አንድ ኑዛዜ አድራጊ ያለኑዛዜ ሉወርሱ የሚችለ ተወላጆችን በኑዛዜ በግልጽ ምክንያት ጠቅሶ ከውርስ መንቀል እንደሚችል እና ምክንያቱ ከውርስ ለመንቀል የሚያበቃ መሆኑን ካልሆነ በስተቀር የምክንያቱን ትክክለኛነት መመርመር አስፈላጊ ስላለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁጥር 937 እና 938
No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) እንዲሻው አዲነ ተሾመ ሽፈራው መላኩ ካሳዬ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች፡- 1ኛ.አቶ መስፍን ደባለ ወልደየስ 2ኛ.ወ/ሪት ገነት ደባለ ወልደየስ 3ኛ.አቶ ደረጀ ደባለ ወልደየስ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አልማዝ ደባለ ወልደየስ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በውርስ ማጣራት ሂደት ላይ ኑዛዜ እንዱፈርስ የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ለዚህ ሰበር ችልት ቅሬታ የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ በጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ላይ ነው። ጉዲዩ በተጀመረበት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካቾች ጣልቃ ገብ ተጠሪ ደግሞ አመልካች ነበሩ።
ተጠሪ በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የሟቾች አቶ ደባለ ወልደየስ እና የእናታችን የወ/ሮ ሶርሱ ልሳነወርቅ የውርስ ሀብት የውርስ አጣሪ ተሹሞ ይጣራልን በማለት አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱ የውርስ ሀብት ተጣርቶ እንዱቀርብ ትዔዛዛ ሰጥቷል። በውርስ አጣሪ ሪፕርቱ ላይ አመልካቾች ባቀረቡት አስተያየት ሟች እናታችን ለተጠሪ ያደረጉት ኑዛዜ ይፍረስልን በሚል ጠይቀው ፍርድ ቤቱም ውርስ እንዱጣራ በተጠየቀበት መዝገብ ላይ የኑዛዜ ይፍረስልኝ ክርክር ላታይ አይችልም። ነገር ግን ሟች እናታቸው ባደረጉት ኑዛዜ በየካ/ክ/ከተማ ወረዲ 12 የቤ/ቁ180 ላይ ያላቸውን ድርሻ ለተጠሪ ብቻ መናዘዛቸው ላልች ወራሾችን ከውርስ የሚነቅላቸው በመሆኑ የተደረገው ጠቅላላ ኑዛዜ ፈርሶ ተጠሪ ከላልች ወራሾች ጋር እኩል ይካፈለ ሲል የውርስ አጣሪ ሪፒርቱን በማሻሻል ወስኗል።
ተጠሪ ሟች እናታቸው ያደረጉት ኑዛዜ ሉፈርስ ይገባል መባለን በመቃወም ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ አመልካቾች ሟች እናታቸው በህይወት እያለ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት የሆነውን በየካ ክ/ከተማ ወረዲ 02 የቤት ቁጥር 180 በሆነው ይዞታ ውስጥ ባድ ቦታ ሰጥተዋቸው በግል ገንዘባቸው ቤት የሰሩበት መሆኑን አልካደም። ይህ ከሆነ ደግሞ አመልካቾች ሟች ወ/ሮ ሶርሱ ባደረጉት ኑዛዜ መነሻነት ከውርስ ሀብቱ ላይ ሉደርሳቸው ከሚገባው የሀብት ድርሻ ከ1/4 በላይ ጉዲት የደረሰባቸው ስለመሆኑ በማስረጃ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።
አመልካቾች ኑዛዜው ከ1/4ኛ በላይ ጉዲት የሚያደርስባቸው መሆኑን ባላስረደበት ሁኔታ ኑዛዜው አመልካቾችን ከውርስ ነቅሎል ልባል አይገባም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ሟች ወ/ሮ ሶርሱ ልሳነወርቅ ለተጠሪ ያደረጉት ኑዛዜ አመልካቾችን ከውርስ የነቀለ ነው ሲል የደረሰበት ድምዲሜም ሉታረም የሚገባው ነው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አሻሽሎል። አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ አጽንቷል።
አመልካቾች በህዲር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር ቅሬታ ሟች ወ/ሮ ሶርሱ ልሳነወርቅ ፈቅደውልን በባድ መሬት ላይ የሰራነው ቤት የውርስ ሀብት የሚባልበት አግባብ የለም። ባድ መሬት የመንግስት ነው። በመንግስት ቦታ ላይ በግል ገንዘባችን ቤት ሰራን እንጂ የውርስ ሀብት የሆነ አንድም ቤት አልተሰጠንም። የሟቾች የውርስ ሀብት የሆነው ዋናው ቤት በመሆኑ በዚህ ቤት ላይ የተሰጠ ኑዛዜ ተወላጅን የነቀለ በመሆኑ ሉፈርስ ይገባል። ሟች ወ/ሮ ሶርሱ ልሳነወርቅ ያላቸው የውርስ ሀብት በየካ ክ/ከተማ ወረዲ 02 የቤ/ቁ 180 የሆነው ቤት ብቻ ሲሆን ይህንኑም ለተጠሪ ብቻ የተናዘዙ እና ኑዛዜው አመልካቾችን ከውርስ የሚነቅል በመሆኑ ፈርሶ የውርስ ሀብቱን ወራሾች እኩል ልንካፈል ይገባል።
በመሆኑም የስር ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ ተሸሮ የስር የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይጽናልን በማለት ጠይቀዋል።
የአመልካቾች ቅሬታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ሟች ወ/ሮ ሶርሱ ልሳነወርቅ በቤት ቁጥር 180 ላይ 50% ለአሁን ተጠሪ እንዱሆን የተናዘዙት ኑዛዜ አመልካቾችን ከውርስ የሚነቅል በመሆኑ ኑዛዜው ይሻርልን ሲለ ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄን በተመለከተ አመልካቾች በሟች ወ/ሮ ሶርሱ ልሳነወርቅ ቦታ ተሰጥቷቸው ቤት ሰርተውበት እያለ እንዱሁም ከሚገባቸው ላይ ከ1/4 በታች ጉዲት ያልደረሰባቸው በመሆኑ ኑዛዜው ሉፈርስ አይገባም የመባለን አግባብነት ከሰበር መ/ አኳያ መጣራት ስላለበት ተጠሪ መልሳቸውን ይዘው እንዱቀርቡ ተጠይቀዋል።
ተጠሪ በየካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ አመልካቾች ሟች ያደረጉትን ኑዛዜ እንዱፈርስ በማለት ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ባልጠየቁበት ሁኔታ ሰበር አጣሪው እንደጠየቁ አድርጎ የደረሰበት ድምዲሜ በስር ፍርድ ቤቶች ከተደረገው ክርክርና ከተሰጠው ውሳኔ ውጭ ነው። የሰበር አጣሪው የጠቀሰው የሰ.መ. ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ነው። ሟች ወ/ሮ ሶርሳ ልሳነወርቅ አመልካቾችን ከውርስ ሀብት ላይ አልነቀለም ይልቁንም በህይወት እያለ ከይዞታቸው ላይ በመቀነስ ለእያንዲንዲቸው አመልካቾች ቤት መስሪያ ቦታ ሰጥተዋቸው ቤት ሰርተው እየተጠቀሙበት ይገኛለ።
ይህንን ሳይክደ ሟች ከውርስ ነቅለውናል ሲለ ያቀረቡት ክርክር ቅን ልቦና የጎደለው ነው። አመልካቾች ከሟች ወ/ሮ ሶርሱ ልሳነወርቅ ሉያገኙት ከሚገባው የውርስ ድርሻ ከሩብ (1/4) በላይ ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑን በተጨባጭ ሁኔታ አላስረደም። በመሆኑም የአመልካቾች አቤቱታ ተሰርዞ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት ነው ተብል ይጽናልኝ ብለዋል።
አመልካቾች በመጋቢት 05 ቀን 2015 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበዋል ።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ያስቀርባል ሲባል የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ በስር ፍርድ ቤት በማስረጃ ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እና ከተገቢው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው ተጠሪና የስር 2ኛ አመልካች የሟች እናት እና አባታቸው የውርስ ሐብት እንዱጣራ ሲጠይቁ የአሁን አመልካቾች ሟች እናታቸው ለ1ኛ ተጠሪ ያደረጉት ኑዛዜ ከውርስ ነቅልናል በሚል እንዱፈርስ ጠይቀዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤት ኑዛዜው ተወላጅ የሆኑትን አመልካቾችን ከውርስ ሐብት የሚነቅል ነው በሚል እንዱፈርስ የወሰነ ቢሆንም ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከቱት የፍደራል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሟች እናታቸው በህይወት እያለ ለአመልካቾች ባድ መሬት ሰጥተዋቸው ቤት የሰሩ በመሆኑ ምክንያት በኑዛዜው ላይ የተጠቀሰውን ቤት 1/2ኛ ድርሻ ለተጠሪ ብቻ መናዘዛቸው አመልካቾች ከውርስ ተነቅለዋል የሚያስብል አይደለም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ድምዲሜ ቀይረዋል። አመልካቾች በሟች እናታቸው ባድ መሬት ተሰጥቷቸው ቤት የሰሩ መሆኑን አይክደም። አጥብቀው የሚከራከሩት ባድ መሬት የመንግስት ነው። በመሬቱ ላይ በግል ገንዘባችን ቤት መስራታችን የውርስ ድርሻ እንዲገኘን ሉያስቆጥር አይገባም በሚል ነው። በእርግጥ ባድ መሬት የመንግስት እና የህዝብ ሐብት መሆኑ በሕገ-መንግስቱ እና በላልች ሕጎች የተገለጸ ጉዲይ ነው።
ይህ ማለት ግለሰቦች በመሬት ላይ የሚኖራቸው መብት የመጠቀም እንጂ የባለቤትነት መብት አይደለም። በዚህም መሰረት የአመልካች እናት የራሳቸው ይዞታ የነበረን መሬት ለአመልካቾች መስጠታቸው ሟች በይዞታው ላይ የነበራቸውን የመጠቀም መብት ማስተላለፊቸውን የሚያሳይ ነው።
ስለዚህ አመልካቾች በሟች እናታቸው ባድ መሬት ተሰጥቷቸው ቤት መስራታቸውን ሳይክደ ባድ መሬት መሰጠቱ ንብረት እንደተሰጣቸው ተደርጎ ሉቆጠር እንደማይችል አድርገው የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
የአመልካቾች እናት ባደረጉት ኑዛዜ ላይ ለአመልካቾች አስቀድሞ ስጦታ ያደረጉላቸው መሆኑን በመግለጽ አከራካሪውን ቤት ተጠሪ ብቻ እንዱወርሱ መናዘዛቸውን የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ ግልባጭ ያሳያል። አንድ ኑዛዜ አድራጊ ያለኑዛዜ ሉወርሱ የሚችለ ተወላጆችን በኑዛዜ በግልጽ ምክንያት ጠቅሶ ከውርስ መንቀል እንደሚችል እና ምክንያቱ ከውርስ ለመንቀል የሚያበቃ መሆኑን ካልሆነ በስተቀር የምክንያቱን ትክክለኛነት መመርመር አስፈላጊ አለመሆኑን ከፍ/ሕ/ቁጥር 937 እና 938 ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። በተያዘው ጉዲይ የአመልካቾች እናት አመልካቾችን በኑዛዜ ከውርስ ሐብት የነቀለት ለአመልካቾች አስቀድሞ ስጦታ መስጠታቸውን በመግለጽ ነው። የኑዛዜ አድራጊው ለተወላጅ አስቀድሞ በስጦታ ንብረትን ማስተላለፈ የስጦታ ተጠቃሚን በኑዛዜ ከውርስ ሐብት ለመንቀል እንደበቂ ምክንያት ሉወሰድ የሚችል ነው። በመሆኑም አመልካቾች በሟች እናታቸው አስቀድሞ ስጦታ የተደረገላቸው መሆኑ ተገልጾ በኑዛዜ ከውርስ ሐብት በግልጽ መነቀላቸው ሕጉን የተከተለ በመሆኑ ኑዛዜው የሚፈርስበት ምክንያት የለም።
ሲጠቃለል የአመልካቾች እናት ያደረጉት ኑዛዜ አመልካቾችን ከውርስ ሐብት የነቀለ ቢሆንም የተነቀለበት ምክንያት በኑዛዜ የተጠቀሰ እና ይህ ምክንያትም ከውርስ ሐብት ለመንቀል የሚያበቃ በመሆኑ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከቱት የፍደራል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሟች ያደረጉት ኑዛዜ ሉፈርስ አይገባም በሚል በሰጡት ውሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም። በመሆኑም ተከታዩ ተወስኗል።
1ኛ. የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በነሐሴ 06 ቀን 2013 ዓ.ም እና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ በጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል።
2ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸውን ይቻለ።
No specific laws extracted.
No topics extracted.