No summary available.
ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የንብረት ክርክርን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/299397 ላይ በ03/04/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት በአሁን አመልካቾች የቀረበለትን የሰበር አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠውን የመጨረሻ ትዕዛዝ በመቃወም ነው።
የጉዲዩ ሥረ ነገር አመጣጥ እንዱህ ነው። የአሁን አመልካቾች የእናታቸው የውርስ ሃብት ተጣርቶ ወራሽነታቸው እንዱረጋገጥላቸው ለበላ ወረዲ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀርባለ። ፍርድ ቤቱም በመ/ቁ/13772 ላይ ጉዲዩን በማየት ላይ እያለ የአሁን ተጠሪ በጣልቃ ገብነት ቀርበው በውርስ ሀብትነት እንዱጣራ የተባለውን ቤት በ233 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ እንዲረፈ ከአመልካቾች ወላጅ እናት ላይ ግንቦት 19/2000 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል የገዙ መሆኑን ገልፀው ‛ንብረቱ የውርስ ሃብት ሳይሆን የግል ንብረቴ በመሆኑ ሉጣራ አይገባም“ በማለት ይቃወማለ። የወረዲው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በውርስ ሀብትነት እንዱጣራ ተብል በአመልካቾች የተጠየቀው ቤት የአሁን ተጠሪ የገዙት መሆኑን አረጋግጫለሁ በማለት ሰኔ 23/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የአመልካቾችን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል።
ይህ ከሆነ በኋላ የአሁን አመልካቾች ተጠሪ የገዙት 122 ካሬ ሜትር ብቻ ሆኖ እያለ 233 ካሬ ሜትር እንደሆነ ተደርጎ የቀረበው ውል የሀሰት መሆኑን ገልፀው የቀደመው ውሳኔ በዲግም ዲኝነት እንዱታረምላቸው ለወረዲው ፍርድ ቤት ጥያቄ ያቀርባለ።
በዚህ መልኩ ጥያቄው የቀረበለት ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የካቲት 17/2007 ዓ.ም በዋለው ችልት የአመልካቾች አውራሽ በሽያጭ ያስተላለፈት 122 ካሬ ሜትር ብቻ ስለመሆኑ ማረጋገጡን ጠቅሶ በተቀረው የውርስ ሀብት ላይ ውርሱ ተጣርቶ እንዱቀርብለት በማድረግ ሚያዚያ 30/2007 ዓ.ም በዋለው ችልት ደግሞ በሽያጭ ለአሁን ተጠሪ ከተላለፈው ውጪ ባለው ንብረት ላይ የአመልካቾችን ወራሽነት በማረጋገጥ ወስኗል።
አመልካቾች ይህንኑ መነሻ በማድረግ የአሁን ተጠሪ በ186 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ግምቱ 450,000(አራት መቶ ሃምሳ ሺህ) የሆነ የውርስ ሀብት ያለአግባብ ይዘው በወር በብር 600(ስድስት መቶ) በማከራየት እየተገለገለበት የሚገኙ መሆኑን ገልፀው ተጠሪ ንብረቱን ለቀው እንዱያስረክባቸው፤
ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ያለውን የኪራይ ዋጋ ብር 7,200(ሰባት ሺህ ሁለት መቶ) እንዱከፈሎቸው እና ቀሪውን የኪራይ ዋጋ የመጠየቅ መብት እንዱጠበቅላቸው ለአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዱስ ክስ አቅርበዋል።
የአሁን ተጠሪ ለዚሁ ክስ በሰጡት መልስ ክሱ በድጋሚ የቀረበ ነው፤ ጉዲዩም የውርስ ክርክር በመሆኑ ፍርድ ቤት ክርክሩን የማየት የሥረ ነገር ስልጣን የለውም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና ቤቱን በግዥ ያገኘሁት በመሆኑ ልለቅ አይገባም የሚል የሥረ ነገር ክርክር በማቅረብ ሞግተዋል።
ፍርድ ቤቱም የመ/ቁ/70460 በሆነ ላይ የግራ ቀኘን ክርክር ከሰማ በኋላ ሚያዝያ 26/2008 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ‛የአመልካቾች ጥያቄ የዲግም ዲኝነት ይታይልኝ በመሆኑ ክሱ በድጋሚ የቀረበ ነው ልባል አይችልም፤ የአመልካቾች ክስ የውርስ ጥያቄ በመሆኑ ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የለኝም፤ የዲግም ዲኝነት ይታይልኝ ጥያቄውም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ በመሆኑ በይርጋ ይታገዲል“ በማለት የአመልካቾችን ክስ ውድቅ አድርጓል።
በዚሁ ጉዲይ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/244480 ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ህዲር 15/2009 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ‛አመልካቾች ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ በውርስ የተላለፈልን እና በፍርድ የተረጋገጠልን ንብረት ከህግ አግባብ ውጭ በተጠሪ ስለተያዘብን ይለቀቅልን የሚል በመሆኑ የውርስ ክርክር ልባል አይገባም፤ የውርስ ክርክር ነው ቢባል እንኳን የንብረቱ ግምት በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዲኝነት ሥልጣን ውስጥ የሚወድቅ በመሆኑ የሥረ ነገር ስልጣን የለኝም መባለ ተገቢ አይደለም፤ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የለኝም ካለ ላላውን ጉዲይ መመልከቱ ተገቢ አይደለም“ በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሥረ ነገር ክርክሩ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ እንዱወስን በነጥብ መልሶለታል።
No topics extracted.
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን የሥረ ነገር ክርክር ሰምቶ፤ ስለጉዲዩም ተገቢ ነው ካለው አካል ካጣራ በኋላ የካቲት 17/2009 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ክስ የቀረበበት ቤት በሽያጭ ለአሁን ተጠሪ የተላለፈ መሆኑን አረጋግጫለሁ በሚል ምክንያት አመልካቾች በቤቱ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችላቸው መብት እና ጥቅም የላቸውም ሲል ክሱን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 33(2) መሰረት ውድቅ አድርጓል።
ይህንኑ ውሳኔ በይግባኝ የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/258621 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ጥቅምት 08/2011 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ አመልካቾች ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ በድጋሚ የቀረበ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 5 መሰረት ክሱን ውድቅ ማድረግ ሲገባው አከራክሮ መወሰኑ አግባብ አለመሆኑን በመተቸት በውጤት ደረጃ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማፅናት የአመልካቾችን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል። በዚሁ ውሳኔ ላይ የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የክልለ ሰበር ችልት በበኩለ በመግቢያው ላይ በተጠቀሰው የመዝገብ ቁጥር ላይ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር አያበቃም ሲል ውድቅ አድርጓል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካቾች የካቲት 08/2011 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ቀደም ሲል በክልለ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/13772 ላይ የአሁን አመልካቾች በ2000 ዓ.ም ከገዛችው ውጭ ያለውን ንብረት እንዱወርሱ በሚል የተሰጠው ውሳኔ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች ይህንን ሳያገናዝቡ የወሰኑበት አግባብ ለዚህ ሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም የቀረበውን ክርክር ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ፤ በስር ፍርድ ቤቶች ከተከናወነው ክርክር ይዘት እና አድማስ አንፃር ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካቾችን ክስ ውድቅ ያደረገው ክሱ በድጋሚ የቀረበ ነው በሚል ምክንያት ነው። በእርግጥ ቀድሞ በፍርድ/ውሳኔ ባለቀ ጉዲይ ላይ ድጋሚ ክስ ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 5 ይደነግጋል። በዚህ ድንጋጌ ስር የተቀመጡት ዋና ዋና የድንጋጌው ማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች ቀድሞ የተሰጠ ፍርድ/ውሳኔ መኖር፣ ይኸው ውሳኔ በክርክሩ ዋናው ጭብጥ(On the merit of the case/ ላይ የተሰጠ መሆኑ፣ ውሳኔውን የሰጠው ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት የዲኝነት የስረ ነገር ስልጣን ያለው መሆን፣ ቀድሞ በፍርድ በተወሰነው ክርክር ስረ ነገር እና የተያዘው ጭብጥ አንድ ዓይነት መሆን፣ እንዱሁም በቀደመው ፍርድ/ውሳኔ ላይ የነበሩት እና አሁን በክርክር ላይ ያለት የክርክር አካላት ተመሳሳይ ወይም ከእነርሱ መብት ያገኙ መሆን የሚለት ናቸው። እናም አንድ ጉዲይ በዚህ ድንጋጌ መሰረት በድጋሚ የቀረበ ነው ለማለት እነዚህን መመዘኛዎች በአግባቡ የሚያሟላ መሆን ይጠበቅበታል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ቀደም ሲል በወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ ላይ ቀርቦ የካቲት 17/2007 እና ሚያዝያ 30/2007 ዓ.ም ውሳኔ ያገኘ መሆኑን ጠቅሷል። ከላይ እንደተመለከተው በተጠቀሰው መዝገብ ላይ ቀርቦ በሁለቱ ቀናት ውሳኔ የተሰጠው አመልካቾች ባቀረቡት የዲግም ዲኝነት ጥያቄን መሰረት በማድረግ ነው። በዚሁ አግባብ የካቲት 17/2007 ዓ.ም በዋለው ችልት የአሁን ተጠሪ ከአመልካቾች አውራሽ ላይ የገዙት 122 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈን ቤት ብቻ ነው በሚል ቀደሞ የተሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል በተቀረው ይዞታ ላይ ውርሱ ተጣርቶ እንዱቀርብ አድርጓል። በዚህ መልኩ ተጣርቶ የቀረበለትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ደግሞ የአሁን አመልካቾች ከ122 ካሬ ሜትር ውጭ ባለው ይዞታ እና ንብረት ላይ ወራሾች ናቸው በሚል ሚያዝያ 30/2007 ዓ.ም ውሳኔ መስጠቱን የቀረበው የውሳኔ ግልባጭ ያሳያል።
በልላ በኩል አመልካቾች ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት ደግሞ የዲግም ዲኝነት ውሳኔውን መሰረት በማድረግ ተጠሪ 186 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ያረፈ የውርስ ሃብት ያለአግባብ ይዘው የሚገኙ መሆኑን በመግለፅ በፍርድ ኃይል ተገደው እንዱለቁላቸው ዲኝነት የሚጠይቅ ነው። እነዚህ ሁለቱ ክሶች በይዘት ደረጃ ሲታዩ ወረዲ ፍርድ ቤት ላይ የነበረው ክርክር ወራሽነትን ከማረጋገጥ ጋር የተያያዘ ሲሆን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ የቀረበው ክስ ደግሞ በፍርድ ቤት የተረጋገጠ የወራሽነት ማስረጃ መሰረት ተደርጎ ያለአግባብ የተያዘ የውርስ ሃብት ለማስለቀቅ የቀረበ ክስ ነው። እናም ቀድሞ ውሳኔ አግኝቷል በተባለው ጉዲይ እና አመልካቾች ኋላ ላይ ባቀረቡት ክስ መካከል ፍፁም የሆነ የስረ ነገር እና የክርክር ጭብጥ ልዩነት ያለ በመሆኑ ክሱ በድጋሚ ቀርቧል የሚባል አይደለም።
ያም ሆኖ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በመ/ቁ/244480 ላይ ጉዲዩን በይግባኝ ተመልክቶ በነጥብ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ሲመልስ ቀድሞ ውሳኔ አግኝቷል የተባለው ጉዲይ እና አመልካቾች ኋላ ላይ ያቀረቡት ክስ የተለያየ ስለመሆኑ አቋም ይዞ በሥረ ነገር ጉዲይ ላይ ውሳኔ እንዱሰጥ ወስኗል። ይህ ውሳኔ እያለ ፍርድ ቤቱ መልሶ እራሱ ቀድሞ የሰጠውን ውሳኔ በሚሽር አኳኋን የተለየ አቋም መያዙ እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም ይህንን ማረም ሲገባው ማለፈ በእርግጥም ሉነቀፍ የሚገባው መሰረታዊ የህግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/299397 ላይ ታህሳስ 03/2011 የሰጠው ትዕዛዝ እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/256821 ላይ ጥቅምት 08/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በውሳኔ የዘጋውን የመ/ቁ/256821 በማንቀሳቀስ በቀረበለት ይግባኝ የሥረ ነገር ክርክር ላይ የመሰለውን እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 343(1) መሰረት መዝገቡ ይመለስለት።
የዚህን ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ወጨ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።