No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ ቀነዓ ቂጣታ ብርሃኑ መንግሥቱ ማርታ ተካ አመልካች- አቶ ካህሱ ወ/ትንሳይ - ቀረቡ ተጠሪዎች-
ጉዲዩ አመልካች ክስ በተመሰረተበት የመሬት ይዞታ ላይ መብትና ጥቅም የላቸዉም ተብል ክሳቸዉ ዉድቅ በመደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል የቀረበ የሰበር አቤቱታ ተከትል የቀረበ ክርክር የሚመለከት ነዉ። አመልካች በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ የመሰረቱት ክስ ይዘት በአጭሩ - አመልካች በኮልፋ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዲ 07 የቤት ቁጥር አዱስ በሆነውና አዋሳኙ በክሱ በተጠቀሰዉ 500 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ይዞታዉ ገዝቼ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ በእጄ አድርጌ በእውነት እያዘዝኩበት ለመኖሪያነት ከዛም የንግድ ፍቃድ አውጥቼ በብልኬት ማምረቻነት ግብር እየገበርኩኝ ስገለገልበት የቆየሁት ይዞታ አለኝ።በ2ኛ ተጠሪ ስር የሚገኘው የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ይዞታዬን ሕገ-ወጥ ነው በማለት ለማፍረስ በመንቀሳቀሱ ሁከት እንዱወገድልኝ ክስ መስርቼ ዔግድ ተሰጥቶበት ሳለ የፍርድ ቤት ዔግድ ተላልፈው ቤቶቼን አፍርሰው ሕገ-ወጥ የሆነ ግንባታ እየሰሩ ይገኛለ። አስቀድሞ በልላ መዝገብ ላይ ሁከት እንዱወገድልኝ ክስ መስርቼ ፍርድ ቤቱም ይዞታው የአመልካች መሆኑን፣ በመመሪያ ቁጥር 18/2006 መስተናገድ እንደሚገባኝ እና የሁከት ተግባሩ ሉወገድ እንደሚገባ በመግለፅ ፍርድ ሰጥቶ ተጠሪም ይግባኝ ብል ውሳኔው ፀንቶበታል።ሆኖም የአመልካች ይዞታና ቤቶቹም በ1997 ዓ/ም የአየር ካር በኮኦርድኔት የሚታዩ፣ማናቸዉም ተግባራት እንዲይፈጸምበት በፍርድ ቤት የታገደ እና በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ያረፈበትን ይዞታ ሆኖ እያለ 2ኛ ተጠሪ ለ3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ማህደር አደራጅቶ በመላክ 1ኛ ተጠሪም ለ3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች በአመልካች ይዞታ ላይ ካርታ መስጠቱ ሕገ-ወጥ ተግባር ነዉ።
በመሆኑም ተጠሪዎች ክስ የቀረበበትን ይዞታ እንዱለቁ እና 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች አመልካች በይዞታው ላይ ለመገልገል አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን እና መስተንግድ በመስጠት እንዱፈፅሙ እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በሰጡት መልስ አመልካች በወረራ በያዙት መሬት ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት እና ጥቅም የላቸውም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም ስረ ነገሩን በተመለከተ በሰጡት መልስ - ለክርክሩ መነሻ የሆነው ይዞታ በ1997 እና በ2003 ዓ.ም በተነሳው የመስመር ካርታ ላይ የማይታይ በመሆኑ በመመሪያ ቁጥር 18/2006 አንቀጽ 5/1 መሰረት በሰነድ አልባ ይዞታነት የሚስተናገድ አይደለም።ይህንንም እስከመጨረሻ ክርክር ተደርጎበት ውሳኔ ሳይሰጥ እና ቤቱ የቴላ ማኅበር የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሆኖ ሳለ በ1997 የአየር ካርታ ላይ ይታያል ስለተባለ ብቻ የአመልካች ይዞታ ነው ለማለት አይቻልም። በተጨማሪም መሬቱ በአሁን ወቅት ምንም አይነት ግንባታ የላለው የመንግስት ባድ መሬት ነው።ይዞታው ግንባታ የላለዉ ባድ እና በአመልካች ያልተያዘ በመሆኑ አመልካች ግንባታ አለው የሚል ክርክር አላቀረቡም።በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ፍትሐ ብሄር ችልት የጠየቁት ዲኝነት ሁከት ይወገድልኝ ሆኖ ሳለ እንደባለይዞታነት ክርክር የአየር ካርታን መነሻ ተደርጎ የተሰጠው ውሳኔ በምንም መልኩ መብት የማይፈጥር መሆኑን ሰበር አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል። 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች አርሶ አደር መሆናቸው በኮልፋ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዲ 07 ተረጋግጦ ለ1ኛ ተጠሪ የተላከ በመሆኑ ከተላኩ ማስረጃዎች አንፃር ካርታ ተዘጋጅቶ እንዱሰጣቸው ተደርጓል። በመሆኑም ከመመሪያ ውጭ የሆነ ነገር ያልሰራን ስለሆነ እና የተላለፍነውም ምንም አይነት ዔግድ ባለመኖሩ ልንጠየቅ አይገባም።ይዞታው በአዋጅ ቁጥር 64/2011 መሰረት በኮድ 411 መሬት ባንክ ገብቶ የሚጠበቅ ይዞታ መሆኑ ተረጋግጦ ለባለመብቶቹ ካርታ ወጥቶበታል።በመሆኑም አመልካች በይዞታው ላይ ያላቸው መብት ከምን የመነጨ እንደሆነ ያላስረደ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ይደረግልን ሲለ ተከራክረዋል።
3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎችም አመልካች በክሱ በተጠቀሰዉ ይዞታ ላይ የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ ያላቀረቡ በመሆኑ ምንም አይነት መብትም ሆነ ጥቅም የላቸውም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም ባቀረቡት መልስ - አርሶ አደር እና የአርሶ አደር ልጅ በመሆናችን በኮልፋ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዲ 07 አርሶ አደር ኮሚቴ ተረጋግጦ ከመሬት ባንክ ወጥቶ በሕጋዊ ካርታ ተመዝግቦ ይዞታው ተሰጥቶናል።ይዞታውን በእጃችን በማድረግ የመንግስት ግብር ስንከፍልበት ቆይተናል። ከዚህም በተጨማሪ በይዞታው ላይ ግንባታ ለመፈፀም የግንባታ ፍቃድ አግኝተን ተገቢውን ሕጋዊ አካሄድ በመከተል ይዞታውን ስንገለገልበት ቆይተናል።ይህ ይዞታ ከጥንት ጀምሮ በቤተሰብ ጭምር ስንጠቀምበት የነበረ ይዞታ እንጂ አመልካች እንደሚለት በአመልካች ቁጥጥር ስር የነበረ ይዞታ አልነበረም።አመልካች ከዚህ ቀደም በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ችልት በ2ኛ ተጠሪ ላይ የሁከት ይወገድ ክስ ያቀረቡ ሲሆን ጉዲዩ አሁን በፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት የሚገኝ ነው።እኛ የክስ ሂደቱ አካል ካለመሆናችንም በላይ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሁከት ይወገድልኝ ክስ የሚያዘው ጭብጥ ሁከት ተፈጥሯል አልተፈጠረም እንጂ ባለቤትነትን የማያጎናጽፍ እንደሆነ በግልፅ ተቀምጧል።ስለሆነም በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል እየተካሄደ ያለው የሁከት ክስ ላይ የሚሰጠው ማንኛውም አይነት ውሳኔ ከዚህ ክስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ተብል ክሱ ዉድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም አስቀድሞ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን በብይን ውድቅ ካደረገ በኋላ ዋናዉን ጉዲይ በተመለከተ በሰጠዉ ዉሳኔ - አመልካች ይዞታውን ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ የያዙት መሆኑን እና ክስ በሚሰማበት ጊዜ ይዞታውን በአካባቢው ከሚገኙ አርሶ አደሮች መግዛታቸውን ከመግለፅ ውጪ ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ የለም።ያቀረቧቸውም ማስረጃዎች አመልካች የቦታው ባለቤት መሆናቸውን የሚያረጋግጡ አይደለም።የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት የሰነድ ማስረጃ ከላለ እንደ አግባብነቱ በሰው ማስረጃ ሉጣራ ይችላል።ይህ የሚሆነው የንብረቱ ባለቤት ነኝ የሚለው አካል ንብረቱን ሕጉ እውቅና በሰጣቸው መንገድ ያገኘ መሆኑን ሲያረጋግጥ ነው።አመልካች ይዞታውን ከአርሶ አደሮች የገዙ መሆኑን በቃል ክርክር ጊዜ ከመግለፅ ውጪ በክሳቸው የገለፁት ነገር የለም።አመልካች ከክሳቸዉ ጋር አያይዘዉ ያቀረቧቸዉ ማስረጃዎች የአከራካሪዉ ይዞታ ባለቤት ለመሆናቸዉ የሚያስረደ ማስረጃዎች አይደለም።
ይዞታዉ በ1997 ዓ/ም አየር ካርታ ላይ በማለት የቀረበዉ ማስረጃ በተመለከተ በ1997 ዓ/ም ኤር ካርታ በሚነሳበት ወቅት ይዞታዉ ያለ መሆኑን ከመግለጽ ዉጭ ይዞታዉ የአመልካች መሆኑን የሚያረጋግጥ አይደለም። እንዱሁም የወረዲ 7 አስተዲደር ጽ/ቤት የተጻፈ በማለት አመልካች ያቀረቡት ማስረጃ በይዞታዉ ላይ አመልካች ብልኬት ማምረቻዉ እንዲላቸዉ መግለጽ ይዞታዉ ለአመልካች የግል ሀብታቸዉ ስለመሆኑ የሚያስረዲ ማስረጃ አይደለም። በተጨማሪም አመልካች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ሁከት ይወገድልኝ የሚል ክስ መስርተዉ የተሰጠዉ ዉሳኔ በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ የሕግ ትርጉም መሰረት ባለቤትነትን በተመለከተ የተሰጠ ዉሳኔ እንኳን ቢሆን ተቀባይነት ስለማይኖረዉ ይህ ዉሳኔ በይዞታዉ ላይ የባለቤትነት መብት እንደሚሰጣቸዉ በመግለጽ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለዉም። አመልካች ይዞታዉን ከአርሶ አደሮች በግዥ መግዛታቸዉን ከመግለጽ ዉጪ በውርስ፣ በስጦታ፣በምሪት እና በመሳሰለት ሕጋዊ ኩነቶች ማግኘታቸውን በክሳቸው ያልገለፁ በመሆኑ ምስክር መስማት አስፈላጊ አይደለም።ስለሆነም አመልካች ለክርክር መነሻ በሆነው ይዞታ ላይ መብት እና ጥቅም ያላቸው መሆኑን የማስረዲት ሸክም ስላልተወጡ ተጠሪዎች የመከላከያ ግዳታ ዉስጥ የሚገቡ ባለመሆኑ ስለተጠሪዎች መተንተን ተገቢ አይደለም በማለት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33/2ን በመጥቀስ ክሱን ውድቅ በማድረግ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ በሰጠዉ ዉሳኔ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የመሬት ይዞታ አመልካች ሕጉ እዉቅና በሰጠዉ መንገድ ይዞታዉን ማግኘታቸዉን ያላስረደ ሲሆን በአንጻሩ ለ3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች አርሶ አደርና የአርሶ አደር ልጅ መሆናቸዉ ተረጋግጦ ከመሬት ባንክ ወጥቶ አከራካሪዉ መሬት እንደተሰጣቸዉ ከቀረበዉ ማስረጃ ተረጋግጧል በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ አፅንቷል።
አመልካች በቀን 28/03/2015 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም ከላይ በተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ፡- የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ክሱን የማቅረበ መብት እና ጥቅም እንዲላቸው ድምዲሜ ላይ በመድረስ መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ ብይን የሰጠ ቢሆንም ለጉዲዩ አወሳሰን አግባብነት ያለው ጭብጥ ሳይመሰረት፣ ክርክሩን በአግባቡ ሳይመራ፣ አስቀድሞ ብይን ዉድቅ ያደረገዉን የክርክር ነጥብ መሰረት በማድረግ አመልካች መብት የላቸዉም በማለት ዉሳኔ ሰጥቷል። ጉዲዩን አልመረመረም። ይህ ደግሞ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 241፣247 እና 248 የተደነገገዉን እና በዚህም ረገድ በሰ/መ/ የሰጠዉን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነዉ።እንዱሁም በተከራካሪ ወገኖች የተቆጠሩ አግባብነት እና ተቀባይነት ያላቸው ማስረጃዎች በአግባቡ በመስማት እና ከነሙለ ይዘታቸው በመመዘን የክርክሩን ውጤት መወሰን ሲገባዉ የአመልካችን ምስክሮች በመስማት የማስረዲት ግዳታዬን በአግባቡ እንዱወጣ ሳያደርጉና ፍሬ ጉዲይ ሳያጣሩ የሰጡት ውሣኔ የአመልካች የመሰማት መብትን የነፈገ በመሆኑ በሰመ/፣63014፣95026 እና በላልች መዛግብት ላይ የተሰጠዉን የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነዉ።በተጨማሪም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1195 እና 1196 እንደተደነገገው የይዞታ ማረጋገጫ ወረቀት የባለይዞታነት ግምት መስጫ ቢሆንም ይህ ግምት ግን ሉስተባበል የሚችል ከመሆኑም በተጨማሪ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ካርታ በማቅረብ ብቻ የሚረጋገጥ ስላለመሆኑ በሰ/መ/ ላይ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ካርታ እንደተሰራላቸው የተከራከሩ ቢሆንም ካርታዎቹ መምከናቸው አለመካዲቸውን እና በመጀመሪያ ደረጃ እና በከፍተኛ ፍርድ ቤቶች መረጋገጡን በተመለከተ በዝምታ መታለፈ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በተሰረዘ የባለሀብትነት ምስክር ወረቀት የሚገኝ የባለሀብትነት መብት ስላለመኖሩ በሰ/መ/ እንዱሁም የማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተያያዘ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ስመ ሃብት ይዞ መገኘት የንብረቱ ባለቤት አድርጎ የማያስቆጥር ስለመሆኑ በሰ/መ/ የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የጣሰ በመሆኑ የሕግ መሰረት የለውም::አመልካች ከዚህ አንጻር ያቀረብኩትን ክርክር የሥር ፍርድ ቤት ከሚመለከተው አካል ሳያጣራ መወሰኑም ፍትህን ያጓደለ ነዉ።
አመልካች በወቅቱ በነበረው አሰራር ከአርሶደሮች የግጦሽ መሬት በግዥ አግኝቼ ለረጅም ጊዜ በይዞታዬ ስር እንደሚገኝ እና አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ የተያዙ ቦታዎችን ለማስተካከልና ለመከላከል በወጣ የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 18/2006 መሰረት መስተንግድ ማግኘት የሚገባኝ ሕጋዊ ይዞታ መሆኑ የሚያስረደ ማስረጃዎችን አቅርቤያለሁ። ያቀረብኳቸዉ ማስረጃዎች ተጠሪዎች በማስረጃነት ካቀረቧቸው በ2013 እና ከዛ በኋላ ከተሰጡ ማስረጃዎች በተሻለ ይዞታው የአመልካች መሆናቸውን የሚያስረደ ናቸው።ይህ ሆኖ ሳለ ግን ከሚመለከታቸው አካላት መቅረብ የነበረባቸው እና አመልካች በራሳቸው ያቀረቧቸው ማስረጃዎች ተጠቃለው ሳይሰሙ እና ከተጠሪዎች ጋር ተነጻጽረው ሳይመዘኑ በንግድ ፈቃደ እና የአየር ካርታው ላይ ብቻ በመመስረት የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ነው።እንደዚሁም በሁከት ይወገድልኝ ክርክሩ እና በተሰጠዉ ዉሳኔ ክርክር ያስነሳው ይዞታ የአመልካች እንደሆነ ፣ አመልካች ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ከ25 ዓመት በላይ ይዞታው ላይ ቤት ሰርቼ ስለመያዘ፣ በመመሪያ ቁጥር 18/2006 መሰረት መስተንግድን ለማግኘት የሚያስችላቸው መሆኑ፤ ይዞታው በ1997 ዓ.ም የአየር ካርታ ላይ የሚታይ እና አመልካች ለረጅም ጊዜ ይዘውት ንግድ ፈቃድ አውጥተው የሚገለገለበት ሕጋዊ ይዞታ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኖ ሳለ ግን የሥር ፍርድ ቤቶች በሁከት ክርክሩ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ለመጠቀም የሚከለክል ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖር ውሳኔዉን የመሻር ውጤት ያለው የሚመስል ውሳኔ መሰጠቱ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 37 እና 40 የተደነገገዉን ፍትህ የማግኘትና የንብረት መብቶች የጣሰ ዉሳኔ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ነዉ ተብል ተሽሮ በአመልካች ክስ መሰረት እንዱወሰንልኝ አሉያም የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃዎች ሰምቶና መዝኖ እንዱወስን ለስር ፍርድ ቤት እንዱመለስ በማለት አመልክተዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ ለክርክር ምክንያት የሆነው ይዞታ በ1997 ዓ/ም አየር ካርታ ላይ የሚታይ ስለመሆኑ ከሚመለከተው አካል ተረጋግጦ ሪፕርት ቀርቦ ባለበት ሁኔታ ተጨማሪ ማጣራት ቢያስፈልግ እንኳን ማስረጃ ተሰምቶ ማጣራት ሲገባ ከሳሽ መብት እና ጥቅም መኖሩን ስላላስረዲ ክሱ ውድቅ ነው ተብል የተወሰነበትን አግባብ ከመመሪያ ቁጥር 18/2006፣ በሰ/መ/፣37105 እና ተያያዥ የሕግ ትርጉሞች አንጻር ተጠሪዎች ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ ተሰጥቶ ተጠሪዎች በሚከተለዉ መሰረት መልሳቸዉን ሰጥተዋል።
1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በጋራ በቀን 25/05/2015 ዓ.ም ጽፈዉ ባቀረቡት መልስ - አመልካች ባቀረቡት ክስ ላይ የጠየቁት ዲኝነት 1ኛ እና 2ኛ ተጠዎች አመልካች በይዞታው ላይ ለመገልገል አስፈላጊውን ተግባርና መስተንግድ እንዱሰጡኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው። ከዚህ አንጻር የስር ፍርድ ቤት መዝገቡን የመረመረው አመልካች ይህን መብት ለመጠየቅ የሚያስችል መብት አላቸው ወይስ የላቸውም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ በፍሬ ጉዲይ ላይ ይህንን በማጣራት ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበው አቤቱታ አግባብነት የላለው ነው።በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ውሳኔ ይዞታው በ1997ዓ/ም ይታያል በሚል የተሰጠው ማስረጃ ሳይመዝንልኝ የሰጠው ውሳኔ ነው ያለትን በተመለከተ በሰ/መ/ በሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሁከት ይወገድ በሚል የቀረበ ክስ ላይ ፍርድ ቤቱ ሉይዘው የሚገባው ጭብጥ ሁከት ተፈጥሯል አልተፈጠረም የሚል መሆን እንዲለበት አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። ከዚህ ውጭ የሁከት ይወገድልኝ ክስ በምን አግባብ መብትን የሚፈጥር አይደለም።ከዚህ አንጻር የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የሚነቀፍበት የሕግ አግባብ የለም።አመልካች ይዞታውን ያገኙት ከአርሶ አደሮች ገዝተው መሆኑን በቃል ክርክር ጊዜ ከመግለጽ ውጭ በክሳቸው በምን መንገድ እንዲገኙት የገለጹት ነገር የለም። በሁከት ይወገድልኝ ክስ ጊዜ የሚቀርቡ ማስረጃዎች እና በመፊለም ጊዜ የሚቀርቡ ማስረጃዎች እና የሚያዙም ጭብጦች የተለያዩ ናችው።ይህ በእንዱህ እንዲለ በሁከት ይወገድልኝ ወቅት የተሰጡ ማስረጃዎች ስህተት በመሆናቸው ለዚህ ለሰበር አቤቱታ ምክንያት በሆነው መዝገብ ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ታርመው የቀረቡ ናቸው።የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ በሚሰጥበት ሰዓት ተጠሪዎች ያቀረቡትን ማስረጃ በተገቢው መንገድ መርምሯል።መብት እና ጥቅም በፍሬ ጉዲይ ላይ የሚጣራ እንጂ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ የሚጣራ ጉዲይ አይደለም። በዚህም ጉዲይ ላይ ሰበር አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። የሁከት ይወገድልኝ ክስ ላይ በወቅቱ ቀርበው የነበሩ ማስረጃዎች ሀሰተኛ ስለነበሩ በወቅቱ ፍርድ ቤቱ እነዚህን ማስረጃዎች ምክንያት በማድረግ የወሰነው ውሳኔ ነው። ነገር ግን እነዚህ ማስረጃዎች በአሁን ሰዓት ጠርተው ወደ ፍርድ ቤቱ የቀረቡ በመሆኑ ነው ለክርክር ምክንያት በሆነው ይዞታ ላይ አመልካች መብት እና ጥቅም የላቸውም በማለት የወሰነው።
ከዚህ በተጨማሪ የሰበር አመልካች ከነዚህ ማስረጃዎች ውጭ ለመፊለም ክስ የሚሆን ያቀረቡት ማስረጃ የለም። በተጨማሪ አመልካች ይዞታውን ለ28 ዓመት ይዤው ነበር ቢለም ይዞታው በ1988 እና በ1997 የአየር ካርታ ላይ አይታይም እንዱሁም በወቅቱ ለገነባሁት ይዞታ ከአስተዲደሩ እውቅና ተሰጥቶኛል ያለትን በተመለከተ በወቅቱ የተሰጡ ማስረጃዎች ከሕግ አግባብ ውጭ በመሆናቸው እንዱታረሙ መደረጉ ተረጋግጦ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ከሕግ አግባብ ውጭ ነው ማለት አይቻለም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት የፍሬ ነገርም ሆነ የሕግ መሰረት የላለ በመሆኑ አቤቱታ ውድቅ እንዱያደርግልን ሲለ ተከራክረዋል።
3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎችም በጋራ በቀን 20/06/2015ዓ.ም ጽፈዉ ባቀረቡት መልስ - በአመልካች ለቀረበው የሰበር አቤቱታ ማስቀረቢያ ምክንያት የተደረገዉ የሰ/መ/ የተሰጠ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በአሰሪና ሰራተኛ ክርክር የተሰጠ የሕግ ትርጉም ሲሆን በተያዘው ጉዲይ ግን የይዞታ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ አስፈላጊ አይደለም በሚል ብቻ ሳይቀርብ እና ሳይመዘን የታለፈ የሰነድ ማሥረጃ ባለመኖሩ ተፈጻሚነት የለዉም። የ1997 ዓ.ም የአየር ካርታም ቢሆን በማሥረጃነት ቀርቦና ተመርምሮ እንዱሁም በ2ኛ ተጠሪ ጭምር ይዞታው የማን እንደሆነ እና ባለቤትነትን እንደማያረጋግጥ ማብራሪያ ቀርቦበት ውድቅ የተደረገ እንጂ ሳይቀርብና ሳይመዘን የታለፈ ባለመሆኑ ከተጠቀሰው የሰበር ትርጉም ጋር የሚገናኝ አይደለም።በተጨማሪም የይዞታ ባለቤትነት ከፍ/ሕ/ቁ.1195 እንዱሁም ላልች አግባብነት ያላቸው ደንቦች እና መመሪያዎች አንፃር በምስክር ብቻ የሚረጋገጥ ፍሬ ነገር ባለመሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ምስክር ተቀባይነት የሚሰጠው ማሥረጃ አይደለም በሚል ሳይሰማ መታለፈ ከተጠቀሰው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ጋር የሚጋጭ አይደለም።በተመሣሣይም ለሰበር አቤቱታው ማስቀረብ ምክንያት በሆነዉ በሰ/መ/ የተስጠ አስገዲጅ ውሣኔ በሥራ ክርክር ከጭብጥ አመሰራረት ጋር ተያይዞ የተሰጠ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሲሆን በተያዘው ጉዲይ ከይዞታው ባለቤትነት ማንነት ማረጋገጥ ጋር በተገናኘ በሥር ፍርድ ቤት ሳይያዝ የታለፈ ጭብጥ ባለመኖሩ፣በፍሬ ነገር ማስረጃ ምዘና ነጥሮ እና ተመዝኖ የተወሰነ በመሆኑ የሰበር አቤቱታዉ ዉድቅ እንዱደረግልን ሲለ ተከራክረዋል።አመልካችም የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከላይ አጠር ባለ መልኩ የተገለጸዉ የግራ ቀኙን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት የሚመለከት ሲሆን ሰበር አጣሪ ችልት የያዘዉን ጭብጥ ከግምት በማስገባት በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠው ውሳኔ በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈጸም አለመፈጸሙን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም በኢፋዱሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40(1-3 እና 6) ስር የግል ንብረት ባለቤትነት መብት እንደሚከበር፤ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት ባለቤትነት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ እንደሆነና መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ንብረት እንደሆነ፤ለግል ባለሀብቶች በሕግ በዝርዝር በሚደነገገዉ አግባብ በሚወሰን ክፍያ በመሬት የመጠቀም መብታቸዉ እንደሚከበርላቸዉ ተደንግጓል። ከዚህ ሕገ መንግሥት በፉት ወጥቶ በሥራ ላይ በሚገኘዉ አዋጅ ቁጥር 47/1967 አንቀጽ 3 እና 4 ስር ይህ አዋጅ ከጸናበት ከቀን 01/12/1967 ዓ.ም ጀምሮ የከተማ ቦታ የመንግሥት ንብረት መሆኑ፤ ማንኛዉም ሰዉ የከተማ ቦታ በግል ባለሀብትነት ለመያዝ እንደማይችል፤የከተማ ቦታ ሉሸጥ፣ ሉለወጥ… እንደማይችል እንዱሁም ከቀን 11/04/1967 ዓ/ም ጀምሮ …በሽያጭ ወይም በልላ መንገድ የከተማን መሬት ለማስተላለፍ የተደረገ ተግባር ወይም ዉል እንደተሻረ ተደንግጓል።ከዚህ በኋላ የከተማ ቦታ በኪራይ ስለመያዝ ለመደንገግ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 80/1986፣አዋጅ ቁጥር 272/1994 እና የከተማ ቦታን በሉዝ ስለመያዝ ለመደንገግ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ላይ የከተማ መሬት አግባብ ባለዉ አካል በሚሰጥ ዉሳኔ በኪራይ ወይም በሉዝ እንደሚያዝ ተመልክቷል።
የከተማ ቦታ በሉዝ ስለመያዝ ለመደንገግ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 6(4 እና 5) ስር በተደነገገዉ መሰረት አዋጁ ከጸናበት ቀን ጀምሮ ባለዉ የአራት ዓመት ጊዜ ዉስጥ አግባብ ያለዉ አካል ሳይፈቅድ የተያዙ ይዞታዎችን ሥርዓት ለማስያዝ ክልልችና የከተማ አስተዲደሮች የሚያወጧቸዉን ደንቦች ተከትል ከከተሞች ፔላንና ከሽንሻኖ ስታንዲርድ አንጻር ተቀባይነት የሚያገኙ ይዞታዎች በሉዝ ሥሪት እንዱተዲደሩ እንደሚደረግ ተደንግጓል። ይህንን ተከትል በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ደረጃ የሉዝ አዋጁን ማስፈጸሚያ ደንብ እና ልዩ ልዩ መመሪያዎች ወጥተዉ እየተተገበሩ ይገኛለ። ከተያዘዉ ጉዲይ ጋር ተያይዞ ሉጠቀስ የሚችለዉ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የወጣዉ መመሪያ “ አግባብ ባለዉ አካል ሳይፈቀድ የተያዙ ቦታዎችን ለማስተካከልና ለመከላከል የወጣዉ የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 18/2006 ነዉ።በዚህ መመሪያ አንቀጽ 2/6 በተመለከተዉ ትርጓሜ እና በአንቀጽ 3 ስር በተደነገገዉ መሰረት አግባብ ያለዉ አካል ሳይፈቅድ የተያዘ ቦታ ነዉ የሚባለዉ በከተማ አስተዲደር መሬትን በይዞታነት እንዱፈቅድ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ሳይፈቀድ እስከ ሚያዝያ 1997 ዓ/ም በግለሰብ የተያዘ የከተማ ቦታ ነዉ። በዚሁ መመሪያ አንቀጽ 2/21 ከተመለከተዉ ትርጓሜ እና በተለይም በአንቀጽ 5.1.1.
ላይ እንደተደነገገዉ አግባብ ያለዉ አካል ሳይፈቅድ የተያዘ ይዞታ ወደ ሕጋዊ ስርዓት ገብቶ በሉዝ እንዱተዲደር ይዞታዉን ለያዘዉ ሰዉ ሉፈቀድ የሚችለዉ በቦታዉ ላይ ለመኖሪያ፣ለንግድ፣ለማህበራዊ ወይም ለማንኛዉም ለላላ አገልግልት የተሰራ ሆኖ በ1997 ዓ.ም በተነሳዉ የመስመር ካርታ ላይ የሚታይ እና አሁንም አገለግልት እየሰጠ የሚገኝ ቤት ሲኖር፣በመመሪያዉ አንቀጽ 5.1.2. መሰረት ቤቱ ከከተማዉ ፔላን ጋር የማይቃረን ሲሆን፣ በመመሪያዉ አንቀጽ 5.1.3. እንደተደነገገዉ በአንቀጽ 5.1.1. ስር የተደነገገዉ ቢኖርም ቤቱ በተለያዩ ምክንያቶች በ1997 የመስመር ካርታ ላይ የማይታይ ሆኖ ስለቤቱ መንግሥታዊ በሆነ ተቋም ከሚያዝያ 1997 ዓ/ም በፉት የተሰጠ የሰነድ ማቅረብ እና ቤቱ በወቅቱ ተገንብቶ በእጃቸዉ የሚገኝ እንደነበር በወረዲዉ አስተዲደር ተረጋግጦ ከቀረበ እና ከሽንሻኖ ማስተካከል ጋር የሚጣጣም መሆኑ ሲረጋገጥ ነዉ።
ከላይ ከተጠቀሱት ሕግጋት መሰረት አግባብ ያለዉ አካል ሳይፈቅድ የተያዘ ይዞታ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት እንዱገባና በሉዝ ሥርዓት እንዱተዲደር ካልተደረገ በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 26/4 በተደነገገዉ መሰረት አግባብ ያለዉ አካል የማስለቀቂያ ትእዛዝ መስጠትና ካሣ መክፈል ሳያስፈልግ የ7 የሥራ ቀናት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ብቻ ይዞታዉን ለያዘዉ ሰዉ በአካል በመስጠት ወይም በቦታዉ በሰፈረዉ ንብረት ላይ በመለጠፍ የማስለቀቅ ሥልጣን አለዉ። በዚህ መልኩ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥበትም ምክንያት ይዞታዉን የያዘዉ ሰዉ ከዝርዝር ምክንያትና ማስረጃ ጋር አግባብ ላለዉ አካል አቤቱታ ማቅረብ እንዱችል፣ አግባብ ያለዉ አካል ጉዲዩን ከሚቀርበዉ አቤቱታና ማስረጃ አንጻር መርምሮ አስተዲደራዊ ዉሳኔ እንዱሰጥበት እንዱሁም የይዞታዉን የያዘዉ ሰዉ አቤቱታ የማያቀርብ ከሆነም በይዞታዉ ላይ ያሰፈረዉን ንብረት በራሱ ወጪ ማንሳት እንዱችል ጊዜና እድል ለመስጠት እንደሆነ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 28(2 እና 3) ስር ከተደነገገዉ መረዲት ይቻላል። አግባብ ያለዉ አካል በአዋጁ አንቀጽ 26/4 መሰረት ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ከሆነ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 31/5 ስር በተደነገገዉ መሰረት በሕገ-ወጥ መንገድ የተያዘ የከተማ ቦታ እንዱለቀቅ በማድረጉ በቦታዉ ላይ ላለ ንብረት ካሳ ለመክፍል ኃላፉነት አይኖርበት። በአንጻሩ አግባብ ያለዉ አካል በሕግ የተጣለበትን ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዳታ ሳይወጣ መሬቱ በሕገ-ወጥ መንገድ ተይዟል በሚል ብቻ በመሬቱ ላይ የሰፈረ ንብረት የሚያወድም ወይም በንብረቱ ላይ ጉዲት እንዱደርስበት የሚያደርግ ከሆነ በደረሰዉ ጉዲት ልክ ካሣ የመክፈል ኃላፉነት እንደሚኖርበት በሰ/መ/ (ያልታተሙ) ላይ የተሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ያሳያል።
ከተያዘዉ ጉዲይ ጋር በተያያዘ የሥረ ነገር ሕጉ አቋም ከሞላ ጎደል ከላይ የተመለከተዉ ሆኖ በልላ በኩል በልዩ ሕግ በተለየ አኳኋን ካልተደነገገ በስተቀር የፍትሐ ብሓር ክርክር መመራት ያለበት በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ በተዘረጋዉ ሥርዓት መስረት መሆኑ ይታወቃል። በዚህ መሰረት የፍትሐ ብሓር ክርክር የቀረበለት ፍርድ ቤት የክስ ማመልከቻዉን፣ የመከላከያ መልስ፣ በግራ ቀኙ የቀረቡትን ማስረጃዎች እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 241 መሰረት ግራ ቀኙን በመመርመር ያጣራዉን መሰረት በማድረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 246 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በተጠየቀዉ ዲኝነት ላይ ተገድቦ ተገቢዉን የሕግና የፍሬ ነገር ጭብጦችን መመስረት ይገባል። ተገቢዉን ጭብጥ ለመመስረት ምስክሮች አስቀርቦ መስማት ወይም የሰነድ ማስረጃ አስቀርቦ መመርመር ካስፈለገም ጭብጥ ከመመስረቱ በፉት ይህንኑ ተግባር መፈጸም እንደሚቻል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 249 እና 250 ላይ ሥርዓት ተዘርግቷል። በዚህ አግባብ ተገቢዉ ጭብጥ ከተመሰረተ በኋላ በተለይም በማስረጃ ሉረጋገጥ የሚገባዉን የፍሬ ነገር ጭብጭ በግራ ቀኙ በቀረቡ ማስረጃዎች እና እንደ ነገሩ ሁኔታ ራሱ ፍርድ ቤቱ ባስቀረባቸዉ ማስረጃዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 258 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የተከራካሪ ወገኖችን ክርክር የመክፈት ቅደምተከተል ጠብቆ የግራ ቀኙን ሙግት በመስማት እና በማስረጃ በማጣራትና በማረጋገጥ እልባት መስጠት ይገባል። ከከሳሽ እና ከተከሳሽ የጽሁፍ ክርክር (pleadings) ጋር ተያይዞ በቀረበዉ እና በመጀመሪያ ክሱ እስከተሰማበት የክርክር ሂደት ደረጃ (First Hearing Stage) በቀረበዉ ማስረጃ ብቻ በመመርመር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 255 መሰረት አከራካሪዉን ጉዲይ በፍርድ መወሰን ፍትህን የሚያጓድል ከሆነ በአከራካሪዉ ጉዲይ ላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 257 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የግራ ቀኙ ተጨማሪ ሙግት እና ምስክሮች ሳይሰማ ዉሳኔ መስጠት የዲኝነት ሥራ አመራር ኃላፉነት በአግባቡ ተግባራዊ አለማድረግ እንደሆነ፤ክርክሩ ከጊዜ፣ከገንዘብና ከሰዉ ሀብት (judicial economy) አጠቃቀም አኳያ ዉጤታማ እንዲይሆን ከማድረግ አልፍ የተከራካሪ ወገኖችን ሥነ ሥርዓታዊ ፍትሕ (procedural justice) እንደሚያጓድል የተከራካሪ ወገኖችን የሥረ ነገር መብት(substantive right) እስከማሳጣት የሚያደርስ ጉዲት የሚያስከትል መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንደሆነ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/(ቅጽ 8)፣189065፣234426፣241461 እና በላልች መዛግብት ላይ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
በተጨማሪም አሟጋች ፍርድ ቤት ተከራካሪ ወገኖች ከጽሁፍ ክርክራቸዉ ጋር እና የመጀመሪያዉ የክስ አሰማም ሥነ ሥርዓት እስከተፈጸመበት የክርክር ሂደት ደረጃ ድረስ ካቀረቧቸዉ ማስረጃዎች ዉጭ ላልች ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት የሚያስችለ ምስክሮችን ወይም የሰነድ ማስረጃዎችን አስቀርቦ በመስማትና በመመርመር አንጻራዊ እዉነታን በማጣራት መወሰን እንዱችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 264 ስር ሥርዓት ተዘርግቷል።ከዚህም ጋር በተያያዘም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ (ቅጽ 6)፣105956(ቅጽ 20) ፣በሰ/መ/ (ያልታተሙ) ላይ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ አመልካች አስቀድሞ ከአሁን 2ኛ ተጠሪ ጋር ተከራክረዉ የተሰጠዉን ዉሳኔ በመጥቀስ ጭምር ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት በ1986ዓ/ም በግዥ አግኝተዉ ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ቤት ሰርተዉ ይዘዉ እንደሚገኙ፤ቤቱም በ1997 ዓ/ም አየር ካርታ ላይ እንደሚታይ በመግለጽ ከሕግ-አግባብ ዉጭ ወደ 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች እንደተላለፈ በመግለጽ ሲከራከሩ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ደግሞ የመሬት ይዞታዉ የመንግሥት ባድ መሬት መሆኑን በመግለጽ በይዞታዉ ላይ አመልካች መብት የላቸዉም፤ለ3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች በአርሶ አደርነት የተላለፈ ነዉ በማለት ተከራክረዋል።3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎችም በአርሶአደርነት በሕግ አግባብ የተሰጣቸዉ መሬት እንደሆነ በመግለጽ ተከራክረዋል።በዚህ መልኩ ግራ ቀኙን በአከራካረዉ ጉዲይ ላይ ዉሳኔ ለመስጠት ሉያዙ የሚገባቸዉ ጭብጦች - 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ለ3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች መብት በመፍጠር በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መዝግበዉ የሰጡት የመሬት ይዞታ አመልካች አግባብ ባለዉ አካል ሳይፈቀድላቸዉ በመያዝ ቤት በመሥራት ይዘዉ የሚገኙት እና በአመልካች ስም እንዱመዘገብ ሕግ የሚፈቅድላቸዉ ነዉ ወይስ አይደለም? 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ይህንን የመሬት ይዞታ ለ3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ማስተላለፊቸዉ ተገቢ ነዉ ወይ ? ለአመልካች መብት ሉፈጠርላቸዉ የሚገባ ነዉ የሚባል ከሆነ አከራካሪዉን የመሬት ይዞታ ተጠሪዎች ለአመልካች ሉለቁ ይገባል ወይስ አይገባም ? የሚለ ናቸዉ።የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እነዚህን ጭብጦች መመስረቱን የዉሳኔዉ ይዘት በግልጽ አያሳይም።
እንዱሁም ግራ ቀኙ የሚከራከሩበትን የመሬት ይዞታ ላይ ተፈጠረ የተባለዉን የሁከት ተግባር ለማስወገድ ከዚህ ቀደም አመልካች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በአሁን 2ኛ ተጠሪ ላይ የመሰረቱትን ክስ ፍርድ ቤቱ በማስረጃ አጣርቶ በቀን 04/09/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ “…ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ ይዞታ ላይ የሚገኘዉ ቤት በ1997ዓ/ም አየርና መስመር ካርታ ላይ እንደሚታይ የክፍለ ከተማዉ የመሬት አስተዲደር አካል አጣርቶ ምላሽ እንደላከለት በመግለጽ ቤቱ የግንባታ ፈቃድ ወጥቶበት የተሰራ ባይሆንም በመመሪያ ቁጥር 18/2006 አንቀጽ 5 መሰረት በሰነድ አልባ ይዞታዎች መስተንግድ ማግኘት የሚችል ነዉ።በመሆኑም 2ኛ ተጠሪ 500 ካሬ ሜትር ስፊት ያለዉን ይዞታ አመልካች እንዱለቅ የሰጠዉ ትእዛዝ የሁከት ተግባር በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1149/1 መሰረት ሉወገድ ይገባል።” በማለት መወሰኑን የዉሳኔዉ ይዘት ያሳያል።የአሁን 2ኛ ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ አመልካችንና 2ኛ ተጠሪን አከራክሮ በቀን 16/11/2013ዓ /ም በሰጠዉ ዉሳኔ “…ምንም እንኳን የአሁን 2ኛ ተጠሪ በአየር ካርታ ላይ ይታያል የተባለዉና ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት የቴላ መኖሪያ ቤቶች ማኅበር ቤቶች በዔቃ ማስቀመጫነት ሲያገለግል የነበረ ቆርቆሮ በቆርቆሮ የሆነ ቤት ነዉ ቢልም በኮልፋ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የይዞታ አስተዲደር ሽግግር ጊዜ አግልግልት ጽ/ቤት ሰነድ ማጣራትና የሽንሻኖ ማስተካከልና ካርታ ዝግጅት የሥራ ሂደት ጉዲዩን ከወረዲዉ ደንብ ማስከበር አገልግልት ጽ/ቤት ጋር በጋራ በማጣራት ያላኩት ምላሽ ቤቱ በ1997 ዓ/ም አየር ካርታ ላይ የሚታይ እንደሆነ ያሳያል በማለት የአሁን 2ኛ ተጠሪ ያቀረበዉን የይግባኝ ቅሬታ ባለመቀበል ይዞታዉ በመመሪያ ቁጥር 18/2006 መሰረት ለመስተናገድ የሚችል ሆኖ እያለ 2ኛ ተጠሪ ቤቱ እንዱፈርስ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የሁከት ተግባር ነዉ ሲል የስር ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ ነዉ ሲል በማጽናት መወሰኑን የዉሳኔዉ ይዘት ያሳያል። በዚህ አግባብ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ይዞታ በመመሪያ ቁጥር 18/2006 መሰረት ሉስተናገድ የሚችል ይዞታ ሆኖ እያለ የአሁን 2ኛ ተጠሪ ቤቱ እንዱፈርስ ለአመልካች የሰጠዉ ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር ነዉ በሚል በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና በይግባኝ ሰሚዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠዉ ዉሳኔዎች እስካሁን ጸንተዉ የሚገኙ መሆናቸዉ አከራካሪ አይደለም። በፍርድ ቤት የተሰጠ ፍርድ፣ዉሳኔ ወይም ላላ ትዕዛዝ በሥነ ሥርዓት ሕጉ በተመለከተዉ አግባብ ካልተለወጠ በስተቀር ሕጋዊ ዉጤት እንዲለዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 212 ከተደነገገዉ መገንዘብ ይቻላል።ከዚህ ድንጋጌ አተገባበር ጋር በተያያዘም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/፣85718 (ቅጽ12)፣ (ያልታተመ) ላይ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
ከላይ የተጠቀሱትን ዉሳኔዎች አመልካች በማስረጃነት ማቅረባቸዉን የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ያሳያል።በማስረጃነት አልቀረበም የሚል ክርክርም አልቀረበም።በተጠቀሱት መዛግብት ላይ ክርክር ሲደረግ 2ኛ ተጠሪ በአንድ በኩል በ1997 አየር ካርታ ላይ የሚታየዉ በመሬቱ ላይ ያለዉ ቤት የቴላ መኖሪያ ቤቶች ማኅበር ቤቶች በዔቃ ማስቀመጫነት የሚያገለግል እንጂ በአመልካች የተሰራ አይደለም እያለ እየተከራከረ በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ቤቱን አፍርሶ ይዞታዉን እንዱለቅ ማስጠንቀቂያ መጻፈ ተመልክቷል።በዚህ መልኩ የቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት አጥቶ በመሬቱ ላይ የተሰራዉ ቤት በአመልካች እንደተሰራ እና ቤቱ እንዱፈርስ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ የሁከት ተግባር ነዉ ተብል መወሰኑ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በተያዘዉ መዝገብ ላይ አከራካሪዉ መሬት ባድ የመንግሥት መሬት ነዉ በሚል ለሚያቀርቡት ክርክር በማስረጃነት የሚኖረዉ ሕጋዊ ዉጤት ምን እንደሆነ በስር ፍርድ ቤቶች በአግባቡ አልተመዘነም።በተጨማሪም በተጠቀሱት መዛግብት ላይ የተሰጠዉ የፍርድ ዉሳኔ ሁከት ሉወገድ ይገባል የሚል ብቻ ሳይሆን አመልካች ለይዞታዉ በመመሪያ ቁጥር 18/2006 መሰረት መስተንግድ ሉያገኝ የሚችል ነዉ በሚል ድምዲሜ ላይ የተደረሰበት በመሆኑ አመልካች “… ተጠሪዎች ክስ የቀረበበትን ይዞታ እንዱለቁ እና 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች አመልካች በይዞታው ላይ ለመገልገል አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን እና መስተንግድ በመስጠት እንዱፈፅሙ እንዱወሰንልኝ።” በማለት የጠየቁት ዲኝነት ከዚህ የፍርድ ዉሳኔ ይዘት አንጻር ጭምር ታይቶ ሉወሰን የሚገባ ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤቶች በማስረጃነት ለቀረበዉ ለዚህ ዉሳኔ ተገቢዉን ዋጋ በመስጠት አለመመዘናቸዉን ተገንዝበናል።የስር ፍርድ ቤት ይህንን አቋም ለመያዝ በሰ/መ/(ቅጽ 6) መሰረት እንዲደረገ የገለጸ ቢሆንም በተጠቀሰዉ መዝገብ ላይ ሁከት ለማስወገድ ዲኝነት ተጠይቆ እያለ ስለባለቤትነት መብት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ተብል የተወሰነ ሲሆን በያዝነዉ ጉዲይ ላይ 2ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ተከራክሮ በመ/ የተሰጠዉ ዉሳኔ ሁከት ለማስወገድ ከተጠየቀዉ ዲኝነት በላይ አመልካችን የመሬት ይዞታዉ ባለይዞታ የሚያደርግ ዉሳኔ ነዉ በማለት ለሰበር ሰሚ ችልት አቀርቦ ያስወሰነ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ባላቀረበበት በተጠቃሾቹ መዛግብት ላይ የተሰጠዉን ዉሳኔ ሕጋዊ ዉጤት በሚያሳጣ አኳኋን ዉሳኔ መስጠቱ ሥነ ሥርዓታዊ አይደለም።በተጠቀሱት መዛግብት ላይ የተሰጡ ዉሳኔዎች ስህተት እንኳ ቢሆኑ በሥነ ሥርዓት ሕጉ አግባብ በሰበር ሥነ ሥርዓት ወይም በልላ ሥነ ሥርዓት አግባብ እስካልታረሙ ድረስ በስር ፍርድ ቤት በልላ መዝገብ ላይ በሚሰጥ ዉሳኔ ሕጋዊ ዉጤት እንዱያጡ ማድረግ አይቻልም።የተጠቀሰዉ የሰበር ሰሚ ችልት የሕግ ትርጉም ለተያዘዉ ጉዲይ አግባብነት ያለዉ አይደለም። እንዱሁም በዚህ የፍርድ ዉሳኔ ላይ ሁከት ይወገድ ተብል ብቻ እንደተወሰነ በመቁጠር የፍርድ ዉሳኔዉን ሙለ ይዘት በማስረጃነት ሳይመዝኑ ማለፊቸዉ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሆነ የማስረጃ ምዘና መርህ አተገባበር ስህተት ነዉ።
ከዚህም በተጨማሪ አመልካች ባቀረቡት ክስ ላይ በግልጽ እንደተመለከተዉ አመልካች አከራካሪዉን ይዞታ በሕግ ሥልጣን በተሰጠዉ አግባብ ባለዉ አካል ሳይፈቀድላቸዉ የያዙት መሆኑን በገለጹበት እና በዚህ አግባብ የተያዙ ይዞታዎችን ወደ ሕጋዊ ሥርዓት ለማስገባት በወጣዉ ሕግ መሰረት እንዱወሰን ዲኝነት በጠየቁበት ሁኔታ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ይዞታዉን ከአርሶ አደሮች በግዥ መግዛታቸዉን ከመግለጽ ዉጪ በውርስ ፣በስጦታ ፣በምሪት እና በመሳሰለት ሕጋዊ ኩነቶች ማግኘታቸውን በክሳቸው ያልገለፁ በመሆኑ ምስክር መስማት አስፈላጊ አይደለም በማለት ዉሳኔ መስጠቱ ከክርክሩ ይዘት ዉጭ ነዉ። እንዱሁም መሬቱ በአመልካች ያልተያዘና የመንግሥት ባድ መሬት መሆኑ ተገልጾ በተጠሪዎች ክርክር በቀረበበት ሁኔታ አመልካች ከሚያዝያ 1997 ዓ/ም በፉት ጀምሮ አከራካሪዉ መሬት ላይ ቤት በመሥራት መያዝ አለመያዛቸዉን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 257 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የግራ ቀኙን ሙግት እና ምስክሮች በመስማት ፍሬ ነገሩን ካረጋገጠ በኋላ መወሰን ሲገባዉ የአመልካችን ምስክሮች መስማት አያስፈልግም ተጠሪዎችም ሉያስተባብለ አይገባም በማለት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33/2 ያለቦታዉ ተፈጻሚ በማድረግ ዉሳኔ መስጠቱም ሆነ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ይህንን ሳያርም ማለፈ በኢፋዱሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 37/1 እዉቅና የተሰጠዉን ፍትህ የማግኘት መብት አካል የሆነዉን የአመልካችን የመሰማት ሥነ ሥርዓታዊ መብት እና በአንቀጽ 40 የተመለከተዉን የንብረት መብት የጣሰ በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ብለናል።
ሲጠቃለል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ሥነ ሥርዓት፣ የማስረጃ አቀባበልና ምዘና መርሆዎች እና የሕግ አተገባበር ጉድለት ያለባቸዉ ስለሆኑ የሥነ ሥርዓት ሕጉን አስገዲጅ ድንጋጌዎችን እና ከላይ በተጠቀሱት መዛግብት ላይ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠዉን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረኑ ናቸዉ።በመሆኑም በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2(4/ሀ እና ሸ) እና 10(1/ሀ) መሰረት ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸሙባቸዉ ስለሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 04/06/2014 ዓ.ም የሰጠዉ የፍርድ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 07/03/2015ዓ.ም የሰጠዉ የፍርድ ዉሳኔ በሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አንቀጽ 9/1 መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተዘጋዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ ከላይ በፍርድ ሀተታዉ ላይ የተገለጹትን ጭብጦች እና ተጓዲኝ ጭብጦችን በመያዝ በጭብጦቹ ላይ የግራ ቀኙን ተጨማሪ ሙግት እና የተቆጠሩን ምስክሮች በመስማት እንዱሁም በፍርድ ሀተታዉ ላይ በተገለጸዉ አግባብ ተጨማሪ ምስክሮችን መስማት እንዱሁም እንደ ነገሩ ሁኔታ በትእዛዝ በሚያስቀርበዉ ተጨማሪ ማስረጃ ፍሬ ነገሮቹን በማጣራት አግባብነት ባለዉ ሕግ መሰረት በተጠየቀዉ ዲኝነት ላይ ዉሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አንቀጽ 9/2 መሰረት መልሰንለታል።
በዚህ ችልት ያወጣ ወጭ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ይመለስ።
ዉሳኔዉ በቀን 05/10/2016ዓ/ም ተነበበ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.