በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሥርዓት ህግ አንቀጽ 151 መሰረት የሚሰጥ የንብረት ማስከበር ትዕዛዝ ሉነሳ ስለሚችልበት አግባብ የሚደነግገዉ የህጉ አንቀጽ 153(3) ድንጋጌ ከፍርድ በፉት በተያዘ ወይም በተከበረ ንብረት ላይ መብት አለኝ የሚል ሦስተኛ ወገን መብት ያለዉ መሆኑ የሚመረመረዉ በፍርድ አፈፃፀም ላይ ያለዉ ንብረት የሶስተኛ ወገን መብት ያለበት መሆኑ በሚመረመርበት ዓይነትና ሁኔታ ስለሆነ መብቱን የሚያስከብረዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህግ አንቀጽ 158 ሳይሆን በአንቀጽ 418 እና ተከታዮቹ ላይ በተመለከተዉ አግባብ ወ/ሮ ጦይባ እንድሪስ እና ወ/ሮ መሰረት አበበ
No summary available.
ሚያዝያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- ወ/ሮ ጦይባ እንድሪስ ተጠሪ- ወ/ሮ መሰረት አበበ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርደ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ አንድ የፍትሐብሕር ጉዲይ በክርክር ሂደት ላይ እያለ የእግድ ትዕዛዝ የተሰጠበትን ተሽከርካሪ ከተከሳሽ በግዥ ይዤ ባለሀብት የሆንኩበት ነዉ በሚል ምክንያት የሚቀርብ የእግድ ይነሳልኝ አቤቱታ ተቀባይነት ሉያገኝ የሚችልበትን አግባብ የሚመለከት ነዉ።
የጉዲዩም አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዚህ ችልት የክርክሩ ተካፊይ ባልሆኑት ወ/ሮ ዲግማዊት ጌታቸዉ ላይ ያቀረቡት ክስ በሂደት ላይ እያለ የሰላዲ ቁጥሩ ኢት 03-91811 የሆነ ጣሉያን አይቪኮ ተሸከርካሪ ታግድ እንዱቆይ በፍርድ ቤቱ ታዟል።
ይህ በእንዱህ እንዲለ ተጠሪ በቀን 07/03/2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ ሰኔ 03 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ የውል ስምምነት እግድ የተሰጠበት ተሽከርካሪ የጋራ ባለሀብት ከሆኑት ከስር ተከሳሽ እና አቶ ሰለሞን ሰመረ ከተባለት ግለሰብ በብር 700,000.00 ገዝቼ ውለ በተደረገበት ቀን ብር 400,000.00 ከፍዬ ቀሪውንም ክፍያ በኋላ ላይ ከፍዬ ንብረቱን በእጄ አድርጌ እየተጠቀምኩበት በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የሰጠው የእግድ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 158 መሰረት እንዱነሳ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች በበኩላቸው በቀን 11/03/2013 ዓ.ም ጽፈው ለፍርድ ቤቱ በሰጡት አስተያየት ተሸከርካሪው የታገደው በአፈፃፀም ተይዞ እንጂ የክርክሩ መነሻ ባለመሆኑ አቤቱታው መቅረብ ያለበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 418 መሰረት እንጂ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 158 መሰረት መሆን አልነበረበትም፤ የቀረበው የሽያጭ ውልም በሰነድች ማረጋገጫ ጽ/ቤት ያልተመዘገበ ሲሆን ንብረቱን በእጅ ማድረግ ብቻውን በቂ አይደለም፤ የንብረት ባለቤትነት የሚረጋገጠው በተመዘገበ የሽያጭ ውል እና ስመ ንብረቱ ተሰርዞ በገዢ ስም ሲተላለፍ ብቻ በመሆኑ የቀረበው የእግድ ይነሳልኝ ጥያቄ ውድቅ ላደረግ ይገባዋል በማለት ተከራክረዋል።
አቤቱታዉ የቀረበለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በተጠሪ እና የተሸከርካሪው ባለንብረት በነበሩት ግለሰቦች መካከል የሽያጭ ውል ስለመኖሩ ባልተካደበት በአዋጅ ቁጥር 681/2002 መሰረት የስም ምዝገባ ባለመደረጉ ብቻ በሽያጭ ውል የተገኘውን የባለቤትነት መብት የሚያሳጣበት የህግ መሰረት የለም በማለት የሰጠውን የእግድ ትዕዛዝ አንስቶታል። በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኙት አመልካች ይግባኛቸውን ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ይግባኙ ተሰርዞባቸዋል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 13/05/2013 ዓ.ም በተፃፈ ስድስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈፅመዋል ያሎቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአቤቱታዉ ይዘትም በአጭሩ የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ተሸከርካሪው የእሳቸው ስለመሆኑ ያቀረቡት ማስረጃ ሳይኖር እግደ እንዱነሳ የሰጡት ውሳኔ የህግ እና የማስረጃ መሰረት የላለው በመሆኑ፤ በተጠሪ እና በተሸከርካሪው ባለንብረቶች መካከል የተደረገ የሽያጭ ውል የላለ እና በማስረጃነት የቀረበውም ሀሰተኛ በመሆኑ፤ ተጠሪ ታግድብኛል በማለት የሰላዲ ቁጥሩን የጠቀሱት ተሽከርካሪ እና እኔ ያሳገድኩት ተሽከርካሪ የሰላዲ ቁጥር የተለያየ በመሆኑ ባላሳገድኩት ተሸከርካሪ ላይ የእግድ አቤቱታ ይነሳልኝ በማለት አቤቱታ ላቀርብ አይገባም ሲል ያቀረብኩት ክርክር ያለበቂ ምክንያት መታለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የሽያጭ ውል ስለመኖሩ በሻጮች እና በተጠሪ አልተካደም በሚል ምክያት የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ እንዱነሳ የመወሰኑ አግባብነት ይህ ሰበር ችልት በመዝገብ ከሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም አንፃር መጣራት አለበት ተብል ስለታመነበት ለዚህ ሰበር ችልት ቀርቧል። በዚሁም መሰረት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ጥሪ ተደርጎላቸው በቀን 10/06/2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ ተሸከርካሪውን መግዛቴን የሚያሳይ የሽያጭ ውል ሰነድ ካቀረብኩ፣ ሻጮችም የሸጡ መሆናቸውን ካረጋገጡ፣ እንዱሁም የሽያጭ ገንዘቡን ለሻጮች ስለመክፈላ ያቀረብኩት ማስረጃ የተሸከርካሪው ባለቤት መሆኔን ለማረጋገጥ በቂ በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ብይን ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለዉ የአሁን አመልካች በስር ፍርድ ቤት ተከሳሽ በሆኑት ወ/ሮ ዲግማዊት ጌታቸዉ በተባለት ግለሰብ ላይ ያቀረቡት ክስ ከቼክ ጋር የተያያዘ ዕዲን የሚመለከት እንጂ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ተሽከርካሪ የሚመለከት አለመሆኑን እና ጉዲዩ በሂደት ላይ እያለ ተሽከርካሪዉ እንዱከበር የተደረገዉ ለፍርድ ማስፈጸሚያ እንዱዉል ታስቦ መሆኑን ነዉ። ይህም እግደ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 151 መሰረት የሚሰጥ ዓይነት ይዘት ያለዉ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ። በዚህ መልኩ የሚሰጥ የንብረት ማስከበር ትዕዛዝ ሉነሳ ስለሚችልበት አግባብ የሚደነግገዉ የህጉ አንቀጽ 153(3) ድንጋጌ ከፍርድ በፉት በተያዘ ወይም በተከበረ ንብረት ላይ መብት አለኝ የሚለዉ ሦስተኛ ወገን መብት ያለዉ መሆኑ የሚመረመረዉ በፍርድ አፈፃፀም ላይ ያለዉ ንብረት የሦስተኛ ወገን መብት ያለበት መሆኑ በሚመረመርበት ዓይነትና ሁኔታ መሆን እንዲለበት ያስገነዝባል። ይህም ማለት ክርክሩ ስለሚመለከተዉ ሳይሆን በልላ ክርክር ምክንያት ከፍርድ በፉት በሚሰጥ ትዕዛዝ በተከበረ ወይም በተያዘ ንብረት ላይ መብት አለኝ የሚል ሦስተኛ ወገን መብቱን የሚያስከብረዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 418 እና ተከታዮቹ ላይ በተመለከተዉ አግባብ መሆን አለበት ማለት ነዉ። የህጉ አንቀጽ 158 ድንጋጌ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ንብረት ወይም ለክርክሩ መነሻ ከሆነዉ ጉዲይ ጋር ተያያዥነት ያለዉ ንብረት ከፍርድ በፉት በአንቀጽ 154 እና 155 መሰረት የታገደ ሲሆን ተፈፃሚ የሚሆን ድንጋጌ እንጂ ለተያዘዉ ጉዲይ ዓይነት ማለትም በልላ ክርክር ምክንያት ከፍርድ በፉት ስለተከበረ ንብረት የሚመለከት ባለመሆኑ ለተያዘዉ ጉዲይ ተፈፃሚነት የለዉም። ስለሆነም ጉዲዩን ከዚህ አንፃር ማየት ሲገባዉ የስር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንብረቱ የተከበረዉ ከፍርድ በፉት እንጂ በአፈፃጸም ምክንያት አይደለም በሚል ምክንያት አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበዉን ክርክር ዉድቅ በማድረግ በህጉ አንቀጽ 158 መሰረት መቅረቡ በአግባቡ ነዉ በማለት የደረሰበት ድምዲሜ መታረም ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
ወደ ዋናዉ የክርክር ነጥብ ስንመለስ፣ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ፣ ተጠሪ ላቀረቡት የእግድ ይነሳልኝ ጥያቄ መሰረት ያደረጉት ተሽከርካሪዉን ገዝተዉ ተረክበዉ እየተጠቀሙበት የሚገኙ መሆኑን ሲሆን፣ ይህም የተጠሪ አቤቱታ ተሽከርካሪዉ የግላ እንጂ የስር ተከሳሽ አይደለም የሚል ይዘት ያለዉ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ። አመልካች ማሳገዲቸዉን ሳይክደ እግደ ተጠሪ በአቤቱታዉ ላይ የጠቀሱትን ተሽከርካሪ አይመለከትም በማለት ነገር ግን የትኛዉን ተሽከርካሪ እንዲሳገደ ለይተዉ ሳይገልጹ በደፈናዉ የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት ያለዉ አይደለም። ይልቁንም እግድ የተሰጠበት ተሽከርካሪ ተጠሪ በአቤቱታቸዉ የጠቀሱት ስለመሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ እልባት ለመስጠት መያዝ የሚገባዉ ጭብጥ ተጠሪ በተሽከርካሪዉ ላይ መብት ያላቸዉ መሆኑን የሚያሳይ በህግ አግባብነት ያለዉን ማስረጃ ያቀረቡ መሆን አለመሆኑ ነዉ።
በዚህም መሰረት ተጠሪ ለመቃወም አቤቱታቸዉ ምክንያት የሆነዉን ተሽከርካሪ ከስር ተከሳሽ እና ከባለቤታቸዉ መግዛታቸዉንና ተሽከርካሪዉን ተረክበዉ እየተጠቀሙበት የሚገኙ መሆኑን እንጂ የተሽከርካሪዉ ስመ ሀብት በስማቸዉ የተዛወረ ስለመሆኑ ያቀረቡት ክርክር የለም። አንድን ንብረት አስመልክቶ የሚደረግ የሽያጭ ዉል የንብረቱን ባለቤትነት ወደ ገዥዉ ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል ነዉ (የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2266 ይመለከቷል)። ይሁንና ንብረትን በዉል የገዛ ሰዉ የንብረቱ ባለቤት ላሆን የሚችለዉ እና የንብረት ባለቤትነት መብት በሚሰጠዉ መብት ተጠቃሚ ላሆን የሚችለዉ ንብረቱ በዉለ መሰረት የተፈጸመ ሲሆን ማለትም የንብረት ባለቤትነት መብቱ በህግ አግባብ የተላለፈለት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል። ስለ ዉል መፈጸም በሚል ርዕስ በፍትሐ ብሓር ህጉ አንቀጽ 2273 እና ተከታዮቹ ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎችም ይህንኑ የሚያስገነዝቡ ናቸዉ። ይህም ማለት አንድን ንብረት መግዛት ብቻዉን በንብረቱ ላይ የባለቤትነት መብትን አያጎናጽፍም፤ የባለቤትነት መብት የሚተላለፈዉ ወይም ገዥዉ በገዛዉ ንብረት ላይ ባለመብት የሚሆነዉ ንብረቱን በዉለ መሰረት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በእጁ ሲያደርግ ነዉ።
ስለሆነም በዉል የገዛሁት ንብረት የባለቤትነት መብቱ ከሻጭ ወደ እኔ ተላልፍልኛል የሚል ክርክር የሚያቀርብ ገዥ በእርግጥም በህግ አግባብ ይህ መብቱ የተላለፈለት መሆኑን የማስረዲት ኃላፉነት ይኖርበታል። በመሆኑም በተያዘዉ ጉዲይ ተጠሪ የሚከራከሩት በሽያጭ ዉለ መሰረት ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ ተሽከርካሪ ላይ የባለቤትነት መብት አግኝቻለሁ በማለት በመሆኑ ተሽከርካሪዉ በህግ አግባብ ከሻጮች የተላለፈላቸዉ መሆኑን የማስረዲት ግዳታ አለባቸዉ።
በዚህ አግባብ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ተሽከርካሪ ከሻጮች ወደ ተጠሪ የተላለፈ መሆን አለመሆኑን ወይም ተጠሪ በእርግጥም የተሽከርካሪዉ ባለቤት መሆን አለመሆናቸዉን በመወሰን ረገድ አንድ ንብረት ከሻጩ ወደ ገዥዉ በህግ አግባብ ተላልፎል የሚባለዉ መቼ ነዉ? የሚለዉን ጭብጥ መመርመር ያስፈልጋል። የፍትሐብሕር ህጉ የንብረት ባለቤትነት የሚተላለፍበትን ሁኔታ በአንቀጽ 1184 እና ተከታዮቹ ላይ ይደነግጋል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች ለተያዘዉ ጉዲይ አግባብነት ያለዉ በአንቀጽ 1186 ላይ የተመለከተዉ ሲሆን፣ ይህ አንቀጽ የሚንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት የሚተላለፍበትን ሁኔታ የሚደነግግ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን የሚመለከቱ ህጎች እንደተጠበቁ ሆነዉ፣ አንድ ሰዉ የሚንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ተላልፍለታል ማለት የሚቻለዉ ንብረቱን በእጁ ማድረጉ ሲረጋገጥ ነዉ። ይህም ማለት ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረት ባለቤትነት ከአንድ ወደ ላላ ሰዉ ተላልፎል ልባል የሚችልበት ሁኔታ በህግ በተለይ የተመለከተ እንደሆነ፣ ንብረቱ ተላልፎል ልባል የሚችለዉ ስለጉዲዩ በሚደነግገዉ ህግ በተመለከተዉ መሰረት መሆኑ ሲረጋገጥ መሆኑን ነዉ።
የተያዘዉ ጉዲይ ተሽከርካሪን የሚመለከት ነዉ። የተሽከርካሪ መለያ፣ መመርመሪያና መመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 681/2002 አንቀጽ 4 የተሽከርካሪ ባለንብረት የባለንብረት መታወቂያ (ሉብሬ) መያዝ ግዳታ መሆኑን ይደነግጋል። ስለሆነም ተሽከርካሪን አስመልክቶ በተደረገ ዉል የተሽከርካሪዉ ባለንብረትነት ከሻጩ ወደ ገዥዉ ተላልፎል ወይም ገዥ በዉለ መሰረት ተረክቧል ማለት የሚቻለዉ ከላይ በተጠቀሰዉ አዋጅ አንቀጽ 6 እና 7 ላይ በተዘረጋዉ ስርዓት መሰረት የመኪናዉ ባለቤት መሆኑ ተረጋግጦ የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በስሙ የተሰጠዉ መሆኑ ሲረጋገጥ ነዉ። አዋጁ ይህን ጥብቅ መስፈርት ሲያስቀምጥ የተለያዩ ምክንያቶችን ታሳቢ በማድረግ ሲሆን ከዚህም ዉስጥ አንደ አንድ ተሽከርካሪ ከአንደ ወደ ላላ የሚተላለፍበትን ጥብቅ የምዝገባ እና የባለቤትነት ማረጋገጫ መስፈርት በማስቀመጥ የሦስተኛ ወገኖችን መብትና ጥቅም ለማስከበር እንደሆነ ይታመናል። ስለሆነም ለተያዘዉ ክርክር መነሻ የሆነዉ ተሽከርካሪ በግዥ ዉል መሰረት ተላልፍልኛል በማለት ተጠሪ ክርክር ያቀረቡ ቢሆንም ባለሀብትነቱ ከላይ በተመለከተዉ አግባብ የተላለፈላቸዉ ስለመሆኑ ገልጸዉ አልተከራከሩም፤ ይልቁንም የተሽከርካሪዉ ስመ ሀብቱ በስር ተከሳሽ ወ/ሮ ዲግማዊት ጌታቸዉ ስም ያለ ስለመሆኑ ግራ ቀኝ የተማመኑበት ፍሬ ነገር መሆኑን ለመገንዘብ ተችሎል። ተጠሪ ላቀረቡት የመቃወም አቤቱታ ምክንያት ያደረጉት የተሽከርካሪዉ ባለሀብት እኔ እንጂ የስር ተከሳሽ አይደለም የሚል ከመሆኑ አንፃር የአመልካች የመቃወም አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 418 መሰረት ተቀባይነት ያለዉ መሆን አለመሆኑን አጣርቶ በመወሰን ረገድ መመርመር ያለበት ነጥብ፣ ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረዉ፣ በህግ አግባብ በተሽከርካሪዉ ላይ የባለቤትነት መብት ያገኙ መሆን አለመሆኑ እንጂ የግዥ ዉለን ህጋዊነት አለመሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል።
በአጠቃላይ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ተሽከርካሪ ገዝቼ ባለሀብት ሆኛለሁ በማለት የመቃወም አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም ይህ የመቃወም አቤቱታቸዉ ተሽከርካሪዉን በዉለ መሰረት ተረክበዉ እና ባለሀብትነትም በስማቸዉ መመዝገቡን በሚያሳይ ማስረጃ ባልተደገፈበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ክርክር ከዉለ ህጋዊነት አንፃር ብቻ በመመርመር የቀረበዉን የመቃወም አቤቱታ በመቀበል እግደ ሉነሳ ይገባል በማለት የደረሱበት ድምዲሜ የተሽከርካሪ ባለንብረትነት መብት ከአንደ ወደ ላላ ሉተላለፍ የሚችልበትን ሁኔታ አስመልክቶ ከፍ ሲል በዝርዝር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ያገናዘበ ባለመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህ ሁለ ምክንያት ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 18/03/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 06/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ተሽከርካሪ ተከብሮ እንዱቆይ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ የነበረዉ ትዕዛዝ ሉነሳ አይገባም ተብሎል።
የሰበር አጣሪ ችልት በቀን 14/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።