የግራ ቀኙን ክርክር ለማጣራት ተከራካሪዎች የሰው ማስረጃቸውን እንዱያቀርቡ ትዕዛዝ ቢሰጥም ከሳሾች ምስክሮችን ማግኘት ባለመቻላቸው ምትክ ምስክሮች ለማቅረብ እንዱፈቀድላቸው ያቀረቡትን አቤቱታ ፍ/ቤት ሳይቀበለው ቀርቶ ተከሳሾች ምስክሮቹን ማቅረብ እንደሚችለ አስተያየት በመስጠታቸው በነሱ በኩል መጥሪያ እንዱደርሳቸው ሲታዘዝ የሥነ ሥርዓት ጉድለት አለበት በማለት ትዕዛዙን ለሰጠው ፍርድ ቤት አቤቱታው ቀርቦ ውድቅ ከተደረገ ለክርክሩ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ሆኖ ከሥረ ነገር ፍርድ በፉት ይግባኝ የማይቀርብበት እነ አቶ መስፍን ጌታቸዉ (2 ሰዎች) እና እነ አቶ መለሰ ግርማ (3 ሰዎች) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.320 (1) እና (3)
No summary available.
ህዲር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡-
ይህ የዉርስ ሀብት ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካቾች የሥር ከሳሾች፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.239640 በ02/12/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ለማጣራት ግራ ቀኙ የሰው ማስረጃቸውን እንዱያቀርቡ ታዞ በቀጠሮው ቀን አመልካቾች 1ኛና 2ኛ ምስክሮቻችን ስልካቸውን እየዘጉና እየተደበቁ ፤ማግኘትም ስላልቻልን ላልች ምትክ ምስክሮች እንዱቀርቡላቸው የጠየቁ ሲሆን፤ ተጠሪዎች በበኩላቸው የአመልካቾች ምስክሮች ያለ በመሆኑ በሚኖሩበት ወረዲ በኩል ወይም እራሳቸው(ተጠሪዎች) ማቅረብ እንደሚችለ አስተያየት በመስጠታቸው፣ ፍ/ቤቱም በአሁን ተጠሪዎች በኩል መጥሪያ እንዱደርሳቸው በማዘዙ መጥሪያውን ለአመልካች ምስክሮች እንዱያደረሱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህን ተከትል አመልካቾች ባቀረቡት አቤቱታ የእኛን ምስክሮች የአሁን ተጠሪዎች እንዱያቀርቡ የታዘዘው ስነ ስርዓታዊ ባለመሆኑ የተሰጠው ትዕዛዝ እንዱሻርላቸው ቢጠይቁም ፍ/ቤቱ አቤቱታዉን በመመርመር በሰጠዉ ብይን የስነ ስርዓት ግድፈት የለበትም በማለት በመወሰኑ እና ይህም ስህተት እንዱታረምላቸው ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢቀርቡም ፍ/ቤቱ ይግባኙ አያስቀርብም በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ብይንና ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካቾች በ6/2/2012 ዓ.ም በተጻፈዉ የሰበር አቤቱታ፡ እነዚህ ምስክሮች በተጠሪዎች ተፅዕኖ ስር ያለ በመሆኑና ትክክለኛ ፍትህም ማስጠት የማይችለ በመሆኑ፤ በእኛ ላይ ጉዲት የሚያደርስ መሆኑ ሲረጋገጥ ትዕዛዙን በትዕዛዝ መበየን ሲችል፤የአመልካቾችን ምስክሮች መጥሪያ የሚያደርሰውና የሚያቀርበው አመልካቾች ሆነው ሳለ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.111 እንዱሁም ማስረጃችንን መለወጥ የሚከለከል አይደለም በማለት በሰበር መ/ቁ.45984 ተወስኖ እያለ ጥያቄያችን ውድቅ መደረጉ አግባብ አይደለም በማለት የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱሻርልን በማለት ጠይቀዋል።
ይህ ችልት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በዚህ መሰረት ተጠሪዎች ባቀረቡት መልስ የአመልካቾች አቤቱታ ጊዜያዊ ትዕዛዝ እንጂ የመጨረሻ ፍርድ አይደለም፤የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.111 እና የሰበር ቅፅ.9 የመ/ቁ.45984 ምስክሮች ያለመጥሪያ ከቀረቡ እና ፍ/ቤትም ምስክር ለመቀየር በቂ ምክንያት እያለ ካለፈ እንጂ እንደ አመልካቾች ያለን ምስክር ያለበቂ ምክንያትና በስር ፍ/ቤት ባልተነሳ ምክንያት ምስክር ለመቀየር የሚቀርብ ጥያቄን አይደለም በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀናላቸው ጠይቀዋል። የአሁን አመልካቾች የሰበር አቤቱታቸዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተጠቀሰዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በዚህ ጉዲይ ምላሽ ማግኘት ያለበት ፣በዚህ ጉዲይ የሥር ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ይግባኝ የሚባልበት ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ መሆኑን ተገንዝበናል። ከዚህ አንጻር የግራ ቀኙ ክርክር ሲታይ የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት አቤቱታ ሁለት የሰዉ ምስክሮቻችን ስልካቸዉን እየዘጉና እየተደበቁን ልናገኛቸዉ ስላልቻልን፣ በእነርሱ ምትክ ላልች ምስክሮች እንድናቀርብ እንዱፈቀድልን የሚል አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን፤ የአሁን ተጠሪዎች በዚህ ጉዲይ ላይ በሰጡት አስተያየት የአመልካቾች ምስክሮች እንዲለ በመግለጽ፣ አመልካቾች ያለበቂ ምክንያት ምስክሮችን ለመቀየር ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለዉም፤ ምስክሮቹ በወረዲዉ በኩል ወይም እኛ መጥሪያ እንያናደርስ እንዱታዘዝልን በማለት መጠየቃችንን ተከትል፤ የሥር ፍ/ቤት የተጠሪዎችን አስተያየት በመቀበል ተጠሪዎች ለምስክሮቹ መጥሪያ እንዱያደርሱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። የአሁን አመልካች ይህ ትዕዛዝ የሥነሥርዓት ጉድለት አለበት በማለት አቤቱታ ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ አቤቱታዉን ዉድቅ ማድረጉን የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል።
እንደሚታወቀዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.320 [1] መሰረት ሕግ በልላ አግባብ ካልደነገገ በስተቀር ከሳሽ ወይም ተከሳሽ በፍትሕ ብሕር ፍ/ቤት በተወሰነበት የመጨረሻ ፍርድ ላይ ይግባኝ ለማለት እንደሚችል ይደነግጋል። እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.320 [3] ሥር የተዘረዘሩት ጉዲዮች በተመለከተ ከሥረ ነገር ፍርድ በፉት ይግባኝ ማለት እንደማይቻልና ለክርክሩ የመጨረሻ የፍርድ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ እነዚህን ነገሮች የቅሬታ ምክንያቶች በማድረግ ከሥረ ነገር ይግባኝ ጋር ማቅረብ እንደሚቻል ያስገነዝባል።
በዚህ መሰረት አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የሥር ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ክሳቸዉ የጠቀሱአቸዉን ምስክሮች ቀይሮ በእነርሱ ፊንታ ላልች ምስክሮች ለማቅረብ በቂ ምክንያት የለም፤ ለምስክሮቹ በተጠሪዎች በኩል መጥሪያ ደርሷቸዉ እንዱቀርቡ በማለት ትዕዛዝ መስጠቱ፣ እና የአሁን አመልካቾች ይህ ትዕዛዝ የስነሥርዓት ጉድለት አለበትና እንዱታረምልን በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ ዉድቅ መደረጉ፣ ይግባኝ የሚባልበት ጉዲይ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ መታየት አለበት። ከፍ ሲል እንደተጠቀሰዉ ለክርክሩ የመጨረሻ የፍርድ ዉሳኔ ባልተሰጠበት ጉዲይ ላይ ይግባኝ ማቅረብ እንደማይቻል የተመለከተ ከመሆኑ አንጻር የሥር ፍ/ቤት አመልካቾች ምስክሮቻቸዉን ለመቀየርና በምትካቸዉ ላልች ምስክሮች ለማቅረብ ያቀረቡት ምክንያት በቂ አይደለም፤ ለምስክሮቹ የፍ/ቤቱ መጥሪያ በተጠሪዎች በኩል ይድረስ፤ ይህም ትዕዛዝ ደግሞ የሥነሥርዓት ጉድለት የለበትም በማለት የሰጠዉ ትዕዛዝ፤ በዚህ ጉዲይ የመጨረሻ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል ለማለት የሚያስችል አይደለም። ምክንያቱም የአመልካቾች ምስክሮች በተጠሪዎች ወይም በወረዲዉ አስተዲደር በኩል መጥሪያ ደርሷቸዉ፣ ምስክሮቹ ቀርበዉ በሕጉ አግባብ የሚያዉቁትን ጉዲይ መመስከር የሚችለበት እድል ሉኖር ስለሚችል ነዉ። ከዚህም በላይ ምስክሮቹ ቀርበዉ ቃላቸዉን ከሰጡ በኋላ እና በሥረ ነገሩ ጉዲይ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ፤ አመልካቾች የሥር ፍ/ቤት ምትክ ምስክሮች ለማቅረብ ያቀረብነዉን ጥያቄ በቂ ምክንያት የለዉም፣ ለምስክሮቹ የፍ/ቤቱ መጥሪያ በተጠሪዎች በኩል ይድረስ ማለቱ እና ይህም ትዕዛዝ የሥነሥርዓት ጉድለት የለዉም በማለት የሰጡት ብይን መብታችንን ጎድቶታል የሚለ ከሆነ፤
በሥረ ነገሩ ላይ በሚሰጠዉ የመጨረሻ ፍርድ ላይ ቅሬታ የሚያቀርቡ ከሆነ እነዚህን ምክንያቶችም ጨምሮ ቅሬታቸዉን ማቅረብ ይችላለ። ስለሆነም የአሁን አመልካቾች በዚህ ጉዲይ ላይ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠዉ ብይን ላይ የይግባኝ ቅሬታ የሚቀርብበት የመጨረሻ ፍርድ ባልሆነበት የይግባኝ ማመልከቻ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ማቅረባቸዉ እና ፍ/ቤቱም ይህ ጉዲይ በክርክሩ የመጨረሻ ፍርድ በፉት ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ፣ የቀረበዉን ይግባኝ በማየት የሰጠዉ ትዕዛዝ የህግ መሰረት የለዉም።
ሲጠቃለል የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዚህ ጉዲይ የሰጠዉ ብይን ላይ ይግባኝ የማይባልበት ሆኖ እያለ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካቾች ያቀረቡትን የይግባኝ ማመልከቻ ይግባኝ የሚባልበት ጉዲይ አይደለም በማለት ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ ይግባኙ አያስቀርብም በማለት የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.239640 በ02/12/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 [1] መሰረት ተሽሯል።
አመልካቾች ያቀረቡት ቅሬታ ከመሰረቱም ከሥረ ነገር ፍርድ በፉት ይግባኝ የሚባልበት ጉዲይ አይደለም ብለናል።
አመልካቾች በሥረ ነገሩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ይግባኝ የሚለ ከሆነ እነዚህን ምክንያቶች በሥረ ነገር ፍርድ ላይ ከሚያቀርቡት ቅሬታ ጋር ጨምሮ ከማቅረብ ይህ ዉሳኔ የሚከለክላቸዉ አይሆንም ብለናል።
በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ፤ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.