በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 839 እስከ 840 በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት አውራሽ ለውርስ አይገባም የተባለ ስለመሆኑ ወይም በዚሁ ሕግ በቁጥር 854 (1) ድንጋጌ መሰረት ውርሱን አልፈልግም ያለ ስለመሆኑ የቀረበ ተቃራኒ ክርክር ከላለ ጉዲዩ ይመለከተኛል በሚል ላላ ተከራካሪ ወገን የሚቀርብ ተቃራኒ ክርክር እና ማስረጃ ካለ የዚህ ዓይነቱ ክርክር እና ማስረጃ እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ ለውርስ አይገባም ያልተባለ እና ውርሱን አልፈልግም ያላለ ስለመሆኑ ግምት የሚወሰድና በፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 830 ድንጋጌ ስር የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ በመሆኑ የመውረስ መብት ያለው ስለመሆኑ አንድ ተተኪ ወራሽ የመውረስ መብት የማይኖረው አውራሹ የሆነ ሰው በሕይወት እያለ የመውረስ መብቱን ተግባራዊ በማድረግ ውርሱን ተካፍል ሲገኝ ስለመሆኑ ለአንድ ውርስ ወራሽ የሆነ ሰው ውርሱ ከተከፈተ በኋላ የሞተ እንደሆነ የወራሽነቱ መብቶች ለእርሱ ወራሾች የሚተላለፈና ወራሽ በህይወት እያለ ውርስ አልተከፈተም የሚባል ከሆነም አለመከፈቱ የወራሽነት መብት መተላለፍ ረገድ የሚያስከትለው ለውጥ የላለ ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 826፣ 833
No summary available.
የሰበር መዝገብ ታህሳስ 24 ቀን 2009 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ፀጋይ አስማማው ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሣሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- ወጣት አቡ ተሉለ - ጠበቃ ፍጹም ሐሞተ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቶአል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት በ1998 ዓ.ም. በሞት የተለዩትን አባታቸውን አቶ ተሉለ ደብሬን ተክተው በ1997 ዓ.ም. በሞት የተለዩትን አያታቸውን /የአባታቸውን እናት/ ወ/ሮ ቦንቱ ደላን የሚወርሱ ስለመሆኑ ተረጋግጦ የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰጣቸው ያቀረቡትን አቤቱታ የተመለከተው የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካች አባት የሞቱት እናታቸው ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ በመሆኑ አመልካች ያቀረቡት የተተኪ ወራሽነት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት በመዝገብ በ17/12/2008 ዓ.ም. የሰጠው እና በከተማው ፍርድ ቤቶች ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች እንደቅደም ተከተለ በመዝገብ በ03/01/2009 ዓ.ም. በመዝገብ በ12/01/2009 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል ነው።የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ የአመልካቹ አያት የሞቱት ከወላጅ አባቱ በፉት መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ የተተኪ ወራሽነት ጥያቄው ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ለማጣራት እንዱቻል ጉዲይ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለጉዲዩ ከተያዘው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት እናታቸው ማለትም የአመልካቹ አያት በሞቱበት ጊዜ ልጃቸው ማለትም የአመልካቹ አባት በሕይወት የነበሩ ስለመሆኑ አመልካቹ ለስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ገልጸዋል።አመልካች ለስር ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት የወራሽነት ደረጃቸው ተገልጾ የምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው በመጠየቅ ነው።በአቤቱታቸው ላይ በተጠሪነት የተሰየመ ተከራካሪ ባለመኖሩ የአመልካቹ አባት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 839 እስከ 840 በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ለውርስ አይገቡም የተባለ ስለመሆኑ ወይም በዚሁ ሕግ በቁጥር 854 (1) ድንጋጌ መሰረት ውርሱን አልፈልግም ያለ ስለመሆኑ የቀረበ ተቃራኒ ክርክር የለም።እንዱህ ከሆነ ደግሞ ጉዲዩ ይመለከተኛል በሚል ላላ ተከራካሪ ወገን የሚቀርብ ተቃራኒ ክርክር እና ማስረጃ ካለ የዚህ ዓይነቱ ክርክር እና ማስረጃ እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ የአመልካች አባት ለውርስ አይገቡም ያልተባለ ስለመሆኑ እና ውርሱን አልፈልግም ያላለ ስለመሆኑ ግምት የሚወሰድበት ይሆናል።እናታቸው በሞቱበት ጊዜ የአመልካች አባት በሕይወት የነበሩ ከሆነ እና ለውርስ አይገቡም ያልተባለ ከሆነ ደግሞ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 830 ድንጋጌ ስር የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟለ በመሆኑ እናታቸውን የመውረስ መብት ይኖራቸዋል።
አንድ ሰው የሞተ እንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያ ስፍራ በሆነበት ቦታ የሟቹ ውርስ የሚከፈት ስለመሆኑ እና በሟቹ ሞት ምክንያት የሚቋረጡ ካልሆኑ በቀር በውርሱ ውስጥ የሚገኙት የሟቹ መብቶች እና ግዳታዎች ለወራሾቹ እና የኑዛዜ ባለስጦታዎች የሚተላለፈ ስለመሆኑ በዚሁ ሕግ በቁጥር 826 የተመለከተ ሲሆን ለአንድ ውርስ ወራሽ የሆነ አንድ ሰው ውርሱ ከተከፈተ በኋላ የሞተ እንደሆነ የወራሽነቱ መብቶች ለእርሱ ወራሾች የሚተላለፈ ስለመሆኑም በቁጥር 833 ተደንግጎ ይገኛል።የአመልካች አባት በሕይወት እያለ የሟች እናታቸው ውርስ አልተከፈተም የሚባል ከሆነም አለመከፈቱ ከላይ በተጠቀሰው ድንጋጌ የሕግ ጥበቃ ባገኘው የወራሽነት መብት መተላለፍ ረገድ የሚያስከትለው ለውጥ አይኖርም።
የስር ፍርድ ቤቶች እንደገለጹት አመልካች አባታቸውን ተክተው ከአባታቸው በፉት የሞቱትን አያታቸውን የመውረስ መብት የማይኖራቸው አባታቸው በሕይወት እያለ የመውረስ መብታቸውን ተግባራዊ በማድረግ የእናታቸውን ውርስ ተካፍለዋል የሚባል ከሆነ ነው።የአመልካች አባት በሕይወት እያለ የእናታቸውን ውርስ የተካፈለ መሆን አለመሆኑ እና ተያያዥ ፍሬ ነገሮች ደግሞ አመልካች በቆጠሯቸው ምስክሮች ተጣርተው ተገቢው ውሳኔ የሚሰጥባቸው ከሚሆን በቀር የአመልካች አባት የሞቱት እናታቸው ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ መሆኑ መገለጹ ብቻውን የአመልካቹን የወራሽነት ማስረጃ ይሰጠኝ ጥያቄ ከወዱሁ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል አይደለም። በመሆኑም የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በማስረጃ ሳያጣራ የወራሽነት ደረጃቸው ተገልጾ የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው አመልካቹ ያቀረቡትን አቤቱታ ከወዱሁ ውድቅ በማድረግ የሰጠው እና በከተማው የበላይ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያገኘው ትዕዛዝ ከላይ የተጠቀሱትን የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ሕጋዊ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚቸል ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እና ሉታረም የሚገባው በመሆኑ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቶአል።
ተሰጥቶ በከተማው ፍርድ ቤቶች ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች እንደቅደም ተከተለ በመዝገብ በ03/01/2009 ዓ.ም. እና በመዝገብ በ12/01/2009 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ትዕዛዝ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሮአል።
ከላይ በፍርደ ክፍል በተገለጸው መሰረት አመልካቹ ያቀረቡትን አቤቱታ አስተናግድ በማስረጃ ካጣራ በኋላ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩ ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዱመለስ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 341 (1) መሰረት ወስነናል።
የውሳኔው ቅጂ ተገቢውን መፈጸም ያስችለው ዘንድ ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣እንዱያውቁት ደግሞ ለከተማው ፍርድ ቤቶች ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች ይላክ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቶአል።
No topics extracted.