በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የክርክር ተካፊይ የሚሆኑ ሰዎች ለክርክሩ የግድ አስፈላጊ የሆኑ (indispensable party) ባልተሳተፈበት ክርክር መብት እና ጥቅማቸው ወይንም ግዳታቸውን የሚነካ ተካፊይ ባልሆኑበት ክርክር የሚሰጠው ፍርድ ወይንም ውሳኔ ውጤት የማይኖረው ሰዎች ሲሆኑ እና በክስ በተከሳሽነት ተካፊይ መሆን የሚገባውን ከሳሽ ያላጣመረው ቢሆንም ለቀረበዉ ክስ የመከላከያ መልስ እንዱሰጥበት በፍርድ ቤት ሉታዘዝ የሚገባ ስለመሆኑ የፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 39(1) እና 40(2)
No summary available.
መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ ቀነዓ ቂጣታ ብርሃኑ መንግሥቱ ማርታ ተካ አመልካች፡- ወ/ሮ ላዋይ መሃሪ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ባወቀ አምባዉ - አልቀረቡም መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረዉ መርምሮ ተገቢዉን ትእዛዝ ለመስጠት በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ተጠሪ በአመልካች ላይ በአማራ ክልል በምዔራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ የመሰረቱት በመካከላችን የነበረዉ የሽያጭ ዉል በፍርድ ቤት እንዱፈርስ ስለተወሰነ አመልካች በሽያጭ ዉለ የተቀበለት ነዉ ያለትን ብር 112,500.00 እና በይዞታዉ ላይ ያፈሩት ንብረት ግምት ነዉ ያለትን ጨምሮ በድምሩ ብር 3,017,500.00 አመልካች እንዱከፍለ እንዱወሰንላቸዉ ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች ክስ የቀረበበት ጉዲይ አስቀድሞ በዋድ አዱስዓለም ንዐስ ወረዲ ፍርድ ቤት በተደረገ ክርክር በመ/ ላይ በተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ እልባት ባገኘ ጉዲይ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበ ክስ ስለሆነ ዉድቅ ይደረግልኝ የሚል እና ላልች መከራከሪያዎችን በማቅረብ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በመ/ ላይ በማከራከር እንዱሁም አስቀድሞ በግራ ቀኙ መካከል ክርክር ተደርጎበት የነበረዉን መዝገብ አስቀርቦ በመመርመር ተጠሪ ክስ የመሰረቱት አስቀድሞ በመ/ ላይ ክርክር ተደርጎ ዉሳኔ የተሰጠበትን ቤትና አትክልት በተመለከተ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 244(2/ለ) እና 245/2 መሰረት ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ዉድቅ አድርጓል።ተጠሪ በዉሳኔዉ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በመ/ ላይ አከራክሮ በሰጠዉ ዉሳኔ አስቀድሞ በግራ ቀኙ መካከል በመ/ ላይ ክርክር ተደርጎ በተሰጠ ዉሳኔ ላይ ተጠሪ ቤቱን በማፍረስ አትክልቶቹን በመቁረጥ እንዱያነሱ ስለተወሰነ ለእነዚህ ንብረቶች ግምት እንዱከፈላቸዉ ያቀረቡት ክስ ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ከዚህ አኳያ የተጠየቀዉን ዲኝኘት ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ብይን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5/1ን የተከተለ ነዉ በማለት በማጽናት ተጠሪ በፈረሰዉ የሽያጭ ዉል መነሻ አመልካች የተቀበለትን ገንዘብ ለማስከፈል ያቀረቡት ክስና የጠየቁት ዲኝነት ግን አስቀድሞ ዉሳኔ የተሰጠበት ባለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ከዚህ ዲኝኘት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የሰጠዉ ብይን ስህተት ነዉ በማለት ሽሯል።ይህንን ተከትልም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ የሽያጩን ገንዘብ በተመለከተ ግራ ቀኙን አከራክሮና አጣርቶ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ ይስጥበት በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341/1 መሰረት ጉዲዩን መልሶለታል።
በመቀጠል አመልካች የሰበር አቤቱታቸዉን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ችልቱ በመ/ቁጥር 03-125708 ላይ በቀን 06/10/2015ዓ/ም በሰጠዉ ትዕዛዝ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341 መሰረት ጉዲዩን ለስር ፍርድ ቤት በመመለስ የሰጠዉ ዉሳኔ የመጨረሻ ፍርድ ባለመሆኑ በሰበር ላታይ የሚችል አይደለም በማለት አቤቱታቸዉን ዉድቅ አድርጓል።
አመልካች በቀን 27/10/2015 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችልቶች የተሰጠዉ ዉሳኔ እና ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ያስባላቸዉን ምክንያት በመዘርዘር ነዉ። ሰበር አጣሪ ችልት በአመልካች የሰበር አቤቱታ ላይ የተጠቀሱትን ምክንያቶች በመቀበል የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች ያቀረቡትን መቃወሚያ በከፉል ዉድቅ በማድረግ ጉዲዩን ለስር ፍርድ ቤት በመመለስ በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ የተፈጸመ ስህተት መኖር አለመኖሩ እንዱመረመር በሚል ጉዲዩን ለሰበር ሰሚ ችልት አስተላልፎል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን በኢፋዱሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 80(1/ሀ) ፣ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 4(1/ሀ፣ለ እና ሸ)፣ 2/5 እና አንቀጽ 10(1/ሐ እና መ) እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 320 ስር ከተደነገጉት መመዘኛዎች አንጻር መርምሯል።በኢፋዱሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 80(3/ሀ) እና በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2(4/ሀ፣ለ እና ሸ)፣10(1/ሐ እና መ) መሰረት በክልል ጉዲይ ላይ በተሰጠ ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የሚችለዉ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 2/5 ስር እንደተመለከተዉ በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ዉሳኔ ከተሰጠበት ብቻ ነዉ።
በኢፋዱሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 80(3/ለ) ስር እንደተመለከተዉ በክልል ጉዲዮች ላይ በክልለ ፍርድ ቤቶች በተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቀብል በሰበር ችልት የማየትና የማረም ሥልጣን ተሰጥቶታል።
በተጨማሪም የመጨረሻ ዉሳኔ ምንነት የበለጠ ለመገንዘብ በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 320 ስር የተዘረጋዉን ሥነ ሥርዓታዊ ደንቦች መመልከት ያስፈልጋል።ይህ ደንብ እንደአግባብነቱ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወጣዉ የሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አንቀጽ 20/1 መሰረት ለሰበር ክርክርም ተፈጻሚነት አለዉ።በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 320/1 መሰረት ይግባኝ ወይም የሰበር አቤቱታ ማቅረብ የሚቻለዉ በመጨረሻዉ ዉሳኔ ላይ ሲሆን አንድ ዉሳኔ የመጨረሻ ዉሳኔ ነዉ የሚባለዉ ደግሞ በዚሁ ሕግ በቁጥር 320(3 እና 4) ጣምራ ንባብ መሰረት ማንም ሰዉ እንዱታሰር ወይም በማረፉያ ቤት ተይዞ እንዱቆይ የተሰጠ ትእዛዝ ካልሆነ በስተቀር እንዱሁም ከሥረ ነገሩ ፍርድ በፉት አንድ ተከራካሪ ወገን በእጁ ያለዉን ንብረት ለላላዉ ወገን እንዱያዘዉር የተሰጠ ዉሳኔ ካልሆነ በስተቀር በሥረ ነገሩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት ጊዜያዊ አገልግልት ባለዉ ትዕዛዝ ላይም ሆነ በሥረ ነገሩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት በሚቀርብ መከራከሪያ ላይ በሚሰጥ ዉሳኔ ላይ ብቻ ይግባኝ ማቅረብ አይቻልም።
በያዝነዉ ጉዲይ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የስር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በከፉል በማጽናት በከፉል ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341/1 መሰረት ለስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት መልሷል።በዚህ መልኩ ከተሰጠዉ ዉሳኔ የጸናዉ ክፍል ለአመልካች የሚጠቅም በመሆኑ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች የሰበር አቤቱታ የሚያቀርቡበት ስርዓት የለም።አመልካች ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ሉያቀርቡ የሚችለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341/1 መሰረት በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ ሲሆን በዚህ መልኩ ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ገና የመጨረሻ ዉሳኔ ባልተሰጠበት ጉዲይ ላይ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነዉ በማለት ሰርዞታል።ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በዚህ መልኩ በሰጠዉ ትእዛዝ ላይ ጭምር ነዉ።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ሆነ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ዉሳኔ እና ትእዛዝ አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለተጠሪ ሉከፍለ ይገባል በማለት የመጨረሻ ዉሳኔ የሰጡበት አይደለም። ዉሳኔዉ ከዉጤት አንጻር ሲታይ አመልካች ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ዉድቅ ተደርጎ የተወሰነበት ነዉ። ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341/1 መሰረት ከተመለሰ በኋላ የመጨረሻ ዉሳኔ ሲያገኝ አመልካች በመጨረሻዉ ዉሳኔ ካልተስማሙ አቅርበዉ የነበረዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ዉድቅ መደረጉን በተመለከተ ጭምር በሥነ ሥርዓት ሕጉ እና አግባብ ባለዉ ላላ ሕግ መሰረት ይግባኝና የሰበር አቤቱታ ማቅረብ የሚችለበት መብት አላቸዉ። በተገለጸዉ መሰረት በጉዲዩ ላይ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም ሆነ በይግባኝ ሰሚዉ ችልት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 80(3/ለ) ፣ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/5 እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 320/3 ስር በተደነገገዉ መሰረት የመጨረሻ ዉሳኔ ስላልተሰጠ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ታይቶ ሉመረመር የሚችል የመጨረሻ ዉሳኔ የለም። በመሆኑም የአመልካች የሰበር አቤቱታ በሰበር ችልቱ ለመታየት ብቁ ስላልሆነ ተጠሪን መጥራት ሳያስፈልግ ተሰርዟል። በዚህ መዝገብ ላይ የተሰጠዉ የዔግድ ትአዛዝ ተነስቷል።ይጻፍ።መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ፍ/ደ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.