በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ ዲግም ክስ ክልከላ ተፈፃሚነት በተከራካሪ ወገኖች በግልፅ ዲኝነት ተጠይቆበት ፍርድ ቤት በዝምታ ባለፈው ጉዲይ ላይ ጭምር ሲሆን ሆኖም በግልፅ ዲኝነት በተጠየቀበት ላይ ፍርድ ቤት እነ አቶ ሀጎስ ገ/ሂይወት (3 ሰዎች) እና የካቲት 26/2012 ዓ.ም 31 የከለከለው መሆን ያለመሆኑ ከላላኛው ተከራካሪ ወገን ከቀረበው ክርክር እና ጥያቄ ጋር ተገናዝቦ መታየት ያለበትና ተከሳሽ ወገን በግልፅ ክድ ሉከራከርበት የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 5(3) እነ መ/ር ሀጎስ በርሀ (2 ሰዎች) 8. ያለፈበት ይግባኝ/የሰበር አቤቱታ/ ቀርቦ እንዱታይለት አቤቱታ የሚያቀርብ ሰው ከአቤቱታው ጋር ጊዜው ሉያልፍ የቻለበትን ምክንያት የሚገልፁ ማስረጃዎቹን ማቅረብና እነኚህ ማስረጃዎቹም ይግባኙ/የሰበር አቤቱታው/ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ያልቀረበበትን ምክንያት የሚገልፁ እና ውሳኔም እንዱሰጥበት በቂ ሆነው መገኘት ያለባቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.352 እና የተሻሻለው የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 216/2011 አንቀፅ 27(2)
No summary available.
መጋቢት 29/2013 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡ አቶ በዲዲ ኤጄርሳ ተጠሪ፡ አቶ ቦከና ጉርሙ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ጊዜ ያለፈበት የሰበር አቤቱታ ይቅረብልኝ አቤቱታን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቀ/318798 ላይ መስከረም 27/2012 ዓ.ም በዋለው ችልት በአሁን አመልካች የቀረበለትን “ጊዜው ያለፈበት የሰበር አቤቱታ ላቅርብ” የማስፈቀጃ ጥያቄን አስመልክቶ በቂ ምክንያት አልቀረበበትም በማለት ውድቅ ያደረገበት ትዕዛዝ “መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው” በማለት ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የማስፈቀጃ ጥያቄውን ያቀረቡት ቀደም ሲል ስራ ላይ በነበረው ህግ መሰረት የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜ ሶስት ወር ሲሆን ተሻሽል በወጣው የክልለ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 216/2011 መሰረት ጊዜው ወደ ሁለት ወር ዝቅ ስለመደረጉ አላውቅም ነበር የሚል ነው። ችልቱም ምክንያቱ በቂ አይደለም ሲል ውድቅ አድርጓል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ላይ ነው። አመልካች ጥቅምት 05/2012 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በክልለ ሰበር ሰሚ ችል ተፈፅሟል ያለትም መሰረታዊ የህግ ስህተተ ጠቅሰው በዚሁ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። ፍሬ ቃለም በገጠር የምኖር አርሶ አደር በመሆኔ እና የክልል ህግጋት እንኳንስ በገጠር በከተማም ተደራሽ ባለመሆናቸው አዱሱ ህግ ስለመውጣቱ አላውቅም፤ የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜም ያለፈው በዚሁ ምክንያት ስለመሆኑ ገልጬ እያለ በቂ ምክንያት አልቀረበም በሚል ምክንያት የማስፈቀጃ አቤቱታዬ ውድቅ መደረጉ አግባብ ባለመሆኑ ትዕዛዙ ተሽሮ የሰበር አቤቱታዬ ቀርቦ እንዱታይ ሉወሰን ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተምርምሮ ያስቀርባል በመባለ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ይህ ችልትም ጉዲዩን መርምሯል። በዚሁ መሰረት በተሻሻለው የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 216/2011 አንቀፅ 27(2) መሰረት የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜ ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው የመጨረሻ ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባለት ተከታታይ 60(ስድሳ) ቀናት ውስጥ እንደሆነ ተደንግጓል። ይህ ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ተቀባይነት የላላቸው ስለመሆኑ ከመደንገጉ ውጭ ጊዜ ያለፈበት የሰበር አቤቱታ ቀርቦ ላታይ ስለሚቻልበት ሁኔታ አዋጁ የደነገገው ነገር የለም። በልላ በኩል እስከ አሁን ድርስ በፋዳራልም ሆነ በክልል ደረጃ ወጥቶ ተግባራዊ የተደረገ ልዩ የሰበር ሰሚ ችልት የሥነ ሥርዓት ህግ ባለመኖሩ እየተሰራበት ያለው በመደበኛው የፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ነው።
እስከ አሁን ስራ ላይ ባለው የ1958ቱ የፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ መሰረት ጊዜ ያለፈበት ይግባኝ/የሰበር አቤቱታ/ ቀርቦ እንዱታይለት አቤቱታ የሚያቀርብ ሰው ከአቤቱታው ጋር ጊዜው ሉያልፈ የቻለበትን ምክንያት የሚገልፁ ማስረጃዎችን ማቅረብ ያለበት መሆኑን እና ማስረጃዎቹም ይግባኙ/የሰበር አቤቱታው/ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ያልቀረበበትን ምክንያት የሚገልፁ እና ውሳኔም እንዱሰጥበት በቂ ሆነው መገኘት ያለባቸው ለመሆኑ በቁጥር 325(2) ደንግጓል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈባቸው አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜውን ያሻሻለው ህግ መውጣቱን ባለማወቃቸው እንደሆነ ገልፀዋል። እንግዱህ አንድ ህግ ተፈፃሚ የሚሆነው በሀገሪቱ ባለው የህግ ማውጫ/ማሳወቂያ ስርዓት መሰረት ከወጣበት ወይም በልዩ ሁኔታ ተፈፃሚ እንዱሆን ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እንጂ እያንዲንደ ዜጋ ህጉ ስለመውጣቱ ካወቀበት ጊዜ አይደለም። በመሰረቱ ማንኛውም ምክንያታዊ ዜጋ በሀገሩ ውስጥ የሚወጡ ህጎችን ያውቃል ተብል ግምት የሚወሰድ በመሆኑ ህግን ያለማወቅ ይቅርታ የሚያሰጥ አይደለም። እናም ህግ መውጣቱን አላውቅም ነበር የሚለው ጉዲይ መከራከሪያ ላሆን አይችልም። ከዚህ አንፃር የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች ያቀረቡት ምክንያት በቂ አይደለም ብል ውድቅ በማድረጉ የፈፀመው መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቀ/318798 ላይ መስከረም 27/2012 ዓ.ም በዋለው ችልት የአሁን አመልካችን “ጊዜ ያለፈበት የሰበር አቤቱታ ላቅርብ” ጥያቄን ውድቅ በማድረግ የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የዚህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.