እግድ እንዱነሳ አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅራቢው እግደ እንዱነሳ ያቀረበው ምክንያት ግልፅ በማድረግ በቂ ምክንያት መኖሩን ባላሳየበት ሁኔታ የቀረበው ምክንያት በቂ ነው በማለት ተቀብል እግድን ማንሳት የማይገባ ስለመሆኑ የፍትሀ ብሄር ስነ ስርአት ህግ ቁጥር 158
No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት ተጠሪ፡- የድሬ ዲዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ተሰጥቶ የነበረው እግድ እንዱነሳ በስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰጠቱና ይህ ትዕዛዝ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ መፅናቱ በስር ፍርድ ቤቶች የተፈፀመን መሰረታዊ የህግ ስህተት የሚያሳይ በመሆኑ በሰበር ሰሚ ችልቱ ሉታረም ይገባል በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ መሰረት በማድረግ ሲሆን አመልካች በፋ/መ/ደረጃ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስም ንብረትነቱ የአመልካች የሆነውን በድሬዲዋ ከተማ ቀበላ 03 የሚገኘውን የቤት ቁጥር 2362 የሆነውን ቤት አከራይተን ተከራዩ በቤቱ ላይ እድሳት በማድረግ ላይ እያለ ተጠሪ በቤቱ ላይ አንዲችም መብት ሳይኖረው ተከራዩ በቤቱ ላይ እድሳት እንዲያደርግና እንዲይገለገል በማድረግ ሁከት የፈጠረ በመሆኑ ሁከቱ እንዱወገድ ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን ይህንን ተከትልም ተጠሪ ቤቱን ለቃችሁ እንድታስረክቡ በማለት አስገድድኛል በማለት አመልካች የእግድ ትዕዛዝ እንዱሰጥለት ጠይቆ በ29/11/2012 ዓም ፍርድ ቤቱ የእግድ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ከዚህ በማስከተልም ተጠሪ ጳጉሜ 03 ቀን 2012 ዓም በተፃፈ አቤቱታ ክርክር የተነሳበት ቤት ለጅቡቲ ፕሬዝዲንት መኖሪያ ቤት ለማስፊፉያነት እንዱጠቀምበት የተሰጠ መሆኑን በመግለፅ እግደ እንዱነሳለት ያመለከተ ሲሆን አመልካች መስከረም 04 ቀን 2013 ዓም በተሰጠ ምላሽ የድሬዲዋ አስተዲደር ካቢኔ የድርጅቱን ንብረት አስመልክቶ ውሳኔ ማሳረፍ የማይችል መሆኑን፤የከተማ አስተዲደር ከላላ ሀገር ጋር የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ በቀጥታ የዱፕልማቲክ ግንኙነት ለማድረግ የማይችል መሆኑን በመጥቀስ ቢከራከርም ፍርድ ቤቱ መስከረም 04 ቀን 2013 ዓም በዋለው ችልት በሰጠው ትዕዛዝ የከተማውን ይዞታ በአግባቡ የማልማትና የማስተዲደር ስልጣኑ የአስተዲደሩ መሆኑን ፤ ለንብረቱ ተገቢው ካሳ የተወሰነ በመሆኑ ካሳው በቂ ካልሆነ በመጠኑ ላይ ቅሬታ ከማቅረብ ባለፈ ይዞታውን አላስረክብም ለማለት ስለማይችል እግደ ሉነሳ ይገባል በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.154 መሰረት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ትዕዛዝ ቅር ተሰኝተው ይግባኛቸውን ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝም በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ትዕዛዝ ጉድለት የለበትም በማለት አቤቱታውን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ ባቀረበው የሰበር አቤቱታም አመልካች ድርጅት የተቋቋመው በሁለቱ ሀገሮች ስምምነት ሆኖ የድርጅቱን ንብረትና ይዞታ ለመጠበቅ በ1973 ዓም እና 1989 ዓም ግዳታ ገብተው ግዳታው ሉጠናቀቅ 14 አመት የሚቀረው ሆኖ እያለ ይህ ስምምነት በህገ መንግስቱ አንቀፅ 9(4) መሰረት የሀገሪቱ የህግ አካል ተደርጎ የሚወሰድ ሆኖ እያለ ተጠሪ በቤቱ ላይ ከህግም ሆነ ከውል የመነጨ መብት ሳይኖረው እግድ በማንሳት በንብረቱ ላይ ጉዲት እንዱያደርስ በመፈቀድ ለካቢኔ ውሳኔ ከአለም አቀፍ ስምምነት እና ከህገ መንግስቱ ቅድሚያ በመስጠት የተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
የከተማ አስተዲደሩ በአለም አቀፍ ግንኙነት ላይ በቀጥታ ተሳታፉ ለመሆን ስምምነቶችንም ለማድረግ የሚያስችል ህገ መንግስታዊ ስልጣን የላለው ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው፤ተጠሪ የፈፀመው ቤቱን ለጅቡቲ ፕሬዝዲንት ማስፊፉያነት በማለት በማፍረስ መስጠት ለህዝብ ጥቅም ልባል የማይችል አዋጅ ቁጥር 455/1997ኝን የሚጣረስ ሆኖ እያለ የእግደም መነሳት የክርክሩን መቋጨት የሚያስከትል ሆኖ እያለ እግደ እንዱነሳ መታዘዙ መሰረታዊ የህግ ስህተት በስር ፍርድ ቤቶች መፈፀሙን ስለሚሳይ መዝገቡ ገና በቀጠሮ ላይ እያለ የመጨረሻ ውሳኔ አይነት ትእዛዝ መሰጠቱ አግባብ ስላልሆነ ትእዛዙ ተሸሮ ሁከት እንዱወገድ ትዕዛዝ ይሰጥልን፤ተጠሪ የድርጅቱን ንብረት በመስበር እየፈፀመ ያለው ተግባር ህገ ወጥ ስለሆነ በግቢው ውስጥ ያሰማራቸውን ግለሰቦች እንዱያወጣ ለቀበላ 03 አስተዲደር ፅ/ቤትና ለከዚራ ፖሉስ ጣቢያ ትዕዛዝ ይሰጥልን በማለት አመልክቷል።
በስር ፍርድ ቤት የቀረበው የሁከት ይወገድልኝ ክርክር የመጨረሻ ውሳኔ ባላገኘበት ሁኔታ አላስረክብም ማለት አትችልም በማለት እግደ እንዱነሳ ትዕዛዝ የተሰጠበትን አግባብ ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ለተጠሪ መጥሪያ ደርሶት ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓም የተፃፈ መልሱን አቅርቧል።
ተጠሪ በዚህ መልሱም ክልልች በክልላቸው የሚገኝን በማንኛውም አካል የተያዘን ይዞታ ፋደራል መንግስት በሚያወጣው ህግ መሰረት ሀገራዊ ፊይዲ ላላቸው ጉዲዮች፤ለኤምባሲዎች፤ለህዝብ ጥቅም ወይም ለተሻለ ልማት ወይም መንግስት ለሚያካሂደው የልማት ስራ አስፈላጊ ሆኖ ካመነበት ይዞታውን በማስለቀቅ ለታሰበው አላማ የማዋል ስልጣን እና ሃላፉነት የተሰጣቸው መሆኑ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 52(2)(መ) እና በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 12 እና 26(3) እንዱሁም በካሳ አዋጅ ቁጥር 1161/2011 አንቀፅ 5 የተመለከተ ሲሆን 1973 እና 1989 በተደረገው ስምምነት አንቀፅ 3 ሁለቱ መንግስታት በየግዛታቸው በሚገኙ የምድር ባቡር ድርጅት መኖሪያ ቤቶች ሀዱድችና ጣቢያዎች ወዘተ መጠቀም እንደሚችለ የሚደነግግ በመሆኑ የአዱስ አበባ መስተዲደርም በዚሁ አግባብ የድርጅቱን ንብረቶች ለልማት እያዋለው በመሆኑ አመልካች የካሳ ግምቱ በቂ አይደለም የሚለ ከሆነ ለተገቢው አካል ከማመልከት ውጪ ካቢኔው የወሰነውን ይዞታ አላስረክብም ለማለት አይችለም፤ተጠሪ ይዞታን ለማስለቀቅ የሚችለው ለህዝብ ጥቅም ብቻ ነው በማለት አመልካች ያቀረበው ክርከር የሉዝ አዋጁን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ለይዞታው ካሳ እንዱከፈል የተወሰነ በመሆኑ፤የእግደ መነሳት የክርክሩን መቋጨት የሚያስከትል ባለመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትእዛዝ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክሯል።አመልካች የመልስ መልሱን በማቅረብ ክርክሩን አጠናክሯል።
በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ፣ ከተገቢው ህግና፤ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረነዋል።አመልካች በተጠሪ ላይ ክሱን ያቀረበው ክርክር የተነሳበትን ቤት አከራይቶ የመጠቀም መብቱን በመተላለፍ ቤቱን የተከራየው ሰው ቤቱን እንዲያድሰና እንዲይገለገል በአካልና ደብዲቤ በመፃፍ ሁከት የፈጠረ መሆኑን በመግለፅ ሁከቱ እንዱወገድ በመጠየቅ ሲሆን በዚህ አግባብ ክርክሩ እየተመራ ባለበት ተጠሪ በ28/11/2012 ዓም በተፃፈ ደብዲቤ ቤቱን በ7 ቀናት ውስጥ ለቀው እንዱያስረክቡ መጠየቁን መነሻ በማድረግ እግድ እንዱሰጥለት ጠይቆ በዚሁ አግባብም የእግድ ትዕዛዝ መሰጠቱን የግራ ቀኙ የስር ፍርድ ቤት ክርክር ያሳያል።
በመሰረቱ ይህ የእግድ ትዕዛዝ የተሰጠው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.154(ሀ) አግባብ በመሆኑ የእግድ ትዕዛዙ መነሻ ተጠሪ ንብረቱን ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ እያደረገ ያለው ጥረት እግድ ትዕዛዝ ሳይሰጥበት እንዱቀጥል ቢደረግ በዋናው ጉዲይ የተያዘው የሁከት ይወገድልኝ ክርክር ዋጋ የሚያጣ መሆኑን መነሻ በማድረግ መሆኑን ከግራ ቀኙ ክርክርና ፍርድ ቤቱ ይህንን ተከትል ከተሰጠው ትዕዛዝ ይዘት ለመረዲት ይቻላል።ፍርድ ቤቱ ለአመልካች በአቤቱታው መሰረት የእግድ ትዕዛዙን የሰጠው እግደን ለመስጠት የሚያስችል በቂ ምክንያት ቀርቦለት በመሆኑ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.158 እግደን ሉያነሳ የሚችለው በህጉ በግልፅ እንደተመለከተው እግደ እንዱነሳ የቀረበው “…አቤቱታ በቂ ምክንያት የሚያስገኝ መሆኑን …”ያረጋገጠ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ላሆን እንደሚገባ ከድንጋጌው ይዘት ለመረዲት ይቻላል።
እግደ በስር ፍርድ ቤት የተነሳው የተሰጠውን የእግድ ትዕዛዝ ለማስነሳት የሚያስችል በቂ ምክንያት ቀርቦ መሆን አለመሆኑን ስንመረምረውም ተጠሪ እግደ እንዱነሳለት የጠየቀው ክርክር የተነሳበት ቦታ ለጅቡቲ ፕሬዝደንት መኖሪያ ቤት ማስፊፉያ በካቢኔ ውሳኔ መሰጠቱን መነሻ በማድረግ ሲሆን ተጠሪ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ባቀረቡት መልስም የእግደ መቀጠል “…በኢትዮጲያና በጅቡቲ መንግስታት መካከል የነበረውን የረዥም አመታት የጉርብትና ታሪክና መልካም ግንኙነት 3000 ካሜ በማይሞላ ቦታ ምክንያት…”ሉያበላሸው ስለሚችል እግደ ሉነሳ ይገባል በማለት የተከራከሩ ቢሆንም ይህ ምክንያት በምን አግባብ ክርክሩ ሳይጠናቀቅ እግደን ለማንሳት በቂ ምክንያት እንደሆነ ግልፅ ያላደረገ ሲሆን ክርክሩ በህጉ አግባብ ተመርቶ በተገቢው ጊዜ እልባት እስኪሰጠው ጊዜ ድረስ የእግደ መቀጠል በምን አግባብ የሀገራቱን የጉርብትና ታሪክና መልካም ግንኙነት እንደሚያበላሽ ተጠሪ ግልፅ በማድረግ እግደ እንዱነሳለት ያቀረበው ምክንያት በቂ ምክንያት መሆኑን ባላሳየበት ፍርድ ቤቱ በተጠሪ የቀረበውን ምክንያት በቂ ነው በማለት ተቀብል እግደን ማንሳቱ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.158ን መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ እያለ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ይህንኑ ሉያርም ሲገባ ማፅናቱ አግባብ ሆኖ ስላልተገኘ ተከታዪን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ድሬዲዋ ምድብ ችልት በመ/ቁ.78425 በ04/01/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት በ15/11/2012 ዓም የሰጠውን የእግድ ትዕዛዝ በማንሳት የሰጠው ትዕዛዝና ይህንን ትዕዛዝ በማፅናት ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በመ/ቁ.17124 በ15/01/2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348(1) መሰረት ተሸረዋል።
በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ.78425 በ15/11/2012 ዓም የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ በግራ ቀኙ መሃል የተያዘው ክርክር በስር ፍርድ ቤት ተገቢውን እልባት እስኪያገኝ ድረስ ወይም በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.158 እግደን ለማንሳት የሚያስችል በቂ ምክንያት ቀርቦ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት አግኝቶ እግደ እንዱነሳ ተገቢው ትዕዛዝ እስኪሰጥበት ድረስ ፀንቶ ሉቆይ ይገባል ብለናል።
ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
ጉዲዩ ተገቢውን እልባት ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል።ይመለስ።
No topics extracted.