተከራካሪዎችን ጊዜና ወጪ የሚወስድ እና ፍርድ ቤቶች ላይ የሥራ ጫና በመፍጠር ውጤታማ እንዲይሆኑ የሚያደርግ ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ካሰበው ዓላማ ውጭ የሆነ መታረም ያለበት የክርክር አመራር ግድፈት ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች በተወሰነው ካሣ አነሰኝ በማለት ይግባኝ ያቀረቡ በመሆኑ ጉዲዩ በሥረ-ነገሩ የተወሰነ መሆኑን ያሳያል። ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩ እንደገና እንዱወሰን የመለሰበት ፍርድ ላይ በቀጥታ ይግባኝ ሆነ የሰበር አቤቱታ ባይቀርብበትም በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ቅጽ 23 ላይ ተጠቃል ሲመጣ የሰበር አቤቱታ ላቀርብበት የሚችልና በሰበር ችልት የሚመረመር ስለመሆኑ በተሰጠው ትርጉም መሰረት የውሳኔው ተገቢነትን ተመልክተናል።
ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ለካሣ አወሳሰኑ የንብረቱ ግምት መገመት አስፈላጊ ነው ካለ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
343(1) እንደተመለከተው ግምቱ ተጣርቶ እንዱቀርብለት በማዘዝ መዝገቡን ለጊዜው በመዝጋት ውጤቱን መላክ ሲገባው ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤት እንደ አዱስ እንደገና እንዱወስን መመለሱ ተገቢ አይደለም። ጉዲዩ የተመለሰለት ፍርድ ቤት ካሣ መጠኑ ላይ መርምሮ ቀድሞ ከወሰነው ብር 15,000.00 በመቀነስ ብር 8,000.00 ለአመልካች እንዱከፈል ወስኗል። አመልካችም የሚከራከሩት ብር 15,000.00 ካሣ ሲወሰን አነሰኝ በማለት ይግባኝ ያቀረብኩት እኔ ሆኜ እያለ ተጠሪዎች ካሣ መጠኑ በዛ በማለት ያቀረቡት ይግባኝ ሳይኖር ቀድሞ ከተወሰነው በታች መወሰኑ ይግባኝ ያቀረብኩበትን ዓላማ ይጥሳል በማለት ነው። ይግባኝ የሚቀርበው በሥር ፍርድ ቤት የተሰራውን ስህተት ለማረምና በይግባኝ ባይ መብት የደረሰውን ጉዲት ለማስተካከል ነው። የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343 እና 344 በሚያዘው አግባብ የንብረቱ ግምት ተጣርቶ እስኪመጣ ጠብቆ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ቢወስን ኖሮ ቀድሞ ከተወሰነውና ይግባኝ ከቀረበበት ከብር 15,000.00 በታች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ሉወሰን አይችልም ነበር።
ምክንያቱም ብር 15,000.00 ካሣ መወሰኑን ተጠሪዎች ተቀብለውት ይግባኝ ያላቀረቡበት በመሆኑ ነው።
ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ከሚያዘው ውጭ ጉዲዩ ላይ የሥር ፍርድ ቤት በሥረ-ነገሩ እንደገና እንደ አዱስ እንዱወስን በመመለሱና ፍርድ ቤቱም በሕግ አግባብ የመሰለውን የመወሰን ነጻነት ያለው በመሆኑ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ቀድሞ የወሰነውን በመለወጥ ወስኗል። ውጤቱም አመልካች የካሣ መጠኑ በቂ አይደለም በማለት ይግባኝ ካቀረቡበት ብር 15,000.00 በታች የሆነ ብር 8,000.00 ካሣ እንዱወስን ሆኗል። በዚህም ይግባኝ የሚቀርበው በሥር ፍርድ ቤት የተሰራውን ስህተት ለማረምና በይግባኝ ባይ መብት የደረሰውን ጉዲት ለማስተካከል ዓላማ ቢሆንም በሂደቱ የይግባኝ ሥርዓትን ዓላማ የለወጠና ይግባኝ ባለው ሰው ላይም የመብትና የጥቅም ጉዲት በሚያመጣ ሁኔታ ክርክሩ ተመርቷል። አመልካች ላይ የመብት ጥሰት ያስከተለው የሥር ፍርድ ቤቶች የክርክር አመራር ግድፈት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት የግምት ውጤት ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ከተላከ በኋላ ግራ ቀኙ ክርክር አድርገውበት አመልካች አስቀድሞ ባቀረቡት የይግባኝ መዝገብና ቅሬታ መሰረት በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባ ጉዲይ ነው።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሉመረመር የሚገባው ጭብጥ የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ.ቁ. 343(1) አተገባበር በሰበር ችልት ያለው ውጤት ነው። የሰበር ችልት በዋነኛነት የሚመራበት ሥርዓት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግሥት፣ በፋደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 እና ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 454/1997 የተመለከቱ ልዩ ደንቦች ካልሆነ በቀር፤ ልዩ የሥነ-ሥርዓት ደንብ እስካልወጣለት ድረስ፤ በፍትሕ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ስለይግባኝ አቀራረብ የተመለከተው ለሰበር ችልቱም ተፈጻሚ ነው። ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 80(3) ሆነ የፍደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ላይ በመጨረሻ ውሳኔ ላይ በተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንጂ ማስረጃው ተመዝኖ የተደረሰበትን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ላይ እንዱመለከት ሥልጣን አልተሰጠውም። ይህም ማስረጃ ማጣራትና መመዘን ሥልጣን እንደላለው ያስገነዝባል። ማስረጃ ለመስማትና ለመመዘን ሥልጣን የለውም ማለት ግን ከማስረጃ ጋር የተያያዘ ጭብጥ ያለውን የሰበር አቤቱታ አይመለከትም ማለት አይደለም። ማስረጃ ለመመዘን ሥልጣን የተሰጠው ፍርድ ቤት ማስረጃ ሲቀበል የተከራካሪዎችን እኩል የመደመጥ መብት ካላከበረ፣ የማስረዲት ሸክም (burden of production) የማን ነው የሚለውን ካልለየ፣ የማስረጃ ተቀባይነትና ተገቢነት ላይ መከተል የሚገባውን ሥርዓት ካልተከተለ፣ በምዘና ጊዜ የሁለንም ተከራካሪዎች ማስረጃ አብሮ ካልመዘነ፣ የተለየ የማስረዲት ደረጃ (standard of proof) የሚጠይቁ ጉዲዮችን በሚጠይቀው ደረጃ ልክ መረጋገጡን ካላሳየ እና በመሰረታዊ ሕግ ሆነ በሥነ-ሥርዓት ሕግ ያለትን የማስረጃ ሕጎችና መርሆች ካላከበረ ጉዲዩ የማስረጃ ምዘና ሳይሆን የሕግ አተረጓጎም ስህተትና ፍርድ ቤት ያለበትን ኃላፉነት አለመወጣት ስለሚሆን የሰበር ሰሚ ችልቱ የሚመለከተው ጉዲይ ይሆናል።
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 342 በተመለከተው ድንጋጌ መሰረት በሥር ፍርድ ቤት የቀረበው ማስረጃ በቂ ከሆነ ነገር ግን የጭብጥ አመሰራረቱ የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 246 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን መሰረት ያላደረገ ከሆነ የተያዘውን ጭብጥ በማሻሻል ወይም በመለወጥ ጉዲዩን ሳይመልስ የሰበር ችልቱ ሉወስን ይችላል። ከዚህ ውጭ ማስረጃ ማጣራትና መመዘን የሚጠይቅ ተግባር ከሆነ እና በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
343(1) እንደተመለከተው ለሥር ፍርድ ቤት የሚመለስ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤት አጣርቶ የሚልከው ውጤት ቀድሞ ከተሰማው ማስረጃ ጋር ምዘና የሚጠይቅ ከሆነ ሰበር ችልት ማስረጃን በመመዝን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ላይ ሉደርስ ስለማይችል ጉዲዩ የተመለሰለት የሥር ፍርድ ቤት አዱስ ያጣራውን አባሪ አድርጎ ሳይልክ ቀድሞ ከተሰማው ማስረጃና ክርክር ጋር አጣምሮ ተመልክቶ ጉዲዩ ላይ እንደገና እንደ አዱስ ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል። ይህም የሥነ-ሥርዓት ሕጉ አቀራረጽና አተገባበር ላይ የተለየ ውጤት የሚያስከትል ነው።
የሥነ-ሥርዓት ሕጉ የወጣው የኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት ሥራ ላይ ከመዋለ በፉት በመሆኑ የክርክር አመራር ሥርዓቱ በሕገ-መንግሥቱ ስለ ሰበር ችልት የተሰጠውን ሥልጣን ታሳቢ ያደረገ አይደለም።
ሕገ-መንግሥቱ በአንቀጽ 9(1) ላይ እንደተመለከተው የሀገሪቱ የበላይ ሕግ በመሆኑ የሥነ-ሥርዓት ሕጉ በሕገ-መንግሥቱ ሰበር ችልት ካለው ሥልጣን ጋር ተጣጥሞ መተርጎም ይኖርበታል። ሥለሆነም በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) የተመለከተው ጉዲዩ የሥር ፍርድ ቤት እንደገና ተመልክቶ ማስረጃ በማጣራትና ተገቢ ያለውን እርምጃ በመውሰድ ለመለሰለት ፍርድ ቤት አባሪ በማድረግ የሚመለስበት ሥርዓት ማስረጃ እንደገና እንዱመዘን የሚያደርግ ከሆነ ሰበር ሰሚ ችልቱ ይህን የማድረግ ሥልጣን ስለላለው ጉዲዩ የተመለሰለት ፍርድ ቤት እንደ አዱስ ውሳኔ የሚሰጥበት እንጂ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሉመለስ አይችልም በማለት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
348(1) መሰረት ተሽሯል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ የሥር ንዐስ ወረዲ ፍርድ ቤት ስለካሣ አወሳሰኑ በመዝገብ የቀረበውን የንብረት ግምት ውጤት አመልካች አስቀድመው ካቀረቡት የይግባኝ መዝገብና ቅሬታ ጋር መርምሮ የመሰለውን እንዱወስን ጉዲዩን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት መልሰናል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ አመልካች የራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔው መሰረት እንዱፈጽም አዘናል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.