ፍርድ ቤቶች ተከሳሽ ሳይቀርብ ቀርቶ ጉዲዩ በላለበት የሚታይ ወይም ተከሳሹ ቀርቦ መቃወሚያውን ያላነሳው ቢሆንም ከሳሽ ያቀረበው ክስ አስቀድሞ ፍርድ ባገኘ ጉዲይ ላይ የቀረበ መሆኑን በክርክሩ ሑደት ባረጋገጡ ጊዜ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 ድንጋጌ የተመለከቱት መስፈርቶች መሟላታቸው እስከተረጋገጠ ጊዜ ድረስ አዱስ የቀረበውን ክስ አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ ነው በማለት ውድቅ የማድረግ ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ (የፋ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት በፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በሰ/መ/ መዝገቦች ላይ ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ተለውጧል።)
No summary available.
የሰ.መ.
ሐምል 30 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- መዓዛ አሸናፉ ሰለሞን አረዲ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ወ/ሮ ጠጂቱ ጎረምሶ ማገር ተጠሪ፡- ወ/ሮ ወርቅነሽ በሻ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ሐምል 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ አመልካች በስር የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይዞታና ቤቴ ይለቀቅልኝ፤ በተጠሪ ስም የተሰራው ካርታም እንዱመክን ይወሰንልኝ ሲለ ያቀረቡት ክስ አስቀድሞ የመጨረሻ ፍርድ ያገኘ ጉዲይ ነው ተብል በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 5 መሰረት ውድቅ መደረጉ እና ይህም ውሳኔ በይግባኝ መጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረምልኝ ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው መነሻነት ነው።
አመልካች ለስር ፍርድ ቤት አቅርበውት የነበረው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ ወረዲ 08 ቤ.ቁ 147 የይዞታ መለያ ቁጥሩ 559 የሆነ እና በ5ዐዐ ካ.ሜ. ላይ ያረፈውን ቤት ተጠሪዋ በስጦታ ወይም በግዢ ሳይተላለፍላቸው 25ዐ ካ.ሜ. የሆነውን ይዞታ በስማቸው ካርታ አሰርተው የያዙባቸው መሆኑን በመግለጽ ይዞታውን እንዱለቁ እና አላግባብ ያሰሩት ካርታ እንዱመክን ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። ተጠሪ መጥሪያ ተልኮላቸው ስላልቀረቡ ጉዲያቸው በላለበት የታየ መሆኑን ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ የቀረበልን የውሳኔ ግልባጭ ያመለክታል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ክሱን ሲሰማ ተጠሪ በአሁን አመልካችና በባለቤታቸው ላይ የሁከት ይወገድልኝ ክስ አቅርበውባቸው ክሱ ተቀባይነት አግኝቶ ሁከት እንዱወገድ ተወስኖ ቤቱንም በአፈፃፀም ተገደው በመልቀቃቸው የመፊለም ክስ ያቀረቡ መሆኑን ለፍ/ቤቱ ገልጸዋል። ፍርድ ቤቱም በተጠሪ ክስ አቅራቢነት ውሳኔ እና የአፈጻጸም ትዕዛዝ ተሰጥቶባቸዋል የተባለትን የመዝገብ የሆኑትን መዛግብት ካስቀረበ እና ጉዲዩ የሚመለከተው የአስተዲደር አካልም ተጠሪ ቤቱን በምን አግባብ እንደያዙ አጣርቶ እንዱልክለት ካደረገ በኋላ አመልካች ያቀረቡት ክስ አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ ነው በማለት ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል። ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍ/ቤት የአመልካችን ክስ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ነው ሲል አጽንቶታል።
አመልካች ሐምል 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት የሰበር አቤቱታው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል የቀረበ ሲሆን ይዘቱም፡- ተጠሪ በአመልካች እና በባለቤቱ ላይ በመ. ያቀረበችው ክስ ሁከት ይወገድልኝ በሚል የቀረበ እንጂ ይዞታ እንዱመለስ ወይም ካርታ እንዱመክን በሚል የቀረበ ክስ አይደለም፣ በጉዲዩ ላይ ውሳኔ የተሰጠውም የተፈጠረው ሁከት እንዱወገድ በሚል እንጂ ይዞታው የተጠሪ መሆኑ ተገልጾ የተሰጠ ውሳኔ የለም፤ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ተጠሪ ቀርባ ባልተከራከረችበት እና ካርታውም ባልመከነበት ሁኔታ ጉዲዩን ከሁከት ክስ ጋር አገናኝቶ አመልካች ያቀረቡት ክስ አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪው ችልቱ ተመርመሮ ቀደም ሲል በመዝገብ በቀን 3ዐ/11/1999 ዓ.ም. ውሳኔ ያረፈበት ጉዲይ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሆኖ አሁን የቀረበው ክስ ግን ባለቤትነትን የሚመለከት ሆኖ ሳለ፤ ተጠሪዋም በዚህ ረገድ ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሳይኖር ጉዲዩ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ስለሆነ በድጋሚ የክርክር ምክንያት ላሆን አይችልም በሚል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ተጠሪ መጥሪያ ተልኮላቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መልስ የማቅረብ መብታቸው ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነውን ውሳኔ አመልካች ካቀረቡት ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ፡-
ፍርድ ቤቶች ከሳሽ ያቀረበው ክስ አስቀድሞ ፍርድ ባገኘ ጉዲይ ላይ የቀረበ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል መቃወሚያ ከላላው ተከራካሪ ወገን ባልቀረበበት ሁኔታ ይህንኑ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የቀረበውን ክስ ውድቅ ማድረግ ይችላለ? ወይስ አይችለም?
ፍርድ ቤቶች በልላው ተከራካሪ ወገን የቀረበ መቃወሚያ ባይኖርም ከሳሽ ያቀረበው ክስ አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ መሆኑን በማናቸውም ምክንያት ባረጋገጡ ጊዜ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት ክሱን ውድቅ ማድረግ ይችላለ ከተባለ የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ በተጠቃሹ ድንጋጌ መሰረት ውድቅ ያደረገው በድንጋጌው ላይ የተቀመጡት ሁኔታዎች የተሟለ መሆኑን አረጋግጦ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለትን ጭብጦች በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረነዋል።
የመጨረሻ ውሳኔ ስላገኙ ጉዲዮች የሚደነግገው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 በንዐስ ቁጥር (1) ላይ በሕግ ስልጣን የተሰጠው ማንኛውም ፍርድ ቤት ክርክሩን ተቀብል የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ቀድሞ በፍርድ የተወሰነው ክርክር ሥረ ነገር እና የተያዘው ጭብጥ አንድ ዓይነት ከሆነ በክርክሩ ላይ የነበሩት ወይም ከተከራካሪዎቹ መብት ያገኙ ሶስተኛ ወገኖች በዚያው ነገር ሁለተኛ ክስ ወይም ማናቸውንም ዓይነት ላላ ክርክር ለማቅረብ አይችለም በማለት ይደነግጋል። በዚህ አግባብ የሚቀርበው መቃወሚያም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚቀርብበትን ሥርዓት አስመልክቶ በተደነገገው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244 ድንጋጌ ላይ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የሚቀርቡ ናቸው ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ አንደ ነው። የዚሁ ድንጋጌ ንዐስ ቁጥር (3) የቀረቡት መቃወሚያዎች ከአንድ በላይ ሲሆኑ በተቻለ መጠን በቶል ተጠቃለው ሁለም መቅረብ እንዲለባቸው፤ መቅረብ ከሚገባቸው መቃወሚያዎች ውስጥ ሳይቀርቡ የቀሩት ትክክለኛውን ፍርድ ለመስጠት የማያሰናክለ ከሆኑ ባለጉዲዩ ራሱ ሆነ ብል ለማቅረብ ባለመፈለግ እንደተዋቸው ይቆጠራል በማለት ይደነግጋል።
ከላይ በዝርዝር የተመለከቱት የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች አንድ ጉዲይ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ ነው በሚል የሚቀርበው መቃወሚያ የሚቀርብበትን ሥርዓት የሚደነግጉ ናቸው። ሆኖም ፍርድ ቤቶች ተከሳሽ የሆነው ተከራካሪ ወገን ሳይቀርብ ቀርቶ ጉዲዩ በላለበት የሚታይ በሆነ ጊዜ ወይም ተከሳሹ ቀርቦ መቃወሚያውን ባላነሳው ጊዜ ከሳሽ የሆነው ተከራካሪ ወገን ያቀረበው ክስ አስቀድሞ ፍርድ ባገኘ ጉዲይ ላይ የቀረበ መሆኑን በአንድም ወይም በልላ ምክንያት ባወቁ ጊዜ ሉኖራቸው የሚገባው ሚና በዚህ ችልት ምላሽ ማግኘት ያለበት የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ ነው። ስለሆነም በጉዲዩ ላይ ምላሽ መስጠት ያስችለን ዘንድ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. አንጻር እንደሚከተለው መርምረናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. በሰጠው ውሳኔ በአብዛኛው ትኩረት ያደረገው አስቀድሞ በተሰጠው ፍርድ ላይ የነበረው የፍሬ ነገር ጭብጥ እና አሁን በቀረበው ጉዲይ ላይ የተያዘው የፍሬ ነገር ጭብጥ ተመሳሳይ ነው? ወይስ አይደለም? በሚለው ላይ ሲሆን የፍሬ ነገር ጭብጥ ከመጀመሪያው ጋር ተመሳሳይ ሆኖ የመጨረሻ ፍርድ ያረፈበት መሆኑ ከተረጋገጠ እንዱሁም ጉዲዩ የመጨረሻ ፍርድ አርፍበታል የሚል ተቃውሞ በተከራካሪ ወገን ከተነሳ ተቀባይነት አለው በሚል በውሳኔ ላይ በግልጽ አመልክቷል። ችልቱ ይህንኑ ውሳኔ በመጥቀስ በሰ.መ. የሰጠው ውሳኔ ደግሞ የስር ፍርድ ቤቱ ከተጠሪ ጋር የነበረውን ጋብቻ የፈረሰ መሆኑን በመግለጽ የንብረት ክፍፍል እንዱደረግ ያቀረቡትን አቤቱታ ውድቅ ያደረገው ይህ ክርክር አስቀድሞ ታይቶ አብቅቷል በማለት ቢሆንም በአመልካች የቀረበው አቤቱታ ለተጠሪ ደርሶ ተጠሪ መቃወሚያ አላቀረቡበትም፤ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ በጉዲዩ ላይ መልስ እንዱሰጡበት በማድረግ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ጉዲይ መሆኑን በመግለጽ በድጋሚ ላቀርብ አይገባም በማለት ያቀረቡት መቃወሚያ ካለ ጉዲዩ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ጉዲይ መሆን ያለመሆኑን በማስረጃ አጣርቶ ከሚወስን በቀር ተከራካሪዎች ባላነሱት መቃወሚያ በራሱ ጊዜ ማንሳት አይችልም፤ ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ተከራካሪዎች መልስ ያልሰጡበትን እና ያላነሱትን መቃወሚያ በማንሳት ጉዲዩ በድጋሚ ላቀርብ አይገባም በማለት አቤቱታውን ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም ካለ በኋላ ግራ ቀኙ በስምምነት ፍቺ ፈጽመው የንብረት ክፍፍላቸው በፍርድ ቤት የጸደቀ በመሆኑ ምንም እንኳን ፍርድ ቤቱ ተጠሪ በጉዲዩ ላይ መልስ እንዱሰጡት ሳያደርግ መቃወሚያው በተጠሪ ሳይነሳ በራሱ ጊዜ በማንሳት ጉዲዩ አስቀድሞ ትዕዛዝ ተሰጥቶበታል በማለት መዝጋቱ ተገቢ ባይሆንም የንብረት ክፍፍላቸው በፍርድ ቤት ጸድቆ ባለበት እና ይህ ስምምነት እንዱፈርስ ጠይቀው ባላስፈረሱበት እንደ አዱስ ንብረት እንድንካፈል ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ ተገቢ አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በውጤት ደረጃ ተቀብል ያጸናው መሆኑን የውሳኔው ይዘት ያሳያል።
ከላይ ከተመለከቱት ውሳኔዎች ይዘት መገንዘብ የሚቻለው ሰበር ሰሚ ችልቱ በአንድ በኩል ጉዲዩ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው የሚል መቃወሚያ በተከራካሪ ወገኖች እስካልቀረበ ድረስ ፍርድ ቤቱ ራሱ ማንሳት አይችልም የሚል አቋም ያለው መሆኑን፤ በልላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ጉዲይ የተሰጠ የጸና ፍርድ ባለበት ሁኔታ አዱስ በቀረበው ክስ ላይ ውሳኔ የሚሰጥበት አግባብ አይኖርም የሚል አቋም ያለው መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ሰበር ሰሚ ችልቱ ፍርድ ቤቶች ተከሳሽ የሆነው ተከራካሪ ወገን ሳይቀርብ ቀርቶ ጉዲዩ በላለበት የሚታይ በሆነ ጊዜ ወይም ተከሳሹ ቀርቦ መቃወሚያውን ባላነሳው ጊዜ ከሳሽ የሆነው ተከራካሪ ወገን ያቀረበው ክስ አስቀድሞ ፍርድ ባገኘ ጉዲይ ላይ የቀረበ መሆኑን ባወቁ ጊዜ አዱስ የቀረበው ክስ አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ ነው በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት ውድቅ ማድረግ የሚኖርባቸው ስለመሆን አለመሆኑ ግልጽ የሆነ አቋም ያልያዘበት መሆኑን የሚያሳይ ነው።
በመሰረቱ በሕግ ሥልጣን በተሰጠው ማናቸውም ፍርድ ቤት ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ ጉዲይ ድጋሚ ክስ ላቀርብበት አይገባም በማለት የተደነገገበት ዋና ዓላማ አንድ ተከራካሪ ወገን በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ በተለያየ ጊዜ ክስ እየቀረበበት ጊዜውን እንዲያባክን፤ ተጨማሪ ወጪ እንዲያወጣ እና እንዲይሸማቀቅ ለማድረግ፤ አንድ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በበላይ ፍርድ ቤት እስካልተሻረ ድረስ በሕብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዱኖረው ለማድረግ፤ ክርክሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ መቋጫ እንዱኖራቸው ለማድረግ፤ ሕጉ ላልተፈለገበት ዓላማ እንዲይውል በመከላከል የፍትሕ አስተዲደር ሥርዓቱ ተገማች እና ፍትሐዊ እንዱሆን ለማድረግ ስለመሆኑ በዘርፈ ከዲበረው ሥነ ሕግ መገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም አንድ ጉዲይ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ታይቶ ውሳኔ ያገኘ መሆኑ ከተረጋጠ አዱስ የቀረበውን ክስ በድጋሚ አይቶ ውሳኔ መስጠት ከላይ የተመለከተውን የሥነ ሥርዓት ሕጉን አይነተኛ ዓላማ የማያሳካ እና በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ የተጣረሰ ውሳኔ ላሰጥ የሚችልበትን ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ ፍርድ ቤቶች ተከሳሽ የሆነው ተከራካሪ ወገን ሳይቀርብ ቀርቶ ጉዲዩ በላለበት የሚታይ በሆነ ጊዜ ወይም ተከሳሹ ቀርቦ መቃወሚያውን ባላነሳው ጊዜ ከሳሽ የሆነው ተከራካሪ ወገን ያቀረበው ክስ አስቀድሞ ፍርድ ባገኘ ጉዲይ ላይ የቀረበ መሆኑን በአንድም ወይም በልላ ምክንያት ባወቁ ጊዜ በድንጋጌው የተመለከቱት መስፈርቶች መሟላታቸው እስከተረጋገጠ ጊዜ ድረስ አዱስ የቀረበውን ክስ አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ ነው በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት ውድቅ ሉያደርጉት ይገባል በማለት ቀደም ሲል የተሰጠውን የሕግ ትርጉም አሻሽለን በያዝነው ጉዲይ የተሰጠው የሕግ ትርጉም ገዢ ላሆን ይገባል ብለናል። ፍርድ ቤቶች በፉታቸው የቀረበላቸው ጉዲይ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ መሆኑን በክርክሩ ሂደት ባረጋገጡ ጊዜ ድረስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት አዱስ የቀረበውን ክስ ውድቅ ማድረግ ይችላለ ከተባለ የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ ድጋሚ የቀረበ ክስ ነው በማለት ውድቅ ያደረገው በእርግጥም በድንጋጌው ላይ የተቀመጡት መስፈርቶች መሟላታቸውን አረጋግጦ ነው?
ወይስ አይደለም? የሚለውን ቀጥለን እንመለከታለን።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5(1) ላይ በግልጽ እንደተመለከተው አንድ ጉዲይ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ ነው ተብል ውድቅ ላደረግ የሚችለው ቀድሞ በፍርድ የተወሰነው ክርክር ሥረ ነገር እና የተያዘው ጭብጥ አሁን ከቀረበው ጉዲይ ጋር አንድ ዓይነት ከሆነ እና አዱስ በቀረበው ክስ ላይ ተከራካሪ በመሆን የቀረቡት ወገኖች ቀድሞ በነበረው ክርክር ላይ የነበሩ ወይም ከተከራካሪዎቹ መብት ያገኙ ሶስተኛ ወገኖች በሆኑ ጊዜ ነው።
በያዝነው ጉዲይ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች እና በባለቤታቸው ላይ በመ. አቅርበውት የነበረው ክስ ይዘት ሁከት ይወገድልኝ በሚል የቀረበ ሲሆን አሁን በእጃችን ባለው ጉዲይ አመልካች ያቀረቡት ክስ ደግሞ ተጠሪ አከራከሪ የሆነው ቤት በስጦታም ሆነ በሽያጭ ሳይተላለፍላት ካርታ በስሟ ያወጣችበት ስለሆነ ያለአግባብ የተሰጣት ካርታ እንዱሰረዝልኝ የሚል ነው። ይህም ቀድሞ በነበረው ክስ ሉያዝ የሚችለው ጭብጥ ሁከት ተፈጥሯል? ወይስ አልተፈጠረም? የሚል መሆኑን አመልካች ባቀረቡት አዱስ ክስ ላይ ደግሞ ሉያዝ የሚችለው ጭብጥ የንብረቱ ባለቤት ማነው? የሚል እና ከዚሁ ጭብጥ ጋር ተያያዥነት ያለው ላላ ጭብጥ መሆኑን ነው። ስለሆነም ቀድሞ በፍርድ የተወሰነው ክርክር ሥረ ነገር እና የተያዘው ጭብጥ አሁን ከቀረበው ጉዲይ ጋር አንድ ዓይነት ባልሆነበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤቶች አስቀድሞ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ጸንቶ ባለበት ሁኔታ በድጋሚ አዱስ ክስ ማቅረባቸው ተገቢ አይደለም በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ በማድረግ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረቡት ክስ በድጋሚ የቀረበ አለመሆኑን ተገንዝቦ አግባብነት ያለውን ትዕዛዝ በመስጠት ጉዲዩን አጣርቶ እንዱወስን ማድረግ ስነ- ስርዓታዊ ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ከላይ በፍርድ ሐተታው በተገለጸው ምክንያት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል ፍርድ ቤቶች ተከሳሽ የሆነው ተከራካሪ ወገን ሳይቀርብ ቀርቶ ጉዲዩ በላለበት የሚታይ ወይም ተከሳሹ ቀርቦ መቃወሚያውን ያላነሳው ቢሆንም ከሳሽ የሆነው ተከራካሪ ወገን ያቀረበው ክስ አስቀድሞ ፍርድ ባገኘ ጉዲይ ላይ የቀረበ መሆኑን በክርክሩ ሑደት ባረጋገጡ ጊዜ በድንጋጌው የተመለከቱት መስፈርቶች መሟላታቸው እስከተረጋገጠ ጊዜ ድረስ አዱስ የቀረበውን ክስ አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ ነው በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት ውድቅ ሉያደርጉት ይገባል በማለት ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. በቀን 02/ዐ5/2ዐ11 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ፤
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. ሐምል 17 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
ይህ ውሳኔ ይታተም ዘንድ ለሕግ እና ጥናት ክፍል ግልባጩ ይድረሰው።
የሰ/መ/ መስከረም 25 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ደረጀ አያና ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- የደቡብ ኦሞ ዞን ዲሰነች ወረዲ ገቢዎች ባለስልጣን፡- አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- 1.ፍራኦል ኢትዮጵያ የእርሻ ልማት ድርጅት፡- አልቀረቡም 2. የፋዳራል መንግስት ልማት ድርጅት ይዞታና አስተዲደር ኤጀንሲ፡- ነ/ፈጅ ምህረቱ መኮንን ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በሕግ የተሰጠ የቀደምትነት መብት አፈጻጸም የሚመለከት ሆኖ የፍርድ አፈጻጸም ክርክር በዉክልና በሚታይበት በደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት 1ኛ ተጠሪ ደግሞ የፍርድ ባለእዲ ሆነዉ በሚከራከሩበት መዝገብ ላይ አመልካች የመቃወም አመልካች በመሆን የተከራከረ ነዉ። ከክርክሩ እንደተረዲነዉ የደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍርደን እያስፈጸመ የሚገኘዉ 2ኛ ተጠሪ በ1ኛ ተጠሪ ላይ ያስፈረደዉን ፍርድ እንዱያስፈጽም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠዉ የዉክልና ሥልጣን መነሻ ነዉ። ይህ የተወከለዉ ፍርድ ቤት የፍርድ ባለእዲዉ ንብረት የሆኑትን የዕርሻ መሳሪያዎች ፣የዕርሻና ኮንስትራክሽን መሳሪያዎች፣ ተቀጽላ መሳሪያዎች፣ ሞተሮች፣ የዉሃ ፓምፖችና ጀኔሬተሮች፣ የወርክ ሾፕ መገልገያ መሣሪያዎች እና የተለያዩ አይነት መገልገያ መሳሪያዎች ተከብረዉ እንዱቆዩ ካደረገ በኋላ የመነሻ ዋጋቸዉ እንዱታወቅ አድርጎ በብር 25,284,862.69 መነሻ ዋጋ በሐራጅ እንዱሸጥ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ከላይ የተመለከተዉ ትእዛዝ ከመሰጠቱ በፉት የአሁን አመልካች ለፍርድ ቤቱ ባቀረበዉ አቤቱታ 1ኛ ተጠሪ ብር 10,393,364.75 የግብር እዲ ስላለበት እንዱከበሩ(እንዱታገደ) በተደረጉት በተጠቃሾቹ ንብረቶች ላይ በታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 እና በደቡብ ክልል የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 166/2009 አንቀጽ 39፣41፣እና 43 መሰረት 1ኛ ተጠሪ ባልከፈለዉ ዉዝፍ የግብር እዲ ልክ አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ የቀደመ መብት ስላለኝ በሕጉ መሰረት የቀደምትነት መብት ይጠበቅልኝ በማለት ጠይቋል።
ፍርደን እያስፈጸመ ያለዉ የደቡብ አሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ በመ/ ላይ በቀን 07/09/2011 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ የአሁን 2ኛ ተጠሪ(የፍርድ ባለመብት) የንብረት ዝርዝርና ግምታቸዉን አቅርቦ ንብረቶቹ በሐራጅ ተሽጠዉ ገንዘቡ እንዱከፈለዉ በጠየቀበት ሁኔታ የአሁን አመልካች 1ኛ ተጠሪ(የፍርድ ባለዕዲዉ) ላለበት የግብር እዲ እነዚህን ንብረቶች በመያዣያነት ማስከበሩን የሚያስረዲ ማስረጃ ከአቤቱታዉ ጋር አያዞ አላቀረበም።ስለሆነም መብቱን አስከብሮ ባልቀረበበት በ2ኛ ተጠሪ በኩል የቀረቡት ንብረቶች በጨረታ ሲሸጥ የቀደምትነት መብት ይሰጠኝ በማለት መጠየቁ ተገቢነት የለዉም። ነገር ግን ንብረቱ በሐራጅ ተሸጦ ከሚቀረዉ ቀሪ ገንዘብ ላይ ገንዘቡን ከፍርድ ባለእዲዉ ላይ መቀበል ይችላል በሚል 2ኛ ተጠሪ በጠየቀዉ መሰረት ንብረቶቹ በሐራጅ ተሸጠዉ በፍርደ መሰረት ለ2ኛ ተጠሪ እንዱከፈለዉ አዟል። አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ አቅርቦ ችልቱ በመ/ ላይ በቀን 18/11/2011 ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ትእዛዝ ይግባኙን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዟል።
አመልካች በቀን 10/02/2012 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ በዚህ አግባብ በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።የስር ፍርድ ቤት የሰጠዉ ትእዛዝ በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 39 ስር ያልተከፈለዉን የግብር እዲ አመልካች የግብር ባለእዲዉን ንብረት በማሸጥ ለማስከፈል የቀዲምነት መብት እንዲለዉ የተደነገገዉን የሚቃረን ነዉ። የአዋጁን ድንጋጌ አለአግባብ በመተርጎም የቀደምትነት መብት ተጠቃሚ ለመሆን የግብር ባለእዲዉ ንብረት በዋስትና መያዝና መያዣዉ መመዝገብ አለበት በማለት አመልካች ያቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418 እንደተደነገገዉ እና በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ ትርጉም መሰረት በፍርድ አፈጻጸም በታገደዉ ንብረት ላይ አመልካች ተቀዲሚ መብት አለኝ በሚል ያቀረበዉን አቤቱታ ተቀብል በመደበኛ የሙግት አመራር መሰረት ግራ ቀኙን ሳያከራክር ፣የአመልካችን የሰነድ ማስረጃዎች ሳይመረምር የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ አድርጎ አፈጻጸሙ እንዱቀጥል ማዘዙ ከስነ ስርዓት ሕጉ ዉጪ ነዉ።2ኛ ተጠሪ ያለዉ መብት በንብረቱ ወይም በሽያጭ ገንዘቡ ላይ የቀዲሚነት መብት ያለዉ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈልገዉን የግብር እዲ በቀዲሚነት ካስከፈለ በኋላ የሚተርፈዉን ገንዘብ መዉሰድ በመሆኑ አመልካች በተጠየቀዉ መሰረት በንብረቱ ላይ 2ኛ ተጠሪ ያሰጠዉ እግድ እንዱነሳ ማዘዝ ሲገባዉ የሥር ፍርድ ቤት ከአመልካች ዲኝነት ጥያቄ ዉጭ ንብረቱ በሐራጅ ከተሸጠ በኋላ ከ2ኛ ተጠሪ የሚተርፈዉን ገንዘብ መጠየቅ ይችላል በማለት መወሰኑ በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን አስገዲጅ ትርጉም እና የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418 ላይ የተደነገገዉን ያልተከተለ በመሆኑ ስህተት ነዉ።አመልካች ዲኝነት ባልጠየቀበት ንብረቱ በሐራጅ ሲሸጥ ንብረቱን አመልካች በቀደምነት የመግዛት መብት እንዱጠበቅለት እንደጠየቀ አድርጎ የሥር ፍርድ ቤት በትእዛዙ ላይ መግለጹም ስህተት ነዉ።1ኛ ተጠሪ የግብር እዲ ዉሳኔ ማስታወቂያ ደርሶት በተጠየቀ ጊዜ ካልከፈለ አመልካች የግብር እዲዉን ለማስከፈል በሕግ የሚጠበቅበት ተግባር የባለእዲዉን ንብረት አግድ በመሸጥ ግብር ያስከፍላል እንጂ ለፍርድ ቤት ጥያቄዉን አቅርቦ ንብረቱን እንዱያስከብር አይገደድም። በተጨማሪም ንብረቱን ይዞ መሸጥ የሚችለዉ ንብረቱ ላይ በፍርድ ቤት የተሰጠ እግድ ካለ እግደን ካስነሳ በኋላ በመሆኑና 1ኛ ተጠሪ የግብር እዲ የሚፈለግበት መሆኑን የሚያሳይ የግብር ማስታወቂያ ዉሳኔ 1ኛ ተጠሪ ለ2ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለእዲ ከመሆኑ በፉት አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ መስጠቱን ለስር ፍርድ ቤት ያቀረብነዉ ማስረጃ የሚያሳይ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታ ከሕግና ካቀረብነዉ ማስረጃ እንጻር ሳይመረምር የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ እያለ ስህተቱን ይግባኝ ሰሚዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አለማረሙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ ሲል አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ እንዱከፈለዉ ለሚጠይቀዉ የግብር እዲ ንብረቱን በመያዣነት ስላላስከበረም የቀዲሚነት መብት የለዉም የመባለን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 983/2008 እንቀጽ 39/1 ከደቡብ ክልል አዋጅ ቁጥር 166/2009 ጋር ተገናዝቦ እንዱመረመር ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትል ተጠሪዎች እንደቅደም ተከተላቸዉ በቀን 01/05/2012 ዓ/ም እና በቀን 30/04/2012 ዓ/ም የተጻፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱ በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
1ኛ ተጠሪ ባቀረበዉ መልስ 1ኛ ተጠሪ በዉጭ ባለሀብቶች የተቋቋመ፣የኢንቨስትመንት እና የንግድ ፈቃድ የተሰጠዉ ከፋዳራል መንግስት በመሆኑ አመልካች 1ኛ ተጠሪን ግብርና ታክስ የማስከፈል ሥልጣን የለዉም።አመልካች እየጠየቀ ያለዉ የመሬት መጠቀሚያ ግብርና የቴምብር ቀረጥ ያልተከፈለኝ አለ በሚል ቢሆንም መከፈል ያለበትን የቴምብር ቀረጥ የከፈልን ሲሆን የሉዝ ክፍያ የለም እንጂ የሉዝ ክፍያ አለ ቢባል እንኳን አመልካች በመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ ከመጠየቅ በስተቀር የቀደምትነት መብት አለኝ በሚል መጠየቅ የሚችልበት የሕግ መሰረት የለም።የመሬት የሉዝ ክፍያ ማስከፈል እንዱችል በሕግ ከላልች ባለመብቶች የቀደመ መብት ለአመልካች አልተሰጠዉም። የቀደምትነት መብት የሚኖረዉ የሉዝና የቴምብር ቀረጥ ለማስከፈል ሳይሆን ያልተከፈለ የንግድ ግብርና የግብርና ግብር ክፍያ ሲኖር ብቻ ሲሆን ከዚህ አንጻር እዲ እንደላለብን የፋዳራል ግብር አስከፊይ መስሪያ ቤት በጽሁፍ ስላሳወቀ አመልካች አለአግባብ የቀደምትነት መብት አለኝ በሚል ያቀረበዉን አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤት ዉድቅ ማድረጉ ተገቢ ስለሆነ የሰበር አቤቱታዉ ተቀባይነት ሉያገኝ አይገባም በማለት ተከራክሯል።
እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ ባቀረበዉ መልስ አመልካች የግብር ሰብሳቢ በመሆኑ ብቻ ያለምንም ገደብ የግብር ከፊይ ንብረት ላይ ቀዲሚ መብት አለኝ በማለት የሐራጅ ማስታወቂያዉ እንዱታገድና እግደ እንዱነሳ መጠየቅ አይችልም።በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 41(4/ለ) መሰረት በማንኛዉም የፍርድ ሂደት እገዲ በተደረገበት ወይም የአፈጻጸም ትእዛዝ በተሰጠበት ንብረት ላይ የመያዣ ዋስትና መስጠት እንደማይቻል ስለተደነገገ አመልካች በንብረቱ ላይ የቀደምትነት መብት አለኝ በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ የሕግ ድጋፍ የለዉም።በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 39 እና በደቡብ ክልል አዋጅ ቁጥር 166/2009 አንቀጽ 41 በተዘረጋዉ ስርዓት መሰረት ለግብር እዲዉ ንብረቱን በመያዣያነት መያዙን የሚገልጽ ማስረጃ በማቅረብ ሳያስረዲ እንዱሁም በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418/3 መሰረት በንብረቱ ላይ የቀደምትነት መብት እንዲለዉ የሚያሳይ የጽሁፍ ማስረጃ ሳያቀርብ በማንኛዉም ግብር ከፊይ ንብረት ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የቀደምትነት (absolute preemption right) አለኝ ሲል አቤቱታ ማቅረቡ የሕግ መሰረት ስለላለዉ የሥር ፍርድ ቤት አቤቱታዉን ዉድቅ ማድረጉ ተገቢ ነዉ።አመልካች ያቀረበዉ አቤቱታ በስነ ስርዓት ሕጉ መሰረት ሙግት ከተደረገ በኋላ ዉድቅ የተደረገ በመሆኑ ተገቢዉ ሙግት ሳይደረግ ዉድቅ እንደተደረገ በመቁጠር የሰ/መ/ ን በመጥቀስ ያቀረበዉ መከራከሪያም አግባብ አይደለም።በእዲ ምክንያት በፍርድ ቤት የተከበረ ንብረት እንዱሸጥ በተደረገ ጊዜ ንብረቱን ያስከበረዉ ወገን የሚኖረዉ መብት ከሽያጭ ገንዘብ ላይ የቀደምትነት መብት ካላቸዉ ባለገንዘቦች የሚተርፍ ካለ የመዉሰድ መብት ብቻ እንዲለዉ በሰ/መ/ ላይ አስገዲጅ ትርጉም ስለተሰጠና አመልካች በንብረቱ ላይ የቀደምትነት መብት እንዲለዉ በማስረጃ ስላላስረዲ አመልካች ያለዉ መብት እንደማንኛዉም መብት ጠያቂ ለ2ኛ ተጠሪ ተከፍል በሚቀረዉ ገንዘብ ላይ ብቻ ነዉ ተብል በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም።ማንኛዉም ታክስ ከፊይ ታክስ የመክፈል ግዳታዉን ያልተወጣ እንደሆነ ባለስልጣኑ እዲዉን በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ ማስፈጸም የሚፈልግ ከሆነ በዋስትናነት ማስመዝገብና ንብረቱን በማሸጥ ታክሱን እንደሚያስከፍል የሚገልጽ ማስታወቂያ ለታክስ ከፊዩ ይሰጣል ተብል ተደንግጓል እንጂ የግብር ዉሳኔ ማስታወቂያ እንደደረሰዉ የግብር ከፊይ ንብረት ይይዛል የሚል ሕግም ሆነ አሰራር ባለመኖሩ በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ትእዛዝ የተፈጸመ ስህተት የለም ተብል አቤቱታዉ ዉድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክሯል።
ከላይ በአጭሩ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በዚህ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና በስር ፍርድ ቤት የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም አመልካች የቀደምትነት መብት አለኝ በሚል የፍርድ አፈጻጸሙን በመቃወም አቤቱታ ያቀረበዉ 2ኛ ተጠሪ በ1ኛ ተጠሪ ላይ ያስፈረደዉን የገንዘብ ፍርድ ለማስፈጸም 2ኛ ተጠሪ ባስከበረዉ የ1ኛ ተጠሪ ንብረቶች ላይ በ1ኛ ተጠሪ የግብር እዲ ልክ የቀደምትነት መብት አለኝ በሚል እንደሆነ ክርክራቸዉ ያሳያል። 1ኛ ተጠሪ ደግሞ የግብር እዲ ስለላለብኝ የጠቀሳቸዉን ሕጎች መሰረት በማድረግ በንብረቶቹ ላይ የቀደምትነት መብት አለኝ ብል መጠየቅ አይችልም ብል ተከራክሯል።
እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ ደግሞ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈልገዉን እዲ ለማስከበር ንብረቱን ከ2ኛ ተጠሪ አስቀድሞ ያስከበረ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ባለማቅረቡ ይህንን ሳያደርግ ሕግ የቀደምትነት መብት አይሰጠዉም በሚል ተከራክሯል።
በመሰረቱ በፋዳራል ታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 39 እና በደቡብ ክልል የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 166/2009 ስር በተመሳሳይ እንደተደነገገዉ መሰረት ታክስ ሰብሳቢ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በታክስ ሕግ መሰረት ታክስ ከፊዩ መክፈል የሚገባዉ የመክፈያ ጊዜዉ የደረሰ ታክስ በሙለ ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ ባለሥልጣኑ በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ የቀደምትነት መብት አለዉ።በዚህ ድንጋጌ የታክስ ሕግ ተብል የተገለጸዉ በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 2(36) ላይ በተመለከተዉ ትርጓሜ መሰረት የታክስ አስተዲደር አዋጁን ጨምሮ የገቢ ግብር አዋጅ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ፣የሴክሳይዝ ታክስ አዋጅ፣የቴምብር ቀረጥ አዋጅ፣የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ፣የጉምሩክ ሕግ ሳይጨምር ማንኛዉም ታክስ፣ ቀረጥ ወይም ክፍያ የሚጥል ሕግና እነዚህን አዋጆች ለማስፈጸም የሚወጣ ደንብና መመሪያ እንደሆኑ በግልጽ ተመልክቷል።በመሆኑም ታክስ የመጣልና የመሰብሰብ የሥልጣን ክፍፍለን ተከትል የፋዳራል እና የክልል ታክስ ሰብሳቢ ባለሥልጣን የሚሰበስቡት የታክስና የቀረጥ ዓይነት እንዱሁም የእነዚሁ ምንጭ የሆኑ ሕጎች ሉለያዩ የሚችለ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በፋዳራለ ታክስ አስተዲደር አዋጅ አንቀጽ 39(በክልለ አዋጅም በተመሳሳይ እንደተደነገገዉ) መሰረት በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ የቀደምትነት መብት የሚኖረዉ በእነዚህ ሕጎች መሰረት ታክስ ከፊዩ መክፈል የሚገባዉን የመክፈያ ጊዜዉ የደረሰዉን ታክስ ቀረጥና ተያያዥ ክፍያ ለማስከፈል መሆኑ ሉረጋገጥ ይገባል።ይህም ቅቡልነት ያለዉ ዋና ግዳታ መኖሩን(valid principal obligation) መሰረት ያደረገ ነዉ።
ከላይ በተመለከተዉ መሰረት ታክስ ሰብሳቢ ባለስልጣን በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ የሚኖረዉን የቀደምትነት መብት አፈጻጸምና አድማስ ላልች ከታክስ ከፊዩ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች ከሚኖራቸዉ መብት ጋር በማነጻጸር መመርመር እና ያላቸዉን ልዩነት በግልጽ ማወቅ ያስፈልጋል።በዚህ መልኩ በታክስ ከፊይ ሀብት ላይ ታክስ ሰብሳቢዉ ባለስልጣን ያለዉ የቀደምትነት መብት በሕግ ጽንሰ ሐሳብ በእንግሉዝኛዉ Preferential/Preferred Creditor ተብል የሚታወቅ ሲሆን ጥቅል ሀሳቡም በአገራችን የታክስ አስተዲደርና በላልች የታክስ ሕጎች ላይ ጭምር እንደተንጸባረቀዉ በመርህ ደረጃ ገንዘብ ጠያቂ (በታክስ ጉዲይ ታክስ ሰብሳቢ ባለስልጣን) በባለእዲዉ(በታክስ ከፊዩ) ሀብት ላይ ከላልች ከባለዕዲዉ ገንዘብ ከሚጠይቁ ተራ ባለገንዘቦች(unsecured/ordinary creditor) ቅድሚያ እንዱከፈለዉ መብት የሚሰጠዉ ነዉ።እንዱህ አይነት የገንዘብ ጠያቂዎች የቀደምትነት መብት( Preferential/Preferred Creditor) ከባለእዲዉ ሀብት ላይ በቅድሚያ እዲ የማስከፈል መብት እንደመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1386ና ተከታዮቹ ፣በቁጥር 1410ና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ እንዱሁም በላልች የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተደንግጎ ከሚታወቀዉ ከሕግ ወይም ከዉል ከሚመነጨዉ አንድን ንብረት በቀደምትነት መግዛትን (Pre- emption) ከሚመለከተዉ የተለየ ነዉ።
እንዱሁም ከፍርድ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 394/1 እና ከቁጥር 404 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የፍርድ ባለእዲዉ የሆነዉን ታክስ ከፊይ ንብረት ያስከበሩ የፍርድ ባለመብቶች በሕግ የቀደምትነት መብት ከተሰጠዉ ታክስ ሰብሳቢ ባለሥልጣን ጋር የሚኖራቸዉ የመብት ቅደም ተከተል ምን እንደሆነ መመርመር ይገባል።በዚህ መልኩ የሚሰጠዉ ንብረት የማስከበር ትእዛዝ ዓላማዉ የፍርድ ባለዕዲዉ ዕዲዉን ከመክፈለ በፉት ይህንን ንብረት ለላላ ሰዉ እንዲይሰጥ፣እንዲይሸጥ፣እንዲይለዉጥ ወይም በማናቸዉም ላላ ሁኔታ መብቱን ለማንም እንዲያዛዉር ለማገድና የፍርድ ባለእዲዉ እዲዉን መክፈል ካልቻለ ንብረቱን በሐራጅ በማሸጥ በፍርደ መሰረት ለፍርድ ባለገንዘቡ ለመክፈል ቢሆንም በዚህ መልኩ የሚደረገዉ ንብረት ማስከበር በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 3044 መሰረት በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ በፍርድ ከሚቋቋመዉ የመያዣያ መብትን (Judicial mortgage right) የተለየ መሆኑን መገንዘብ ይገባል።ምክንያቱም በፍርድ የሚቋቋም መያዣ አስቀድሞ በፍርድ ቤት ወይም በግልግል ዲኝነት አካል አንደ ተከራካሪ ወገን ለላላዉ ተከራካሪ ወገን እንዱከፍል የተወሰነን የገንዘብ እዲ ለማስፈጸም ዲኝነት ተጠይቆ ተለይቶ በሚታወቅ ንብረት ላይ እዲ ለማስከፈል የሚቋቋም በመሆኑ በፍርድ አፈጻጸም መዝገብ ላይ ንብረት ለማስከበር ከሚሰጥ ትእዛዝ የተለየ በመሆኑ ነዉ።ስለሆነም በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት የፍርድ ባለእዲዉን ንብረት ያስከበረ ሰዉ የቀደምትነት መብት አለኝ ብል ለመጠየቅ እንደሚችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 404 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ አልተደነገገም።
በልላ በኩል በታክስ አስተዲደር አዋጅ አንቀጽ 39(2 እና 7) ላይ እንደተመለከተዉ በታክስ ሰብሳቢዉ ባለስልጣን ታክስ ከፊዩ እንዱከፍል የጠየቀዉ ታክስ ከተከፊይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ የሚከፈል ታክስ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ፣የተርን ኦቨር ታክስ ወይም የኤክሳይስ ታክስ ካልሆነ በስተቀር ባንኮች በንብረቱ ላይ የዋስትና(የመያዣያ) መብት ያቋቋሙት ብድሩን ከመስጠታቸዉ በፉት ታክስ ከፊዩ የታክስ እዲ የላለበት መሆኑን ከታክስ ሰብሳቢ ባለስልጣን አረጋግጠዉ ከሆነ በታክስ ከፊዩ ንብረት ላይ የዋስትና(የመያዣያ) መብት ያቋቋሙ ገንዘብ ጠያቂ ባንኮች (secured creditor) እና ከታክስ ከፊዩ ደመወዝ የሚጠይቁ የታክስ ከፊዩ ተቀጣሪዎች ከታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ ከታክስ ሰብሳቢ ባለስልጣን የቀደመ መብት አላቸዉ።
እንዱሁም ታክስ ከፊዩ ታክስ የመክፈል ግዳታዉን ያልተወጣ እንደሆነ ታክስ ሰብሳቢ ባለስልጣን በሕግ የተሰጠዉን የቀደምትነት መብት በታክስ ከፊዩ ሀብት ላይ የሚጠቀም መሆኑን፣ ያልተከፈለዉን ታክስ እና ታክሱን ለማስከፈል የሚወስደዉ እርምጃ የሚያስከትለዉን ወጪ እንደሚያስከፍለዉና በንብረቱ ላይም የዋስትና መብት እንደሚያስመዘግብ የሚገልጽ ማስታወቂያ ለታክስ ከፊዩ መስጠት እንዲለበት በታክስ አስተዲደር አዋጅ አንቀጽ 39/3 ላይ በግልጽ ተደንግጓል።በተጨማሪም ታክስ ከፊዩ የታክስ ማስጠንቀቂያ በደረሰዉ በ30 ቀናት ዉስጥ ታክሱን አለመክፈለን ምክንያት በማድረግ ታክስ ሰብሳቢዉ ባለሥልጣን የታክስ ከፊዩ ንብረት በማናቸዉም የፍርድ ሂደት እገዲ ተደርጎበት ከሆነ ወይም በንብረቱ ላይ የፍርድ አፈጻጸም ትእዛዝ ተሰጥቶበት ከሆነ ንብረቱ ላይ የተሰጠዉን እግድ ወይም የአፈጻጸም ትእዛዝ ካላስነሳ በስተቀር የታክስ ከፊዩን ንብረት መያዝ (Seizure of Property) እንደማይችል በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 41(4/ለ) ስለተደነገገ የቀደምትነት መብቱን ከመጠቀም ጋር ተያይዞ የታክስ ከፊዩን ንብረት ለመያዝ በንብረቱ ላይ የተሰጠዉን የፍርድ ቤት እግድ ወይም የፍርድ አፈጻጸም ትእዛዝ አሰቀድሞ ማስነሳት ይጠበቅበታል።
በተያዘዉ ጉዲይ 2ኛ ተጠሪ በ1ኛ ተጠሪ ላይ ያስፈረደዉን ፍርድ ለማስፈጸም የ1ኛ ተጠሪን ንብረት ያስከበረ ተከራካሪ ወገን እንደመሆኑ ያለዉ መብት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ 394/1፣ቁጥር 404 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት እግደን የሰጠዉ ፍርድ ቤት እግደን እስካላነሳ ድረስ ያስከበረዉን ንብረት 1ኛ ተጠሪ ዕዲዉን ከመክፈለ በፉት ለላላ ሰዉ እንዲይሰጥ፣ እንዲይሸጥ፣ እንዲይለዉጥ ወይም በማናቸዉም ላላ ሁኔታ መብቱን ለማንም እንዲያዛዉር አስከብሮ ማቆየትና የፍርድ ባለእዲዉ እዲዉን መክፈል ካልቻለ ንብረቱ በሐራጅ ተሸጦ ገንዘቡ እንዱከፈለዉ መጠየቅ ነዉ። ከዚህ ዉጭ የፍርድ ባለእዲውን በዚህ አግባብ ማስከበሩ ንብረቱ ከመከበሩ ወይም ከመያዙ በፉት በንብረቱ ላይ መብት የነበራቸዉና በክርክሩ ዉስጥ የላለ የሦስተኛ ወገኖች በሕግ፣በፍርድ ወይም በዉል በንብረቶቹ ላይ ያቋቋሙትን የቀደምትነት መብት የሚነካ አይደለም። ከያዝነዉ ጉዲይ ጋር በተያያዘ አመልካች በፋዳራልም ሆነ በክልል የታክስ አስተዲደር አዋጆች ላይ በተመሳሳይ በተደነገገዉ መሰረት 1ኛ ተጠሪ አልከፈለም ብል ንብረቱን ይዞ በመሸጥ ለማስከፈል የፈለገዉ የክልለን ታክስ የታክስ አስተዲደር አዋጅን ጨምሮ ከገቢ ግብር አዋጅ፣ከተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ፣ከሲክሳይዝ ታክስ አዋጅ፣ከቴምብር ቀረጥ አዋጅ፣ከተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ፣የጉምሩክ ሕግ ሳይጨምር ማንኛዉም ታክስ፣ ቀረጥ ወይም ክፍያ የሚጥል ሕግና እነዚህን አዋጆች ለማስፈጸም ከወጣ ደንብና መመሪያ የመነጨ መሆኑን እስካረጋገጠ ድረስ በ1ኛ ተጠሪ ንብረት ላይ ከ2ኛ ተጠሪ ቀድሞ ንብረቱን በመሸጥ ያለተከፈለዉን ታክስና ቀረጥ የማስከፈል በሕግ ጥበቃ የተደረገለት መብት አለዉ። ነገር ግን አመልካች 1ኛ ተጠሪ እንዱከፍለዉ የጠየቀዉ ታክስና ቀረጥ አንዱሁም ተያያዥ ክፍያ በዝርዝር ከተጠቀሱ ሕግጋት የመነጩ መሆናቸዉን እና በሥልጣኑ ክልል ዉስጥ የሚገኝ ታክስና ቀረጥ መሆኑን በልላ አገላለጽ ቅቡልነት ያለዉ ዋና ግዳታ መኖሩን(valid principal obligation) ማስረዲት እና ፍርድ ቤቶችም ማስረዲቱን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።ሆኖም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ ያየዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 418 በሚጠይቀዉ የክርክር አመራር መሰረት ከዚህ አኳያ የግራ ቀኙን ክርክር ካለመመርመራቸዉም በተጨማሪ ፍሬ ነገሮቹን ከሕግና ከማስረጃ አንጻር አለማጣራታቸዉን ተገንዝበናል።
እንዱሁም በሕግ የተሰጠዉን የቀደምትነት መብት በ1ኛ ተጠሪ ሀብት ላይ የሚጠቀም መሆኑን፣ ያልተከፈለዉን ታክስ እና ታክሱን ለማስከፈል የሚወስደዉ እርምጃ የሚያስከትለዉን ወጪ
No topics extracted.