No summary available.
መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) በእውቀት በላይ ተሾመ ሽፈራው ዋዚሞ ዋሲራ ሰናይት አድነው አመልካች፡- የኢትዮጵያ መንገድች አስተዲደር ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የተያዘው ክርክር የካሳ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን የጀመረውም በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው። የአሁን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፤ አመልካች ተከሳሽ እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ በመሆኑ ተከራክረዋል።
1ኛ ተጠሪ በቀን 21/03/2011 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ አመልካች በደር ቤቴ ሻሁራ ያለውን የጠጠር መንገድ ሲያሰራ ይዞታነቱ የ1ኛ ተጠሪ የሆነውንና በይዞታ መለያ ቁጥር A/M/H/H/03/27/995 የተመዘገበውን 05 ገመድ መሬት ለጠጠር ማምረቻነት ከተጠቀመ በኋላ ወደ ነበረበት መመለስ ሲገባው ለሶስት ዓመት ካሳ ብር 40,181.40 (አርባ ሺ አንድ መቶ ሰማኒያ አንድ ብር ከ40/100) ቢከፍልም መሬቱን ወደ ነበረበት አልመለሰም። ከዚህም ባለፈ የ10 ዓመት ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ ያልከፈለን በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀጽ 8(1) መሰረት ከመሬቱ በቋሚነት እንድፈናቀል ሲደረግ በሚከፈለው ስላት መሰረት ተሰርቶ ብር 1,347,318.60 (አንድ ሚሉዮን ሶስት መቶ አርባ ሰባት ሺ ሶስት መቶ አስራ ስምንት ብር ከ60/100) ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍል ወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች በበኩለ ለክሱ መቃወሚዎችን ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ነገሩ ላይ በሰጠው መልስ መሬቱ ሙለ ለሙለ ለግብዓት ማምረቻ የዋለና ወደ ነበረበት ለመመለስ የማይቻል ስለመሆኑ ማስረጃ አልቀረበም፤ እንዱከፈል የተጠየቀው የካሳ ገንዘብ እጅግ የተጋነነ እና የካሳ አሰላል ስርዓቱን የተከተለ አይደለም፤ ካሳውን የመክፈል ኃላፉነት አለባቸው ብንባል እንኳን መሬቱ ወደ ነበረበት ሉመለስ ይችላል ወይስ አይችልም የሚለው በባለሞያ ሉጣራ ይገባል እንዱሁም በውላችን መሰረት ካሳውን የመክፈል ኃላፉነት ያለበት 2ኛ ተጠሪ በመሆኑ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ይግባልን በማለት ተከራክሯል።
2ኛ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብቶ ባቀረበው መልስ ለ1ኛ ተጠሪ በቅድሚያ ካሳ የተከፈለው በመሆኑ ልንከሰስ አይገባም የ1ኛ ተጠሪ ጥያቄ የካሳ ይከፈለኝ እንዱ መሬቱ ወደ ነበረበት ይመለስልኝ የሚል ባለመሆኑ ኃላፉነት የለብንም የመንገድ ስራውን በውል አስቀድሞ የያዘው ላላ ተቋራጭ በመሆኑ ካሳ የመክፈል የውል ግዳታ የለብንም፤ ለስራው ግብዓት የማቅረብ ኃላፉነትም የአመልካች በመሆኑ ልንጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ የቀረቡትን መቃወሚያዎች ውድቅ በማድረግ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ እንዱሁም የካሳው መጠን በባለሞያ ተሰልቶ እንዱቀርብለት ካደረገ በኃላ ውሳኔ ሰጥቷል። በሰጠው ውሳኔ አመልካች የ1ኛ ተጠሪን የእርሻ መሬት ለመንገድ ስራ አገልግልት የሚውል ጋራጋንቲ (ጠጠር) ለማውጣት ለመዋዋል ለ3(ሶስት) አመት ካሳ መክፈለ በማስረጃ ተረጋግጧል፤ የተከፈለው የካሳ ገንዘብም የሶስት አመት እንጂ ዘላቂ ከእርሻ ወይም ከመሬቱ ለሚፈናቀል ባለመሬት የሚከፈል የ10 ዓመት ካሳ አለመሆኑን ችልቱ አረጋግጧል።
መሬቱም ወደ ነበረበት ሉመለስ የማይችልና ለምንም ዓይነት ለሰብልም ሆነ ለላላ የግብርና ሰራ እንደማይውል በማስረጃ ተረጋግጧል። ኃላፉነቱን በተመለከተም 1ኛ ተጠሪ ከይዞታ ማፈናቀያ ካሳ እንዱከፈለው ላቀረበው ጥያቄ 2ኛ ተጠሪ ኃላፉነት እንዲለበት አመልካች ያላሰረዲ ሲሆን በቀረበው ማስረጃ የተረጋገጠው ኃላፉነት ያለበት አመልካች ሰስለመሆኑ ነው። የካሳ መጠኑን በተመለከተም በባለሞያ ተሰርቶ የቀረበው የ10(አስር) አመት የካሳ መጠን ብር 3,466,333.44 (ሶስት ሚሉዮን አራት መቶ ስላሳ ስድስት ሺ ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ከ44/100 ቢሆንም 1ኛ ተጠሪ እንዱከፈለው የጠየቀው ብር 1,347,318.60 (አንድ ሚሉዮን ሶስት መቶ አርባ ሰባት ሺ ሶሰስት መቶ አስራ ስምንት ብር ከ60/100 በመሆኑና ዲኛነት ከተጠየቀው በላይ ሉፈርድ ስለማይችል በጠየቀው ዲኝነት ልክ ይኸው ገንዘብ ይከፈለው በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም ውሳኔው ጉድለት የለበትም ተብል ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረታዊ ተሰርዟል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች ባቀረበው 5 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈጽመዋል ያላቸውን ስህተቶች በመዘርዘር ውሳኔው የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብል እንዱታረም ጠይቋል። ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ቀደም ሲል ለ1ኛ ተጠሪ የሶስት ዓመትካሳ ታስቦ የተከፈላቸው ስለመሆኑ ባልተካደበት የስር ፍርድ ቤት ይህንን ታሳቢ ሳያደርግ የ10 ዓመት ካሳ እንዱከፈላቸው የወሰነበትን አግባብ ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
በዚሁም መሰረት 1ኛ ተጠሪ በሰጡት መልስ አመልካች ለተጠሪ የሶስት ዓመት ጊዜያዊ ካሳ የከፈለ ቢሆንም የተጠሪ የይዞታ መሬት ሙለ በሙለ በማያገግም ሁኔታ ጉዲት የደረሰበት ጊዜያዊ ካሳ በተከፈለ ከዓመታት በኋላ በመሆኑ አመልካች ለደረሰው ዘላቂ ጉዲት ካሳ እንዱከፍል ሲወሰን ጊዜያዊ የሶስት ዓመት ካሳ ክፍያው ታሳቢ ተደርጎ ተቀናሽ አለመደረጉ ተገቢና ህጉን የተከተለ ነው ቋሚ የመፈናቀያ ካሳው የተጠየቀው ውልን መነሻ በማድረግ ሳይሆን በተጨባጭ ጉዲቱ ከደረሰ በኋላ የቀረበን ጥቅም መነሻ በማድረግ የቀረበ ከመሆኑም በላይ የጉዲቱ መጠን ምን ያህል ጥቅም እንዲስቀረብን በማስረጃ ተደግፍ በቀረበበት ሁኔታ በውል የካሳ አሰላለን እንደተስማማን አስመስል አቤቱታ ማቅረቡ ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
2ኛ ተጠሪን በሚመለከት መጥሪያ የደረሰውና ጠበቃው ቀርቦ መልስ በማቅረብ እንዱችል ተለዋጭ ቀጠሮ እንዱሰጠው ጠይቆ በቀጠሮው መልስ ያላቀረበ በመሆኑ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኙ ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ህጎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንደተመለከትነው የማስቀረቢያ ነጥቡ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ይዞታ አስመልክቶ ለአሁን 1ኛ ተጠሪ የሶስት ዓመት ካሳ ተከፍል እያለ ይህ ታሳቢ ሳይደረግ የ10 ዓመት ካሳ እንዱከፈላቸው የተወሰነበት አግባብ ሉመረመር ይገባል የሚል ነው።
እንደሚታወቀው የመሬት የይዞታ መብት በህግ መንግስት ጥበቃ ከተደረገላቸው መሰረታዊ መብቶች ውስጥ አንደ ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 ድንጋጌ መረዲት ይቻላል።
ይህ መብት ሉታጣ የሚችለው ይዞታው ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜም ቢሆን ይዞታው በዘፈቀደ የሚነጠቅ/የሚወሰድ/ እና ጥቅም ላይ እንዱውል የሚደረግ ሳይሆን ለህጋዊ ባለይዞታው በቅድሚያ ተመጣጣኝ ካሳ በመክፈል ስለመሆኑ ከዚሁ የህገ መንግስቱ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 8 ይዘት መገንዘብ ይቻላል። ይዞታው ወይም ንብረቱ ለሚወሰድበት ባለይዞታ/ባለመብት ቅድሚያ ካሳ የሚከፈልበት እንዱሁም ተጓዲኝ መብቶች የሚጠበቅበትን ስርዓት አስመልክቶ ክርክሩ በተነሳበት ጊዜ ስራ ላይ በነበሩት በአዋጅ ቁጥር 455/1997፣ ደንብ ቁጥር 135/1999፣ መመሪያ ቁጥር 19/2006 ላይ በዝርዝር ተመልክቷል። አንድን ባለይዞታ ወይም ባለንብረት ለህዝብ ጥቅም በሚል ምክንያት ከይዞታው ለማስለቀቅ እንዱሁም በጊዚያዊነትም ሆነ በቋሚነት በይዞታው የመጠቀም መብትን የሚያሳጣ ሁኔታ ሲከሰት ሉከፈል ስለሚገባው ካሳ በዝርዝር ተደንግጓል።
በአዋጅ ቁጥር 455/1997 አንቀጽ 8(1) ስር እንደተመለከተው የመሬት ይዞታውን በቋሚነት እንዱለቅ የሚደረግ የገጠር መሬት ባለይዞታ መሬቱን እንዱለቅ ከመደረጉ በፉት የነበረው አመታዊ ገቢ በ10 ተባዝቶ የመፈናቀያ ካሳ ይከፈለዋል። በአንቀጽ 8(2) ስር እንደተመለከተውም የመሬት ይዞታውን ለተወሰነ ጊዜ እንዱለቅ ለሚደረግ የገጠር መሬት ባለይዞታ አመታዊ ገቢው መሬቱ እስከሚመለስ ድረስ ባለው ጊዜ ታስቦ የማፈናቀያ ካሳ ይከፈለዋል።ሆኖም ይህ ክፍያ በአንቀጽ 8(1) መሰረት ከሚከፈለው ካሳ መብለጥ የለበትም።
ከፍ ሲል ከተመለከተው የህግ ማዔቀፍ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለው በይዞታ መሬቱ በቋሚነት ጥቅም እንዱያገኝ (እንዱለቅ) ለሚደረግ የገጠር መሬት ባለይዞታ አመታዊ ገቢው በ10 ተባዝቶ የሚከፈለው የማፈናቀያ ካሳ ላይ በተጨማሪ ይዞታውን ለተወሰነ ጊዜ እንዱለቅ በተደረገ ጊዜ መሬቱ እስከሚመለስ ድረስ ያለው ጊዜ ታስቦ ተደራቢ የማፈናቀያ ካሳ ሉከፍል እንደማይችል ነው።
በተያዘው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ ይዞታውን በጊዜያዊነት ሲለቅ ለሶስት ዓመት ካሳ ብር 40,181.40(አርባ ሺ አንድ መቶ ሰማኒያ አንድ ብር ከ40/100) የተከፈላቸው መሆኑ አላከራከረም።
ባቀረቡት ክስም ይኸው ተመልክቷል። ይሁንና መሬቱ ወደ ነበረበት አልተመለሰም ተብል የቋሚ ማፈናቀያ ካሳ ሲጠየቅ አስቀድሞ ተወሰደው ሳይታሰብ የ10 ዓመት ካሳ መጠየቁና የስር ፍርድ ቤቶችም ከሳሽ በጠየቁት መሰረት እንዱከፈላቸው የደረሱበት መደምደሚያና ያሳለፈት ውሳኔ ከፍ ሲል የተገለጹትን በህጉ ስለ ቋሚ እና ጊዜያዊ የማፈናቀያ ካሳ የተደነገገውን መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ውሳኔው ሉቃና ይገባል ብለናል። ተከታዩንም ወሰነናል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 01-02066 የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ሀምላ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ያሳለፈው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
1ኛ ተጠሪ ይዞታውን በጊዜያዊነት ሲለቁ ብር 40,181.40(አርባ ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ አንድ ብር ከ40/100) ካሳ የተከፈላቸው መሆኑ ያላከራከረ በመሆኑ የቋሚ ማፈናቀያ ካሳ ሲጠየቅ አስቀድሞ የተወሰደው ይኸው ገንዘብ ሳይታሰብ የ10 ዓመት ካሳ መጠየቁና የስር ፍርድ ቤቶችም 1ኛ ተጠሪ በጠየቁት መሰረት እንዱከፈላቸው ያሳለፈት የውሳኔ ክፍል የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። ስለሆነም ይኸው ይዞታው በጊዜያዊነት ሲለቀቅ የተከፈለው ገንዘብ ተቀናሽ እንዱሆን ወሰነናል።
ቀሪው የውሳኔ ክፍል አልተነካም።
ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.