No summary available.
ጥር 25/2013 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ ሸለመ አበራ ተጠሪዎች፡
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ድንጋጌን መሰረት አድርጎ የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/303165 ላይ ሚያዚያ 29/2011 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የክርክሩ ሥረ ነገር የጀመረው የአሁን አመልካች በወንጪ ወረዲ ፍርድ ቤት በአሁን 2ኛ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። የክሱም ይዘት ቦታ እና አዋሳኙ በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተመለከተው ይዞታ የወላጅ አባታቸው መሆኑን፤ አባታቸው በ1992 ዓ.ም ከሞቱ ወዱህ የአሁን 2ኛ ተጠሪ በውርስ ሉተላለፍላቸው የሚገባውን የአባታቸውን ድርሻ ይዘው የሚገኙ መሆኑን በመግለፅ እንዱያካፍሎቸው የሚጠይቅ ነው። የአሁን 2ኛ ተጠሪም “አመልካች የአባታቸውን ድርሻ ቢካፈለ ተቃውሞ የለኝም” የሚል መልስ ሰጥተዋል። በዚሁ ጉዲይ ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ወላጅ አባት በአመልካች እና 2ኛ ተጠሪ መካከል የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 አቤቱታ አቅርበዋል። የአቤቱታው ጭብጥም “ግራ ቀኙ ተከራክረዉበት ውሳኔ ያረፈበት ይዞታ በ1ኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቢሆንም ይዞታነቱ የራሴ በመሆኑ ውሳኔው በይዞታዬ ላይ የተሰጠ ነው” የሚል ነው። የመቃወም አቤቱታው የቀረበለት ፍርድ ቤትም በአቤቱታው ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ግንቦት 22/2010 በዋለው ችልት የመቃወም አቤቱታውን ውድቅ አድርጓል።
ይህ ከሆነ በኋላ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ግንቦት 29/2010 ዓ.ም በተፃፈ የመቃወም አቤቱታ በአመልካች እና 2ኛ ተጠሪ መካከል የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 አቤቱታ አቅርበዋል። የመቃወም አቤቱታው መነሻም “ውሳኔ ያረፈበት ይዞታ ነባር ይዞታነቱ የአመልካች ወላጆች ቢሆንም ‘ግብር መገበር አልቻልንም’ በሚል ይዞታውን ለአስተዲደሩ በመመለሳቸው ምክንያት በ1989 ዓ.ም ተሰጥቶኝ እስከ 1992 ዓ.ም ድረስ ሳርስ ቆይቼ ከ1992 በኋላ ደግሞ በቦታው ላይ ዛፍ እና ፅድ ተክዬበት ከ21 ዓመት በላይ በእጅ አድርጌ እየተጠቀምኩበት ያለ ይዞታዬ በመሆኑ በይዞታዬ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ሉሰረዝ ይገባል” የሚል ነው።
በዚሁ አቤቱታ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት የአሁን አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ መቃወሚያ እና የስረ ነገር ክርክር በማቅርብ ተከራክረዋል። የመቃወሚያው ይዘትም የመቃወም አቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ በተመለከተ ቀደም ሲል የመቃወም አቤቱታ አቅራቢ ወላጅ አባት ይዞታው በ1ኛ ተጠሪ ስም የሚገኝ ቢሆንም የራሴ ነው፤ 1ኛ ተጠሪም የአእምሮ ታማሚ እና ከእኔ ጋር የሚኖር በመሆኑ ውሳኔው በይዞታዬ ላይ የተሰጠ ነው በሚል ያቀረቡት የመቃወም አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል፤ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ከወላጅ አባቱ ጋር የሚኖር በመሆኑ ይህ ሲሆን ያውቃል፤
አቤቱታውም የቀረበው የክርክሩን ውጤት በመጠበቅ ወላጅ አባቱ ሞክሮ ያልተሳካለትን በ1ኛ ተጠሪ በኩል ለማሳካት ተመሳጥረው ያቀረቡት ነው፤ ክርክር መደረጉን እያወቁ ውጤቱን በመጠበቅ የመቃወም አቤቱታ ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁ/56745 ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሰጠ በመሆኑ የመቃወም አቤቱታ ሉያቀርብበት አይችልም የሚል ነው። በሥረ ነገር ክርክሩ ደግሞ ውሳኔ ያረፈበት ይዞታ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ወላጅ አባት ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ በእኩላታ ሲያርሱ የቆዩ ከመሆኑ ውጭ ይዞታው የ1ኛ ተጠሪ አይደለም፤ 1ኛ ተጠሪ ይዞታው ከመንግስት ተሰጠኝ ባለበት 1989 ዓ.ም ህፃን የነበረ በመሆኑ በራሱ ስም ይዞታ ለማግኘት በሚያስችለው እድሜ ላይ አልነበረም፤ አሁንም ቢሆን 1ኛ ተጠሪ የመንግስት ሰራተኛ እንጂ ገበሬ ባለመሆኑ ይዞታው የራሴ ነው በሚል ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም በመቃወም አቤቱታው ላይ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን በመስማት እንዱሁም ስለይዞታው ከክፍለ መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት ተጣርቶ እንዱቀርብለት ካደረገ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ክርክር የቀረበበት ይዞታ ነባር ይዞታነቱ የአሁን አመልካች ወላጅ አባት ነው፤ ይህንን ይዞታ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ይዞ እያረሰ የሚገኘው የመቃወም አቤቱታ አቅራቢው ሳይሆን ወላጅ አባታቸው ነው፤ የመቃወም አቤቱታ አቅራቢ ወላጅ አባት ደግሞ ይዞታውን በተመለከተ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ያቀረቡት አቤቱታ ግንቦት 22/2010 ዓ.ም በዋለው ችልት ውድቅ ተደርጓል፤ የይዞታው ስም ሀብት በመቃወም አመልካች ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቢሆንም ይዞታውን ያገኘበት መንገድ የማይታወቅ ስለመሆኑ ከክፍለ አስተዲደር የተገለፀ በመሆኑ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መያዛቸው ብቻ ከፍ/ብ/ህ/ቁ/1146(1-3) መሰረት የሚፈጥርላቸው የይዞታ መብት የለም፤ የይዞታ ማረጋጋጫ ምስክር ወረቀት በፍ/ብ/ህ/ቁ/1196 መሰረት ሉስተባበል የሚችል ማስረጃ በመሆኑ እና የመቃወም አመልካች ማስረጃውን ያገኘበት መንገድ የማይታወቅ እና ሥርዓቱን የጠበቀ ባለመሆኑ የሚያጎናፅፊቸው መብት የለም በማለት አቤቱታውን ውድቅ አድርጓል። የአሁን 1ኛ ተጠሪ ይህንኑ ውሳኔን በመቃወም ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህግ ቁጥር 337 መሰረት ውድቅ ተደርጓል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በበኩለ ከላይ በመግቢያው ላይ በተመለከተው የመዝገብ ቁጥር እና ቀን በሰጠው ውሳኔ ለክርክር ምክንያት የሆነው ይዞታ ከ20 ዓመት በላይ በአሁን 1ኛ ተጠሪ እጅ የሚገኝ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ መሆኑን፤ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 40(3 እና 7) መሰረት መሬት በርስት የማይተላለፍ የህዝብ እና የመንግስት የጋራ ሀብት በመሆኑ ከ20 ዓመት ቆይታ በኋላ አመልካች ያቀረበው ጥያቄ በክልለ ገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀፅ 32 መሰረት በይርጋ ይታገዲል በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሽሯል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ሐምል 16/2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። መሰረታዊ ይዘቱም 1ኛ ተጠሪ የመቃወም አቤቱታ ያቀረቡበትን ውሳኔ አስመልክቶ ቀደም ሲል ወላጅ አባታቸው ተመሳሳይ የመቃወም አቤቱታ አቅርበው ውድቅ መደረጉ እና የአሁን 1ኛ ተጠሪም የዚህኑ ክርክር ውጤት ጠብቀው መቃወምያውን ያቀረቡ ለመሆኑ የቀረበው ክርክር እያሳየ አቤቱታው ተቀባይነት ማግኘቱ አግባብ አይደለም፤ ክርክር የቀረበበት ይዞታንም በተመለከተ 1ኛ ተጠሪ በማይታወቅ መንገድ የይዞታ ማረጋገጫ ከመያዛቸው በቀር ይዞታውን ይዘውም ሆነ ተጠቅመውበት እንደማያውቁ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ አባቱ በይዞታው ተጠቅሟል በሚል ለልጁ የይርጋ መብት መሰጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፤ የ1ኛ ተጠሪ ወላጅ አባትም ቢሆኑ በይዞታው መጠቀም የጀመሩት በ2001 ዓ.ም መሆኑን እና የአመልካች ወላጅ አባት በ1992 ዓ.ም ሲሞቱ አመልካች የ5 ዓመት ህፃን የነበረ ስለመሆኑ ተረጋግጦ እያለ ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን ጊዜ በመቁጠር ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ክርክር ያስቀርባል በመባለ ተጠሪዎች የፅሁፍ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል። በዚሁ አግባብ ተጠሪዎች መጋቢት 02/2012 ዓ.ም የተፃፈ የተናጠል መልስ አቅርበዋል። የ1ኛ ተጠሪ መልስ መሰረታዊ ይዘትም ክርክር በተነሳበት ይዞታ ላይ ውሳኔ መሰጠቱን ያወቅሁት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ እንጂ ከዚያን በፉት ወላጅ አባቴ አቅርበዋል ስለተባለው የመቃወም አቤቱታም ሆነ ስለክርክሩ የማውቀው ነገር የለም፤ ይዞታውን በተመለከተ የአመልካች እናትና አባት በ1988 ዓ.ም መሬት ለማስተዲደር ስልጣን ላለው አካል ቀርበው የመሬት ግብር መክፈል አለመቻላቸውን በመግለፃቸው ምክንያት ከነበራቸው ይዞታ ላይ ተቀንሶ አሁን ክርክር የቀረበበት ይዞታ ተሰጥቶኝ እስከ 1992 ዓ.ም ድረስ ካረስኩ በኋላ በ1992 ዓ.ም ፅድና ባህርዛፍ ተክዬበት እና ቤት ሰርቼበት እንዱሁም በ1996 ዓ.ም የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ወስጄበት እየተጠቀሙበት የምገኝ ህጋዊ ይዞታዬ እንጂ የውርስ ይዞታ አይደልም፤ በዚህ መልኩ ይዞታውን በእጄ አድርጌ ስጠቀምበት አመልካች የሚያውቅ ሲሆን ያቀረበው መቃወሚያ አለመኖሩን የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አረጋግጦ ጥያቄን ውድቅ ያደረገ በመሆኑ ውሳኔው የሚነቀፍ አይደለም የሚል ነው። 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው በአመልካች ጥያቄ መሰረት ቢወሰንለት ቅሬታ የላላቸው መሆኑን ገልፀዋል። አመልካችም የሰበር ቅሬታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ በመስጠት ሞግተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም ጉዲዩን መርምሯል። በዚሁ መሰረት የአሁን 1ኛ ተጠሪ የመቃወም አቤቱታውን ያቀረቡት ክርክር መኖሩን እያወቁ የክርክሩን ውጤት በመጠበቅ በመሆኑ የመቃወም አቤቱታ ልታቀረቡ አይገባም በማለት በአሁን አመልካች የቀረበው መቃሚያ የታለፈበት አግባብ በቅድሚያ መጣራት ያለበት ነጥብ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ጥር 358 መሰረት የፍርድ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችለው ቀድሞ በተደረገው ክርክር የሙግቱ አካል ላሆን ይችል የነበረ ሆኖ እርሱ ባላወቀው እና ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር በተሰጠው ውሳኔ መብቱ የሚነካ ሶስተኛ ወገን ነው። ከዚህ ድንጋጌ ተግባራዊ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ አንድ ሰው መብቱን የሚነካ ክርክር መጀመሩን እያወቀ የክርክሩን ውጤት ጠብቆ መብቱን የሚነካበት ሆኖ ባገኘው ጊዜ ከውሣኔው በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 መሰረት ፍርደን ሉቃወም የማይችል ስለመሆኑ ይኸው ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁ/56795 ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል። መቃወሚያ አቅራቢው ቀድሞ ሲደረግ የነበረውን ክርክር የሚያውቅ መሆኑን ያለመሆኑ ጉዲይ ደግሞ የህግ ነጥብ አልያም በችልት ግንዛቤ ሉወሰድበት የሚችል ክርክር ሳይሆን ተከራካሪ ወገኖች በሚያቀርቡት አግባብነት ያለው ማስረጃ ነጥሮ የሚወጣ የፍሬ ነገር ክርክር በመሆኑ ከዚህ አኳያ ተከራካሪዎች የሚያቀርቡት ክርክር እና ማስረጃ በአግባቡ ላታይ የሚገባው ጉዲይ ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ በሰጡት መልስ 1ኛ ተጠሪ ከወላጅ አባቱ ጋር በአንድ ቤት የሚኖር በመሆኑ እና አባቱ የመቃወም አቤቱታ አቅርቦ ውድቅ ሲደረግበት ክርክሩን ያውቅ የነበረ በመሆኑ የክርክሩን ውጤት ጠብቆ መቃወሚያ ሉያቀርብ አይገባም በማለት ተቃውመዋል። 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸው በዚህ መልኩ የቀረበውን ክርክር ክደዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ “ቀድሞ ሲደርግ የነበረውን ክርክር ማወቅ” የሚለው ሀረግ ለፍርድ መቃወሚያ አቤቱታው መሰረት የሆነውን ክርክር ብቻ የሚመለከት ነው ወይስ ፍርደን በመቃወም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 መሰረት ቀርቦ የተደረገውን ክርክርንም የሚጨምር ነው የሚለው በአግባቡ መታየት ያለበት ጉዲይ ነው። እንግዱህ ከላይ እንደተመለከተው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 መሰረታዊ ዓላማ ባላወቀው እና ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር በተሰጠ ፍርድ መብቱ የተነካበት አካል ከፍርደ በኋላ መብቱን የሚያስከብርበትን ሥርዓት መዘርጋት ነው። ከዚህ መሰረታዊ ዓላማ አኳያ የመቃወም አቤቱታ አቅራቢው ክርክር እየተደረገ ስለመሆኑ የነበረው እውቀት በዋናው ጉዲይ ላይም ሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 መሰረት በቀረበ አቤቱታ ላይ መሆኑ የሚያመጣው ለውጥ የለም። እናም መብቴን እና ጥቅሜን ነክቷል በተባለ ፍርድ ላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 መሰረት ክርክር ሲደረግ የነበረ መሆኑን የሚያውቅ አካል ውጤቱን ጠብቆ ከፍርድ በኋላ በራሱ ፍርደን በመቃወም የሚያቀርበው አቤቱታ ፍርድን መቃወም ከተፈቀደበት መሰረታዊ ዓላማ ውጭ በመሆኑ ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም።
በተያዘው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ የመቃወም አቤቱታ ባቀረቡበት ፍርድ ላይ ቀድሞ ሲደረግ የነበረውን ክርክር ከማወቃቸው ጋር ተያይዞ ግራ ቀኙ ተካክደዋል። ይህ ከሆነ ደግሞ 1ኛ ተጠሪ በእርግጥም እውቀቱ የነበራቸው መሆን ያለመሆኑ ጉዲይ ግራ ቀኙ ባቀረቡት ማስረጃ በአግባቡ አጣርቶ መወሰንን ይጠይቃል። ከዚህ አንፃር የወረዲው ፍርድ ቤት የ1ኛ ተጠሪ ወላጅ አባት ቀደም ብለው የመቃወም አቤቱታ አቅርበው ውድቅ የተደረገባቸው ስለመሆኑ በፍርድ ሀተታው ውስጥ ከመግለፁ ውጭ 1ኛ ተጠሪ ያንን ክርክር ያውቁ የነበረ መሆኑ ስላለመሆኑን አስመልክቶ ያደረገው ማጣራትም ሆነ ከቀረበው መቃወሚያ አኳያ የወሰደው ግልፅ አቋም የለም። 1ኛ ተጠሪ ቀድሞ ሲደረግ የነበረውን ክርክር ማወቅ ያለማወቃቸው ጉዲይ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 ድንጋጌ ይዘት እና መንፈስ አኳያ 1ኛ ተጠሪ የመቃወም አቤቱታ ማቅረብ የሚችለ መሆን ካለመሆኑ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው። ከዚህ አንፃር የወረዲው ፍርድ ቤት ይህንን ነጥብ በግራ ቀኙ ማስረጃ በተገቢ አኳኋን አጣርቶ አቋም ሳይያዝ በልላው የክርክር ዘንግ ላይ ውሳኔ መሰጠቱ እና በየደረጃው ያለት የክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶችም ይህንን ሳያርሙ መቅረታቸው መሰረታዊ የሙግት አመራር ግድፈት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/303165 ላይ ሚያዝያ 29/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍትኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/47133 ላይ ታህሳስ 04/2011 ዓ.ም የሰጠው ብይን እንዱሁም የወንጪ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/18497 ላይ ህዲር 19/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ “ቀድሞ የተደረገውን ክርክር እያወቁ ውጤቱን ጠብቀው የመቃወም አቤቱታ ያቀረቡ በመሆኑ ፍርደን ሉቃወሙ አይችለም” በማለት አመልካች ያቀረቡት መቃወሚያ በተገቢው ማስረጃ ተጣርቶ አቋም ሳይያዝበት በልላው የክርክር ዘንግ ላይ ውሳኔ መሰጠቱ መሰረታዊ የሙግት አመራር ግድፈት የተፈፀመበት ነው በማለት ተወስኗል።
የወንጪ ወረዲ ፍርድ ቤት በውሳኔ የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ፤
3.1. የአሁን 1ኛ ተጠሪ የመቃወም አቤቱታ ያቀረቡበት ጉዲይ ላይ ክርክር ሲደርግ ያውቁ የነበረ መሆን ስላለመሆኑ ግራ ቀኙ ቀድሞ በጠቀሷቸው ማስረጃዎች በማጣራት፤ ቀድሞ የተቆጠረ ማስረጃ ከላለም ከዚህ አኳያ ግራ ቀኙ አለን የሚለትን ማስረጃ እንዱያቀርቡ በማድረግ ፍሬ ነገሩን ካጣራ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ረገድ የሚኖረውን ውጤት በአግባቡ በመመርመር የመሰለውን እንዱወስን፤
3.2. 1ኛ ተጠሪ የመቃወም አቤቱታ ማቅረብ ይችላል የሚባል ከሆነ በሥረ ነገር ክርክሩ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር እና ቀድሞ የቀረቡትን ማስረጃዎች ይዘት በመመርመር እንዱሁም ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስፈላጊ መስል የታየውን ተጨማሪ ምስክር በመስማት ወይም ማስረጃ በማስቀረብ ማስረጃዎቹን ከቀረበው ክርክር አኳያ ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ መርምሮ እና መዝኖ የመሰለውን እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 343(1) መሰረት መዝገቡ ይመለስለት።
የዚህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.