በፍትሀ ብሄር ስነ ስርአት ህግ ቁጥር 358 መሰረት ፍርድ ላይ መቃወሚያ ለማቅረብ ተነካብኝ የተባለው መብት ራሱን ችል ዲኝነት ሉጠየቅበት የማይችል መሆን ያለበት ወ/ሮ ስንቅነሽ አስፊው እና እነ ፍቅርተ ይሄይስ (9 ሰዎች) ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም 6. የውርስ ሀብት ተጣርቶ ወራሽነት እንዱረጋገጥ የቀረበ አቤቱታ ውድቅ ከተደረገ በኋላ በዲግም ዲኝነት እንዱታይ ቀርቦ ፍ/ቤት የቀደመውን ውሳኔ በመሻር በግማሽ የውርስ ሀብት ላይ ውርስ እንዱጣራና አቤቱታ አቅራቢዎች ወራሽ መሆናቸውን አረጋግጦ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ወራሾች በቀደመው ክርክር ውሳኔ የተወሰነበትን ተከራካሪ ንብረት ከህግ አግባብ ውጭ ስለያዘብን ይለቀቅልን በሚል ለበላይ ፍርድ ቤት የሚያቀርቡት አዱስ ክስ በዲግም ዲኝነት የቀረበ ነው በሚል ውድቅ የማይደረግ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ እነ ወ/ሮ ፀሐይ ሐይለ (2 ሰዎች) እና ወ/ሮ ሰማ ሰይድ ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም
No summary available.
የካቲት 26/2012 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 5 ጋር የተያያዘ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት በአድዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካቾች በተጠሪዎች እና በላልች ሶስት ሰዎች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። በስር ፍርድ ቤት አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ጭብጥም ፣ አዋሳኙ እና መጠኑ በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰውን ቤት እና ይዞታ የአውራሻቸው ሟች ወ/ሮ ብዙ ገብረሂዎት መሆኑን፤ ሟች ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ የላላቸው በመሆኑ የምትክ ወራሽነታቸውን በፍርድ ቤት አረጋግጠው የሟች የውርስ ሃብት መጣራት ሲጀመር ተጠሪዎች ንብረቱ የእኛ ነው በማለት የተቃወሙ መሆኑን በመግለፅ ንብረቱ የውርስ ሀብት መሆኑ ተረጋግጦ በፍርድ ኃይል እንዱያስረክቧቸው ዲኝነት የሚጠይቅ ነው።
በዚሁ ክስ ላይ ተከሳሾች መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት ተጠሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና አማራጭ የስረ ነገር ክርክር አቅርበዋል። የመቃወሚያው ይዘትም ክስ የቀረበበት ጉዲይ ቀደም ሲል የአሁን አመልካቾች አውራሽ ተጠሪዎች በቤቱ የኖሩበትን ኪራይ ከፍለው እንዱለቁ በሚል በአድዋ ወረዲ ፍርድ ቤት ክስ አቅርበዉባቸው አቤቱታቸው በመ/ቁ/83/95 ላይ ውድቅ የተደረገ በመሆኑ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ ድጋሚ ክስ ላቀርብ አይገባም፤ ቦታ እና ቤቱንም ከ25 ዓመት በላይ ይዘን ስንጠቀምበት የቆየን በመሆኑ ክሱ በይርጋ ይታገዲል የሚል ነው። አማራጭ የስረ ነገር ክርክሩ ይዘት ደግሞ ክርክር የተነሳበትን ቤት እና ይዞታ ከሟች በስጦታ የተላለፈልን በመሆኑ ልንለቅ አይገባም የሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ክሱ በድጋሚ የቀረበ ነው የተባለውን ክርክር አስመልክቶ ቀድሞ ውሳኔ አግኝቷል በተባለበት መዝገብ ላይ የቀረበው ክርክር የቤት ኪራይ ክርክር ስለመሆኑ መዝገቡን አስቀርቦ በመመርመር ማረጋገጡን ጠቅሶ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን ውድቅ አድርጓል። በፍሬ ጉዲይ ላይም ተጠሪዎች ክስ የቀረበበት ቤት እና ይዞታ በስጦታ የተላለፈላቸው ለመሆኑ አግባብነት ያለው አስረጂ አልቀረበም በማለት ለቀው ለአመልካቾች እንዱያስረክቡ ወስኗል።
በዚሁ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የይግባኝ ክርክር ከሰማ በኋላ በአሁን አመልካቾች አውራሽ እና በተጠሪዎች መካከል በመ/ቁ/83/95 ላይ በተደረገው ክርክር በአመልካቾች አውራሽ የተጠየቀው ዲኝነት የአሁን ተጠሪዎች በቤቱ የኖሩበትን ኪራይ ከፍለው ቤቱን ሉለቁልኝ ይገባል የሚል መሆኑን፤ ፍርድ ቤቱም በግራ ቀኙ መካከል የኪራይ ውል ግንኙነት ስለመኖሩ ያልተረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪዎች የተጠየቀውን የኪራይ ዋጋ ሉከፍለ አይገባም በሚል ወስኖ የቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄን በዝምታ ያለፈ መሆኑን፤ በግልፅ ዲኝነት ተጠይቆበት ውሳኔ ያላረፈበት ጉዲይ እንደተነፈገ የሚቆጠር ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 5(3)የሚደነግግ መሆኑን፤ አመልካቾች ክስ ያቀረቡበት ጉዲይ ቀደም ሲል በተደረገው ክርክር ላይ በአመልካቾች አውራሽ ዲኝነት ተጠይቆበት ውሳኔ ሳይሰጥበት የታለፈ በመሆኑ ድጋሚ ክስ ላቀርብበት አይችልም በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በመለወጥ የአመልካቾችን ክስ ውድቅ አድርጓል። አመልካቾች በዚሁ ውሳኔ ላይ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካቾች ጳጉሜ 04/2011 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ በክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። የአቤቱታው ፍሬ ቃልም ቀደም ሲል በመ/ቁ/83/95 ላይ የነበረው ክርክር የቤት ኪራይ ጉዲይን የሚመለከት ሲሆን አሁን ክስ የቀረበው ደግሞ በውርስ ሉተላለፍልን የሚገባ የሟች ንብረት ይለቀቅልን የሚል በመሆኑ ሁለቱ ጉዲዩች የተለያዩ ሆነው እያለ ክሱ በድጋሚ የቀረበ ነው በሚል አቤቱታችን ውድቅ መደረጉ ከህግ አግባብ ውጭ በመሆኑ የክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ውድቅ ተደርጎ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሉፀና ይገባል የሚል ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ በድጋሚ የቀረበ ነው ተብል ውድቅ የተደረገበት የህግ አግባብ ቀደም ሲል በአድዋ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/83/95 ላይ ቀርቦ ከነበረው እና ውሳኔ ከተሰጠበት ክርክር ይዘት አኳያ በዚህ ሰበር ችልት ቀርቦ እንዱመረመር በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አኳያ የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንግዱህ ከክርክሩ አመጣጥ በግልፅ መረዲት እንደሚቻለው የአመልካቾች የክስ አቤቱታ ውድቅ የተደረገው ክስ የቀረበበት ንብረት በተመለከተ በመ/ቁ/83/95 ላይ ክርክር ሲደረግ አሁን ዲኝነት የተጠየቀበት ጉዲይ በአመልካቾች አውራሽ በግልፅ ዲኝነት ተጠይቆበት ውሳኔ ሳይሰጥበት በዝምታ የታለፈ በመሆኑ ክሱ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ በድጋሚ የቀረበ ነው በሚል ምክንያት ነው።
በእርግጥ ቀድሞ በፍርድ/ውሳኔ ባለቀ ጉዲይ ላይ ድጋሚ ክስ እንዲይቀርብ የሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 5 ይከለክላል። በዚህ ድንጋጌ ስር የተቀመጡት ዋና ዋና የድንጋጌው ማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች ቀድሞ የተሰጠ ፍርድ/ውሳኔ መኖር፣ ይኸው ውሳኔ በክርክሩ ዋናው ጭብጥ(On the merit of the case/ ላይ የተሰጠ መሆኑ፣ ውሳኔውን የሰጠው ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት የዲኝነት የስረ ነገር ስልጣን ያለው መሆን፣ ቀድሞ በፍርድ በተወሰነው ክርክር ላይ ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ የነበሩት ጉዲዮች በድጋሚ በቀረበው ክስ ላይም ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ ሆነው የቀረቡ መሆን፣ እንዱሁም በቀደመው ፍርድ/ውሳኔ ላይ የነበሩት እና አሁን በክርክር ላይ ያለት የክርክር አካላት ተመሳሳይ ወይም ከእነርሱ መብት ያገኙ መሆን የሚለት ናቸው።
በዚህ ድንጋጌ ማቋቋሚያ ፍሬ ነገር ውስጥ “ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ” የሚለው ሀረግ የሚያመለክተው በቀደመው ክርክር ላይ ከአንደኛው ተከራካሪ ወገን ተጠይቆ በልላኛው ወገን የተካደ ወይም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የታመነና በዚሁ ላይ የፍርድ ውሳኔ ያረፈበትን የክርክር ነጥብ ነው። በልላ በኩል በቀደመው ክርክርና ሙግት ላይ በግልፅ ዲኝነት ተጠይቆበት ጥያቄው ተቀባይነትን ሳያገኝ ከታለፈ የተጠየቀው ዲኝነት እንደተከለከለ የሚቆጠር በመሆኑ በዚያው ጉዲይ ላይ ድጋሚ ክስ ማቅርብ እንደማይቻል የዚሁ ድንጋጌ ንዐስ ቁጥር 3 ድንጋጌ ይዘት ያስገነዝባል።
በእርግጥ በዚህ ንዐስ ድንጋጌ ውስጥ “በግልፅ ዲኝነት ተጠይቆበት ጥያቄው ተቀባይነት ሳያገኝ ከታለፈ” የሚለው አገላለፅ በተጠየቀው ዲኝነት ላይ ግልፅ ክልከላ መኖሩን የሚያሳይ ነው። ሆኖም የድንጋጌው ይዘት ከስነ ስርዓት ህጉ የእንግሉዘኛ ትርጎም ጋር ተዲምሮ ሲታይ የንዐስ ድንጋጌው አንኳር መልዕክት በግልፅ የተጠየቀውን ዲኝነት በዝምታ ማለፍን የሚመለከት ለመሆኑ መረዲት ይቻላል። ከዚህ አኳያ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 5 ስር የተመለከተው በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ ዲግም ክስ ክልከላ ተፈፃሚነት በተከራካሪ ወገኖች በግልፅ ዲኝነት ተጠይቆበት ፍርድ ቤት በዝምታ ባለፈው ጉዲይ ላይ ጭምር እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። ሆኖም በግልፅ ዲኝነት በተጠየቀበት ጉዲይ ላይ ፍርድ ቤቱ በዝምታ የከለከለው መሆኑን ያለመሆኑ ጉዲይ ዲኝነት የተጠየቀበትን ጉዲይ አስመልክቶ ከላላኛው ተከራካሪ ወገን ከቀረበው ክርክር እና ጥያቄ ጋር ተገናዝቦ መታየት ያለበት ጉዲይ ነው። በልላ አገላለፅ ፍርድ ቤት በዝምታ ያለፈውን የዲኝነት ጥያቄ ተከሳሹ ወገን በግልፅ ክድ የተከራከረበት ላሆን ይገባል ማለት ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካቾች አሁን ክስ ያቀረቡበትን ንብረት አስመልክቶ አውራሻቸው ቀደም ሲል ተጠሪዎች በቤቱ ውስጥ የኖሩበትን የ18 ወራት ውዝፍ የቤት ኪራይ ከፍለው ቤቱን ያስረክቡኝ በሚል ክስ አቅርበው የነበረ መሆኑን፤ ተጠሪዎች ለዚሁ ክስ በሰጡት መልስ ክስ የቀረበበትን ቤት ተከራይተው ሳይሆን ያለኪራይ እንዱኖሩበት የተሰጣቸው መሆኑን ገልፀው ኪራይ ልንጠየቅ አይገባም በማለት የተከራከሩ መሆኑን፤ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም “በግራ ቀኙ መካከል የኪራይ ውል ግንኙነት አለ? ወይስ የለም?” የሚል ጭብጥ ይዞ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተጠሪዎች ያለኪራይ በቤቱ ውስጥ እንዱኖሩ በአመልካቾች አውራሽ ተፈቅድላቸው ሲኖሩ የነበረ ስለመሆኑ አረጋግጫለሁ በሚል መነሻነት ተጠሪዎች የተጠየቀውን ኪራይ ሉከፍለ አይገባም የሚል ውሳኔ ሰጥቶ ቤቱን ለመረከብ የቀረበው ጥያቄ በዝምታ ያለፈ መሆኑን አጣሪው ችልት አስቀርቦ ከመዝገብ ካያያዘው ሰነድ እና የስር ፍርድ ቤቶች የመዝገብ ግልባጭ ለመረዲት ተችሎል።
በመ/ቁ/83/95 ላይ በቀረበው ክርክር የአሁን ተጠሪዎች የቤት ኪራይ ልንጠየቅ አይገባም በሚል ከመከራከራቸው በስተቀር ቤቱን በተመለከተ ያቀረቡት የይገባኛል ክርክር የለም። ይህም ማለት የአመልካቾች አውራሽ ቤቱን ለመረከብ ያቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄ ተጠሪዎች በግልፅ ክደው ያቀረቡት ክርክር አለመኖሩን ያሳያል። የተጠየቀው ዲኝነት በልላኛው ወገን በግልፅ ባልተካደበት ሁኔታ ጉዲዩን የያዘው ፍርድ ቤት የዲኝነት ጥያቄን በዝምታ ማለፈ ዲኝነቱ እንደተከለከለ የሚያስቆጥር አይደለም። ይህ ከሆነ ደግሞ በጉዲዩ ላይ አዱስ ክስ እንዲይቀርብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 5 የሚከለክል ባለመሆኑ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ በድጋሚ የቀረበ ነው የሚያስብል አይደለም።
ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካቾች ጥያቄ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ ድጋሚ የቀረበ ነው በሚል ውድቅ ማድረጉ እና ሰበር ችልቱም ይህንኑ ሳያርም ማለፈ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህግ ቁጥር 5 ድንጋጌን መሰረታዊ አላማ እና የተፈፃሚነት ወሰን ያላገናዘበ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ/መ/ቁ/116353 ላይ ሰኔ 11/2011 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፤ እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/112927 ላይ መጋቢት 27/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
አመልካችች ክስ ያቀረቡበት ጉዲይ ቀደም ብል በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ አይደለም ተብል ተወስኗል።
የትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በውሳኔ የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ በክሱ ሥረ ነገር ላይ የቀረበለትን የይግባኝ ቅሬታ መርምሮ የመሰለውን እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 341(1) መሰረት ጉዲዩ ይመለስለት።
የዚህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.