የፍትሐ ብሓር ክርክር ተከራካሪን የተከተለ (party doctrine) ሲሆን አቤቱታ የቀረበለት የዲኝነት ነክ አካልም ውሳኔው መመስረት ያለበት ተከራካሪውን አስመልክቶ የተጣሱ መብቶችን በማረም፣ አቶ ፀጋይ ተስፊይ እና የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ብረታ ብረት በመመርመርና አመልካች በጠየቀው መብት ልክ/ዲኝነት ላይ ስለመሆኑ ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት
No summary available.
ቀን፡- ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ፀጋይ ተስፊይ፡- ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ብረታ ብረት ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት-ነ/ፈጅ አድማስ ደምሳቸው ቀረቡ መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
ጉዲዩ የደረጃ ዕድገት ውድድርን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው።
የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች በተጠሪ መሥሪያ ቤት ሰራተኛ ሲሆኑ በመሥሪያ ቤቱ በወጣው የገበያ ልማት ቡድን መሪ የደረጃ ዕድገት ውድድር ላይ ያላቸው የሥራ ልምድ በቂ አይደለም ተብል ከውድድሩ ውጭ በመሆናቸው ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ያመለከቱ ሲሆን ኮሚቴው ለሥራ መደቡ ከሚያስፈልገው ስምንት ዓመት የሥራ ልምድ አመልካች ያላቸው ሰባት ዓመት ከአስራ ስድስት ቀን የሥራ ልምድ በመሆኑ ለሥራ መደቡ በቂ አይደለም በማለት ቅሬታቸውን ሳይቀበለው ቀርቷል። አመልካች በውሳኔው ባለመስማማት ለፋደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአስተዲደር ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን አስተዲደር ፍርድ ቤቱ የደረጃ እድገት ውድድሩ ለነባሩ የሥራ መደብ የተዘጋጀውን ፍርም ቁጥር 14 መከተል ሲገባው በነጥብ የሥራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን አፈጻጸም መመሪያ ለማስፈጸም በተዘጋጀው ፍርም-14 ሥራ መዘርዝር መሰረት የደረጃ ዕድገት ውድደሩ መደረጉ ተገቢ አይደለም። በነባሩ የሥራ መደብ የተዘጋጀው ፍርም ቁጥር 14 መሰረት ለገበያ ልማት ቡድን መሪ የሚጠይቀውን የትምህርት ዝግጅት አመልካች ስለማያሟለት በደረጃ ዕድገት ውድድሩ እንዲይሳተፈ መደረጉ ተገቢ ነው በማለት ወስኗል። አመልካች ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ የአስተዲደር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጽንቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም በሥር ከተከራከርንበት ጭብጥ እና ከቀረበው ማስረጃ ውጭ መወሰኑ ተገቢ አይደለም። ለሁለም የደረጃ ዕድገት ውድድር በነጥብ የሥራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን አፈጻጸም መመሪያ ለማስፈጸም በተዘጋጀው ፍርም-14 ሥራ መዘርዝር መሰረት ተደርጎ እያለ ለምንከራከርበት የሥራ መደብ ብቻ በነባሩ የሥራ መደብ የተዘጋጀው ፍርም ቁጥር 14 ተግባራዊ ይደረግ መባለ ስህተት ነው። ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በነጥብ የሥራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን አፈጻጸም መመሪያ ለማስፈጸም በተዘጋጀው ፍርም-14 ሥራ መዘርዝር መሰረት የተደረጉ የደረጃ ዕድገት ውድድሮችን ውጤት አጽድቋል። ለሥራ መደቡም ከስምንት ዓመት በላይ የሥራ ልምድ ስላለኝ ልወዲደር ይገባል የሚል ነው። የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ ለግራ ቀኙ ክርክር መነሻ የነበረው የአመልካች ቀጥታ አግባብነት ያለው የሥራ ልምድ ለደረጃ ዕድገቱ በቂ ነው ወይስ አይደለም የሚል ሆኖ ሳለ የሥር ፍርድ ቤቶች ግራ ቀኙ ባልተከራከሩበትና ዲኝነት ባልተጠየቀበት የትምህርት ዝግጅት ላይ መሰረት በማድረግ መወሰናቸው ሕጋዊነቱን ለመመርመር ለሰበር ችልት ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ አዟል። ተጠሪ የሰጠው መልስ የአመልካች የሥራ ልምድ ሰባት ዓመት ከአስራ ስድስት ቀን ብቻ ነው። የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔም ከጭብጡ ውጭ ሳይሆን የውድድሩን መሰረት ያደረገ ስለሆነ ውሳኔው ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብሎል። አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ክርክሩ የተደረገው የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ተከትል መሆን አለመሆኑን? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች በተጠሪ መሥሪያ ቤት ሰራተኛ ሲሆኑ በመሥሪያ ቤቱ በወጣው የገበያ ልማት ቡድን መሪ የደረጃ ዕድገት ውድድር ላይ ያላቸው የሥራ ልምድ በቂ አይደለም ተብል ከውድድሩ ውጭ በመሆናቸው ለፋደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአስተዲደር ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን አስተዲደር ፍርድ ቤቱ የደረጃ እድገት ውድድሩ ለነባሩ የሥራ መደብ የተዘጋጀውን ፍርም ቁጥር 14 መከተል ሲገባው በነጥብ የሥራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን አፈጻጸም መመሪያ ለማስፈጸም በተዘጋጀው ፍርም-14 ሥራ መዘርዝር መሰረት የደረጃ ዕድገት ውድደሩ መደረጉ ተገቢ አይደለም።
በነባሩ የሥራ መደብ የተዘጋጀው ፍርም ቁጥር 14 መሰረት ለገበያ ልማት ቡድን መሪ የሚጠይቀውን የትምህርት ዝግጅት አመልካች ስለማያሟለት በደረጃ ዕድገት ውድድሩ እንዲይሳተፈ መደረጉ ተገቢ ነው በማለት ወስኗል።
ተጠሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 182/2002 ተጠሪነቱ ለንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ሆኖ የተቋቋመ የፍደራል መሥሪያ ቤት ስለመሆኑ በደንቡ አንቀጽ 3 ላይ ተመልክቷል። ሰራተኞችንም በፋደራል የመንግሥት ሰራተኞች ሕጎች መሰረት የሚያስተዲድር ስለመሆኑ በደንቡ አንቀጽ 11(2)(ለ) ላይ ተደንግጓል። እንደ አስተዲደር መሥሪያ ቤት ከሚፈጽመው የሥራ ተግባር እና ከሚያስተዲድራቸው ሰራተኞች ጋር በተያያዘ አስተዲደራዊ ውሳኔ የመስጠት የራሱ ብቸኛ ሥልጣኑ ስለመሆኑ የኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 50(2) ላይ የተመለከተው የመንግሥት አካላትን የሥልጣን ክፍፍል መርህ (principle of separation of powers) ያሥገነዝባል። በሦስቱ የመንግሥት አካላት በሆኑት ሕግ አውጭው፣ ሕግ አስፈጻሚው እና የሕግ ተርጓሚው መካከል የሥልጣን ክፍፍል ያለ ቢሆንም በመካከላቸው የእርስ በእርስ ቁጥጥር (check and balance) ከላለ ተቋማቱ በሕግ የተጣለባቸውን የዜጎችን ሰብዓዊና ዱሞክራሲያዊ መብት ማክበርና ማስከበር አይችለም። የእርስ በእርስ ቁጥጥሩ ጣልቃ መግባትን ካስከተለ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዲቱ የሚያመዝንና የተጣለባቸውን ግዳታ እንዲይወጡ ሉያደርጋቸው ስለሚችል ቁጥጥሩ በሕግ በተዘረጋው ሥርዓት አግባብ መፈጸም አለበት።
አስተዲደራዊ አካላት የሚሰጧቸው ውሳኔዎች በፍ/ሕ/ቁ. 401(1) እንደተመለከተው ከተሰጣቸው ሥልጣን በማለፍ ከወሰኑ (ultra vires) ወይም በተሰጣቸው ሥልጣን ስር ሆኖ ነገር ግን በሕጉ የተመለከቱትን አስገዲጅ ሁኔታዎችና ፍርም ሳይከተለ የሚፈጽሙት ተግባር ወይም ውሳኔ ፈራሽ ነው።
በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37 ላይ ሰዎች ፍትሕ የማግኘት መብት ያላቸው በመሆኑ አስተዲደራዊ ውሳኔዎች የሰዎችን መብቶች ሲነኩ በዲኝነት አካል ጉዲዩ ቀርቦ ውሳኔያቸው ሕግን የተከተለ መሆን አለመሆኑ ይመረምራል። የመዲኘት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ቢሆንም የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 78(4) እና 37 ላይ አንድ ላይ ሲነበቡ በሕግ የተደነገገን የዲኝነት ሥርዓትን የሚከተል የዲኝነት ነክ አካላት በሕግ የመዲኘት ሥልጣን ሉሰጣቸው እንደሚችል ያስገነዝባል። የእነዚህ አካላት የዲኝነት ሥልጣን በተፈጥሮ የሚገኝ ሳይሆን በግልጽ ሕግ ለመዲኘት ሥልጣን ሲሰጣቸውና የሚሰሩበት የተደነገገ የዲኝነት ሥርዓት ሲኖራቸውና ይህን ተከትለው ሲሰሩ የሚኖራቸው ሥልጣን ነው። ይህም በዘመናዊው የመንግሥት ሥርዓት መንግሥት ብዙ ጉዲዮች ላይ ሰፉ ሥልጣን ያለው በመሆኑ ለመንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል የዲኝነት ነክ ሥልጣን አስፈላጊ በመሆኑ፣ የተወሰኑ ጉዲዮች ደግሞ ፍሬ ነገሮችን ለመመልከት ልዩ ዕውቀት የሚጠይቁ (specialization) በመሆኑ እና ፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን የሥራ ጫና ለማቃለል ሥራ ላይ ይውላለ።
የፍደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዲደር ፍርድ ቤትም በዚህ አግባብ የተቋቋመ የዲኝነት ነክ አካል ነው። ተጠሪ የሰጠው አመልካችን ከደረጃ ዕድገት ውድድር ውጭ የማድረግ አስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የሚቀርብበት ስለመሆኑ የፍደራል መንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 81 የተመለከተ በመሆኑ ጉዲዩ በአስተዲደር ፍርድ ቤት በይግባኝ ተጀምሮ መመራቱ ሕጉን የተከተለ ነው።
ነገር ግን ጠንካራና አስተማማኝ የዜጎች ሰብዓዊ መብት የሚከበርበት ዳሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የሕግ የበላይነትን ማስፈን ወሳኝ ነው። በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት መግቢያ ክፍል ላይ እንደተመለከተው የሕግ የበላይነት የሕገ-መንግሥቱ ዋነኛ መገለጫ ሲሆን አንደ መስፈርት ደግሞ የዲኝነት ሥልጣን በነፃና ገለልተኛ ፍርድ ቤት መታየቱ ነው። ሥለሆነም ከመደበኛ ፍርድ ቤት ውጭ በሕግ የመዲኘት ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት የሚወስኑት ውሳኔ በዲኝነት ክለሳ (judicial review) ሂደት በማለፍ በፍርድ ቤት መታየት ይኖርበታል። በተያዘው ጉዲይም አስተዲደር ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሳኔ በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በዲኝነት ክለሳ ሂደት ታይቶ ለዚህ ችልት የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
የሰበር አቤቱታው የተመሰረተው የሥር ክርክሩ አመልካች ያላቸው የሥራ ልምድ ለሥራ መደቡ በቂ ነው ወይስ አይደለም የሚል ሆኖ እያለ አስተዲደር ፍርድ ቤቱ የትምህርት ዝግጅት ላይ ተመስርቶ መወሰኑ ተገቢ የሆነ የዲኝነት አመራር ሂደት አይደለም በሚል ነው። የዲኝነት ነክ አካል ከመደበኛው ፍርድ ቤት ውጭ በአስፈጻሚው አካል ሥር የሚቋቋም በሕግ በግልጽ የተለዩ ውስን ጉዲዮችን የሚመለከት ዲኝነት ሰጭ አካል እንደመሆኑ መጠን መደበኛው ፍርድ ቤት የሚመራበት ሥርዓትን መከተል ሳይገባው በሚወጣለት ልዩ ሥነ-ሥርዓት ተከትል ውሳኔ ላሰጥ ይችላል። ነገር ግን ማንኛውም የዲኝነት አካል ሉከተለው የሚገባ የዲበረ የዲኝነት አሰጣጥ ዝቅተኛ መስፈርቶች አለ። ዋና ዋናዎቹም የቀረበለትን ጉዲይ ለመመልከት ሥልጣን ያለው መሆኑ፣ ጉዲዩን ያቀረበው ሰው አቤቱታውን ለማቅረብ መብት ያለው መሆኑ (standing right)፣ መብቱ የበሰለ ስለመሆኑ (ripeness)፣ የግራ ቀኙን ወገን የመደመጥ መብት (basic due process) ያከበረ መሆንና ውሳኔው የተመሰረተው በተጠየቀው ዲኝነት አግባብ መሆን ናቸው።
የፍትሐ ብሓር ክርክር ተከራካሪን የተከተለ (party doctrine) ሲሆን አስተዲደር ፍርድ ቤቱ የተመለከተውም አቤቱታ የቀረበለት በአመልካች በመሆኑ ውሳኔው መመስረት ያለበት አመልካችን አስመልክቶ የተጣሱ መብቶችን በመመርመርና አመልካች በጠየቀው ዲኝነት ላይ ነው። የአስተዲደር መሥሪያ ቤት በራሱ አነሳሽነት ሆነ አቤቱታ ሲቀርብለት በደረጃ ዕድገት ውድደሩ ላይ ጥሰት ካገኘ ማንኛውንም አስተዲደራዊ ጥሰት የማረም ሙለ ሥልጣን ያለው በመሆኑ ግድፈቱን ማረም ይችላል።
ጉዲዩ ለዲኝነት አካል ከቀረበ ግን የዲኝነት አካል የሚመራበት ሥርዓት ያለው በመሆኑ ማንኛውንም ስህተት የማረም ሥልጣን የለውም። ማረም የሚችለው አቤቱታውን ባቀረበው ሰው መብት ልክና በተጠየቀው ዲኝነት አግባብ ነው። የአመልካች ክርክር ለደረጃ ዕድገት ውድድሩ በቂ የሥራ ልምድ አለኝ የሚል ሆኖ እያለ ባልተጠየቀ ዲኝነት አስተዲደር ፍርድ ቤቱ ውድድሩ መሰረት ያደረግበትን ፍርምና የአመልካች የትምህርት ዝግጅትን መሰረት በማድረግ ውሳኔ መስጠቱም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ስህተቱን ሳያርም ውሳኔውን ማጽናቱ መሰረታዊ የሆነ የዲኝነት አሰጣጥ ሂደት ግድፈት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ/ም እና የፍደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዲደር ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 697/2011 ነሀሴ 16 ቀን 2011 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፍደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዲደር ፍርድ ቤት አመልካች በይግባኝ ማመልከቻቸው በጠየቁት ዲኝነት አግባብ ለሥራ መደቡ የደረጃ ዕድገት ውድድር ያላቸው የሥራ ልምድ በቂ መሆን አለመሆኑን አጣርቶ የመሰለውን እንዱወስን ጉዲዩን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት መልሰናል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። በውሳኔው መሰረት የፍደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዲደር ፍርድ ቤት እንዱፈፅም አዘናል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.