ፍርድ ቤቶች ተከሳሽ ሳይቀርብ ቀርቶ ጉዲዩ በላለበት የሚታይ ወይም ተከሳሹ ቀርቦ መቃወሚያውን ያላነሳው ቢሆንም ከሳሽ ያቀረበው ክስ አስቀድሞ ፍርድ ባገኘ ጉዲይ ላይ የቀረበ መሆኑን በክርክሩ ሑደት ባረጋገጡ ጊዜ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 ድንጋጌ የተመለከቱት መስፈርቶች መሟላታቸው እስከተረጋገጠ ጊዜ ድረስ አዱስ የቀረበውን ክስ አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ ነው በማለት ውድቅ የማድረግ ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ (የፋ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት በፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በሰ/መ/ መዝገቦች ላይ ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ተለውጧል።)
No summary available.
መስከረም 27/2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡ ወ/ሮ ተሰሜ ገዲ ቀርበዋል ተጠሪዎች፡
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዲዩ በፍርድ ቤት በተሰጠ የወራሽነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቅት ላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 መሰረት የቀረበ መቃወሚያን የሚመለከት ሲሆን የሰበር አቤቱታው የቀረበውም የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/310729፤ ሰኔ 10/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ በማፅናት የሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ለማስለወጥ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ እንዱህ ነው። የአሁን አመልካች ወላጅ አባታቸው አቶ ገዲ ኡርጌሳ መስከረም 11/2010 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን እና ሟች በህይወት እያለ በስማቸው ተመዝግቦ የይዞታ ማረጋጋጫ ምስክር ወረቀት የተሰጠበት 1.61 ሄክታር የገጠር እርሻ መሬት ያላችው መሆኑን በመግለፅ የወላጅ አባታቸው ወራሽ መሆናቸው ተረጋግጦ የወራሽነት ምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው ለዱክሰስ ወረዲ ፍርድ ቤት ባመለከቱት መሰረት ፍርድ ቤቱ በመ/ቁ/15004 ላይ ህዲር 17/2011 ዓ.ም ይህንኑ አረጋግጡ የወራሽነት ምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል። ይህ ከሆነ በኋላ የአሁን ተጠሪዎች ጥር 2/2011 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ በፍርድ ቤቱ የተሰጠው የወራሽነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መብታችንን ነክቷል በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 358 መሰረት ውሳኔውን በመቃወም ይቀርባለ።
የአቤቱታቸው ይዘትም አመልካች የወራሽነት ምስክር ወረቀት በወሰደበት ይዞታ ላይ ቀደም ሲል የአመልካች ወንድሞች በዚያው ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/14008 ተመሳሳይ የውርስ ክስ በተጠሪዎች ላይ አቅርበው ጥያቄያቸው በይርጋ ይታገዲል ተብል ውድቅ ተደርጎ ይኸው ውሳኔ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የፀና መሆኑን፤ ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ በይዞታቸው ላይ ለአመልካች የተሰጠው የወራሽነት ምስክር ወረቀት መብታችንን የሚጎዲ በመሆኑ የተሰጠው የወራሽነት ምስክር ወረቀት ሉሰረዝ ይገባል የሚል ነው።
አመልካች ለዚሁ መቃወሚያ በሰጡት መልስ መኖሪያ ቦታቸው ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዲ በመሆኑ በመዝገብ ላይ ተደረገ የተባለውን ክርክር እንደማያውቁ፤ የወራሽነት ምስክር ወረቀት የወሰደበት ይዞታ የወላጅ አባታቸው ሲሆን እስከ 2010 ዓ.ም ድርስ በወላጅ አባታቸው ስም ግብር ሲገበርበት የቆየ መሆኑን፤ የአሁን ተጠሪዎች ይዞታውን በኪራይ ለረዥም ጊዜ ሲያርሱ የነበረ በመሆኑ ከይዞታው ላይ የተወሰነውን በመጀመሪያ ዙር የይዞታ ምዝገባ በወላጅ አባታቸው ከተመዘገበ በኋላ ሁለተኛ ዙር አመልካች ባላወቁት መንገድ በስማቸው ከማስመዝገባቸው ውጭ ከይዞታው ላይ መብት የላላቸው መሆኑን በመግለፅ መቃወሚያቸው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ሞግተዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ጉዲዩ ከዚህ በፉት በአመልካች ወንድሞችና በተጠሪዎች መካከል ክርክር ተካሂድበት ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ አመልካች የመውረስ መብት የላቸውም በማለት ቀድሞ የሰጠውን የወራሽነት ማረጋገጫ ማስረጃውን ሰርዟል። ይኸው ውሳኔ በአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ሆነ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ፀንቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ነው። አመልካች ነሐሴ 01/2011 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። መሰረታዊ ይዘቱም የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/79871 ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች ይህንን ተላልፈው በተጠሪዎች መቃወሚያ አቤቱታ መነሻነት የወራሽነት ማረጋጋጫ ማስረጃቸውን መሰረዛቸው አግባብ እንዲልሆነ፤ የወራሽነት ምስክር ወረቀት የተሰጠበት ይዞታም የሟች አባታቸው መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ተጠሪዎች በስማቸው ሳያስመዘግቡ በሀሰት ምስክርነት ውሳኔ መሰጠቱ የአመልካችን የመውረስ መብት የሚያሳጣ መሆኑን፤ ተጠሪዎች በይዞታው ላይ በጉልበታቸው እያለሙ ከአመልካች አባት ጋር በእኩል ሲጠቀሙ የነበረ ከመሆኑ ውጭ ከይዞታው ላይ የሚጠይቁ መብት የላላቸው መሆኑን፤ ተጠሪዎች የሀሰት ማስረጃ አያይዘው ከሆነም የስር ፍርድ ቤቶች ተጨማሪ ማስረጃ በማቅረብ ጉዲዩን ማጣራት ሲገባቸው ከላልች ሰዎች ጋር ሲከራከሩ የተሰጠ ውሳኔን መሰረት አድርገው በህግ አግባብ የተሰጣቸውን የወራሽነት ማስረጃን መሰረዛቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት መሆኑን በመጥቀስ የተሰጠው ውሳኔ ሉሻር ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የአመልካች የወራሽነት ማስረጃ የተሻረበት አግባብ ግራ ቀኙ በተገኙበት በዚህ ችልት እንዱፈተሽ በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
በዚሁ አግባብ ተጠሪዎች የካቲት 03/2012 ዓ.ም በተፃፈው ባቀረቡት መልስ አመልካች የአባቷ ወራሽ ብትሆንም መሬቱን ተጠሪዎች በህግ አግባብ ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ በስማቸው ተመዝግቦ ካርታ ተሰርቶላቸው ግብር እየገበሩበት ከ30 ዓመት በላይ ይዘው እየተጠቀሙ ያለ መሆኑን፤ የአመልካች ወንድሞች በዚሁ መሬት ላይ ቀደም ሲል ክስ አቅርበዉባቸው እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ የተወሰነላቸው መሆኑን፤ አመልካች የግል ይዞታቸውን ከተጠሪዎች ይዞታ ጋር ቀላቅለው የወራሽነት ማስረጃ የወሰደበት በመሆኑ እና ውሳኔው መብታቸውን የሚነካ በመሆኑ መቃወማቸውም ሆነ የስር ፍርድ ቤቶችም በመቃወሚያ መሰረት ማስረጃውን መሰረዛቸው አግባብ መሆኑን በመግለፅ ተከራክረዋል። አመልካች የሰበር ቅሬታቸውን የሚያጠናክር የመል መልስ በማከል ሞግተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክር ይዘት አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ፤ በስር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ጥር 358 መሰረት የፍርድ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችለው አካል ቀድሞ በተደረገው ክርክር የሙግቱ አካል ላሆን ይችል የነበረ ሆኖ እርሱ ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር በተሰጠው ውሳኔ መብቱ የሚነካው ማናቸውም አካል ስለመሆኑ እና መቃወሚያውም ላቀርብ የሚገባው ፍርድ ከመፈፀሙ በፉት ስለመሆኑ ከድንጋጌው ይዘት መረዲት ይቻላል።
በልላ በኩል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ጥር 358 መሰረት የሚቀርብ የፍርድ መቃወሚያ ወራሽነትን ለማረጋገጥ በሚሰጥ ማስረጃ ላይ ላቀርብ እንደማይችል፤ ይልቁንም በማስረጃውም ምክንያት መብቴ ተነክቷል የሚል አካል ካለ ተገቢውን ዲኝነት ከፍል ተጓደለብኝ የሚለውን መብት ማረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ ይኸው ችልት በሰ/መ/ቁ/79871 ላይ የካቲት 11/2005 ዓ.ም በዋለው ችልተ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት ችልት የሚሰጠው የህግ ትርጉም በማናቸውም ደረጃ ባለት የፋዳራልም ሆነ የክልል ፍርድ ቤቶች ላይ የአስገዲጅነት ኃይል ያለው ስለመሆኑ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ እንደገና ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀፅ 2/4/ ይደነግጋል።
ሆኖም የሰበር ችልቱ የህግ ትርጉም የአስገዲኝነት ባህሪ የሚኖረው በምን ዓይነት ጉዲይ ላይ ነው የሚለውን ማየቱ ተገቢ ይሆናል። ይህንን ጉዲይ በተመለከተ በሰበር ችልቱ የሚሰጠው የህግ ትርጉም የአስገዲጅነት ኃይል ወይም ባህሪ የሚኖረው ቀድሞ በተሰጠው የህግ ትርጉም እና ዲኝነት ተጠይቆበት በክርክር ላይ ባለው ጉዲይ መካከል ተመሳሳይ የፍሬ ነገር እና የህግ ክርክር ሲኖር ብቻ እንደሆነ (The same fact and the same question of law) ይኸው ችልት በሰ/መ/ቁ/67924 እና በላልች በርካታ መዝገቦች ላይ ትርጉም ተሰጥቶ አቋም ተይዟል።
የሰበር ችልቱ የሚሰጠው የህግ ትርጉም አስገዲጅ እንዱሆን የተፈለገው በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ ህጎች በተመሳሳይ ሁኔታ ተተርጉመው እንደ ሀገር ወጥ እና የተረጋጋ የህግ ሥርዓት እንዱሰፍን ለማስቻል እንጂ ችልቱ በማናቸውም መልኩ የሚጠቅሳቸው ጉዲዮች በሙለ እንደ ህግ እንዱወሰደ አይደለም።
ከዚህ አንፃር በሰ/መ/ቁ/79871 ላይ ቀርቦ ትርጉም የተሰጠበት ጉዲይ ወራሽነታቸውን በፍርድ ቤት አረጋግጠው ማስረጃውን መሰረት በማድረግ የውርስ ሃብት ነው በሚል የያዙትን ንብረት የሚመለከት ክርክር ሲሆን በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ክርክር ደግሞ የውርስ ሀብት ተለይቶ በሀብቱ ላይ የተሰጠ የወራሽነት ምስክር ወረቀትን የሚመለከት ነው። እናም በሁለቱ ጉዲዮች መካከል ተመሳሳይ የህግ እና የፍሬ ነገር ክርክር ባለመኖሩ በሰ/መ/ቁ/79871 የተሰጠው ትርጉም በዚህ መዝገብ ላይ ለቀረበው ጉዲይ አግባብነት ያለው ባለመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ አስገዲጅ የህግ ትርጉምን ተላልፎል የሚባል አይደለም።
ከዚህ በመለስ ለአሁን አመልካች የተሰጠው የወራሽነት ማስረጃ የአሁን ተጠሪዎች በፍርድ መብት ባገኙበት ይዞታ ላይ የተሰጠ ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ መረጋገጡን ከቀረበው የስር ፍርድ ቤቶች የፍርድ ግልባጭ መገንዘብ ተችሎል። አመልካች የወራሽነት ማስረጃ የወሰደበት ሀብት ላላ ሰው በፍርድ መብቱን ባረጋገጠበት ሀብት ላይ ስለመሆኑ ከተረጋገጠ ቀደም ሲል የተሰጠው ማስረጃ መሰረዝ ያለበት በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች በዚህ መልኩ በመወሰናቸው የፈፀሙት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/310729 ላይ ሰኔ 10/2011 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፤ የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/88043 ላይ የካቲት 29/2011 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና የዱክሰስ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/15004 ላይ የካቲት 12/2011 ዓ.ም የሰጠው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የዚህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.