በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.74 (2) ድንጋጌ መሰረት ‛በቂ ሆኖ የሚገመት እክል“ ምን እንደሆነ የተመለከተ ባይሆንም በቀጠሮ ለመቅረት ምን ምክንያት እንደሆነ አጠቃላይ ሁኔታዉን መመርመር የሚያስፈልግ ሆኖ፣ አመልካች በራሱ ጉድለት ወይም ቸልተኛነት ቀጠሮዉን ሳይከታተል ቀርቶ ካልሆነ በቀር፣ ፍትሕ የማግኘትና የመከራከር መብት ከግምት በማስገባት አመልካች የገጠመዉ እክል እንደ በቂ ምክንያት በመዉሰድ ለተጠሪ ተገቢ ኪሳራና ወጪ በማስከፈል፣ የተዘጋዉ መዝገብ ተከፍቶ ክርክሩ እንዱሰማ መድረጉ አግባብ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.32 (2) እና 74 (1)
No summary available.
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡-
ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር የተጀመረዉ በትግራይ ክልል የሒየልም ቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር።
ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.102019 በ21/9/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከቱ ነዉ።
የአሁን ተጠሪ በሥር ቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ከአሁን አመልካች ጋር የነበራቸዉ ጋብቻ እንዱፈርስ፣ በጋራ ያፈራናቸዉ ንብረቶች እንድንካፈል በማለት ዘርዝሮ አቅርቧል። የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ የአሁን ተጠሪ አሻሽለዉ ያቀረቡት ክስ የክስ ማሻሻል ዓላማን የሚቃረን ስለሆነ ዉድቅ እንዱደረግልኝ፣ ከተጠሪ ጋር ጋብቻ የፈጸምን በ1992 ዓ.ም ሳይሆን በ1997 ዓ.ም ነዉ፣ የአሁን ተጠሪ ያልደከሙበትና ያልጣሩበት ሃብት ለመዉሰድ በማሰብ እዉነታ የላለዉ ክስ ስለሆነ ዉድቅ እንዱደረግልኝ በማለት ዝርዝር ክርክር አቅርበዋል።
የሒየልም ቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት፣ የሰዉ ምስክሮች በመስማት፣ የሰነድ ማስረጃ በመመርመር የግራ ቀኙ ጋብቻ ከ11/6/2009 ዓ.ም ጀምሮ እንዱፈርስ፣ የጋራ ንብረቶች ናቸዉ ያላቸዉን እንዱካፈለ እና የልጆች ቀለብ ወስኗል። የአሁን ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ ይግባኝ ለትግራይ ክልል የሒወልቲ ወረዲ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በማከራከር ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ ሰጥቷል። የአሁን ተጠሪ አሁንም በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ ይግባኝ ለመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ ሰጥቷል።
የአሁን አመልካች በበኩላቸዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበዉ አመልካች በ27/7/2011 ዓ.ም በዋለዉ ቀጠሮ መቅረብ ባለመቻለ
ስለነበረኝ ነዉ የሚል ምክንያት ያቀረቡ ሲሆን፣ የአሁን ተጠሪ በበኩላቸዉ ባቀረቡት ክርክር የአመልካች ጠበቃ ያቀረቡት ምክንያት በቂ ስላልሆነ መዝገቡ ሉንቀሳቀስ አይገባም በማለት ተከራከሯል። ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር የአመልካች ጠበቃ በቀጠሮ ቀርቶ መዝገቡ ሉዘጋ የቻለዉ በልላ ፍ/ቤት ቀጠሮ ነበረኝ የሚል እንጂ ላላ በቂ ምክንያት ስላላቀረቡ እና ይህ ምክንያት ደግሞ በቂ ሆኖ ስላላገኘነዉ የተዘጋዉ መዝገብ ሉከፈት አይገባዉም በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች ሐምል 29 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ የሥር የክልል ሰበር ሰሚ ችልት በያዘዉ ቀጠሮ በችልቱ ብቻ ሳይሆን አራት የተለያዩ መዝገቦች የነበሩ መሆኑ እየታወቀ መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም የአመልካች ጠበቃ በልላ ፍ/ቤት ቀጠሮ ነበረኝ እንጂ ላላ በቂ ምክንያት አላቀረቡም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። ምክንያቱም የሥር የሰበር ሰሚ ችልት ላላ ቀጠሮ መኖሩን ተቀብል እያለ ይህን ነባራዊ ሁኔታ፣ ከመከራከር መብትና የሕጉን ዓላማ አንጻር ከግንዛቤ ሳይገባ በቂ ምክንያት አልቀረበም በሚል መዝገቡን በመዝጋት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልኝ፣ መዝገቡ ተከፍቶ ክርክሩን ሰምቶ ዉሳኔ እንዱሰጥልኝ በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣አመልካች መዝገቡ በተዘጋበት ቀን ከላላ ቦታ ሁለት መዝገብ ቀጠሮ ያለዉ መሆኑን ገለጾ እያለ ያከራከረዉ ምክንያት በቂ አይደለም የተባለበትን አግባብ ለማጣራት ሲባል ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፣ በ24/4/2012 ዓ.ም በሰጡት መልስ ከአመልካች ጋር በፍ/ቤት በ27/7/2011 ዓ.ም በነበረን ቀጠሮ አመልካች ራሳቸዉ የቀረቡ ሲሆኑ ጠበቃቸዉ ግን በቀኑ በነበረን ሶስት ቀጠሮዎች አልነበሩም፣ ስለዚህ የሥር የክልል ሰበር ሰሚ ችልት በዚህ ጉዲይ የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ እንዱጸናልኝ በማለት ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በነበረዉ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር አመልካች የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታ ለክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበዉ ችልቱ ግራ ቀኙን ለመስማት በቀጠረዉ ቀነ ቀጠሮ የአመልካች ጠበቃ ከቀጠሮ በመቅረታቸዉ መዝገቡ የተዘጋ መሆኑን የግራ ቀኙ ክርክርና የችልቱ የትዕዛዝ ግልባጭ ያሳያል። የአሁን ተጠሪ ካቀረቡት ክርክር መረዲት እንሚቻለዉ በተባለዉ ቀጠሮ አመልካች ራሳቸዉ እንደቀረቡና የአመልካች ጠበቃ በቀኑ በነበራቸዉ ሶስት ቀጠሮዎች ያልነበሩ መሆናቸዉን ገልጸዋል። የሥር የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰጠዉ ትዕዛዝ እንዲረጋገጠዉ አመልካች ጠበቃ በተያዘዉ ቀነ ቀጠሮ በልላ ፍ/ቤት ቀጠሮ ነበረኝ በማለት የተጠቀሰዉን ፍሬ ነገር ከተቀበለ በኋላ ይህ በቂ ምክንያት ላሆን አይችልም፤ አመልካች በቀጠሮዉ የቀሩበትን ላላ በቂ ምክንያት አላቀረቡም በማለት ዉድቅ አድርጓል። ከክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ትዕዛዝ መረዲት እንደሚቻለዉ በልላ ፍ/ቤት ቀጠሮ መኖሩ በቂ ምክንያት ላሆን እንደማይችል ነዉ።
እንደሚታወቀዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.73 መሰረት በአንድ ነገር ክስ ያቀረበ ሰዉ ክርክሩ እንዱሰማ በተወሰነ ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነና ተከሳሹ ቀርቦ የተከሰሰበትን ነገር በሙለ ወይም በከፍል ያመነ እንደሆነ ከሳሹ በላለበትም ቢሆን ፍ/ቤቱ ተከሳሹ በሙለ ወይም በከፉል ላመነዉ ጉዲይ የፍርድ ዉሳኔ ለመስጠት ይችላል። ከሳሹ የካደ እንደሆነ ግን መዝገቡን በመዝጋት ያሰናብተዋል በማለት ይደነግጋል። ይህ ድንጋጌ ደግሞ ለይግባኝ ጉዲይም ተፈጻሚነት እንዲለዉ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.32 [2] እና 74 [1] ድንጋጌ ይዘት መረዲት ይቻላል። በዚህ ረገድ ለሰበር ጉዲይ የተለየ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌ እስከላለ ድረስ ይህ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌ ተፈጻሚነት ይኖረዋል ማለት ነዉ።
በዚህ መሰረት ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ የሕግ ድንጋጌ መሰረት ከሳሽ ክርክር በሚሰማበት ቀነ ቀጠሮ በመቅረቱ መዝገቡ የተዘጋ እንደሆነ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.74 [1] መሰረት መዝገቡ በተዘጋ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ እንደገና ተከፍቶ ነገሩ እንዱታይለት መጠየቅ እንደሚችል እና ከሳሹ በቀዲሚዉ ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረዉ በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት መሆኑን ፍ/ቤቱ የተረዲዉ እንደሆነ ስለ ኪሳራዉና ስለ ወጪዉ አከፊፈል ተስማሚ መስል የታየዉን ዉሳኔ ከሰጠ በኋላ የተዘጋዉ መዝገብ ተከፍቶ ነገሩ እንደገና እንዱቀጥል ትዕዛዝ መስጠትና የሚሰማበትን ቀጠሮ መወሰን እንደሚችል ተመልክቷል። ነገር ግን በዚህ ድንጋጌ ‛በቂ ሆኖ የሚገመት እክል“ ምን እንደሆነ የሚጠቁም ነገር የለዉም።
በዚህ አግባብ አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ለመስማት በያዘዉ ቀነ ቀጠሮ ከችልት ለመቅረት የቻለዉ የአመልካች ጠበቃ በቀጠሮዉ ቀን በልላ ፍ/ቤት ቀጠሮ ስለነበረዉ መሆኑን የችልቱ የትዕዛዝ ግልባጭ ያሳያል። የሥር የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የአመልካች ጠበቃ በቀነ ቀጠሮዉ በልላ ፍ/ቤት ቀጠሮ የነበረዉ መሆኑን አረጋግጦ ከተቀበለ በኋላ፣ ነገር ግን ይህ ምክንያት በቂ ሆኖ የሚገመት እክል አይደለም የሚል ድምዲሜ ላይ በመድረስ የተዘጋዉ መዝገብ መከፈት የለበትም ማለቱን መረዲት ተችሎል። ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.74 [2] ደንጋጌ መሰረት ‛በቂ ሆኖ የሚገመት እክል“ ምን እንደሆነ የተመለከተ ባይሆንም አመልካች ቀጠሮ ለመቅረት የቻለዉ በምን ምክንያት እንደሆነ አጠቃላይ ሁኔታዉን መመርመር የሚያስፈልግ ሆኖ፣ አመልካች በራሱ ጉድለት ወይም ቸልተኛነት ቀጠሮዉን ሳይከታተል ቀርቶ ካልሆነ በስተቀር፣ ፍትሕ የማግኘትና የመከራከር መብት ከግምት በማስገባት አመልካችን የገጠመዉ እክል እንደ በቂ ምክንያት በመዉሰድ ለተጠሪ ተገቢ ኪሳራና ወጪ በማስከፈል፣ የተዘጋዉ መዝገብ ተከፍቶ ክርክሩ እንዱሰማ መድረጉ አግባብ ነዉ። በመሆኑም አመልካች ክርክሩን በጠበቃ ለማካሄድ ወስኖ በሕጉ አግባብ ተገቢዉን ዉክልና ሰጥቶ እያለ ጠበቃዉ ችልት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ ተገኝቶ አመልካችን ወክል ተገቢዉን ክርክር የማቅረብ ኃላፉነት ይኖርበታል። ነገር ግን ጠበቃ የተለያዩ ደንበኞች ሉኖሩት ስለሚችል ፍ/ቤት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ በተቻለ መጠን ለደንበኞቹ ተገቢዉን የጥብቅና አገልግልት መስጠት በሚያስችለዉ አግባብ አጀንዲዉን አስማምቶ ቀጠሮ እንዱያዝለት ለፍ/ቤቱ ማመልከት ይጠበቅበታል። ይህም ሆኖ ቀጠሮ ተደራርቦበት በአንድ ጊዜ በተለያዩ ችልቶች የሚቀርብበትን እድል በማዛባቱ ምክንያት የባለጉዲዩ መዝገብ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ የህጉ ድንጋጌ መሰረት ተዘግቶ እንደሆነ፣ አጠቃላይ የነገሩን ሁኔታ በመመርመር፣ የአመልካች የመከራከርና ፍትሕ የማግኘት መብት ታሳቢ በማድረግ መዝገቡ ተከፍቶ ክርክሩ እንዱሰማ ማድረጉ ተገቢ ነዉ።
ሲጠቃለል የአሁን አመልካች ራሱ በችልት መገኘት በተጠሪ የተነገረ ቢሆንም ጠበቃዉ በልላ ፍ/ቤት ቀጠሮ ስለነበረዉና ባለመቅረቡ መዝገቡ የተዘጋ መሆኑን በፍሬ ነገር ደረጃ የሥር የክልል ሰበር ሰሚ ችልት የተቀበለ እስከሆነ ድረስ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.74 [2] መሰረት መዝገቡ የተዘጋዉ ‛በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት መሆኑን“ የሚያስገነዝብ ሆኖ ሳለ፣ የሥር የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ይህ እክል በቂ ምክንያት አይደለም በማለት የተዘጋዉ መዝገብ ሉከፈት አይገባም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.102019 በ21/9/2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የተዘጋዉ መዝገብ ሉከፍት አይገባም በማለት የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 [1] መሰረት ተሽሯል።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በፍርድ ሐተታዉ በተመለከተዉ አግባብ የአመልካች ጠበቃ ችልቱ ክርክሩን ለመስማት በያዘዉ ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረዉ ‛በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት“ ስለሆነ የተዘጋዉ መዝገብ ተከፍቶ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.341 [1] መሰረት ተመልሶለታል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ ብለናል።
የአሁን አመልካች በዚህ ምክንያት በተጠሪ ላይ ለደረሰባቸዉ ወጪና ኪሳራ ብር 5000 [አምስት ሺህ] ለተጠሪ ሉከፍለ ይገባል ብለናል።
ይህ ችልት የካቲት 4 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
No topics extracted.