እግድ እንዱሰጥ የተጠየቀው ክስ ሳይቀርብ ከሆነ ተከሳሽ የሚሆነው ወገን ላይ ያልተገባ የመብት ገደብ እንዲይደረግበት፤ ጊዜያዊ እግድ የሚጠይቀው ወገን ክስ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ እንዲለና የክስ ዝግጅቱ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈለገበትን ምክንያት፣ ክሱ እስኪቀርብ ድረስ የእግድ ትዕዛዙ ባይሰጥ የሚያስከትለው ጉዲት ማሳየት ያለበት ሲሆን ፍርድ ቤቱም ክሱን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ ብቻ በጊዜ ገደብ የተገደበ የእግድ ትዕዛዝ ላሰጥ የሚችል የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ኃ/የተ/የግል ማህበር እና ቻይና ሲ ኢ ኤም ሲ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ሉሚትድ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 154(ለ) የእግድ ትእዛዝ እንዱሰጥ የተጠየቀው ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚከፈል የዋስትና ክፍያ ላይ ከሆነ፣ የገንዘብ ግዳታ/ዋስትና ሰነድ የፊይናንስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 648/2001 አንቀጽ 2(20)ን ጨምሮ በተለያዩ ሕጎች የፊይናንስ ቃል ኪዲን ወይም የፊይናንስ ግዳታን ለመፈጸም የሚሰጥ ወይም የሚያዝ ማንኛውም ሰነድ ሲሆን የግምጃ ቤት ሰነድን፣ የተስፊ ሰነድን እና ቦንድን ይጨምራል ተብል ትርጉም የተሰጠበትና፤ ዋስትናው የተሰጠው ያለ ቅድመ ሁኔታና የሚፈጸመውም ያለ ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ፤ በዚህ ላይ የሚቀርብ ክስ የሚታገድ ከሆነ የውለን ባሕሪ የሚቀይረው፣ ህግንና ተዋዋዮች ያሰቡትን ዓላማ ማሳካት የማይቻል ስለመሆኑ ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመክፈል የተገባን የዋስትና ግዳታ እንዲይከፈል እግድ ማቅረብ ህጋዊነት የላለው ስለመሆኑ (2 ሰዎች)
No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ኃ/የተ/የግል ማህበር ፡- ጠበቃ አውግቸው ክብረት ቀረበ ተጠሪ፡-
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ እና 2ኛ ተጠሪ 2ኛ ተከሳሽ ነበሩ። አመልካች ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ያቀረባቸው ክሶች ተጣምረው የታዩ ሲሆን ይዘቱም 1ኛ ተጠሪ በወልቃይት ስኳር ፊብሪካ የሲቪል ወርክ ሥራዎች ለመገንባት ባወጣው ጨረታ አመልካች አሸናፉ በመሆን ሚያዚያ 26 ቀን 2008 ዓ/ም የግንባታ ውል ተደርጓል። ለዚህም የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ብር 20,800,000.00 እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ብር 28,801,383.62 ከ2ኛ ተጠሪ የተሰጠ በአመልካች ቀርቧል። 1ኛ ተጠሪ ግንባታው ዘግይቷል በሚል ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ/ም ውለን በመሰረዝ 2ኛ ተጠሪ በዋስትናው መሰረት እንዱፈጽምለትም ጠይቋል። ግንባታው የዘገየው አመልካች ባለሀብት ላይ በደረሰ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያትና በ1ኛ ተጠሪ ጥፊት በመሆኑ የሥምምነት ውል ማቋረጥ ተግባሩ ውድቅ እንዱደረግና የችሮታ ጊዜ እንዱሰጠኝ እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ የቅድመ ክፍያ ዋስትና እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ገንዘብ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲይከፍል ትዕዛዝ እንዱሰጥ ዲኝነት ጠይቋል። 1ኛ ተጠሪ የሰጠው መልስ ውለ የተቋረጠው አመልካች በሥምምነቱ መሰረት ባለመፈጸሙ ነው። አመልካች ጥፊት ባይኖርበትም ውለን የማቋረጥ በሕግ መብት አለን። ውለ የችሮታ ጊዜን አይፈቅድም። ሁለቱም ዋስትናዎች ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚከፈለ በመሆናቸው በፍርድ ቤት ክርክር የሚቀርብባቸውና የሚታገደ አይደለም። ስለዚህ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል። 2ኛ ተጠሪ በበኩለ አመልካች እግድ ካላሰጠ በስተቀር ክፍያውን ለ1ኛ ተጠሪ እንፈጽማለን ብሎል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ ውለ የግንባታ ውል በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ. 3035 መሰረት አሰሪው ተቋራጩ አንዲችም ጥፊት ባያደርግም እንኳን የፈረመውን ውል ማፍረስ እንደሚችል ተደንግጓል። ለሥራ ተቋራጩ የሰጠው መብት ላልች የይገባኛል መብቶች/ጥቅሞች ካለ ማቅረብ ነው። ስለዚህ ሕጉ ውለን በተናጠል ማፍረስ ስለሚፈቅድ ውለ መፍረሱ ተገቢ ነው። በፈረሰ ውል የችሮታ ጊዜ ሉጠየቅ አይችልም። ዋስትናዎቹም በፍ/ሕ/ቁ. 1925(1) መሰረት ያለ ቅድመ ሁኔታ የተደረጉ በመሆኑ 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ከመክፈል የሚያስቀር የሕግ ሆነ የውል ግዳታ የለም በማለት ክሱን ውድቅ በማድረግ ወስኗል። አመልካች ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበው ቅሬታ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዟል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ባደረግነው የግንባታ ውል መሰረት ዝቀተኛ አፈጻጸም ነው ያለን ወይስ አይደለም የሚለውን እና ውለ ቢቋረጥ እንኳን የምንጠይቀውን የተለያዩ ክፍያዎች መጠየቅ የምንችለው በሥምምነታችን መሰረት በግልግል ጉባዔ ሆኖ እያለ የግንባታ ውለን አስመልክቶ በፍርድ ቤት ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም።
ጉዲዩ ለግልግል ቀርቦ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስም በዋስትናው የተያዘው ብር 48,300,000.00 ገንዘብ ታግድ እንዱቆይ ትዕዛዝ ላሰጥ ይገባል የሚል ነው። የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን መርምሮ በውላቸው አለመግባባት የሚፈታው በግልግል ጉባዔ እንደሆነ ተመልክቶ እያለ ይህ ታልፍ ውለ ተቋርጧል፤
በዋስትና የተያዘው ገንዘብም ለ1ኛ ተጠሪ ይከፈል መባለ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርብ በማዘዙ 1ኛ ተጠሪ ያቀረበው መልስ የአመልካች የሰበር አቤቱታ በዋነኛነት መሰረት ያደረገው እግድ እንዱሰጥ ሲሆን የእግድ ጥያቄ የሚቀርበው ዋና ክርክር ወይም ክስ ኖሮ ክርክሩ በፍርድ ቤት እስኪወሰን ድረስ ለጊዜው የሚሰጥ ትዕዛዝ ነው። ዋና ክርክር በላለበት ገና ለገና ጉዲዩ በግልግል እስኪታይ ድረስ እግድ ይሰጥልኝ ብል ዲኝነት መጠየቅ በሕግ ያልተፈቀደ ነው።
በሥር ፍርድ ቤትም ያልተነሳ ክርክር ነው። ክሱን ለግልግል ጉባዔ ማቅረብ እየቻለና የእግድ ጥያቄውን በዚሁ ማቅረብ እየተቻለ ሆነ ብል ሥልጣን ለላለው ፍርድ ቤት ክስ አቅርቧል። አመልካች ክስ ሲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ሥልጣን የለውም በማለት የተከራከረን ሲሆን አመልካች ፍርድ ቤቱ ሥልጣን አለው በማለት ክርክር አቅርቧል። ይህም በውለ መሰረት ለግልግል ጉባዔ ማቅረብ የሚችለውን መብቱን እንደተወ ይቆጠራል። ማንም ሰው በጥፊቱ ተጠቃሚ ላሆን አይችልም። ውለን ማቋረጥ መብት አለን። ዋስትናውም ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚከፈል በመሆኑ እግድ ላቀርብበት አይገባም በማለት ተከራክሯል። 2ኛ ተጠሪ ለሰበር አቤቱታው መልስ ባያቀርብም በዚህ ችልት በነበረው የእግድ ክርክር ላይ ቀርቦ የዋስትናው ገንዘብ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲይከፈል እግድ ስለተሰጠበት እንጂ አንከፍልም አላልንም በማለት ክርክር አቅርቧል። አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ፍርድ ቤት የግንባታ ውለን አስመልክቶ ክርክር ለማድረግ ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የዋስትና ገንዘቡ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲይከፈል እግድ እንዱሰጥ ዲኝነት መቅረቡ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከለተ መሆን አለመሆኑን? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ እንደመረመርነው አመልካች ያቀረበው ክስ 1ኛ ተጠሪ በወልቃይት ስኳር ፊብሪካ የሲቪል ወርክ ሥራዎች ለመገንባት ባወጣው ጨረታ አመልካች አሸናፉ በመሆን ሚያዚያ 26 ቀን 2008 ዓ/ም የግንባታ ውል ተደርጓል። ለዚህም የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ብር 20,800,000.00 እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ብር 28,801,383.62 ከ2ኛ ተጠሪ የተሰጠ በአመልካች ቀርቧል። 1ኛ ተጠሪ ግንባታው ዘግይቷል በሚል ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ/ም ውለን በመሰረዝ 2ኛ ተጠሪ በዋስትናው መሰረት እንዱፈጽምለትም ጠይቋል። ግንባታው የዘገየው አመልካች ባለሀብት ላይ በደረሰ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያትና በ1ኛ ተጠሪ ጥፊት በመሆኑ የሥምምነት ውል ማቋረጥ ተግባሩ ውድቅ እንዱደረግና የችሮታ ጊዜ እንዱሰጠኝ እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ የቅድመ ክፍያ ዋስትና እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ገንዘብ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲይከፍል ትዕዛዝ እንዱሰጥ ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ በበኩለ ውለ የተቋረጠው አመልካች በሥምምነቱ መሰረት ባለመፈጸሙ ነው። አመልካች ጥፊት ባይኖርበትም ውለን የማቋረጥ በሕግ መብት አለን። ውለ የችሮታ ጊዜን አይፈቅድም። ሁለቱም ዋስትናዎች ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚከፈለ በመሆናቸው በፍርድ ቤት ክርክር የሚቀርብባቸውና የሚታገደ አይደለም። ስለዚህ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል። 2ኛ ተጠሪም አመልካች እግድ ካላሰጠ በስተቀር ክፍያውን ለ1ኛ ተጠሪ እንፈጽማለን ብሎል። የሥር ፍርድ ቤቶች ውለ የግንባታ ውል በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ. 3035 መሰረት አሰሪው ተቋራጩ አንዲችም ጥፊት ባያደርግም እንኳን የፈረመውን ውል ማፍረስ እንደሚችል ተደንግጓል። ለሥራ ተቋራጩ የሰጠው መብት ላልች የይገባኛል መብቶች/ጥቅሞች ካለ ማቅረብ ነው። ስለዚህ ሕጉ ውለን በተናጠል ማፍረስ ስለሚፈቅድ ውለ መፍረሱ ተገቢ ነው። በፈረሰ ውል የችሮታ ጊዜ ሉጠየቅ አይችልም። ዋስትናዎቹም በፍ/ሕ/ቁ.
1925(1) መሰረት ያለ ቅድመ ሁኔታ የተደረጉ በመሆኑ 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ ከመክፈል የሚያስቀር የሕግ ሆነ የውል ግዳታ የለም በማለት ክሱን ውድቅ አድርገዋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ የተመሰረተው በግንባታው ውል መሰረት የሚጠየቁ ክፍያዎችን ለመጠየቅ በውላችን መሰረት አለመግባባት የሚፈታው በግልግል ጉባዔ በመሆኑ ግንባታ ውለን አስመልክቶ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም እንዱሁም ክሱን ለግልግል ጉባዔ እስክናቀርብ ድረስ 2ኛ ተጠሪ የቅድመ ክፍያ ዋስትና እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ገንዘብ 48,300,000.00 ለ1ኛ ተጠሪ እንዲይከፍል ታግድ ሉቆይ ይገባል የሚል ሲሆን 1ኛ ተጠሪ በበኩለ ክሱን ለግልግል ጉባዔ ማቅረብ እየቻለና የእግድ ጥያቄውን በዚሁ ማቅረብ እየተቻለ ሆነ ብል ሥልጣን ለላለው ፍርድ ቤት ክስ አቅርቧል። አመልካች ክስ ሲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ሥልጣን የለውም በማለት የተከራከርን ሲሆን አመልካች ፍርድ ቤቱ ሥልጣን አለው በማለት ክርክር አቅርቧል። ይህም በውለ መሰረት ለግልግል ጉባዔ ማቅረብ የሚችለውን መብቱን እንደተወ ይቆጠራል። ማንም ሰው በጥፊቱ ተጠቃሚ ላሆን አይችልም በማለት ተከራክሯል።
አመልካች ሆነ 1ኛ ተጠሪ በዚህ ችልት ባደረጉት ክርክር የግንባታ ውለ አስመልክቶ ያለመግባባት ካለ የሚፈታው በግልግል ጉባዔ ስለመሆኑ መስማማታቸውን ግራ ቀኙ ተማምነዋል። የዲኝነት ሥልጣን በመርሕ ደረጃ የሚወሰነው በሕግ ቢሆንም ተዋዋዮች በሕግ በተፈቀደው አግባብ አለመግባባት የሚታይበትን የዲኝነት አካል የመምረጥ መብት አላቸው። ሰዎች በመካከላቸዉ ከፈጠሩት ሕጋዊ ተግባራት በመነጨ ወይም ከዚህ ጋር በተያያዘ ለወደፉት በመካከላቸዉ የሚፈጠረዉን አለመግባባት ወይም ተፈጥሮ ያለዉን አለመግባባት ከመደበኛ ፍርድ ቤት ዉጭ በግልግል ዲኝነት በኩል ለመፍታት የመዋዋል ነጻነታቸዉን በመጠቀም መስማማት እንደሚችለ የፍ/ሕ/ቁ. 3328 እና የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
315(1) ያስረዲለ። የግልግል ዲኝነት ሥምምነት በጽሁፍ በተዋዋለት በዋናዉ ዉላቸዉ በሚያደርጉት የግልግል ዲኝነት ስምምነት ቃል (Arbitration Clause) ወይም አስቀድሞ በመካከላቸዉ ተከስቶ ያለዉን አለመግባባት በግልግል ዲኝነት ለመፍታት ራሱን በቻለ የጽሁፍ የግልግል ዲኝነት ስምምነት (Arbitral Submission) ሉመለከት ይቻላል።
ተዋዋዮች በውል አለመግባባቱ የሚታይበትን ሥርዓት ከወሰኑ ውል በፍ/ሕ/ቁ. 1731(1) እንደተመለከተው በተዋዋዮች መካከል እንደ ሕግ አስገዲጅ በመሆኑ በወሰኑት የዲኝነት አካል የመዲኘት ግዳታ ይጥልባቸዋል። በግልግል ዲኝነት ላታይ የሚገባው ክስ ፍርድ ቤት ከቀረበ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለላው ስለመሆኑ ውላቸውን መሰረት በማድረግ ተከራካሪዎች ወይም ፍርድ ቤቱም በግልግል እንዱታይ ሥምምነት መኖሩን ካወቀ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 9(2) መሰረት በማናቸውም የክርክሩ ደረጃ ሉያነሳው ይችላል። ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የማይኖረው በሕግ መሰረት ይሁን በተዋዋዮች የግልግል ዲኝነት ጉባዔን መምረጥ ውጤቱ ተመሳሳይ ነው። ተዋዋዮች በግልግል ዲኝነት ጉባዔ ላታይ የሚገባን ጉዲይ ፍርድ ቤት ካቀረቡ በኋላ መልሰው ጉዲዩን ለግልግል ጉባዔ ማቅረብ የማይችለት በሁለትዮሽ የኢንቨስትመንት ሥምምነቶች (Bilateral Investment Treaties) ሁለት አማራጮች የያዙ ድንጋጌዎች (fork in the road provisions) ሲኖሩ ነው። መርሐ ተዋዋዮች አለመግባባትን በዓለም አቀፍ የግልግል ጉባዔ ሆነ በሀገሪቱ ፍርድ ቤት እንዱታይ ሥምምነት ሲያደርጉ እና በመጀመሪያ በፍርድ ቤት ከታየ ሥምምነታቸውን መሰረት አድርገው ለሁለተኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ የግልግል ጉባዔ እንዱታይ ክስ ከማቅረብ የሚከለክል ነው። ይሕም በሥምምነቱ ጉዲዩ በሀገሪቱ ፍርድ ቤት ሆነ በግልግል ጉባዔ እንዱታይ አማራጭ የሚሰጥ መሆኑን መሰረት ያደረገ ነው። በዚህ አግባብ አማራጭ ሥምምነት ከላለ ጉዲዮች ከፍርድ ቤት ውጭ እንዱታዩ ካስፈለገበት ዓላማ አንደ የፍርድ ሂደት ቅልጥፍና (efficiency) ለመጨመር በመሆኑ ተዋዋዮች ጉዲዩ በግልግል ጉባዔ እንዱታይ ከተስማሙ በኋላ ሉተው እንደሚችል መብት (waivable right) ተቆጥሮ ክሱን በፍርድ ቤት ካቀረቡት ለግልግል ጉባዔ የማቅረብ መብታቸውን እንደተውት የሚቆጠርና ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመመልከት ሥልጣን የሚሰጠው አይደለም። ሥለሆነም ጉዲያቸው በግልግል ዲኝነት ያደረጉትን የፅሐፍ ስምምነት በተመሣሣይ የፅሁፍ ምምነት አድርገው እስካላሻሻለት ድረስ የዲኝነት ሥልጣን በተከራካሪዎች የክርክር አቀራረብ ሆነ ክርክሩ በደረሰበት ደረጃ ምክንያት የሚወሰን አይደለም። በግንባታ ውል አለመግባባት ላይ ዲኝነት ለመስጠት ሥልጣን ያለው የግልግል ጉባዔ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካች የግንባታ ውል ማቋረጥ ተግባር ውድቅ ተደርጎ ውለን የሚፈጽምበት የችሮታ ጊዜ እንዱሰጠው የጠየቀውን ዲኝነት በሥረ-ነገሩ አከራክረው መወሰናቸው ሥልጣን ሳይኖራቸው የተሰጠና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ወደ ሁለተኛው ጭብጥ ስንመለስ አመልካች በሰበር አቤቱታው ለግልግል ጉባዔ የሚገቡንን ክፍያዎች በተመለከተ ክስ እስከምናቀርብ ድረስ ዋስትናዎች እንዲይከፈለ ታግድ እንዱቆይ ላደረግ ይገባል ያለ በመሆኑ ለክርክሩ አወሳሰን ዋናው ጭብጥ ክስ ባልቀረበበት ሁኔታ የእግድ ጥያቄ ላቀርብ ይችላልን?
ዋስትናዎቹ ያለቅድመ ሁኔታ የሚከፈለ መሆናቸው ሲታይ እግድ ላሰጥባቸው ይችላል ወይስ አይችልም? የሚለውን መመርመር ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ 1ኛ ተጠሪ የሚከራከረው የእግድ ጥያቄ የሚቀርበው ዋና ክርክር ወይም ክስ ኖሮ ክርክሩ በፍርድ ቤት እስኪወሰን ድረስ ለጊዜው የሚሰጥ ትዕዛዝ ነው። ዋና ክርክር በላለበት ገና ለገና ጉዲዩ በግልግል እስኪታይ ድረስ እግድ ይሰጥልኝ ብል ዲኝነት መጠየቅ በሕግ ያልተፈቀደ ነው በማለት ነው።
እግድ በሰው የንብረት መብት አጠቃቀም ላይ ገደብ የሚፈጥር ነው። በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40(1) ላይ ጥበቃ የተደረገለት ንብረት መብት ላይ ገደብ ለማድረግ ደግሞ በሕግ በግልጽ በተመለከተ፣ ውስን ጉዲይና አፈጻጸሙም መብቱን መልሶ የመውሰድ ያህል ውጤት በማይፈጥር ሁኔታ ውስጥ ብቻ ላሆን ይገባል የሚለው ስለሰብዓዊ መብት ጥበቃ የተደረጉ የሥምምነት ድንጋጌዎች ሆነ በሕገመንግሥቱ ውስጥ የተቀረጸ የሕግ መርሕ ነው። በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 151 መሰረት ከፍርድ በፉት ንብረት ተከብሮ እንዱቆይ (attachment) የሚደረግበትን ሥርዓትና ሁኔታ የሚመለከተው ሆነ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 154 መሰረት ነገሩ በፍርድ እስኪወሰን ወይም ላላ ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ ንብረቱ እንዲለ እንዱቆይ፣ ከመጥፊት እንዱድን ወይም እንዲይበላሽ፣ ለላላ ሰዉ ተላልፍ እንዲይሰጥ፣ ወደ ላላ ስፍራ እንዲይዛወር ወይም እንዲይባክን የእግድ ትዕዛዝ የተጠየቀው ለጥያቄው መሰረት የሆነው ክስ ቀርቦ ከሆነ እግድ መሰጠቱ የተከሳሹ ወገን የንብረት መበት አጠቃቀም ላይ የሚያስከትለውን ውጤት በመረዲት በጥንቃቄ መታየት ያለበት ነው።
የእግድ ትዕዛዝ በመርሕ ደረጃ የቀረበ ክስን መሰረት ያደረገ እና በሥነ-ሥርዓት ሕጉ አግባብ በተመለከቱት መስፈርቶች የሚሰጥ ነው። ዓላማው ደግሞ ክሱ ያለ ውጤት እንዲይቀርና ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜም የሚፈጸምበት ንብረት እንዱኖርና ዜጎች መብታቸውን ማስከበር የሚችለበትን ዕድል የሚፈጥርና በሂደቱም ፍርድ ቤቶች ላይ ያላቸውን እምነት የሚጨምር ነው። በመሆኑም ሰዎች ክስ ከማቅረባቸው በፉት ነገር ግን በክስ ዝግጅት ላይ እያለ ተከሳሽ የሚሆነው ወገን ጉዲዩን በመረዲት ክስ ሲቀርብ ክሱ ውጤት እንዲይኖረው በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 154(ለ) እንደተመለከተው ተግባሮችን እየፈጸመ ከሆነ፤ ተግባሩን አለመከላከል ሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተቀረጸበትን ዓላማ እንዲይሳካ ያደርገዋል። ነገር ግን እግደ እንዱሰጥ የተጠየቀው ክስ ሳይቀርብ ከሆነ ተከሳሽ የሚሆነው ወገን ላይ ያልተገባ የመብት ገደብ እንዲይደረግበት፤ ጊዜያዊ እግድ የሚጠይቀው ወገን ክስ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ እንዲለ፣ የክስ ዝግጅቱ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈለገበትን ምክንያት፣ ክሱ እስኪቀርብ ድረስ የእግድ ትዕዛዙ ባይሰጥ የሚያስከትለው ጉዲት ማሳየት ያለበት ሲሆን ፍርድ ቤቱም ክሱን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ ብቻ በጊዜ ገደብ የተገደበ የእግድ ትዕዛዝ ላሰጥ ይችላል።
አመልካች እንዱሰጥ የጠየቀው የዋስትና ክፍያ የእግድ ትዕዛዝን እንደተመለከትነው በግልግል ጉባዔ ክፍያ እንዱከፈለው የሚያቀርበው ክስ ካለ ለምን እስካሁን እንዲላቀረበ፣ ክስ ለማቅረብ እያደረገ ያለው ዝግጅትና የክስ ዝግጅቱ በዚህ ጊዜ ሂደት ሁለ ያልተጠናቀቀበትን ምክንያት ላይ ክርክር ያላቀረበና ያላስረዲ በመሆኑ የእግድ ትዕዛዝ እንዱሰጥ ያቀረበው ጥያቄ የሕጉን መስፈርት ያላሟላ ስለሆነ አልተቀበልነውም። በልላ በኩል አመልካች የእግድ ትእዛዝ እንዱሰጠው የሚጠይቀው ያለቅድመ ሁኔታ የሚከፈል የዋስትና ክፍያን (irrevocable and unconditional bank bond guarantee) ነው።
የገንዘብ ግዳታ/ዋስትና ሰነድ የፊይናንስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 648/2001 አንቀጽ 2(20) ጨምሮ በተለያዩ ሕጎች የፊይናንስ ቃል ኪዲን ወይም የፊይናንስ ግዳታን ለመፈጸም የሚሰጥ ወይም የሚያዝ ማንኛውም ሰነድ ሲሆን የግምጃ ቤት ሰነድን፣ የተስፊ ሰነድን እና ቦንድን ይጨምራል ተብል ትርጉም ተሰጥቶታል። ዋስትናው የተሰጠው ያለቅድመ ሁኔታ በመሆኑ የሚፈጸመውም በውለ አግባብ ያለ ማናቸውም ቅድመ ሁኔታ መሆን ይገባዋል። ያለቅድመ ሁኔታ የሚከፈለን ዋስትና ክስ ስለሚቀርብ የሚታገድ ከሆነ የውለን ባሕሪ የሚቀይረው ስለሚሆን ሕጉ ሆነ ተዋዋዮች ያሰቡትን ዓላማ ማሳካት አይችልም። ሥለሆነም ያለቅድመ ሁኔታ ለመክፈል በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የተገባውን የዋስትና ግዳታ ውል 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲይከፍል እንዱታገድለት ያቀረበው ጥያቄ ሕጋዊ ባለመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለናል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ/ም እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሕዲር 16 ቀን 2012 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች የግንባታ ውል ማቋረጥ ተግባር ውድቅ ተደርጎ ውለን የሚፈጽምበት የችሮታ ጊዜ እንዱሰጠው የጠየቀውን ዲኝነት በሥረ-ነገሩ መወሰኑ ሥልጣን ሳይኖራቸው የተሰጠ በመሆኑ ተሽሯል።
የዋስትና ክፍያ ሉታገድ አይገባም ተብል የተሰጠው ውሳኔ በውጤት ደረጃ ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
የካቲት 20 እና ሚያዚያ 08 ቀን 2012 ዓ/ም የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.