ወራሽ የሆነ ወገን አውራሽ ተካፊይ በነበረበት ክርክር ላይ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 መሰረት መቃወም የማይችል ሀዊ ሁንዳ እና እነ አምበሳ አደና (26 ሰዎች) ህዲር 28/2013 ዓ.ም 2 2. በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 መሰረት የቀረበ አቤቱታ የክርክር ውጤት ተጠብቆ የቀረበ ነው በሚል ውድቅ ለማድረግ አቤቱታ አቅራቢው የቀደመውን ክርክር ስለማወቁ በተገቢው ማስረጃ ሉጣራ የሚገባ አቶ ሸለመ አበራ እና እነ አቶ መገርሳ ምትኩ (2 ሰዎች) ጥር 25/2013 ዓ.ም 6 3. በፍትሀ ብሄር ስነ ስርአት ህግ ቁጥር 358 መሰረት የሚቀርብ የፍርድ መቃወሚያ ወራሽነትን በማረጋገጥ በተሰጥ ማስረጃ ላይ ላቀርብ የማይችልና በማስረጃው ምክንያት መብቴ ተነክቷል የሚል አካል ተገቢውን ዲኝነት ከፍል ተጓደለብኝ የሚለውን መብት ማረጋገጥ የሚችል መሆኑን በሰበር መዝገብ ላይ የተሰጠው አስገዲጅ ውሳኔ የውርስ ሀብት ተለይቶ በተሰጠ የወራሽነት ምስክር ወረቀት ክርክር ላይ በአስገዲጅነት ሉጠቀስ የማይችል ወ/ሮ ተሰሜ ገዲ እና እነ አቶ ለማ ነጋሽ (2 ሰዎች) መስከረም 27/2013 ዓ.ም 4. በፍርድ የተረጋገጠ መብት ስነ ስርዓቱን ጠብቆ እስካልተሻረ ድረስ ሉፈፀም የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 392
No summary available.
ጥር 28/2013 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ ግርማ የሺጥላ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አመለወርቅ እሸቴ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ በሁከት ይወገድልኝ ክስ መነሻነት ቀርቦ ውሳኔ ያገኘ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አፈፃፀም ክርክርን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ በቀን ሐምል 18/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ የሻረበትን የመጨረሻ ውሳኔ በመቃወም ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ እንዱህ ነው። የአሁን አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአሁን ተጠሪ እና በከተማ አስተዲደሩ ሶስት የመንግስት ጽ/ቤቶች ላይ ክስ ያቀርባለ። በቀረበው ክስ የአሁን ተጠሪ 2ኛ ተከሳሽ ነበሩ። ቀርቦ የነበረው ክስ ጭብጥም የአሁን ተጠሪ ከመንግስት ተከራይተው የነበረውን የንግድ ቤት ለሁለት ከፍለው ግማሹን ለአሁን አመልካች ያከራይዋቸው መሆኑን፤ በዚሁ አግባብ አመልካች በተከራዩት ቤት የንግድ ፈቃድ አውጥተው በመስራት ላይ እንዲለ መመሪያ ቁጥር 4/2004 በመውጣቱ እና በመመሪያው መሰረት የአሁን ተጠሪ ከመንግስት የተከራዩትን ንግድ ቤት ሸንሽነው ለ3ኛ ወገን እያከራዩ ስለመሆኑ በማስረጃ በመረጋገጡ ምክንያት አመልካች ከተጠሪ የተከራዩት ቤት በቤት ቁጥር 913(1) ተሰይሞ በስማቸው ከመንግስት ጋር የኪራይ ውል የተዋዋለ መሆኑን፤ ይህ ከሆነ በኋላ በፍርድ ቤቱ 1ኛ ተከሳሽ የነበረው የአዱስ አበባ ከተማ ዱዛይንና ግንባታ ልማት አስተዲዲር ጽ/ቤት ያቋቋመው ግብረ ኃይል አመልካች የተከራዩት ቤት ለአሁን ተጠሪ ይገባል በሚል ባቀረበው የተሳሳተ ሪፖርት መነሻነት “የንግድ ቤቱ አልተሸነሸነም፤ የአሁን ተጠሪም ገቢ የላላቸው እና አቅመ ደካማ ናቸው” የሚለ ነጥቦችን በመጥቀስ ተጠሪ በስማቸው የኪራይ ውል እንዱዋዋለ ያደረገ መሆኑን፤ በዚሁ መነሻነት በቤቱ ላይ የተሰጣቸው የንግድ ፈቃድም የተሰረዘባቸው መሆኑን በመጥቀስ የተከሳሾቹ ድርጊት የሁከት ተግባር ነው ተብል ከአስተዲደሩ ጋር የገቡት የኪራይ ውል እንዱቀጥል እና የተሰረዘባቸው የንግድ ፈቃድ ወደነበረበት እንዱመለስ ዲኝነት የሚጠይቅ ነው።
በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት የአሁን ተጠሪ ክስ የቀረበበት ቤት የሚገባኝ መሆኑ ተጣርቶ የተወሰነልኝ በመሆኑ የፈጠርኩት ሁከት የለም የሚል የመከላከያ መልስ እና አመልካች ክስ ያቀረበበትን ቤት ከህግ አግባብ ውጭ የያዘ በመሆኑ የ4 ወር ውዝፍ ኪራይ ከፍል ሉለቅልኝ ይገባል የሚል የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የአሁን ተጠሪ ለክርክር ምክንያት የሆነውን ቤት ሸንሽነው ማከራየታቸው ተረጋግጦ እያለ አስተዲደሩ ከአመልካች ጋር የገባውን የኪራይ ውል ማቋረጡ የሁከት ተግባር በመሆኑ ሉወገድ ይገባል፤ የንግድ ፈቃደም መሰረዙ አግባብ ባለመሆኑ ወደነበረበት ሉመለስ ይገባል፤ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱን በተመለከተ አከራክሮ ለመወሰን የሚያስችል የሥረ ነገር የዲኝነት ሥልጣን የለኝም ሲል ወስኗል።
በዚሁ ውሳኔ ላይ በአሁን ተጠሪ ይግባኝ ባይነት ጉዲዩ የቀረበለት የከተማው ይግባኝ ሰሚ ችልት የተጠሪን ይግባኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት ዘግቷል። የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በበኩለ በመ/ቁ/19288 ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የካቲት 18/2005 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ የአሁን ተጠሪ ቀደም ሲል ከአስተዲደሩ ጋር የገቡት የንግድ ቤት ኪራይ ውል ፀንቶ ባለበት አስተዲደሩ ከአሁን አመልካች ጋር የገባው የኪራው ውል ህገ ወጥ ነው፤ የአሁን አመልካችን የንግድ ፈቃድ በተመለከተ በአዋጅ ቁር 686/2002 አንቀፅ 39(1(ሀ-ሰ)) መሰረት ፈቃደን የሚያሰርዝ ምክንያት በላለበት መሰረዙ አግባብ ባለመሆኑ ወደነበረበት ይመለስ ተብል መወሰኑ ተገቢ ነው፤
የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱን በተመለከተ የከተማ አስተዲደሩ አከራክሮ የመወሰን የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለው በመሆኑ በዚሁ ነጥብ ላይ አከራክሮ ይወስን በሚል ጉዲዩን በነጥብ መልሷል።
በዚሁ ውሳኔ ላይ የአሁን አመልካች ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበው በሰ/መ/ቁ/87917 ላይ በመታየት ላይ እያለ የአሁን ተጠሪ ደግሞ በከተማ አስተዲደሩ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔው መሰረት ጉዲዩን ለከተማ አስተዲደሩ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በማቅረብ ክርክሩን አስቀጥለዋል። የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱም በተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ጥቅምት 08/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የአሁን አመልካች ክስ የቀረበበትን ቤት ውዝፍ ኪራይ ከፍለው ለአሁን ተጠሪ እንዱለቁ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ስለመባለ የስር ፍርድ ቤት መዝገብ የሚገልፀው ነገር የለም።
ይህ ከሆነ በኋላ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/87917 ላይ በመታየት ላይ የነበረው የግራ ቀኙ የሰበር ክርክር ጥቅምት 22/2006 ዓ.ም ውሳኔ አግኝቷል። በውጤቱም የከተማ አስተዲደሩ ሰበር ሰሚ ችልት የመስተዲድሩ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ለማየት የሥረ ነገር የዲኝነት ሥልጣን አለው ብል መወሰኑ በአግባቡ መሆኑን፤ ግራ ቀኙ ከአስተዲደሩ ጋር የገቡትን ውል በተመለከተ ከቀረበው ክርክር አኳያ የአሁን ተጠሪ በመመሪያ ቁጥር 4/2004 አንቀፅ 6(1) መሰረት በልዩ ሁኔታ በመመሪያው ተጠቃሚ ስለመሆናቸው በአግባቡ ለማረጋገጥ የሚያስችል በቂ ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤቶች የውለን ህጋዊነት አስመልክቶ በየፉናቸው ውሳኔ መስጠታቸው አግባብ አለመሆኑን በመተቸት ከዚሁ አኳያ የግራ ቀኙ ክርክር በተጨማሪ ማስረጃ በድጋሚ ተጣርቶ እንዱወሰን ጉዲዩን ለመስተዲድሩ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በነጥብ ተመልሷል።
በዚሁ አግባብ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ክርክሩን በመስማት ላይ እንዲለ የአሁን ተጠሪ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ አስመልክቶ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት እንዱፈፀምላቸው ግንቦት 18/2006 ዓ.ም የተፃፈ የአፈፃፀም አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም በዚሁ ነጥብ ላይ የአሁን አመልካችን መከራከሪያ ከሰማ በኋላ ሐምል 17/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የአፈፃፀም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ የተሰጠው በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/87917 ላይ በመታየት ላይ የነበረው የግራ ቀኙ ክርክር ውጤት ሳይታወቅ መሆኑን፤ ሰበር ሰሚ ችልቱ ጥቅምት 22/2006 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እንደገና እንዱጣራ በሚል ካዘዘው ነጥብ አኳያ ውሳኔው በውጤት ደረጃ የአፈፃፀም አቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ የሻረ በመሆኑ ውሳኔው ሉፈፀም የሚችል አይደለም ሲል የተጠሪን አቤቱታ በብይን ውድቅ በማድረግ በዋናው ጉዲይ ላይ ክርክሩ እንዱቀጥል አዟል። ይኸው ብይን እስከ ከተማ አስተዲዲሩ ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ክርክር ቀርቦበት ፀንቷል።
ዋናውን ክርክር በተመለከተ ሐምል 01/2008 ዓ.ም በዋለው ችልት ክርክር የተነሳበትን ቤት አስተዲደሩ በመመሪያ ቁጥር 4/2004 መሰረት የአሁን ተጠሪን ተጠቃሚ ያደረገበት ሁኔታ አግባብ አለመሆኑን ማረጋገጡን ጠቅሶ በአሁን አመልካች ላይ የተፈጠረው ሁከት ሉወገድ ይገባል ሲል ወስኗል። የአሁን ተጠሪ ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለአስተዲደሩ ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም።
በመቀጠል ተጠሪ የሰበር አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት አቅርበው በሰ/መ/ቁ/140055 ላይ ሲታይ ቆይቶ መጋቢት 24/2010 ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ አስተዲደሩ በቅሬታ ሰሚ አካል ጉዲዩን በማጣራት የአሁን ተጠሪ በመመሪያ ቁጥር 4/2004 አንቀፅ 6(1) መሰረት ልዩ ተከራይነት ሉፈቀድላቸው እንደሚገባ ያሳለፈው ውሳኔ ለአስተዲደሩ በህግ ከተሰጠው ሥልጣን ውጭ የተወሰነ ነው ወይም በህግ የተመለከቱ ሁኔታዎችን ወይም የተዘረጋውን ስርዓት ባለመከተል የተወሰነ ነው የሚያሰኝ ባለመሆኑ የአስተዲደሩ ውሳኔ ፈራሽ የሚሆንበት ምክንያት የለም በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ሽሯል።
ይህንን ተከትል የአሁን ተጠሪ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱን አስመልክቶ ጥቅምት 08/2006 ዓ.ም በተሰጠው ውሳኔ መሰረት እንዱፈፀምላቸው ሚያዝያ 26/2010 ዓ.ም የተፃፈ የአፈፃፀም አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም በዚሁ ጉዲይ ላይ የአመልካችን መልስ ከሰማ በኋላ ጥቅምት 16/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት አፈፃፀም የተጠየቀበት ውሳኔ ቀደም ሲል የአሁን ተጠሪ የአፈፃፀም አቤቱታ አቅርበዉበት ሐምል 17/2006 ዓ.ም በተሰጠ ብይን ሉፈፀም የሚችል ውሳኔ የለም በሚል ውድቅ የተደረገ በመሆኑ እና ይህ ብይን ፀንቶ ባለበት የአፈፃፀም ጥያቄው በድጋሚ መቅረቡ አግባብ አይደለም በማለት የተጠሪን አቤቱታ በብይን ውድቅ አድርጓል።
በአሁን ተጠሪ ይግባኝ ባይነት በዚሁ ውሳኔ ላይ ጉዲዩ የቀረበለት የከተማው ይግባኝ ሰሚ ችልት የተጠሪን ይግባኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት ዘግቷል። የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በበኩለ በመ/ቁ/30140 ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሐምል 18/2011 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ የአሁን ተጠሪ ቀደም ሲል አቅርበዉት የነበረው የአፈፃፀም አቤቱታ ሐምል 17/2006 ዓ.ም በተሰጠ ብይን ውድቅ የተደረገው ከፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ክርክሩ ሳይቋጭ የቀረበ ጥያቄ ነው በሚል መሆኑን፤ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱን አስመልክቶ በመስተዲድሩ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ይግባኝ ተጠይቆበት ያልተለወጠ በመሆኑ ፀንቶ ያለ ውሳኔ መሆኑን፤ በኋላም እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በተደረገ ክርክር የአሁን ተጠሪ ክርክር በቀረበበት ቤት ላይ በፍርድ የተረጋገጠ መብት ያገኙ በመሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል ፍርደ ሉፈፀም አይችልም ያለበት ምክንያት ቀሪ መሆኑን ተገንዝቦ አፈፃፀሙን ማስቀጠል ሲገባው በድጋሚ የቀረበ ነው በሚል ውድቅ ማድረጉ በህግ አግባብ የተሰጠ ፍርድንና በፍርድ የተረጋገጠውን የተጠሪን መብት ዋጋ የሚያሳጣ መሆኑን በመግለፅ የስር ፍርድ ቤቶችን ብይን እና ትዕዛዝ ሽሮ በአፈፃፀም አቤቱታው መሰረት ጥያቄውን ተቀብል እንዱያስፈፅም ጉዲዩን ለመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ መልሷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ነሐሴ 9/2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በከተማ አስተዲደሩ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የቀድሞ ውሳኔዎች እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ደርሰው ሉፈጸም የሚችል ነገር የለም ተብል በተሻረበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤት አፈፃፀም ይቀጥል በማለት የወሰነበትን አግባብ ለዚ ችልት ቀርቦ እንዱጣራ በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ነጥብ አኳያ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንግዱህ ከላይ በፍርድ ሀተታው ላይ በዝርዝር ከተመለከተው የክርክሩ አመጣጥ በግልፅ መረዲት እንደሚቻለው ግራ ቀኙን ለዚህ የሰበር ችልት ክርክር ያበቃው የአሁን ተጠሪ ያቀረቡትን የፍርድ አፈፃፀም አቤቱታን አስመልክቶ በስር ፍርድ ቤቶች የተወሰደው አቋም ነው። የአፈፃፀም አቤቱታው የቀረበለት የከተማ አስተዲደሩ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥያቄውን ውድቅ ያደረገው ቀደም ሲል ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦ ሉፈፀም የሚችል ውሳኔ የለም በሚል ውድቅ የተደረገ በመሆኑ በድጋሚ ላቀርብ አይገባም በሚል ምክንያት ነው።
በመሰረቱ አፈፃፀም የሚቀርበው በፍርድ በተረጋገጠ መብት ላይ ነው። የአፈፃፀም ጥያቄ የቀረበበት መብት ፍርድ ያረፈበት ቢሆንም በተለያየ ምክንያት ፍርደ በሙለም ሆነ በከፉል ሉፈፀም የማይችል ስለመሆኑ አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት ከተረዲ ስለፍርደ አፈፃፀም ትዕዛዝ ላሰጥ እንደማይገባ፤ ይልቁንም ፍርደ ሉፈፀም በሚችልበት በማናቸው ጊዜ እንደፍርደ እንዱፈፀም ሉታዘዝ የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 392(2) ይደነግጋል። ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ የሚቻለው መሰረታዊ ቁም ነገር በፍርድ የተረጋገጠ መብት እንደማናቸውም ክርክር ተቆጥሮ በድጋሚ የቀረበ ነው በሚል ሙግት ላቀርብበት የሚቻል ሳይሆን መብቱ እስከሚፈፀም ድረስ አመቺ በሆነ ጊዜ ሁለ ስለአፈፃፀሙ ተገቢው ትዕዛዝ ላሰጥ የሚቻል መሆኑን ነው። እናም የአፈፃፀም አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት በዋናነት ማረጋገጥ ያለበት የአፈፃፀም ጥያቄ የቀረበበት ጉዲይ ፍርድ ያረፈበት እና ጥያቄው በቀረበበት ወቅት ሉፈፀም የሚችል መሆኑን እንጂ የአፈፃፀም ጥያቄው ስንት ጊዜ ቀረበ የሚለው አይደለም።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች የሁከት ክስ ያቀረቡበትን ቤት አስመልክቶ የአሁን ተጠሪ አቅርበዉት በነበረው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ መነሻነት አመልካች ቤቱን ለተጠሪ እንዱለቁ እና ውዝፍ የቤት ኪራይም እንዱከፍለ ውሳኔ ተሰጥቷል። ይህ ውሳኔ ይግባኝ ተጠይቆበት ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ስለመለወጡም በአመልካች በኩል የቀረበ ክርክር የለም። እንዱያውም ውሳኔው ይግባኝ ያልተጠየቀበት ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች የውሳኔ ግልባጭ ያሳያል። በእርግጥ ይህንን ቤት በተመለከተ ከግራ ቀኙ መካከል ማን ህጋዊ የተከራይነት መብት እንዲለው አስመልክቶ በተለያየ ጊዜ እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ክርክር ሲደረግበት ቆይቷል። የመጀመሪያው የአፈፃፀም አቤቱታ የቀረበውም ይኸው የመብት ማረጋገጥ ክርክር መቋጫ ባላገኘበት ወቅት በመሆኑ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት በዚያ ደረጃ ውሳኔው የሚፈፀም አለመሆኑን ጠቅሶ የአፈፃፀም አቤቱታውን ውድቅ አድርጓል።
የተከራይነት መብቱን አስመልክቶ በግራ ቀኙ የቀረበው ክርክር በየደረጃው ባለት ፍርድ ቤቶች ሲታይ ቆይቶ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁ/140055 ላይ መጋቢት 24/2010 ዓ.ም በተሰጠ ፍርድ መብቱ የአሁን ተጠሪ ስለመሆኑ በውሳኔ ተረጋግጧል። የአሁን ተጠሪ ድጋሚ የአፈፃፀም አቤቱታ ያቀረቡትም ይህንኑ መነሻ በማድረግ ነው። እናም የቤቱ የተከራይነት መብት የአሁን ተጠሪ ስለመሆኑ በፍርድ በተረጋገጠበት እና ከዚሁ ቤት ጋር በተያያዘ አመልካች ውዝፍ ኪራይ ከፍለው ቤቱን ለአሁን ተጠሪ እንዱያስረክቡ የተሰጠ እና የፀና ውሳኔ ባለበት የአፈፃፀም ጥያቄው ድጋሚ የቀረበ ነው ተብል ውድቅ መደረጉ በእርግጥም በፍርድ የተረጋጠ መብትን ዋጋ ያሳጣ መሰረታዊ የህግ አረዲድ እና አተረጓጎም ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። የከተማ አስተዲደሩ ሰበር ሰሚ ችልትም ይህንኑ ተገንዝቦ በየደረጃው ያለትን ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመሻር አፈፃፀሙ እንዱቀጥል ማለቱ የጉዲዩን ባህሪ እና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁር 392 ድንጋጌን መንፈስ የተከተለ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍበት ነጥብ የለውም። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/30140 ላይ ሐምል 18/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የዚህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.