በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 394/1፣ ቁጥር 404 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በፍርድ አፈጻጸም መዝገብ ላይ ንብረት ለማስከበር በተሰጠ ትእዛዝ የፍርድ ባለእዲን የታክስ ከፊይ ንብረት ያስከበሩ የፍርድ ባለመብቶች ከላልች የቀደምትነት መብት አለኝ ብለው ለመጠየቅ እንደሚችለ የተደነገገ ባለመሆኑ ንብረቱ ከመከበሩ ወይም ከመያዙ በፉት በንብረቱ ላይ መብት የነበራቸዉና በክርክሩ ዉስጥ የላለ ሦስተኛ ወገኖች በሕግ፣በፍርድ ወይም በዉል ንብረቶቹ ላይ ያቋቋሙት የቀደምትነት መብት የማይነካ ስለመሆኑ የፍርድ ባለእዲን ታክስ ከፊይ ንብረት ካስከበረ የፍርድ ባለመብት ይልቅ በሕግ የቀደምትነት ጥበቃ መብት የተሰጠዉ ታክስ ሰብሳቢ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በታክስ ህግ መሰረት በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ ከፍርድ ባለመብቱ የቀደምትነት መብት ያለው በመሆኑ ከፍርድ ባለመብቱ ቀድሞ ንብረቶቹን ያስከበረ ስለመሆኑ ማስረጃ እንዱያቀርብ ሉጠየቅ የሚችልበት የሕግ አግባብ የላለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418
No summary available.
መስከረም 25 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ደረጀ አያና ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- የደቡብ ኦሞ ዞን ዲሰነች ወረዲ ገቢዎች ባለስልጣን፡- አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- 1.ፍራኦል ኢትዮጵያ የእርሻ ልማት ድርጅት፡- አልቀረቡም 2. የፋዳራል መንግስት ልማት ድርጅት ይዞታና አስተዲደር ኤጀንሲ፡- ነ/ፈጅ ምህረቱ መኮንን ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በሕግ የተሰጠ የቀደምትነት መብት አፈጻጸም የሚመለከት ሆኖ የፍርድ አፈጻጸም ክርክር በዉክልና በሚታይበት በደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት 1ኛ ተጠሪ ደግሞ የፍርድ ባለእዲ ሆነዉ በሚከራከሩበት መዝገብ ላይ አመልካች የመቃወም አመልካች በመሆን የተከራከረ ነዉ። ከክርክሩ እንደተረዲነዉ የደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍርደን እያስፈጸመ የሚገኘዉ 2ኛ ተጠሪ በ1ኛ ተጠሪ ላይ ያስፈረደዉን ፍርድ እንዱያስፈጽም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠዉ የዉክልና ሥልጣን መነሻ ነዉ። ይህ የተወከለዉ ፍርድ ቤት የፍርድ ባለእዲዉ ንብረት የሆኑትን የዕርሻ መሳሪያዎች ፣የዕርሻና ኮንስትራክሽን መሳሪያዎች፣ ተቀጽላ መሳሪያዎች፣ ሞተሮች፣ የዉሃ ፓምፖችና ጀኔሬተሮች፣ የወርክ ሾፕ መገልገያ መሣሪያዎች እና የተለያዩ አይነት መገልገያ መሳሪያዎች ተከብረዉ እንዱቆዩ ካደረገ በኋላ የመነሻ ዋጋቸዉ እንዱታወቅ አድርጎ በብር 25,284,862.69 መነሻ ዋጋ በሐራጅ እንዱሸጥ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ከላይ የተመለከተዉ ትእዛዝ ከመሰጠቱ በፉት የአሁን አመልካች ለፍርድ ቤቱ ባቀረበዉ አቤቱታ 1ኛ ተጠሪ ብር 10,393,364.75 የግብር እዲ ስላለበት እንዱከበሩ(እንዱታገደ) በተደረጉት በተጠቃሾቹ ንብረቶች ላይ በታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 እና በደቡብ ክልል የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 166/2009 አንቀጽ 39፣41፣እና 43 መሰረት 1ኛ ተጠሪ ባልከፈለዉ ዉዝፍ የግብር እዲ ልክ አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ የቀደመ መብት ስላለኝ በሕጉ መሰረት የቀደምትነት መብት ይጠበቅልኝ በማለት ጠይቋል።
ፍርደን እያስፈጸመ ያለዉ የደቡብ አሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ በመ/ ላይ በቀን 07/09/2011 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ የአሁን 2ኛ ተጠሪ(የፍርድ ባለመብት) የንብረት ዝርዝርና ግምታቸዉን አቅርቦ ንብረቶቹ በሐራጅ ተሽጠዉ ገንዘቡ እንዱከፈለዉ በጠየቀበት ሁኔታ የአሁን አመልካች 1ኛ ተጠሪ(የፍርድ ባለዕዲዉ) ላለበት የግብር እዲ እነዚህን ንብረቶች በመያዣያነት ማስከበሩን የሚያስረዲ ማስረጃ ከአቤቱታዉ ጋር አያዞ አላቀረበም።ስለሆነም መብቱን አስከብሮ ባልቀረበበት በ2ኛ ተጠሪ በኩል የቀረቡት ንብረቶች በጨረታ ሲሸጥ የቀደምትነት መብት ይሰጠኝ በማለት መጠየቁ ተገቢነት የለዉም። ነገር ግን ንብረቱ በሐራጅ ተሸጦ ከሚቀረዉ ቀሪ ገንዘብ ላይ ገንዘቡን ከፍርድ ባለእዲዉ ላይ መቀበል ይችላል በሚል 2ኛ ተጠሪ በጠየቀዉ መሰረት ንብረቶቹ በሐራጅ ተሸጠዉ በፍርደ መሰረት ለ2ኛ ተጠሪ እንዱከፈለዉ አዟል። አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ አቅርቦ ችልቱ በመ/ ላይ በቀን 18/11/2011 ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ትእዛዝ ይግባኙን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዟል።
አመልካች በቀን 10/02/2012 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ በዚህ አግባብ በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።የስር ፍርድ ቤት የሰጠዉ ትእዛዝ በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 39 ስር ያልተከፈለዉን የግብር እዲ አመልካች የግብር ባለእዲዉን ንብረት በማሸጥ ለማስከፈል የቀዲምነት መብት እንዲለዉ የተደነገገዉን የሚቃረን ነዉ። የአዋጁን ድንጋጌ አለአግባብ በመተርጎም የቀደምትነት መብት ተጠቃሚ ለመሆን የግብር ባለእዲዉ ንብረት በዋስትና መያዝና መያዣዉ መመዝገብ አለበት በማለት አመልካች ያቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418 እንደተደነገገዉ እና በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ ትርጉም መሰረት በፍርድ አፈጻጸም በታገደዉ ንብረት ላይ አመልካች ተቀዲሚ መብት አለኝ በሚል ያቀረበዉን አቤቱታ ተቀብል በመደበኛ የሙግት አመራር መሰረት ግራ ቀኙን ሳያከራክር ፣የአመልካችን የሰነድ ማስረጃዎች ሳይመረምር የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ አድርጎ አፈጻጸሙ እንዱቀጥል ማዘዙ ከስነ ስርዓት ሕጉ ዉጪ ነዉ።2ኛ ተጠሪ ያለዉ መብት በንብረቱ ወይም በሽያጭ ገንዘቡ ላይ የቀዲሚነት መብት ያለዉ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈልገዉን የግብር እዲ በቀዲሚነት ካስከፈለ በኋላ የሚተርፈዉን ገንዘብ መዉሰድ በመሆኑ አመልካች በተጠየቀዉ መሰረት በንብረቱ ላይ 2ኛ ተጠሪ ያሰጠዉ እግድ እንዱነሳ ማዘዝ ሲገባዉ የሥር ፍርድ ቤት ከአመልካች ዲኝነት ጥያቄ ዉጭ ንብረቱ በሐራጅ ከተሸጠ በኋላ ከ2ኛ ተጠሪ የሚተርፈዉን ገንዘብ መጠየቅ ይችላል በማለት መወሰኑ በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን አስገዲጅ ትርጉም እና የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418 ላይ የተደነገገዉን ያልተከተለ በመሆኑ ስህተት ነዉ።አመልካች ዲኝነት ባልጠየቀበት ንብረቱ በሐራጅ ሲሸጥ ንብረቱን አመልካች በቀደምነት የመግዛት መብት እንዱጠበቅለት እንደጠየቀ አድርጎ የሥር ፍርድ ቤት በትእዛዙ ላይ መግለጹም ስህተት ነዉ።1ኛ ተጠሪ የግብር እዲ ዉሳኔ ማስታወቂያ ደርሶት በተጠየቀ ጊዜ ካልከፈለ አመልካች የግብር እዲዉን ለማስከፈል በሕግ የሚጠበቅበት ተግባር የባለእዲዉን ንብረት አግድ በመሸጥ ግብር ያስከፍላል እንጂ ለፍርድ ቤት ጥያቄዉን አቅርቦ ንብረቱን እንዱያስከብር አይገደድም። በተጨማሪም ንብረቱን ይዞ መሸጥ የሚችለዉ ንብረቱ ላይ በፍርድ ቤት የተሰጠ እግድ ካለ እግደን ካስነሳ በኋላ በመሆኑና 1ኛ ተጠሪ የግብር እዲ የሚፈለግበት መሆኑን የሚያሳይ የግብር ማስታወቂያ ዉሳኔ 1ኛ ተጠሪ ለ2ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለእዲ ከመሆኑ በፉት አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ መስጠቱን ለስር ፍርድ ቤት ያቀረብነዉ ማስረጃ የሚያሳይ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታ ከሕግና ካቀረብነዉ ማስረጃ እንጻር ሳይመረምር የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ እያለ ስህተቱን ይግባኝ ሰሚዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አለማረሙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ ሲል አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ እንዱከፈለዉ ለሚጠይቀዉ የግብር እዲ ንብረቱን በመያዣነት ስላላስከበረም የቀዲሚነት መብት የለዉም የመባለን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 983/2008 እንቀጽ 39/1 ከደቡብ ክልል አዋጅ ቁጥር 166/2009 ጋር ተገናዝቦ እንዱመረመር ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትል ተጠሪዎች እንደቅደም ተከተላቸዉ በቀን 01/05/2012 ዓ/ም እና በቀን 30/04/2012 ዓ/ም የተጻፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱ በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
1ኛ ተጠሪ ባቀረበዉ መልስ 1ኛ ተጠሪ በዉጭ ባለሀብቶች የተቋቋመ፣የኢንቨስትመንት እና የንግድ ፈቃድ የተሰጠዉ ከፋዳራል መንግስት በመሆኑ አመልካች 1ኛ ተጠሪን ግብርና ታክስ የማስከፈል ሥልጣን የለዉም።አመልካች እየጠየቀ ያለዉ የመሬት መጠቀሚያ ግብርና የቴምብር ቀረጥ ያልተከፈለኝ አለ በሚል ቢሆንም መከፈል ያለበትን የቴምብር ቀረጥ የከፈልን ሲሆን የሉዝ ክፍያ የለም እንጂ የሉዝ ክፍያ አለ ቢባል እንኳን አመልካች በመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ ከመጠየቅ በስተቀር የቀደምትነት መብት አለኝ በሚል መጠየቅ የሚችልበት የሕግ መሰረት የለም።የመሬት የሉዝ ክፍያ ማስከፈል እንዱችል በሕግ ከላልች ባለመብቶች የቀደመ መብት ለአመልካች አልተሰጠዉም። የቀደምትነት መብት የሚኖረዉ የሉዝና የቴምብር ቀረጥ ለማስከፈል ሳይሆን ያልተከፈለ የንግድ ግብርና የግብርና ግብር ክፍያ ሲኖር ብቻ ሲሆን ከዚህ አንጻር እዲ እንደላለብን የፋዳራል ግብር አስከፊይ መስሪያ ቤት በጽሁፍ ስላሳወቀ አመልካች አለአግባብ የቀደምትነት መብት አለኝ በሚል ያቀረበዉን አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤት ዉድቅ ማድረጉ ተገቢ ስለሆነ የሰበር አቤቱታዉ ተቀባይነት ሉያገኝ አይገባም በማለት ተከራክሯል።
እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ ባቀረበዉ መልስ አመልካች የግብር ሰብሳቢ በመሆኑ ብቻ ያለምንም ገደብ የግብር ከፊይ ንብረት ላይ ቀዲሚ መብት አለኝ በማለት የሐራጅ ማስታወቂያዉ እንዱታገድና እግደ እንዱነሳ መጠየቅ አይችልም።በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 41(4/ለ) መሰረት በማንኛዉም የፍርድ ሂደት እገዲ በተደረገበት ወይም የአፈጻጸም ትእዛዝ በተሰጠበት ንብረት ላይ የመያዣ ዋስትና መስጠት እንደማይቻል ስለተደነገገ አመልካች በንብረቱ ላይ የቀደምትነት መብት አለኝ በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ የሕግ ድጋፍ የለዉም።በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 39 እና በደቡብ ክልል አዋጅ ቁጥር 166/2009 አንቀጽ 41 በተዘረጋዉ ስርዓት መሰረት ለግብር እዲዉ ንብረቱን በመያዣያነት መያዙን የሚገልጽ ማስረጃ በማቅረብ ሳያስረዲ እንዱሁም በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418/3 መሰረት በንብረቱ ላይ የቀደምትነት መብት እንዲለዉ የሚያሳይ የጽሁፍ ማስረጃ ሳያቀርብ በማንኛዉም ግብር ከፊይ ንብረት ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የቀደምትነት (absolute preemption right) አለኝ ሲል አቤቱታ ማቅረቡ የሕግ መሰረት ስለላለዉ የሥር ፍርድ ቤት አቤቱታዉን ዉድቅ ማድረጉ ተገቢ ነዉ።አመልካች ያቀረበዉ አቤቱታ በስነ ስርዓት ሕጉ መሰረት ሙግት ከተደረገ በኋላ ዉድቅ የተደረገ በመሆኑ ተገቢዉ ሙግት ሳይደረግ ዉድቅ እንደተደረገ በመቁጠር የሰ/መ/ ን በመጥቀስ ያቀረበዉ መከራከሪያም አግባብ አይደለም።በእዲ ምክንያት በፍርድ ቤት የተከበረ ንብረት እንዱሸጥ በተደረገ ጊዜ ንብረቱን ያስከበረዉ ወገን የሚኖረዉ መብት ከሽያጭ ገንዘብ ላይ የቀደምትነት መብት ካላቸዉ ባለገንዘቦች የሚተርፍ ካለ የመዉሰድ መብት ብቻ እንዲለዉ በሰ/መ/ ላይ አስገዲጅ ትርጉም ስለተሰጠና አመልካች በንብረቱ ላይ የቀደምትነት መብት እንዲለዉ በማስረጃ ስላላስረዲ አመልካች ያለዉ መብት እንደማንኛዉም መብት ጠያቂ ለ2ኛ ተጠሪ ተከፍል በሚቀረዉ ገንዘብ ላይ ብቻ ነዉ ተብል በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም።ማንኛዉም ታክስ ከፊይ ታክስ የመክፈል ግዳታዉን ያልተወጣ እንደሆነ ባለስልጣኑ እዲዉን በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ ማስፈጸም የሚፈልግ ከሆነ በዋስትናነት ማስመዝገብና ንብረቱን በማሸጥ ታክሱን እንደሚያስከፍል የሚገልጽ ማስታወቂያ ለታክስ ከፊዩ ይሰጣል ተብል ተደንግጓል እንጂ የግብር ዉሳኔ ማስታወቂያ እንደደረሰዉ የግብር ከፊይ ንብረት ይይዛል የሚል ሕግም ሆነ አሰራር ባለመኖሩ በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ትእዛዝ የተፈጸመ ስህተት የለም ተብል አቤቱታዉ ዉድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክሯል።
ከላይ በአጭሩ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በዚህ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና በስር ፍርድ ቤት የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም አመልካች የቀደምትነት መብት አለኝ በሚል የፍርድ አፈጻጸሙን በመቃወም አቤቱታ ያቀረበዉ 2ኛ ተጠሪ በ1ኛ ተጠሪ ላይ ያስፈረደዉን የገንዘብ ፍርድ ለማስፈጸም 2ኛ ተጠሪ ባስከበረዉ የ1ኛ ተጠሪ ንብረቶች ላይ በ1ኛ ተጠሪ የግብር እዲ ልክ የቀደምትነት መብት አለኝ በሚል እንደሆነ ክርክራቸዉ ያሳያል። 1ኛ ተጠሪ ደግሞ የግብር እዲ ስለላለብኝ የጠቀሳቸዉን ሕጎች መሰረት በማድረግ በንብረቶቹ ላይ የቀደምትነት መብት አለኝ ብል መጠየቅ አይችልም ብል ተከራክሯል።
እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ ደግሞ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈልገዉን እዲ ለማስከበር ንብረቱን ከ2ኛ ተጠሪ አስቀድሞ ያስከበረ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ባለማቅረቡ ይህንን ሳያደርግ ሕግ የቀደምትነት መብት አይሰጠዉም በሚል ተከራክሯል።
በመሰረቱ በፋዳራል ታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 39 እና በደቡብ ክልል የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 166/2009 ስር በተመሳሳይ እንደተደነገገዉ መሰረት ታክስ ሰብሳቢ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በታክስ ሕግ መሰረት ታክስ ከፊዩ መክፈል የሚገባዉ የመክፈያ ጊዜዉ የደረሰ ታክስ በሙለ ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ ባለሥልጣኑ በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ የቀደምትነት መብት አለዉ።በዚህ ድንጋጌ የታክስ ሕግ ተብል የተገለጸዉ በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 2(36) ላይ በተመለከተዉ ትርጓሜ መሰረት የታክስ አስተዲደር አዋጁን ጨምሮ የገቢ ግብር አዋጅ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ፣የሴክሳይዝ ታክስ አዋጅ፣የቴምብር ቀረጥ አዋጅ፣የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ፣የጉምሩክ ሕግ ሳይጨምር ማንኛዉም ታክስ፣ ቀረጥ ወይም ክፍያ የሚጥል ሕግና እነዚህን አዋጆች ለማስፈጸም የሚወጣ ደንብና መመሪያ እንደሆኑ በግልጽ ተመልክቷል።በመሆኑም ታክስ የመጣልና የመሰብሰብ የሥልጣን ክፍፍለን ተከትል የፋዳራል እና የክልል ታክስ ሰብሳቢ ባለሥልጣን የሚሰበስቡት የታክስና የቀረጥ ዓይነት እንዱሁም የእነዚሁ ምንጭ የሆኑ ሕጎች ሉለያዩ የሚችለ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በፋዳራለ ታክስ አስተዲደር አዋጅ አንቀጽ 39(በክልለ አዋጅም በተመሳሳይ እንደተደነገገዉ) መሰረት በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ የቀደምትነት መብት የሚኖረዉ በእነዚህ ሕጎች መሰረት ታክስ ከፊዩ መክፈል የሚገባዉን የመክፈያ ጊዜዉ የደረሰዉን ታክስ ቀረጥና ተያያዥ ክፍያ ለማስከፈል መሆኑ ሉረጋገጥ ይገባል።ይህም ቅቡልነት ያለዉ ዋና ግዳታ መኖሩን(valid principal obligation) መሰረት ያደረገ ነዉ።
ከላይ በተመለከተዉ መሰረት ታክስ ሰብሳቢ ባለስልጣን በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ የሚኖረዉን የቀደምትነት መብት አፈጻጸምና አድማስ ላልች ከታክስ ከፊዩ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች ከሚኖራቸዉ መብት ጋር በማነጻጸር መመርመር እና ያላቸዉን ልዩነት በግልጽ ማወቅ ያስፈልጋል።በዚህ መልኩ በታክስ ከፊይ ሀብት ላይ ታክስ ሰብሳቢዉ ባለስልጣን ያለዉ የቀደምትነት መብት በሕግ ጽንሰ ሐሳብ በእንግሉዝኛዉ Preferential/Preferred Creditor ተብል የሚታወቅ ሲሆን ጥቅል ሀሳቡም በአገራችን የታክስ አስተዲደርና በላልች የታክስ ሕጎች ላይ ጭምር እንደተንጸባረቀዉ በመርህ ደረጃ ገንዘብ ጠያቂ (በታክስ ጉዲይ ታክስ ሰብሳቢ ባለስልጣን) በባለእዲዉ(በታክስ ከፊዩ) ሀብት ላይ ከላልች ከባለዕዲዉ ገንዘብ ከሚጠይቁ ተራ ባለገንዘቦች(unsecured/ordinary creditor) ቅድሚያ እንዱከፈለዉ መብት የሚሰጠዉ ነዉ።እንዱህ አይነት የገንዘብ ጠያቂዎች የቀደምትነት መብት( Preferential/Preferred Creditor) ከባለእዲዉ ሀብት ላይ በቅድሚያ እዲ የማስከፈል መብት እንደመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1386ና ተከታዮቹ ፣በቁጥር 1410ና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ እንዱሁም በላልች የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተደንግጎ ከሚታወቀዉ ከሕግ ወይም ከዉል ከሚመነጨዉ አንድን ንብረት በቀደምትነት መግዛትን (Pre- emption) ከሚመለከተዉ የተለየ ነዉ።
እንዱሁም ከፍርድ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 394/1 እና ከቁጥር 404 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የፍርድ ባለእዲዉ የሆነዉን ታክስ ከፊይ ንብረት ያስከበሩ የፍርድ ባለመብቶች በሕግ የቀደምትነት መብት ከተሰጠዉ ታክስ ሰብሳቢ ባለሥልጣን ጋር የሚኖራቸዉ የመብት ቅደም ተከተል ምን እንደሆነ መመርመር ይገባል።በዚህ መልኩ የሚሰጠዉ ንብረት የማስከበር ትእዛዝ ዓላማዉ የፍርድ ባለዕዲዉ ዕዲዉን ከመክፈለ በፉት ይህንን ንብረት ለላላ ሰዉ እንዲይሰጥ፣እንዲይሸጥ፣እንዲይለዉጥ ወይም በማናቸዉም ላላ ሁኔታ መብቱን ለማንም እንዲያዛዉር ለማገድና የፍርድ ባለእዲዉ እዲዉን መክፈል ካልቻለ ንብረቱን በሐራጅ በማሸጥ በፍርደ መሰረት ለፍርድ ባለገንዘቡ ለመክፈል ቢሆንም በዚህ መልኩ የሚደረገዉ ንብረት ማስከበር በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 3044 መሰረት በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ በፍርድ ከሚቋቋመዉ የመያዣያ መብትን (Judicial mortgage right) የተለየ መሆኑን መገንዘብ ይገባል።ምክንያቱም በፍርድ የሚቋቋም መያዣ አስቀድሞ በፍርድ ቤት ወይም በግልግል ዲኝነት አካል አንደ ተከራካሪ ወገን ለላላዉ ተከራካሪ ወገን እንዱከፍል የተወሰነን የገንዘብ እዲ ለማስፈጸም ዲኝነት ተጠይቆ ተለይቶ በሚታወቅ ንብረት ላይ እዲ ለማስከፈል የሚቋቋም በመሆኑ በፍርድ አፈጻጸም መዝገብ ላይ ንብረት ለማስከበር ከሚሰጥ ትእዛዝ የተለየ በመሆኑ ነዉ።ስለሆነም በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት የፍርድ ባለእዲዉን ንብረት ያስከበረ ሰዉ የቀደምትነት መብት አለኝ ብል ለመጠየቅ እንደሚችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 404 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ አልተደነገገም።
በልላ በኩል በታክስ አስተዲደር አዋጅ አንቀጽ 39(2 እና 7) ላይ እንደተመለከተዉ በታክስ ሰብሳቢዉ ባለስልጣን ታክስ ከፊዩ እንዱከፍል የጠየቀዉ ታክስ ከተከፊይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የሚከፈል ታክስ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ፣የተርን ኦቨር ታክስ ወይም የኤክሳይስ ታክስ ካልሆነ በስተቀር ባንኮች በንብረቱ ላይ የዋስትና(የመያዣያ) መብት ያቋቋሙት ብድሩን ከመስጠታቸዉ በፉት ታክስ ከፊዩ የታክስ እዲ የላለበት መሆኑን ከታክስ ሰብሳቢ ባለስልጣን አረጋግጠዉ ከሆነ በታክስ ከፊዩ ንብረት ላይ የዋስትና(የመያዣያ) መብት ያቋቋሙ ገንዘብ ጠያቂ ባንኮች (secured creditor) እና ከታክስ ከፊዩ ደመወዝ የሚጠይቁ የታክስ ከፊዩ ተቀጣሪዎች ከታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ ከታክስ ሰብሳቢ ባለስልጣን የቀደመ መብት አላቸዉ።
እንዱሁም ታክስ ከፊዩ ታክስ የመክፈል ግዳታዉን ያልተወጣ እንደሆነ ታክስ ሰብሳቢ ባለስልጣን በሕግ የተሰጠዉን የቀደምትነት መብት በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ የሚጠቀም መሆኑን፣ ያልተከፈለዉን ታክስ እና ታክሱን ለማስከፈል የሚወስደዉ እርምጃ የሚያስከትለዉን ወጪ እንደሚያስከፍለዉና በንብረቱ ላይም የዋስትና መብት እንደሚያስመዘግብ የሚገልጽ ማስታወቂያ ለታክስ ከፊዩ መስጠት እንዲለበት በታክስ አስተዲደር አዋጅ አንቀጽ 39/3 ላይ በግልጽ ተደንግጓል።በተጨማሪም ታክስ ከፊዩ የታክስ ማስጠንቀቂያ በደረሰዉ በ30 ቀናት ዉስጥ ታክሱን አለመክፈለን ምክንያት በማድረግ ታክስ ሰብሳቢዉ ባለሥልጣን የታክስ ከፊዩ ንብረት በማናቸዉም የፍርድ ሂደት እገዲ ተደርጎበት ከሆነ ወይም በንብረቱ ላይ የፍርድ አፈጻጸም ትእዛዝ ተሰጥቶበት ከሆነ ንብረቱ ላይ የተሰጠዉን እግድ ወይም የአፈጻጸም ትእዛዝ ካላስነሳ በስተቀር የታክስ ከፊዩን ንብረት መያዝ (Seizure of Property) እንደማይችል በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 41(4/ለ) ስለተደነገገ የቀደምትነት መብቱን ከመጠቀም ጋር ተያይዞ የታክስ ከፊዩን ንብረት ለመያዝ በንብረቱ ላይ የተሰጠዉን የፍርድ ቤት እግድ ወይም የፍርድ አፈጻጸም ትእዛዝ አሰቀድሞ ማስነሳት ይጠበቅበታል።
በተያዘዉ ጉዲይ 2ኛ ተጠሪ በ1ኛ ተጠሪ ላይ ያስፈረደዉን ፍርድ ለማስፈጸም የ1ኛ ተጠሪን ንብረት ያስከበረ ተከራካሪ ወገን እንደመሆኑ ያለዉ መብት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ 394/1፣ቁጥር 404 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት እግደን የሰጠዉ ፍርድ ቤት እግደን እስካላነሳ ድረስ ያስከበረዉን ንብረት 1ኛ ተጠሪ ዕዲዉን ከመክፈለ በፉት ለላላ ሰዉ እንዲይሰጥ፣ እንዲይሸጥ፣ እንዲይለዉጥ ወይም በማናቸዉም ላላ ሁኔታ መብቱን ለማንም እንዲያዛዉር አስከብሮ ማቆየትና የፍርድ ባለእዲዉ እዲዉን መክፈል ካልቻለ ንብረቱ በሐራጅ ተሸጦ ገንዘቡ እንዱከፈለዉ መጠየቅ ነዉ። ከዚህ ዉጭ የፍርድ ባለእዲውን በዚህ አግባብ ማስከበሩ ንብረቱ ከመከበሩ ወይም ከመያዙ በፉት በንብረቱ ላይ መብት የነበራቸዉና በክርክሩ ዉስጥ የላለ የሦስተኛ ወገኖች በሕግ፣በፍርድ ወይም በዉል በንብረቶቹ ላይ ያቋቋሙትን የቀደምትነት መብት የሚነካ አይደለም። ከያዝነዉ ጉዲይ ጋር በተያያዘ አመልካች በፋዳራልም ሆነ በክልል የታክስ አስተዲደር አዋጆች ላይ በተመሳሳይ በተደነገገዉ መሰረት 1ኛ ተጠሪ አልከፈለም ብል ንብረቱን ይዞ በመሸጥ ለማስከፈል የፈለገዉ የክልለን ታክስ የታክስ አስተዲደር አዋጅን ጨምሮ ከገቢ ግብር አዋጅ፣ከተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ፣ከሲክሳይዝ ታክስ አዋጅ፣ከቴምብር ቀረጥ አዋጅ፣ከተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ፣የጉምሩክ ሕግ ሳይጨምር ማንኛዉም ታክስ፣ ቀረጥ ወይም ክፍያ የሚጥል ሕግና እነዚህን አዋጆች ለማስፈጸም ከወጣ ደንብና መመሪያ የመነጨ መሆኑን እስካረጋገጠ ድረስ በ1ኛ ተጠሪ ንብረት ላይ ከ2ኛ ተጠሪ ቀድሞ ንብረቱን በመሸጥ ያለተከፈለዉን ታክስና ቀረጥ የማስከፈል በሕግ ጥበቃ የተደረገለት መብት አለዉ። ነገር ግን አመልካች 1ኛ ተጠሪ እንዱከፍለዉ የጠየቀዉ ታክስና ቀረጥ አንዱሁም ተያያዥ ክፍያ በዝርዝር ከተጠቀሱ ሕግጋት የመነጩ መሆናቸዉን እና በሥልጣኑ ክልል ዉስጥ የሚገኝ ታክስና ቀረጥ መሆኑን በልላ አገላለጽ ቅቡልነት ያለዉ ዋና ግዳታ መኖሩን(valid principal obligation) ማስረዲት እና ፍርድ ቤቶችም ማስረዲቱን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።ሆኖም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ ያየዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418 በሚጠይቀዉ የክርክር አመራር መሰረት ከዚህ አኳያ የግራ ቀኙን ክርክር ካለመመርመራቸዉም በተጨማሪ ፍሬ ነገሮቹን ከሕግና ከማስረጃ አንጻር አለማጣራታቸዉን ተገንዝበናል።
እንዱሁም በሕግ የተሰጠዉን የቀደምትነት መብት በ1ኛ ተጠሪ ሀብት ላይ የሚጠቀም መሆኑን፣ ያልተከፈለዉን ታክስ እና ታክሱን ለማስከፈል የሚወስደዉ እርምጃ የሚያስከትለዉን ወጪ እንደሚያስከፍለዉና በንብረቱ ላይም የዋስትና መብት እንደሚያስመዘግብ የሚገልጽ ማስታወቂያ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ(ለታክስ ከፊዩ) የሰጠ መሆኑን ማስረዲት የሚጠበቅበት ሲሆን ፍርድ ቤቶችም አመልካች ባቀረበዉ ማስረጃ ማስረዲቱን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። አመልካች በዚህ መልኩ ማስረዲት እስከቻለ ድረስ በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት በተከበሩት በ1ኛ ተጠሪ ንብረቶች ላይ የቀደምትነት መብት መጠቀም ይችላል። አመልካች በዚህ በቀደምትነት መብቱ መጠቀም ይችል ዘንድ ንብረቶቹን ለማስከበር የተሰጠዉ የእግድ ትእዛዝ እንዱነሳለት መጠየቁ በፋዳራልና በክልለ ታክስ አስተዲደር አዋጆችም ሆነ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418 ስር የተደነገገዉን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ከ2ኛ ተጠሪ ቀድሞ ንብረቶቹን ያስከበረ ስለመሆኑ ማስረጃ እንዱያቀርብ ሉጠየቅ የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም። ምክንያቱም የቀደምትነት መብት ያገኘዉ በሕግ በመሆኑና ንብረቶቹን መያዝና ሽጦ ታክስና ቀረጥ እንዱሁም ከላይ ከተጠቀሱ ሕጎች የመነጩ ላልች ክፍያዎችን ማስከፈል የሚችለዉ አስቀድሞ በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ንብረቶቹን ለማስከበር የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ሲነሳለት ብቻ በመሆኑና ለዚህ የፍርድ ዉሳኔ መነሻ የሆነዉን አቤቱታ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418 መሰረት ያቀረበዉንም ለዚሁ ዓላማ በመሆኑ ነዉ።ከዚህም ረገድ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ ያየዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418 በሚጠይቀዉ የክርክር አመራር መሰረት የግራ ቀኙን ክርክር ሳይመረምሩና ፍሬ ነገሮቹን ከሕግና ከማስረጃ አንጻር ማስረዲት ያለበት ተከራካሪ ወገን እንዱያስረዲ በማድረግ ሳያጣሩ በሕግ ጥበቃ የተደረገለትን የአመልካችን የቀደምትነት መብት ዉድቅ ማድረጋቸዉ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።
የደቡብ አሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 07/09/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 18/11/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥ 348/1 መሰረት ተሸረዋል።
2ኛ ተጠሪ በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ባስከበራቸዉ የ1ኛ ተጠሪ ንብረቶች ላይ አመልካች የቀደምትነት መብት አለዉ ብለናል።ሆኖም አመልካች በዚህ የቀደምትነት መብት መጠቀም የሚችለዉ የክልለን የታክስ አስተዲደር አዋጅን ጨምሮ ከገቢ ግብር አዋጅ፣ከተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ፣ከኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ፣ከቴምብር ቀረጥ አዋጅ፣ከተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ፣የጉምሩክ ሕግ ሳይጨምር ማንኛዉም ታክስ፣ ቀረጥ ወይም ክፍያ የሚጥል ሕግና እነዚህን አዋጆች ለማስፈጸም ከወጣ ደንብና መመሪያ የመነጨ እና ይህም በአመልካች እንዱሰበሰብ በሕግ ለአመልካች ሥልጣን የተሰጠዉ መሆኑን እንዱሁም አመልካች በሕግ የተሰጠዉን የቀደምትነት መብት በ1ኛ ተጠሪ ሀብት ላይ የሚጠቀም መሆኑን፣ ያልተከፈለዉን ታክስ እና ታክሱን ለማስከፈል የሚወስደዉ እርምጃ የሚያስከትለዉን ወጪ እንደሚያስከፍለዉና በንብረቱ ላይም የዋስትና መብት እንደሚያስመዘግብ የሚገልጽ ማስታወቂያ ለ1ኛ ተጠሪ(ለታክስ ከፊዩ) መስጠቱ ሲረጋገጥ በመሆኑ የደቡብ አሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ ከዚህ አኳያ ግራ ቀኙን አከራክሮና በማስረጃ ሉረጋገጡ የሚገባቸዉን ፍሬ ነገሮች በሥነ ሥርዓት ሕጉ አግባብ በማስረጃ እንዱረጋገጡ በማድረግ ሕግን መሰረት ያደረገ ዉሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን መልሰንለታል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጪ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ።
በዚህ መዝገብ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል። ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.