No summary available.
ህዲር 28/2013 ዓ.ም ዳኞች፡- መዓዛ አሸናፉ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ አመልካች፡- ሀዊ ሁንዳ ተጠሪዎች፡
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ላቀርብ የቻለው በፍትሐ ብሕር ክስ ክርክር ተከሳሽ የነበረ ሰው በክርክር ላይ እያለ መሞቱን ተከትል የሟቹ ወራሾች ሟቹን አስመልክቶ የተሰጠውን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት ሉቃወሙ አይችለም በሚል የተወሰነበትን የህግ አግባብ መርምሮ ለመወሰን ነው።
ጉዲዩ እንዱህ ነው። የአሁን ተጠሪዎች የአመልካችን እናት ጨምሮ በሶስት ሰዎች ላይ የገጠር መሬት ይዞታን በተመለከተ በኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ሸዋ ዞን ግንደበረት ወረዲ ፍርድ ቤት ክስ ያቀርባለ። ጉዲዩ በክርክር ላይ እያለ የአሁን አመልካች እናት ከዚህ ዓመት በሞት ይለያለ። ክርክሩም በዚሁ ቀጥል ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የአሁን አመልካች ከእናታቻው አኳያ የተሰጠው ውሳኔ መብታቸውን የሚነካ መሆኑን ጠቅሰው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ ውሳኔን ለሰጠው ወረዲ ፍርድ ቤት ያቀርባለ። ፍርድ ቤቱም በመቃወም አቤቱታው ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ክርክር የቀረበበት ይዞታ የአሁን አመልካች እናት እና አባት መሆኑ እና በስማቸውም ተመዝግቦ የሚገኝ ስለመሆኑ አረጋግጫለሁ በሚል ምክንያት ቀድሞ የተሰጠውን ውሳኔ ሽሯል። በዚሁ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንኑ ውሳኔን አፅንቷል።
የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በበኩለ በመ/ቁ/305233 ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ሐምል 02/2011 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ አመልካች የመቃወም አቤቱታ ባቀረቡበት ጉዲይ ላይ የአመልካች እናት የክርክሩ ተካፊይ ሆነው በክርክር ላይ እያለ ከሞቱ አመልካች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 50 በሚያዘው መሰረት በእናታቸው እግር ተተክተው ክርክሩን ከሚያስቀጥለ በቀር በሚያውቁት ጉዲይ ላይ ውሳኔውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት ሉቃወሙ አይችለም በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ውድቅ አድርጓል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ነው። አመልካች ሐምል 05/2011 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። ፍሬ ቃለም የአሁን ተጠሪዎች ክርክር የተነሳበት ይዞታ ይገባናል የሚል መከራከሪያ ከማቅረብ ባለፈ አመልካች በመቃወም አመልካችነት ቀርባ ልትከራከር አይገባም የሚል ክርክር ባላቀረቡበት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ባልተነሳ ጉዲይ ላይ ውሳኔ መስጠቱ አግባብ አይደለም፤ ወላጅ እናት ከተጠሪዎች ጋር በክርክር ላይ የነበሩ ስለመሆኑ የማውቀው ነገር የለም፤ እናቴ በክርክር ላይ እያለ ሞሞታቸውን ፍርድ ቤቱ ከተረዲ ከእርሳቸው አንፃር ጉዲዩን ማቋረጥ ሲገባው ክርክሩን ቀጥል በተጠሪዎች ማስረጃ ብቻ ውሳኔ መስጠቱ ከሥነ ሥርዓት ውጭ በመሆኑ እና የስር ፍርድ ቤቶች ከዚህ አኳያ ስህተቱን አርመው የሰጡትን ውሳኔ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
No topics extracted.
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች የውርስ ሀብቱን ለመጠየቅ መብታቸው የሚቋቋመው እናታቸው ሲሞቱ ሆኖ እያለ የአሁን ተጠሪዎች ከአመልካች እናት ጋር ሲከራከሩ አመልካች ታውቅ ነበር በሚል ምክንያት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ያቀረቡትን መቃወሚያ ውድቅ ያደረገበት አግባብ ለዚህ ችልት ቀርቦ እንዱመረመር በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
በዚሁ አግባብ 24ኛ ተጠሪ መሞታቸው በመረጋገጡ ምክንያት ከእኚህ ተጠሪ ውጭ ያለት ተጠሪዎች በጠበቃቸው አማካኝነት ጥር 14/2012 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ ባቀረቡበት ጉዲይ ላይ ወላጅ እናታቸው በተከራካሪነት ተካፊይ የነበሩ ስለመሆኑ እና ላልች ተከሳሾች የነበሩትም የአመልካች ወንድሞች በመሆናቸው አመልካች ክርክሩን ታውቅ ነበር፤ አመልካች በክርክሩ ተካፊይ መሆን የሚፈልጉ ከሆነ አንድም በክርክር ላይ እያለ በሞቱት እናታቸው እግር ተተክተው ክርክሩን ማስቀጠል አልያም ከውሳኔው በኋላ ቅሬታ ካላቸው በይግባኝ ከሚያሳርሙ በቀር መብቱ በውርስ እንደተላለፈላቸው ወራሽ ሳይሆን መብቱ እንደተነካ 3ኛ ወገን ሆነው በፍርድ ተቃዋሚነት ሉቀርቡ አይችለም፤ ወሳኔውም በአፈፃፀም ያለቀ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት መቃወሚያ የሚቀርብበት ባለመሆኑ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት ነጥብ የለውም በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም የሰበር ቅሬታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም የቀረበውን ክርክር ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ጥር 358 መሰረት የፍርድ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችለው ቀድሞ በተደረገው ክርክር የሙግቱ አካል ላሆን ይችል የነበረ ሆኖ እርሱ ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር በተሰጠው ውሳኔ መብቱ የሚነካ ሶስተኛ ወገን ነው። አንድ ሰው ወይም አካል በፍርድ ቤት በተያዘ ክርክር የክርክሩ አካል ላሆን የሚችለው በፍርድ ቤት በሚሰጥ ትዕዛዝ፣ በራሱ በጣልቃ ገብ አቤቱታ አቅራቢነት አልያም በተከሳሽ ወገን ጥያቄ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 40፣ 41 እና 43 ድንጋጌዎች ይዘት መረዲት ይቻላል። ከእነዚህ በሂደት ላይ በሚገኝ ሙግት መግቢያ መንገድች ውስጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ጥር 358 መሰረት በፍርድ ተቃዋሚነት ላቀርብ የሚችለው በዋናነት ቀድሞ በተደረገው ክርክር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 41 በተመለከተው መሰረት በጣልቃ ገብነት ቀርቦ መብቱን እና ጥቅሙን ማስከበር ይችል የነበረ ሶስተኛ ወገን ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች ውሳኔ ያረፈበት ይዞታ የግል ይዞታዬ ነው በሚል ሳይሆን ከወላጅ እናቴ በውርስ ሉተላለፍልኝ የሚገባ ሀብት ነው የሚል ነው። አውራሻቸው የሆኑት ወላጅ እናታቸው ደግሞ ይህንን ይዞታ በተመለከተ በአሁን ተጠሪዎች ክስ ቀርቦባቸው በክርክር ላይ እያለ ስለመሞታቸው የተካደ አይደለም። ጉዲዩ ይህ ከሆነ ለክርክር ምክንያት የሆነውን ይዞታ በተመለከተ አመልካች የሚኖራቸው መብት ከአውራሻቸው የተላለፈላቸው እንጁ እራሱን የቻለ መብት ባለመሆኑ ወላጅ እናታቸው ተካፊይ ለነበሩበት ክርክር 3ኛ ወገን የሚባለ አይደለም።
ቀድሞ በተደረገ ክርክር እና በተሰጠ ውሳኔ 3ኛ ወገን ያልሆነ ሰው ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት በፍርድ ተቃዋሚነት የሚመጣበት የህግ አግባብ የለም። የአመልካች ጉዲይም በክርክር ላይ እያለ የሞተን ተከሳሽ መብት የሚመለከት በመሆኑ ጉዲዩ የሚመራው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 50 እና ተከታዮቹ ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት አመልካች በክርክር ላይ የነበሩት ወላጅ እናቴ ከሞቱ በኋላ ወደ ክርክሩ እንድገባ እና የክርክሩ አካል እንድሆን ለሟች ወራሾች ተገቢው መጥሪያ አልተደረገም የሚል መከራከሪያ በአመልካች በኩል አልቀረበም። ይህ ባልሆነበት አመልካች አውራሻቸው ተከራካሪ በነበሩበት ጉዲይ ላይ በፍርድ ተቃዋሚነት ቀርበው የሚከራከሩበት የህግ አግባብ ባለመኖሩ የክልለ ሰበር ችልት የደረሰበት ድምዲሜ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/305233 ሐምል 02/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የዚህን ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።