No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) ላሉሴ ደሳለኝ ተሾመ ሽፈራው መላኩ ካሳዬ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን፡- አልቀረቡም ተጠሪ፡- ሐያት ሆስፑታል ሜዱካል ኮላጅ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፡- ጠበቃ ፍቅሬ ሞያ - ቀረበ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአክስዮን ማህበር አባላት መካከል የአክስዮን ድርሻ በሽያጭ ሲተላለፍ እንደውህደት ተቆጥሮ ለአመልካች የውህደት ማስታወቂያ የሚሰጥ መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረበት በንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የዲኝነት ችልት የአሁን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካች በግንቦት 26 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው ክስ ተጠሪ በትምህርት አገልግልት የንግድ ስራ ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ካፑታለ ብር 132,000,000 ደርሷል። ከማህበሩ አባል አንዶ የሆኑት ወ/ሮ ዲንሴ ጉርሙ የአንደ ዋጋ ብር 1000 የሆነ 95,000 አክስዮኖች በድምሩ የብር 95,000,000 የአክስዮን ድርሻ የነበራቸው ሲሆን በተጨማሪም ከአቶ ኢብራሂም ናውድ 22,400 አክስዮኖች አጠቃላይ ዋጋቸው ብር 22,400,000 የሆነ እና ከዶ/ር አህመድ ኢብራሂም 4,800 አክስዮኖች አጠቃላይ ዋጋቸው ብር 4,800,000 የሆነ ገዝተዋል። በአዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 9/3/ለ መሰረት የንግድ ማህበር አክስዮኖች በሽያጭ ከአንድ ሰው ወደላላ ሰው ሲተላለፍ የውህደት ድርጊት እንደተፈጸመ ተቆጥሮ የውህደት ማስታወቂያ ለአመልካች መቅረብ አለበት። ተጠሪ የውህደት ማስታወቂያ ለአመልካች ባለማቅረቡ ውህደቱ በንግድ ውድድር ላይ ሉያስከትል የሚችለው አለታዊ ተጽኖ እንዲይጠና አድርጓል። በመሆኑም ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 42/4 መሰረት ከአመታዊ የሽያጭ ገቢው 10% እንዱቀጣ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪም በሐምል 11 ቀን 2011 ዓ.ም አሻሽል ባቀረበው መልስ የሕክምና አገልግልት እና የህክምና ትምህርት መስጠት ስራ ከማንም ላላ ድርጅት ጋር ሳልዋሀድ ብቻዬን በመስራት ላይ እገኛለሁ። ተጠሪ ተጠቃሚውን በአገልግልት ዋጋም ሆነ በልላ ሁኔታ ለመጉዲት እና የገበያ የበላይነት ለማግኘት ከማንኛውም ግለሰብ ነጋዳ፣ድርጅት ወይም ሸሪክ ጋር የንግግርም ሆነ የድርጊት ግንኙነት አላደረኩም።
ይህ በላለበት አንድ ድርጅት ውህደት ፈጥሯል ልባል አይችልም። ወ/ሮ ዲንሴ ጉርሙ ያደረጉት የአክስዮን ሽያጭ ግብይት እንጂ የንግድ ግብይት አይደለም። የአክስዮን ገዢም ሆኑ ሻጭ ነጋዳዎች አይደለም። የአዋጁ አንቀጽ 9/3/ለ ተፈጻሚ የሚሆነው አክስዮኖቹ በአንድ ባለአክስዮን ተጠቃለው ሲያዙ እንጂ አብላጫ እና አናሳ የአክስዮን ባለድርሻዎች ባለበት አይደለም። ወ/ሮ ዲንሴ ጉርሙ ከፍተኛ ባለአክስዮን ቢሆኑም በማኔጅመንት ስራ ውስጥ ስለላለ ውህደት ፈጥረው ገበያ አዛብተዋል ወይም ሸማቾችን ጎድተዋል የሚያስብል አይደለም። የአክስዮን ሽያጭ ውለም ውህደት መደረጉን የሚያስረዲ አይደለም። ውህደት አለ ቢባል እንኳን በጅምር ያለ እና ያልተጠናቀቀ ነው። በመሆኑም ክሱ ተገቢነት የላለው ስለሆነ ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክሯል።
የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የዲኝነት አካል የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የአዋጁ አንቀጽ 9 እና 10 የማስታወቅ ግዳታን ያስቀመጠው ማንኛውም ነጋዳ በሚል ነው። የአክስዮን ሽያጭ እና ግዢው የተፈጸመው በተጠሪ ሳይሆን በተጠሪ ማህበር አባላት መካከል ነው። አባላቱ ደግሞ ነጋዳ ስለመሆናቸው አመልካች በማስረጃ አላረጋገጠም። የአዋጁ አንቀጽ 9/3/ለ ተፈጻሚነትም የንግድ ማህበር አክስዮኖች በቀጥታ ከማህበሩ በመግዛት የራስ ሲደረጉ ወይም የላላ ሰውን የንግድ መደብር መቆጣጠር ሲቻል ነው። ከዚህ ውጪ በአክስዮን ማህበር አባላት መካከል የአክስዮን ሽያጭ ሲደረግ ድንጋጌው ተፈጻሚነት የለውም። በመሆኑም ተጠሪ ማስታወቂያ ሳያቀርብ የውህደት ድርጊት ፈጽሟል ልባል አይችልም በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታውን ለባለስልጣኑ ይግባኝ ሰሚ አስተዲደር ፍርድ ቤት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው የአስተዲደር ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ በአዋጁ አንቀጽ 9/3/ለ መሰረት በባለአክስዮኖች መካከል የአክስዮን ሽያጭ ሲደረግ የውህደት ስምምነት የተፈጸመ በመሆኑ ይህን የውህደት ድርጊት በአዋጁ አንቀጽ 10/1 መሰረት ተጠሪ ለአመልካች የማሳወቅ ግዳታ አለበት። በመሆኑ ተጠሪ የውህደት ማስታወቂያ ሳያቀርብ በውህደት ተግባር መሳተፈ ጥፊተኛ ስለሆነ በአዋጁ አንቀጽ 42/4 መሰረት ከአመታዊ የሽያጭ ገቢው 5% ሉቀጣ ይገባል በማለት የስር የዲኝነት አካለን ውሳኔ ሽሯል። በዚህ ውሳኔ ላይ ደግሞ ተጠሪ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የአክስዮን ሽያጩ በአባላት መካከል መደረጉ አከራካሪ አይደለም። በዚህ የሽያጭ ሂደት ላይ ተጠሪ ስለመሳተፈ በአመልካች የቀረበ ማስረጃ የለም። ባለአክስዮኖች የአክስዮን ሽያጭ ላይ መሳተፊቸው ተጠሪ በውህደት ስምምነቱ ወይም በቅንብሩ ተሳትፎል የሚያስብል አይደለም። በመሆኑም ተጠሪ የማስታወቅ ግዳታ ሳይኖርበት በስር የዲኝነት አካለ የተሰጠው ውሳኔ መሻሩ ተገቢ አይደለም በሚል የአመልካች መስሪያ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮ የስር የአመልካች የዲኝነት አካል የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል። አመልካችም ይህንን ውሳኔ በመቃወም የሚከተለውን የሰበር ቅሬታ አቅርቧል።
አመልካች በሐምል 08 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር ቅሬታ ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያለው ድንጋጌ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 9/3/ለ ነው። በዚህ ድንጋጌ ላይ አንድ ሰው ወይም ብዙ ሰዎች በግዢ ወይም በልላ በማንኛውም መንገድ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ሁኔታ የንግድ ማህበር አክስዮኖችን የራስ ሲያደረጉ የውህደት ድርጊት እንደተፈጸመ እንደሚቆጠር ተደንግጓል። ይህንን ድንጋጌ ከአዋጁ አንቀጽ 2/16 ጋር አጣምሮ በማንበብ በአንድ ወይም በብዙ ሰዎች አማካይነት የንግድ ማህበር አክስዮኖች የራስ ሲደረጉ እንደውህደት ስምምነት እንደሚቆጠር መረዲት ይቻላል። አክስዮኖች የራስ ሉደረጉ የሚችለት ደግሞ በነጋዳዎች ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ሰው ነው። በውህደት መመሪያም አክስዮን የሚገዙ አባላት ነጋዳ ሉሆኑም ላይሆኑም እንደሚችለ ተደንግጓል። የአክስዮን ዝውውር የተደረገበት የተጠሪ ማህበርም ነጋዳ ነው። የውህደት ማስታወቂያ መቅረብ ያለበት አንድ ማህበር ከላላ ማህበር ጋር ሲዋሀድ ብቻ ሳይሆን በአንድ ማህበር ውስጥ ያለ ባለአክስዮኖች ላላ ነጋዳ ላልሆነ ሰው ሲያስተላልፈ እንደውህደት ስለሚቆጠር በአዋጁ አንቀጽ 10/1 መሰረት ተጠሪ የውህደት ማስታወቂያ ለአመልካች የማቅረብ ግዳታ አለበት። ተጠሪ የውህደት ማስታወቂያ ማቅረቡ አመልካችን ውህደቱ የሚኖረውን ተጽኖ ለመመርመር ያስችለዋል። በመሆኑም የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ አመልካች የውህደት ምርመራ እንዱያከናውን በህግ የተሰጠውን መብት የሚያሳጣ መሰረታዊ የህግ ስህተት የፈጸመ ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር ቅሬታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የተፈጸመው የአክስዮን ሽያጭ ውህደትን ስለማያስከትል ለአመልካች የውህደት ማስታወቂያ ማቅረብ አያስፈልግም በሚል የተወሰነበትን አግባብ ከአዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 9/3/ለ፣ 10/1 እና ላልች አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንጻር ለማጣራት ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ ታዟል።
ተጠሪም በጥር 05 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ አዋጁ የውህደት ማስታወቂያ የመስጠት ግዳታ የጣለው ለነጋዳ ግለሰብ ወይም ማህበር ነው። አላማውም ተገቢ ባልሆነ የንግድ ውድድር የሸማቾች መብት እንዲይጎዲ ለመከላከል ነው። በተጠሪ ድርጅት የአክስዮን ዝውውር የተደረገው ነጋዳ ባልሆኑ ግለሰቦች መካከል ስለሆነ ተጠሪ የማስታወቅ ግዳታ የለበትም። በመሆኑም በስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል።
አመልካችም በየካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታውን አጠናክሯል።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ያስቀርባል ሲባል የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ በስር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እና ከተገቢው ህግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው የተጠሪ የካፑታል መጠን ብር 132,000,000 መሆኑ፤ የተጠሪ አክስዮን ማህበር አባል የሆኑት ወ/ሮ ዲንሴ ጉርሙ ከነበራቸው የብር 95,000,000 አክስዮን በተጨማሪ ከሁለት የአክስዮን ማህበሩ አባላት አክስዮኖችን ገዝተው ያላቸው የአክስዮን ዋጋ መጠን ወደ ብር 122,000,000 ከፍ ማለቱ፤ ወ/ሮ ዲንሴ ጉርሙም ሆኑ የአክስዮን ድርሻቸውን በሽያጭ ያስተላለፈት ግለሰቦች ነጋዳ አለመሆናቸው፤ የአክስዮን ሽያጩ ተጠሪ ባደረገው የባለአክስዮኖች ስብሰባ ላይ ጸድቆ የአክስዮን ዝውውሩ በሰነድች ማረጋገጫ እና ምዘገባ ኤጀንሲ የተመዘገበ መሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። አመልካች በተጠሪ የአክስዮን አባላት መካከል የአክስዮን ሽያጭ መደረጉ እንደ ውህደት ስለሚቆጠር ተጠሪ ለአመልካች የውህደት ማስታወቂያ የማቅረብ ግዳታ እያለበት ግዳታውን አልተወጣም በሚል የሚከራከር ሲሆን ተጠሪ በበኩለ የአክስዮን ሽያጭ የተደረገው ነጋዳ ባልሆኑ የማህበር አባላት መካከል ነው። በህጉ የውህደት ማስታወቂያ የመስጠት ግዳታ የተጣለው ደግሞ ነጋዳ ለሆነ ግለሰብ ወይም ማህበር በመሆኑ ተጠሪ የማስታወቅ ግዳታ የለብኝም በማለት ተከራክሯል።
በመሆኑም ለዚህ የግራ ቀኙ ክርክር እልባት ለመስጠት በህጉ እንደውህደት የሚቆጠሩት ድርጊቶች ምንድናቸው? ለአመልካች የውህደት ማስታወቂያ የመስጠት ግዳታስ የተጣለው በምን ሁኔታ እና በማን ላይ ነው? የሚለትን ነጥቦች መመርመር ያስፈልጋል።
በመጀመሪያም እንደ ውህደት የሚቆጠሩ ድርጊቶች ምንድናቸው? ወይም ወህደት ተደርጓል የሚባለው መቼ ነው? ለሚለው ነጥብ ምላሽ ለማግኘት ውህደት (Merger) ማለት ምንማለት ነው የሚለውን መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። በ2004 ዓ.ም የወጣው የምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ሀገራት ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት የንግድ ውድድር ደንብ (The common market for Eastern and Southern Africa/COMESA/ competition Regulation) በአንቀጽ 23 /1 ውህደት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንደሚከተለው ተተርጉሞ እናገኛለን።
«Merger means the direct or indirect acquisition or establishment of a controlling interest by one or more person in the whole or part of the business of a competitor, supplier, customer or other person whether that controlling interest is achieved as a result of; a. The purchase or lease of the shares or assets of the competitor, supplier, customer or other person; b. The amalgamation combination with a competitor, supplier, customer or other person; or c. Any means other than as specified in sub-paragraph a or b.» ይህም በግርድፈ ሲተረጎም ውህደት ማለት አንድ ድርጅት ወይም ግለሰብ የላላ ድርጅት አክስዮን በሙለ ወይም በከፉል በመግዛት ወይም በየግላቸው ሲሰሩ የነበሩ የንግድ ማህበራት በመቀላቀል ወይም አንድ በመሆን ወይም በልላ መንገድ የአክስዮን ማህበሩን ውሳኔ አሰጣጥ እና አጠቃላይ የንግድ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር የሚያስችል ተግባር ነው። በአውሮፒ ዩኒየን የውህደት ደንብ (European Community Merger Regulation) በተመሳሳይ ሁኔታ የውህደት ትርጉም ተሰጥቶ እናገኛለን።
በሀገራችን የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 ከአንቀጽ 9-13 ውህደትን ስለመቆጣጠር የተደነገጉ ድንጋጌዎች ሲሆኑ በአንቀጽ 9/3/ሀ እና ለ የውህደት ድርጊት ተፈጸመ የሚባለው መቼ እንደሆነ ተመልክቷል። ከዚህ ድንጋጌ ይዘት ውህደት ማለት ምን ማለት እንደሆነም መገንዘብ ይቻላል። በዚህም መሰረት ውህደት ማለት ግላዊ ተቋምነታቸውን ይዘው የነበሩ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ የንግድ ማህበራት ተቀላቅለው አንድ ማህበር ሲሆኑ ወይም አንድ አላማ ያለው የንግድ ስራ ለማከናወን ሁለንም ወይም ከፉለን ሀብታቸውን ሲያቀላቅለ ነው። በተጨማሪም ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም በአንድ ሰው ወይም በብዙ ሰዎች በግዢ ወይም በልላ በማንኛውም መንገድ የንግድ ማህበር አክስዮኖች፤ ሴኩሪቲዎች ወይም ንብረቶች የራስ ሲደረጉ ወይም የላላ ሰው የንግድ መደብርን አመራር መቆጣጠር እንደውህደት የሚቆጠር ይሆናል። በተለይም በተያዘው ጉዲይ የመጀመሪያው አከራካሪ ነገር በአክስዮን ማህበር አባላት መካከል የሚደረግ የአክስዮን ሽያጭ እና ግዢ እንደውህደት ይቆጠራል ወይስ አይቆጠርም የሚል ሲሆን የአዋጁ አንቀጽ 9/3/ለ ድንጋጌ በአንድ አክስዮን ማህበር አባላት መካከል የተደረገ የአክስዮን ሽያጭ እና ግዢ የውህደት ተግባር ተደርጎ እንደሚቆጠር በግልጽ የሚያመለክት ነው። በመሆኑም የአክስዮን ሽያጭ የተደረገው በማህበር አባለት መካከል ቢሆንም ህጉ ለአዋጅ አፈጻጸም ሲባል እንደውህደት እንዱቆጠር የፈለገ በመሆኑ ተጠሪ በአባላቱ መካከል የተደረገ የአክስዮን ሽያጭ እንደ ውህደት አይቆጠርም በሚል የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት የለውም።
በውህደት የተለያዩ የንግድ ማህበራት ወይም ግለሰቦች የንግድ ማከናወኛ ግብአቶች በአንድ ላይ አቀናጅተው የተሻለ አቅም በመፍጠር የተሻለ የንግድ ተወዲዲሪነት እና የንግድ አቅርቦት እንዱኖር በማድረግ እንዱሁም የሀገርን ኢኮኖሚ በማሳደግ ረገድ በተናጥል የንግድ ስራ ከመስራት የተሻለ ጥቅም እንዲለው የሚታወቅ ቢሆንም በተቃራኒው ውህደት በሀገር ኢኮኖሚ እና በተጠቃሚ ማህበረሰብ/ሸማቾች ብልም በላልች የንግድ አካላት ላይ ያልተገባ ውድድር(unfair competition) በመፍጠር አለታዊ ተጽኖ ሉያስከትል የሚችልበት ሁኔታ ስለሚኖር ውህደትን መቆጣጠር ያስፈልጋል። የውህደትን አለታዊ ተጽኖ መቆጣጠሪያ መንገድ ከሆኑት ውስጥ አንደ የውህደት ማስታወቂያ(merger notification) ለተቆጣጣሪ ባለስልጣን መስጠት ነው። ይህም እንደየ ሀገራቱ የህግ ማእቀፍ በግዳታ ወይም በፍቃደኝነት የሚፈጸም ሲሆን ለምሳላ በምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ሀገራት(COMESA) እና በአውሮፒ ዩኒየን(EU) አባል ሀገራት የውህደት ማስታወቂያ መስጠት ግዳታ ሲሆን በእንግሉዝ ግን የውህደት ማስታወቂያ መስጠት በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው። ኢትዮጵያም የምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና አባል ሀገራት መካከል አንዶ እንደመሆኗ እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 9/2 እና 10/1 መሰረት ለአመልካች የውህደት ማስታወቂያ ማቅረብ ግዳታ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
ከውህደት ማስታወቂያ ጋር ተያይዞ የውህደት ማስታወቂያ የማቅረብ ግዳታ የተጣለው ነጋዳ በሆነ ግለሰብ ላይ ብቻ ነው ወይስ ነጋዳ ያልሆነ ግለሰብም ማስታወቂያ የመስጠት ግዳታ አለበት የሚለው መታየት አለበት። የምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የንግድ ውድድር ደንብ አንቀጽ 24/1 ውህደት እስካለ ድረስ ለሚመለከተው ባለስልጣን ማሳወቅ ግዳታ መሆኑን ተመልክቷል። ይህም የውህደት ተግባር እስከተፈጸመ ድረስ የማስታወቅ ግዳታ በነጋዳ ማህበር ወይም በነጋዳ ግለሰብ ላይ ብቻ የተጣለ አለመሆኑን ይልቁንም በውህደት ድርጊቱ የተሳተፈው ነጋዳ ባይሆንም እንኳን የማስታወቅ ግዳታ እንዲለበት የሚያስገነዝብ ነው።
በአዋጅ ቁጥር 813/2013 አንቀጽ 10/1 የማስታወቅ ግዳታ የተጣለው ነጋዳ በሆነ ማህበር ወይም ግለሰብ ላይ ብቻ እንደሆነ በሚመስል መልኩ ተደንግጓል። ይህ ድንጋጌ ከአዋጁ አንቀጽ 9/3/ሀ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ በአንቀጽ 10/1 ማንኛውም ነጋዳ በሚል የተገለጸው በአንቀጽ 9/3/ሀ ላይ የተመለከቱትን የንግድ አካላትን ብቻ የሚመለከት ይመስላል። ነገር ግን በህግ አተረጓጎም ረገድ ጥቅም ላይ ከሚውለ የአተረጓጎም መርሆዎች ውስጥ አንደ ወርቃማ የአተረጓጎም ዘዳ (Golden rule of interpretation) ሲሆን የዚህ አይነት አተረጓጎም መሰረተ ሀሳብ ህጉ በአጠቃላይ ወይም በህጉ በተወሰኑ ድንጋጌዎች ለማሳካት የታሰበውን አላማ(purpose) ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ትርጉም መስጠት ነው። ይህን የአተረጓጎም መርህ ተግባራዊ ለማድረግ ህጉን ለማውጣት ያስፈለገበትን አጠቃላይ ምክንያት ከህጉ መግቢያ፣ ህግ አውጪው ህጉን ሲያወጣ የተወያየበትን ሰነድ (ሀተታ ዘምክንያት) እና መሰል ሰነድችን እንዱሁም በህጉ በተለያዩ ድንጋጌዎች ላይ የተመለከቱትን መሰረተ ሀሳቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት አንደን ከላላው ጋር በማዛመድ መመልከት ያስፈልጋል።
በዚህም መሰረት አጠቃላይ የአዋጅ ቁጥር 813/2006 አላማ ተገቢ ባልሆኑ የንግድ ውድድሮች ሸማቶች ወይም ተጠቃሚዎች እንዲይጎደ መከላከል ነው። በተጨማሪም የውህደት ስምምነት ወይም ቅንብር በአዋጁ አንቀጽ 11 መሰረት ከባለስልጣኑ(ከአመልካች) ፍቃድ ሳይገኝ ተፈጻሚ ላሆን እንደማይችል በአዋጁ አንቀጽ 9/2 ተመልክቷል። ባለስልጣኑ ፍቃድ የሚሰጠው ደግሞ ውህደቱ በንግድ ውድድር ላይ አለታዊ ተጽኖ የላለው መሆኑን ካጣራ በኋላ ስለሆነ አለታዊ ተጽኖ መኖር አለመኖሩን ለማጣራት ባለስልጣኑ ውህደት መደረጉን እንዱያውቀው ማድረግ የግድ ነው። ስለዚህ በአዋጁ አንቀጽ 9/3/ለ መሰረት በአንድ ሰው ወይም በብዙ ሰዎች በተዘዋዋሪ ወይም በቀጥታ የንግድ ማህበር አክስዮኖችን፤ ሴኩሪቲዎችን ወይም ንብረቶችን የራስ ማድረግ እንደውህደት ተግባር ይቆጠራል እስከተባለ ድረስ ይህ ውህደት ተፈጻሚነት እንዱኖረው በአዋጁ አንቀጽ 9/2 መሰረት የውህደቱ ፈጻሚ/አድራጊ ነጋዳ ቢሆንም ባይሆንም ውህደቱን ለአመልካች ማስታወቅ ግዳታ ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ነው። በመሆኑም ነጋዳ ባልሆኑ አክስዮን ማህበር አባላት መካከል የተደረገ የአክስዮን ሽያጭ እንደወህደት የሚቆጠር በመሆኑ ይህንን ውህደት በአዋጁ አንቀጽ 9/2 መሰረት ለአመልካች ማሳወቅ የአዋጁን አጠቃላይ አላማ የሚያሳካ ይሆናል።
ላላው መታየት የሚገባው በአንድ ነጋዳ ባልሆኑ የአክስዮን ማህበር አባላት መካከል በተደረገ የአክስዮን ሽያጭ ምክንያት የውህደት ድርጊት ሲፈጸም ለባለስልጣኑ ወይም ለአመልካች የማሳወቅ ግዳታ የማነው?
ወይም የአክስዮን ማህበሩ ውህደቱን የማስታወቅ ግዳታ አለበት ወይ? የሚለውን ስንመለከት የአክስዮን አባላት የሚያደርጉት የአክስዮን ሽያጭ የአክስዮን ማህበሩ በገዢው ስም እንደሚመዘገብ ግልጽ ነው። ይህም የአክስዮን ማህበሩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በውህደት ሂደቱ ላይ መሳተፈን የሚያሳይ ነው።
በተጨማሪም የአንድ የአክስዮን ማህበር አባል የአክስዮን ድርሻ መጠን እየጨመረ መሄደ የአክስዮን ገዢው በማህበሩ ውስጥ ያለው ድምጽ(vote) እንዱጨምር የሚያደርገው በመሆኑ በማህበሩ አባላት በድምጽ ብልጫ በሚወሰኑ ጉዲዮች ላይ በሚፈልገው መልኩ ወይም በንግድ ውድድር ላይ ተገቢ ያልሆነ ተጽኖ የሚፈጥር ውሳኔ ለመስጠት ያስችለዋል። ማስታወቂያ የመስጠት አላማ ደግሞ እንደዚህ አይነት ተጽኖዎች ሉፈጠሩ የሚችለ መሆን ያለመሆኑን ገምግሞ ውህደቱን መፍቀድ ወይም መከልከል በመሆኑ የአክስዮን ማህበር በአባላት መካከል በተደረገ የአክስዮን ሽያጭ ምክንያት የተፈጠረውን ውህደት የአክስዮን ማህበሩ የማሳወቅ ግዳታ ሉኖርበት ይገባል።
በተያዘው ጉዲይ ወ/ሮ ዲንሴ ጉርሙ ያደረጉት የአክስዮን ግዢ የተወሰነው የማህበሩ አባላት ተገኝተው ባደረጉት ስብሰባ መሆኑን በአመልካች የተገለጸ ሲሆን ተጠሪ ይህንን በግልጽ በመካድ ያቀረበው ክርክር የለም። የአክስዮን ግዢው በስብሰባ እንኳን አልተወሰነም ቢባል ግለሰቧ የአክስዮን ግዢውን ከፈጸሙ በኋላ በማህበር ውስጥ ያላቸው የአክስዮን መጠን በአመልካች እንደተገለጸው ወደ ብር 122,000,000 ማደጉን ተጠሪ በመካድ ያቀረበው ክርክር የለም። ግለሰቧ በተጠሪ ማህበር ውስጥ ያላቸው የድርሻ መጠን ከአጠቃላይ የማህበሩ ካቲታል አንጻር ሲታይ ከ92 በመቶ በላይ እንዱሆን ያደርገዋል። ይህም የግለሰቧን የድምጽ መጠን ከፍተኛ የሚያደርገው በመሆኑ ግለሰቧ የማኔጅመነት አባል ባይሆኑም እንኳን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በተጠሪ ማህበር ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ተጽኖ እንዱፈጥሩ ሉያደርጋቸው ይችላል። በመሆኑም አመልካች የውህደት ማስታወቂያ ደርሶት የአክስዮን ግዢው ምን ተጽኖ ሉኖረው እንደሚችል ባልመረመረበት ሁኔታ ተጠሪ የአክስዮን ሽያጩ በንግድ ውድድር ላይ የሚያስከትለው ተጽኖ የለም በሚል የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት የለውም።
ሲጠቃለል በተጠሪ ማህበር አባላት መካከል የአክስዮን ሽያጭ የተደረገ ቢሆንም ሽያጩ እንደ ውህደት ድርጊት እንደሚቆጠር በህግ በግልጽ የተመለከተ በመሆኑ፤ ማንኛውም የውህደት ድርጊት ሲፈጸም ለአመልካች የውህደት ማስታወቂያ ላሰጥ እንደሚገባ በአዋጁ አንቀጽ 9/2 ላይ ተመልክቶ እያለ ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የአዋጁን አንቀጽ 10/1 በመጥቀስ እንዱሁም ተጠሪ በውህደቱ ሂደት ያደረገው ተሳትፍ በማስረጃ ስላልተረጋገጠ ተጠሪ ማስታወቂያ የመስጠት ግዳታ የለበትም በሚል የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የስር ይግባኝ ሰሚ አስተዲደር ፍርድ ቤት ውሳኔን መሻሩ የአዋጅ ቁጥር 813/2006 ድንጋጌዎች ይዘት እና አላማ የሚቃረን መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ. የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽሯል።
2ኛ. የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ይግባኝ ሰሚ አስተዲደር ፍርድ ቤት በመዝገብ በጥቅምት 19 ቀን 2012 ዓ.ም ሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል።
3ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.