የጣልቃ ገብነትን አቤቱታ ለመቀበል በቀደመው በሁለት ተከራካሪ ወገኖች መካከል በተጀመረው ሙግትና በኋላም በሚሰጠው ውሳኔ አፈፃፀም ጣልቃ ገብ ሆኖ መከራከር የሚፈልግ ሰው ጥቅሙ ይነካል ወይስ አይነካም የሚለው መሰረታዊ መስፈርት በመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት ሉያገኝ የሚችለው መብት የሚነካ መሆኑ ሲረጋገጥ፤ አቶ ዘውድነህ አባተ እና ወ/ሮ ከበቡሽ ጋሻው የተለየና ቀደም ሲል ከተጀመረው ክርክር የማይጣጣም አዱስ ጭብጥና የግል የዲኝነት ጥያቄ ይዞ ያልቀረበ ሲሆን ብቻ ስለመሆኑ የፍትሀ ብሄር ስነ ስርአት ህግ ቁጥር 41
No summary available.
መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ ዘውድነህ አባተ መኮንን ተጠሪ፡- ወ/ሮ ከበቡሽ ጋሻው ተገኝ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የሁከት ይወገድ ክርክርን የተመለከተ ሲሆን አመልካች በስር ፍ/ቤት ከሳሽ እና ተከሳሽ በሚያደርጉት ክርክር ጣልቃ ገብቼ እንድከራከር ይፈቀድልኝ በማለት ያቀረቡትን ክስ መነሻ ያደረገ ሲሆን አመልካች በፋደራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት የጣልቃ ገብነት አቤቱታም የስር ከሳሽ እና ተከሳሽ የሚከራከሩበት በቦላ ክ/ከ/ወ/10 የቤት ቁጥር አዱስ የሆነው ቤት አመልካች ጳጉሜ 01 ቀን 2008 ዓ.ም በተጻፈ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል ስምምነት በሰነድች ማረጋጋጫና ምዝገባ ጽ/ቤት በቁ/ቅ8/283/2ለ/2008 በ01/13/08 ዓ.ም የስር ተከሳሽ ቤቱን እና ቤቱን የተመለከቱ ሰነድችን ሽጦልኝ እና አስረክቦኝ በቤቱ በመጠቀም ላይ ስለምገኝ ክርክር ለተነሰበት ቤት ባለቤት እና ባለመብት ስለሆንኩ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 41(2) መሰረት ጣልቃ ገብቼ መከራከር ይገባኛል በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በሰጡት መልስ ጣልቃ ገብ ያያያዙት ማስረጃ ውል ከስር ተከሳሽ ጋር ውል እንደተዋዋለ ያስረዲል እንጂ የይዞታ ማረጋጋጫውና የግንባታ ፍቃደ አሁንም በስር ተከሳሽ በአቶ ደረጀ ደፊሩ ስም መሆኑን ከቀረበው ማስረጃ መረዲት ይቻላል ክርክሩም አቶ ደረጀ ደፊሩ የተጠሪን አጥር በማፍረስ እና በግቢዬ ላይ መንገድ በማውጣት የፈጠረውን ሁከት እንዱወገድልኝ በማለት አቤቱታ አቀረብኩ እንጂ የአመልካችን መብት አልነካሁም በማለት ተከራክረዋል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት አመልካች ባቀረቡት የጣልቃ ገብ አቤቱታ ላይ የተጠሪን አስተያያት በመቀበል በሰጠው ብይን ተጠሪ እና የስር ተከሳሽ የሚከራከሩበት ቤት አመልካች ከስር ተከሳሽ የገዛሁት ቤት ነው በማለት የባለቤትነትን አቤቱታ ማቅረባቸውን፤ ተጠሪ በስር ተከሳሽ ላይ የሁከት ይወገድልኝ ክስ አቅርቦ እያለ እና ሁከቱም ተፈጠረብኝ ያለው በተጠሪ መኖሪያ ቤት ላይ ሆኖ እያለ አመልካች ደግሞ በስር ተከሳሽ የመኖሪያ ቤት ክርክር የባለቤትነት ክርክር እንዱያደርጉ ጣልቃ እንዱገቡ መጠያቃቸው አግባብነት የላለው እና ተጠሪ ከቀረበው ክስ ጋር ተመሳሳይነት የላለው እና የአመልካችንም መብትና ጥቅም የሚነካ ስላልሆነ አመልካች በጉዲዪ ላይ ጣልቃ ገብቶ የሚከራከርበት የህግ አግባብ የለም በማለት አቤቱታው በብይን ውድቅ አድርጎታል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካች ከስር ተከሳሽ ላይ የካርታ ቁጥር 10/55/4/12/36823/00 የሆነ ቤት ገዛሁ ቢለም ክርክር ባስነሰው ይዞታ /መንገድ/ ላይ ያላቸውን መብትና ጥቅም አላስረደም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።
አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም በፋደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍ/ቤት ተከሳሽ እና ተጠሪዋ አጎራባች መሆናቸውን፣ ተከሳሽ ሁከት ፈጠሩበት የተባለውን ቤት ለአመልካች ሽጠውልኝ የተከሳሽ መብትና ግዳታ ሁለ ጳጉሜ 1 ቀን 2008 ዓም ቤቱን ገዝቼ ወደኔ እንዱዛወር ማድረጌ፤ የስር ተከሳሽም ሆነ አመልካች በላለንበት ክርክሩ ተሰምቶ ውሳኔ ቢሰጥ በተለይ በአመልካች ላይ ሉመለስ የማይችል ጉዲት ሉደርስብኝ ስለሚችል ወደ ክርክሩ ጣልቃ በመግባት ተጠሪዋ በቤቱ ባለቤት በነበሩት አቶ ደረጀ ደፊሩ ላይ የመሰረቱት የሁከት ይወገድልኝ ክስ የተሳሳተና በአንፃሩ ሁከት ፈጥረው በመካከለችን 8 ሜትር መንገድ ዘግተው መውጫ መግቢያ ያሰጡኝና ሕገ ወጥ ግንባታ ያደረጉት ሁከትም የፈጠሩት ተጠሪዋ ራሳቸው መሆናቸውን አስረድቼ ክሱ እንዲላዘጋ ወደ ክርክሩ አትገቢም መባላ አግባብ አይደለም፤
አመልካች ሁከት ተፈጠረብኝ የሚለትን መንገድ ዘግተው ከተፈቀደላቸው ይዞታ አልፈው የፈጸሙት ግንባታ ሕገ ወጥ በመሆኑ ግንባታውን እንዱያቆሙ መስተዲድሩ በስልጣኑ መሰረት ሕጋዊ ትዕዛዝ መስጠቱ ሁከት አንደማያሰኘው ማስረዲት እንድችል ጣልቃ ሳያስገባኝ በክርክሩ መብትና ጥቅም የለውም በማለት የሰጠው ፍርድ እና የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ክርክር ከተነሳበት ንብረት ጋር ግንኙነትና መብት ያለው አመልካች በማስረጃ የተደገፈ ጥያቄ ካቀረበ ወደ ክርክሩ ገብቶ ሙግቱን እንዱያቀርብ መፍቀድ ይገባዋል እንጂ ፍ/ቤቶች ላላ ምክንያት በመስጠት ክርክሩን እንዲያቀርብ ሉያግደ አይገባም በማለት የሰጠው አስገዲጅ ውሳኔ መሰረት ያላደረገ በመሆኑ የተሰጠው ብይን መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ እንዱሻርልኝ በማለት አመልክተዋል።
የስር ተከሳሽ የነበሩት ግለሰብ የነበራቸውን ቤት እና ይዞታ ለአሁን አመልካች በሽያጭ አስተላልፈዋል በተባለበት እና የስር ተከሳሽ በአሁኗ ተጠሪ ይዞታ ላይ ሁከት ፈጥረዋል የተባለው ከዚሁ ለአመልካቹ ካስተላለፈት ይዞታ ጋር በተያያዘ ሁኔታ መሆኑ በተገለጸበት ሁኔታ እንዱሁም በክርክሩ መጨረሻ የሚሰጠው ውሳኔ የአመልካቹን መብትና ጥቅም ሉነካ እንደሚችል ግምት መውሰድ በሚቻልበት ሁኔታ አመልካች በጣልቃ ገብነት ገብተው ለመከራከር ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ የመደረጉ አግባብ ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ተጠሪ በሰጡት መልስ አመልካች ከገዙት ቤት ካርታ ላይ ያልተመለከተ እና ተያያዥነት የላለው ሲሆን በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር መንገድች ባለስልጣን የመንገድ ፕላን የላለውና ገና ለወደፉት ምን አልባት አስፈቅዲለሁ ብለው የገመቱትን ቤት መንገድ እንጂ በአሁኑ ደረጃም ሆነ ከመግዛታቸውም በፉት ከገዙም በኋላ መንገድ ነው ተብል የተሰጠው ፕላን እውቅና የለውም።
በአጠቃላይ አመልካች የጣልቃ ልግባ ጥያቄ ያቀረቡበት ጉዲይ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ሁከት ይወገድልኝ በማለት ካቀረብኩበት አቤቱታ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የላለበት እና የአመልካችን መብትና ጥቅምን የማይነካ በመሆኑ መብትና ጥቅም ስለላለው በክርከሩ ጣልቃ መግባት የለብህም ተብል የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ያለውና የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ባለመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱፀናልኝ በማለት ተከራክረዋል። አመልካች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል።
በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ፣ ከተገቢው ህግና፤ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረነዋል።
በመሰረቱ ከክርክር አመራር መርህ አንፃር የክርክሩን አድማስ ቅጥ የለሽ የሚያደርጉትን እና መዘግየትን የሚያስከትለ አዲዱስ ጭብጦችን በማስቀረት ለጉዲዩ መጨረሻ እንዱኖረው ማድረግ የአንድ ፍርድ ቤት መሰረታዊ ግዳታው ነው።በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.41 መሰረት የጣልቃ ገብነት አቤቱታ ያቀረበው ወገን በተጀመረው ክርክር መብት ወይም ጥቅም ያለው መሆኑ መረጋገጡ ግዳታ ቢሆንም ጣልቃ ገብ እንዱሆን የተፈቀደለት ወገን ፍፁም የተለየና ቀደም ሲል ከተጀመረው ክርክር የማይጣጣም አዱስ ጭብጥና ጥያቄ ይዞ እንዱቀርብ ግን ሉፈቀድለት አይገባም።የግለን የዲኝነት ጥያቄ ይዞ የሚቀርብ አቤቱታ አቅራቢ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.41 መሰረት ጣልቃ ገብ ሆኖ እንዱከራከር ሉፈቀድለት የሚችልበት የህግ አግባብ አይኖርም።
የጣልቃ ገብነትን አቤቱታ ለመቀበል በሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች መካከል በተጀመረው ሙግትና በኋላም በሚሰጠው ውሳኔ አፈፃፀም ጣልቃ ገብ ሆኖ መከራከር የሚፈልገው ጥቅሙ ይነካል?ወይስ አይነካም ?የሚለው መሰረታዊ መስፈርት በመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት ሉያገኝ የሚችለው በክርክሩና ክርክሩን ተከትል በተሰጠው ውሳኔ አፈፃፀም ወቅት መብቱ የሚነካ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።አሁን በያዝነው ጉዲይ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ እደተመለከተው ተጠሪ በስር ተከሳሽ ላይ በስር ፍርድ ቤት ክሱን ያቀረቡት በጊቢዬ ውስጥ የማከናውነውን ግንባታ ግቢዬ ውስጥ በመግባት እንዲልገባና እንዲልጠቀም አድርጎኛል በዚህም የሁከት ተገባር ፈፅሟል በማለት የስር ተከሳሽ የግል የሆነው የሁከት ተግባር እንዱወገድላቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቀረበው ክስ በተገቢው ማስረጃ ቢረጋገጥ እንኳ ለጉዲዩ የሚሰጠው የስር ተከሳሽ ፈፀሙት የተባለውን ድርጊት ብቻ መሰረት የሚያደርግ በመሆኑ አመልካች በተጠሪ በስር ፍርድ ቤት የቀረበውን ክስ መሰረት ያደረገው ክርክር መብትና ጥቅሜን የሚነካ ነው በማለት ጣልቃ ለመግባት መጠየቃቸው የሚያሳምን ሆኖ አልተገኘም።
በአጠቃላይ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ የስር ተከሳሽ ፈፀመ ያለትን የሁከት ተግባር መሰረት ያደረገ በመሆኑ አመልካች ደግሞ ወደ ክርክር ጣልቃ ለመግባት መነሻ ያደረጉት በግዢ አገኘሁ የሚለትን ቤትና ይዞታ አስመልክቶ የመፊለም ክስን መሰረት በማድረግ ውሳኔው በቤቱ ላይ ያለኝን መብት ያጣብባል በማለት በመሆኑ አመልካች በቤትና በቦታው ላይ አለኝ የሚለት መብት የስር ተከሳሽን የግል ተግባር መሰረት አድርጎ የቀረበን ክስ መርምሮ ለሁከት ይወገድልኝ ክስ ተገቢውን እልባት በሚሰጠው የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሉጣበብ የሚችልበት የህግ አግባብ ባለመኖሩ የስር የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ይህንኑ መሰረት በማድረግ የአመልካችን የጣልቃ ገብነት አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ ህጉን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ፤ጉዲዩን በይግባኝ ያየው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የአመልካች የጣልቃ ገብነት አቤቱታው ተመርምሮ ጉዲዩ እልባት ባላገኘበት ወደ ፍሬ ጉዲዩ ክርክር በመግባት የስር ተከሳሽ የላላቸውን መብት ለአመልካች ሉያተላለፈ አይችለም በማለት የስር ተከሳሽን የግል ተግባር መነሻ በማድረግ በቀረበው የሁከት ይወገድልኝ ክርክር ላይ አመልካች ክርክር ባስነሳው ይዞታ ላይ መብትና ጥቅም የላቸውም በማለት መወሰኑ አግባብ ባይሆንም ከውጤት አንፃር የስር ፍርድ ቤትን ብይን ማፅናቱ አግባብ በመሆኑ ተከታዪን ውሳኔ ሰጥተናል።
1.የፍደራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 16/07/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 03/02/2012 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ ከውጤት አንፃር በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348(1) መሰረት ፀንተዋል።
2.በዚህ መዝገብ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 332 መሰረት በቀን 14/2/2012 ዓ.ም የተሰጠው ዕግድ ተነስቷል። ይጻፍ።
3.ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.