አዱስ በቀረበ ክስ በጭብጥነት ተይዞ እልባት ላሰጥበት የሚገባ ጉዲይ በልላ መዝገብ ላይ በጭብጥነት ተይዞ እልባት የተሰጠበት መሆኑ ከተረጋገጠ ምንም እንኳን በቀደመዉ ክስ ለተጠየቀዉ ዲኝነት ምክንያት የሆነዉ ጉዲይ አዱስ ከቀረበዉ ክስ ጋር የተለያየ ቢሆንም አዱስ የቀረበዉን ክስ መሰረት በማድረግ በጭብጥነት ተይዞ መጣራት የሚገባዉ ጭብጥ በቀደመዉ ክርክር እልባት የተሰጠበት መሆኑ ከተረጋገጠ አዱስ የቀረበዉ ክስ ድጋሚ እነ አቶ ጉዐሽ ካሳ (2 ሰዎች) እና አቶ ሲሳይ ታረቀኝ (res judicata) ነዉ የሚባል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህግ አንቀጽ 5
No summary available.
የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ኑረዱን ከድር ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አንድ ክስ በድጋሚ የቀረበ ነዉ ልባል የሚችልበትን ሁኔታ የሚመለከት ነዉ። ክርክሩ በተጀመረበት በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ ሲሆን አመልካቾች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን ተከራክሯል።
የተጠሪ ክስ ይዘትም ተከሳሾች ባለአክሲዮኖች የሆኑበት ጂድጂ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የሚባል ኩባኒያ በህዲሴ ግድብ ዉስጥ የምንጣሮ ስራ ለመስራት ከብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር ዉል የፈጸመ ሲሆን ከሳሽ እና ላልች ጓደኞቼ ደግሞ የምንጣሮ ስራዉን ለመስራት ከኩባኒያዉ የንዐስ ተቋራጭነት ዉል ፈጽመን ስራዉን የሰራን ቢሆንም ኩባኒያዉ የሰራንበትን ገንዘብ ሉከፍለን ፍቃደኛ ባለመሆኑ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ አቅርበን ብር 21,362,40.00 ከታህሳስ 21 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍል ተወስኗል።
ይሁንና ኩባኒያዉ በዉሳኔዉ መሰረት ገንዘቡን ባለመክፈለ የአፈፃፀም ክስ ያቀረብን ቢሆንም 1ኛ ተከሳሽ (1ኛ አመልካች) ኩባኒያዉ ምንም ዓይነት ገንዘብ የላለዉ እና በምንጣሮ ስራዉ የተከፈለዉ ገንዘብ ያለመኖሩን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል። ይሁንና ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ኩባኒያዉ ብር 22,408,085 የተከፈለዉ መሆኑንና ለተከሳሾችም ከ02/08/2006 ዓ.ም እስከ 19/10/2007 ዓ.ም ባለዉ ጊዜ ዉስጥ በአጠቃላይ ብር 16,420,383.00 ለተከሳሾች የተከፈለ መሆኑ ተረጋግጧል። ተከሳሾች የኩባኒያዉን ትርፍ የተከፊፈለት በንግድ ህጉ አግባብ ኩባኒያዉ ትርፍ ማግኘቱ በኦዱተር ሳይረጋገጥ መሆኑ ክፍፍለን ህገ ወጥ የሚያደርገዉ ሲሆን ተከሳሾች ይህን በማድረግ ከሳሽ በፍርድ ባገኘሁት መብት እንዲልጠቀም ምክንያት በመሆናቸዉ ወለደን ጨምሮ ከተወሰነዉ ብር 2,811,436.48 ዉስጥ የእኔን ድርሻ ብር 702,859.12 ክሱ ከቀረበበት ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ።
አመልካቾች ክሱ በድጋሚ የቀረበ ነዉ የሚል የመጀመሪያ መቃወሚያ በማስቀደም የተለያዩ የፍሬ ነገር ክርክሮችን አቅርበዉ የተከራከሩ ሲሆን፣ ክሱ በድጋሚ የቀረበ ነዉ በሚል ላቀረቡት የመጀመሪያ መቃወሚያ መሰረት ያደረጉትም ከሳሽ ከላልች ከሳሾች ጋር አብሮ በመሆን በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በጂዱጂ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ላይ ያቀረቡት ክስ የመጨረሻ ፍርድ የተሰጠዉ በመሆኑ በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ ድጋሚ ዲኝነት ማቅረብ አይችልም የሚል ነዉ።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር ከሰማ በኋላ ከሳሽ ከላልች ጋር በመሆን ክስ መስርተዉ ከኩባኒያዉ ጋር ባደረጉት የንዐስ ኮንትራት ዉል መሰረት 0.00 እንዱከፈላቸዉ ተወስኗል፤ ፍርደ ባለመፈጸሙ ምክንያት በአፈ/መ/ አቅርበዉ ከሳሾች የአፈፃፀም ተከሳሽን ንብረት ወይም ገንዘብ አጣርተዉ ሲያቀርቡ አፈፃፀሙ የሚቀጥል መሆኑን ጠቅሶ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መዝጋቱ መረጋገጡን፤
ይህ ከሆነ በኋላ የኩባኒያዉ ወራሾች በሆኑት ተከሳሾች ላይ ከሳሽ ያቀረበዉ ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 5 መሰረት በድጋሚ የቀረበ ነዉ በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በበኩለ ተጠሪ ከላልች ሰዎች ጋር በመሆን ቀደም ሲል በመ/ በሆነዉ መዝገብ ጂዱጂ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ላቀረቡት ክስ ዉልን መሰረት ያደረገዉ ሲሆን በመ/ በአሁን አመልካቾች ላይ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ደግሞ አመልካቾች የማህበሩን ገንዘብ ወደ እራሳቸዉ በማዛወራቸዉ የተወሰነላቸዉ ገንዘብ እንዲይፈጸምላቸዉ በማድረግ ጉዲት አድርሰዋል የሚል ያላግባብ መበልጸግን የሚመለከት በመሆኑ በድጋሚ የቀረበ ነዉ ለማለት አይቻልም በማለት የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካቾች በጠበቃቸዉ አማካይነት ሐምል 22 ቀን 2012 ዓ.ም አዘጋጅተዉ ባቀረቡት አቤቱታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚለባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር ታርሞ እንዱወሰንላቸዉ ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን፣ የአቤቱታቸዉ መሰረታዊ ይዘትም በአጭሩ የአሁን ተጠሪ አስቀድመዉ መርጠዉ እና ወስነዉ አመልካቾችን መክሰስ ሲችለ ሆን ብለዉ ትተዉ ጂዱጂ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ላይ በመ/ ላይ ዲኝነት ጠይቀዉ ተወስኖላቸዉ የኩባኒያዉን ንብረት ባገኙ ጊዜ መዝገቡን ማንቀሳቀስ እንዱችለ መብት ተጠብቆላቸዉ እያለ በአመልካቾች ላይ ያቀረቡት ክስ በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ በድጋሚ የቀረበ ሆኖ እያለ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክሱ በድጋሚ የቀረበ አይደለም በሚል የሰጠዉ ዉሳኔ ክስ በድጋሚ እንዲይቀርብ የሚከለክለዉን የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉን ዓይነተኛ ዓላማ ያገናዘበ አይደለም የሚል ነዉ።
የሰበር አቤቱታዉ በአጣሪ ችልት ተመርምሮም ተጠሪ ያቀረቡት የመጀመሪያ መቃወሚያ ተቀባይነት የማግኘቱን አግባብነት ከፍ/ብ/ህጉ አንቀጽ 5 አንፃር ለማጣራት ሲባል ለሰበር ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በተደረገላቸዉ ጥሪ መሰረት ህዲር 23 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ መልስ በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት ሁለቱ ክሶች የተለያዩ በመሆናቸዉ ክሱ በድጋሚ የቀረበ አይደለም በማለት በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት አለመሆኑን ጠቅሰዉ ጸንቶ እንዱወሰንላቸዉ ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካቾች ባቀረቡት የመልስ መልስ አቤቱታቸዉን በማጠናከር ተከራክረዋል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት በአጭሩ ከላይ የተገለጸዉን ሲመስል ይህ ችልትም መዝገቡን ለማስቀረብ በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘዉን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
እንደመረመረዉም ተጠሪ ከላልች ሰዎች ጋር በመሆን ጂዱጂ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ላይ ባቀረቡት ክስ ከማህበሩ ጋር ባደረጉት የምንጣሮ ስራ ዉል መሰረት ለሰሩት ስራ ያልተከፈላቸዉ ገንዘብ መኖሩን ጠቅሰዉ ዲኝነት መጠየቃቸዉን ተከትል የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ፍትሐብሕር ችልት ጉዲዩን በመ/ ላይ አስተናግድ ከታህሳስ 21 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር 0.00 እንዱከፈላቸዉ መወሰኑንና ማህበሩ እንደ ፍርደ ባለመፈጸሙ ምክንያትም የአፈፃፀም ክስ ቀርቦበት ማህበሩ ገንዘብ እንደላለዉ በመረጋገጡ ምክንያት ተጠሪን ጨምሮ በፍርደ መብት ያገኙት ላልች ሰዎች ማህበሩ ገንዘብ ሲያገኝ የማንቀሳቀስ መብታቸዉ ተጠብቆ የአፈፃፀም መዝገቡ ለጊዜዉ እንዱዘጋ ስለመደረጉ የግራ ቀኝ ክርክር እና የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ይዘት ያሳያል። ተጠሪ ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት በሆነዉ ክስ ለጠየቁት ዲኝነት መሰረት ያደረጉት አመልካቾች የጂዱጂ ኃላ/የተወ/የግል ማህበር ባለአክሲዮኖች በተለይም 1ኛ አመልካች የማህበሩ ስራ አስኪያጅ በመሆን የማህበሩን ስራ ባልተገባ መንገድ በመምራት ማህበሩ ትርፍ ማግኘቱ ሳይረጋገጥ ለማህበሩ የተከፈለዉን ገንዘብ የንግድ ህጉ ከሚፈቅደዉ ዉጪ ያላግባብ ተከፊፍለዉ ማህበሩ ገንዘብ እንዲይኖረዉ በማድረግ ተጠሪ በማህበሩ ላይ ያስፈረደዉን ገንዘብ እንዲያገኝ ምክንያት መሆናቸዉን ስለመሆኑ ለመገንዘብ ተችሎል። እንግዱህ የተጠሪ ክስ ይዘት ይህ ከሆነ ቀደም ሲል በማህበሩ ላይ በቀረበዉ ክስ መነሻነት የተሰጠ ዉሳኔ ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ያቀረበዉን ክስ በድጋሚ የቀረበ ነዉ የሚያስብለዉ መሆን ያለመሆኑ የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሻዉ መሰረታዊ ጭብጥ ይሆናል።
በመሰረቱ የፍትሐብሕር የክርክር አመራር ሥርዓት ዓይነተኛ ዓላማ የክርክርን ሂደት ለማቀላጠፍና አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ መቋጫ ለማበጀት መሆኑ ይታወቃል። ይህን ዓላማ ለማሳካት ከተደነገጉት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ጽንሰ ሃሳቦች ዉስጥ አንደ የመጨረሻ ፍርድ ያገኙ ጉዲዮች (Res judicata) የሚለዉ ጽንሰ ሃሳብ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጋችን አንቀጽ 5 ላይ በግልጽ ተመልክቷል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 5 ድንጋጌ መሰረት ማንኛዉም ፍርድ ቤት ወይም በህግ የዲኝነት ስልጣን የተሰጠዉ አካል ክርክሩን ተቀብል የመጨረሻ ዉሳኔ ከሰጠ በኋላ ቀድሞ በፍርድ የተወሰነዉ ክርክር ሥረ ነገርና የተያዘዉ ጭብጥ አንድ ዓይነት ከሆነ በክርክሩ ላይ የነበሩት ወይም ከተከራካሪ መብት ያገኙት 3ኛ ወገኖች በዚያዉ ነገር ላይ ሁለተኛ ክስ ወይም ማናቸዉም ዓይነት ላላ ክርክር ላቀርብባቸዉ አይችልም። አንድ ጉዲይ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነዉ ለማለት መረጋገጥ ካለባቸዉ ሁኔታዎች ዉስጥ ቀደም ሲል ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ የነበሩ ጉዲዮች በድጋሚ በቀረበዉ ክስም ላይ በቀጥታ የፍሬ ነገር ጭብጥ ሆነዉ መቅረባቸዉ፣ ቀደም ሲል የነበረዉን ክርክር አሁን በክርክር ተሳታፉ በሆኑ ወገኖች ወይም ከእነሱ መብት በተላለፈላቸዉ ወገኖች መሆኑንና እነዚህ ጉዲዮችም ቀደም ሲል በተካሄደዉ ሙግት የመጨረሻ ዉሳኔ ያረፈባቸዉ መሆኑን ስለመሆኑ ከድንጋጌዉ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን ይህ ሰበር ችልት በሰ/መ/ እና በላልች መዛግብት ላይ የሰጣቸዉ የህግ ትርጉሞችም ይህንኑ የሚያስገነዝቡ ናቸዉ። ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ የሚለዉ ሐረግ አጠቃላይ ይዘቱ ሲታይም በመጀመሪያዉ ክርክር ላይ በአንደኛዉ ወገን ተጠይቆ በልላኛዉ ወገን የተካደ ወይም በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የተካደ እና በዚህ ጉዲይ ላይም ዉሳኔ የተሰጠበት ወይም ላሰጥበት ይገባ የነበረ መሆኑንም መገንዘቡ ተገቢ ነዉ። አዱስ በቀረበዉ ክስ መሰረት በጭብጥነት ተይዞ እልባት ላሰጥበት የሚገባ ጉዲይ በልላ መዝገብ ላይ በጭብጥነት ተይዞ እልባት የተሰጠበት መሆኑ ከተረጋገጠ ምንም እንኳ በቀደመዉ ክስ ለተጠየቀዉ ዲኝነት ምክንያት የሆነዉ ጉዲይ አዱስ ከቀረበዉ ክስ ጋር የተለያየ ቢሆንም አዱስ የቀረበዉን ክስ መሰረት በማድረግ በጭብጥነት ተይዞ መጣራት የሚገባዉ ጭብጥ በቀደመዉ ክርክር እልባት የተሰጠበት መሆኑ ከተረጋገጠ አዱስ የቀረበዉ ክስ ድጋሚ የቀረበ (resjudicata) ነዉ የማይባልበት ምክንያት የለም።
ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት፣ ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ፣ ተጠሪ ከላልች ሰዎች ጋር በመሆን ቀደም ሲል በማህበሩ ላቀረቡት ክስ መሰረት ያደረጉት በመካከላቸዉ የተደረገዉን የምንጣሮ ስራ ዉል ሲሆን በክሱ ላይ የተመለከተዉን ገንዘብ ማህበሩ የመክፈል ኃላፉነት ያለበት መሆን ያለመሆኑን አጣርቶ በመወሰን ረገድ በጭብጥነት የሚያዘዉ ወይም በጭብጥነት ተይዞ ላሆን የሚችለዉ በመካከላቸዉ የምንጣሮ ስራ ዉል ግንኙነት መኖር ያለመኖሩ እና ዉለ መኖሩ ካልተካደ ወይም መኖሩ በማስረጃ ከተረጋገጠ ማህበሩ በዉለ መሰረት ገንዘቡን የማይከፍልበት ህጋዊ ምክንያት መኖር ያለመኖሩ ነዉ። በአንፃሩ ለዚህ ሰበር አቤቱታ ምክንያት በሆነዉ ጉዲይ ላይ ግን ተከሳሾች የአሁን አመልካቾች እንጂ ማህበሩ (ማህበሩ ምንም እንኳን በአመልካቾች የተቋቋመ ቢሆንም ራሱን የቻለ ህለረዉና ያለዉ መሆኑን ልብ ይሎል) አይደለም፤ አመልካቾች ከፍሬ ነገር ጋር በተያያዘ ያቀረቡትን ክርክር መሰረት በማድረግም በፍርድ ቤቱ የሚያዘዉ ጭብጥ አመልካቾች ለማህበሩ መከፈል የነበረበትን ገንዘብ ከህግ አግባብ ዉጪ ተከፊፍለዉ በዚህም ምክንያት ማህበሩ ገቢ እንዱያጣ አድርገዋል? ወይስ አላደረጉም? ድርጊቱን መፈጸማቸዉ ከተረጋገጠ ይህ ድርጊታቸዉ ተጠሪ በማህበሩ ላይ ያስወሰነዉን ገንዘብ እንዲያገኝ ምክንያት ሆኗል ወይ? አልሆነም? የሚለ እና ተያያዥ ጭብጦች እንደሚሆን ይታሰባል። ይህም የሚያሳየዉ ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ባቀረበዉ ክስ እና በቀደመዉ መዝገብ ላይ በሚያዙ የክርክር ጭብጦች መካከል ልዩነት መኖሩን ነዉ። ለዚህ ሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉን ክስ መሰረት በማድረግ ከላይ በተመለከተዉ መልኩ የሚያዙ ከጭብጦች በቀደመዉ ክርክር በጭብጥነት አልተያዙም፤ መያዝ የሚገባቸዉ ጭብጦችም አይደለም። በመዝገብ ላይ በቀረበዉ ክስ መነሻነት ለተሰጠ ዉሳኔ ምክንያት የሆነዉ ዉል ሲሆን፣ አሁን በተያዘዉ ጉዲይ ለተጠየቀዉ ዲኝነት ምክንያት የሆነዉ ከዉል ዉጪ ኃላፉነትን የሚመለከት መሆኑ ሲታይ በሁለቱ መዝገቦች ላይ የቀረቡት ክሶች የተለያዩ የክስ ምክንያቶችን መሰረት ያደረጉ መሆናቸዉን ነዉ።
በአጠቃላይ በመ/ ላይ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ ተጠሪ ለዚህ ሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉን ክስ እንዲያቀርብ የሚከለክል ባለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት፣ የተጠሪ ክስ በድጋሚ የቀረበ አይደለም በሚል ምክንያት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር፣ የሰጠዉ ዉሳኔ በሁለቱ መዝገቦች ላይ በቀረቡት ክሶች መካከል ያለዉን መሰረታዊ ልዩነት እና ባህሪ ክስ በድጋሚ ቀርቧል ለማለት የሚቻልበትን ሁኔታ አስመልክቶ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 5 ላይ ከተመለከተዉ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ የተሰጠ ትክክለኛ ዉሳኔ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ሰህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት የለም። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 28/07/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ፀንተዋል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.