No summary available.
ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡ ወ/ሮ ስንቅነሽ አስፊው- ወኪል ጥሩእናት ከልክላ ቀርበዋል ተጠሪዎች፡
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት የቀረበ መቃወሚያን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/235677 ላይ ሐምል 04/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማፅናት የሰጠውን የመጨረሻ ትዕዛዝ በመቃወም ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ እንዱህ ነው። የአሁን ከ1ኛ እስከ 6ኛ ያለት ተጠሪዎች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአሁን ከ7ኛ እስከ 9ኛ ባለት ተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ በጉለላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 5 ውስጥ የቤት ቁጥር 789/3 የሆነውን የሻይ እና ምግብ መሸጫ ንግድ ቤት ለንግደ ሥራ አስፈላጊ የሆነውን ቅድም ሁኔታ አላሟላችሁም በሚል ከጥር 22/2005 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱ ውስጥ ካለው ንብረት ጋር ቤቱን ያሸገባቸው መሆኑን፤ የንግድ ስራው በመቋረጡ ምክንያት እሽጉን እንዱያነሱላቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ምላሽ ያልተሰጣቸው መሆኑን በመግለፅ በፍርድ ኃይል ተገደው እሽጉን አንስተው ቤቱን እንዱያስረክቧቸው እና በቤቱ ውስጥ በነበሩት ንብረቶች ላይም ለደረሰው ጉዲት ተገቢውን ካሳ የመጠየቅ መብታቸው እንዱጠበቅላቸው ዲኝነት ይጠይቃለ።
በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥ የታዘዘ ቢሆንም ከ7ኛ እስከ 9ኛ ያለ ተጠሪዎች የፅሁፍ መልስ ያልሰጡ እና ክስ በሚሰማበት እለትም ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ትዕዛዝ ይሰጣል።
በዚሁ አግባብ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የከሳሽ ወገንን ምስክር ሰምቶ ታሽጓል ስለተባለው የንግድ ቤትም በአሁን 7ኛ ተጠሪ በኩል ተጣርቶ እንዱቀርብለት ካደረገ በኋላ አስተዲደር ክፍለ ቤቱ ስለታሸገበት ምክንያት ምንም መረጃ ማግኘት አለመቻለን እና በቤቱ ላይም እሽግ አለመኖሩን የገለፀ ቢሆንም ስለመታሸጉ በሰው ምስክር ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ተከሳሾቹ እሽጉን በማንሳት ቤቱን ለከሳሾች እንዱያስረክቡ ወስኗል።
ይህ ከሆነ በኋላ የአሁን አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት ውሳኔውን በመቃወም ይቀርባለ። የመቃወም አቤቱታቸው መሰረትም ታሸገ ተብል ክስ የቀረበበት ቤት በውርስ የተላለፈላቸው እና በእጃቸው የሚገኝ መሆኑን፤ ቤቱም የንግድ ቤት ሳይሆን መኖሪያ ቤት ሲሆን በማናቸውም አካል ያልታሸገ እና በእጃቸው አድርገው እየኖሩበት ያለ መሆኑን፤ ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ ባላወቁት መንገድ የአሁን ከ1ኛ እስከ 6ኛ ያለት ተጠሪዎች አስተዲደር ክፍለ ላይ ክስ አቅርበው ቤቱ የታሸገበት እሽግ ተነስቶ ቤቱን ለመረከብ ያስወሰኑት ውሳኔ መብታቸውን የሚነካ መሆኑን በመግለፅ በላለበት የተሰጠው ውሳኔ እንዱሰረዝ የሚጠይቅ ነው።
በዚህ መልኩ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ትዕዛዝ ሰጥቶ ከ9ኛ ተጠሪ በስተቀር ላልቹ አለን ያለትን ክርክር በፅሁፍ ማቅረባቸውን፤ መልስ ከሰጡት ተጠሪዎች ውስጥም 7ኛ እና 8ኛ ተጠሪዎች የፅሁፍ መልስ ብቻ ሰጥተው ከቀጠሮ በመቅረታቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ የተደረገ መሆኑን፤ በኋላም ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ሰምቶ ቀድሞ የተሰጠውም ውሳኔ የሚያስለውጥ ምክንያት አላገኘሁም በሚል የአመልካች አቤቱታ ውድቅ አድርጓል። በዚሁ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በዚህ ፍርድ መግቢያ ላይ በተጠቀሰው የመዝገብ ቁጥር እና ቀን በዋለው ችልት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት ይግባኙን ዘግቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ሐምል 17/2011 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
No topics extracted.
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ አድማስ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም ጉዲዩን መርምሯል። በዚሁ መሰረት አመልካች ያቀረቡት ጥያቄ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት የሚስተናገድ የመሆኑ ጉዲይ በቅድሚያ ሉጣራ የሚገባው ነጥብ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ጥር 358 መሰረት የፍርድ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችለው ቀድሞ በተደረገው ክርክር የሙግቱ አካል ላሆን ይችል የነበረ ሆኖ እርሱ ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር በተሰጠው ውሳኔ መብቱ የሚነካ ሶስተኛ ወገን ነው። አንድ ሰው ወይም አካል በፍርድ ቤት በተያዘ ክርክር የክርክሩ አካል ላሆን የሚችለው በፍርድ ቤት በሚሰጥ ትዕዛዝ፣ በራሱ በጣልቃ ገብ አቤቱታ አቅራቢነት አልያም በተከሳሽ ወገን ጥያቄ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 40፣ 41 እና 43 ድንጋጌዎች ይዘት መረዲት ይቻላል። ከእነዚህ በሂደት ላይ ባለ ሙግት መግቢያ መንገድች ውስጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ጥር 358 መሰረት በፍርድ ተቃዋሚነት ላቀርብ የሚችለው በዋናነት ቀድሞ በተደረገው ክርክር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 41 በተመለከተው መሰረት በጣልቃ ገብነት ቀርቦ መብቱን እና ጥቅሙን ማስከበር ይችል የነበረ ሶስተኛ ወገን ነው።
በእርግጥ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 41 በላልች ተከራካሪ ወገኖች መካካል በመካሄድ ላይ ባለ በአንድ ክስ ያገባኛል የሚል ማንኛውም ወገን የመብቱን ሁኔታ በመግለፅ የክርክሩ አካል መሆን የሚችል ስለመሆኑ ከመግለፁ ውጭ ለጣልቃ ገብነት የሚያበቁ ግልፅ እና ዝርዝር መመዘኛዎች አላስቀመጠም። ሆኖም የዚህ ድንጋጌ ይዘት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 33(2) ድንጋጌ ጋር ተዲምሮ ሲታይ የክርክሩ ተካፊይ ላሆን የሚችለው ክርክር ከቀረበበት ጉዲይ ላይ መብት ወይም ጥቅም ያለው ወገን እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።
እናም ሶስተኛ ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 41 መሰረት ወደ በሂደት ላይ ባለ ተካፊይ ለመሆን በመሰረታዊ ህግ የተረጋገጠ መብት ወይም ጥቅም ያለው እና በክርክር ላይ ያለው ጉዲይም በህግም ሆነ በፍሬ ነገር ረገድ ከዚሁ መብት እና ጥቅም ጋር የተያያዘ መሆኑን፤ በጣልቃ ገብነት ቀርቦ ይህንን መብቱን ካላስከበረ በቀር ላላ መብት እና ጥቅሙን የሚያስጠብቅበት ዘዳ ወይም እድል የላለ መሆኑን እና በክርክሩ ውጤትም በቀጥታ የሚነካ አልያም የክርክሩ ውጤት በቀጥታ ሉፈፀምበት የሚችል አካል ላሆን እንደሚገባ ከዚሁ ድንጋጌ መንፈስ እና በዚሁ ዙሪያ ከተደረጉ የምርምር ፅሁፍች መገንዘብ ይቻላል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች መቃወሚያ ባቀረቡበት ውሳኔ ላይ የቀረበው ክርክር ያላግባብ የታሸገው ቤት እሽጉ ሉነሳ ይገባል የሚል ነው። የአሁን አመልካች ጥያቄ ደግሞ ታሽጓል የተባለው ቤት ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ከባለቤትነት ጋር የተያያዘ ነው። የቀደመውን ክርክር በተመለከተ በጭብጥነት ተይዞ እልባት ላሰጥበት የሚችለው ነጥብ ‛እሽጉ ሉነሳ ይገባል? ወይስ አይገባም?“ የሚል ሲሆን ከአመልካች ጥያቄ አኳያ ደግሞ በጭብጥነት ሉያዝ የሚችለው ከቤቱ ትክክለኛ ባለቤትነት ጋር የተያያዘ ይሆናል።
እነዚህ ሁለት ዲኝነቶች ሉነሳ ከሚችለው የፍሬ ነገር እና የህግ ክርክር አኳያ የተለያዩ ናቸው።
በተጨማሪም ቀድሞ ከተደረገው ክርክር ጋር በተያያዘ የእሽጉ መነሳት ወይም አለመነሳትን አስመልክቶ የሚሰጠው ውሳኔ የአሁን አመልካች በንብረቱ ላይ የይገባኛል ጥያቄን ከማቅረብ የሚያግዲቸው አይደለም።
ይህ ከሆነ ደግሞ የአመልካች ጥያቄ እራሱን ችል ዲኝነት ተጠይቆበት መፍትሄ ማግኘት የሚችል በመሆኑ በቀደመው ክርክር በጣልቃ ገብነት ተካፊይ የሚሆኑበትም ሆነ ከፍርድ በኋላ በተቃዋሚነት ሉቀርቡ የሚችለበት የህግ አግባብ ባለመኖሩ የአመልካች ጥያቄ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ሉስተናገድ የሚገባ አይደለም።
ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ጥያቄ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ተቀብለው ማስተናገዲቸው የድንጋጌውን መንፈስ እና የተፈፃሚነት ወሰን መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የህግ አረዲድ እና አተረጓጎም ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/235677 ላይ ሐምል 04/2011 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ/ 56417 ላይ ሚያዝያ 08/2011 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአመልካች ጥያቄ እራሱን ችል በተገቢ ሥነ ሥርዓት ዲኝነት ተጠይቆበት የሚስተናገድ እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት የሚስተናገድ አይደለም።
የዚህን ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።